cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኢትዮ መረጃ - NEWS

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም። ለአስታየት @ethio_merjabot @biruke_promotion

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
58 441
المشتركون
+524 ساعات
-417 أيام
+12530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሁለት ጭንቅላት ያለው ህጻን ተወለደ። በኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ ትላንት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ አንዲት እናት በተደረገላት የቀዶ ህክምና ከአንገት በላይ ሁለት ጭንቅላት (Dicephalic parapagus) ያለው ወንድ ልጅ፤ ክብደቱ 4.2 ኪ.ግ የሚመዝን በሰላም ተገላግላለች። ልጁ የተወለደው በሲሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን በሆስፒታሉ የህጻናት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ቶኩማ ባይሳ የልጁን ቀጣይ ህይወት ለመወሰን ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል ሪፈር እንዲደረግ መወሰኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ቶኩማ አክለውም፥ እናትየው የመጀመሪያ ልጇ እንደሆነ ጠቅሰው አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳለች ገልጸዋል። ዘገባው የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።
إظهار الكل...
👍 16🔥 1
"አንዱ ሰለ ሁሉ ሞተ።" (2ኛ ቆሮ ም. 5:14) ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳቹ። አደረሰን። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ይሁንልን።
إظهار الكل...
34👍 10😁 2
በአቃቂ የገበያ ማዕከል ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ 16 ንግድ  ሱቆች ወደሙ ሚያዚያ 24 ቀን2016  ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ  ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ  ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል መውደማቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። የእሳት አደጋዉን  ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሁለት የዉሀ  ቦቴ  የተሰማራ ሲሆን እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፎቶ በሰዉና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ፈጅቷል። በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሰው  ላይ የደረሰ ጉዳት  የለም። አቃቂ የገበያ ማዕከል ትንሹ መርካቶ እየተባለ የሚጠራ የገበያ ማዕከል ሲሆን ገበያ ማዕከሉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩ አንዱ ነው። በገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ መቆየቱንም አቶ ንጋቱ ጨምረው ነግረውናል።ኮሚሽኑ ገበያ ማዕከሉ ለአደጋ የተጋለጠባቸዉን ዝርዝር ጉዳዮችን የመፍትሄ ሀሳቦችን አካቶ ለገበያ ማዕከሉ ማህበራትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ከዚህ ቀደም ያቀረበ ቢሆንም የማስተካከያ እርምጃዎች አልተወሰዱም። በመሆኑም በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ መፍትሄ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳስቧል። ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 15😭 6👎 1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ማስተር ካርድ ለአምስት ዓመት የሚቆይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። ዛሬ ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት በተደረገው በዚሁ ስምምነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሰጠውን የካርድ ባንክ አገልግሎት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ለማስፋፋት እንደሚያግዘው ተነግሯል። በተጨማሪም አዳዲስ የካርድ አገልግሎቶችን ለማስጀመር እንደሚረዳም ተጠቁሟል።በዚህ የአምስት አመት ሰምምነት መሰረት የባንኩን ደንበኞች ፍላጎት በማሟላት ላይ የሚያተኩሩ እና አለም የደረሰበትን አዳዲስ አገልግሎቶችን በሀገር ውሰጥ በማስተዋወቅ ጥሬ ገንዘብ አልባ ማህበረሰብን ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንደሚያደርግ ይገመታል። ማስተር ካርድ ከ210 ሀገሮች በላይ የሚሰራ አለማቀፍ የክፍያ አቀላጠፊ ድርጅት ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር መስራት ከጀመረ እረጅም አመታት እንደሆነ ይታወቃል።
إظهار الكل...
👍 13 1
They predicted yesterday the DUMP of Bitcoin Already in the channel published the dates of the next BTC PUMP! Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈 Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈 Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈 JOIN FAST! Only the first 1000 people will be accepted! 🔥
إظهار الكل...
👍 5 1
ተፈታች‼️ አርቲስት አዲስአለም ጌታነህ ከ21 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ተፈታለች። @sheger_press @sheger_press
إظهار الكل...
👍 53 9😁 2
ተጨማሪ‼️ ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድን ጨምሮ ሁለት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ታሠሩ በቅርቡ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ ለጥያቄ ይፈለጋሉ በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለሚዲያችን ገልጸዋል። በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል። @sheger_press @sheger_press
إظهار الكل...
👍 16😭 8👎 5 2
ያሳዝናል‼️ ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እየሄዱ የነበሩ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና አንድ ጎረቤትን ጨምሮ የ4 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከል መረጃና ስታቲክስ ክፍል ኃረፊ ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ እንደገለፁት በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ አስተዳደር ማዞሪያ ቀበሌ ሌሊት 11 ሰዓት 40 ከወላይታ ሶዶ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ፒካፕ መኪና በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ ባለሶስት እግር ባጃጅ ጋር ተጋጭቶ በውስጡ የነበሩ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት እና አንድ ጎረቤት በድምሩ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል። በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው። ከሟቾቹ መካከል ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እያመራች የነበረች እናት እንደምትገኝበት ነው ኢንስፔክተር ታምራት የገለጹት። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ኢንፔክተር ታምራት ጠቁመዋል።
إظهار الكل...
😭 56👍 21 5
#ሰበር በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸው ታውቋል። የሁለቱ አገልጋዮች መኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም። ምንጭ፦ የማህበረ ቅዱሳን የፌስቡክ ገፅ
إظهار الكل...
👍 19😭 16👎 4 2
መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በአስቸጋሪ ኹኔታ ላይ የነበሩ 1 ሺህ 180 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መልሷል። ትናንት ከተመለሱት ፍልሰተኞች መካከል፣ 1 ሺህ 98ቱ ወንዶች፣ 79ኙ ሴቶች እንዲኹም ሦስቱ ጨቅላ ሕጻናት እንደኾኑ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። 228ቱ ተመላሾች ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ናቸው ተብሏል። ኮሚቴው ከሚያዝያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት በጠቅላላው 13 ሺህ 900 ፍልሰተኞችን ከሳዑዲ ዓረቢያ መልሷል። @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news
إظهار الكل...
👍 10 1