cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡» https://t.me/joinchat/8gFiOsA4mkE5OGM8

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
189
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

↪️ አዲስ ሙሀደራ ➖➖➖➖➖➖ ♦️የሙሀደራው ርዕስ ➫➫➫➫➫➫➫➫ 🌐«ባወቅነውና በተማርነው ነገር ላይ የመስራት አስፈላጊነት።» 🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
إظهار الكل...
ባወቁት መስራት.mp33.48 MB
የተዳሰሱ ነጥቦች - አቡበክር አህባሹ ለ ዮናታን ጴንጤው አቀበለው፣ - ሙስሊሞችን “ጣኦት አምላኪዎች” ላለው አቡበክር የተሰጠ መልስ፣ - “ቸገረኝ ብለህ አታውራ ወሬ፣ ጓዝህን ይዘህ ግባ ቃጥባሬ” … - “እኔ ባንቱ ሸሸሁ፣ አንቱ በጌታሁ…. ባንቱ የሸሸን ይምራል ጌታሁ” ላለችው ሴት የተሰጠ መልስ - “ጫት ጉዳት የለውም” ላለው የተሰጠ መልስ https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
إظهار الكل...
የአህባሾች ቅጥፈት.mp314.61 MB
ይህ ጥያቄ ላይ ብዙዎች ተሳስተው እናገኛለን። ትክክለኛው መልስ አይቻልም የሚለው ነው። የተገኘው ሁሉ ኡስታዝ ደርስ ማዳመጥ ፈትዋ መስማት እንዲሁም መማር የማይቻል ለመሆኑ ብዙ ነጥቦችን ማንሳት ይቻላል። ለምሳሌ የሱፍያ፣ የአህባሽ፣ የተብሊግ እንዲሁም የሺአ አመለካከት ያላቸው አስተማሪዎች በዘመናችን በዝተዋል። የሁሉም መከታተል ይቻላል የምንል ከሆነ በቀላሉ በነሱ ተፅእኖ ውስጥ እንወድቃለን። በሽርክና በቢድአ በቀላሉ እንዘፈቃለን። የነዚህን ሰዎች የተበላሸ አመለካከትና እምነት በመያዝ እውነት እየመሰላቸው ለሀቅና ለሀቅ ሰዎች ጠንቅ የሆኑ ምስኪኖች እጅግ ብዙ ናቸው። በነሱ ሰበብ ከቅናቻው መንገድ ይወጣሉ። ያገኘውን ሁሉ የሚያነብ በተገኘው ሁሉ የሚማር ሰው ከሀቁ ጎዳና ለመውጣት እጅግ የቀረበ ነው የሚሆነው። ነብያችን ኡመር ኢብኑል ኸጧብ እጅ ላይ ከተውራት የሆነን ፅሁፍ ስላዩ በዲናችሁ ትጠራጠራላችሁን? በማለት አውግዘውበታል። ስለዚህ እውቀት ዲናችን ነው። የሚወሰደውም ከማንም ሳይሆን እምነታቸው፣ አቂዳቸውና አካሄዳቸው የተስተካከለ ከሆኑትና የቁርአንና የሀዲስ መልእክት በሰለፎች አረዳድ የሚገነዘቡ እንዲሁም በታማኝነታቸው ከሚታወቁት እንጂ በተገኘው ሁሉ አይደለም። ውዱ ነብያችንም ከጥመት ተጣሪዎች፣ ከፊትና ሰዎችና ከቢድአ ባለቤቶች እውቀት ከመውሰድና ከመማር በግልፅ አስጠንቅቀዋል። ያለእውቀት ፈትዋ የሚሰጡ፣ በማይመለከታቸው ላይ የሚገቡ፣ ወደ ጀሀነም በር የሚጣሩ ተጣሪዎች እንዳሉና ለህዝባቸው ከደጃል ፊትና በላይ የነዚህ ፊትና የከፋ እንደሆነ በማያሻማ መልኩ ገልፀዋል። ከታናናሾች እውቀት መውሰድ ከየውመል ቂያማ ምልክቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል። በሀዲሱ ላይ ታናናሽ ሲባል የሚፈለግበት የቢድአ ባለቤቶች እንደሆነ ኡለማዎች አስፍረዋል። ሸኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል። «ከስሜት ተከታይ ከሙብተዲእና አዲስ ፈጠራ ከሚያመጣ ሰው እውቀትን አትቅሰም። ይልቁንስ መማር ያለብህ፦ ከአህለሱናዎች ከሱና ኡለማዎችና ከትክክለኛ አቂዳ ባለቤቶች ነው።» በተጨማሪም መሀመድ ኢብኑ ሲሪን አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል። ይህ እውቀት ዲን (ሀይማኖት) ነው። ስለዚህ ከማን መውሰድ እንዳለባችሁ ጠንቅቃችህ እወቁ።) እውቀት ማለት እስልምናህ ነው። ስጋና ደምህም ጭምር ነው። ለጤናህ ከምትሳሳውና ጥሩ ዶክተር ከምትመርጠው በላይ እንዲሁም የትዳር አጋር ስትመርጥ ከምትጨነቀውና ትኩረት ከምትሰጠው በላይ የዲን አስተማሪህ ማን መሆን እንዳለበት በትኩረት ልታጤን ይገባል። በተለይ በዚህ ዘመን በዲን ስም የሚያጭበረብሩ ከቀጥተኛው መንገድ የሳቱ የጥመትና የፊትና ተጣሪዎችና አስተማሪዎች እጅግ በጣም በዝተዋል። ሰለፎች የቢድአ ባለቤትን እጅግ በጣም ይጠነቀቁ ነበር። ወጥ የሆነ የማያሻማ መርሆ ነበራቸው። እነሱን መጥላት፣ ከነሱ መለየትና መራቅ፣ ሌሎችንም ማራቅ፣ ማህበረሰቡ ከነሱ ማስጠንቀቅ፣ ንግግራቸውን አለመስማት፣ ኪታባቸውን አለማንበብ ከተቻለም ማቃጠል፣ ፈትዋቸው አለመስማት፣ ከእነሱ ጋር አለመቀማመጥ፣ እነሱን ከማወደስና ከማላቅ መጠንቀቅ እንዳለብንና ሌሎችም ወሳኝ ተያያዥ ነጥቦች በኪታባቸው አስፍረው ይገኛል። የቢድአ ባለቤት መሆኑ ከተረጋገጠ ከዚህ በፊት በሱና የሚታወቅ እንኳ ቢሆን ሰለፎች ከሱ ሊማሩ ይቅርና በእጅጉ ነበር የሚርቁት። በዚህ ዙሪያ ብዙ መዘርዘር ቢቻልም ለምሳሌ ያክል የተወሰነ ልጥቀስ። =ታላቁ ሶሀብይ አብደላህ ኢብኑ ኡመር ቀደርን ስለሚያስተባብሉ የቢድአ ባለቤቶች እንዳሉ ሲነገረው «እኔ ከነሱ የጠራሁ መሆኔና እነሱም ከኔ የጠሩ መሆናቸውን ንገሩዋቸው» ነበር ያለው። =አብደላህ ኢብኑ አባስ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል። ከስሜት ባለቤቶች ጋር አትቀማመጡ። ከነሱ ጋር መቀማመጥ ቀልብን ያሳምማል። =ሀሰነል በስርይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል። ከስሜት ባለቤቶች ጋር አትቀማመጡ። ከነሱም ጋር አትከራከሩ። ከነሱ ምንም ነገር አትስሙ። =አቢ ቂላባ አላህ ይዘንላቸውና የቢድአ ባለቤቶችን በተመለከተ እንዲህ ብሏል። አታቀማምጧቸው፣ አትቀላቀሏቸው። ምክንያቱም በጥመቶቻቸው ውስጥ ይዘፍቋችኋል። ብዙ ስታውቁት የነበረን እውነታ ያለባብሱባችኋል። =ኢብኑ ጣውስ ተቀምጦ ባለበት ሁኔታ አንድ የሙእተዚላ ቢድአ አራማጅ የሆነ ሰው መጣ። ይህ ሰው የሆነ ነገር መናገር ሲጀምር ኢብኑ ጣውስ ጣቶቹ ጆሮዎቹ ውስጥ አስገባ። አጠገቡ ለነበረው ልጁ እንዲህ አለው። ልጄ ሆይ ጣቶችህ ጆሮህ ውስጥ አስገባ። በደምብ አጠንክረህ ዝጋ። ከንግግሩ ምንም እንዳትሰማ አለው። መእመር ይህ ያደረገበት ምክንያት ሲናገር ቀልብ በጣም ደካማ ስለሆነች ነው ብሏል። =ሁለት የቢድአ ባለቤቶች መሀመድ ኢብኑ ሲሪን ዘንድ በመግባት የበክር አባት ሆይ ሀዲስ እንንገርህ? አሉት። እሱም አልፈልግም አላቸው። እሺ በቃ ከአላህ ኪታብ ከቁርአን አንዲት አንቀፅ እናንብብልህ አሉት። አሁንም አልፈልግም አላቸው። በመቀጠልም ተነስታችሁ ውጡልኝ አልያም እኔ እወጣለሁ አላቸው። እነሱም ተነስተው ወጡ። ይህንን ክስተት የሚከታተሉ የተወሰኑ ሰዎች ነበሩና ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ ለመሀመድ ኢብኑ ሲሪን ለምን እምቢ አልካቸው ቁርአን ቢያነቡልህ ምን ችግር ነበረው ብለው ጠየቁት። እሱም «አዛብተው ቀርተው (ሹብሀ) ፈጥረውብኝ ቀልቤ ላይ እንዳይፀና ፈራሁኝ» አላቸው። የፈለግነውን ብናነብና ብናዳምጥ ጥሩውን ወስደን መጥፎውን እንተዋለን የሚለው አባባል ብዙዎች ጥፋት ላይ የሚወድቁበት እጅግ በጣም አደገኛ አባባል ነው። ከዛም ከዚም እየሰማ፣ እያዳመጠና እያነበበ በቀላሉ ሹብሀ ላይ ይወድቃል። በባጢል ሰዎች አነጋገርና በፅሁፋቸው ምጥቀት በመማረክ ሸይጧን ልቡ ላይ ባጢል አሳምሮለት በቀላሉ መስመር ይስታል። ከላይ እንዳየነው እነዚያ በእውቀት ባህር የነበሩ ሀቅና ባጢል አብጠርጥረው የሚያውቁ ታላላቅ የዲን ሊቃውንቶች እነ መሀመድ ሲሪን ኢማሙ አህመድና መሰሎቻቸው እንኳ እንዲህ አልተዘናጉም። ጥሩውን እንውሰድ መጥፎውን እንተው በማለት የቢድአ ባለቤቶችን ቀለል አድርገው አልተመለከቱም። እኛ ከነሱ በልጠን ነው እንዲህ የምንለው? በየትኛው እውቀታችን ተማመንን? በየትኛው ደረጃችን? ሽቡሀ በራሳችን ላይ ከነሱ በላይ እንዴት አልፈራንም? በመጨረሻም ከቢድአ ባለቤት ቁርአን መቅራት፣ ተፍሲር መማር፣ ሀዲስ መቅራት፣ ፈትዋ መጠየቅ፣ ሙሀደራው ማዳመጥ የተከለከለ መሆኑን ልናውቅ ይገባል። == http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
إظهار الكل...
ቆየት ካሉ ምርጥ ሙሐደራዎች ሙሐደራው በሰፋት የሚያጠነጥነው‼️ 1 በሼህ የህያ እና በተከታዬቹ ላይ ያለው ሰህተት ምን ይመሰላል??? 2 እንደዝሁም በጀምዕያ ጉዳይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰቶበታል። በኡስታዝ አብዱረህማን ( አቡ ሂዛም) አላህ ይጠብቀው። https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
إظهار الكل...
ሙሐደራ በቢድዓ ዙሪያ.amr7.34 MB
በጫት የተተረተረው የጫሌ ጉንጭ?
إظهار الكل...
በጫት የተተረተረ ጉንጭ.mp39.44 KB
ልብ ያለዉ ልብይበል በአፍብቻ እኔ ሀቅላይነዉያለሁት እኔሰለፍይነኝ አይሰራም ሸይኻችን እያላችሁ የምትጠሩት ምን አይነት ላይእንደነበረ ብዙ አሉ በትቂቱይሄዉ
إظهار الكل...
6.85 MB
📝محاضرة جديدة ↪️ አዲስ ሙሓደራ ♦️ርዕስ" እኛና ወጣትነት 🎙በወንድማችን አቡ ዑሰይሚን አብዱረህማንhttps://t.me/abuUseyminabdurehman/5881
إظهار الكل...
እኛና ወጣትነት _1.mp35.60 MB
🔉ሙሀደራ ክፍል / 23 ◉مخالفات يحيى الحجوري وأتباعه لمنهج السلف الصالح ◉ያህያ አል ሀጁርይ እና ተከታዮቹ የሰለፎችን አካሄድ ከተቃረኑባቸው ጉዳዮች በከፊሉ። 👉#እህት ወንድሞች እኛ ተአሱብ አያስፈልገንም ያለውን መስአላ ቁጭብለን እንይ አሣሡን እንየው። #ያሕያ አልሀጁሪ ስለምንወደው ብቻ 👉የምንወደው ኡስታዝ የነሱ ተከታይ ሰለሆነ ብቻ‼️ #ሴቷ የምታፈቅረው ወንድ እዚያ ጀመዓ ስለአለ ብቻ‼️ 👉ወይም ደግሞ ወንድሟ እዚያ ውስጥ ስላለ ብቻ‼️ #ወንዱም የሚያፈቅራት ሴት እዚያ ውስጥ ስላለች ዝም ብሎ በጭፍን መከተል አያስፈልግም‼️ ከሙሐደራው በጨረፍታ የተወሰደ 👂አዳምጥ//አዳምጭ👂 🗒 ልናደምጠው የሚገባ ጠቃሚና ወሳኝ ሙሐደራ 🎙 በኡስታዝ አቡሙስሊም ሀፊዘሁሏህ ════✺═ ════ ═✺═ ═ ሌሎች የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት ወደ ዋናው ቴሌግራም ቻናላችን ጎራ ይበሉና ይቀላቀሉ በአሏህ ፈቃድ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ⬇️⬇️ ⬇️⬇️ ⬇️⬇️ ⬇️⬇️ https://t.me/abuhuzeyfahseid ════✺═ ════ ═✺═ ═ https://t.me/menarutewhidwesunna ጡባ ሊል ጉረባእ የሰለፍዮች መወያያ እና መተራረሚያ ግሩፕطبى للغرباء ════✺═ ════ ═✺═ ═ የዋትሳፕ አድራሻችን ደግሞ 👇👇 👇👇 https://chat.whatsapp.com/KviAKDSAGPnDPJljqW1vUY ════✺═ ════ ═✺═ ═
إظهار الكل...
24kb_ሙሀደራ_14.46 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.