cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

FDRE, Ministry of Labor and Skills

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
25 292
المشتركون
+1824 ساعات
+2377 أيام
+73630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የገጠር ሥራ ስራ ስምሪት አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ማሻሻያ ኘሮጀክት ሥራ ማስጀመሪያ መድረክ ተካሄደ። በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ለማገዝ በጣሊያን ልማት ድርጅት ድጋፍ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካኝነት የሚተገበረው ይህ ኘሮጀክት ሥራ ያስጀመሩት በሚኒስቴሩ የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ናቸው። ኘሮጀክቱ በፓይለት ደረጃ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልሎች በሚገኙ 16 የሥራ ስምሪት ማዕከላት ተግባራዊ ይደረጋል። በኘሮጀክቱ ከ11 ሺህ በላይ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጠር ሲሆን በክልሎቹ የተመረጡ 16 የሥራ ስምሪት ማዕከላት ለሥራ ምቹ ለማድረግ በአዲስ የመገንባት ስራ፣ በቁሳቁስ የማሟላት እና የማዘመን ስራም ይከናወንበታል ተብሏል። በኘሮጀክቱ ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ፤ ኘሮጀክቱ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙባቸው አካባቢዎች መነሻ በማድረግ በሙከራ ደረጃ ቢጀመርም ውጤታማነቱ ታይቶ እንዲሰፋ ይደረጋል ብለዋል። በኘሮጀክቱ የሚደገፋ በማዕከላቱ የተመዘገቡ ስራ ፈላጊዎች ከክህሎት ተቋማት በማስተሳሰር  የህይወት ክህሎት ስልጠና፣ የኢንተርኘረነርሺኘ ስልጠና እና በመረጡት ሙያ የክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል ሲሉም አክለዋል። ስልጠና ያገኙ ወጣቶችም ከኢንዱስትሪዎች የማስተሳሰር ስራ፣ በግል ስራ ተደራጅተው እንዲሰማሩ እና ከፈለጉም በቅጥር የስራ እድል እንዲያገኙ ሁሉአቀፍ ድጋፍ እንደሚደረግም አብራርተዋል። በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑት 50 በመቶ ሴት ወጣቶች መሆናቸውን ገልጸው የታለመለትን ግብ እንዲመታ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እና ትብብር ይጠይቃል ብለዋል። ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 44 13👏 8
የመንግሰትና የግሉ ዘርፍ በትብብር  ለሚሰጡት  ተግባር ተኮር የቴክኒክና ሙያ  ስልጠናዎች በመንግስት በኩል  ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው   ተገለጸ ሀገር አቀፍ  የቴክኒክና ሙያ ትብብር ሥልጠና ብሔራዊ ኮንፍረንስ በአዲስ አባባ መካሄድ ጀምሯል፡፡ በኮንፈረንሱ   ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር  የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ  ሚኒስተር ዴኤታ  ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ   እንደገጹት  የትምህርት ስልጠና  ማዕከላት  ክህሎትና  ብቃት ያላቸው ሰልጣኞችን ማፍራት ይጠበቅባቸዋል፡፡  ለዚህም የግሉ ዘርፍ የሚጠቅበትን ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል። የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ  ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ያመላከቱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ይሄም ሊበረታታ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ የመንግሰትና የግሉ ዘርፍ በትብብር  ለሚሰጡት  ተግባር ተኮር የቴክኒክና ሙያ  ስልጠናዎች በመንግስት በኩል  ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠውም አመላክተዋል። ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
إظهار الكل...
👍 7 5
05:07
Video unavailableShow in Telegram
Building a Brighter Future
إظهار الكل...
33.77 MB
👍 22 9🙏 1
ሚኒስቴሩ የፋይናንስና የግዢ ሥራዎችን ማሳለጥ የሚያስችል ስልጠና ሰጠ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አገልግሎት አሠጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ ሥራዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። በዚህም በሥራ ላይ ባሉት IFMIS እና EGP ሲስተሞች ላይ ተግባር ተኮር ስልጠና ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሰራተኞች ሰጥቷል። በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት በተሰጠው በዚህ ስልጠና የግዥና ፋይናንስ እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች እና ፀሀፊዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ስልጠናው መሰረታዊ የበጀት፣ የፋይናንስና የግዢ ስራዎችን ላይ ወደ ስራ መግባት የሚያስችላቸው እንደሆነ ገልፀዋል። ግንቦት 21/2016 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
إظهار الكل...
16👍 13👌 1
ህብረተሰቡ ስምምነት ወዳልተደረገባቸው ሀገራት ለሥራ እንልካለን ከሚሉ ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና አጭበርባሪዎች ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ ተጠቆመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሀገር ውስጥ ሥራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን በዓለም አቀፍ በደረጃ የሚገኙ የሥራ ገበያ ዕድሎችንም በአግባቡ ለመጠቀም ሰፋፊ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ የምንከተል እንደመሆኑ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎች መብት፣ ደህንት እና ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ እንዲሆን ተደረጓል፡፡ በዚህ ሂደት ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ብቻ 304 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ስምምነት ወደተደረገባቸው አራት ሀገራት ህጋዊ ስምሪት እንዲያገኙ መደረጉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል፡፡ በአንፃሩ ካናዳን ጨምሮ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ወዳልተገባባቸው ሀገራት ለሥራ እንልካለን የሚሉ ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡን ላልተገባ ወጪና እንግልት እየዳረጉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሰል ህገ-ወጥ ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ ጥብቅ ክትትልና እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ህብረተሰቡም መሰል ስራዎችን የሚሰሩ አካላትን በማጋለጥ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡ በዘርፉ የመዳረሻ ሀገራትን ለማስፋት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አዳዲስ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ስምምነት የሚደረስባቸውን ሀገራት ሲኖሩ በይፋ ለህብረተሰቡ የሚገለጽ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዝርዝር በሚስቴር መስሪያቤቱ ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ የተቀመጡ መሆኑንም ነው ክብርት ሚኒስትር የገለጹት፡፡ ስምምነት ወዳልተደረገባቸው ሀገራት ለሥራ እንልካለን ከሚሉ ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡ ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አሳስበዋል፡፡ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ጆርዳን እና ኳታር እስከ አሁን ድረስ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ስምምነት የተገባባቸው ሀገራት ሲሆኑ በህጋዊ መንገድ ወደ ቤሩት ለመላክ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምምነቱ በቅርቡ የፀደቀ በመሆኑ ወደ ሥራ የሚገባ መሆኑን ገልፅዋል። ኩዌት ስድስተኛው ህጋዊ የሥራ ስምሪት ለማካሄድ ስምምነት የተደረሰባት ሀገር ሆናለች፡፡ ይሁን እንጂ ስምሪቱ ተግባር ላይ የሚውለው በህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት መፅደቁን ተከትሎ ይሆናል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ግንቦት 21/2016 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 61 10👏 2🤩 2
إظهار الكل...
የዜጎችን መብትና ክብር በማስጠበቅ በውጭ ሀገራት የሚሰጠው ህጋዊ የሥራ ስምሪት  ተጠናክሮ ይቀጥላል -  ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2016(ኢዜአ)፦ የዜጎችን መብትና ክብር በማስጠበቅ በውጭ ሀገራት የሚሰጠው ህጋዊ የሥራ ስምሪት ትርጉም ባለው መልኩ ተጠናክሮ እንደሚ...

👍 65 21👏 7
ውይይቱ በአፍሪካና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ የሠራተኞች እንቅስቃሴ እውን ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተጠቆ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤ ተሬሳ የተመራ ልዑካን ቡድን በ‹‹ዶሃ ውይይት›› ያደረገውን ተሳተፎ አጠናቆ ተመልሷል፡፡ በመድረኩ የሠራተኞች እንቅስቃሴን ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ ከማድረግ ባለፈ በላኪና ተቀባይ ሀገራት መካከል ፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታና የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አስተዳደር አስፈላጊነት ላይ ሰፊ ውይይት እንደተደረገ የልዑካን ቡድኑ አመላክተዋል፡፡ በኳታር ዶሃ የተካሄደው ይህ ውይይት በአፍሪካና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ የሠራተኞች እንቅስቃሴ እውን ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነም ነው የልዑካን ቡድኑ ያመላከቱት፡፡ በመድረኩ ዮርዳኖስ፣ ሊባኖስ፣ እና የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት አባል ሀገራት እና የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ የ33 ሀገራት ተወሃዮች እናሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳትፈውበታል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ግንቦት 19/2016 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
إظهار الكل...
👍 30 10🤩 5
በሀገራችን በቤቱ መብራት የማይጠፋበት ብቸኛው  ወጣት ድምጽ አልባ እና ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የማይጠቀም ጄኔሬተር ይኖራል ብለው አስበው  ያውቃሉ?  በአካባቢዎ  ለረዥም ጊዜ መብራት ቢቋረጥ ስልክዎም ሆነ ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችዎን ቻርጅ ለማድረግ ከሶላር አማራጮች ውጪ የሆነ ቴክኖሎጂ አገኛለሁ ብለው አስበውስ ያውቁ ይሆን? ይህ ለብዙዎቻችን የማይቻል የሚመስል ነገር ቢሆንም በእኛው ሀገር ወጣቶች ተችሏል ብንልዎትስ ያምኑ ይሆን? ካላመኑ ብዙዎች ለማመን ከብዷቸው አይተው ነውና ያመኑት እርስዎም እስኪያዩት ድረስ በሀይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት መፍጠር የሚያስችለውን ቴክኖሎጂና የቴክኖሎጂውን ባለቤት እናስተዋውቅዎ፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው ልዩ የክረምት ወራት የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሀ ግብር  ካሰባሰባቸው ወጣቶች አንዱ ነው። ፈዴሳ ሹማ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ነው፡፡ በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያውም ብዙዎች ያውቁታል፡፡ ሥራው ጥገና እንደመሆኑ የመብራት መጥፋትና መቆራረጥ ሥራውን ብዙ ጊዜ ያስተጓጉልበታል። ችግር ብልሃትን ይወልዳል እንዲሉ ወጣቱ ለችግሩ መላ መዘየድ እንዳለበት አሰበ፤ አስቦም ወደ ተግባር ገባ። ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ግዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ። ፈዴሳ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚመራው በልዩ የክረምት ወራት የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሀ ግብር ተሳትፎው ባገኘው ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ቴክኖሎጂውን ይበልጥ አዘምኖ መስራት ችሏል። ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠቱ ባለፈ  ሞባይል ፣ ለቴሌቭዥን፣ ፍሪጅና የትኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስና በገመድና ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሰራ ነው። አንዴ የያዘውን ሀይል ሪሳይክል እያደረገ ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ሀይል ማመንጨት የሚችለው ይህ ቴክኖሎጂ በሀገራችን ብቻ ሣይሆን ምን አልባትም በዓለማችን ላይ በሀይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት መፍጠር እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል። ከ300 ዋት ጀምሮ እንደ ተጠቃሚው አቅምና ፍላጎት የሚዘጋጀው ይህ ድምፅ አልባ ጄኔሬተር አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ነው ወጣቱ ያረጋገጠው። በዚህም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በቤቱ መብራት የማይጠፋበት ብቸኛው ሰው ለመሆን ችሏል። አሁን ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወጣቱ የራሱን ካምፓኒ የሚከፍትበትንና  ቴክኖሎጂው በስፋት ተመርቶ ለህብረተሰቡ ማድረስ የሚቻልበትን ሁኔታ ላይ እየሠራ ይገኛል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ግንቦት 17/2016 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 83 20👏 9🙏 5
በፈጣን ምግብ ዝግጅት ለሰለጠኑ ሴት ሠራተኞች ሥራ ማስጀመሪያ የሚሆን የማብሰያ የቁሳቁስ  ስጦታ ተበረከተ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ከቱሪዝም ኢኒስቲትዩትና ስትሪፕ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በፈጣን ምግብ ዝግጅት ላሰለጠናቸው 25 ሴት ሠራተኞች ሥራ ማስጀመሪያ የሚሆን የማብሰያ የቁሳቁስ  ስጦታ አበረከተ፡፡ የቴክኒክና ሙያ  ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ስጦታዎቹን ባበረከቱበት ወቅት  ባስተላለፉት መልዕክት ሰዎች ሥራቸውን፣ ተቋማቸውንና ሀገራቸውን ወደው መስራት  አለባቸው የሚል መርህን የሚከተለው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተመሰረተበት ማግስት ጀምሮ ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለመላ ሠራተኞች የቢዝነስና እና የፐብሊክ ኢንተርፕሪነረሺፕ ሥልጠናን በመስጠት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሥራውን መጀመሩ የዚህ ማሳያ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል፡፡ ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ሴት ሠራተኞች የመደበኛ የሥራ ሰዓታቸውን በማጎይዳ መልኩ ተጨማሪ ገቢ በሚያስገኝ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ  የተደረገላቸው የስልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ የኑሮ ጫና የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚያስችል አቅምን በመፍጠር በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚበረክትም  በመድረኩ ተብራርቷል፡፡ ሴት ሠራተኞቹ ያገኙትን ድጋፍ በመጠቀም ለሌሎች ሠራተኞችም አርአያ ለመሆን መትጋት እንደሚኖርባቸው ያሳሰቡት  ኩቡር ደ/ር ተሻለ በሬቻ  በቀጣይም ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡    በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ በዕለቱ በተዘጋጀው መድረክ በተግባቦት ክህሎትና በሥርዓተ ፆታ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሃንስ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የተግባቦት ክህሎትን ማዳበር  ሴት ሠራተኞች በተሰማሩበት ሥራ ዘርፍ ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ ከማስቻል ረገድ ጉልህ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን መነሻ በማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡ ሥራ አስፈፃሚው የሴት ሠራተኞችን አቅም የሚያሳድጉና ተወዳዳሪነታቸውን የሚጎለብቱ ሥልጠናዎችን በቋሚነት መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ወ/ሮ እርቅነሽ ገልፀዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ግንቦት 15/2016 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 26 12