Woizero Siheen Polytechnic College
الذهاب إلى القناة على Telegram
713
المشتركون
+124 ساعات
-27 أيام
+830 أيام
جاري تحميل البيانات...
القنوات المماثلة
سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
ديسمبر '24ديسمبر '24
ديسمبر '24
+4
في 0 قنوات
نوفمبر '24
+25
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+39
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+685
في 0 قنوات
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 09 ديسمبر | 0 | |||
| 08 ديسمبر | 0 | |||
| 07 ديسمبر | 0 | |||
| 06 ديسمبر | 0 | |||
| 05 ديسمبر | +1 | |||
| 04 ديسمبر | 0 | |||
| 03 ديسمبر | +1 | |||
| 02 ديسمبر | +1 | |||
| 01 ديسمبر | +1 |
منشورات القناة
+1
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ደ/ር) የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጻ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ተሻለ በመግለጫቸው የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ እንደሚዘጋጅ ገልጸው በዚህ ዓመትም የ12 ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 526,683 የሚሆኑት ከደረጃ 1 እስከ 5 በመደበኛ ስልጠና ለመሰልጠን ተቋማቱን ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡
ገበያ ተኮር በሆኑ በአጫጭር ስልጠናዎች ደግሞ ከ3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተቋማቱ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሰልጣኞች በተቋማቱ በቂ ክህሎት ታጥቀው እንዲወጡ በክረምቱ የአሰልጣኞች የአቅም ግንበናታ ስልጠና፣ የማሽነሪዎች ጥገና እና አስፈላጊ የማሰልጠኛ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ማሰልጠኛ ተቋማት ይህንን የመቁረጫ ነጥብ መነሻ አድርገው ሰልጣኞችን መቀበል ይጀምራሉ ብለዋል፡፡
| 2 | በደሴ ከተማ ህዝብ ዘንድ በሁሉም ሀይማኖት ተከታይ ተወዳጅነት የነበራቸው ለከተማችንም እንደ አርማ የሚጠቀሱት ለብዝኀ ህይወት ትልቅ አስተዋፅኦ በነበራቸው ታላቅ አባት በሊቀ ትጉሀን መፍቀሬ ሰብ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በኮሌጃችን ማህበረሰብ ስም እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እንዲሁም ለደሴ ከተማ ህዘብ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን ። | 532 |
| 3 | የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ ተካሄደ፡፡
ደሴ፡- ጥቅምት1/2017ዓ.ም
ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ ዛሬ ተካሂዷል፡፡
እቅዱን ያቀረቡት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ኮሌጁ በ2017 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት አንፃር በትምህርትና ስልጠና፣በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እንዲሁም በአስተዳደር ሰራተኞች ሊከናወኑ የታቀዱ ስራዎችን ያቀረቡ ሲሆን እነዚህን ስራዎች በሚሰሩበት ወቅት ሊገጥሙ ይችላሉ ተብለው የታሰቡ ችግሮችና በመፍትሄነት የሚወሰዱ ተግባራትም በእቅዱ ተካተው ቀርበዋል፡፡
በዕለቱ በእቅዱ ዙሪያ ከተሳታፊዎች ቢካተቱና በቀጣይ ቢከናወኑ ተብለው የታሰቡ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በኮሌጁ ዲኖችም ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
#WSPC PR | 671 |
| 4 | لا يوجد نص... | 698 |
| 5 | ለኮሌጁ የቀድሞ ተማሪ የእውቅናና ምስጋና ፕሮግራም ተደረገ
ደሴ፡- መስከረም 28/2017ዓ.ም
ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
በአሜሪካን ሀገር ለ57 አመታት የኖሩት ዶ/ር ንጋቱ ሞላ በኮሌጃችን በቀድሞ ስሙ የወ/ሮ ስኂን ት/ቤት ከ1-3ኛ ክፍል እንዲሁም ከ6-8ኛ ክፍል ተምረዋል፡፡በ2014ዓ.ም በከተማችን በነበረው ጦርነት ወቅት በኮሌጁ የመማሪያ ቁሳቁሶች ላይ ውድመት በደረሰ ጊዜ ከ ወ/ሮ ስኂን ት/ቤት የቀድሞ ተማሪ አቶ ሚካኤል አስፋህ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ከቤተሰቦቻቸውና ከወዳጆቻቸው እንዲሁም ከስራ ባልደረቦቻቸው ገንዘብ አሰባስበው ላደረጉት ድጋፍ በኮሌጁ ማህበረሰብ ስም የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ተደርጎላቸዋል፡፡
በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ኮሌጁ የወደመበትን ንብረት በሰሙ ጊዜ ባደረጉት ድጋፍ ለትምህርት ክፍሎቹ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች እንዲሟሉና የምንሰጠው ስልጠና ሙሉ እንዲሆን ስላደረጉ በኮሌጁ ስም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
ዶ/ር ንጋቱ በበኩላቸው የቀረበልኝን ጥሪ እኔ ብቀበልም ገንዘባቸውን ሰጥተው የኮሌጁ የስልጠና ሂደት እንዳይቋረጥ ላደረጉ ቀና ሰዎች ምስጋና ይገባቸዋልና አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
በኮሌጁ ላይብረሪ ውስጥ አንዱ የሆነውን የኢንተርኔት ክፍል በዶ/ር ንጋቱ ሞላ ስም የተሰየመ ሲሆን በድጋፉ ለተሳተፉ ሰዎችም የምስጋናና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
#WSPC PR | 661 |
| 6 | لا يوجد نص... | 806 |
| 7 | لا يوجد نص... | 781 |
| 8 | ለ2016ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ | 763 |
| 9 | ለነባር የማታ ሰልጣኞች በሙሉ
የ2017ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ክፍያ ከመስከረም 20 እስከ 27/01/2017ዓ.ም ድረስ በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ በኩል በመክፈል የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በኮሌጁ ሂሳብ ክፍል እና የማታ ትምህርት ክፍል በመምጣት እንድታስመዘግቡ እናሳውቃለን ፡፡ | 653 |
| 10 | ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ
ደሴ፡- መስከረም7/2017ዓ.ም
ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
DMV FOR DESSIE ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በጋራ በመተባበር የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ ተደርጓል፡፡
በድጋፍ አሰጣጥ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የደሴ ከተማ አስተዳደርና ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ፍቅር አበበ “ሀገርን የሚወድ ሁሉ ትውልድ ላይ ይሰራልና ሁለቱም የበጎ አድራጎት ማህበራት በትብብር የሰሩት ስራ ይበል የሚያሰኝ ነውና ሊመሰገኑ ይገባል::” ብለዋል፡፡
የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከ2007ዓ.ም ጀምሮ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስና መሰል ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር አራት ተማሪዎችን እስከ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ማድረስ ችሏል፡፡
በዛሬው እለት በሁለቱ በጎ አድራጎት ማህበራት የተደረገውንም ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
#wspc pr | 582 |
| 11 | لا يوجد نص... | 459 |
| 12 | ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) ልደት የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። | 443 |
| 13 | የሀዘን መግለጫ
በኮሌጃችን በጨርቃጨርቅና አልባሳት ስልጠና ዘርፍ አሰልጣኝ መምህር የነበሩት አቶ ሰይድ አስፋዉ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።
ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጆቻቸዉ እና በቅርበት ለሚያውቋቸዉ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
#WSPC | 448 |
| 14 | ዝንባሌው ያላችሁ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና ለመመዝገብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ ማግኘት ትችላላሁ፡፡ 👇
https://l.facebook.com/l.php?u=https%3A%2F%2Fmp.weixin.qq.com%2Fs%2Fc6JPNez2u0FSZSkGb3x-mA%3Ffbclid%3DIwZXh0bgNhZW0CMTEAAR2_BTE6kEo_9RMZsNdpfUZoxm4AlNKmTeTLFWQt2zV3lzA1Dh2eFqBlD6k_aem_zBHn9B6ejxVP5bx1dvf1DA&h=AT0Az8r_h6ptc9fb-19gyNAgf-EtcN5i2w-szA6vlt-ysGiwCjt1JOoCw7eP9OaU7MbyZFQP9sQvRWihV971D50fdv6R2bFm6x5N-UdEt2ZEKE1A94xjiYsSRgoKrujK3gm3&__tn__=H-R&c[0]=AT1HWEbZkSHf5pK8ukc3KQV8DTA77IuStB5sum9-YirgqLCGA3h6ZMCblpftm2t6Ba9SY6LwX1WYe_OHpx43-x2_CriMpuJQ-g0tYBbTNyfXTPIXQENUtZLy4WHv2wG1RmPoIJV1GDeDwk7G1yUWCAsZi7scp9FJur9WTmJNfZNjhBFLKHroJpulwlgV9i-mzwyBBfrhS_tKqZc4eYCkHpk7L0E-o88yITfspmPZ7g | 415 |
| 15 | ለኮሌጃችን መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ፤ ሰልጣኞች ፤ ለቀድሞ ተማሪዎች እና የኮሌጃችን ወዳጆች እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ።
በዓሉም የሰላም ፤ የጤና ፤ የአንድነት ፤ የመተሳሰብ ፤ የእድገት እንዲሁም ኮሌጃችን የተሻለ እድገት የሚያስመዘግብበት ዘመን ይሁንልን።
ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን !
መልካም በዓል!
አቶ ሰለሞን ይመር
የኮሌጁ ዲን | 468 |
| 16 | ውድ የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መምህራንና ሰራተኞች እንዲሁም የኮሌጁ የቀድሞ ተማሪዎችና ሁለንተናዊ እድገቱን ለምትከታተሉ ቅን አሳቢ የኮሌጁ ደጋፊዎች በተጨማሪም በ2016አ.ም ስልጠናችሁን ጨርሳችሁ ለተመረቃችሁና በኮሌጁ ትምህርታችሁን ለምትከታተሉ ሰልጣኞች በሙሉ፦
እንኳን ለ2017አ.ም በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ አዲሱ አመት የሰላም የደስታ የፍቅር የመተሳሰብ እንዲሆንልን ምኞቴን እየገለጽኩ አገራችንን ሰላም አድርጎ ህዝባችንን ከስጋት ነጻ ሆኖ በስራው ረክቶ የድሃ እምባ ታብሶ የምናይበት ስለችግራችን የማንሰማበት ሆኖ አመቱ እንዲያልፍልን እመኛለሁ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
አቶ አያሌው መኮነን
ም/ል ዲንና የኢ/ኤ/ቴ/ሽ ቡድን መሪ | 494 |
| 17 | ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ | 616 |
| 18 | "ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት" በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡
ደሴ፡-ነሀሴ 22/2016ዓ.ም
ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የኢፌድሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴርና የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ በቅንጅት ያዘጋጁት የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች፣ኢንስትራክተሮችና ዲኖች የአቅም ግንባታ ስልጠና በአማራ ክልል 4 ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጥ ሲሆን በወሎ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተጀምሯል፡፡
ስልጠናው ለተከታታይ 12 ቀናት ማለትም ከነሃሴ22-ጷጉሜ3/2016ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የደሴ፣ኮምቦልቻና ወልድያ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ ከሰሜን ወሎ፣ደቡብ ወሎና ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ከሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ አሰልጣኞችንና ዲኖች ተሳታፊ ናቸው፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተቋማት ማስፋፋትና የአቅም ግንባታ ባለሙያ አቶ አስናቀ አይችሉህም ስልጠናው በዘርፉ ወቅታዊ ፖሊሲ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጥና አዳጊ ቴክኒካዊ ባህሪና እውቀትን ባለባሰ መልኩ የአሰልጣኞችን አቅም ማጎልበት የሚለውን ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የበቃ የሰው ሃይል መፍጠርና የአመለካከት ችግር በዘርፉ የነበሩ ተግዳሮቶች ሲሆኑ እነዚህ ተግዳሮቶች ከስልጠናው በኋላ ይቀረፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአማራ ክልል የስራና ስልጠና ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ይታየው ተናግረዋል።
በስልጠናው ተሳታፊ ከሆኑት መካከል የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር በበኩላቸው ከ150 በላይ የሚሆኑ የኮሌጁ አመራርና አሰልጣኞች በስልጠናው የሚሳተፉ ሲሆን በቂ እውቀት ለመቅሰም መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡ | 725 |
| 19 | لا يوجد نص... | 693 |
| 20 | የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሰልጣኞች የምረቃ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡
የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቀንና በማታ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን 854 ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ስራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ዶክትር ስቡህ ገበያው፣የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፣የኮሌጁ የቀድሞ ተማሪዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ዛሬ በተካሄደው የምረቃ መርሃ ግብር 522 ወንድ እና 332 ሴት ተማሪዎችን ማስመረቅ መቻሉን የገለፁ ሲሆን ተመራቂዎች ከምረቃ በኋላ በሚኖራቸው ህይወት እንደ ወይዘሮ ሰኂን ለትምህርት ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ተመራቂዎች ከስራ ፍለጋ ይልቅ ስራ መፍጠር ላይ ትኩረት አድርጉ ያሉ ሲሆን በዚህ ታሪካዊ በሆነው ወይዘሮ ሰኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተምራችሁ ለምረቃ በመብቃታችሁ በተለይም ሴት ተማሪዎች ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡
በክብር እንግዳነት የተገኙት የአማራ ክልል ስራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ዶክትር ስቡህ ገበያው ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የኢንዱስትሪ ጅምር ቴክኖሎጂና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በመሆናቸው ትምህርታችሁ በተግባር የታገዘ ነውና ውጤታማ በሚያደርጋችሁ ትምህርት እንዲሁም በዚህ ታሪካዊ ትምህርት ቤት በመማራችሁ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በኮሌጁ በስልጠና ወቅት የተሻለ ውጤት ለነበራቸው ተመራቂዎች የምስክር ወረቀት፣ሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት ከአማራ ክልል ስራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ዶክትር ስቡህ ገበያውና ከደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እጅ ተበርክቶላቸዋል። | 557 |
