ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ETHIO CRYPTO ™

ETHIO CRYPTO ™

الذهاب إلى القناة على Telegram

Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟

إظهار المزيد
3 571
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-8230 أيام
أرشيف المشاركات
የትግራይ ዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባ የመግብያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የተመደቡበትም ዩኒቨርስቲ በ፦ 1.W
የትግራይ ዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባ የመግብያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የተመደቡበትም ዩኒቨርስቲ በ፦ 1.Website: https://result.ethernet.edu.et 2.TelegramBot: @moestudentbot ላይ መመልከት ይችላሉ ተብሏል። በትግራይ ክልል በኮቪድ ወረርሽኝ እንዲሁም በአስከፊው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ፈተናቸውን መውሰድ ያልቻሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በዚህ ዓመት መፈተናቸው ይታወሳል። እንደ ክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ፤ ፈተናው ላይ ከተቀመጡት ከ9000 በላይ ተማሪዎች 73.09 በመቶ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እና 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል። @stuDenT_TeXT

የቴክኒክና ሙያ የመግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ወደ ቲክኒክና ሙያ መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።5 ሚኒስቴሩ የመግቢያ ነጥቡን ይፋ ያደረገው ረቡዕ ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ላምበረት በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። መግለጫውን የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 5 የመቁረጫ ነጥብ ወንድ ከ218፣ ሴት 199 በላይ፣ የታዳጊ ክልል (የአርብቶ አደር አካባቢዎች) ወንድ ከ192፣ ሴት 187 በላይ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ አካል ጉዳተኞች 147ና ከዚያ በላይ (ሁሉንም ክልሎች ታሳቢ ያደረገ ነው)  ብለዋል። ደረጃ 3 እና 4 ወንድ ከ173፣ ሴት 163 በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ ከ157፣ ሴት 156 በላይ፣ አካል ጉዳተኞች 130ና ከዚያ በላይ ነው ተብሏል። ተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 1 እና 2 ወንድ 172፣ ሴት 162ና ከዚያ በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ 156፣ ሴት 155ና ከዚያ በላይ ነው። ማኅበራዊ ሳይንስ ደረጃ 5 ወንድ 179፣ ሴት 170ና ከዚያ በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ 166፣ ሴት 162፣ አካል ጉዳተኞች 147ና ከዚያ በላይ ነው። ደረጃ 3 እና 4 በማኅበራዊ ሳንይንስ ወንድ 149፣ ሴት 147፣ ታዳጊ ክልል ወንድ 138፣ ሴት 137ና ከዚያ በላይ፣ አካል ጉዳተኞች 130ና ከዚያ በላይ ሆኗል። ደረጃ 1 እና 2 በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 148፣ 146፣ ታዳጊ ክልል ወንድ 137፣ ሴት 136፣ አካል ጉዳተኞች 129ና ከዚያ በላይ መሆኑን አስረድተዋል። ሚኒስትሯ አክለውም፣ "በ2016 ዓ.ም 844 ሺሕ 384 የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደዋል። ከእነዚህ ውስጥ በእኛ ምልከታ 632 ሺሕ 587 የሚሆኑት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ይመጣሉ የሚል ግምት አለን" ነው ያሉት። የሰው ሃይል ለመቀበል የተሻለ ዝግጁነት አላቸው ያልናቸውኝ የመንግሥትና የግል የቴኪኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን ፈትሸናል ያሉት ሚኒስትሯ፣ እስካሁን ባለው ከ28 ሺህ በላይ የሚሆኑ አሰልጣኞች፣ ወደ 1ሺሕ 400 ገደማ የተሻለ ብቃት ያላቸው ማሰልጠኛ ኮሌጆች አሉ ብለዋል። @Student_Text

"የሬሜዲያል ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ ህዳር 12 ድረስ ማስተካከል ይችላሉ" - የትምህርት ሚኒስቴር በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወ
"የሬሜዲያል ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ ህዳር 12 ድረስ ማስተካከል ይችላሉ" - የትምህርት ሚኒስቴር  በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የሬሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤቱ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዚህ ዓመት የሬሜዲያል ፕሮግራም አዲስ አበባ፣ ሀዋሳ፣ አርሲ፣ ኮተቤ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሙን የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @student_text

አዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት የተማሪዎች ምዘና እና የክፍል ዝውውር መመሪያ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች 50% እና በላይ ያገኘ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ይዛዋወራል፡፡ ✔ ከ1ኛ - 3ኛ ክፍል ላሉ ተከታታይ ምዘና ከ70% ወስደው የማጠቃለያ ምዘና (ፈተና) ከ30 % እንዲወስዱ ያዛል። ያላለፉ ተማሪዎች በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ድጋፍ አግኝተው የሚዘጋጀውን ፈተና ተፈትነው እንዲገቡ ይደረጋል። ✔ ከ4ኛ - 5ኛ ላሉ ደግሞ ተከታታይ ምዘና ከ60% ወስደው የማጠቃለያ ምዘና (ፈተና) ከ40 % እንዲወስዱ ያስቀምጣል። በእነዚህ ክፍሎች ተማሪዎች ለማለፍ ከ50 በመቶ በላይ ማግኘት አለባቸው። ✔ ከ7ኛ ወደ 8ኛ እንዲሁም ከ8ኛ ወደ 9ኛ ለሚሸጋገሩ ደግሞ 40% ተከታታይ ምዘና 60% ደግሞ የማጠቃለያ ምዘና እንደሚወስዱ ያስቀምጣል። ለማለፍም 50 ከመቶ በላይ ማስመዝገብ አለባቸው። ✔ ከ9-11ኛ ክፍል ሂሳብ (Maths) እና እንግሊዘኛ (English) ትምህርት ከ50% በታች ያመጣ ተማሪ እንዲሁም 1-7ኛ ክፍል 6ኛን ሳይጨምር Maths እና የማስተማሪያ ቋንቋውን ከ50% በታች ካመጣ ወደቀጣይ ክፍል መዛወር የማይችል እንደሆነ ተጠቅሷል። ✔ በመመሪያው አንኳር የትምህርት ዓይነት ተብለው የተለዩ የትምህርት አይነቶች ሲቀመጡ ለአንደኛ እና ለመካከለኛ ደረጃ የትምህርት እርከኖች ትምህርቱ የሚሰጥበት ቋንቋ እና የሒሳብ ትምህርት ዓይነቶች እንዲሁም ለሁለተኛ ደረጃ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና የሒሳብ ትምህርት  አንኳር ዓይነቶች ሆነው ተለይተዋል። ✔ በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍሎች ላይ በሚሰጡ ፈተናዎች የማለፊያ ነጥብ ካላገኘ ለአንድ ጊዜ በትምህርት ቤቱ በመደበኛነት ትምህርት እንዲከታተል ይደረጋል። ነገር ግን ከ9ኛ_11ኛ ክፍል ተማሪ በአንድ ክፍል ከ2 ጊዜ በላይ ከደገመ ወይም በተከታታይ ክፍሎች ከደገመ ከትምህርት ዓለም ይሰናበታል። ✔ በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች 50% እና በላይ ያገኘ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ይዛዋወራል፡፡ ✔ የአንደኛ ደረጃ ከ1-5 እና 6ኛ የክፍል ክፍል ዝውውር የራሱ የዝውውር አፈፃፀም እንደሚኖረው ሲጠቀስ በተመሳሳይ ፥ የመሀከለኛ ደረጃ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል የተማሪዎች ምዘና እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዘና እና የክፍል ክፍል ዝውውር አተገባበር የየራሳቸው ዝርዝር መመሪያ ወጥቶላቸዋል። ✔ አስራ አራት አመት የሚወስደውን አጠቃላይ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች በአንድ የሥራና የተግባር ትምህርት መስክ ጥናት ማጠናቀቃቸውንና በዚያም መስክ መመረቃቸውን ለማረጋገጥ የሚካሄድ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ይኖራል። ✔ መመሪያው ተግባራዊ የሚደረገው ከቅድመ አንደኛ ደረጃ አስከ 12ኛ ክፍል በመደበኛ እንዲሁም በማታውና በርቀት መርሃ ግብሮች ትምህርት በሚሰጡ ተቋማት ሲሆን ከዓለም አቀፍና ከውጭ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች በስተቀር በመንግስትና በሌሎች በሁሉም አይነት ትምህርት ቤቶች/ተቋማት/ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። https://t.me/student_text

#ትግራይ በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 66.96 በመቶዎቹ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገለፀ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ በማኅበራዊ ገፁ ባወጣው መልዕክት
#ትግራይ በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 66.96 በመቶዎቹ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገለፀ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ በማኅበራዊ ገፁ ባወጣው መልዕክት እንደገፀው ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 73.09% በተፈጥሮ ሳይንስ እና 51.38% በማኅበራዊ ሳይንስ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን አሳውቋል። በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በድረ-ገጽ eaes.et ወይም በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ መመልከት ይችላሉ ተብሏል። ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በአገልግሎቱ ድረ-ገጽ ላይ እንዲሁም በትግራይ ትምህርት ቢሮ በአካል በመቅረብ እስከ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም ድረስ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተመላክቷል። በተያያዘ በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል። ሙሴ ኪዳነ የተባለ የቀላሚኖ ትምህርት ቤት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ መሆኑን ለመመልከት ችለናል። https://t.me/student_text

Tigray 657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል። በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል። ይህንን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ ሙሴ ኪዳነ የሚባል ሲሆን የ " ቀላሚኖ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመመልከት ችሏል። እንደ ትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ መረጃ አጠቃላይ መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች  73.09 በመቶ የሚሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች  እንዲሁም 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል። በትግራይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኃላም በደም አፋሳሹ ጦርነት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው መቆየታቸው የሚዘነጋ አይደለም። https://t.me/student_text

WolaitaSodo_University በ2015 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሳምንት መጨረሻ መርሐግብር በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ማለፊያ ውጤት ያገኛችሁ
WolaitaSodo_University በ2015 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሳምንት መጨረሻ መርሐግብር በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ማለፊያ ውጤት ያገኛችሁ ተማሪዎች እስከ ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም ድረስ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና ኮፒውን በመያዝ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል፡፡ የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት፣ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ውጤት ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች ናቸው። ትኩረት፡ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስክ የተማረ ወደ ማኅበራዊ ሳይንስ ማመልከት ይችላል ተብሏል። ፍላጎት ያላችሉ በመንግሥት የትምህርት ተቋማት Remedial ያለፋችሁ ተማሪዎች በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማመልከት ትችላላችሁ።

" የሬሜዲያል ተማሪዎች ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል " - ትምህርት ሚኒስቴር ትላንት ይፋ በተደረገው የማካካሻ ትምህርት / ሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከተደረገላቸው በኃላ ለ4 ወራት የማካካሻ ትምህርት የሚወስዱ ሲሆን ይህንን ተከታትለው በተቋማቸው እና በማዕከል የሚሰጣቸውን ፈተና ማለፍ ሲችሉ በቀጣይ መደበኛ ተማሪ ሆነው ወደ ፌሽማን ይቀላቀላሉ። ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የመቁረጫ ነጥብ በሁሉም አማራጮች ማለትም በግል እና በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፤ ይህም ማለት 210 ከ700፣ 180 ከ600 እና 150 ከ500 ማስመዝገብ አለባቸው። በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) በዩኒቨርሲቲ ተመድበው የሬሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ በ ተፈጥሮ_ሳይንስ የመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች መቁረጫው 255 ከ700 ነው። የሴት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫው ደግሞ 234 ከ700 ነው። በዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚማሩ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡ 218 ከ600 ሲሆን ፤ የሴት ተማሪዎች መቁረጫው 200 ከ600 ነው። እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ዘንድሮ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው ይማራሉ። https://t.me/student_text

የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ። የአቅም ማሻሻያ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል። ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 ከ700 ያመጡ ☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 ከ700 ያመጡ ☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 ከ600 ያመጡ ☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 ከ600 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ከ700 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 192 ከ600 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ ☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል። መረጃውን ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ያሰራጨው ኤፍ ቢ ሲ ነው። https://t.me/student_text

የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወ
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። Website https://result.ethernet.edu.et/ Telegram bot @moestudentbot https://t.me/student_text

#MOE ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል። የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል። የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፤ በነዚህ ውስጥ ይመደባሉ። የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል። በተቋማት የጾታ ተዋጽኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋጽኦና ሚዛን እንዲጠበቅ መደረጉ ተገልጿል። የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን እንደሚያግፅ ተነላክቷል። ይህም ከአንድ ት/ቤት የወጡ ተማሪዎች በአንድ ዩኒቨርሲቲ ወይም ፕሮግራም ውስጥ እንዳይታጨቁ ይደርጋል። የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት  ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር እንደሚያግዝ ተገልጿል። የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው ተብሏል። በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡ በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል። በተማሪዎቹ መካከል ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል። የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል እድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል። ትምህርት ሚኒስቴር ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ  የሚያቀርብ ተማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከምደባ ውጭ የሚሆን መሆኑን አሳስቧል። ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር @Student_TexT

Repost from ETHIO CRYPTO ™
✅ የምንለቃቸው መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ፤ ከስልካቹ እታች ያለው ከላይ በፎቶላይ እንደምትመለክቱት (MUTE) ማለቱን አረጋግጡ፤ UNMUTE ከሆነ የሚለው፤ አንዴ ብቻ ተጫኑት @student_te
✅ የምንለቃቸው መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ፤ ከስልካቹ እታች ያለው ከላይ በፎቶላይ እንደምትመለክቱት (MUTE) ማለቱን አረጋግጡ፤ UNMUTE ከሆነ የሚለው፤ አንዴ ብቻ ተጫኑት @student_text @student_text @student_text @student_text @student_text

MOE የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ከሚማሩት ትምህርት ውጪ ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ሔደው ለሚያደርጓቸው የተግባር ላይ ልምምዶች የሚደረግ ወጪ÷ ከምርቃት በኋላ በሚከፍሉት የወጪ መጋራት ውስጥ እንዲካተት ጥናት መጀመሩ ተገለጸ፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወጪ መጋራት (Cost Sharing) መመርያ መሠረት ወደ መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀላቀሉ አዳዲስ ተማሪዎች÷ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ተመርቀው እስኪወጡ ድረስ፣ መንግሥት ለምግብና ለመኝታ ያወጣውን ወጪ በሚገቡት ውል መሠረት ከምርቃት በኋላ ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡ ተማሪዎች ወደ ተግባር ልምምድ ሲወጡ ለሚቆዩባቸው ጊዜያት ለሚኖራቸው የተግባር ላይ ትምህርት፣ ከምረቃ በኋላ ከወጪ መጋራት ጋር ተደምሮ እንዲከፍሉ ለማድረግ የትምህርት ሚኒስቴር ዕቅድ መያዙንና ጥናት መጀመሩን፣ በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ተሾመ ዳንኤል ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡ ሐሳቡ በጥናት ላይ መሆኑንና ዓላማውም ወደፊት ተማሪዎች የተግባር ላይ ልምምድን ትኩረት ሰጥተው እንዲማሩ ለማድረግ በማሰብ የታቀደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ለክፍያው የልማት አጋር ድርጅቶች ለትምህርት ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ትስስር የሚመድቡት ገንዘብ ስለሚኖር፣ ከዚህ ገንዘብ ለወጪ መጋራት ሊከፈል የሚችልበት አሠራርም ሊዘረጋ እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡ https://t.me/student_text

የ2015 የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት በአማካይ ነጥብ በተለያዩ መቁረጫ ነጥቦች የተማሪዎች ብዛት 50%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች 40%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 63,694 35%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 102,177 34%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 113,625 33%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 127,017 32%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 143,625 31%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 164,110 https://t.me/student_text

M_O_E በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ያለፋችሁና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም እንድታመለክቱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማይቀበል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል። https://t.me/student_text

" አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል "  - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፤ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በአግባቡ እንደሚሰራበት አመልክተዋል። " በምንም አይነትና መስፈርት አግባብ የሌለውና አድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል። " እያንዳንዱ ተማሪ በጠየቀው በችሎታው ፣ በሚገባው ቦታ እንዲመደብ እናደርጋል " ያሉት ሚኒስትሩ " አንድና ብቸኛው ከዛ የምንወጣበት አስቸኳይ የሆነና ቅርብ የሆነ ክትትል የሚያስፈልጋቸው የህክምና ጉዳይ ሲኖር ነው " ብለዋል። " የህክምና ኬዞችንም ስንመለከት ከዶክተር ወረቀት ማምጣት ብቻ ሳይሆን በቦርድ ደረጃ ተነጋግረውበት ያ የህክምና ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመማር የማያስችል ነው፤ ለህይወቱ/ቷ አስቸጋሪ ነገር ያመጣል ከተባለ ብቻና ብቻ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፤ " ለአንድ የመንግሥት ባለስልጣን ፣ አንድ የምክር ቤት አባል፣ አንድ ዝም ብሎ ሃብታም ነኝ ብሎ ለሚያስብ ሰው ከሚገባው ውጭ ለልጁ የሚሰጥ ምንም ነገር የለም " ብለዋል። ከምደባ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ጥያቄዎች እየተጠየቁ መሆኑን ያልደበቁት ፕ/ር ብርሃኑ " ስልኮች ይደወላሉ ነገር ግን የምንሰጠው መልስ አንድ ነው ፤ ' ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው። በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው ከዛ ውጭ ባለ ሌላ መስፈርት ማንንም እድል አንሰጥም ' የሚል ነው " ብለዋል። " ከዚህ ውጭ የተሰራና የሚሰራ ስራ ካለ አሳዩን፤ ንገሩን እናስተካክላለን " ሲሉ ተናግረዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ለምደባ በሚል ጉዳይ እሳቸውም ጋር የሚመጡ እንዳሉ ገልጸው ትክክለኛ ጥያቄ አለን ካላችሁ በትክክለኛው ሂደት እለፉ ከዛ ውጭ ግን የሚመጣ የአቋራጭ መንገድ የለም " ሲሉ ተናግረዋል። @student_text

" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል። እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? በ2014 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ፦ ወደ መንግሥት ተቋማት ተመድበው የሬሜዲያል ትምህርት ከተከታተሉት 105,00 ተማሪዎች 63,033 ተማሪዎች አልፈዋል። በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለው  ከተፈተኑት ውስጥ 44,500 ተማሪዎች 27,587 ተማሪዎች አልፈዋል። በአጠቃላይ ወደ 145,000 ገደማ ተማሪዎች ሬሜዲያል ገብተው በዛው በተቋማቸው ከ30% እንዲሁም ከማዕከል 70% ተፈትነው ከ50% እና በላይ አምጥተው ያለፉት 90,620 ተማሪዎች ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች ዘንድሮ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ። በ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ያለፉት ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች 27,267 ገደማ ናቸው። በቀጥታ ፌሽማን / አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ። በአጠቃላይ በ2014 ዓ/ም ተፈትነው ሬሜዲያል ያለፉና በ2015 ዓ/ም 50 በመቶ አምትጥተው በቀጥታ ያለፉትን ጨምሮ 117,887 ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ። (90,620 ከሬሜዲያል፤ 27,267 ከ2015 ዓ/ም አላፊዎች) ዘንድሮ በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡት 191, 509 ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች ናቸው፤ እነዚህ በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ ይደረጋል። @stUDenT_TExT

የቅሬታ ምላሽን ይመለከታል። በ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ለይ በአካል በመምጣት ቅሬታ ላቀረባችሁ በስልክ ወይም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ምላሽ ተሰጥቷል። እየተሰጠም ይገኛል። በበይነ መረብ(Online) ቅሬታ ያቀረባችሁ ምላሹም በበይነ መረብ የተሰጠ በመሆኑ ከዚህ በፊት ውጤት ባያችሁበት መልኩ በድረ ገጽ eaes.et ላይ ምላሹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። በቁጥር የተወሰኑ ቅሬታዎች በምላሽ ሂደት ላይ ያሉ በመሆኑ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን።                 @stUDenT_TExT

አዲሱንም ካሪዩኩለም መጽሐፍት ለምትፈልጉ በሙሉ ከታች ባለዉ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ 📚📚New Curriculum Books📚📚     Grade 1- 8 https://t.me/student_text/1080 Grade 9 & 10 https://t.me/student_text/1169?single

Repost from ETHIO CRYPTO ™
#የመቁረጫ_ነጥብ የአቅም ማሻሻያ (ረሜዲያል) የመቁረጫ ነጥብ፦ - የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 263 - የተፈጥሮ ሳይን
#የመቁረጫ_ነጥብ የአቅም ማሻሻያ (ረሜዲያል) የመቁረጫ ነጥብ፦ - የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 263 - የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 227 - የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 220 - የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 190 - የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 210 - የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 210 - የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 180 - የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 180 @stUDenT_TExT