cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ፍሬ ሃይማኖት

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአ/አ ሐገረ ሥብከት የመ/ደ/ገ/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረቦች ግጥማቸው ከነዜማ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡ ® ለማናኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄና ጥቆማ @Frehaymanoteebot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 707
المشتركون
-124 ساعات
-17 أيام
-830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በሰንበት ትምህርት ቤታችን ፍሬ ሃይማኖት ለነዳያን ማስፈሰኪያ አገልግሎት እየተካሄደ ነው:: ሁላችሁም አባላት መጥታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ እንጠይቃለን::
إظهار الكل...
የጌታችን የስቅለት በዓል በካቴድራላችን በመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል እየተከበረ ይገኛል:: እንኳን አደረሳችሁ::
إظهار الكل...
ሰላም እንዴት ናችሁ የፍሬ ሃይማኖት ልጆች :- እንኳን አደረሳችሁ :: እነሆ የምግባረ ሰናይ ክፍል ለትንሳኤ የነድያን ምገባ እና ጉብኝት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ::በመሆኑም ሐሙስ አርብ ቅዳሜ እና እሁድ የተለያዩ ስራዎችን ያከናውናል :: ስለሆነም ሁላችንም ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በመገኘት በአገልግሎቱ ተሳታፊ እና የበረከቱ ተካፋይ እንዲንሆን በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ። ከሐሙስ ጀምሮ የሚከናወኑ ተግባራት 👉ለነድያን የሚበተኑ አልባሳትን መምረጥ መለየት እና ማስተካከል 👉አካባቢውን ማስተካከል እና ማጽዳት 👉ሽንኩርት መላጥ 👉ከምእመናን የሚመጡ ቁሳቁሶችን መቀበል ✝️ቅዳሜ ለእሁድ አዳር ✝️ 🐂 በሬ ማረድ 🧅 ሽንኩርት ማቁላላት 🥩 ስጋ መክተፍ 🥘 ወጥ መስራት 🥡 ለፀበልተኞች ምግብ መቋጠር 🥡 የተቋጠረው በተመረጡ ቦታዎች መውሰድ እና ማደል ነድያንን ማስፈሰክ ሌሎችም በርካታ አገልግሎቶች ስላሉ ከሐሙስ ጥዋት ጀምሮ ሙሉ ቀን ስላለን እየመጣን ምንተ ንግበር (ምን እናድርግ) እንበል የበዓሉ የበረከት ተሳታፊ እንሁን ሁላችንም እንገኝ በህብረት እናገልግል ። የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ምግባረ ሰናይ ዋና ክፍል !
إظهار الكل...
ሰላም ለእናንተ ይሁን የፍሬ ሃይማኖት አባላት ለትንሳኤ የሚደረገው የነዳያን ምገባ ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ ነው:: ማገዝ እና መርዳት የምትችሉ ሁላችሁም የበረከት ተሳታፊዎች እንደምትሆኑ በትንሳኤው ባለቤት በልዑል እግዚአብሔር ስም አሳስባለሁ::
إظهار الكل...
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ የሐመረ ብርሃን የብራና መፅሀፍት ሥራ ድርጅት "ንፁህ ምንጭ ኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ በዘመናችን ትልቅ ታሪካዊ አሻራ አሳርፎ የሚያልፍ ከሚያዝያ4 - ሚያዝያ13 የሚቆይ ልዩ ዓውደ ርይ በግዮን ሆቴሌ እንዳዘጋጁ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ሲያስተዋውቁ የቆዩ ሲሆን ስለሆነም ለዚህ ተከታታይ 10 ቀን የሚቆይ አውደ ርይ ከሰንበት ት/ቤታችን የቀን አበል እየተከፈላቸው የሚያገለግሉ አባል ስለሚፈልጉ በአወደ ርዩ ላይ እንደ ኤግዚቢተር ለመሳተፍ የምትፈልጉ አባላት በሰንበት ት/ቤታችን ፅ/ቤት መታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ!      ፍ/ሀ/ሰ/ት/ቤት ጽ/ቤት
إظهار الكل...
"ተፈፀመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል:: የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈፀመ:: መድኃኒት የሚሆን መስቀልም በቀራንዮ ተተከለ::" መልክአ ሥላሴ እንኳን ለጌታችን ጥንተ ሥቅለት አደረሳችሁ:: ለእኛ ሲል የተንገላታ የተሰቀለ አምላካችን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን :: አገልግሎታችንን ይባርክልን::
إظهار الكل...
የሱባኤ ያሬድ ምዝገባ ሊንኩን ተጭነው ይመዝገቡ! https://janderebaw.org/subae-yared በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የጃን ያሬድ የኅብረ ዝማሬ አገልግሎት ክፍል "ሱባኤ ያሬድ" የተሰኘ ኦርቶዶክሳዊ የቅድመ ዘማሪነት መንፈሳዊ ትምህርት አዘጋጅቶአል:: በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለሰባኪነት እና ለክህነት አገልግሎቶች የሚያበቁ ትምህርቶች እንዳሉ ይታወቃል:: ለዘማሪነት አገልግሎት ግን ከጥሩ ድምፅና የማገልገል ፍላጎት በስተቀር ምንም ዓይነት የትምህርት ቅድመ ሁኔታ የለም:: ይህ መሆኑም ቤተ ክርስቲያንን ብዙ ዋጋ ያስከፈለና እያስከፈለ ያለ መሆኑ ይታወቃል:: "እነሆ ውኃ" በሚል የአገልግሎት ፍልስፍና የሚመራው ኢጃት በመዝሙር ዘርፍ ለሚያገለግሉ የነገ ዘማርያን "ሱባኤ ያሬድ" በሚል ርእስ ለዘማሪነት የሚያበቃ በመምህራን ተጠንቶ በተዘጋጀና በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተመረመረ ሥርዓተ ትምህርት ተከታታይ ሥልጠና አዘጋጅቶአል:: በትምህርቱ እንዲሳተፉ የሚጠበቁት አካላት በሦስት ወገን የተከፈሉ ናቸው 1. የዜማ ጸጋ ያላቸውና ከዚህ በፊት በየትኛውም የቤተ ክርስቲያንዋ የዝማሬ አገልግሎት ላይ የመሳተፍ ዕድል ላላገኙ ታዳጊዎችና ወጣቶች 2. በመዝሙር አገልግሎት ላይ እያገለገሉ ላሉ ዘማርያን 3. የመዝሙር ግጥምና ዜማ ደራሲዎች ፣ የመዝሙር ቀረጻ ስቱድዮ ባለሙያዎች ፣ የዜማ መሣሪያ ተጫዋቾችና የመዝሙር ሳውንድ ሲስተም ኦፕሬተሮች ናቸው:: በምዝገባ ፎርሙ ላይ በሚደረግ ማጣሪያ የመጀመሪያውን ዙር ሠልጣኞችን የመመልመል ሥራ ይካሔዳል:: በመሆኑም የዜማ ተሰጥኦ ያላችሁ ምእመናን በአእላፋት ዝማሬና መሰል አገልግሎቶች ላይ በዝማሬ ለማገልገል የሚያስችለውን ሥልጠና ከመጋቢት 15 ጀምሮ በዚሁ ገፅ በሚለቀቀው በOnline ቅጽ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን:: #እንዳልዘምር_የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
إظهار الكل...
Subae Yared Registration - ጃንደረባው ሚዲያ

ሱባኤ ያሬድ Please enable JavaScript in your browser to complete this form.Please enable JavaScript in your browser to complete this form. የግል መረጃ ስም *ሙሉ ስም እስከ አያትስልክ ቁጥር *የኢሜል አድራሻ *ንስሓ አባት አለዎት? * አዎየለኝም የመኖርያ አድራሻ ሀገርከተማ ክፍለ ከተማወረዳአጥብያ ቤተክርስትያን የሱባኤ ያሬድ ትምህርቶን በተመለከተ የሚሞላ መረጃ 1. በትምህርቱ ወቅት ለመጓጓዣ የሚሆን መኪና አሎት? […]