cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የፍቅር...

የ ፍቅር.... የእውነተኛ ፍቅር ምንነትን ጥሩ ጥሩ ግጥሞችን እንዲሁም አጫጭር ታሪኮች የሚያገኙበት ውድዬ ቻናል Please Join And share @yefikr5 @yefikr5

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
225
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ብለሻል ከዛ በፊት በፊት እምትኖሩበትን እና የተወለድኩት ቤት ለፓስቲ ጠባሽዋ እንድትኖርበት ስጣችኋታል እዛ እንሂድ " አላት። ፅናትም "እሺ ልጄ" ብላ ወደዛ ሄዱ ደመቁን አግኝተው ሰላም ብለዋት ገቡና ፅናት ቤካን የተወለደበትን ክፍል አሳይታው ጊቢውን ሁሉ አስቃኝታው ወጡ። ቤካንም " የአክስቴ ባል ቢኒም ፍፁም ነው በቃ አሁን ወደ መቃብር ስፍራው" አለ ቤካን ፨ፅናትም "እሺ ልጄ በሉ እየመሸ ነው ቶሎ ብለን ወደ መቃብሩ ቦታ እንሂድ" አለች ፅናት። ሁሉም መኪና ውስጥ ገብተው ወደ ሊባኖስ እና ጋሽ በሬሳ መቃብር ቦታ ሄዱ። ቤካን ትንሽዋ ሊባኖስን እጅዋን ይዞ መቃብሩ ፊት ለፊት ቆሞ "ሰላም ሊባኖስ አየሽ ኢቺ የአክስቴ በፀሎት ልጅ ናት" አለና ትንሽዋ ሊባኖስን ስምሽን ንገሪያት አላት። "ሊባኖስ ነው ስሜ እናቴ ባንቺ ስም ነው የጠራችኝ " አለቻት። ቤካንም "እናቴ ታሪኩን ስትነግረኝ መጀመሪያ ላይ ፈርቼሽ ነበር ከዛ ግን መጨሻውን ስሰማ ወደድኩሽ ታሪኩ እውነተኛ መሆኑን ሳቅ ደሞ በአካል ላውቅሽ ፈለኩ " አለና አይኑን ከሊባኖስ መቃብር ነቅሎ ጋሽ በሬሳ ላይ ተክሎ "ጋሼ እርሶም ጥሩ ነበሩ እናቴ ስለ እርሶ ጥበብ እና ስለ ሊባኖስ ከነገረችኝ በኋላ ንግግሪ እና ሀሳቤ እንደ ትልቅ በሳል ልጅ ሆኖል አመሰግናለሁ። እናንተንም ልክ አክስቴ እና እናቴ ልጅ ሆነው ሲንከባከቧቸው እንደነበረው እማማ እየመጣን እናያቹኋለን እናቴ ስለ እማማ ነግራኝ ነበር። እማማን እና አያቶቼን በእየሳምንቱ ቀብራቸው ጋር እየሄድን እንጠይቃቸዋለን ስለ አባቴ እህት ግን ማንም አያቅም " አለ። ፨ሁሉም አለቁሱ ትንሽዋ ሊባኖስ "ቤካን እኔ ግን ይህ ሁሉ በደንብ አልገባኝም" ስትለው። ቤካን "አስረዳሻለው " አላት። በፀሎትም በቃ ኑ ወደቤት እንሂድ" አለችና በፀሎት ቤት ሄዱ እያወሩ እና እየተጫወቱ እራት ደረሰ። የበፀሎት ሰራተኞች እራቱን አቀረቡ እና እየተመገቡ ቤካን "ስለዚህ የትልቅ የጨረቃጨርቅ ባለቤት አጎቴ ፍፁም ነው ስኬታማዋ ሚስቱ አክስቴ እና የትንሽዬዋ ቆንጆ ባል እብዱ ከዛ ደሞ ታታሪው የቢዝነስ ሰው አባቴ ነው" አለ። ፅናትም አዎ ልጄ የእናታችን ህይወት ብቻ ሳይሆን የእኔ እና የእህቴ ህይወትም በፅናት እና በፀሎት የቆመ ነው" አለች።ቤካን "ቆይ ሰአሊው ደሞ ወደ ውጪ ሀገር ሲሄድ ባለፈው አመት የሞተው ሰአሊው ጓደኛክ ነው እሺ ሊላ ደሞ ደራሲው እሱንም አወኩት እና ሌላ ቅድም ሄደን የተወለድኩት ቤት ያገኘናት ደመቁ ስትይ ስሙዋን ሰምቻለው ማማ እሷ ደማ ፓስቲ ስሸጡ ምታግዛቹ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ማማ እና ባባ አብረው ሲተኙ የያዘቻቸው ናት እና የቆነጃጂቶች ህልም በቁርባን ማግባት ነበር ትልቋ ቆንጆ በአክሊል አገባች " አለና ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን የበፀሎትን የሰርግ ፎቶ አየና "ትንሽዋ ቆንጆ ግን ክብሯን ለምትወደው እና ለልጅዋ አባት ስለሰጠች አልቻለችም ምክንያቱም በተክሊል ለመጋባት ክብርን ለሚያገባት ቢሰጥም ስለማይፈቀድ እና ቆነጃጂቶቹ ብለሽ የነገርሽኝ ታሪክ የራሳቹ ነው እማማ ግን ከአባባ ጋር ለምን ከትዳር በፊት" ሲል ትንሽዋ ሊባኖስ "ቤካን እየተበላ አይወራም" ስትለው ሁሉም ከልባቸው ሳቁ ቤካንም "ዝም በሉና ብሉ እናቴ እንዳለችው ሊባኖስ እና ጋሺ ለዘላለም በልባችን ይኖራሉ አለ። ሁሉም በአግራሞት ቤካንን አዩት ቤካንም አታፈጥጡ ትኩረታችሁን ምግቡ ላይ አረጉ አለ። አሁንም በድጋሜ ሳቁ ፨፨፨፨፨ተፈፀመ፨፨፨፨፨፨ ፨፧፨፧፨፧፨፧........... ህይወት ይቀጥላል... እስትፍስ ግን ይቆማል ህያው ሆኖ ለዘላለም በምድር የሚኖር ሰው የለም በልብ ውስጥ ግን ጥሩም መጥፎም ይኖራል።!!!!!!!! . . . 🔥/ተፈፀመ/🔥 ፅናት በዚህ መልኩ ተጠናቋል ። # እንዴት ነው ታሪኩን ወደዳችሁት....? 🔥 Share 🙏 @yefikr5 @yefikr5 @yefikr5
إظهار الكل...
😘ፅናት😘 🔥ክፍል 45 🔥የመጨረሻ ክፍል ✍ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) . . . ፨ቤካን እና ፅናት ተደናግጠው ወደ ሳሎን ሄዱ። በፀሎት ፣ ፍፁም እና ትንሽዬ የምታምር የበፀሎት ልጅ ሳሎን ቁጭ ብለው አገኟቸው። ቤካን "እኔ እና ማማ ጩከት ሰምተን ነበር የመጣነው" ሲል ትንሽዬዋ የበፀሎት ልጅ ሊባኖስ "እናቴ ናት የጫኸችው" አለች። ፍፁምም "አዎ በረንዳ ላይ ውሀ ነበር እሱ አንሸራቶት ነበር ግን እኔ ደግፌ አስቀረዋት" ሲል። ትንሿ ሊባኖስ ከአባትዋ ፍፁም ጋር ሳቁ ቤካንም ሳቀ። ፨ከውጪ የመኪና ክላክስ ተሰማ። ቤካን "ባባ መጣጣ ብሎ ሮጦ ሄደ" ፅናም "ቀስ በል ቤኮ እንዳትወድቅ" አለችው እና ሶፋው ላይ ተቀምጣ "እሺሺ እንዴት ናቹህ" አለቻቸው። በፀሎትም "ደና ነን እህቴ አንቺስ" አለቻት። "እኔን ተይኝ ያው እሁድ ለእኔ ከቤካን ጋር የምዳረቅበት ቀን አደል" አለች። ትንሽዋ ሊባኖስም "ማሚዬ ዛሬ ደብሯታል ልክ እንደ አሻጉሊት ኩርፍ ብላ ተቀምጣ አባቢ ሲያወራት እ ፣አዎ ፣በጣም፣ ልክ ነክ፤ ኧረ እያለች ነው የመጣችው።" አለች። ፍፁም ፅናት እና በፀሎት ሳቁ ፅናት "የእኔ ቅመም" አለቻት። ፨ቤካን ወደ ሳሎን መጣና "ታታታ አባ መጣልኝኝኝ "አለ የያቤፅን እጅ እየጎተተ እያስገባው። "ኦኦኦ የእኔ ቆንጅዬ አማች እስከ ባለዋ እና ልጅዋ መታለች። የእኔ ልዩ እና ቆንጅዬ የልጄ እናትም አለች" አለ። ቤካንም "አሀ ቆይ እኔስ" አለው። ያቤፅ ፈገግ ብሎ "ገና መቼ ተናግሬ ጨረስኩኝ ውዱ ልጄ የእኔ ቀስ ኬኮ ደሞ እንደ እሳት ፈጥኖ መጥቶ ተቀበለኝ" አለ። ሁሉም ሳቁ። ፨አሁንም የመኪና ክላክስ ተሰማ። ቤካን "ውይ አያቴ እና ቅድም አያቴ መጡ" ብሎ እሮጦ ሄደ። ፅናት "ወይ አምላኬ ምን አይነት ቀውስ ልጅ ነው የወለድኩት " ስትል በፀሎት "ኧር የእኔዋ ቃጠሎ ምላሳምስ" አለች። ያቤፅ "በሉ በሉ ከልጆቹ ወረድ መጣው ልብሴን ቀይሬ" ብሎ ሄደ። ፨ቤካን ስማ አቅፍው የያቤፅ አያትም ከኋላ እየተከተሉ ተከታትለው ገቡ። ሁሉም ብድግ ብለው ሰላም አሉዋቸው። ቤካን "ውይ አያቴ ሳሲ ዛሬ ደሞ ቆንጅዬ ሆነሽ ፉንጋዋን እናቴን በልጠሻታል " አላት። ሶስና ክትክት ብላ ስቃ "በምን" አለችው። ቤካንም "በፉንጋነት" አለ። ይህ የተለመደ የሚያዝናና የሁለቱ የሁል ጊዜም ንግግር ነው። ፨ቤካን ወደ ያቤፅ አያት ሄዶ አጠገባቸው ተቀመጠና "ቅድም አያቴ ዛሬ ደሞ አምሮብሀል" አላቸው። እሳቸውም በምን አሉት። ቤካንም "በበበ በ በቃ ተወው" ብሎ ምላሱን ነከሰው ይህ ደሞ ቤካን ሁሌም ከቅድም አያቱ ጋር የሚያደረገው ንግግር ነው። ቤካን እንዲ ነው ልክ እንደ አባቱ ነው ነገሮችን የሚያከናውነው መልኩም አባቱን ቁጭ ነው። ሰራተኛዋ ለፅናት ምሳ እንደደረሰ ምልክት ሰጠቻት። ፅናትም በሉ ተነሱ ምሳችንን እንብላ ምሳ ደርሷል" አለች ሁሉም ተነስተው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ተቀመጡ። ፨ቤካን ልክ ሊበሉ ሲሉ "ቆይ ፀሎት" አለ። ሁሉም ፈገግ ብለው ፀልየው መመገብ ጀመሩ። እየበሉ ያቤፅ መጣና "መልካም ምግብ" ብሎ ሊበላ ሲል። ቤካን "ባባ እንዲባርክህ መጀመሪያ ፀልይ" አለው። ያቤፅም ፈገግ ብሎ ፀልዮ መብላት ጀመረ። ትንሽዋ ሊባኖስ "ስማ ቤካን ያንን ታሪክ ትጨረስልኛለህ" አለችው። ቤካንም "ምግብ ላይ ቁጭ ብለሽ ስለተረት መፅሀፍ አታውሪ በይና ጠይቂኝ " አላት። በፀሎት ሳቀች። "ቤካን ምግብ ክብር ነው አክስቴ አንቺ እና ልጅሽ ዛሬ ገበታ ላይ ጥሩ ፀባይ አላሳያችሁም" አለ። ሁሉም በልተው ጨሱ እና ከጠረጴዛው ተነሱ።እና ሶፋው ላይ ተቀመጡ። ፨ ፅናት እና በፀሎት ሶስና የሰጠቻቸው የየራሳቸው ቤት ውስጥ ነው የሚኖሩት። በፀሎት "ዛሬ እራት እኛ ቤት ነን ከዛ በፊት ለልጆቻችን እና ለእናንተ ከእህቴ ጋር የምናሳያቹህ ነገር አለ።" አለች። ፨ሁሉም "ምንድነው ምንድነው" አሉ። ፅናትም "እሱን ታይውታላቹ አሁን ለመውጣት ያልተዘጋጀነው እኔ ፣ ልጄ እና ባሌ ነን ስለዚህ ተዘጋጅተን እንመጣለን "በሉ ኑ" አለቻቸው ያቤፅ እና ቤካንን ሁለቱም ፅናትን ተከተለዋት ሄዱ እና ለባብሰው ወጡ። ቤካንም "ልክ እንደ እናቴ እና አክስቴ አይነት ቆንጆ አይቼ አላቅም" አለ። ትንሽዋ ሊባኖስም "እህ እኔስ" ስትለው። ቤካን "አንቺም ቆንጆ ነሽ ያው አንቺንም ይጨምራል ልእልቷ" አላት። ፨ሁሉም በትልቅ መኪና ውስጥ ገብተው በሹፊር መጀመሪያ ወደ ጋሽ በሬሳ ቤት ሄዱ። አሁን የጋሽ በሬሳ ቤት ቤት አደለም አሁን ሁሉም ነገር ተቀይሮ የሀይምሮ ህሙማን ትልቅ ሆስፒታል ሆኗል። የሆስፒታሉ ስም ህይወት ነው። ህይወት የሀይምሮ ህሙማን ድርጅት። ይላል። ፅናት በእዚህ ድርጅት ውስጥ በዋናነት ትሰራለች። ፅናት "ሊባቲ ትንሽዋ እና ቤካን ይህ ሀኪም ቤት ማለት ባለፈው የነገርኳቹ ታሪክ ውስጥ የነበረ የጋሽ በሬሳ ቤት ነው። ጥቂቱን ክፍል እኔ ጋሼ ለሰጡኝ መፅሀፋ መመራመሪያ " ነው አለቻቸው። ፨ቤካንም "እንዴ ማማ የነገረሽን ታሪክ እውነተኛ ነው ማለት ነው " አለ። በፀሎትም "አዎ እናትህ የነገችህ እውነተኛ ታሪክ እንጂ ተረት አልነበረም " አለችው። ቤካንም "ስለዚህ ቆነጃጂቶቹ እናንተ ናቹሁ ከቆነጃጅቶቹ አንድዋ እና ማየት ሳትችል ቁርታ ያየችውም አክስቴ ናት ማለት ነው" አለ። ፅናት "አዎ በትክክል" አለች። ቤካንም "ስለዚህ እብዱ ቤሎል የእኔ አባት ነበር ቤሎል ሳይሆን ያቤፅ ነበር።" አለ። ያቤፅም "አዎ ልጄ" አለው። ቤካን "እናቴ ማማ እኔን ስትወልጂ በእዛ ስቃይ አልፈሽ ነበር " አለ። በፀሎት "አዎ ልክ ነክ እናትህ ጠንካራ ሴት ናት" አለችው። ቤካንም "የስሜ ትርጉም ድብቅ ፍቅር ነው ሊባኖስም ሊባኖስ የተባችው ስሟን በአምሬላ ቀይረሽ የነገርሽኝ ናት ከቆንጆዎቹ እህትማማቾች ውስጥ ትልቅዋ ልጇን አምሬላ አለቻት። ነገር ግን አምሬላ ስትሞት ለትንሽዋ ቆንጆ ነበር ልጅሽ ሴት ከሆነች አምሬላ በያት ያለቻት አጋጣሚ ስትወልድ ወንድ ወለደችና ማለት አልቻለችም ስለዚህ ቆንጅዬዋ ታላቅ እህቷ አጋጣሚ ሴት ስለወለደች ስሟን አምሬላ አለቻት አምሬላ ማለት ሊባኖስ ናት" አለ። ፨የቤካን እንዲህ ስለ ታሪኩ ማብራሪያ መስጠቱ ሁሉንም አስገርሟቸዋል። ቤካን አሁንም ማውራቱን አላቆመም "ስለዚህ የእኔ ሴት አያት በወንድ አያቴ ወንድ አያቴም በራሱ እጅ ነው የሞቱት ማለት ነው። እና ዶክተር ስለሺ ማለት የእኛ የቤተሰብ ዶክተር ዶክተር ዳመነ ነው። አክስቴ እና እናቴ የሚኖሩበት ቤትም ከአያቴ ሶስና እና ከጋሼ የተሰጣቸው ነው ማለት ነው" አለ። ሶስናም "አዎ ልጄ" አለችው። ቤካን "ይህ ማለት እኮ ባለ ሱቋ ሴት አንቺ ነሽ ማለት ነው አደል? አያቴ" አላት። ሶስና አዎ ልጄ አለችው። ቤካን አሁንም ግርም እያለው "መናገር የማይችለው ሹፌር አሁን በጣም እሩቅ ቦታ ሄዶ መዳኒት ቀማሚው በሰጡት ቤት እየኖረ ነው የእሱስ ትክክለኛ ስም ማንነው" አላት። እናቱ ፅናትን ፅናትም "ማርቆስ" አለችው ቤካን ወደ ፅናት ሄደና "ማማ በይ አሁን ያቺ መልካም ሴት ብለሽ የነገርሽኝ እና ፈዋሽ እና አዳኝ የሆኑት ሰዎች መቃብር ጋር ውሰጅኝ ምክንያቱም ታሪኩ ማብቂያ ላይ ሁለቱ ቆነጃጂቶች ልጆቻቸውን እና ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ መልካም ሰዎች መቃብር ይሄዱና ለልጆቻው ያሳዩዋቸል
إظهار الكل...
መጨረሻ ላይ "ለምታይዋቸው ሰዎች ትልቅ አስተዋፆ አረገው ካሉበት ችግር የወጡት ለብቻቸው ሳይሆን በዳር በዳሩ ላይ ላሳያየው በሞከርኩት የተያያዙ ጠንካራ እጆች ነው። ስለ እጆቹ ማወቅ ትፈልጋላቹ ብዬ አስባለሁ" ሲል በጭብጨባ አጀብት። ፨ ሰአሊውም ንግግሩን ቀጠለ። በስእሉ ዳር ዳር ላይ በስእሉ ላይ ያሉትን ሴቶች እጅ የያዙ ይመስላል አተኩሮ ላያቸው ማለቴ ነው። እነዚህ እጆች ለእነዚህ እንስቶች ህይወት ትልቅ ቦታ ያላቸው ሰዎች ናቸው ሰማያዊ ቀለም የተተቀምኩት በአሁኑ ሰአት እነዚህ ሰዎች በህይወት ስለሌሉ ነው" አለ። ፨ዳኞች እና ተዳሚዎች አጨበጨቡ የሽልማቱ ሰአት ደረሰ። እና ያለ ምንም ተቋውሞ ሰአሊ ቀመር በሚገርም ውጤት አሸነፈና የብር እና የዋንጫ ሽልማት አገኘ። ሁሉም ተደሰቱ ቀመር " በሉ ላድርሳቹ ወደ ቤት" አላቸው የመውጫ በሩ ላይ ሲደረሱ። ያቤፅም " አያስፈልግም ጓደኛዬ እናመሰግናለን መኪና ይዘናል" አለው። ደራሲው መጥቶ ሁሉንም ሰላም አላቸውና "በጣም ጥሩ አሳዛኝ ታሪክ ነበር ያሳለፈችሁት" አላቸው። ስአሊ ቀመረም "ልክ ነው ህይወት ትፈትናለች ግን በእዚህ መጠን ስትፈትን ከባድ ነው በእነሱ ታሪክ እኔም አልፎልኛል እና ህይወቴን የሚቀይር ገንዘብ አግቻለሁ" አለ። በፀሎትም ለሰአሊው ቀመር " ልክ ብለካል አሁን እኛም ያገኘከውን ገንዘብ በጭራሽ አንጋራክም ያንተ ስኬት ለእኛ በቂ ነው" አለች። ፅናትም "እህቴ ልክ ናት እኛ በህይወት አጋጣሚያችን ባገኘናቸው ሰዎች አሳቦ አምላክ በቂ የሆነ ሀብት ከጤና ጋር ሰጥቶናልና ካንተ ደስታክን ብቻ ነው የምንፈልገው።" አለችው። ፨ደራሲ መሀመድ ሳላዲንም "ጥሩ አስተሳሰብ የያዛቹ ናቹሁ እኔ ኑሮዬን ጠቅልዬ ከእዚህ ሀገር ልወጣ ነው። ባለኝ ጊዜ ሙሉ ታሪካችሁን መስማት ከባድ ነው በእረግጥ በሚገረም መልኩ ሰአሊው ስለ ህይወታቹ ባጭሩ አስረድቶል ግን ደሞ ሙሉን በደንብ ብሰማው ምኞቴ ነው" አላቸው። ያቤፅም "ሁሉን ነገር የፆፍኩበት ማስታወሻ አለኝ እሱን ልሰጥህ እችላለሁ ከዛ ኮፒ አረገክ መውሰድ ትችላለህ አለው። ደራሲውም ስልኩን ለያቤፅ ሰጥቶት ሄደ። እነ ያቤፅም ወደ ቤታቸው ሄዱ። ፨፨፨ከ8 አመት በኋላ ፨፨፨ አንድ የሚያምር ቤት ሳሎን ውስጥ የፅናት በቬሎ ያገባችበት ፎቶ በትልቁ ግድግዳ ላይ ተሰቅሏል። ፅናት መኝታ ቤት አልጋ ላይ ከልጅዋ ቤካኔ ጋር በትራስ እየተደባደች (እየተጫወተች) ነው። በድንገት ጨዋታውን አቁመው አልጋው ላይ በጀረባቸው ተንጋለው እኩል "ኡፍፍፍፍ" አሉ ፅናት "ልጄ" አለችው ቤካንም "አቤት ማማ" አላት። የህይወት ጣእምን በምን ልንለካ እንችላለን " አለችው። ቤካንም "በምንወዳቸው ሰዎች" አላት። "የህይወት መጥፎ ጣሙዋንስ" ስትለው "በሚፈትኑን ሰዎች" አላት። ፅናት ጎበዝ ልጄ ብላ ግንባሩን ሳመችው። በድንገት ጩከት ሰሙና ተደናገጡ። ይቀጥላል..... #ሊጠናቀቅ 1 የመጨረሻ ክፍል ብቻ ይቀረዋል 🙏Share🔥 @yefikr5 @yefikr5 @yefikr5
إظهار الكل...
😘ፅናት😘 #ሊጠናቀቅ 1 ክፍል ብቻ ቀረው 🔥ክፍል 44 ✍ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) . . . ፨ ሀዘን ተፈራርቆባቸዋል። ግን ደሞ ጠንካራ መሆን አለባቸው። ፅናት በአራስነቷ ጊዜ ሁሉም ተረባርበው ነው ያረሷት። ደመቁ ለማንም ሳታወራ ጠፈታ ነበር። ግን ፅናት በወለደች በሳምንቷ ከየት መጣች ሳትባል ነው የመጣችው ። የሊባኖስን እና የጋሽ በሬሳን መሞት ስትሰማ በተለይ ደሞ በደንብ ለምታቃት ሊባኖስ ተንሰቅስቃ ነው ያለቀሰችው። ከዛ በኋላ ከበፀሎት ጋር ተጋግዘው አረስዋት ያቤፅ ከፅናት ጎን ጠፍቶ አያውቅም ሶስና እና የያቤፅ አያት ለፅናት በግ አረጉላት። ሁሉም ማታ ላይ እነ ፅናት ቤት ተሰብስበው ያሳልፉታል ፅናት በእንክብካቤ ታርሳ አራስነቷን ጨረሰች። ፨የፅናትን የክርስትና ጊዜ ደረሰ። ያቤፅ ፣ ፅናት እና በፀሎት በሀዘን ምክንያት የለበሱትን ጥቁር ልብስ አውልቀው ለክርስትናው የሚመጣን ልብስ ሁሉም ለብሰው ክርስትናውን ሞቅ አረጎት ይህ ደስታ ሁሉም በልባቸው የያዙትን ቁስል አላስረሳ ብሏቸዋል። የሶስና እና የያቤፅ አያት የስራ ባልደረቦች በተሰበሰቡበት እነ ያቤፅ ቤት ነበር። ክርስትናው የተከበረው ዝግጅቱ ሊያልቅ ሲል "ቆይ ቆይ አንዴ" አለ ያቤፅ። ሁሉም ዝም ብለው ግራ በተጋባ ስሜት እያዩት ነው ሶስና ያቤፅን ጠቀሰችው ያቤፅም ፈገግ ብሎ ወደ ፅናት ሄደና ተንበረከከ ፅናት ልጅዋን አቅፋ ቆማለች። ያቤፅ ከተንበረከከበት ከወገብ ሰበር ብሎ "ፅኑ ታገቢናለሽ" አላት። ሁሉም አጨበጨቡ ፅናት "አዎ ያቤፆ" አለችው። ድግሱ ላይ ያሉ ሁሉ እድለኛ ነው በጣም ውብ ልጅ ነች የፈጣሪ ያለ በጣም ቆንጅዬ ናት ማለት ጀመረ። ያቤፅ ቀለበቱን ፅናት እጅ ላይ አረገላት። በእዚህ መልኩ ዝግጅቱ አበቃ። ፨ በነጋታው ፅናት ልጅዋን ይዛ ከበፀሎት ጋር ተኝታለች። ደመቁ ቤት እያፀዳች ነው። በር ተንኳኳ ደመቁ ሮጥ ሮጥ ብላ ከፈተች ያቤፅ ነበር። ደመቁ "ጉደኛው ልጅ ደና አደርክ" አለችው። ያቤፅም ፈገግ ብሎ " አቤት ደምዬዬዬዬ እንዴት አደርሽ የእኔ ልእልት እና ቆንጅየዋ በፂ ተነስተዋል ልጄስ" አላት። ደመቁም "አይ ማናቸውም አልተነሱም ግባ" አልችው። ያቤፅ ጫማውን አውልቆ በቀስታ ወደ መኝታ ቤት ገባና። "እንዴት አደራቹ ቆነጃጂቶች እና ውዱ ልጄ " አለ። በፀሎት "አንተ ቀውስ እንዴት አደረክ" አለችው። ፅናትም "ደና አደርክ ያቤፆ" አለችው። "አድሬያለሁ ደና ነኝ ከእናንተ ናፍቆት በስተቀር ልጄም ናፍቆኛል በሉ ዛሬ አንድ ቦታ ይዦቹህ እሄዳለሁ ተዘጋጁ" አለ።" የት " አሉ ሁለቱም እኩል። ያቤፅም አትቸኩሉ ሰርፕራይዝ ነው" አላቸው። ልብስ እስኪቀያይሩ ነገራቸው። ያቤፅ ከቤካን ጋር ሲጫወት ቆየ እና ቤካንንም አልብሰው ደመቁን ተሰናብተው ሄዱ። ፨ አሁን ፅናት ፣ ያቤፅ፣ ቤካን እና በፀሎት አንድ የስእል አዳራሽ ውስጥ ናቸው። ትንሽ ቁጭ ካሉ በኋላ አንድ ወጣት ልጅ መጣ። ወጣቱ ልጅ በፀሎት እና ፅናትን ገና ሲያያቸው ነበር ከሁለቱም አይኑን ሳይነቅል የቆየው። ቆይቶ ያቤፅን ከዛ ፅናትን ከዛ ደሞ በፀሎትን ጨበጣቸው እና ያቤፅን "እነዚህን ነው አደል ያልከኝ አለው። ያቤፅም "አዎ ልክ ነክ ቀመር እነዚህ ናቸው" አለ። ያቤፅ "ፅኑ በፂ ቀመር ሰአሊው ነው ሰአሊ ጓደኛዬ የባለፈውን ውድድር ሌላ ነገር ስሎ አልፎል አሁን ደሞ እናንተን ሊስላቹ ነው ፍቃዳቹ ከሆነ" አለ። ሁሉቱም "መቼ" አሉ። ቀመር ዛሬ አሁኑኑ ምትሄዱበት ከሌለ" አላቸው። ፅናት "የለም" አለች። ሰአሊውም "እንደዛ ከሆነ ወደ መሳያ ክፍል " አለና እየመራቸው ወደ ስእሉ መሳያ ወሰዳቸው። ፨ የስእል መሳያ ክፍል ውስጥ የተለያዩ የሚያማምሩ ስእሎች እና ይህ ነው የማይባሉ ሙንጭርጭር ስእሎች አሉ። ሰአሊው ቀመር የመሳያ ቦታውን አመቻቸና "በሉ አሁን ልብስ እሰጣችኋለሁ አለና ስስ እና ነጭ ልብስ ሰጣቸው። ሁለቱም ልብሱን ሲያዩት በጣም እረዥም ነው ግን ገላ ያሳያል አናረግም ብለው ነበር። ግን ሰአሊው እና ያቤፅ እንደምንም አግባብተው አስለበሷቸው ሰአሊው ፅናት ልጅዋንም ይዛ ቢሳሉ ብሎ አሰበ ፅናት እና በፀሎት ጥሩ ሀሳብ ነው ብለው ተስማሙ። ከዛም ቀኑን በሙሉ ቆይተው ፅናትን ፣ በፀሎትን እና ቤካንን ሳላቸው። ስሏቸው ሲጨርስ እየውላቹ ውድድሩ ከነገ ወዲያ ነው። በዝግጅቱ ላይ መታደም ከፈለጋቹ ብሎ ከለበሰው ሸሚዝ ውስጥ ሶስት ትኬት ሰጣቸው። ልክ በሶስተኛው ቀን ትኬቱ ላይ በተፃፈው መሰረት ወደ አመሻሽ 12:35 ላይ ወደ ስእሉ ኢግዝቢሽን ሄዱ። ሁሉም ሰው በይበልጥ ቀመር የሳለው ስእል ላይ ትኩረቱን አርጓል ያዩት ሰዎችም መልሰው እየመጡ ሲያዩት ነበር። ፨ፅናት በፀሎት እና ያቤፅ ወደ ኤግዚብሽኑ ሲገባ በጣም አምሮባቸው ነበር። ሰው አይኑን እነሱ ጋር ጣለ ከስእሉ ይልቅ በአካል በጣም ያምራሉ እያሉ ሁሉም ይንሿካሿኩ ነበር የጉብኝቱ ጊዜ አልፎ አሁን ዳኖች ውጤት የሚሰጡበት ጊዜ ደርሷል። ይህንን ዝግጅት ለየት ያለ ዝግጅት የሚያረገው ስእሎቹ በጥቂት ታዋቂ ሰዎቸ የሚጎበኝ እና በመጨረሻም በዳኞች ዳኝነት እና በታዋቂ ሰዎች እና ሰአሊዎች የድምፅ ብልጫ የሚካሄድ ነው። አሁን የዳኝነት ሰአቱ ደርሷል እና ፅናት ከበፀሎት እና ያቤፅ ጋር ልጇ ቤካንን አቅፍ ተቀምጣለች። በኋላዋ አንድ እጅ ሲያርፍባት ታወቃት እና ዞር አለች። ፨ ፂሙ ፊቱን ሙልት ያረገው ፀጉሩም እስከ ግንባሩ ጥቅጥቅ ያለ ነው። ሽበት ፂሙ እና ፀጉሩ ላይ ጣል ጣል ብሎበታል። ከተቀመጠበት ተነሰቶ ወደ እነ ፅናት ሄዶ ከፅናት አጠገብ ተቀመጠ። " ሰላም እንዴት ነሽ ደራሲ መሀመድ ሳላዲን እባላለሁ" አላት ፅናት በድምፁ ነበር ያወቀችው። ፅናት " እኔ አላምንም በጣም ነው የማደንቅክ እኮ አንተን ለማግኘት በጣም እመኝ ነበር" አለችው። ደራሲውም " እኔም ስላገኘውሽ ደስ ብሎኛል አንቺ እና እህትሽ በጣም ቆንጆ ውቦች ናቹሁ አላህ ከአይን ያውጣቹ ድርስት ላይ ስፅፍ ብዙ ቆነጃጂት ሴቶች በምናቤ ስዬ ፅፊ አቃለሁ ግን በምናቤ የምስላቸው አንዳቸውም እናንተ ጋር አይደረሱም ስእሉ ላይ የተካተተው እሳት በችግር የተፈተኛቹ እንደሆነ ያስታውቃል የምርም ይደንቃል " አላት። ፨ ፅናት ወደ ያቤፅ ጠጋ ብላ "ስማ ለሰአሊው የነገርከው ነገር አለ እንዴ ስለ እኛ" አለችው ያቤፅ " አዎ ፅኑዬ አንቺ ታመሽ በነበረበት ውቅት ስቃይሽን መስማት ሲያቅተኝ ሁሌም ለእሱ ሄጄ ስለ እናንተ እማቀውን እነግረው ነበር። ጠንካራ ፣ ስኬታማ እና ቆንጆ ሴቶች ስለሆኑ ለመሳል በጣም ጎጉቻለሁ ብሎኝ ነበር ሳላችሁ" አላት። ፅናት "እሺ ጥሩ" ብላ ወደ ደራሲው ዞር አለችና "ይቅርታ አረግልኝ እና ስእሉን ወደድከው አደል " አለችው። "አዎ በትክክል ወድጄዋለሁ የተፃፈ እና የተኖረ ነገር መፃፍ ከባድ ነው ግን ባልፃፈውም ታሪክሽን ብስማው ደስ ይለኛል።" አላት። ፅናትም "እሺ ጥሩ ታሪኩን እነግርሃለሁ " አለችው። ደራሲውም "በቃ አሁን ፕሮግራሙ ተጀመረ አለና ማየት ጀመረ። ፨ፕሮግራሙ ጀምሮ በዳኞቹ ስእሎቹ እና ታሪካቸው መታየት ጀመረ። ሁሉም ታይተው የሰአሊ ቀመር ተራ ደረሰ። ስእሉን ገና ይዞ ሲመጣ ነበር ሁሉም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ያረጉለት። ሰአሊውም ጥሩ አድርጎ ስለ ስእሉ አብራራ በኋላ 🙏Share🔥
إظهار الكل...
እንዳለባት ቢነግሯትም ልሰማ አልቻለችም። ጭራሽ ልጄንም ይዤ ነው ምሄደው አለች። ሊያስቆሙያት አልቻሉም ስለዚህ ያቤፅ ከሹፌሩ ማርቆስ ያቤፅ እና ከበፀሎት ጋር ሄዱ። ፅናት ሊባኖስ መቃብር ጋር ሄዳ እሪ አለች። አለቀሰች። አፈሩን በእጅዋ እየዛቀች እላይዋ ላይ ነሰነሰችው ግን ሊወጣላት አልቻለም። ፅናት ብዙ ደቂቆች ሊባኖስ መቃብር ጋር ሄዳ ስታለቅስ ቆየች። የማርቆስ ስልክ ጠራ አነሳው ደነገጠ "ምንድነው?" አለ ያቤፅ ማርቆስም ስልኩን ላውድ እስፒከር ላይ አረገው። የጋሽ በሬሳ የቤት ሰራተኛ ነበረች። " "ፍቅርተ ነኝ ጋሼ በሬሳ ወድቀዋል አቅምም የላቸውም ኧረ ድረስላቸው ምንም ሰው የለም።" አለች። ሁሉም በፍጥነት ለመድረስ ተደናግጠው ሄዱ በፀሎት እና ያቤፅ ፅናትን ደግፈዋት መኪና ውስጥ ገብተው ማርቆሰሰ በፈጥነት እየነዳ ወደ ጋሽ በሬሳ ከንፈው ደረሱ። ፨ሲደረሱ ጋሽ በሬሳ በእዛ ያማረ እና የተንጣለለ ሳሎን ላይ ተዘረርዋል። ፍቅርተም ውሀ በፎጣ ጭንቅላታው ላይ እያረገችላቸው ነው። ማርቆስ ፈጠን ብሎ ለማንሳት ሞከረ አልከበዱትም ፍራሽ መሳይ ሶፍ ላይ ጋደም አረጋቸው። እያጣጣሩ የሊባኖስ ሚጢጢ ነይ እስቲ ወደዚህ" አሉዋት። ፅናት በፋጥነት ወደ ጋሽ በሬሳ ተጠግታ ቁጢጥ ብላ ተቀመጠች። ጋሽ በሬሳም የፅናትን እጅ እንድትሰጣቸው እጃቸውን ዘረጉ ፅናትም እጇን ሰጠቻቸው። " ልጅ ፅናት የልጅ ሊባኖስ ሚጢጢ" አሉዋት። ፅናት " አቤት ጋሼ" አለቻቸው። እሳቸውም " እኔ ወደ ልጅ ሊባኖስ እየቀረብኩ እንደውም እየሄዱኩኝ ነው እና ልጅ ለሊባኖስ መልክት አለሽ" አሉዋት። ፅናት ደነገጠች እና "ማለት ቆይ ይሄ ምን ማለት ነው እርሶም ጥለውን ሊሄዱ ነው" አለቻቸው። በፀሎትም " ይህ ሊሆን አይችልም" አለች። ፨ ጋሽ በሬሳም "ለምን አይሆንም እንኳን እኔ እድሜን ጠግቤ አንድ ፍሬዋ ልጅ ሊባኖስ እንኳን የህይወትን ሙሉ ክፍል ሳታይ ልጅ የልጅ ልጅ ሳታይ ሞታ የለ። ልጄ እኔ እኮ ህይወት ልትስጥ እምችለውን ሁሉ ሰጣኝ ተቀብዬ ኖሬዋለው መልሳ ነጥቃኝ ነው እንጂ መልሳም ሰጥታኝ ግን ሳላጣጥመው" አሉ እና ዝም አሉ። ሊላኛውን እጃቸውን ለበፀሎት እየዘረጉ። በፀሎትም " አይዞት አይሞቱም" ብላ እጃቸውን ያዘቻቸው። ጋሽ በሬሳም "ልጄ ሰው በቁሙ ሲሞት ነው መጥፎ" አሉ። ማውራት አቅቷቸው ተዳከሙ። ፅናት እና በፀሎት የሊባኖስን የመጨረሻ ቀን የመጨረሻ ሰአት አስታወሱ። ጋሽ በሬሳም "ፅናት ስሚኝ ለልደትሽ የሰጠውሽን መፅሀፍ በደብ አንብቢው የመኝታ ቤቴ መሳቢያ አለ እሱ ውስጥ ሙሉ የንብረቴ ወራሽ አረጊሻለው ቤቴን አፈረሰሽ ለሰው የሚሆን ነገር ለሰው የሚጠቅም ነገር ስሪበት አስፈላጊ ከሆነ እዚህ ያሉትን አስክሬኖች ማርቆስ መላ ይላቸዋል" አሉ። ለልጄ ማርቆስም ከከተማ ውጪ ያለውን ቤት አውርሼዋለሁ ማውራት ደከማቸውና አ አ አአአአ ብለው አይናቸውን እንደከደኑ ቀሩ። ፨ፅናት "አይሆንምምም" ብላ ጮከች። "እርሶም ጨከኑ" አለች። መልስ የለም ሁሉም አለቀሱ አዘኑ መጮህ እና ማዘናቸው ግን የሚወዷቸውን ጋሽ በሬሳ እና የህይወት አስተማሪያቸውን ሊባኖስን አልመለሰላቸውም። አለቀሱ ተጮጮሁ የጋሽ በሬን ቀብርም ፈፀሙት።የተቀበሩት ከሊባኖስ ጎን ነበር። ይቀጥላል 🙏Share🔥 @yefikr5 @yefikr5 @yefikr5 @yefikr5
إظهار الكل...
😘ፅናት😘 🔥ክፍል 43 ✍ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ ( የሸዋ ልጅ) . . . ፨የሊባኖስ መሞት ሁሉንም የሚያቋትን ሰዎች ጎድቶ አቁስሎ ውስጥን ሰርስሮ አለፈ። ሰልስት ከዛ አርባውም አለፈ። የሊባኖስን አርባ ያሳለፉት አባ በሬሳ ባሉዋቸው ሰራተኞች ምግብ በማሰራት የተቸገሩ ወገኖችን መግበው ስሟን አስጠሩ። ፅናት አሁንም ስቃይ ላይ ናት አሁንም "ሊቦዬ ጥሪኝ አንቺ ጋር ልምጣ" የሚለውን ቃል እንደደጋገመች ነው። በፀሎትም ስራዋን እረግፍ አረጋ ትታ እህቷን ማስተማር ላይ ናት ያቤፅም ትምህርቱን መማር ስላልቻለ አቋርጦታል። ሶስና እና የያቤፅ አያት ግን ድርጅታቸው ውስጥ በብቃት እየሰሩ ነው በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ነበር የያቤፅ አባት ያበላሸውን ስራ መስመር ያስያዙት። ፨ጊዜው ነጉዶ ነጉዶ ፅናት የ 9 ወር ከ 15 ቀን እርጉዝ ሆነች። በእርግዝናዋ ወቅት ከሁሉም በላይ ሆዶ ከገፋ ጀምሮ እና የመጨረሻዎቹ ቀኖች ላይ ፅናት እንደልብዋ ተፈራግጣ ጮሃ ህመሙዋን ማስተናገዱን አልቻለችም ነበር። ምክንያቱም ሆዷ በጣም አስቸግሯት ስለነበር። ልጅዋ ሆዶ ውስጥ መንቀሳቀስ ሲጀምር ፅናት ለልጅዋ ስትል መጠንከር ጀመረች። አሁን የፅናት ጩከት ከሊላው ጊዜ ይለያል በጣም ጨምሯል። ዶክተር ዳመነ አንድ ነገር ተናግሯል "ብዙውን ጊዜ ልክ እንደፅናት አይነት በሽታ የያዛቸው ሰዎች በሆዳቸው ፅንስ ከያዙ ልክ በሚወልዱበት ወቅት ያ ስቃያቸው በሽታውን የማጥፍት እና ዳግመኛ እንዳይመለስ የማድረግ እድል አለው ነገር ግን እርጉዝ መሆናቸውን ዶክተር ሲያውቅ የሚላቸው ተቃራኒ ነው። እርግዝናው አስጊ እንዲሆን ይንን የምናረገው ልክ ሆዳቸው መግፍት ሲጀምር ከጭንቅላት በሽታቸው በተጨማሪ ሆዳቸው ውስጥ ስላለው ልጃቸው እንዲጨነቁ ነው። ለበሽተኛው መጨነቅ እና እራስን መሳቱ ጥሩ ነው የበሽታው መድሀኒት በጣም መጨነቅ ነው ለበሽተኛው አካል ግን ይበልጥ እንዲጨነቁ እና መውደቁ ጥሩ እንዳልሆነ እንነግረዋለን የመጨረሻዎቹ የስቃይ ቀናት ፅናትን ወደ ጤናዋ ይመሯታል ፨ ለፅናት እርጉዝ እንደሆነች ነግሬያት ከዛ እንድታስወረድው ነገርኳት እሺ አላለችም እኔም አልተጫንኳትም ምን አለችኝ መሰላችሁ ይህንን ነገር ስነግራት የታካሚ መረጃ ለማንም መስጠት አይቻለም እኔም የዶክትሬት ተማሪ ነኝ ለማንም ብትናገር እከስካሁ አለችኝ የህክምና ኢቲክስ ባይፈቅድም ግን ሰው መሆኔ ስለሚያስገድደኝ አስፈላጊ ቢሆን ለእናንተ ማረገዟን እና ስለ በሽታዋ እነግራቹሁ ነበር። ግን ህመሙዋን ብቻዋን ብትሰቃየው ለመዳንዋ ጥሩ ነው ብዬ ነው።" ነበር ያለው። ጋሽ በሬሳም "እኔም ለፅናት ስለበሽታው ባህሪ ልክ እንዳንተ አረጌ ነግሬያታለሁ። በነገራችን ላይ እንደ ፅናት ያሉ ታማሚ ሴቶች በሽታው ሲጀምራቸው እንዲያረግዙ እንገፋፋቸዋለን በሽታው ሴት ልጅን ብቻ ነው የሚያጠቃው በምጥ ተገፈቶ ከሆነግን የሚወጣው ዳግመኛ በሽታው አያገረሽም " ብለው ነበር። ይህንን ያሉት (የተነጋገሩት ለሊባኖስ አርባ እለት ያቤፅ ፅናትን ቤት እየጠበቀ ባለበት ሰአት በፀሎት እና ጋሽ በሬሳ ዶክተር ዳመነን ስለ ፅናት ሊያወሩት ሄደው በነበረበት ሰአት ነበር። ፨ጊዜው ገፍቷል ሁሉም የሚጠብቁት የፅናትን የምጥ ቀን ነው። ዛሬ ያ ቀን ደርሶል። ግን ሳሎን ቤት ያሉ እነ በፀሎት ፣ያቤፅ፣ እና ዶክተር ዳመነ አላስተዋሉም እንኳንስ እነሱ ፅናትም ያወቀችው የሚሰማት ስሜት ሆድዋ ላይ ስቃይዩ ስለበረታ ነው። የፅናት ጩኸት መብዛት ሁሉም ግራ አጋብቷቸዋል። ፅናት ሆድዋን ዝቅ ዝቅ ሲያረጋት ሲሰማት "እህቴ ልጄ ልጄ መጣ" አለች። አላመኑዋትም የመውጫ ምክንያት ነበር የመሰላቸው። ከብዙ ሰአት ቆይታ በኋላ ልክ ከቀኑ 6:39 ላይ የፅናት ድምፅ ጠፈቶ የህፃን ልጅ ድምፅ መሰማት ጀመረ። ፨ ያቤፅ "የፈጣሪ ያለ ምንድንነው የምሰማው ድምፅ ዶክተር" አለ። ዶክተር ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ "ቶሎ በሉ በፈጥነት በሩን ክፈቱት" አለ። በፀሎት በፍጥነት ቁልፉን ከ ኪስዋ አውጥታ ከፈተችውና በሩን ብርግድ አረጋ ገባች። ፅናት የምትለብስውን አልጋ ልብስ ደልድላ ልጅዋን እዛ ላይ አሳርፈዋለች። እና በጣም ተዝለፈልፋለች። ዶክተር ዳመነም በሉ በፈጥነት ለብ ያለ ውሀ ፎጣ እና መቀስ አምጡልኝ መቀሱ ባለፈው ያመጣውት ይሁን አለ። ያላቸውን ሁሉ ያቤፅ እና በፀሎት ተጋግዘው እየተጣደፈ አመጡለት። ፨ ዶክተሩም የምግብ መገናኛው እትብቱን ቆርጦ በፎጣ እና ለብ ባለ ውሀ ፅናትን እና ህፃኑን አፀዳዳቸው። ያቤፅ ተደሰተ "ፅኑ ልጅ ወለድሽልኝ ፅኑ ልጅ ሰጠሽኝ" አለ። በፀሎትም "እኔም አክስት ሆኛለሁ" ብላ ፅናትን ሳመቻት። ዶክተር ዳመነም "የወንድ ልጅ እናት ሆነሻል" አላት። ፅናትም "አዎ ልክ ናቹሁ ልጄ ሴት ከሆነች ሊባኖስ ልላት ነበር ግን ደሞ ዶክተሩ ገና እርጉዝ ነሽ ሲለኝ ልጄን ወንድ ከሆነ ቤካን ልለው ነው ያሰብኩት።" አለች። በፀሎትም " ትርጉም አለው ማለቴ ከእራስሽ ጋር የሚገናኝ?" ስትላት። ፅናት "አዎ እህቴ ቤካን ማለት ድብቅ ፍቅር ማለት ነው። ያው በእኔ እና በያቤፅ ድብቅ ፍቅር ውስጥ የተፀነሰ ተፀንሶም የተወለደ ልጅ ነው። ለእዚህ ነው እህቴ" አለቻት። በፀሎት ተገርማ " ከድሮም ብልህ ልጅ ነሽ" አለቻት። ፨ ያቤፅም ፅኑዬ " ታገቢኛለሽ አደል" አላት። በፀሎትም " እንዴ እና እንዴት አታገባክም የልጅዋ አባት አደለክ እንዴ" አለችው። ፅናትም " ልክ ነው አይደል ልጄ እእእ" አለች። ልጅዋን በስስት እያየችው። ዶክተር ዳመነ በመገረም ውስጥ ሆኖ በህይወቴ አንዴም ልክ እንደ እናንተ አይነት ሰው አይቼ አላቅም" አለ። ያቤፅም " ልክ ነው ፅኑዬ እስቲ ልጄን ልቀፈው" አለና ወደ ፅናት ተጠጋ። ፅናትም ቀስ አረጋ ሰጠችው። ያቤፅ ልጁን ሲያቅፈው ልብ ውስጥ ሀይል እና ፍቅር ተደምሮ ተሰማው ልጁን እያየው "ቤካን የእኔ ልጅ እንኳን ደህና መጣህ ተመልከት አባትህ እጅ ውስጥ ነህ ሁሌም ቢሆን ባገኘውት አጋጣሚ አንተን ከማቀፍ የሚያግደኝ ነገር አይኖርም በትልቅ ችግር ውስጥ ብሆንም እኔ ያጣሁትን የአባት ፍቅር አላሳጣህም" አለና ከአይኑ ያቀረረው እንባ እረግፍ የህፅኑ ፊት ላይ አረፈ። ፨ህፅኑ ቤካን አለቀሰ ያቤፅም "ውይይ አታልቅስ አታልቅስ አሁኑኑ ለእናትህ እሰጥሀለው" ብሎ ሰጣት። ፅናት እያለቀሰች "ሊቦዬ ጥላን ሄደች አደል" አለች። በፀሎትም "አዎ እህቴ ግን ሊቦቲዬ እንድናዝን አትፈልግም" አለቻት። ያቤፅም "ልክ ነው ህይወትን እምንኖራት አምላክ በቃቹ እስኪለን ድረሰ ነው" አለ። ፨ፅናት ዛሬ ሁለት ነገርን በድል ተወታለች። ሁሉም ሰው በሰአታት ልዩነት ስለ ፅናት ደህንነት ለማወቅ ሲመጡ ነው የምስራቹን ያወቁት የያቤፅ ቤተሰቦች ፣ ጋሽ በሬሳ እና ማርቆስ ፅናት ጋሽ በሬሳን እና ማርቆስን ስታያቸው ሊባኖስን ይበልጥ አስታውሳ እሪሪ አለች። ያቤፅ አቅፎ አፅናናት። ጩኸት እና ጭንቀት ቤት ውስጥ የለም። ያለው የሚያለቅስ የህፃን ልጅ ነው። ምንም አይነት የሚሰቃይ የሚጫህ ሰው ቤት ውስጥ የለም። ፅናት በወለደች በነጋታው ሊባኖስ መቃብር ጋር ካልወሰዳችሁኝ አለች። በፀሎት ፣ ያቤፅ እና ሊሎች እንደማይሆን እና መጠንከር
إظهار الكل...
፨ በፀሎትም " እህቴ ልጅሽ እኮ ገና ነብስ አልዘራም እባክሽን ጠንካራ ሁኒ" አለቻት። አሁን ሁሉም ፀጥ ብለው ልክ እንደተለመደው ፅናት እየጮከች ሁሉም በትካዜ እና በጭንቀት ውስጥ ተዋጡ። ሊባኖሰም በጣር ውስጥ ናት። በእዚህ መልኩ ሰአቱ ነጉዶ ማታው ለሊት ሆኖል ፅናትም ጩከትዋ አዳክሟት በሽታው እረፍት ሰጥቷቶት ተረጋግታ ተልፈሳለች። ፨በፀሎት እና ያቤፅ ፅናት ያለችበትን ክፍልን ከፈተው ፅናትን ደግፈው ትልቁ ሶፋ ላይ የተኛችው እና ወደ ሞት ለመሄድ እየታገለች ወዳለችው ሊባኖስ ይዘዋት ሄዱ። ሊባኖስ ፅናትን ስታያት "በተዳከመ ድምፅ የኔ ሚጢጢ አምሮብሻል በጣም ተዳክሜ የመጨረሻ እስትንፍሴን ልተነፈሳት ስል መጣሽ። ያልኩሽን አትረሺ እሺ የኔ ቆንጆ" አለቻት። ፅናት ሊባኖስ ሆድ ላይ ተደግፋ "ሊቦዬ እንደዛ አትበይ እባክሽ ጠንከር በይ ታስፈልጊናለሽ ስቃይ ላይ ነኝ ስቃይ ላይ ስሆን ሞቴን ናፍቄ በሽታዬ ፍታ ሲሰጠኝ ደሞ ህይወት ታጎጎኛለች ምክንያቱም ህይወቴ ውስጥ እናንተ ስላላቹ ነው ሊባ ብርታት ሁኒኝ።" እያለች በሀይል ማልቀስ ጀመረች። ፨ የያቤፅ አያት ልጄ ሊባኖስ አሁን ሞታለች አሉዋት። ልብዋን በስለት ሳይሆን ስለት በሊለው ነገር ተጭነው የወጉዋት ያክል ተሰማት። ቀና ብላ አየቻት የሊባኖስ አይን ፈጦ አፈዋም በስሱ ተከፈቷል። የሳሎኑ በር ተከፈተ ሁሉም ድንጋጤ ውስጥ ናቸው። ጋሽ በሬሳ ነበሩ ሊባኖስን አዩዋት። "ልጄ ልጅ ሊባኖስ ደና ሁኒ" ብለው በዝግታ ተጠግተው አይኑዋን እና አፉዋን ገጠሙላት። የጋሽ በሬሳ አይን በእንባ ተሞልቶ ፈሰሰ ሁሉም ድንዛዜ ውስጥ ናቸው። ፅናት "አይሆንም አይሆንም" ብላ ማልቀስ ስትጀምር። ፍፁም ክፍሏ አስገብቶ ቆለፈባት። ሁሉም አሁንም ድረስ በፍፁም አላመኑም። ያቤፅ "ቆይ ቆይ ተረጋጉ እሷ አልተችም ውሸት ነው ሊባኖስዋ እኳ እማትሞት ዘላለማዊ ሰው ናት" አለ። ጋሽ በሬም "ልጄ ሊባኖስ ሞታለች በእዚህ አለም ዘላለማዊ አምላክ ብቻ ነው" ሲሉ በፀሎት መፈዘዝዋን አቁማ ወደ ሊባኖስ ተጠግታ " እባክሽን አታድርጊው ሊቦቲዬ ጥለሽን አትሂጂ የኔ እናት እባክሽን ታስፈልጊናለሽ" እያለች ፣ እሪ አለች። ሁሉም እያለቀሱ ለሊቱን አለፉት። ፨ ጋሽ በሬሳም የሊባኖስን አስክሬን ውሀ አፈልተው ከፍፁም ከዶክተር እና ከ ያቤፅ አያት ጋር ወደ ኩሽና ወስደው አጥበው ገንዘው አቆዩዋት። ፅናት ለሊቱን ሙሉ ከህመሙ ጋር የሊባኖስ ሞት አሳብዷት እየደጋገመች የሊባኖስን ስም እየጠራች ስታለቅስ ቆየች። ሊነጋጋ ሲል የሊባኖስን አስክሬን ለመቅበር ጋሽ በሬሳ ቦታውን አመቻችተው የእሬሳ ሳጥንም ከማርቆስ እና ከዶክተር ዶመነ ጋር ገዝተው መጡ። ፨ ከፅናት በስተቀር ሁሉም ሊባኖስን ለመቅበር እያለቀሱ እና እያዘኑ ወደ ቀብሩ ታ ለመሄድ ተዘጋጁ። ማርቆስ ፣ያቤፅ፣ ፍፁም እና ዶክተር ዳመነ ለአራት የሊባኖስን አስክሬን ተሸከሙ እና ከመኪናው ኋላ ያለው ሰፊ ቦታ ላይ እሬሳውን አጋደሙት። መኪና ውስጥ ገብተው የያቤፅ አያት መንዳት ጀመሩ። በፀሎት ሶስና ጋር ተደግፋ እያለቀሰች እና ሁሉም እየተላቀሱ ቀብር ቦታው ጋር ደረሰው ሊባኖስ የምትቀበርበትን ጉድጎድ ለቀብር ቆፋሪ አስቀብርው ያቤፅ ፣ፍፁም፣ ማርቆስ እና ዶክተር ዳመነ ተጋግዘው ሊባኖስን የተቆፈረው ጉድጎድ ውስጥ አስገቡዋት። ከመሬት ተቆፍሮ የወጣውን አፈር መልሰው ሊባኖስ አስክሬን ላይ ከመሩት። በፀሎት ልክ እንደ እብድ አደረጋት። "አፈሩን አንሱት እሷ አልሞተችም ሊቦቲዬ እባክሽን እንዲህ አታድርጊን " እያለች በለቅሶ እና በጩኸትዋ ልሳንዋ እስኪዘጋ ጮኸችላት። አይኑዋ ደም እስኪለብስ አለቀሰችላት ፤ ጉልበትዋ እስኪላላጥ ተንፈራግጣ ታድናት ይመስል በእንብርክኳ ሆና መሬቱን ደበደበችው። ሌሎችም ለሊባኖስ አብዝተው አለቀሱ የጋሽ በሬሳ አይን ቀይ ስጋ መስሏል ያቤፅም ጨው በመሰለ ፊቱ ላይ ለቅሶ ተጨምሮ ፊቱ ሀዘን ወሮታል ፅናትም እዛው ቤትዋ ሆና አትውስዱዋት እንዳቀብሯት እያለች ነው። ፨መቀበሯን መች አየችና። ማርቆስ ድምፅ አልባ ለቅሶውን አለቀሰ እንኳንስ በደብ የሚያቋት እነ ፅናት ፣ በፀሎት ፣ ጋሽ በሬሳ እና ማርቆስ ይቅርና በደብ እማያውቋት የያቤፅ ቤተሰቦች እና ዶክተር ዶመነ እሪሪሪ ብለው ነው ያለቀሱላት ሁሉም ቢያለቅሱም ምንም ያህል ቢያዝኑ እና ቢጮሁ ሊባኖስን ታሪክ ከመሆን አላዳኑዋትም ሊባኖስ አሁን ታሪክ ሆና አልፍለች ፤ ሊባኖስ አሁን ህይወት ካለው ነገር ወደ በድንነት ተቀይራለች ፤ ሊባኖስ አሁን አካልዋ ሳይሆን ነብሷ ከምትወልዳቸው እና ከሚወዶት ልብ ውስጥ ትዝታዋ ለዘላለም ይኖራል። የያቤፅ ሊባኖስዋ ፤የበፀሎት ሊቦቲዬ ፤ የፅናት ሊቦ፣ የጋሽ በሬሳ ልጅ ሊባኖስ ፤ የማርቆስ አጋዥ አሁን የለችም ሞታለች ፣ አዎ በለቅሶ አሰና በጩከት በሀዘን እና በምልጃ ላትመለስ ሄዳለች። ይቀጥላል.... 🔥Share 🙏 @yefikr5 @yefikr5 @yefikr5 @yefikr5 @yefikr5 ::::::::**/////:::::*/////:::::
إظهار الكل...
፨ በፀሎትም "አመሰግናለሁ ሊላ ምን ማለት እንደምችል አላቅም" ብላ የያቤፅን አያትን አቅፍቸው "አመሰግናለሁ ከምንም በላይ ልጄ ስላሉኝ እና ስላረጉልኝ ተጨማሪ ነገሮች።" አለቻቸው። የያቤፅ አያትም " ሁሌም አንቺም አህትሽም እንዲሁም የህይወታቹ መልካም ሴት የሆነችው ሊባኖስም አባቴ አባዬ ብቻ የፈለጋችሁትን በሉኝ እኔ በጣም ደስስስስ ይለኛል በሉ ኑ እቀፉኝ" አሉዋቸው። ከዛ ያቤፅ ፣ ሊባኖስ ፣ ሶስና፣ እና ደሞ ፅናት የያቤፅ አያትን አፏቸው ብዙ ደቂቃዎች ተቆጠሩ። ፨ አሁን ደሞ ከፅናት ቤት ምኑም በማይለይ መልኩ የተሰራ ቤት ለፅናት አበረክተውላት። መኪናም በከለር የሚለኝ ያማረ መኪና ሰጡዋት። የዛሬው ቀን ለፅናት እና ለበፀሎት አዲስ ሊላ ነገር ተጨምሮ ደስስተኛ ሆነዋል። ፨ ፨ ፨ ከሶስት ወር በኋላ ፨ ፨ ፨ "ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል ህይወት እንዲህ ነው ይህ አስቀያሚ ህይወት ፊቱን አዙሮ በየት አረጎ እና ዞሮ መጣ። አሁን ይህንን በምን መንገድ ነው እምንወጣው?" አለች በፀሎት ያቤፅን እና ፍፁምን። ፍፁም መኪናውን በሀይል እየነዳ ነው የሶስቱም ፊት ተደሳቅሏል። ይቀጥላል.......... 😘ፅናት😘 🔥ክፍል 42 ✍ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) . . . ፨ ያቤፅ እና ፍፁም ለበፀሎት መልስ አልሰጧትም። አሁን ላይ ሶስቱም ከጋሽ በሬሳ የሚጨስ ጭሳጭስ መዳኒት ለፅናት እያመጡላት ነው። ያቤፅ እፅ ያደነዘዘው ሰው መስሏል። ድምፁን ለስለስ አረጎ "አምላኬ እባክህን ፅኑን እና ሊባኖሷን ጠብቅልኝ" እያለ ደጋግሞ መፀለይ ጀመረ። ፍፁምም "ይድናሉ ደና ይሆናሉ ብቻ እኛ እንፀልይ" አለ። ያቤፅ እነ ፅናት ቤት ደርሶ ከመኪናው ወርዶ የመግቢያ በሩ ላይ እስኪደረስም ፀሎቱን አላቆመም። በፀሎት በሩን አንኳኳችው ሶስና "መጣውውው ብላ በሩን ከፈተችው። ያቤፅ እና በፀሎት እኩል ነበር። "ፅኑ ደና ናት ፅናቴ እንዴት ናት" ያሉት። ሶስናም ባዘነ ፊት "ለውጥ የላትም ያው ናት" አለቻቸው። በፀሎትም "እሺ ሊቦቲስ መታለች" አለቻት። ሶስና የሊባኖስን አለመምጣት ፊቷን በመነቅነቅ ገለፀችላት። ፨ፍፁም በፀሎትን ለማፅናናት ያክል ትከሻዋን መታ መታ አረጎ አቅፎ ቤት ገብ። ገና የቤቱ በር ሲከፈት ነበር የፅናትን ጩከት መስማት የጀመሩት "ኡኡኡኡኡኡ ወይኔ ኧረ ግደሉኝ የሚወደኝ የለም ለምን አትገሉኝም ልጄን አትረፍቹ እኔን ግደሉኝ" አለች። ይህ ልጄን አትረፍቹ እኔን ግደሉኝ የሚለው ቃል ሁሉም ግራ ቢገባቸውም "የበሽታው ፀባይ ነው"ብለው ስለሚያስቡ በዝምታ አልፈውታል። ፅናት የ4 ወር ከ 15 ቀን እርጉዝ መሆኑዋን ማንም አያውቅም ምግብም የሚሰጣት በመኝታ ቤታቸው በር ስር ቀዳዳ ተሰርቶ ነው። በሽታው የምግብ ፈላጎት ይጨምራል ለእዛም ነው ምግብ ሲሰጡዋት ልክ እረዥም አመት ሳይመገብ የቆየ ሰው ይመስል በፈጥነት እምትበላው። የሆነ ሰአት አላት ጮሃ ተዝለፈልፋ ፀጥ እምትልበት እና በሽታው እረፈት የሚሰጣት ሰአት በእዛ ሰአት ነበር ሽንት ቤት እንድትጠቀም ደግፈው የሚወስዶት ለሊት ላይ ሁሌም ሽንት ቤት ይዘዋት ይሄዳሉ። ቀን ቀን ሽንቷን በላይዋ ላይ አንዳንዴ ለቃው ያገኙዋታል በእዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ለአንድ ወር ብቻ ነበር ሊባኖስ እንደነብሷ የምትወዳትን ፅናት ያስታመመቻት። ፨ ከዛ ግን አቅሟም እየተዳከመ ስለሆነ እየመጣች ድምፅዋን ስምታት ትሄዳለች። በር ተንኳኳ በፀሎትም "ውይ ሊቦቲዬ መጣች ቆይ ልክፈትላት" ብላ ሄደች። እንዳለችውም ሊባኖስ ነበረች ከሹፌሩዋ ማርቆስ ጋር የመጣችው። ማርቆስ ሊባኖስን አጥብቆ ደግፏታል ዛሬ ጠንካራዋ ሊባኖስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ገርጥታለች እናም ደሞ ተዳክማለች። በፀሎት "ነይ ነይ ሊቦቲዬ አይዞሽ" ብላ ደጎፋ ከማርቆስ ጋር ወደ ቤት አስገብዋት። ፨ያቤፅ ሊባኖስን ሲያያት በፍጥነት ሄዶ ተጠምጥሞባት "ሊባኖሷ እባክሽን አንቺ እንኳን ጠንክሪ እባክሽን ልለምንሽ" አላት።ሊባኖስም በሲቃ በታጀበ ድምፅ " አሁን አልችልም ዛሬ ልክ እንደ ትናት ወይ እንደ ትናት ወዲያ ተመልሼ የመምጣት ተስፋን ሳልይዝ ነው የመጣሁት ዛሬ ማታ ሁላችሁንም ለማየት ብቻ ሳይሆን ለመሰናበትም ነው የመጣሁት እስከ ለሊት እንኳን ፈጣሪ አቆይቶኝ የእኔ ሚጢጢን እንድሰናበታት ፀልዩልኝ" አለች። በፀሎት ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች " እባክሽን እንዲህ አትበይ እባክሽን ሊቦቲዬ አንቺ ጠንካራ ሰው ነሽ ምንም አትሆኒም ገና ብዙ ነገሮችን አብረን እናሳልፋለን" አለችና በቀስታ ደግፋ ሶፋው ላይ እንድትቀመጥ ከማርቆስ ጋር እየረዳቻት እና በቀስታ አስቀመጦት ሊባኖስ በተዳከመ ስሜት ውስጥ ሆና በቀስታ ነው የተቀመጠችው። ሊባኖስ የግድግዳ ሰአቱን እያየች ነው። ፨ከምሽቱ 1 ሰአት ይላል። እንደምንም ብላ በማርቆስ እረዳታ ወደ መኝታ ቤቱ በር ተጠግታ "የእኔ ሚጢጢ፤ የኔ ቆንጆ ፤ እባክሽን ጠንካራ ሁኚ ደና መሆን አለብሽ እንዲህ ስትሆኒ ማየት ከህመሜ በላይ ነው።" እያለች ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። በሩ ተንኳኳ ያቤፅ ተነሳና የውጩን በር ከፈተው። ዶክተር ዳመነ እና የያቤፅ አያት ነበሩ። ያቤፅ ስላም ብሏቸው ወደ ውስጥ ገቡ። "ሰላም ለእዚህ ቤት" እያሉ የያቤፅ አባትም ዶክተር ዳመነም እንደምን አመሻቹ ብለው ገቡ። ፅናት እየጫከች ነው ሊቦ እባክሽን ከባድ ነው ሊቦ መሞት እፍልጋለሁ" ትላለች። ሊባኖስም ተይ ለእህትሽ ስትይ መኖር አለብሽ ፤ የኔ ሚጢጢ ለያቤፅ ስትይ መኖር አለብሽ ለሁላችንም ስትይ እኔም እንድትኖሪ እፈልጋለሁ" አለቻት። ፨ ዶክተር ዳመነም ጮክ ብሎ "መቼስ ከንግግሯ ፅናት እረጉዝ መሆኑዋን ተረድታቹዋል አሁን ሆዱዋ የሚገፍበት ጊዜ ነው" አለ። ሁሉም ደነገጡ "ምን እያለክ ነው ዶክተር?" አለች በፀሎት ያቤፅም ድምፁን ቀዝቀዝ አረጎ መዳፎቹን እያሻሸ "ልጁ የእኔ ነው" አለ። ሶስና "አልገባኝም ቆይ ይህ እንዴት ነው ሊሆን የቻለው" አለች። ያቤፅም "ለበፂ ህክምና ጊዜ ነው" አለ። ሁሉም ደነገጡ በፀሎት "ወይኔ እህቴ ለካ ልብሷን ስቀይርላት ሆድዋ ትንሽ የጨመረው እና ሶስት ወር ሙሉ የወር አበባዋ ያልመጣው ልጄን አድኑት የምትለው እረጉዝ ስለሆነች ነው።" አለች። ፨ሊባኖስ " የኔ ሚጢጢ እናት ልትሆኒ ነው አደል ልጅሽን ማየት አልችልም አንቺን እንደምትመስል አልጠራጠረም ሴት ከሆነች ወንድ ከሆነ አባቱን በእዚህ እድሜሽ ብዙ ተሰቃየሽ አደል የእኔ ሚጢጢ ልጅሽ ሴት ከሆነች በእኔ ስም ጥሪያት" አለቻት። በሚገረም ሁኔታ ፅናት መጮህ እና ማማረርዋን ትታ በፀጥታ ሊባኖስን ያዳመጠቻት ነው። ፅናት ልክ ሊባኖስ አውርታ ስጨረሽ "ሊቦዬ የእኔ እናት አንቺ እኮ ለሁላችንም እናት ነሽ" ብላ መልሳ በጩከት " ትወጅናለሽ?" አለቻት። ሊቦኖስም "አዎ የእኔ ሚጢጢ በጣም እወደዋለሁ" አለቻት። ፅናትም "እምልሽን ነገር ሁሉ ታረጊልናሽ" አለቻት። ሊባኖስ "አቅሜ ከፈቀደ አዎ" አለቻት። ፅናትም "ሊቦዬ" አለቻት። ሊባኖስም " ወዬ የኔ ሚጢጢ ፤ ወዬ የእኔ ቆንጆ" ስትላት። ፅናት" ሊቦዬ አልቻልኩም እባክሽ ልጄን አትርፈሽ እኔን ግደይኝ" አለቻት። ሊባኖስ ስቅስቅ ብላ እያለቀስች። "እባክሽ ጠንካራ ሁኒ የኔ ሚጢጢ ሁሉም ሰው መሞቱ አይቀረም ከትንሽ ሰአታት በኋላ እኔም እሟታለሁ ግን ሁሉም ሰው ምድር ላይ አሻራውን ጥሎ ማለፍ አለበት" አለቻት። ፅናት "ግደይኝ ሊቦ፣ እህቴቴ፣ ያቤፆ ዳክተር ዳመነ ከወደዳችሁኝ ግደሉኝ" አለች።
إظهار الكل...
😘ፅናት😘 🔥ክፍል 41 ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) . . . ፨ ፅናትም "ምነው ችግር አለ እንዴ ዶክተር ዳመነ " አለች። ዶክተር ዳመነም "ፅናትን ብቻዋን ላወራት ስለምፈልግ እባካቹህ ውጡ" አላቸው። እነሱም "እሺ እሺ ብለው ወጡ" ልክ ሁሉም እንደወጡ ዶክተር ዳመነ በንዴት እና በሀዘን ከመቀመጫው ተነስቶ በመዳፉ ጠረጴዛውን ተደግፎ "ፅናት ቆይ አንቺ ገና ልጅ አደለሽ እንዴ እንዴት ታረግዣለሽ እንዴት" አላት። ፅናትም "እንዴ ቆይ ምን እያልከኝ ነው እኔ እረጉዝ ነኝ እንዴ" አለች ተደናግጣ። ፨ዶክተር ዳመነም እንደለመደው በፍጥነት እያወራ "ይህ እረግዝና ካለሽበት የጤና ሁኔታ ጋር እንደሚጋጭ አታቂም?" አላት። ፅናት " እእእ እእእኔ እንዴት አውቃለሁ " አለችና ፈገግ አለች። ዶክተሩ "እንዴ ቆይ ለምንድነው ፈገግ እያልሽ ያለሽው" ሲያት። ፅናት "አይይ ምንም ዶክተር " አለችና ሆዶን ያዝ አረገችው። ዶክተር ዳመነም " ስሚኝ እየውልሽ በሽታሽ እንዴት እንደሆነ ባላቅም ምልክቱ በአፈጣኝ ታይቷል ግን ልክ ምልክቱ ሲታይ በተራ የምንሰጥሽ መዳኒት የስቃይ እና የህመምሽን ጊዜ ለማራዘም ይጠቅመን ነበር። ፨ደሞ አሁን አረግዘሻል መዳኒቱን ከወሰድሽ ፅንሱ ይጨናገፍል። እንዲህ አይነት ግንኑነት እንደምታረጊ በእዚህ እድሜሽ እንዴት ላቅስ እችላለሁ እንደማይሽ ከሆነ ደሞ እንደፀነሽ ከነገረኩሽ በኋላ በፈገግታ ተሞልተሽ እጅሽን ከ ሆድሽ ላይ ማንሳት አልቻለሽም ፅንሱ መውረድ አለበት ይህንን ካላረግሽ አንቺ እና ልጅሽ በህይወት አትቆዩም መዳኔቱን ከወሰድሽ ልጅሽ ካልወሰድሽ ደሞ አንቺ እና ልጅሽ ትሟታላቹ" አላት። ፅናት ኮስተር ብላ "ይህንን ነበር በጭራሽ ለማናቸውም እንዳትናገር እኔም በህክምና እያጠናሁ ነው የታካሚ ሚስጥር በጭራሽ ለሊላ ወገን አልፎ መስጠት እንደማይቻል አውቃለሁ ሚስጥሬን ካወጣህ እከስሀለው።" አለችና በሩን በሀይል ከፈታ ወጣች። በፀሎት ሊባኖስ ፣ ያቤፅ እና የእነ ያቤፅ ሹፌር በር ላይ እየጠበቋት ነው። ፅናት ፈገግ ብላ ወጥታ መጀመሪያ ያቀፈችው ያቤፅን ነበር። ሊባኖስ እና በፀሎት ተያይተው ግራ ተጋቡ። ከዛ በፀሎት እና ሊባኖስን አንድ ላይ አቀፈቻቸውና እያፈራረቀች ሳመቻቸው። በፀሎት "እንዴ እህቴ ምን ተገኘ" አለች። ፅናትም "ዶክተሩ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነሽ አለኝ በተደጋጋሚ ሲያመኝ ሊላ ህመም የያዘኝ መስሎኝ ነበር ያው የህክምና ተማሪ አደለሁ" አለች። ሊባኖስም " እኔ ግራ ነው የገባኝ " አለች። ያቤፅም ፅናትን አቅፎ "በሉ ዛሬ የደስታ ቀን ይመስላል ቤት ደውለውልኝ ቁርሱን ወደ ምሳ እንዲያዞሩት ነግሪያቸዋለው እና ምክንያቱንም ነግሬያቸው ወደ እዚህ እየመጡ ነው" አለና እጁን እየጠቆመ "ኣ ተመልከቱ ቤተሰቧቼ ወደ እዚህ እየመጡ ነው" አለ። ሶስና እና የያቤፅ አያት ወዳሉበት ተጠጉና ሰላም ተባባሉ። ሶስናም ወደ ፅናት ተጠግታ "ልጄ ደና ነሽ ሳይሽ በጣም ደስ ያለሽ ትመስያለሽ" አለቻት። ፅናትም "አዎ አዎ ደና ነኝ አሁንም ከ እዚህ በኋላም ደና እና ደስተኛ እሆናለሁ" አለች። የያቤፅ አባትም "እንደዛ ከሆነ በሉ ወደ ሰርፕራይዙ እንሄድ ተከተሉኝ" አሉና ከፊት ቀድመሙ መራመድ ጀመሩ። ፨ሶስናም ሁላችንንም የሚይዝ ትልቅ መኪና ነው የያዝነው ሹፌሩ እናንተ የመጣችሁበትን መኪና ይዞ ይሄዳል። ትልቁን መኪና ደሞ እኔ እየነዳው እንሄዳለን አለች። እንዳለችው ሹፌሩ መኪናውን አስነስቶ ወደ ቤቱ ሄደ። ሶስናም መኪና ውስጥ ገብታ ሹፌሩ ወንበር ላይ ተቀጠች የያቤፅ አያትም ጋቢና ሆነው የቀሩት ከኋላ ገቡ እና ሶስና እየነዳች መንገድ ጀመሩ። እየተሳሳቁ እየተቀላለዱ ሄዱ። ፨ ሶስና በመጨረሻም መኪናዋን አቁማ በሉ ኑ ውረዱ አለችና ወረደች። ሁሉም ወረዱ መኪናውን ካቆመችበት ፊት ለፊት ወዳለ ቤት ተጠግታ ለፅናት ቁልፉን ሰጠቻት። ፅናት በደስታ ውስጥ ናት። ቤቱን ከፈተችውና በቀስታ ገባች። ትንሽ እራቅ ብላ የምታምረ መኪና ቁማች የያቤፅ አባትም ወደ ፅናት ሄደው ጀረባዋን ያዙዋትና ያቺ መኪና ትታይሻለች እሷ ደሞ ወደ እዚህ ያማረ ቤትሽ በጉጉት የምትገቢባት እና ወደ የምትወጪባት መኪና ናት" አሉዋት። ፅናት ወደ በፀሎት ሄዳ "እህቴ የፈጣሪ ያለ አየሽ በእዛች ደሳሳ ክፍል የምንበላው ጠፈቶ ተሰቃይተናል ፤ መኝታችን ሳይመቸኝ ቀረቶ ተሰቃይተን ነበር ፤ ብዙ መንገዶችን በእግራችኝ ተጉዘን ተምረናል። ፨ አሁን ሁሉም በተቃራኒው ሆኖል ድሮ እረስ በእራሳችን እንተሳሰባለን እንጂ ሊላ የሚያስብልን ሰው አልነበረም አሁን ተመልከች ልክ እንደ ታልቅ እህት እና እናት ሆና ለእኛ የምትኖር እና የምትሞት ሊቦ አለች። ከዛ ደሞ እሷ እና ህይወት ባስተማረችን ትምህርት አማካኝነት በእኛ ምክንያት የተደሰቱ ሰዎች እዚህ አሉ። እኒ ሰዎች ደሞ አዙረው እኛን ለማስደሰት እየጣሩ ነው ይህንን ሁሉ ሊሰጠን ነው ያን ሁሉ ፈተና ያለፍነው።" አለችና። በፀሎትን አቀፈቻት። ፨በፀሎትም ፅናትን ይበልጥ በጥብቃ አቀፈቻትና "እህቴ ያልሽው ሁሉ ነገር ልክ ነው ህይወት እንዲ ናት እኛ መቼም ቢሆን ክፉዎች ፊታቸውን ላዞረችባቸው ሰዎች እኛ ፊታችንን አናዞረባቸውም ምክንያቱም ችግረን ሰጥቶ እና ተቀብሎ መደሰትን እናቀዋለን" አለች። ሶስናም በሉ ኑ ውስጡን በደብ እንየው አለችና " ፅናት በይ በትልቁ ቁልፍ የሳሎኑን በር ከፈተሽ ቤትሽ አስገቢን" አለቻት። ፅናት "እሺ ኑ በቃ" ብላ ወደ ሳሎኑ በር ሄዳ ከፈተችውና ውስጥ ገባች።ሁሉም ተከትለዋት ገቡ ልክ ስታየው "አአ ፎቅ ነው እንዴ ይህ ቤት ቪላ መስሎኝ ነበር።" አለች። እያንዳዱ ክፍል እየገብ አዩ ልዩ ቤት ነበር። ሲመጡ መኪናዋንም አዩዋት በፀሎት እና ፅናት መኪና ውስጥ ገብተው ቆዩ። ፨ ሶስና "አሁን ወደ በፀሎት ሰርፕራይዝ ለመሄድ ተነሱ" አለች። "ምን ይሆን የኔ ደሞ?" አለች። ሶስናም "ታይዋለሽ የእኔ ቆጆ" አለቻት። ጉዞ ጀመሩ። ልክ እንደ ቀድሞ እየተሳሳቁ ሄዱ። በመጨረሻ አንድ ቦታ ላይ ሶስና መኪናውን አቆመችውና። "በሉ ውረዱ ሰዎች እኔ እና የያቤፅ አያት ያዘጋጀንልሽን ነገር ለማየት መቼስ ጎጉተሻል አደል " አለች።በፀሎትን ስቃ እያየቻት። በፀሎትም "በሚገባ" አለቻት። የያቤፅ አባትም " በሉ አሁን ለበፀሎት ስጦታዬን እኔ ልስጣት" ብለው። ወደ በፀሎት ተጠግተው የበፀሎትን እጅ ያዙና " አንቺ በልጅ አይምሮሽ እህትሽን እና አንቺን በደብ በስርዓቱ ያኖርሽ ልጅ ነሽ እንዴት አውቁ ልትይኝ ትችያለሽ ግን እኔ ስላንቺ እና ስለ እህትሽ ለማወቅ ስለፈለኩኝ ሊባኖስን የሆነ ቀን አግኝቻት ነግራኛለች። እናም በህይወትሽ ብዙ ፈተና ተፈትነሽ አልፈሻል ጠንካራ ሴት ደስ ይለኛል ልጄ በምድር ህይወትሽ ተፈትነሽ ላለፈሽበት ህይወት ፈጣሪ እንደሚከፈልሽ አልጠራጠርም እኔም በበኩሌ የራሴን ነገር ለህይወትሽ ልከፈልሽ ፈለኩኝ። የልጄ መለወጥ ላይ አንቺም አስተዋፆ አለሽ እባክሽ ይህንን ተቀበይኝ ብለው ሁለት ቁልፍ ሰጧት አንደኛው የመኪና ሲሆን ሊለው ደሞ የቤት ይመስላል በጣም ብዙ ቁልፎች ተጠባብቀው አሉበት። በፀሎት "በጣም ከልቤ አመሰግናለሁ ግን ይቅርታ ይሄ ይገባኛል ብዬ አላስብም መቀበል አልችልም" አለች። ያቤፅም ተቀበይው "በፂዬ እባክሽን ተቀበይው ይህ እኮ ያለ ነገር ነው። አታካብጅው አያቴ ሁሌም በጣም በስራው ለተደሰተበት ሰው የሚያረገው ነገር ነው እባክሽን ተቀበይው እባክሽን" አላት።
إظهار الكل...
ያቤፅም "ደና አድሪያለሁ የኔ ፍቅር" አላት። ፅናት ፈገግ እያለች "አንተ ቀውስ ኧረ እንዳይሰሙክ" አለችው። ያቤፅም "ቢሰሙም ግድ የለኝም አፈቅርሻለሁ" አላት። ፅናት እየተሽኮረመመች "እኔም" አለች። ያቤፅ "ስሚ ዛሬ ሁለታችም ክላስ የለንም ስለዚህ ወደ እኛ ቤት ሄደን ከዛ እማማ እና አያቴ የሰጡሽን ስጦታ ሊያሳዩሽ ስለሚፈልጉ ወደዛ እንድንሄድ ይዘሀት ና ተብዬ ነው ቁርስም ተዘጋጅቷል" ሲላት። ፅናት " እሺሺሺ መጣው በቃ ና ግባ እስከዛ " ብላ ወደ መኝታ ቤት ገባች። ያቤፅም ሳሎን ገብቶ ቁጭ አለ። ፨ፅናት ምን ልልበስ ብላ አሰበችና በመጨረሻ ማርቆስ የሰጣትን ቀሚስ እና ጫማ ሊባኖስ የሰጠቻትን የፀጉር ጌጥ እህቷ የሰጠቻትን የአንገት ሀብል እና ያቤፅ የሰጣትን ጆሮ ጌጥ አርጋ። እህቷን እና ሊባኖስን ቀሰቀሰቻቸው። ሁለቱም አይኞቻቸውን እያሹ ተነሰተው ፅናትን አዩዋት። ፨በፀሎትም "አአ እህቴ ልእልት መሰለሻል በእዚህ በጠዋት " አለች። ሊባኖስም "እውነትም ልእልት ከዛም በላይ ነው እንጂ የሆነችው ለመለካት አልነጋለሽ ብሎ ነው አደል በእዚህ በጠዋት እንዲ እንደ ልእልት የተሽቆጠቆጥሽው" አለቻት። ፅናትም "ኧረ አደም ያቤፅ እኳ" ብላ ያቤፅ የነገራትን ሁሉ ነገረቻቸው። ሊባኖስም "እንደዛ ከሆነማ በቃ እኛም እናግዝሽ" ብላ ከአልጋዋ ተነች በፀሎትም እንደዛው። ከዛ ፀጉሯን አስተካክለውላት እሷንም አሳመሩዋት። ሲጨርሱ ሊባኖስ እና በፀሎት ወደ ሳሎን ሄደው ያቤፅን ሰላም አሉት። ያቤፅም "ኣኣ ቆንጅዬዋ በፂ እና ተቆጪዋ ሊባ እንዴት አደራቹ" አላቸው ሁለቱም በጣምም ስቀው ተሽቀዳድመው ፈጣሪ ይመስገን አንተ እንዴት አደረክ አሉት እና ተቀመጡ። ትንሽ ቆይታ አልጋውን አንጥፋ መኝታ ቤቱን አስተካክላ ፅናት ወደ ሳሎን መጣች። ፨ ያቤፅ "ኡፍፍፍፍፍ እንዴት እንዳማረብሽ የፈጣሪ ያለ ወይ ፅኑዬዬ አንቺና እህትሽ እኮ ውበታቹ ሙሉ አለም ቢጨመቅም አያወጣም" አለ። ሊባኖስ "አይይይ አንተ ልጅ እሺ እኔስ" አለችው። "እንደነሱ ባይሆንም ቆኝጆ ነሽ ግን ያንቺ ቁጣ ደሞ የአለም ቁጣ ቢጨመቅም አንቺ ጋር ድርሽ አይልም" አላት። ሁሉም ከልባቸው ሳቁ። ፨ ያቤፅም "በሉ በሉ አሁን ሁላችሁም ከነቃቹ አይቀረ ሁላችንም አንድ ላይ እኛ ቤት እንሄድ ከዛ ቁርስ በልተን ወደ ፅናት ሰርፕራይዝ" አለ። በፀሎት "ኧረ እንደዛ ከሆነማ ሊቦቲዬ ነይ እንዘጋጅ" ብላ ወደ መኝታ ቤት ገባች። ሊባኖስም "እሺ ካላቹ እንግዲ" ብላ በፀሎትን ተከትላ ገባች። እነሱ ለባብሰው እስካወጡ ድረስ ያቤፅ ፅናትን ለሰከንድ አይኑን ሳይነቅል እያያት ነበር። እሷም "ሆ" ብላ እየሳቀች ቆየች። ፨ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሊባኖስ እና በፀሎት ለባብሰው ወጡ ያቤፅ በፀሎትን አያትና "አይይይ ውበት በስማም ፀጥ ነው ሊላ ምን ይባላል በሉ ተነሱ እንሄድ" ብሎ ከፊት ቀድሞ ሄደ። እነሱም ተከተሉት። በር ላይ የሚያምር መኪና ከእነ ሹፌሩ ቋሟል። "በሉ ኑ ግቡ" አለና ያቤፅ የኋላውን በር ከፈተላቸው እና ገቡ እሱም ጋቢና ተቀመጠ። መንገድ ጀመሩ ትንሽ እንደቆዩ ፅናት መንቋራጠጥ ጀመረች። ፊቷ ላይ ላብ ጭፍፍፍ አለ። በፀሎት ፅናትን እንዳየቻት "እህቴ ወይኔ እህቴ" አለች።ሊባኖስም "የእኔ ሚጢጢ ምነው" አለች። ያቤፅ ሹፊሩን "ወደ ሀኪም ቤት ንዳውውው" ብሎ ጮከ። ፨ **አሁን ፅናት ክትትል የምታረግበት ሀኪም ቤት ናት። ዶክተሩ የፅናትን የምርመራ ውጤትዋን ሊነግራት ነው። "አዝናለሁ" ብሎ ጠረጴዛው ላይ ድፍት አለ። ይቀጥላል 🔥 Share 🙏 @yefikr5 @yefikr5 @yefikr5
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.