cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ልብ ላላሉ ልቦች

ላ! ኢላሀ ኢለላህ ከአንድ አላህ በስተቀር በ"እውነት" የሚመለክ አምላክ የለም!! አህለን ወሳህለን አላህ በምናነበው ነገር ተጠቃሚ ያድርገን ቅን ልቦና ይስጠን አላህ ሆይ ሂዳያን ስጠን ለሌሎችም የሂዳያ ሰብብ መሆንን ወፍቀን። ኢላሂ መጨረሻችንን አሳምርልን ሞትን የምንፈራ ሳይሆን ሙተን አንተን መገኛነት የምንናፍቅ ምርጥ ባህሮችህ አድርገን ያኢላሂ @liblalaluliboch

إظهار المزيد
Ethiopia8 062Amharic7 040الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
437
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-1030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ኢላሂ. ........! ወዳንተ ስመጣ ስንቄ ጎድሎ እንደሆን፤ ባንተ በመመካት ተስፋዬን አስውቤያለሁ። ኢላሂ. ..! ሀፅያተኝነቴ የቅጣት ፅዋህን እንዳልቀምስ ቢያስፈራኝም፤ ባንተ ያለኝ ተስፋ ከበቀልክ እንዳልሰጋ አድርጎኛል። . ኢላሂ ...! ለቂያም ቀን እንዳልዘጋጅ ሸይጣን የመዘናጋትን ካባ ቢያጠልቅብኝም፤ ቸርነትህ እና አንተነትህ አንቅቶኛል። . ኢላሂ. ..! አመፄ እና ወንጀሌ በእኔ እና ባንተ መካከል አራርቆን በባይተዋርነት ሜዳ ላይ ቢጥለኝም፤ የእዝነትህ እና የመሀሪነትህ ስፋት አፅናንቶኛል። . ኢላሂ. ..! ሀፅያቴ የወራዳነትን ልብስ አስለበሰችኝ ...፣ ካንተ መራራቅም የባይተዋርነትን ቆብ ከራሴ ላይ ዳፋ.. .፣ የሀፅያት ድግግሞሹም ልቤን አጥቁሮ ገደለብኝ.. .። . ኢላሂ. ..! አልኝታዬ.. .! ብቸኛው ተስፋዬ...! የሞተ ልቤን በቀዝቃዛው ማርታህ ህያው አድርግልኝ። . ኢላሂ. ..! ጥራት ይገባህ። አንተ መሪው ያልሆንክበት መንገድ ምንኛ ጠበበ.. .አንተ መሪው የሆንከው መንገድስ ምንኛ ግልፅ ሆነ...! . ኢላሂ. ..! ጣፋጭ ፍቅርህን ከቀመሰ በኋላ ካንተ ሌላን የለመደ ማንስ አለ... ? ያንተን ጉርብትና ለምዶ፤ ሌላን ወዳጅ የከጀለ ከየት ይገኛል...? . ኢላሂ. ..! ያንተን የውዳሴ ማማ ምላሶች መድረስ አቃታቸው.. .፣ የማንነትህን ውበትም ምዕናቦች መድረስ ተሳናቸው... ፣አይኖችም የፊትህን ብሩህ ነፀብራቅ ከማየት አቀረቀሩ.። . ኢላሂ. ..! የፍቅርህ ዛፍ ስሩ በልቦቻቸው ማሳ ውስጥ ሰርፆ ከገባባቸው ወዳጆች መድበኸን፤ በውዴታህ ወጥመድ አስረህ በማዕበሉ አንሳፍፈን። . ኢላሂ. ..! ለልዕልናህ እጅ ነስታ ሱጁድ የወረደችልህን ፊት የቂያም ቀን ታጠቁራታለህን. ..? አንተን በማወደስ እና በመቀደስ የኖረችውን ምላስስ የቂያም ቀን ትቆልፋታለህን...? በፍቅርህ የዋለለችን ቀልብስ በእድለ ቢስነት ትዘጋታለህን... ? . ኢላሂ. ..! አንተን ተስፋ አድርገው በመተናነስ ወደአንተ የተዘረጉ እጆችን ቀፍድደህ ወደ ጀሀነም ትወረውራለህን.. .? የአመፅ ህይወት መሯት ወዳንተ ኢላሂ ኢላሂ የምትለዋን ነፍስስ በርህን ትዘጋባታለህን... ? . ኢላሂ. ..! ባንተ ካመንንብህ በኋላ ትቀጣናለህን...? ከወደድንህስ በኋላ ታርቀናለህን.. .? እዝነትህን ካስከጀልከንስ በኋላ ትነፍገናለህን. ..? በይቅርታህ ጥገኝነት ውስጥ ከገባንስ በኋላ አሳልፈህ ትሰጠናለህን.. .? . ኢላሂ. ..! ይህን ሁሉ ከማድረግ ጥራት የተገባህ እንደሆንክ ፍጥረታት ሁሉ ይመሰክራሉ። . ኢላሂ. ..! በዚህ ዘመን አድማሱን ተሻግሮ በሰፋው የጥፋት ውቅያኖስ ውስጥ ከምትንሳፈፈው አንዲቷ እና ባይተዋሯ የመዳን መርከብ ውስጥ ሰብስበን። አሚን ያ ረብ.... t.me/muselimnegn
إظهار الكل...
muselim negn

አድናቆትን ዝናን ስምን ፈልጌ ሳይሆን አሏህ በሰጠኝ እዉቅና ወንድም እና እህቶቼን ለማገልገል አንድ ጊዜ ተፈጥሪያለዉ እናም ዱኒያ አኼራሄን እንዲያሳምርልኝ በዱዓ አግዙኝ ለማንኛዉም ጥያቄ ============ 💌👇 👇 💌 @seid_abuzerbot 👳👳👳👳👳👳 ነብያት እና ህዝባቸዉ ነብዩም ሶሀቦቻቸዉ ስለ እስልምና የለፉ ሙስሊም ነን በለዉ አለፉ

አማራ ክልል ውስጥ ፋኖ ነን በሚሉ አካላት በኩል ሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጠናክረው ቀጥለዋል። በተለይም የሙስሊሙ ቁጥር አናሳ በሆነባቸው አካባቢዎች ግድያዎች፣ እገታዎችና ዘረፋዎች ከእለት ወደ እለት እየጨመሩ ነው። ከፋኖ ወይም ከደጋፊዎቹ በኩል እነዚህን እምነት ተኮር ጥቃቶች የሚኮንን ድምፅ እስካሁን አልሰማሁም። ከዚህ ይልቅ እየደረሰ ያለውን በደል ቀድሞ የመሸፋፈንና የማለባበስ ጥረቶች ናቸው የሚታዩት። በዘር ብቅል የናወዛችሁ አካላት እዚህ መጥቻችሁ ለመከላከል ወይም ለማስተባበል እንዳትሞክሩ። ተጨባጭ መረጃ ይዤ ነው የምፅፈው። እንዲያውም ጫፉን እንጂ የማውቀውን ሁሉ አልፃፍኩም። እኔ የፖለቲካ አላማም ፍላጎትም የለኝምና እዚህ መጥታችሁ "ወለጋ ሲሆን ..."፣ ሸገር ሲሆን ..." እንዳትሉብኝ። እንዲህ አይነት ማሸማቀቂያችሁን ፈርተው ብዙ የተለጎሙ ሙስሊሞችን እያየሁ ነው። ሁላችንም ዝም እንል ዘንድ በእምነት እየተለየ የሚፈፀመውን ጥቃት አስቁሙ። እውነት አላማችሁ ፖለቲካ ከሆነ ፖለቲካ እንዲህ አይሰራም። ቆይ ሙስሊሙ ምን ያርጋችሁ? ምን ይሁንላችሁ? በዘር ተኮር ጥቃቶች ከሆነ የትም ቢሆን ከናንተ በላይ የተጎዳው ሙስሊሙ ነው። የሙስሊሙን በዘር መጠቃት ለብሶት መቀስቀሻ እየተጠቀማችሁበት እንደገና ዞራችሁ እንዴት ታጠቁታላችሁ? ወወላሂ በዚህ ዘመን እንደ አማራ ሙስሊም መከራ የበዛበት የለም። ሌላ ቦታ አማራ ተብሎ ይጨፈጨፋል። ክልሉ ውስጥ በሙስሊምነቱ ይጠቃል። እሺ የት ይሂድ?! ምን ዓይነት ፈተና ነው?! በመጨረሻም ክልሉ ውስጥ እየደረሱ ስላሉ እምነትን ያነጣጠሩ ጥቃቶች መረጃው ላላችሁ ሙስሊሞች አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። ዝምታችሁ እልባት ላያመጣ ነገር ዝም አትበሉ። ይልቅ ሰለባ እየሆነ ላለው ሙስሊም በጊዜ በምትችሉት ድምፅ ሁኑ። ገዳዩ አካል ይሉኝታ ሳይዘው አጉል ይሉኝታ አይያዛችሁ። ህመማችሁ ህመሙ ላልሆነ ትግል አትጨነቁ። ብዙ ወገን ሙስሊሞች ላይ ተለይቶ እየተፈፀመ ስላለው ጥቃት መረጃ የለውምና ቢያንስ በዚህ ላይ መስራት ከምንም ይሻላል። Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👍 1
ትክክለኛ አራዳ ከሆንሽ ወደ ውጭ ስትወጪ በጅልባብ እና ኒቃብ ተዋቢ ቤት ውስጥ በፈለግሹ የልብስ አይነት ተዋቢ ስፈልጊ አጭር ብቻ በፈልግሹ አይነት ልብስ ዘንጪ ይሄ ነው አራድነት ቤት ውስጥ የወጣለሽ ዘናጭ ሁኚ ያኔ ትክክለኛ አራዳ ነሽ ✍ሀያት ብንት ባባ
إظهار الكل...
👍 1
በኔ ሚዛን ሷሊህ እና ውድ ሚስት ብዙ ጭንቀቶች ሃሳቦች የስራ ድካሞች ወረውክ ነገራት ሁሉ ግራ ገብቶክ ከአላህ ቀጥሎ ልክ ቤት ገብተህ የልብህን የሃሳብህን ሁሉ እርግፍ አድርገህ ጨርሰህ ነግረሃት ከነገርካት ቦሃላ ስሜትህን ተረድታህ ከልቧ አድምጣህ መፍትሄ አብራህ ፈልጋ ... ፈታ የምታደርግህ ከሆነች አላህ አድሎሃል ይህን ሚዛን ያገኘሁት በኸዲጃ እና በውዱ ነቢይ መሃል በነበረው ቁርኝት ነው የዛኔ በዋሻው ውስጥ ደንግጠው መጥተው ለእመት ኸዲጃ ነበር የነገሯት ኸዲጃም ከልቧ ሰምታቸው አይዞኝ አላህ አያዋርድህም !!! ዘመድን ትቀጥላለህ ደካማን ታግዛለህ ... መፍትሄም ፍለጋ ወደ አጎቷ ይዛቸው ሄደች... የፍቅር ጥግ ... ኸዲጃ ሰለፍሽ አንቺ ሰለፊይ ወላሂ የሆነ ደስስስስስስስ የሚል ስሜት ይሰማል ስለ ሁለቱ ስታወራ ስለ ሁለቱ ስትሰማ ... ያ አላህ ከእነርሱ ጋር ቀስቅሰን እህቴ ሰለፍሽን ኸዲጃን ምሰይ ✍ አቡ ሙስዐብ https://t.me/Jebrilsultan/3725
إظهار الكل...
🚧 ሼር ሼር ሼር ሼር 🚧 📮 እውነት መውሊድ ኡለማ ፈቅዶዋልን? 🔄 ስለመውሊድ ኢብኑባዝ ኢማሙ አልባኒ ሸህሙቅቢል رحمه الله ሸህ ፈውዛን ሸህ የህያ حفظه الله ምን አሉ? 📮 ስለ መውሊድ ኡስታዞች ምን ንብለዋል? 🔄 መውሊድ ማክበር እውነት ነቢዮንﷺ መውደድ ነውን? 🔄 መውሊድ ማክበር ቢዳአዓቱል ሀሰናት ነውን? 🔄 እስልምና ላይ ቢዳአቱል ሀሰናት የሚባል ነገር አለን 🔄 ዛሬ ላይ መውሊድ ብለው የሚያከብሩት እውነት መልክተኛውﷺ የተወለዱበት ቀን ነውን? 🎙️ በኡስታዝ አቡ ቀታዳ አብደላህ ቢን ሙዘሚል አላህ ይጠብቀው። 🔄 ነቢዩን ﷺ መውደድ ብሎ ማለት ምን ማለት ነው ? 🔄 መውሊድ ማንመች የት ነው የተጀመረው 🔄 መውሊድ እና ሹባሀዎቹ 🔄 መንዙማ እና መዘዞቹ 🎙️ በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጠፋ አብደላህ አላህ ይጠብቀው። 📮 ከ24 በላይ ድምፆችን በአፕልኬሽን አንዴ በማውረድ ሁሌ ያዳምጡ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ። https://t.me/islamic_app_omi/15 https://t.me/islamic_app_omi
إظهار الكل...
መውሊድ በኢስላም መነፀር v1.0.apk87.47 MB
👍 1
ያልተነበበ ታሪክ ወንድሜ ልጁ ሙስሊም ለዛውም 20_30 ባለው የእድሜ ክልል ላይ ነው ያለው መጀመሪያ ቀጥታ የትዳር ጥያቄ ጠየቀኝ እኔም ከመቀበሌ በፊት ኢስቲሃራ ሰግጄ ማማከር ያለብኝን ሰው አማክሬ ከዛም ለቤተሰቦቼ የሆነ ልጂ እንዲ እያለኝ ነው አልኳቸው ከዛም እሱን አጣርተው ቤተሰቦቹን አይተው ይሆናል ጥያቄው ተቀበዩ አሉኝ በእርግጥ ልጁ ሰለፊያ መንሃጅ ላይ አልነበረም ግን መለወጥ እንደሚፈልግ መድረሳም አብሮኝ እንደሚሄድ በአሏህ ስም ምሎልኝ ነበር ደሞ ብዙ ነገራቶችን መተውና ወደ ሱና መጠጋት ጀምሮ ነበር ግን ኒካ ታስሮ እቤት እንደገባሁ ነገራቶች በጣም ተቀየሩብኝ። 1,መድረሳ አቁሚ አለኝ 2,ሁዙ አቂዳ የጀመርኩላቸው እህቶች ነበር እሱንም አስቆመኝ 3, አንፎ የነ ኢብኑ ሙነወር ደርስ እሱንም አስቆመኝ ። 4, ጓደኞቼን ሙሉ እንድርቅ አዘዘኝ እንዳሌድም እንዳይመጡም አደረገኝ ከዛም ከተወሰኑ ቀናቶች በኋላ ሂክማ ወንድሞቼ የራቁኝ ባንቺ ምክንያት ነው አለኝ ምን አጠፋሁ እንዲ ተሸፍና እንዴት እንመጣለን አሉኝ አለኝ ። እኔም ከዚህ በፊት ነግሬሃለው እኔ በኒቃቤ ብዙ ፊትና ደርሶብኛል እናም ቤተሰቦችህ ይቀበሉሃል ወይ ስልህ እኔ ኒቃብሽ አይቼ ነው የመጣሁት እነሱ አይመለከታቸውም አላልከኝም ወይ አልኩት ። ነበር ግን እነሱ አልተቀበሉኝም እኔም ያለ እነሱ መኖር አልችልም አለኝ እና ስለው ለወንድሞቼ ብቻ ተከፈቺ አለኝ ላንተ ወንድሞችህ ናቸው ግን ለኔ አጅነቢ ናቸው ይህ አይሆንም አልኩት በቃ በዚህ ብቻ እየጨቀጨቀኝ 4 ሞላን ከዛ በኋላ አንድ ተብሊግ ወንድሙ ከ4ወር ሁሩጅ ተመልሶ ታኮ ገባለት ነገሮች እየተባባሱ መጡ ምንም አልሸነፍ ስለው ለእህቴ ነገራት ሰለፊ አደለችም ግን እሷም እኔን ማሸነፍ እንደማትችል ነገረችው ታላቄ እህቴ ናት። ከዛም ታናሽ ወንድሜ አለ እሱ ሰለፊ ነው የሆነ ቀን በዚ ጉዳይ ሳለቅስ መጣ ምን ሆንሽ አለኝ ያለውን ነገር ነገርኩት አብሮኝ አልቅሶ ለባለቤቴ ማናገር ጀመረ ምን እያልካት ነው አለው ወንድሜ የ16 አመት ልጅ ነው ከዛም እስከዛሬ እያለኝ ያለውን አለው። ወንድሜም ይህ በፍፁም አይሆንም ኒቃብዋ ብትፈታ ካንተ ወይም ከኔ አሊያም ከመላው ቤተሰብ አደለም ምትጣላው ከአሏህ ነው ከአለማቱ ጌታ ባይሆን ወንድሞችህ እውቀት ከሌላቸው አምጣቸውና ታስረዳልህ አለ። አልተቀበለም አንድ ጅህልና ላይ ያለ ታላቅ ወንድም አለኝ እሱጋ ሄደ እሱ ደሞ በግዜ ሂደት ልጅ ሲመጣ ታሸንፋታለህ አሁን ተዋት አለው ለኔ ደሞ ዲኑን በማይጋጭ መልኩ ቅረቢያቸው እቤት እንዲመጡ አርጊ አለኝ እሺ ብዬው አሪፍ መቀጠል ጀመርኩ ግን ረመዷን ሲገባ ነገሩ በጣም ከበደ ተብሊግ ወንድሙ አብሮን መኖር ጀመረ ሁለት እህቶቹም አሉ በቃ አንድ ሆኑብኝ ጭራሽ አብሮት መቃም መንዙማ በጣም ሚያስጠላ ሁኔታ ላይ ደረስን ከዛም አንድ ቀን ወንድሙ ለሊት እየቃሙ ልምከራቹ ብሎ ብዙ መጥፎ ነገራቶች አነሳ አንቺ እና ባልተቤትሽ እልህ ነው ምትያያዙት እሱ ቲቪ ሲከፍት አንቺ ኪታብ ነው ምታነቢው ስልኩ ላይ ሲሆን ቁርአን መንዙማማ ሲሰማም ሌላ ነገር ላይ ነሽ አለኝ። ይህ እኮ እራሱ ፈቅዶልኝ ነው እኔ በሌላ ነገር ቢዚ ስሆን ቂራትሽ ተከታተይ ብሎኛል ቀን አብሬው ስራ ነው ምውለው ለዲኔ ሚሆን ግዜ የለኝም አልኩት ብቻ ወንድሜ ምንጣላበትን መንገድ ያለው ሁሉ አነሳ የባለቤቴ ጓደኛ ጋር ብዙ ሰው ያፈጥራል እዚ ሰው ማይመጣው አንቺን እንዲ ስለተሸፈንሽ ነው እኔ ፍቺ አትፍቺ አልልሽም ሁለታቹ ልታወሩበት ሚገባ ጉዳይ ነው ብሎ አያይዞ ተወን ። ከዛም ብዙም ሳይቆይ አንድ ለሊት ላይ ከነገ ጀምሮ ኒቃብሽ ፈተሽ አብረሽን ከወንድሞቼ ጋር ማታፈጥሪ ከሆነ ወደ ቤተሰቦችሽ ሂጂ ይህንን መንገድሽ ሚያከብርልሽን ማግባት ትችያለሽ አለኝ ዝም አልኩት ብዙ አወራ ከዛም ስሚ እኔ እወድሻለው አከብርሻለው ላንቺ የተለየ ቦታ አለኝ ግን ኒቃብሽ ወንድሞቼን አርቆብኛል ስለዚህ ወይ እኔን በይ ወይ ኒቃብሽን በይ አለኝ እኔም በማግስቱ ወደ ቤተሰብ ሄጄ ምርጫ ሰቶኛል እናም ሂጃቤን መርጫለሁ አልኳቸው !!! የአሏህ ውሳኔ ተፈፃሚ ሆነ ወንድሜ ከትዳሬ ኒቃብ መርጫለሁ አንድ ነገር ላስቸግርህ እህቶችን አማና በልልኝ ወደሱና እገባለሁ የሚል ወንድ የፈለገ ቢምል እንዳያምኑ ምክንያቱም መሃላን ማጠፍ በጣም የቀለለበት ዘመን ላይ ነን ለጉንችሬ እህትቼ ደሞ የእናንተው አይገርምም በአሏህ ከካዱ ጠላቶች በግልፅ የመጣ ነው ይኸው የኛን ስም ይዘው ወደኛው ቂብላ ከሚሰግዱ ሰዎች ይህንን አስተሳሰብ አለ በርቱልኝ በልልኝ በዚሁ አንደበትክ ደሞ ለትዳር ተብሎ ባል እስካልፈለገው ድረስ ኒቃብ ማውለቁ ግዴታ ነው ብለው ሚያወሩ ሰዎች አሏህን ፍሩ በልልኝ ምክንያቱም ከባለቤቴ በላይ ሲጎተጉቱኝ የነበሩ ደካማ ማስረጃ እየዘረዘሩልኝ የነበሩ እራሳቸው ወደ ሱና ያስጠጉ ግን በተግባር ያልገቡ ሰዎች በጣም ብዙ ነበሩ እናም አንቺ ከእገሌ በእውቀት ትበልጫለሽ አንቺ የያሹ መንገድ የተሳሳተ ነው ስባል ነበር ፈትዋ መስጠት በጣም ቀሏል እህቶችም ነቃ በሉ በልልኝ ለእነዚህም አሏህን ፍሩ በልልኝ አሂ ። ✍ የሱና እህታችሁ ሂክመት ቢንት ኸድር ከአዲስ አበባ
إظهار الكل...
👍 1
ፍቅር ምን ማለት ነዉ? ፍቅር ምንድ ነዉ ? 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ፍቅር ማለት አንድን ሰዉ በስሱ መዉደድ ማለት ነዉ 1 ፍ ላፈቀርከዉ ሰዉ ፍርሀት ማለት ነዉ 2 ቅ ላፈቀርከዉ ሰዉ ቅን መሆንና ያንተ ባይሆንም እንዃን በሱ ደስታ መደሰት ማለትንም ያካትታል 3 ር ደሞ ለፍቅርህ መራራትና ማዘን ያፈቀርካትን ሴትም ሆንሽ ወንድ ህመሟን መታመም ለወንድ ብቻም አደለም ሴቷም ብትሆኚ የሱን ህመም መታመም መቻል መሞከር አለብሽ።።። ነገር ግን ብዙዎቻችን ይህንን ነገር አንተገብረዉም ለኛ ፍቅር መስሎ ሚታየን  በቃ አስተሳሰባችን ፍቅር በእዉነታዉ አለም የለም በፊልም ብቻ ነዉ ብለን እናምናለን ለኛ የተፈጠረዉን ሰዉ ላለመቀበል እንፈልጋለን ነገር ግን ሁላችንም ልብ ብለን መረዳት ያለብን ነገር ቢኖር ፍቅር አለ አፍቃሪዉ ሰዉ ግን ከ100% 25 ብቻ ነዉ ያለዉ አንተ ወንድ ሆይ ላንተ ያላት ሴት የትም አትሄድም በእርግጠኝነት ወደአንተ ትመጣለች ነገር ግን እሷን እስክታገኝ ያቺ ላንተ የተፈቀደችዉን ሀላልህን ሀዋህን እስክትመጣልህ ድረስ ለምን በሌላዋ ሴት ሂወትና ስሜት ትጫወታለህ አንተ በስሜቷና በሂወቷ የተጫወትክባትን ሴትኮ አንተን ስለወደደችህና አንተን ከማጣት ብላ ሊሆን ይችላል ሁሉን ነገር አሜን ብላ ምትቀበልህ እሷኮ ምናልባትም ሌላ ሚወዳትና ሚያፈቅራት ወንድ ሊኖር ይችል ይሆናል ነገር ግን ልብ በልህ አዳምጠኝ አንዲት ሴት ስትወድህ ላንተ ብዙ ነገርህ እንደምትሆንህ አትጠራጠር እሷ ከወደደችህ በፍቅርህ ካመነችብህ ከአባቷም አስበልጣ ልትሞትልህም እንዃን ትችላለች ልብ በል ከወንድሟ አደለም ከአባቷ ነዉ እያልኩህ ያለዉት ነገር ግን የዚህን ያህል ወዳህ አንተ ካልወደድካት ስሜቷን አትጉዳዉ ከቻልክ አንተም ለመዉደድ ሞክር ነገር ግን ሙከራህ ካልተሳካ ስሜቷን ሳትጎዳና ሳታስከፋት ከዚህ ስሜት ምትወጣበትን መንገድና መፍትሄ ምረጥ ። ይሄንን ተግባር ካከናወንከዉ አንተ ማለት ከምርጦቹ ምርጥና ከአክተሮቹ መሪ አክተር ነህ ማለት ነዉ
إظهار الكل...
"እስኪ ተሰተሪ" ንግግርሽ አንሶ ቁምነገርሽ ይብዛ ግዜሽን አትፍጅ በዋዛ ፈዛዛ አውቃለሁ ብዙ ነው የሚዲያ ፊቲና ከዚህ ሁሉ ጥንቁቅ ምትሆኚው ጤና ስትርቂ ነው እህት ሰላም የምታገኘው በጌታሽ ትእዛዝ አውቀሽ ምትኖሪው ሁሌም ተናፋቂ የሱና ተከታይ መንገድሽ አጥብቂ በተግባር ታገይ በተውሂድ በሱና ሆነሽ መንገደኛ ዘለቄታ ባለው ዘላለም መዳኛ መሰናክል ገጥሞ ሳይጥልሽ በመንገድ ራስሽን ለጉሚ በሸሪአ ገመድ ጠብቂ አማና ረሱል ያወረሱሽ የሴት መገለጫ ሀያእ ነው እንዳሉሽ እንኳንስ በገሀድ በቤታችንም ቢሆን ልናወራ እንጂ ድምፃችን ዝቅ አርገን አልታዘዝንም ከቶ ልንጮህ በጋራ አደባባይ ወተን ልክ እንደ ባዲራ መውለብለብ አቁሚ ወተሽ በሚዲያ በሆነው ባልሆነው ፈጥነሽ በቅድሜያ መታየት ይቅርብሽ ስሚ እህት አለም ያላቀሽ ኢስላም ነው በሀያእ ዘላለም ሀያዕን የሚረግፍ ንግግር እወቂ ወሬ ሳቅና አሻንጉሊት ፍፁም አትልቀቂ እስቲ ተሰተሪ ውስጥ ላይሽ ይመር ሙእሚኗ እህቴ ሒወትሽ እንዲያምር!
إظهار الكل...
,   #ፊት_ነው_የደፈረሽ_!! ሉአላዊይ ውበት፣ ክብርሽን ጣልሽና አደባባይ ወጥተሽ ጀምረሽ ጅንጀና ደረት ታፋ ሳይቀር ነግቶ ከጎበኘው በየ ሚዲያው ላይ ወይ በየ ጎዳናው ዳሌሽን ወጥረሽ ዘና ብሎ ካየው በፀጉርሽ ተማርኮ ልቡን ካረካበት ምን ቀረው መሰለሽ ተደፍረሻል በእውነት በዚህ መልክ ደፍሮሽ ካበቃ በኀላ ጅምሩን ሊጨርስ መጣብሽ በገላ በአሰቃቂ ጫና በጣም በሚያስጠላ። subhanallah ያረብ ሰትረን
إظهار الكل...
በብዙ ሰዎች መወደድ ብርቅ የምመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ ከነሱ እንዳትሆን እንዳትሆኚ እንዳንሆን ጥንቃቀ አናርግ ያው ለላ ነገር እንዳይመስላቹ ፈተና እንጂ ። ጀብድ የምመስለው ይኑር እኔ አላውቅም እኔ የማውቀው ፈተና እንደሆነ ብቻና ብቻ ነው።በብዙዎች ስለተወደድን እና ስለተፈለግን ብቻ ከለሎች የመሻለችን መለያ እንዳይመስለን ከመሰለን ተሳስተናል እንዳይመስለንም አሉ ብዙ የአላህ ባህሮች ማንም የማያውቃቸው ትንፋሻቸውን አጥፍተው የምኖሩ አበት የነዚ እደለኝነት ይለያል እራሳቸውን ዝቅ አድርጎ ተደብቀው የምኖሩት እና የምሰሩትስ ምን አይነት መታደል እንደሆነ አስብት። ጠንቀቅ በል/ይ ወንድም አንቺም እህት ዋናው መስፈርትህ/ሽ/ታችን ሰዎች ዘንድ መወደድ ሳይሆን አላህ ዘንድ መወደድ ይሁን ገባህi ገባሽ! አዎ ብዙ ሰዎች ልወዱን ይችላሉ በብዙዎች እንፈለግ ይሆናል ብሆንም በብዙዎች መፈለጋችን ከመስመር እንዳያወጣን እንዳያዘናጋን ከዋናው አላማ ከትልቁ ግብ አይሸንግለን እሱም የአላህ ውደታ የህወታችን ትልቁ ግብ ይሁን ።ውዳጆቸ እንንቃ ሁለም ለምን እንተኛለን ለምን ኒቁ መሆን አቃተን እኛ የማንነቃ ሁነን ነው ?ወይስ ቸለተኛ ሁነን መልሱን ጥያቀው ለገባው ትቻለው በደንብ ይታሰብበት በተለየ መልኩ ነቃ በሉ ነቃ እንበል ማንቀላፋት እስከ መቸ በተለይም የቻናል ባልተበቶች ጋ ለየት ያለ ክፍተት ስለታየኝ ነው ክፍተቱ እነን ብቻ ይታይ ወይም ለላ የታየውም ይኑር ¿ሰዎ ከበፊቱ በተለየ መልኩ እራሱን ዝቅ እያደረገ መተናነሱ እየጨመረ የትልቅ አላማ ባለበት እንደሆነ እየተሰማው ይመጣል ስባል ጭራሽ መዘናጋት ¿! ምን ይሁን ምክንያታችን ያኢሊሂ ሰትረን ማረን መልክቱ በቅርብ ለማውቃቹ ነው ደውል እንድሆነን በማሰብ ነው ነቃ እንበል ነቃ በሉ አናንቀላፋ ! ምንም ከማታውቀው እህታቹ
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.