cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Admas Media - አድማስ ሚዲያ

ይህ Admas Media -አድማስ ሚዲያ - ኦፈሽአል ቴሌግራም ነው። የሚወዱትን Admas Media -አድማስ ሚዲያ ማህበራዊ ገፅ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። This is Admas Media - አድማስ ሚዲያ Official Telegram Channel መልዕክት መቀበያ እና ለማንኛውም አይነት ጥያቄ @Admas_media_bot እንዲሁም ለማስታውቂያ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
4 119
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-47 أيام
-19130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
Update የህውሃት ሰው የሆኑት አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር ከሳምንታት ጋር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ውስጥ በኢንተርፖል ቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።ለኢትዮጵያ መንግስትም ተላልፈው ይሰጣሉ ተብሎ ነበር።ሆኖም በርካታ የትግራይ ተወላጆች ባሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ ኢንተርፖል ሰውየውን ትናንት እንደለቀቃቸው ታውቋል።ቢሊየነሩ አቶ ዳዊት የወ/ሮ ፈትለወርቅ/ሞንጀሪኖ/ወንድም ናቸው።ለመንግስት ተቃዋሚዎችን የትጥቅ ድጋፍ በማጠናከር በተደጋጋሚ ስማቸው ይነሳል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በዓለም አሳሳቢ የሆነው የሞት ፍርድ❗️ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በ2023 ጥፋተኛ በተባሉ ሰዎች ላይ የሞት ቅጣትን ተፈጻሚ በማድረግ ኢራን እና ሳዑዲ አረቢያ ቀዳሚ አገራት ናቸው ብሏል። የመብት ተሟጋቹ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ተፈጻሚ የሚያደርጉትን የሞት ቅጣት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመራቸው በ2023 የተመዘገበው አሃዝ ከባለፉት 8 ዓመታት ከፍተኛው ነው ብሏል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በ16 አገራት 1ሺህ 153 ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል። ከእነዚህ መካከል 74 በመቶ የሚሆኑት በኢራን የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው ሲሆን 15 በመቶ የሚሆኑት የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው ደግሞ በሳዑዲ ነው ተብሏል። በዚህ የአምነስቲ ሪፖርት ላይ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በሞት ከምትቀጣው ቻይና መረጃ ማግኘት ባለመቻሉ ቤይጂንግ በሪፖርቱ አለማካተቱን ገልጿል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ በሰላም ወጥቶ መግባት አጠራጣሪ ሆኗል- ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ በኢትዮጵያ በሰላም ወጥቶ መግባት አጠራጣሪ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ። ፓትሪያሪኩ ይህን ያሉት ዛሬ በተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባት ለጠቅላላ ማህበረሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሯል ያሉት ፓትሪያሪኩ፥ የቤተክርስቲያኗ ፈተና ምንጭ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዕድል ሰጩው ሁኔታ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው ብለዋል፡፡ በዚህ አለመግባባት ምክንያት መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት፣ ምእመናን፣ አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት እየደረሰባቸውም ቢሆንም “ይህን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም’’ ሲሉ ተናግረዋል። “ባለፉት አመታት በቤተክርስቲያኗ እና በአገልጋዮቿ ላይ የሚደርሱ በደሎች ቀጥለዋል፤ ወደፊትም የሚያስቆም ሁኔታ መኖሩን እንጠራጠራለን” ያሉት አቡነ ማትያስ፥  በደልን በካሣ እና በዕርቅ፣ በይቅርታ እና በምህረት መዝጋት ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቋማስርዓት ማበጀት እንደሚገባ አሳስበዋል። ፓትሪያሪኩ በመክፈቻ ንግግራቸው ከውጫዊ ችግሮች ባሻገር ቤተክርስቲያኗ የገጠማትን ውስጣዊ ፈተና አንስተዋል። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሹመት ፈላጊነት እና የገንዘብ ፍቅር መንገሱን፣ መለያየት እና መነቃቀፍ እየሰፋ መምጣቱን በማንሳትም ኃላፊነት የጎደላቸው ንግግሮች “በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነት እና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው” ብለዋል። ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፤ በአገልጋዮች እና ምዕመናንን ላይ የሚደርሱ ግድያዎች እንዲቆሙ ቤተክርስቲያኗ በተደጋጋሚ ማሳሰቧ ይታወሳል። ቤተክርስቲያኗ ውስጣዊ አንድነቷን አደጋ ላይ ይጥላሉ ባለቻቸው ጉዳዮች ላይም አቋሟን የሚያንጸባርቁ መግለጫዎችን ስታወጣ ቆይታለች። ባለፈው አመት ጥር ወር ከቤተክርስቲያኗ አፈንግጠው የራሳቸውን ሲኖዶስ አቋቁመናል ካሉ የቀድሞ አባቶች ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት መቋጨቷ የሚታወስ ነው። በተመሳሳይ በትግራይ ክልል የተከናወነውን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲቆም ጥረት ስታደርግ መቆየቷና ሹመቱ መካሄዷ በእጅጉ እንዳሳዘናት መግለጿም አይዘነጋም። ቤተክርስቲያኗ ቀኖናዋን ባልጠበቀ መልኩ የኦሮሚያ ሲኖዶስን ከመሰረቱ አባቶች ጋር ስምምነት ላይ መድረሷን ካሳወቀች በኋላም የቤተክርስቲያኗን አንድነት የሚፈታተኑ ድርጊቶች መቀጠላቸውን በመግለጫዎች ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ የጀመረው እና ለቀናት በሚዘልቀው ምልዓተ ጉባኤው ቤተክርስቲያኗን እየፈተኑ በሚገኙ ሀገራዊ ሁኔታዎች እና ውስጣዊ ችግሮች ዙሪያ መክሮ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ተገልጿል። Via አል አይን
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የካርድ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  ተጠቃሚዎች በየሱቁ  ካርድ መግዛት የሚችሉበት አሰራር ይፋ ሊሆን ነው የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 10 ወራት ሚያዚያን ጨምሮ  76 አዳዲስ የገጠር  ከተሞች እና አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታየ  በካርድ እያስሞሉ የሚጠቀሙ ደንበኞች አገልግሎት በተመለከተ ቴክኖሎጂውን ለማዘመን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ። በተጨማሪም  አሁን ላይ በቴሌብር የሚከፍሉ ደንበኞች  የኤሌክትሪክ ካርድ በየሱፐር ማርኬቱ እና በየሱቁ በሞባይል ካርድ ይዘት ባለው መልኩ  የሚያገኙበት  አሰራር  እየተዘጋጀ እንደሚገኝ  እና አፈጻጸሙ  84 በመቶ እንደደረሰ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ባለፈው 10 ወራት ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ  ሶስት መቶ ሁለት አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት ተችሏል ከእቅድ አንጻር 66.5 በመቶ ማሳካት የተቻለበት ዓመት መሆኑንም ገልዋል። በሌላ በኩል ወላይታ ሶዶ ፣ ሻሸመኔ ፣ ሀረር፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደር  ከተሞች ላይ የኔትወርክ ማሻሻያ እና የመልሶ ግንባታ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው የተሰሩባቸው አካባቢዎችም  ናቸው ። የመንግስት ተቋማትን ጨምሮ በርካታ የአገልግሎቶት ሂሳባቸውን የማይከፍሉ ደንበኞች ፣ እንዲሁም የመስመር ብልሽት እና ማርጀት እንዲሁም የኤሌክትሪክ አገልግሎት  መስመሮች ስርቆት   በበጀት ዓመቱ የነበሩ ተግዳሮች መሆኑም ተነግሯል ።
إظهار الكل...
ቲክቶክ በመንግስታት የሚደገፉ የሚዲያ ተቋማት አካውንቶችን ላይ አዲስ ህግ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው። ከዚህ በፊት ቲክቶክ የእነዚህ ተቋማት የቲክቶክ አካውንት "State controlled media" የሚል ታግ ይለጥፍባቸው ነበር። በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚያደረገው የገለፀው ህግ ጣቢያው ከሚሰራጭበት ሀገር ውጪ ባሉ ቲክቶክ ተጠቃሚዎች ላይ የጣቢያዎች ቪዲዮ for you page ላይ አይመጣም። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ አካውንቶች for you page ላይ አይመጣም ማለት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የእነዚህ ጣቢያዎች የአካውንት ማስታወቂያ ከሀገሪቱ ክልል ዉጭ የማይታይ ይሆናል። ይህ ህግ የወጣበት ምክንያት ሀገሮች በሌሎች ሀገሮች ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ፕሮፖጋንዳ ስለሚነዙ ነው ተብሏል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በመሬት መንሸራተት 300 ሰዎች ተቀበሩ❗️ በፓፑዋ ኒው ጊኒ በተደረሰ የመሬት መንሸራተት 300 ሰዎች መቀበራቸው ተነገረ። በፓፑዋ ኒው ጊኒ አንድ መንደር ባወደመው ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ 300 ሰዎች እና 1100 ቤቶች መቀበራቸውን ሮይተርስ የሀገሪቱን ሚዲያዎች ጠቅሶ ዘግቧል። ከዋና ከተማዋ ሞረስቢ 600 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው የኢንጋ ግዛት ውስጥ የካዎካላም መንደር የመታው የመሬት መንሸራተት አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ሳይቀጥፍ እንደማይቀር ተሰግቷል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ኦሮሚያ ባንክ ለብድር ካቀረበው 43.5 ቢሊዮን ብር 26 በመቶ የሚሆነውን ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በብድር ማቅረብን አስታወቀ! ከተመሰረተ 15 ዓመታት ያስቆጠረው ኦሮሚያ ባንክ 54 ቢሊዮን ብር በቁጠባ መልክ ማሰባሰቡን፤ ከዚህ ውስጥም ለብድር ካቀረበዉ 43.5 ቢሊዮን ብር ዉስጥ በነፍስ ወከፍ ሲሰላ በአማካይ አንድ ተበዳሪ 1.5 ሚሊዮን ብር ከባንኩ ማግኘቱ ተገልጿል።ይህም የብድር ስርጭቱ ከባንኩ ደንበኞች ምጣኔ አኳያ 92 በመቶ ይይዛል እንዲሁም ከተበደሩት ብድር አንፃር ደግሞ 26 በመቶ ይሸፍናሉ ተብሏል። ቀሪው የብድር አቅርቦት ለከፍተኛ ተበዳሪዎች ማቅረብን የገለፀዉ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ይህም የብድር አቅርቦት በአማካይ አንድ ተበዳሪ 5 ሚሊዮን ብድር መውሰዱ ተናግረዋል።የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ጨምረዉ እንደተናገሩት የባንኩ የተበላሸ የብድር መጠኑ ከ1.6 በመቶ እስከ 2 በመቶ የሚደርስ እንደሆነ ገልፀዋል። በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት የተበላሸ ብድር መጠን ጣሪያ 5 በመቶ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ አሁን ላይ በዘርፉ ያለው አማካይ የተበላሸ የብድር መጠን 3.6 በመቶ መሆኑን አብራርተዋል።አሁን ላይ ቅርንጫፎችን ከመክፈት ወደ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት ፊቱን ያዞረዉ ባንኩ "ኦሮ ዲጂታል" በተሰኘው አገልግሎት ቴሌግራምን ጨምሮ በ7 አማራጮች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። Via Capital
إظهار الكل...
በሱዳን ያንዣበበውን የዘር ማጥፋት ዓለም ችላ እንዳለው የተመድ ባለሙያ ተናገሩ! በሱዳን ዳርፉር ግዛት የዘር ማጥፋት እያንዣበበ ቢሆንም የዓለም ትኩረት ግን የዩክሬን እና ጋዛ ጦርነት ላይ ብቻ እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት ባለሙያ ገለጹ።የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊን የዘር ማጥፋትን ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት በተመለከተ የሚያማክሩት ልዩ ልዑክ አሊስ ዋይሪሙ ንደርቱ ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ በዳርፉት የዘር ማጥፋት የተካሄደበት ወይም ሊካሄድ የሚችልበት ሁኔታ አለ። በሱዳን ኤል ፋሽር ከተማ ውስጥ ሰዎች በጎሳ ማንነታቸው ምክንያት የጥቃት ዒላማ መሆናቸውን ባለሙያዋ ተናግረዋል።በከተማው የሚገኝ የሕክምና እርዳታ የሚሰጥ ተቋም ባለፉት 10 ቀናት 700 ሰዎች መገደላቸውን መዝግቧል።ከዳርፉር ግዛት በሱዳን ጦር ሥር የሚገኘው ብቸኛ ከተማ ኤል ፋሽር ሲሆን፣ ባለፉት ቀናት ጦርነቱ ተባብሷል። ፈጥሮ ደራሽ ኃይሉ እና የሱዳን ጦር ከአንድ ዓመት በላይ ጦርነት ውስጥ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተድለዋል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው ተሰደዋል።ኢብራሒም አል-ታይብ አለ-ፋኪ የተባለ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደገለጸው፣ እህቱ የተገደለችው ቤታቸው ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ነው። ሦስት ልጆቹ ከአያታቸው ጋር እንዲቆዩ ቢልካቸውም ይህ ቤትም በአየር ጥቃት እንደወደመ ገልጿል። አሁን መላ ቤተሰቡ መጠለያ ውስጥ ይገኛል።“በኤል ፋሽር ምንም ደኅንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም” ብሏል።የተመድ ባለሙያ እንደተናገሩት ሁኔታው “እንደ ሩዋንዳ” እየሆነ ነው። “በኤል ፋሽር ጥቃት እየተባባሰ ነው። ግጭቱ አስጊ ደረጃ ላይ ይገኛል። ድምጼን ለማሰማት ብሞክርም ትኩረት ያለው በዩክሬን እና ጋዛ ጦርነቶች ላይ ስለሆነ ሰሚ አላገኘሁም” ብለዋል።ሂውማን ራይትስ ዋችም በዳርፉር የዘር ማጥፋት ስጋት እንዳለ አስታውቋል። በማሳሊት ብሔር እንዲሁም አረብ ባልሆኑ ማኅበረሰቦች ላይ የዘር ማጽዳትና ሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።የመብት ጥሰቱን እየፈፀሙ ይገኛሉ ያላቸው የፈጥኖ ደራሽ መሪው መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሔሚቲ)ን ጨምሮ ሌሎችም ኃይሎች ተጠያቂ እንዲደረጉም ጠይቋል። አረብ ያልሆኑ አርሶ አደሮችና አረብ አርብቶ አደሮች መካከል ለረዥም ጊዜ የቆየ ቁርሾ ያለ ሲሆን፣ ጦርነቱ ውጥረቱን አባብሷል።የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከተማዋ ላይ ከበባ ከማድረጉም ባሻገር የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።ተመድ እንደሚለው አምና በዳርፉሯ ኤል ጀኒና ከተማ ወደ 15 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል። Via BBC
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በ13ተኛው "ለዛ ሽልማት" እነማን አሸናፊዎች ሆኑ?  13ኛው የ "ለዛ ሽልማት" ስነ ሥርዓት ትናንት ግንቦት 16 2016 ዓ/ም በሂልተን ተካሄዷል። 🎞 በዚህም መሰረት በፊልም እና ትወና ዘርፍ ፦ - የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ፦ አርቲስት ግሩም ዘነበ (በዶቃ ፊልም) - የዓመቱ ምርጥ ፊልም፦ ዶቃ ፊልም  - የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት፦ አርቲስት መስከረም አበራ (በ የሱፍ አበባ ፊልም) - የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም፦ በስንቱ  - የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይ፦ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ (በስንቱ) - የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይት፦ አርቲስት መስከረም አበራ (በስንቱ ) አሸናፊ መሆን ችለዋል። 🎙 በሙዚቃ ዘርፍ የዓመቱ የለዛ አሸናፊዎች እነማን ናቸው ? - የዓመቱ ምርጥ አልበም፦ የግርማ ተፈራ ካሣ " ግን የት ሀገር ?" አልበም - የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ፦ የድምጻዊት ራሔል ጌቱ "ኢትዮጵያዬ" - የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዘፈን፦ የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ "ናዕት" - የአልያስ መልካ ሽልማት (ምርጥ አዲስ ድምጻዊ)፦ ወግዳይት (አሳላፊ አልበም) - የዓመቱ ምርጥ ዘፈን፦ የድምጻዊት ሔዋን ገ/ወልድ "ሼሙና"   🙏 የህይወት ዘመን ተሸላሚው ደግሞ አንጋፋው ድምጻዊ ንዋይ ደበበ መሆን ችለዋል። #LezaAward #Award #Admasmedia1
إظهار الكل...