cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

"እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤" (የሉቃስ ወንጌል ፩:፵፰ https://telegram.me/werbngg https://telegram.me/werbngg . . . @Beki_2013 @YAMSGNAWA 👆👆👆👆👆 ማንናወም ጥያቄ ካላችሁ. መጠየቅ ይቻላል 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/joinchat/oRvilXX5A1I0ZDc0

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
191
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ጥቅምት 14 አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው "ንጉሥ ይስሐቅ" እና "ቅድስት እድና" ይባላሉ። የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው። ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው "ዘሚካኤል" ሲሏቸው በበርሃ "ገብረ አምላክ" ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ "አረጋዊ" ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ። በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል። "የት ልሒድ?" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለስምንት ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየኋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር።" ብለው ከስምንቱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጡ። በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጸሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል። ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል። በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን(ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት። የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ ስልሳ ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል። እንደወጡም " ሃሌ ሉያ ለአብ ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፣ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ሲያመሰግኑ ከሰማይ ህብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል። በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች። ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ(ገዳም ካደረጉት) በኃላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ስድስት ሺህ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል። ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸው "አብሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮጵያ" ትርጉም - "የኢትዮጵያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ። አብነ አረጋዊ በህይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎት እና መጽሐፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል። ቅዱስ ያሬድ እና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ። በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው "ንግሥት እድና" ሁናለች። ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በዘጠና ዘጠኝ ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተ ምስራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል። ጌታም አሥራ አምስት ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ስንክሳር ዘጥምቀት 14
إظهار الكل...
፨፨፨፨የወራት ስያሜ፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ዲ/ን ሕሊና በለጠ ከመስከረም እስከ ጳጉሜ የተሰየሙት ወሮቻችን ስያሜያቸውን ከየት እንዳገኙ ያውቃሉ? እስኪ የሚከተለውን ይመልከቱ፡፡ 1 የወሩ ስም - መስከረም የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሴ እና ከረም ትርጉም - መሴ-አለፈ ፣ መሸ ፤ ከረም-ክረምት፤ ክረምት አለፈ ፣ ክረምቱ መሸ 2 የወሩ ስም - ጥቅምት የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ጠቀመ ትርጉም - ሠራ፤ ጠቃሚ ጊዜ 3 የወሩ ስም - ኅዳር የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀደረ ትርጉም - አደረ-ሰው በወርኃ አዝመራ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ይገልፃል 4 የወሩ ስም - ታኅሳስ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀሠሠ ትርጉም - መረመረ- በመኸር ወቅት የሰብል ምርመራን ያመለክታል ፤ ሰብዐ ሰገል በታኅሳስ ወር የተወለደውን ጌታችንን ማሰሳቸውን ፣ መፈለጋቸውንም ያመለክታል። 5 የወሩ ስም - ጥር የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ነጠረ ፣ አጥረየ ትርጉም - ነጠረ - ጠረረ- ብልጭ አለ፤ ነጻ፤ የፀሐይን ግለት ወቅት ያሳያል ፤ አጥረየ - ገዛ (ከብቱም ምርቱም የሚሸጥበት የሚገዛበት ወቅት) 6 የወሩ ስም - የካቲት የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ከተተ ፣ ከቲት ትርጉም - መክተቻ (እኅልን ወደ ጎተራ) 7 የወሩ ስም - መጋቢት የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መገበ ትርጉም - በቁሙ የሚመግብ (በጎተራ የተከተተው የሚበላበት) 8 የወሩ ስም - ሚያዝያ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሐዘ ትርጉም - ጎለመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ (ወርኀ ሰርግ መሆኑን ሲያጠይቅ) 9 የወሩ ስም - ግንቦት የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ገነበ ትርጉም - ገነባ፤ ሠራ፤ ቆፈረ፤ ሰረሰረ (ለእርሻ የመሬቱን መዘጋጀት ያሳያል) 10 የወሩ ስም - ሠኔ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሠነየ ትርጉም - አማረ (አዝርዕቱ) 11 የወሩ ስም - ሐምሌ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሐመለ ትርጉም - ለመለመ ፣ ሐመልማል ሆነ ፣ ለቀመ (ለጎመን) 12 የወሩ ስም - ነሐሴ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - አናሕስየ ትርጉም - አቀለለ፤ ተወ (የክረምቱን እያደር መቅለል ያሳያል) 13 የወሩ ስም - ጳጉሜ ሥርወ ቃሉ - ኤጳጉሚኖስ (ግሪክ) ትርጉም - ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ (1.ኅብረ አትዮጵያ፤ ከቴዎድሮስ በየነ፤ አዲስ አበባ፤ 1999ዓ.ም.፤ ገጽ 16-17 2. ከሊቃውንት አስተምህሮ)
إظهار الكل...
ሥርዓተ ማህሌት ዘነሐሴ ተክለሃይማኖት ሥርዓተ ነግሥ ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ በአሐቲ ቃል መልክዐ ሥላሴ ሰላም ዕብል ለንዋየ ውሰጥ ምሕረትክሙ ትሩፋተ ገድል ኵኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ ጊዮርጊስ ኢወሰነ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ ዚቅ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘኢይነውም ትጉህ: በውስተ ቅዱሳን ሰቡሕ ከመ ቀስተ ደመና የዓውዶ ሱራሄ: ሎቱ ለባሕቲቱ ይደሉ ስባሔ ነግሥ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ለወልድኪ አምሳለደሙ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ ዚቅ ኣመ ኖኅ ይእቲ መድኃኒት እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት: ማርያም ቅድስት፡፡ ወረብ ማርያም ቅድስት አንቀጸ ሕይወት አመ ኖኅ አንቀጸ ሕይወት ማርያም ቅድስት ይእቲ መድኃኒት እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት መልክዐ ተክለሃይማኖት ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘጥንተ ፊደሉ መስቀል: ስም ክቡር ወስም ልዑል: ተክለሃይማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል: ከመ እወድሰከ መጠነ አውሥኦተ እክል: ማዕሠረ ልሳንየ ትፍታሕ ማርያም ድንግል፡፡ ዚቅ ወንጌለ መለኮት ሰበከ ስምዓ ጽድቅ ኮንኪ ወበእንተዝ ተክለ ሃይማኖት ተሰመይከ ወረብ ወበእንተዝ ተሰመይከ ተክለሃይማኖት ስምዓ ጽድቅ ኮንከተክለሃይማኖት መልክዐ ተክለሃይማኖት ሰላም ለአዕይንቲከ ዘአርያኣሆን ሐዋዝ እለ ጽዱላት እማንቱ ከመ ሠርቀ ቤዝ ተክለ ሃይማኖት ኅብአኒ እሞተ ኃጢአት አዚዝ ለከሰ አኮ ከመዝ ኢይረክበከ ሞት ዳግም እምዝ አመላለስ ዳግም እምዝ ኢይረከቦ ሞት ለተክለ ሃይማኖት ዓዲ ወረብ ዳግም እምዝ አይረከቦ ከመዝ ሞት ለተክለ ሃይማኖት ኢይረከቦ እምዝ ሞት ለተክለሃይማኖት መልክዐ ተክለሃይማኖት ሰላም ለኵልያቲከ ዘፈተኖን በትዕግስት ኢየሱስ ክርስቶስ አበብርሃናት ተክለ ሃይማኖት ሰጋዲ ከመ መላእክት ጸሎትከ ዝገበርካሃ እስከነ ጐልቍ ምዕት ዓመት መድኃኒተ ትኩነኒ እምግሩም ቅሥት ዚቅ ተክለ ሃይማኖት ሰማዕት ሰባኬ መድኃኒት ጸሎትከ ትኩነነ ፀወነ እመንሱት ተክለ ሃይማኖት ሰማዕት ሰባኬ መድኃኒት ወረብ ሰማዕት ሰባኬ መድኃኒት ተክለ ሃይማኖት ጸሎትከ ትኩነነ ጸወነ እመንሱት መልክዐ ተክለ ሃይማኖት ሰላም ለፀዐተ ነፍስከ በስብሐተ አዕላፍ እንግልጋ ለዓለም ዛቲ እምግብርናቲሃ ወጹጋ ተክለ ሃይማኖት ቶማስ ለመርአስ ዐቃቤ ሕጋ ለእለ ገብሩ ተዝካረከ እንዘ ሀለዉ በሥጋ ሀቦሙ እግዚእየ ሞገሰ ወጸጋ ዚቅ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌምሰማያዊተ መልክዐ ተክለ ሃይማኖት ሰላም ለበድነ ሥጋh ኤልሳዕ መምህር ዘገነዛ ሰሠናይ ፄና መዓዛ: ተክለ ሃይማኖት ሰባኪ ፊልጶስ ዘብሔረ ጋዛ: ለሥጋየ መሬታዊት እመ የኀልቅ እዘዛ: ስብረተ ዕፅምከ ይኩነኒ ቤዛ ዚቅ ሖረ ኀቤሁ ለተክለ ሃይማኖት ቀዲሙ ሌሊተ ኤልሳዕ ስሙ መልአኮሙ ለአርድዕት ውእቱኒ አምጽአ ከርቤ አፈዋት ገነዝዎ በሰንዱናት ለተክለሃይማኖት መልክዐ ተክለሃይማኖት ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዘቦቱ ይትመኀፀኑ ነገሥተ እስራኤል ጌራን ዘአስተሣነይዎ በበዘመኑ ተክለ ሃይማኖት ሠዋዒ ለእግዚአብሔር ካህኑ አድኅነኒ እምጸብአ ከይሲ ዘዕሥር ቀርኑ ወእምብእሲ ዘክልኤ ልሳኑ ዚቅ መላእክት አእመሩ ሃይማኖተኪ: ነገሥት ሐነፁ መካነከ: አባ ተክለሃይማኖት ክርስቶስ ዘአፍቀርከ። መልክዐ ተክለሃይማኖት ሰላም ለመቃብሪከ እምቅድመ ትኑም ውስቴታ ታቦተ ማርያም ድንግል ዘአንበርከ በውሳጢታ: ተክለሃይማኖት አቡየ ለወልድከ ዕጓለ ማውታ: ለበረከትከ ይከልለኒ ረድኤታ: ወይዑደኒ ዘጽድቅከ ወልታ። ዚቅ ጸለየ ተክለ ሃይማኖት እንዘ ይብል ኀበ ተቀብረ ሥጋየ ወተክዕወ ደምየ ህየ ይኩን በረከት ወረብ ጸለየ ተክለ ሃይማኖት እንዘ ይብል ኀበ ተክዕወ ደምየ ህየ ይኩን በረከት አንገርጋሪ ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ እስመ ለጻድቅ ይትሌዓል ቀርኑ በክብር ጻድቃን እለ አስመርዎ ለእግዚኦሙ ምድረ ብርህተ ወጽዱ ይወርሱ እስመ ለዓለም ደሪፆሙ ተአጊሦሙ መጠዉ ነፍሶሙ ለሞት እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕወቶሙ እምፀሐይ ይበርህ ገጾሙ እለ አጥረይዋ ለትዕግስት እለ እፎ አምሰጥዎ ለመድብብ ከመ ይባዕዎ ለመርኀብ እሊ ዕፎ አመሠጥዎ ለሞት ዓደዉ እሞት ውስተ ሕይወት እለ እለ ጸውዖሙ ወይቤሎሙ ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ እሊ አመ ያቀውም አባግዐ በየማኑ ወአጣሌ በጸጋሙ እሊ አሜሃ ይቤሎሙ ለእለ በየማኑ ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ እለወያወርሶሙ ምድረ ሐዳሰ እንተ ታውኀዝ ሀሊበ ወመዓረ: እለ ገነት ትፍሥሕት ኪያሃ አውረሶሙ ወዓቅቦሙ ከመ ብንተ ዓይን ለጻድቃን እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ
إظهار الكل...
ስርዓተ ማህሌት ዘአብነ ተክለሃይማኖት ወቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ዘ ሀምሌ ፳፬
إظهار الكل...
ክርስቶስ ሆይ !!!!!!! ክርስቶስ ሆይ እነርሱንም አትለፋቸው ተመልከታቸው ማራቸው ፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በዓለም ያለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ኅብረቷን ከርኩሰት በቅድስና ከክህደት በአሚነ ሥላሴ ጠብቃት የሚጣላትን ሁሉ ፈጥነህ አሸንፍላት በልዩ ልዩ መንገድ ከቤትህ የኮበለሉትት አንተ በማይከራከሩት ጥበብህ በማይገፉት ፍቅርህ መልሳቸው/ መልሰን !!!! በዓለማችን ላይ የመጣውን ይህንን ወረርሽኝ ሁሉ "የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቆርጣል" እንዲል መጽሐፍ ይህ መቅሰፍት በምሕረትህ ድምፅ ይቆረጥ፥ በትንፋሽ ማቆያ ያሉትን ስለ ስምህ ደግሞም ስለ ሚናፍቁ ወዳጆቻቸው ብለህ አንቃ ፤ አምላካችን መዘነጋታችንን ይቅር በለው፥ ሸፋኙ ሆይ ሸፍነን ፥ህፃናቱ ያለበደላቸው በበደላችን አይቀጡ ተዘከረን፥የጅማሪውን አስፈሪነት ፍጻሜ አታሳየን የምሕረትህ ጣልቃ ገብነት ከተቀጠረብን ክፉ ያድነን !!!! ልዑላችን በሁሉ የተዘነጋውን ሕዝብ ሁሉ በሁሉ የሆነከው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ሆይ አስብ!!! ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በማዕከለ ምድር በቤዛነትህ በሕመምህ ባፈሰስከው ደምህ በልዩ በልዩ መንገድ ከሠራነው ነውር ርኩሰት ኃጢአት መተላለፍ ሁሉ እጠበን ፥እጠበን የእውነት ቆሽሸናልና "ደምህ ኃጢአትን ሁሉ ያነጻል እንዲል ምስክርህ" ፥ደግሞም ንስሐ ገብተን ከአዕምሮ ክስ ያልተላቀቅነውን አዕምሮአችንን እንድታሳርፍ በአዲስ የቅድስና ሀብት እንድትሞላን እንማጸንሃለን ፤ አቤቱ አምላካችን የሃይማኖታችን ጎዳና እና መሠረት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ስለ ስምህ ተመስገን ፥ስለ ስምህ ስማን ፥ስለ ስምህ ማረን ማረን ማረን፥ አምላኬ ሆይ ጸሎት በአንድ ዘመን መልስ ደግሞ በአንድ ዘመን እንደሆነ የቅዱሳን ሕይወት ምስክራችን ነው ፤ ነገር ግን ለነገ ብለህ የማታሸጋግረው ጸሎት "ማረን" ነው አዎን እባክህን ስለ ፍቅርህ ብለህ ማረን ፤ በእኔ/ በእኛ ኃጢአት የሚደርሰው ነበልባል ይቅር ብለንና ይገታ ፥ ታጋሽነትህ ብዙ ነው እያልን ፈራጅነትህን ረስተን በስንፍና የፈጸምነውን ርኩሰት ሁሉ ይቅር በለን ስለ ስምህ ብለህ ማረን ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ለስምህ ክብር ምስጋና ይሁን በጸናው መንግስት ለዘለዓለሙ አሜን !!!!!
إظهار الكل...
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡ ✍️"ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፋጫል፤ የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡ ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮኽ እንደ ሰማ ኹሉ ይደነግጣል፤ አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፤ ባንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፤ ከፍጡራን ወገኖች ኹሉ ይልቅ ሰይጣን አንቺን ይጠላል" ምንጭ 📚 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
إظهار الكل...
ክፍል - ፪ (2) 🔱ሙሴና ኤልያስ ለምን ተመረጡ?🔱 👉. ሙሴንና ኤልያስን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት የባሕርይ አምላክ መሆኑን እንዲመሰክሩ ነው፡፡ ሙሴ ከመቃብር ተነሥቶ ስለ ጌታችን እንዲህ የሚል ምስክርነት ሰጥቷል፡- “እኔ ባሕር ብከፍልም፣ ጠላት ብገድልም፣ ደመና ብጋርድም፣ መና ባወርድም እስራኤልን ከክፋታቸው መልሼ ማዳን ያልተቻለኝ ደካማ ነኝ፤ የእኔን ፈጣሪ እንዴት ሙሴ ይሉሃል? የሙሴ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!”። ኤልያስም ደግሞ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ፦ “እኔ ሰማይ ዝናብ እንዳይሰጥ ብለጉም፣ እሳት ባዘንብም እስራኤልን ከክፋታቸው ማዳን የማይቻለን ነኝ፤ እንዴት የእኔን ፈጣሪ ኤልያስ ነህ ይሉሃል? የኤልያስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” ብለው የባሕርይ አምላክነቱን በደብረ ታቦር ላይ መስክረዋል፡፡ /ማቴ.16፥14/ 👉. ሙሴና ኤልያስ የተመረጡበት ሌላው ምክንያት ሙሴ “ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴን ግን አይታይም”  ተብሎ ስለተነገረለት /ዘጸ. 33፥23/ ኤልያስ “በኋለኛው ዘመን ምስክሬ ትሆናለህ” ስለተባለ ያንን ለመፈጸም ነው። 👉. ካገቡት ሙሴን ከደናግል ኤልያስን ያመጣቸው መንግሥተ ሰማያትን በሕግ የተጋቡ ሕጋውያንም ሥርዓት ጠብቀው የሚኖሩ ደናግላም እንደሚወርሷት ሲያጠይቅ ነው፡፡   የደብረ ታቦር ምሳሌነት ✨✨✨✨✨✨ 👉. የወንጌል ምሳሌ ነው፡፡ ተራራ ሲወጡት በጣም ያስቸግራል፤ ከብዙ ድካምና ውጣ ውረድ በኋላ ተራራውን ጨርሰው ከላይ ሲወጡ ግን አባጣ ጎባጣውን ሜዳና ገደሉን ያሳያል፡፡ ወንጌልንም በሚገባ ከተማሯት ጽድቅን ከኃጢአት ለይተን እንድናውቅ ታደርገናለችና፡፡ 👉. ለቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በደብረ ታቦር ምሥጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታል፡፡ አንድም ተራራ መሠረቱ ከመሬት አናቱ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ሰማያዊት የመሆኗ ምሳሌ፡፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነውና›› እንዲል። /ፊል. 3፥20/ 👉. የታቦር ተራራ ይህን ሁሉ ምሥጢር የያዘ በመሆኑ በክርስትና ታሪክ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮት የተገለጠበት፣ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው። በሀገራችንም ዘንድ ቡሄ ይባላል፡፡ የቡሄ በዓል ሃይማኖትና ትውፊትን የያዘ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ልናከብረው ይገባናል፡፡   🔥 ቡሄ 🔥 👉. ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል ለማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ 👉. ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡ 💫 ጅራፍ 💫 👉. በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምሥጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ምሥጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መግመድ እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምሥጢር ይዞ የሚከወን ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ እንዲሁም የጌታችንን ድምፅ ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የምስክርነት ቃል፣ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡ ☄☄ ችቦ ☄☄ ⚡️⚡️⚡️⚡️   👉. ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ ግን በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሄደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጒም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ ምሳሌ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፤ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ሊሆን ይገባዋል፡፡   🌭 ሙልሙል 🌭 👉. በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ቡሄ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፤ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንዲሄዱ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ብለው ይሄዳሉ፡፡ 👉. በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ወላጆች ለአዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ሲሆኑ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፤ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ 👉. አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምሥጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ 👉. ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፍ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፣ አስተዋዮችም ይሆናሉ፣ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ። በሥነ ምግባር የታነፁ፣ ሀገርንና ወገንን የሚጠቅሙ፣ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ። ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ 🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱 🙏 ሠናይ በዓል፣ ሠናይ ጾም ወሠናይ ሱባዔ፤ 🙏 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን። ⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜
إظهار الكل...
⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜💫⚜ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን። ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜ ⚜ በዓለ ደብረ ታቦር ⚜ ⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜ 👇 ክፍል - ፩ (1) 👉. የታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በምዕራብ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተነግሯል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ “ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ፤ - ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል” ብሎ የተናገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል። /መዝ. 88፥12/ 👉. በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሣራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው፡፡ ምሳሌነቱም ባርቅ የጌታችን፣ ሲሣራ ደግሞ የአጋንንት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው። /መሳ. 4፥6/ 👉. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በቂሳርያ “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ አዕማድ ተብለው የሚጠሩ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ረጅሙ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ መልሶ ጌታችን ኢየሱስን "ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ በዚህ እንሥራ" አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት።" የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ሐዋርያት ይህንን ሰምተው የጌታችንን መለኮታዊ ክብር ዐይተው በፊታቸው ወደቁ፤ እጅግም ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችንም "ተነሡ አትፍሩም" አላቸው፡፡ በዚህ መልኩ አምላክነቱን ገለጠላቸው። /ማቴ. 17፥1-10/ 🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃 አዕማደ (የምሥጢር) ሐዋርያት ለምን ተመረጡ? 🌻🌻🌻 👉. አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን  “አዕማደ ሐዋርያት” እያለ ጠርቷቸዋል። /ገላ. 2፥9/ 👉. አዕማደ ሐዋርያት የሚለውን ሥያሜ ያገኙበት ዋናው ምክንያት የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን በኃላፊነት ያስተባብሩ ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእርሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሄደ ነው። /ማር.5፥37-43/ 👉. ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ለምሥጢር ሐዋርያነት የተመረጡበትን ምክንያት ሲያትቱ እንዲህ ብለዋል፦ 📖. ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ሐሳብ እንዲወጡ ከብልየታቸው እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሕማማቱ በሞቱ ቤዛ የሚሆነን አምላክ “ልሰቀል ነው” ባላቸው ጊዜ “አይሁንብህ” ብሎት ነበር፡፡ እንዲህ ያለው ሐሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኅነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው ብሏልና “አይሁንብህ” አለ፡፡ /ማቴ. 16/ በሌላም ሥፍራ እንዲሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት ይጠይቃል፡፡ /ማቴ.19/ ጌታ ግን ዋጋችሁ ሰማያዊ ክብራችሁ ዘለዓለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነገራቸው፡፡ 📖. ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም እናታቸውን ልከው ሹመት ሽልማት መዓርግ ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፤ ሞቱ እርግጥ ሆነ ማለት ነው፡፡ አባቱም “ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ፤ እሺ በሉት እርሱን ስሙት" አላቸው፡፡ ጌታችንም ሞቱ እርግጥ በመሆኑ ከልባቸው እንዲጠፋ መርጦ ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡ 📖. “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል /ሚል. 3፥6/ በእርሱ ዘንድ ወረት የለም፡፡ አስቀድሞ ከተአምራቱ ከምሥጢሩ አይለያቸውም ነበርና ብርሃነ መለኮቱን ለማየት አበቃቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመጠየቅ ባሳዩት ትጋት ምሥጢር ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ምሥጢር ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከ ዓለም ፍጻሜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሲገለጥ፣ በመረጣቸውም ሲነገር የሚኖር ነውንጂ፡፡ 📖. ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ጴጥሮስ “አልክድህም አልተውህም” የሚለው /ማቴ. 26፥35/ ቢወድደው አይደለምን? ስለዚህ ፍቅሩን መግለጡ ለክብር አብቅቶታል፡፡ ሁለቱን ደቀ መዛሙርትም “ጽዋዬን ልትጠጡ አትችሉም” ቢላቸውም /ማቴ. 20፥22/ አንዳችን በቀኝ ሌላችን በግራ ሆነን አብረንህ እንሞታለን ሲሉ በምሥጢር ለምነዋል፡፡ ሞታቸውን ከሞቱ ጋር መደመራቸው ፍቅራቸውን መግለጣቸው ነው፡፡ ከተራራው ግርጌ 🌹🌼🌹🌼 👉. ከቅዱሱ ተራራ ግርጌ ዘጠኙ ደቀ መዛሙርት ተቀምጠዋል። ነቢዩ “አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውስ ተራራህ ማን ይኖራል” /መዝ.14፥1/ በማለት ጠይቆ ወደ ተቀደሰው ተራራ የሚወጡ ሰዎች ምን ዓይነት ሕይወት ያላቸው ሊሆን እንደሚገባ ሲገልጥ “…በአንደበቱ የማይሸነግል፣ በባልንጀራው ላይ ክፉትን የማያደርግ… በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል...” በማለት የጠቀሳቸው ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ /መዝ. 14፥1-5/ 👉. ወደ ቅድስናው ሥፍራ ወጥቶ ምሥጢር ለማየት ብቃት ያልነበረው ይሁዳን ለመለየት አምላክ ባወቀ ዘጠኙን ከተራራው ግርጌ አቆይቷቸዋል፡፡ /ይሁዳ እኔን ብቻ ለየኝ እንዳይል ከእርሱ ጋር ሌሎች ስምንት ሐዋርያትን ከተራራው ግርጌ አቆይቷቸዋል/ 👉. “የኃጥእ ዳፋ ጻድቁን ያዳፋ” የሚል ብሒል አለ፡፡ ይህ አባባል ግን ከተራራዉ ግርጌ ለቀሩት ደቀ መዛሙርት አይሆንም፡፡ ይሁዳን በጥበብ ከምሥጢር ለየው እንጂ ጌታ ስምንቱ ደቀ መዛሙርቱን የምሥጢሩ ተካፋይ አድርጓቸዋል፡፡ ለጥፋቱ ምክንያት እንዳያገኝ "ከምሥጢሩ ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁበት" እንዳይል ጥበብ ክርስቶስ በጥበብ ይህን አደረገ፡፡ ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ግን በንጹሕ ልቡና ከተራራው ግርጌ ተቀምጠውም ምሥጢር አልተከለከላቸውም፡፡ ምክንያቱም “ልበ ንጹሐን ብፁዓን ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና”። /ማቴ.5/ ቅዱስ ጳውሎስ እግዚአብሔርን ለማየት ለሚወዱ፦ “ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚቻለው የለምና” እንዲል፡፡ /ዕብ.11/
إظهار الكل...
የተዋህዶ✝✝ ፍሬዎች የእግዚያብሔር ቃል እንድንማማር መንፈሳዊ ጥያቄዎች እየተጠይያየቀን አይምሮአችንን እናሳድግ የማያቁትን እንድናስተዋዉቅ ሁለቹም ኦርቶዶክስን add እያረጋቹ ለማያዉቁት አሳውቁ መዝሙር ትረካ ግጥም ጥያቄና መልስ ከመንፈሳዊ ዉጪ መፖሰት የተከለከለ ነዉ የተቻለ ነው አለ ምትሉኝ ካለ በዚ አዋሩኝ @YAMSGNAWA https://t.me/agelageyoch
إظهار الكل...
የተዋህዶ✝✝ ፍሬዎች

የእግዚያብሔር ቃል እንድንማማር መንፈሳዊ ጥያቄዎች እየተጠይያየቀን አይምሮአችንን እናሳድግ የማያቁትን እንድናስተዋዉቅ ሁለቹም ኦርቶዶክስን add እያረጋቹ ለማያዉቁት አሳውቁ መዝሙር ትረካ ግጥም ጥያቄና መልስ ከመንፈሳዊ ዉጪ መፖሰት የተከለከለ ነዉ የተቻለ ነው አለ ምትሉኝ ካለ በዚ አዋሩኝ @YAMSGNAWA

#ደብረ_ታቦር ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው። በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ። ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና። ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው። የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት። ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው። ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም። ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ። ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ። እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ። ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። (ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ)
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.