cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ተዋሕዶ መዝሙር

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮነ ስርአት የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ከነዜማቸው በየቀኑ ወደነንተ ያቀርባል። ይቀላቀሉ አስተያየት ሀሳብ ጥያቄዎች ከአላቸው (0979871602) ✟✟✟✟

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 386
المشتركون
-124 ساعات
-187 أيام
+930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

"ይላል አንደበቴ" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው ትላንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ ትልሀለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ የትላንት ህይወቴን ዞር ብዬ ሳየው ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው ወደ እረፍቴ መጣሁ ይድረስ ምስጋናዬ ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታዬ /2/ ይላል አንደበቴ .............................. በጥልቁ በረሀ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ መንገዴን አቀናው እጄን በአፌ አስጫነኝ በእሳትና ውሃ መካከል አልፌ ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ /2/ ይላል አንደበቴ ................................. የብቸኝነቴን ማዕበል ገስጿል ለእኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል ቀስቱን እያጠፈ ታደገኝ ከስቃይ የጌታዬ ሀሳብ ፍቅር ነው በእኔ ላይ /2/ ይላል አንደበቴ ................................. ትላንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ የልቤን ፍላጎት ሳልነግረው አዋቂ በባህሪው ቅዱስ የሌለው አምሳያ ስሙ ወደቤ ነው መልህቄን መጣያ /2/ ይላል አንደበቴ .................................../2/ @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
إظهار الكل...
“ርስታችን ነሽ ” ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። የእንጀራ ምድር የፍቅር ሐገር፣ የለንም ወገን ካንቺ በስተቀር። በአክዓብ መሬት የማንቀይርሽ፣ ደጅሽ ቁመናል ባርኪን በእጆችሽ። ዳዊት አባትሽ እንዳለው፣ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። ወደ ምድራችን መጥተን ስንገባ፣ አንቺን አገኘን ታላቋን መባ፣ የሕይወት ውኃ ፈልቋል በሆድሽ፣ እንዳንጠማ ድንግል ልጆችሽ። ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። አሁን በደስታ ሥፍራ ይዘናል፣ መስቀል ላይ ሁኖ ጌታ ሰጥቶናል። ከዚህች ርስት ሚነቅለን የለም፣ አትሞበታል የደሙን ማህተም። ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊         [   የአርያም ንግሥት  !     ]        † እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል [ ደብረ ምጥማቅ ] በሰላም አደረሳችሁ † 🕊  †   ደብረ ምጥማቅ  †   🕊 የአርያም ንግሥት : የሰማይና የምድር እመቤት : የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት ፳፩ [ 21 ] ቀን በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: 🕊 [ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለዐምስት ቀናት ያኽል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያኽል ደስ ታሰኚ ኖሯል ! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው ] [ አባ ጽጌ ድንግል ] †                       †                         † 💖                    🕊                     
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
✞ሃሌ ሃሌ ሉያ✞ የማይመረመር ክብርና ምስጋና በሰማይ ለእግዚአብሔር ይገባዋልና መላእክት ለቅጽበት መች ያቋርጣሉ ያመሰግኑሃል ሃሌ ሉያ እያሉ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ፍጥረታት ለእግዚአብሔር ያቅርቡ ምስጋና(፪) ጽርአ ርያምን ዙፋን ያደረገ የእሳት መጋረጃ በእዛ የጋረደ በብርሃን ጸዳል መንበረ መንግሥትን ፈጠረው እግዚአብሔር ግድግዳ እንዲሆን        አዝ= = = = = ካህናተ ሰማይ መንበሩን ያጥናሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ያመሰግናሉ የሥላሴ መንበር በምን ይመሰላል ከግምት በላይ ነው ለማሰብ ያቅታል       አዝ= = = = = ዙፋኑ በእሳት የተቀጸረ ነው በቤቶቹም ዙሪያ የውሃ መርገፍ አለው በሰማይ ውዱድ ዘባነ ኪሩቤል የሰማዩ ስራ እጅግ ያስገርማል        በእሳት ነበልባል የተቀጸረችው ከምድር እስከ ሰማይ የምትናፈቀው እየሩሳሌም ነች ፍጹም ሰማያዊ ልዩ ህብር ያላት ዕንቁ ናት ሐምራዊ        አዝ= = = = = ታቦት ዘዶር በዚያ ከመሀሏ አለ መልኳ የሚያንጸባርቅ ብርሃኗ ያየለ በእመቤታችን የምትመሰል ነች ለቃሉ ማደሪያ በድንቅ የተሰራች        አዝ= = = = = ኢዮርና ራማ ኤረርም በግርማ ይባላሉ ከጥንት የመላዕክት ከተማ መላእክትም በዚያ እያሸበሸቡ ይኖራሉ ለአምላክ ምስጋና ሲያቀርቡ መዝሙር ይልማ ኃይሉ @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
إظهار الكل...
🕊 [ † እንኳን ለመናኙ ንጉሥ ቅዱስ አፄ ካሌብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † † 🕊 መናኙ ንጉሥ ካሌብ 🕊 † † ቅዱሱን ንጉሥ አፄ ካሌብን በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በትልቁ ያከብሩታል:: ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አክሱም አካባቢ ካልሆነ ከነ ስም አጠራሩ እንኳ እየተዘነጋ ይመስለኛል:: ነገር ግን ውለታው : ምናኔውና ቅድስናው የማይረሳ ነውና እንኳን በእምነት የሚመስሉን ይቅርና የማይመስሉን ምሥራቅ ኦርቶዶክሶችና ካቶሊኮች ዓመታዊ በዓሉን በወርኀ ጥቅምት ያከብራሉ:: ከአክሱም ነገሥታት በኃይሉም ሆነ በሃይማኖታዊ ቅድስናው አፄ ካሌብ ዋናው ነው:: ቅዱሱ የነገሠው በ፬፻፹፭ [485] ዓ/ም አካባቢ ሲሆን እስከ ፭፻፲፭ [515] ዓ/ም ድረስ በዙፋኑ ላይ ቆይቷል:: ከመልካም ትዳሩ አፄ ገብረ መስቀልን ጨምሮ ልጆችን ወልዷል:: † ስለ ቅዱስ አፄ ካሌብ እስኪ እነዚህን ነገሮች ብቻ እናንሳ :- ፩. በንግሥና ዙፋን ከመቀመጡ በፊት የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ጠንቅቆ ተምሯል:: ፪. ሃይማኖቱ የጠራና እጅግ የሚደነቅ ነበር:: በእርሱ ዘመን ሃይማኖት ለነገሥታቱ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ነበር:: እርሱ ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ አምልኳል:: ፫. ለእመቤታችንና ለቸር ልጇ የነበረው ጥልቅ ፍቅር የተገለጠና የሚያስቀና ነበር:: ፬. ገና በዙፋኑ ሳለ ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: ፭. ዛሬም ድረስ ሁሉም ክርስቲያኖች የማይረሱትን መንፈሳዊ ቅንዓትን አሳይቷል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- - በወቅቱ ዐመፀኛው የአይሁድ መሪ ፊንሐስ በሃገረ ናግራን [የአሁኗ የመን] ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖችን ክርስቶስን ካዱ በሚል ጨፈጨፋቸው:: ከተማዋንም ለአርባ ቀናት በእሳት አነደዳት:: ዜናው በመላው ዓለም ሲሰማ በርካቶቹ ቢያዝኑም የተረፉትን ለመታደግ የሞከረ አልነበረም:: ቅዱስ አፄ ካሌብ ግን የሆነውን ሲሰማ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በግንባሩ ሰገደ:: ወደ ፈጣሪም ጸለየ :- "ጌታዬ ሆይ ! የክርስቲያኖችን ደም እመልስ ዘንድ እርዳኝ? እኔ በጦሬ ብዛት አልመካም:: እኔ ተሸንፌ ክርስትና ከሚናቅ እዚሁ ግደለኝ" ብሎ በበርሃ ላሉ መነኮሳት እንዲጸልዩ ላከባቸው:: ጊዜ ሳያጠፋ በመርከብና በፈረስ : በበቅሎና በግመል ናግራን [የመን] ደረሰ:: ፊንሐስን ገድሎ ሠራዊቱንም ማርኮ ክርስቲያኖችን ነጻ አወጣ:: ደምና እንባቸውንም አበሰ:: አብያተ መቅደሶችን አንጾላቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ:: ወዲያው እንደተመለሰ ወደ አክሱም ጽዮን ገብቶ "ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላደረክልኝ የምሰጥህ ሰውነቴን እንጂ ሐብቴን አይደለም" ብሎ መንግስቱን ለልጁ ገብረ መስቀል አውርሶ ከዙፋኑ ወጣ:: የወርቅ አክሊሉን ወደ ኢየሩሳሌም ልኮ እርሱ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ መንኩሶ መነነ:: [በፎቶው ላይ የምታዩት አፄ ቅዱስ ካሌብ የመነነበት : አክሱም አካባቢ የሚገኝ የአባ ጰንጠሌዎን ገዳም ነው] ከዚሕች ዓለም ከአንዲት ረዋት [ኩባያ] : ከአንዲት ሰሌንና ከአንዲት ቀሚስ በቀር የወሰደው አልነበረም:: ከዚያም በበዓቱ ውስጥ በጾምና በጸሎት ተወስኖ አንድም ሰው ሳያይ በሰባ ዓመቱ [በ፭፻፳፱ [529] ዓ/ም] ዐርፏል:: ጌታችንም በሰማይ ክብርን አጐናጽፎታል:: † ለቅዱስ አፄ ካሌብ የተለመነ አምላክ ለእኛም ይለመነን:: በጻድቁም ጸሎት ከመከራ ይሠውረን:: [ † ግንቦት ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ አፄ ካሌብ [ መናኙ ንጉሠ ኢትዮጵያ ] ፪. ቅዱስ አሞንዮስ ገዳማዊ [ ታላቁ አሞኒ ዘቶና ] ፫. ቅድስት ሳድዥ የዋሂት ፬. አባ ሖር ጻድቅ ፭. አባ ዳርማ ገዳማዊ ፮. ቅዱስ ዘካርያስ አንጾኪያዊ ፯. አባ በትረ ወንጌል ዘደብረ ሊባኖስ [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ ሰማዕት ] ፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ † " አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል:: የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው:: የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም:: በበጐ በረከት ደርሰህለታልና:: ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ:: ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም:: ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ:: በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው:: " † [መዝ. ፳፥፩-፭] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
✞ ገብርኤል ✞ ገብርኤል (፪) ገብርኤል መልአከ ራማ (፪) ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እንስማ ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ የአምላክን ሰውን መሆን ለአለሙ ሰበክ(፪) አዝ= = = = = ከውኃ እና ከሳት ከሞት አመለጡ በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ ምንም ቦታ የለውም ሞትና መከራ(፪) አዝ= = = = = የመንገድ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና ዛሬም ለአገራችን ምስራች ይዘህ ና(፪) አዝ= = = = = አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ ስለአንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ እሳተ ነህ ገብርኤል ነባልባልባ አስወጋጅ የአምላክ መወለድ ለአለም ምታውጅ(፪) መዝሙር አቤል መክብብ @mazmur2122
إظهار الكل...
"ፍቅርህ ማረከኝ" ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ እግዚአብሔር ለኔ መድሃኒቴ ፍቅርህ ማረከኝ በህይወቴ በዘመኔ (X2) አዝ......... ተገዝቻለሁ በወርቅ ደምህ ዓለምን ትቼ ላገለግልህ ሞትህ ህይወቴ ለኔ ሆኖኛል ባንተ መከራ ሸክሜ እርቋል ለክብርህ ቆሜ እዘምራለሁ እንደ አቅሜ አገኝሃለሁ (X2) አዝ........ ምድርና ሰማይ እልል ይበሉ ምስጋና ላንተ ይድረስ እያሉ መሳይ የለህም ለቅድስናህ አቀርባለሁኝ ላንተ ምስጋና ጣቴ በገና ይደረድራል በቀን በሌሊት ያመስግናል (X2) አዝ....... ክብርህን አይተው ጠላቶች ፈሩ ለጌትነትህ ወድቀው ተገዙ እንዲህ ነህ አምላክ እንዲህ ነህ ጌታ ሁሉን በፍቅር የምትረታ ባንተ ተመካሁ በፈጣሪያችን አዳኝ በሆንከው በንጉሳችን (X2) @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
إظهار الكل...
✞ የኛ አባት ሚካኤል ✞ ሲያርፍ ያመሰግናል ሲያመሰግን ያርፋል ሲያርፍ ያመሰግናል ሲያመሰግን ያርፋል የኛ አባት ሚካኤል/2/ምሕረት ይለምናል በቅድመ ሥላሴ በጉልበቱ ሰግዶ ምስጋናን ያቀርባል የውዳሴን ነዶ ምሕረትን ይዞ ከአምላክ ዘንድ ተላከ ለማኑሄ ድርሳን ምስራች ሰበከ አዝ= = = = = ችግርን አልፋለሁ ይረሳል ሀዘኔ በሕይወቴ ሠልፎች ስላለ ከጎኔ ከአምላኬ ተልኮ የታደገኝ ከሞት መርቶ ያደርሰኛል ከሠማዩ መንግስት አዝ= = = = = የአምላክ ስም በላዩ ስላለ ታትሞ ከፊቴ ይወጣል በመንገዴ ቀድሞ ያድናል ሚካኤል ጭንቀትን አርቆ የወህኒውም መዝጊያ ይከፈታል አውቆ አዝ= = = = = ልጄ ነህ ብሎኛል አባቴ እለዋለሁ ለአምላኬ ዘመርኩኝ ሲዘምር ስላየሁ አይደክምም ልሳኑ አያውቅም ዝምታ ምስጋና ምግቡ ነው ዘውትር ጠዋት ማታ አዝ= = = = = ስለህዝቡ ልጆች የሚነሳው መልዓክ አንተነህ ሚካኤል የመረጠህ አምላክ ዝማሬ ጸሎቴ አይሁንብኝ ከንቱ ከእጣኑ ጢስ ጋር ይውጣልኝ በፊቱ መዝሙር ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ @mazmur2122 @mazmur2122
إظهار الكل...
🕊 [ † እንኩዋን የመነኮሳት አባት ለተባለው "ቅዱስ ዻኩሚስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ] 🕊  ቅዱስ ዻኩሚስ [ አባ ባኹም ]  🕊 ዛሬን አያድርገውና ምንኩስና ማለት መላእክትን መስሎ የሚኖርበት ሕይወት ነበር:: ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ዻኩሚስን ያሕል የደከመና የተሳካለት ግን የለም:: ቅዱሱ በትውልዱ ግብፃዊ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ከቀደመ ሕይወቱ ጋር በተያያዘ የሚተረክ ነገር በመጽሐፈ ገድሉ ላይ አለ:: ዻኩሚስ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣ በታላቁ አባ ዸላሞን አማካኝነት ነው:: ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል:: በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሔድ ከአባ ዸላሞን ተለይቶ : ማሕበር መስርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል:: ቅዱስ ዻኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር:: አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ ጾሟል:: ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል:: እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር:: ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር:: ስለ ክብሩም መላእክት ወደ ሰማይ ወስደው ገነትና ሲዖልን አሳይተውታል:: አባታችን ቅዱስ ዻኩሚስ ከርሕራሔው የተነሳ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን : ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያዛቸው ነበር:: ከዚያም በጾም : በጸሎትና በስግደት ያማስናቸዋል:: ያኔ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ ደጉ አባት "ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ" ይላቸዋል:: አጋንንቱም እያደነቁ "ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ዓይነት ፍጡርስ ዓይተን አናውቅም" ብለው እንደ ጢስ በነዋል:: አጋንንት ስለሚፈሩት "አርበኛው መነኩሴ" ይሉታል:: "  የቅዱስ ዻኩሚስ ፍሬዎች   " ፩. በግብፅ በርካታ ገዳማትን አቁዋቁሟል:: ፪. ለሁሉም ገዳማት አበ ምኔቶችን ሹሞ እየዞረ ይጠብቃቸው ነበር:: ፫. የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል:: ፬. መነኮሳት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል:: ፭. መነኮሳት ከገዳማቸው በፍፁም እንዳይወጡ ከልክሏል:: ፮. ከግብፅ ውጪ ምንኩስናን ያስፋፉ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል:: [ለምሳሌ በኢትዮዽያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው] ከዚሕም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል:: ቅዱስ ዻኩሚስ ጫማ ሳይጫማ: እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር:: የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እጥፍ ሆኖ የበዛለት ቅዱሱ መነኮስ ወደ ወደደው እግዚአብሔር በዚህች ቀን ሔዷል:: የጻድቁ መነኮስ ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን:: 🕊 [ †  ግንቦት ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ አባ ዻኩሚስ [አበ መነኮሳት ሣልሳዊ] ፪. አባ ሲማኮስ ሰማዕት [ †  ወርሐዊ በዓላት ] ፩. አቡነ አረጋዊ [ዘሚካኤል] ፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ ፫. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ ፬. ቅዱስ ሙሴ [የእግዚአብሔር ሰው] ፭. አባ ስምዖን ገዳማዊ ፮. አባ ዮሐንስ ጻድቅ ፯. እናታችን ቅድስት ነሣሒት " ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም:: በእናት ማሕጸን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ:: ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ:: ስለ መንግስተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ:: ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው:: " [ማቴ.፲፱፥፲፩] (19:11) [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...