cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Crazy jocks 😜😂

No Matter what language you speak. This channel will make You Laugh. ➡️ Some time i have to post ads to Grow the channel. 📷 Funny pic ⚜ Funny gif📺 ⚜ jokes 😂😂 ⛔⛔don't leave us. @Jessylingard 😂😂Have fun 😂😂

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
Advertising posts
1 694المشتركون
لا توجد بيانات24 hour
لا توجد بيانات7 يوم
لا توجد بيانات30 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ከ3 ሺ በላይ የሚሆኑ በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማገናኘቱን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምክትል ዋና ፀሀፊ አቶ እንግዳ ማንደፍሮ ለአሀዱ እንዳሉት ከአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበርና በክልሉ ከሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን የማገናኘት ስራ እየሰራ ነው፡፡ ማህበሩ ከ 3 ሺ በላይ የሚሆኑ የተማሪዎችን መልክት በማስተላለፍ እና የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀምም በስልክ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማገናኘት ስራ ተሰርታል ያሉት ዋና ፀሀፊ አቶ እንግዳ ማንደፍሮ ናቸው፡፡ ይህ ተግባር ቀጣይነት ያለው ሲሁን አሁን ላይ መንግስት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመነጋገር በክልሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችን የማስወጣት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
إظهار الكل...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሣሪያና ወታደሮችን ወደ ትግራይ ክልል እያመላለሰ ነው የሚለውን ክስ አወገዘ፡፡ አየር መንገዱ ሐምሌ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ክሱ መሠረተ-ቢስ ነው ሲል አጣጥሎታል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደሚለው ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ ሁሉም በረራዎች ከህዳር ወዲህ ተቋርጠዋል፡፡ በረራ በነበረባቸው ”አንዳንድ ጊዚያትም” ቢሆን ወደ ክልሉ ሲቪሎችን በማጓጓዝ ለንገድ አስፈላጊ አገልግሎት ስሰጥ ነበር ብሏል፡፡ ለጥቂት ጊዚያት ተከፍቶ የነበረው በረራም ዳግም ከተቋረጠ አንድ ውር ሆኖታል ሲል ገልፆል፡፡አንደ አየር መንገዱ መግለጫ ከሆነ ኢትዮጵያ ሁሉንም ዓለምአቀፍ የበረራ ህግጋትና መመሪያዎችን ታከብራለች፡፡
إظهار الكل...
የህወሓት ፕሮፓጋንዳ አራጋቢዎች የሐሰት ምስሎችን እና ስዕላዊ ቅንብሮችን በመጠቀም ሐሰተኛውን ‹የሁመራ ጭፍጨፋ› ዘመቻ እንደገና በማነሳሳት ላይ መሆናቸውን የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡ ስለሆነም ሁሉም ሰው የህወሓትን የፈጠራና የተሳሳተ መረጃን ስርጭት እንዲያከሽፍ እና እንዲያከስም የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ጥሪ አቅርቧ
إظهار الكل...
አቶ ስብሐት ነጋ ወ/ ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 19 ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እንዲደርሳቸው ተደረገ፡፡ በማረሚያ ቤት የሚገኙት አንባሳደር አባይ ወልዱና ዶ/ርአስገዶም ተስፋዬ ያልቀረቡ ሲሆን 19 ኙ ግን በችሎት ተገኝተዋል፡፡ ያልቀረቡት ቀሪዎቹ እነ ዶ/ር ደብረጺኦን ፡ጌታቸው ረዳ፡ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ( ሞንጆሪኖ) ጨምሮ 41 ተከሳሾችን ፖሊስ አፈላልጉ ለማቅረብ በትግራይ ክልል ካለው ፀጥታ ችግር አንፃር እንደሚቸገር መግለጹን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አብራርቷል፡፡ ነገር ግን በችሎት የተገኙ ተከሳሾች የመኖሪያ አድራሻቸውን፡ የትዳር ሁኔታቸውን እና የስራቸውን ደረጃ አጠቃላይ ማንነታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስመዝግበዋል፡፡
إظهار الكل...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገቢ ንግድ ሲያቀርብ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ ለረዥም ጊዜ አቋርጦ የነበረ ቢሆንም፣ በቅርቡ መልሶ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ባንኩ ለገቢ ንግድ በተለይ ለግል ዘርፉ ያቀርብ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቋረጥ ያደረገው በውጭ ባንኮች የነበሩበትን ክፍያዎች ማጠናቀቅ ስለነበረበት ነው፡፡ በባንኩ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ዙሪያ ያነጋገርናቸው የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳመለከቱት፣ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ተቋርጦ የነበረው ትልቅ ችግር የነበረበት ከመሆኑም በላይ ያለውን የውጭ ምንዛሪ ለገቢ ንግድ ከማዋል ይልቅ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች መስጠት በማስፈለጉ ነው፡፡
إظهار الكل...
ኢትዮጲያ የብር ሜዳሊያ በ3ሺ መሰናክል አገኘች! በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ3ሺ ሜትር መሰናክል ውድድር ኢትዮጲያ በለሜቻ ግርማ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።ለሜቻ ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዶሃ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ማግኙቱ ይታወሳል። እንኳን ደስ አለን!!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹
إظهار الكل...
ኢትዮጲያ የነሀስ ሜዳሊያ በሴቶች 5ሺ ሜትር አግኝታለች! በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ5ሺ ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጲያ በጉዳፍ ፀጋዬ የነሀስ ሜዳሊያ አግኝታለች።ሲፋን ሀሰን የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ ኬንያዊቷ አትሌት አትሌት ሄለን ኦብሪ ሁለተኛ ወጥታለች። በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹
إظهار الكل...
በጂቡቲ ከተማ በአፋር እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል ግጭት ተከስቶ ነበር ተባለ! በጂቡቲ ዋና ከተማ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በአፋር እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ እና ንብረት መውደሙ ተገለጸ።የጂቡቲ መንግሥት በዋና ከተማዋ ጂቡቲ በአፋር እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል የተነሳውን ግጭት አውግዟል።በግጭቱ ሕይወታቸው ያለፉ ዜጎች ምን ያህል እንደሆኑ እስካሁን ድረስ ያልታወቀ ቢሆንም ንጹሀን ዜጎች መሆናቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል። የጂቡቲ የአገር ውስጥ ሚንስትር ኑህ ሐሰን ትናንት ምሽት በሁለቱ ብሔር ተወላጆች መካከል የተከሰተውን ግጭት መንግሥት "እንደማይታገሰው" ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።ሚኒስትሩ በግጭቱ ወቅት መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው እና ፖሊስ ላይ ድንጋይ መወርወሩንም አክለው ገልጸዋል።የዓይን እማኞች በግጭቱ የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን ይናገራሉ።የጂቡቲ የአገር ውስጥ ሚኒስትር በበኩላቸው ዜጎች ከማንኛውም ግጭት እንዲታቀቡ ጥሪ አቅርበው፤ መንግሥት ግጭት የሚቀሰቅሱ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል። ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ በአፋር እና በሶማሌ ክልል ተወላጆች መካከል በገርባ ኢሴ ከተማ ግጭት ተቀስቅሶ በርካቶች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።ይህንንም ተከትሎም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የክልሉን ተወላጆች ሕይወት ለመታደግ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንደሚወስዱ ተናግረው ነበር።በአፋር እና በሶማሌ ክልል መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ግጭቶች ይከሰታሉ።ይህንንም ተከትሎ በተደጋጋሚ በተነሳ ግጭት የንጹሀን ዜጎች ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ ተፈናቅለዋል። [BBa
إظهار الكل...
በጎንደር ከተማ ለቀደሞው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ በስማቸው ጎዳና ተሰየመ! የተሰየመው መንገድ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በር እስከ ሽንታ ወንዝ ድልድይ ያለዉ የአስፓልት ነው።
إظهار الكل...
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የትግራይ ግጭት የኢትዮጵያን አንድነት ባስጠበቀ መልኩ በውይይት እንዲፈታ ጠየቁ ፕሬዝዳንት ማክሮን ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር በስልክ ተወያይተዋል ትግራይ ክልል ያለውን ግጭት ለመፍታት ሁሉም አካላት ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲመጡ ፕሬዝዳንት ማክሮን ጠይቀዋል የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሰሜን ኢትዮጵያ፤ በትግራይ ክልል ያለው ግጭት የኢትዮጵያን አንድነት ባስጠበቀ መልኩ በውይይት እንዲፈታ ጠየቁ። ፕሬዝዳንት ማክሮን በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። የመሪዎቹ ውይይትም በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት ዙሪያ መሆኑን አል ዐይን ኒውስ ከኤሊዜ ቤተ መንግሥት ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝዳንቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ግጭት ለመፍታት ሁሉም አካላት ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲመጡም መጠየቃቸውን የፈረንሳይ ቤተ መንግስት ጽ/ቤት በመግለጫው አስታውቋል። የኢትዮጵያን አንድነት ባስጠበቀ መልኩ በግጭት ላይ እየተሳተፉ ያሉ ኃይሎች በሙሉ ፖለቲካዊ ውይይት ሊያደርጉ እንደሚገባም ፕሬዝዳንት ማክሮን ጥሪ አቅርበዋል ተብሏል። በትግራይ ክልል ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት እርዳታዎች በአስቸኳይ እንዲደርሱ የጠየቁት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ዕርዳታ እንዳይደርስ የሚያደርጉ ገደቦችም እንዲነሱ ጠይቀዋል። ፕሬዝዳንት ማክሮን፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ እና አስቸኳይ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ገሪፊትስ የሚያደርገውን ጥረት ፓሪስ እንደምትደግፍም አስታውቀዋል። ከድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች በተጨማሪም ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።
إظهار الكل...