cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Hot Pic's & Memes Of N.C.A

#Official Hot Pic's Of N.C.A Channel Your Admin @Nata_9877 . In This Channel We Will Post Hot Pic,MEMES, So Join For More !!!!Only Neway Students Any Comments : 👉 @Sule4749 @moha_196 👈

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
667
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ ! የዉድ የሆት ፒክስ ቤተሰቦች😁 ይህን በዓል በሰላም እና በደስታ ማክበር የተጨነቁ ከጭንቀት ነፃ የሚሆኑበት የሰላም ፣ የደስታ፣ የአንድነት፣ የፍቅር በዓል ይሆን ዘንድ እንመኛለን። መልካም በዓል ! በአል እንዴት ነበር ወገን?
إظهار الكل...
👏 21
🙁
🤌 5
إظهار الكل...
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! @newaychallnege
إظهار الكل...
የGroup አሳይመንት ሲሰጥ አንዳንድ Memberoch😁😁 @Newaychallnege
إظهار الكل...
1.22 MB
የካንፓስ መምህራን አይነቶች ....💡 📚 ሁሉም ካንፓስ ተነግሯቸው ይመስል አነድ አይነት ሙድ የሚያራምዱ አስተማሪዎች ማግኘት የተለመደ ነው ። በካንፓስ ቆይታ ከቻላችሁ ከየትኛውም መምህር ላለመጣላት ሞክሩ ምክንያቱም ሰገጤ እና ገገሙ የሆኑ ስላሉ ለጓደኞቻቸው ሁሉ እየነገሩ F በ F ነው የሚያረጉላችሁ ። ብትቀያየሙም አትናገሩ መታገስ ነው ግን ፒስ ለመሆን ሞክሩ ። ብትከሱዋቸውም ስለሚተዋወቁ ችላ ነው የሚላቹሁ አሪፍ ዲስፒሊን ያለበት ግቢ ማግኘት ከባድ ነው ። ትምህርታችሁ ላይ አተኩሩ የተለየ ሙድ ለማራመድ አትሞክሩ ። ለዛሬ የአስተማሪ አይነቶችን እንሹፍ ፦ 💡 MR ...F 📚 ተማሪዎቹ ዲ ራሱ ሲያመጡ የሚጨንቀው ...በቃ ለሁሉም F ለመስጠት የሚጓጓ ጋሽ አዝግ ....የሌለ የሌለ ጥያቄ የሚያወጣ .....እንዳትመልሱት አስቦ ፈተና ሚያወጣ ከፈለገ 4 ሞጁል በ 2 ሳምንት አንብባችሁ ጨርሱ ፈተና አለ ይላል ። ከዛ ሰግጣችሁ አንብባቹ ስትሄዱ ፈተናው ላይ ከሞጁሉ 2 ጥያቄ ቢወጣ ነው ። እንዳለ ከሌላ source አምጥቶ....ጉድ ነው ሚሰራችሁ ። ስጠይቁት ሌሎችንም መፅሀፍ ማንበብ ነበረባችሁ ይላል ...." ደሞ አንዳንዱማ እየተናገረ ነው የኔን ሳብጀክት D ካመጣችሁ ጀግና ናቹሁ እያለ ነው ....ሙድ የሚይዝባችሁ .... ይሄ ቲቸር ከደረሳችሁ ተበላቹሁ ። አንዳንዶቹ ውጤት ላይ ያዝናሉ ....B+ እና C ይሰጣሉ ....አንዳንዱ ግን በዛው F የሚያበላም አለ ። ፈጣሪ ይሰውራቹህ ። 💡 ዶ/ር ጢባሮ ......! 📚 ይቺኛዋ ሰውዬ ደግሞ ጢባሯ ዳሽንን ይተልቃል ። በቃ አሜሪካን ትቼ የመጣሁት ኮ ...ቅብርጥሶ ቅብርጥሶ ...ከፈለገ እኔ 500 ገፅ መፅሀፍ በአንድ ለሊት ተረድቼ የምጨርስ ሰው ነኝ ...ምናምን ይላል ....።ዶ/ር እንትና ኮ ድ/ር አይደለም ....ሁሉም የውሸት ነው ዶክትሬታቸው ...እኔ ብቻ ነኝ ብቸኛው ለዮኒቨርስቲው ...ቅብርጥሶ በቃ ይቆለልባቹሃል ። ሀገሬ ብዬ እንጂ እጄ ስመው ነው ባህር ማዶ የሚቀበሉኝ .....መቻል ነው ። የሚያስቁ ሙዶች ነው የሚያራምድባችሁ ...ድንገት እንኳን ተሳስቶ ስህተት ከሰራ ተሳስቼ ነው ሞቶ ነው በፍፁም ተሳስቼ አይሉም ...ልፈትናችሁ ብዬ ነው ...እንጂ አውቃለሁ ...አውቄ ኮ ነው ይላሉ .....ግን ብዙ ግዜ እነዚ ሰዎች ሲያስተምሩ ጎበዝ ናቸው ። ታዲያ ጉራውን ትቶ እውቀቷን ቀጨም ነው ። 💡አቶ ዝባዝንኬ........! 📚 ክላስ ገብቶ ስለ ግል ህይወቱ የሚዘላብደው ነው ይሄ ...! canda ሄጄ ሚስቴ ጋር ሽርሽር ሰዎቹ በጣም ሀገራቸውን ይወዳሉ ....ኧረ ወዲያ እኛ ምን አገባን ❓ ...አትሉት ታዳምጣለቹሁ ....ሲዳማ የቆንጆ ሀገር ሲባል ልይ ብዬ ባለፈው ሄጄ ሳያየቸው....ኧረ ቁንጅና በቃ የአፈር ገንፎ ነው ሚመስሉት.....አንድ አንደው አፍንጫዋ የቆመም ሴት የለም...ፎንጋ ብቻ....መቻል ነው ። ከሰውየዋ ጋር የማትገቡበት የለም .....መዞር ነው....ቤተሰቡን ይቀባጥረል አንዴ.....አክስቴ ደንበኛ ባልቴት ነበረች እናላቹ እኔን ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ....አሁን እዚ ደርሼ....መቀደድ ነው .....ከዛ ይመሻል ወይ ግዜው ሲሄድ ሮብ እንጨርሰዋለን የቀረውን ይላል ሳይጀምር ....ሮብም እንዲሁ ይዘላብዳል ....! ዝብዝብ ሲልባቹሁ ....መቀረት እንዳታበዙ ቻሉት ...!. 💡 ቲቸር..... እምዬ...! 📚ይሄ ብዙ ግዜ ወጣት አንዳንዴም ጎልማሳ እንደ እናት የሆነ መምህር ነው ።ስትቸገሩ ይረዳቹሃል ከመምህር ስትጣሉ ለማግባባት ይሞክራል ። ክላስ ላይም ለLIFE የሚሆኑ tips እና መላዎች ...ስለ ግቢው ምናምን ይመክራቹሃል ። በቃ ችግር ሲገጥማችሁ ቀድማችሁ ብትነግሩዋቸው መፍትኤ ይሰጧቹሃል ። አይዞን ይሏቸውል ፤ያጀግናቹሃል ... የምትወዱት አይነት መምህር ነው ። ውጤትም ቢሆን እነደ ልፋታችሁ ነው የሚሰጣቹሁ ። በቃ የምር አስተማሪነት የገባቸው ናቸው ። ይመቻቸው ...! 💡 ፕሮፌሰር ላተሽናቹሁ ......! 📚 ቴንሽናም ሼቦች ናቸው ። በገቡ ቁጥር አባታችሁ በሬ ሸጦ አስተምሯቹሁ ....እናንተ በየመጠጡ ቤት ...በዚ ከቀጠላችሁ መጫራችሁ ነው ። በየአመቱ ይን ያህል ተማሪ ይጫራል ፤ ካልሰገጣቹሁ እናንተም ዕጣ ፈንታቹሁ ይሄ ነው ። ቡኃላ በፀፀት ከምትታነቁ አሁኑኑ አንቡብ ....በተራ ውጤት ተመርቃችሁ እናታችሁ ጋ ሸክም ከምትሆኑ ብትሞቱ ይሻላል በማዕረግ ካልተመረቃችሁ ስራ የለም ...ድንጋይ ነው የምታሞቁት ቅብርጥሶ እያለ over ቴንሽን ነው ሚያረጋችሁ ። አንዳንዴ ልክ ቢሆንም ያን ያክል ሲኦል ግን አይደለም ። ይሄ ሰውዬ ስታገኙት እነደ ህንድ ፊልም አጋኖት ነው ብላቹ እለፉ ፤ ግን በመጠኑ መተሸኑም ቆንጆ ነው ። 💡 MR...ሳክስ 📚 ይቺ ደግሞ መጀመርያ ክላስ ገብታ የምትቅለሰለስ ነች ። በእኔ ሳብጀክት አታስቡ ትንሹ የምታመጡት B+ ነው ። እኔ ለማንም ከዛ በታች አልሰጥም ይላል ... ይሰክሳል ሳትጨናነቁ ትማራላችሁ ውጤት ሲመጣ ግን C እና D ነው ። ምነው ? ስትሉት ...B+ የምርጫ ቅስቀሳ ነው ይላቹሃል ። ሳክሱ እና ተግባሩ አይገናኝም .....በተስፋ ሞልቷቹሁ በኃላ ጉድ እንዳይሰራቹሁ እናንተ 24 ስታንድ ባይ ነው መሆን ያለባችሁ ። ሊያዘናጋቹ ነው ። ዘ ....ኖት 💡 📚 አጅሬ ቸክችክ ናት .....በቃ መፃፍ ነው ። እጅ ይዝላል ።ትፅፋለህ በ3 ሰዓት 6 ብላክቦርድ/ስላይድ ሙሉ ትፅፋለህ .....አልፅፍም የለም .....ወላ ከነሸጠው ደብተር ሁላ ከ20 ሊይዝ ይችላል ....ኖት በኖት ነው ምትሆኑት ፈጣን ካልሆናቹ ያጠፋባቹሃል ፤ ከላይ ከላይ ይፅፋል በቃ ነቀላቹሁ ...! በኖት ቀልድ የለም ...ከዚ ይሰውራቹሁ .....ግን አንድ መምህር እንደዚ አይታጣም ...!
إظهار الكل...
ብር ስለታሸገ ብቻ ሳትቆጥሩ እንዳትቀበሉ
إظهار الكل...
5.60 MB
إظهار الكل...
BÈBÂ on TikTok

ሰለታሸገ ብቻ ሳይቆጥሩ አይቀበሉ !!!!! #ethiopian_tik_tok #ሀበሻ🇪🇹🇪🇹🇪🇹tikt

♻️ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ አዲስ ሊሆኑባቹህ የሚችሉ የግቢ ቃላቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት። 🎊ካፌ- ብዙሃኑ ተማሪ የሚጠቀምበት የግቢው መመገቢያ ቦታ 🎊ላውንጅ - ግቢ ውስጥ የሚገኝ ተማሪን ባመከለ መልኩ ክፍያ የሚያስፈልግ ካፌ ነገር ነው ፤ ምግብና መጠጦቹ(ለስላሳ ፣ ትኩስ ነገር ምናምን) ጥራት ያላቸው እና በዋጋም በጣም ቅናሽ ናቸው። 🎊በግ ተራ - የሴቶች ዶሪሚተርይ አከባቢ ያሉ መጃጃያዎች። 🎊ችከላ- ጥናት 🎊ቴንሽን- ጭለላ ፣ ውጥረት፣ መረበሽ፣ መጨናነቅ 🎊 11 - ግማሽ እንጀራ በዳቦ ( የካፌ ምግብ ነው በተለይ እራት ላይ) 🎊Non-cafe -የግቢውን ካፌ የማይጠቀሙ ተማሪዎች 🎊Space - ባዶ ክፍል ብዙውን ጊዜ መማሪያ ክፍሎችን ለንባብ ስንጠቀምባቸው ስፔስ ይባላሉ 🎊Therefore- የካፌ ስጋ ( ስጋ ሲባል ግን ሰፍ እንዳትሉ ! እንደስሙ ነው ማለት ትንሽ ስጋ ጣል ጣል የተደረገበት ገራሚ መረቅ ) 🎊Cost -ካፌ ለማይጠቀሙ ተማሪዎች የሚሰጥ ወርሃዊ ክፍያ ፤ የሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ክፍያው ተመሳሳይ ነው። 🎊Add and drop - በትምህርት ሂደት ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ነገሮች ናቸው ፤ ይሰውራቹህና የሆነ ኮርስ ከፈላ(F) add and drop process ግድ ይሆናል 😊ድድ ማስጫ- አላፊ አግዳሚውን ለማየት አመቺ የሆነ ቦታ ወይም መቀመጫ 🎊ሸራ - ለማታውቁት አትወቁት ያው የጫማ ስም ነው 🎊ዛፓ - ጥበቃ ሰራተኞች 🎊GC- ተመራቂ ተማሪዎች Fresh፣ጦጣ ምናምን - አዲስ ገቢ ተማሪዎች ( ግቢ ስትገቡ ፍሬሽ ምናምን እያሉ አዛ የሚያደርጓቹህ ብዙውን ጊዜ ሁለተኛ አመቶች ናቸው ሁሉም ሁለተኛ አመቶች ሳይሆኑ ፍሬሽነታቸውን ያልጨረሱት ወይም ገራሚ ፉገራ የተፎገሩት ናቸው 🎊በርጮሎጂስት- የፍየልን መኖ የሚጋፉ ጫት ቃሚዎች ማለት ነው 🎊ኦቨር- መጠጥ ቤት መሄድና ሰክሮ መምጣት 🎊ሻታ - ይቅርባቹህ እንዳያስመልሳቹህ ብዬ ነው 🎊3D/ 7D - around በግተራ ይላ ኤድናሞል ነው 🎊ጥፊ- የዶርምን ላይፍ እንዳይረሳ ከሚደርግ ግሩም ጠረኖች ውስጥ አንዱ ነው፤ በተለይ በተለይ ወንዶች ጋር የተለመደ የካልሲ ጭስ ነው ( ወንዶችዬ ተዉ ግን አታሰደቡን? )
إظهار الكل...
🔥12ኞች ስለ የትኛው ዩኒቨርሲቲ ማወቅ ይፈልጋሉ? ❶Addis Ababa University https://t.me/Freshstudents/2802 ➋ Astu Adama https://t.me/Freshstudents/2806 ➌ Gonder University https://t.me/Freshstudents/2810 ➍ Bahirdar University https://t.me/Freshstudents/2816 ➎Jimma University https://t.me/Freshstudents/2821 ❻Hawassa University https://t.me/Freshstudents/2823 ❼Ambo University https://t.me/Freshstudents/2831 ❽Debra Markos University https://t.me/Freshstudents/2843 https://t.me/Freshstudents/2834 ❾Arbaminch University https://t.me/Freshstudents/2839
إظهار الكل...
Fresh students 2021

1.አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ፡ አዲስ አበባ በውስጡ ያሉ ግቢዎች ፡ በጣም ብዙ ማለትም አስራ ምናምን ይደርሳሉ የአየር ሁኔታ ፡ የመጀመሪያዎቹ ወራቶች መጠነኛ ብርዳማ ሆነው ወደ ኋላ ላይ ግን ሞቃታማ የአየር ንብረት አለው ይሄን info ለሰጣችሁኝ ላቅ ያለ ምስጋና ይድረስልኝ COURSES AND PLACES ካሉት ግቢዎች ውስጥ በጥቂቱ 6 ኪሎ፣5 ኪሎ፣4 ኪሎ፣ ሜክሲኮ፣ልደታ ፣18 ማዞሪያ ፣ ጥቁር አንበሳ ( hospital)፡ደብረዘይት. ....etc 🏠6 kilo for social students only 🏠5 kilo for enginering ( Software , electrical , biomedical , mechanical , civil , chemical ... በነገራቹህ ላይ biomedical engineering ከሚሰጥባቸው ጥቂት ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው። 🏠4 kilo computer science 🏠18 Other health 🏠Tikur anbessa Medicine 🏠LIDETA architecture , cottom , urban plannig 🏠Mexico commerce ( marketing management ... minamn ) For Engineering temariwoch ➡ drawing material ➡ Mathematics and Mechanics Statics guide books ይዛቹህ ብትሄዱ መልካም ነው ። 💋AAU ደብረዘይት ላይ Veterinary medicine &Science collage አለው እኛ ስንገባ ብዙዎቻችን confused ሁነን ነበር አዲስ አበባ መስሎን ነበር በመጀመሪያ ስለዚህ ብዙዎቻቹህ ይሄን መረጃ ባለማወቅ እንደኛ ግራ እንዳትጋቡ ካሁኑ info ይኑራቹህ ብዬ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካሉት ብዙ ግቢዎች ውስጥ ደብረዘይትም…

የትኛውም ካንፓስ ቢደርሳችሁ የማታጧቸው 7 ግለሰቦች ...! 📚 ካንፓስ ቆይታ ማለት በህይወታችን በጣም ውዱ ግዜ ነው ።ደግመን ልናገኘው የማንችለው ነው ። በጣም ከብዙ ሰዎች ያስተዋውቀናል በትንሹ የአለም ትክክለኛ ገፅ የምናይበት ነው ። ታዲያ በካንፓስ ቆይታ ግዜ የሚገጥሙን የተማሪ አይነቶች አሉ ። ሚገራርሙ ሰዎችን በህይወታችን እናያለን ። ሚገራርም ሰገጤ ፥ አራድዬ ሰዎች ፤ መማራቸው በራሱ የሚያጠራጥር...! በቃ ውዝግበግብ ያሉ ነፍ ሰዎች አሉ ። ታዲያ እኛም መርጠን በየካንፓሱ የማይጠፉ 7 ታይፖችን መርጠናል ። እንያቸው እስቲ ፦ 💬 7 ወንዶች ታይፕ ተማሪዎች ፦ 💡 MR .ቴንሽን ...! 📚 ካንፓስ ላይ ነፍ ሙድ መያዣ ነገሮች አሉ ። አንዱ ማተሸን ነው ። በቃ ከመሬት እየተነሱ የማይሆነ ነገር እያወሩ ያስፈራራሉ በተለይ ፍሬሽ ስንሆን ሙድ መያዣ ነው የምንሆነው ። በቃ ነገ ፈተና ተብሏል ብሎ ይደውልልሃል አንዱ ከዛ አንቺ ተሽነሽ አዳር ስታነቢ አድረሽ ጠዋት ክላስ ደፈንኩት ብለህ ሱክ ሱክ ስትል ትምህርት ራሱ የለም ። ምናምን ። ታዲያ በነዚ ወሬዎች የሚተሽን ቦቅቧቀ ሰው ሁሌ አለ ። በቃ በሆነው ባልሆነው ይንበጨበጫል ከዚ ሰው ራቁ ይዟቹሁ ገደል ነው ። የሚተሽኑ ተማሪዎች ብዙ ግዜ አንባቢ ናቸው በዛውም ልክ ውጤት ግን አይሰሩም ። ከነዚ ሰዎች ራቅ ነው ። 💡 MR.. ስፓርተኛ ዶርም እስከ 8 ሰዎች ይኖራሉ በእርግጠኝነት አንዱ ብረት ተሸካሚ ነው ። በቃ ፍጋት ያስጠላሃል ። በየቀኑ ስለ 6 pack ነው ወሬው ። በሶ ካላቹሁ በቃ አለቀላችሁ በፍቅርም ሆነ በጉልበት ይጠጠባቹሃል ። ታዲያ ብዙዎች አንድ ሰሞን ይነሽጣቸዋል ደሞ ቺኮችን ለማማል ብለው ። ስፓርት ከጀለስ ጋር ይጀምራሉ ግን አይቆይም ይተውታል ። ታዲያ ይቺ ጀለስ ጥቅም አላት ለስፓርቱዋ ጠዋት ስለምትነሳ ትቀሰቅሳለች ደሞ በጡንቻዋ ማስፈራራት ትችያለሽ የሚያስቸግር ካለ ። 💡MR .አይናፋሩ 📚 ካንፓስ የሄዱ ብዙዎች ይዘውት የሚመጡት ነገር ፎንቃ ነው ። ካዲያ ሴት ተጠግቶ የማያውቀው ጀለስ ድንገት ፎንቃ ሲገባለት በቃ ተውኝ ።የሌለ የሚያስቅ ነው ። ሲጃጃል ታያላችሁ ። እሷን ሲያይ አለቀ ...ቀነኒሳ መቼ ይሮጣል ። ንገራት ብላችሁ ጨቅጭቃችሁ አሳምናቹሁት ሄዶ ስለ አሳይመንት አውሮቶ ይመጣል ሊያው ከደፈረ ወይ መንገድ ቀይሶ ወደ ዶረም ይሸበለላል ። ከዚ ይሰውራቹሁ ። ግን ላይፉ በተለይ የዶርም ልጅ ከሆነ ሳትስቁ አታድሩም ። 💡 ...ዘረኛው ብራዘር..... 📚 በቃ አክቲቪስት አክቲቪስት የሚያጫውተው ነው አጅሬ ። ተጨቁነን ይልሃል እየመጣ ፤ ነፃነት ይልሃል እየመጣ ....በቃ እንት ላይ እንት ሆኑ ነው ። ገደሉን ነው .... የረብሽ ግዜ ከዚ ሰውዬ መራቅ ነው ። ልታስረዳው ስሞክር አልገባህም ይልሃል.... በቃ ሳትፈልግ ይሄ ፖተሊካ ትጋታለህ ። ደሞ ከወደደሽ ወይ ዘሩ ከሆንሽ ሊከትብሽ የማይፈነቅለው ነገር የለም ። ተጠንቀቁ ዘረኝነት ከለከፋችሁ ...ብትሞቱ ነው ሚቀለው ። ደሞ በቀዉጢ ሰዓት ስለሆነ ግቢ የምንገባው አዛ ነው ። ፓለቲካ አቋማችሁ ለራሳችሁ ራሱ እንዳትናገሩ ...ያለበለዚያ ውጣ በተባለ ቁጥር ወጥተህ ይሄን የፌደራል ዱላ ቀምሰህ ትመጣለህ ። ሰልፍ የካፌ ራሱ ረዘም ካለ ይቅርብህ.....ብሮ 💡 THE ፈላስፋው MAN ......! 📚 ካንፓስ ዶርም ይሄን ሰው ካገኛችሁት ዕድለኛ ናችሁ ። በቃ አለ ኣ ለሊት 7 ሰዓት ግድግዳ ላይ እያፈጠጡ ታገኙታላችሁ ፤ ደንግጣችሁ ምን ሆነህ ❓ ነው ስትሉት ክር እፈለኩ ይላቹሃል ..የምን ክር ስትሉት ❓ በማወቅ እና በመማር መሀከል ያለችውን ቀጭር ክር እየፈለኩ ነው ይላቹሃል ።ወይ ደግሞ ድንገት ጠዋት 12 ሰዓት ተነስቶ ይቀሰሰቅሳችሁ እና ከመሞት መኖር እንደሚቀል ማረጋገጥ እፈልጋለሁ ይላቹሃል ❓ ይሄ ሰውዬ.. ያምሃል... ሆ ልተኛበት ባክህ ስትሉት ....ዘላለማዊ እንቅልፍ አላማረህም ይልሃል ....ይሄ ልጅ ሊወጋኝ ነው ዴ ብላችሁ እንቅልፋችሁ ጠፍቶ ስትነሱ ...ትንሽ ቆይቶ አገኘውት ብሎ ሊተኛ ይችላል ። በቃ ሲወዛገብ እያያችሁ መሳቅ ነው ። ሳትስቁ አታድሩም አልኳቹሁ ። ታዲያ እንዳትከተቡ ማዘር ዲግሪ ስጠብቅ ጨልላችሁ እንዳትጫሩ ...ዋ".! 💡 አቶ uniqe.... 📚 አጅሬን ካገኛችሁት እንዳትፋቱት በቃ አለ ኣ የምትቀኑበት አይነት ሰው ነው ።ስለ ህይወት ያለው ዕይታ ....ስለ ገንዘብ ስለ ነገሮች በቃ በተየለ መንገድ የሚኖር ስለ ሌሎቹ የማይመለከተው የራሱ LIFE ስታይል ያለው ምናምን ፐፐ አቦ በቃ ትደመማላችሁ ። እነዚ ሰዎች ትምሮ ብዙ ግዜ ይሰራሉ ግን 24 ሰዓት ሲቸክል አታየውም በቃ የሚያረገውን ያውቃል ። ጥንቁቁቅ ምናምን ዝንጥ ያለ አራዳ .....ይሄ ሰው ጓደኛ ካረጋችሁ የምር ላይፋችሁ ይቀየራል ዶርማችሁ ባይኖር ክላስ ውስጥ በእርግጥም ቢያንስ 1 አለ ጓደኛ አርጉት ስለ ህይወት ብዙ ትማራላችሁ። many hesit አይተሃዋል በቃ ፕሮፌሰሩ ማለት ነው ። ወይም prsion break ካየየሃው ማይክል ስኮፌልድ ማለት ነው ። በቃ ወጣ ያለ ነው ግን የራሱ way ያለው ነው ። 💡 MR ..ቸካይዬ..! 📚 ይቺ ሰው የትም አለች ሰጋጭ ነች ። በቃ ህይወቱ ተመሳሳይ አዙሪት ጠዋት ክላስ ከዛ ካፌ ፤ ከዛ ላይብረሪ ፤ ማታ ዶርም አዳር ንባብ ፤ ጠዋት ክላስ... በቃ ቅዳሜ የለ ፤ ፊልም ልይ የለ ፤ over የለ ....ወይኔ ለገነት ቁልፍ ነው ሚመስላቹ ። ቺክ ላጫውት የለ ፦ ፈተና አልቋል የለ ፤ ፍሬንዶች ይደብራቸዋል የለ ፤ ፓሪ የለ ፤ ፎንቃሼ የለ ...በቃ ሙሉ ህይወቱ x መፈለግ ነው ። ሽምደዳ ንባብ ነው ። ለውጤት ከዚ ጋር መሆን አሪፍ ግን አድክም ንባብ አነባለው ብለሽ ማን እስከ ደም ጠብታ መታገል ይከብዳል ። ሳትንዘላዘይ ግን ፈታ እያልሽ ነው ብሮ እንጂ በገገሙ የሚሆን ነገር የለም ። ደሞ ዶርማቹ እንዲ አይነት ሰው ካለ በቃ ይጨንቃቹሃል ።ፈታ እንዳትሉ እሱ እያሰባችሁ ትተሽናላችሁ ። ያን ያክል ለውጥ ለውም መገገሙ የመጀመርያ ውጤት ስታዮ ትረጋጋላቹሁ ። ግን ይቺ ሰውዬ ስለ ፈተና ምናምን እውቀት ስለሚኖራት መጠጋቱ አሪፍ ነው ። ውጤት ታስተካክላለች ። 📚 ነገ የሴቶቹን type የምናይ ይሆናል::
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.