ETHIO CRYPTO ™
الذهاب إلى القناة على Telegram
Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟
إظهار المزيد3 571
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-8230 أيام
أرشيف المشاركات
3 571
ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው የአ/አ ትምህርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን መስከረም 7-01-2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ።
ቢሮው ይህን ያሳወቀው የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ለህዝብ ካሰራጨ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መልዕክት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 14-1-2016 ዓ.ም እንደሚጀመር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ ነው ብሏል።
ቢሮው በየትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ እንደተሰራጨ በግልፅ አላሰፈረም።
የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረገው የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር መሰረት ከመስረም 7 እስከ 11-2016 ዓ/ም ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።
መስከረም 14 ደግሞ የ1ደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ካላንደሩ ላይ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረግ ብሏል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው መሰረት የ2016 ዓ/ም ትምህርት መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም ተቋም እንደሚጀምር አስረግጦ ተናግሯል መላው የትምህርት ማህበረሰብ ይህን እንዲያውቀው ብሏል።
ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ/ም የትምህርት መስከረም 7/2016 ዓ/ም እንደሚጀምር ማሳወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
@StUdEnT_TExT
3 571
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለጻል?
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤትን ቶሎ ለማድረስ በሙሉ አቅም እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡
ፈተናውን የማረም ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ማንጠግቦሽ አዳምጤ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡
ከመስከረም 07 እስከ 11/2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ጨምሮ ውጤት ለመግለፅ መታሰቡን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡
ምናልባትም እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል" ተናግረዋል፡፡
በነሐሴ መጨረሻ በሰጡት መግለጫ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል ብለው እንደነበር አይዘነጋም።
በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለነበሩ ተማሪዎች ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተናው ይሰጣል መባሉ ይታወቃል።
@Student_TexT
3 571
M_O_E
ዲጂታል የተማሪዎች መታወቂያ ስርዓት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የዲጂታል መታወቂያ ስርዓትን በትምህርት ተቋማት መደበኛ የተማሪዎች መለያ አድርጎ መተግበር ጀምሯል።
የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ የተማሪዎችን ማንነት በወጥነት ለመለየት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ስርዓቱ ከትምህርት ቤቶች እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የትምህርት ተቋማት የተማሪ ቅበላ፣ ፈተናና የማህደር አስተዳደር የመሳሰሉ ሥራዎችን ለማሳለጥ ያግዛል ተብሏል።
እስካአሁን 640 ሺህ ተማሪዎች ብሔራዊ መለያ ቁጥር ማግኘታቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርአያሥላሴ ተናግረዋል። በ2016 የትምህርት ዘመን ስርዓቱን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠራ ገልፀዋል።
@Student_TExt
3 571
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና
በጸጥታ ችግርና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ያልወሰዱ የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን የተዘጋጁ 15,310 ተማሪዎች ከመስከረም 8-11 ለመፈተን ዝግጅት ተጠናቋል
የፈተና ውጤታቸውም ከአንደኛ ዙር ተፈታኞች ጋር በመስከረም ወር መጨረሻ አልያም በጥቅምት ወር መጀመሪያ ውጤት ለመልቀቅ እቅድ ተይዟል
@Student_Text
3 571
የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት በፀጥታ እና በሌሎች ምክንያቶች ፈተናቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኃላ ይገለፃል ተብሎ ይጠበቃል።
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ፈተናቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከመስከረም 8 እስከ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።
የእነዚህ ተፈታኞች እና የመጀመሪያው ዙር ፈተና ተፈታኞች ውጤት አንድ ላይ እንደሚገለፅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ከቀናት በፊት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን መስከረም 2016 ዓ/ም አጋማሽ ድረስ ይፋ ለማድረግ እና ጥቅምት ወር 2016 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲጀመር እቅድ መያዙን መግለፃቸው ይታወሳል።
3 571
MOE
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል።
የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አረጋግጠዋል።
በጥቅምት 2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር ዕቅድ መያዙንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በፀጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሦስት ፈተናዎች ያልወሰዱ ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።
በ2015 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፣ የመጨረሻዎቹን ሦስት ፈተናዎች አለመፈተናቸው ይታወቃል።
እነዚህ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።
3 571
በ2015 ዓ.ም ከ91 ተቋማት የመጡ 4,413 የትምህርት ማስረጃዎችን ማጣራቱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለጸ።
የማጣራት ሥራ ከተደረገባቸው የትምህርት ማስረጃዎች ውስጥ 3 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑት
ሐሰተኛ ሆነው መገኘታቸው ተገልጿል።
ውጤት መቀየር፣ ያልተማሩበትን የትምህርት ማስረጃ መያዝ እና ሌሎች ሐሰተኛ መረጃዎች መገኘታቸውን በአገልግሎቱ የዲጂታል ትምህርት መረጃ አስተዳደርና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ደሳለው ታፈሰ ለኤፍቢሲ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ሐሰተኛ ሰነዶችን ማምከንና ግለሰቦቹን ከሥራ በማገድ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ተቋማት ሠራተኞችን ሲቀጥሩና የደረጃ እድገት ሰሲጡ የትምህርት ማስረጃዎችን ትክክለኛነት ማጣራት እንዳለባቸው ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
FBC
3 571
#ቅዱስ_ጳውሎስ_COC
ዘንድሮ 12ኛ ክፍል ለተፈተናችሁ ተማሪዎች
በርካታ Medicine መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች 12ኛ ክፍል ከተፈተኑ በኋላ የመጀመሪያ ምርጫቸው በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ መወዳደር ነው ...! ይህም ለቀጣይ ጉዟቸው እጅግ በጣም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው
ለመሆኑ መወዳደር የሚችሉት እነማን ናቸው..
Medicine ለመማር ከልጅነት ጀምሮ ፍላጎት ያላቸውና 12ኛ ክፍል በአንፃራዊነት የተሻለ ዉጤት ማምጣት የሚችሉ ተማሪዎች መወዳደር ይችላሉ
(Last year Above 425/700)
ጳውሎስ ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ 12ኛ ክፍል የተፈተናችሁ ተማሪዎች ፤ ከወዲሁ ራሳችሁን ማዘጋጀት ፣ መረጃ መሰብሰብ እና ቱቶሪያሎችን መከታተል ይኖርባችኋል
ዉጤት ከተለቀቀ በኋላ '' ሰርገኛ መጣ...'' እንዲሉ ምንም ጊዜ እንደማታገኙ ማወቅ አለባችሁ !
ለፈተናው ለመዘጋጀት አስባችኋል?
እኛን በመቀላቀል ሁሉንም ጉዟችሁን ማቅለል ደግሞ ብልህነት ነው
ያለፉ አመታት ፈተናዎችን በመስራት
እጅግ አስፈላጊ ፈተናዎችን በማዘጋጀት
በተጨማሪ ዝግጅታችንን ልዩ የሚያደርገው ባለፈዉ ዓመት አስተምረን ህልማቸው እውን እንዲሆን የረዳናቸው የአምና ተፈታኞች በተራቸው የሚችሉትን ለማካፈል ከጎናችሁ መሆናቸው ነው
ለቱቶሪያል ምዝገባ
@medicaltutorbot
3 571
የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን ይሰጣል የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን #በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ ኦንላይን (online) እንደሚሰጥ አሳውቋል።
ይህን ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።
ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።
ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።
በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።
መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
@student_text
3 571
የኦሮሚያ ክልል የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት በኦንላይን https://oromia.ministry.et/#/result
መመልከት ይቻላል።
@student_text
3 571
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን በውድድር ብቻ እንደሚሆን አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን “በልዩ” ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።
ተቋሙ ይህን ያለው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዛሬ ነሐሴ 16/2015 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር “ሁለት ዓመት ባልሞላ” ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ የሥራ ነፃነትን የሚያጎናጽፉ የሕግ ማሻሻያዎች እያደረገ እንደሚገኝ መግለጡ ይታወሳል፡፡ (ተጨማሪ
3 571
" ፈተናው ተራዝሟል ፤ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እናሳውቃለን "
ትምህርት ሚኒስቴር
ከዚህ ቀደም ፈተናቸውን ያልወሠዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ተራዝሟል።
ፈተናው ከነሐሴ 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም በኦንላይን ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።
ይሁን እንጂ በኢንተርኔትና ተዛማጅ ምክንያቶች ፈተናው መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።
ሚኒስቴሩ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
@Student_TexT
3 571
" ተማሪዎች ውጤታችቸውን በ https://aa.ministry.et/#/result ላይ በመግባት ማየት ይችላሉ " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዛሬው እለት የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል።
50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል እንደሚዘዋወሩ የተገለፀ ሲሆን የተለያየ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑ ተመላክቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ 73,385 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደው 70.6% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸው ተነግሯል።
61,840 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 50,812 የሚሆኑት ማለትም 82.16 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።
ተማሪዎች ውጤታችቸውን በ https://aa.ministry.et/#/result
Registration number &
first name በማስገባት መመልከት ይችላሉ ተብሏል።
3 571
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 19 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል።
የተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦
➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።
➭ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽ እና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።
➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መፅሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች እንዲሁም የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።
➭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።
➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበርና መፃፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።
➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።
የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎች፡-
➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።
➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።
➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።
➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።
➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።
➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።
➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል/በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።
➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።
➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።
➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።
ለተፈታኝ ተማሪዎች የተፈቀዱ ነገሮች፦
➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መፅሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መፅሐፍት፣ ባዶ ወረቀት
➣ ደረቅ ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
➣ ገንዘብ (ብር)
➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
➣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)
ለተፈታኝ ተማሪዎች የተከለከሉ ነገሮች፦
➣ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
➣ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።
➣ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
➣ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት)፣ ህክምና መስጫ መርፌ መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
➣ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
➣ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀር)
➣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
➣ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
➣ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
@student_text
