cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መረጃ ትምህርት መዝሙር ግጥም ይገኝበታል በተጨማሪም ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🙏1) የመዝሙር ግጥምና ዜማ ለምትፈልጉ በፈለጉት አይነት እና ቋንቋ 2) ቪዲዮ ክሊፕ መስራት ለምትፈልጉ (የመ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
8 739
المشتركون
-824 ساعات
+267 أيام
+1 43730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 . 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር አንተ ማን ብትሆን ነው?                የቅላፄህ ውበት     እጄን እንድሰጥህ ቃላትህ ማረከኝ               የአንደበትህ ለዛ      የመልክህ ፍሰት ስሜቴን የገዛ     ፍቅርህ ተሰንቅሮ ፀርሶ ልቤ ላይ    ጥልቅ ፍቅር የያዘኝ ካንተ የማይለየኝ          አንተ ማን ብትሆን ነው?              ሚስጥሩን ንገረኝ            በየትኛው አቅም እንዴት        ባለ ጥበብ ስስ ነፍሴን ቃኘኸው           እንዴት ብትበረታስ አለቱን         መንፈሴን በድል አገኘኸው                   እስቲ በል አስረዳኝ             ሚስጥሩን ንገረኝ          አንተ ማን ብትሆን ነው              ልቤን የረታኸው            የጨረቃን  ውበት            የፀሀይን ድምቀት              የአበባን ፍካት          የመውደድን ጥጋት   የፍቅርን ሸማ በላይህ ደርበህ             ልቤንም የሰረክ         አንተ ማን ብትሆን ነው?             ሚስጥሩን ንገረኝ ✍️ብሌን ስንታየሁ ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት 🏆🏆🏆 ለመቀላቀል 👇👇👇 t.me/zemaritnsae 🏆🏆🏆🏆🏆 ግጥም ለመላክ . 👇👇👇 . @Tins7
إظهار الكل...
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መረጃ ትምህርት መዝሙር ግጥም ይገኝበታል በተጨማሪም ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🙏1) የመዝሙር ግጥምና ዜማ ለምትፈልጉ በፈለጉት አይነት እና ቋንቋ 2) ቪዲዮ ክሊፕ መስራት ለምትፈልጉ (የመ

2
👍
👎
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 . 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር ይህችን አመት ተወኝ አልጉደል ከቁጥር ባይጥምም ስራዬ ይህችን አመት ብቻ አኑረኝ ጌታዬ ሁሉን እያሟላህ አንዳች ሳይጎድልብኝ ቅጠል ነው ዙሪያዬ ፍሬ ስትሻብኝ ምን ጎደለ ከእጅህ ለወይንህ ዘለላ ነጠፈች ከፍሬ ቢመቻትም እንኳን ብትኖርም በተድላ ልክ እንደመሻትህ በሀሳብህ ባልገኝ በመላዕኩ ምልጃ በእመብርሀን ምልጃ ይህችን አመት ማረኝ ደግሞ ለቀጣዩ ቆሜ እንድለማመን የምህርትህን ካባ አልብሰኝ ነጭ ልብስ ደጅህ እንድገባ እንጅማ እንጅማ ገሸሽ ካለብኝ የለበስኩት ኩታ ነጩ ነጠላዬ ለሰው የሸሸኩት ወጥቶ የሚያሳጣኝ ጉድ አለ ጀርባዬ የእግሬን ኮቴ ብቻ እየተከሉ የሚያሞጋግሱኝ ከልቤ ጥቂቷን ብትገልጥላቸው ... እንዴት ባለ ቃል ነው ስሜን የሚያነሱኝ ታዘበኝ እንግድህ ሁሉን እያሟላህ ከአትሮኖስህ ከመንበር ብታቋቁመኝም ፍሬ አልባ ነኝ አንድ አልጠቀመኝም ታዘበኝ እንግድህ ዘውትር ሲፈተት ስጋህ ቤተመቅደስ አለሁ ስጎሳቆል በርሀብ ጠኔ ሳለቅስ ታዘበኝ እንግድህ ቅዱስ የሆነ ደምህ ሰርክ እየነጠፈ ተጠማሁ ነው ቃሌ ምንጭ ይለማመናል ዥረት እያለፈ ታዘበኝ እንገድህ መሰቃያ ያልኳት ገመዷ ብትመክረኝ ለንስሀ የሚሆን ጥቂት ጊዜ አጠረኝ ታዘበኝ እንግድህ ቅዱስ ቤተመቅደስ ብታደርገው መልኬን ከሚዛን አይቀርብም ክቡድ ነው ሸክሙ የመከፋት ልኬን የዘወትር ልመና ሰርክ ጥያቄዬ የምመፃፀነህ ይሄ ነው ጌታዬ ምን ይዤ ነው የምጠብቅህ በምን ልኬ ልሰናዳ ታውቀው የለ የእኔን ጉድለት ግልፅ አይደለ የኔ ጓዳ ሳልዘጋጅ በንስሀ ስጋ ደምህ ሳይገነባኝ የመምጫህ ቀን የሚገለጥ ምን ገፅ አለኝ እያወከው ጉልድፍ እግሬን አካሄዴ የተምታታ እስከመቼ አንገድ ልድፋ እንደወጣሁ ከሰው ተርታ ጥዑም ጠረን እያማረኝ የሚስማማ ለመቅደስህ ጎልዳፋ ነው የእኔ ምላስ በምን ከንፈር ላወድስህ እድሜ ገፋሁ ሸበት ሞላው መላ አካሌ ከእድሜ እኩል 'ማስመስለው በምላሴ መሸንገሌ ተጎተትኩኝ ወደሀጥያት ተዘነጋኝ የዋልክልኝ አፍካው ልቤን በመንፈስህ ታሪክ መልኬን ቀይርልኝ ተጨነቀች ድኩም ነፍሴ በርትቶባት ሀጥያት ሸክሟ አቅርቅራ ጉዞ ሆነች እያስማጣት ክፉ ህመሟ ይብቃሽ በላት ይህችን ነፍሴ አለምልመኝ በመንፈሰህ ተቀይሮ የሀጥያት ልቤ ምሉዕ ሆኜ ላወድስህ እስከመቼ በሀጥያት ጎጆ በደል ኩራዝ እንዳበራሁ የሀጥያት ጣሪያ እያቆምኩኝ የሀጥያት ቤት እየሰራሁ ይሄን መልኬን ታውቀዋለህ ሸፍኖት ነው ነጭ ነጠላ ጥቁርነት ያጠለሽው ውበት የለው ከአንተ ሌላ የግድ የግድ ደጅህ ቆሜ ስላነባሁ የግድ የግድ ከማህሌት ስለገባሁ የግድ የግድ የግድ የግድ ብሸፋፈን በነጠላ በምን ያህል እንዳደፈ ታውቀዋለህ የእኔን ገላ ምን ይዤ ነው 'ምጠብቅህ... በምን መልኩ ልስተካከል ከየት በኩል ነው 'ምቃና እየሸሸሁ ስትከል ስትፈልገኝ የእግሬን ዳና የማስመሰልን ነጠላ ገፈፍ ሲል ከትከሻ እግር እንኳን አላጣሁም ልብን እንጅ መመለሻ እንደት ሆኜ ልጠብቅህ... እፈራለሁ መጣ ሲሉኝ ሸርተት አለ አፈር ገላ እንደት ብዬ ጠበቅ ልበል ፅድቅ አልሰራሁ ከሀጥያት ሌላ ሙሽራ ነህ ከእጄ አይጠፋ የሚለኮስ የፅድቅ መብራት ከደጅ አልቅር እንድታደል አብሮ መግባት ከረፈደ ከምሯሯጥ መብራት ጠፍቶ ከምምታታ እንደት ብዬ ነው የምዘጋጅ ምን ልተካ በምን ቦታ ቅጠልነት እንዳይከበኝ... ፍሬ አልባነት እንዳይከበኝ የዛሬ አመት ስትመጣ ልቦናዬን መልስልኝ ከሀጥያት ህይወት እንድወጣ ዓቢይ አለሙ(ሚተራሊዮን) ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት 🏆🏆🏆 ለመቀላቀል 👇👇👇 t.me/zemaritnsae 🏆🏆🏆🏆🏆 ግጥም ለመላክ . 👇👇👇 . @Tins7
إظهار الكل...
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መረጃ ትምህርት መዝሙር ግጥም ይገኝበታል በተጨማሪም ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🙏1) የመዝሙር ግጥምና ዜማ ለምትፈልጉ በፈለጉት አይነት እና ቋንቋ 2) ቪዲዮ ክሊፕ መስራት ለምትፈልጉ (የመ

👍 6
👍
👎
በረከት ከበደ 👆 መነሻ ሀሳቡ ጥሩ ነው ሰፊ እንደመሆኑ ርዕሱ ከመዋቅሩ ጋር ቁርኝቱ በማጥበቅ ሀሳቡ ማሳጠር ትችላለህ ነገር ግን ያ ስላልሆነ ንባብ ሆነ ግጥም ደግሞ በባህሪው አንባቢው በቀላሉ መረዳት የለበትም ቀለም እንዲኖረው ይዘቱ ላይ ማትኮር በጥቂት ቃላት ብዙ ማለት ልምምድ ማድረግ። .....………………………………………… የዳኛ ውጤት።                 45/50   የlike።                           ?/50    ቦነስ።                             6/10 ጠቅላላ ድምር                      ???
إظهار الكل...
Becky👆 ጥሩ ነው ስህተት የግጥም ይዘት የለውም ቃላት ላይ የጎላ ስህተት ስላለው ዝረው ጽሁፍ ወይም የተፋለሰ ስደራ ሆነ ደጋግመህ ለመፃፍ ሞክር! ................................................... የዳኛ ውጤት። 41/50   የlike። ?/50    ቦነስ። 2/10 ጠቅላላ ድምር ????
إظهار الكل...
Nahom 👆 ጥሩ ነው ..…............................ የዳኛ ውጤት።                 44/50   የlike።                           ?/50    ቦነስ።                             7/10 ጠቅላላ ድምር                      ???
إظهار الكل...
ዮሴፍ ታሪኩ👆 በጣም ጥሩ ነው ርዕሱ ከመዋቅሩ ጋር አልተጋጨም እንደመነሻ ... ስህተት 1) ውበት የለውም በሳድስ መግጠምህ ቅልም አውርዶታል 2 ) ቃላት "መላእክ ሞት " 3) ሀሳብ ድግግሞሽ .….......….…………………… የዳኛ ውጤት።                 44/50   የlike።                           ?/50    ቦነስ።                             5/10 ጠቅላላ ድምር                      ???
إظهار الكل...
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 .   12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር ገጣሚ አይደለሁም ይመስለኝ ነበረ ገጣሚ የሆንኩኝ፤ ሐሳቤን በኅቡዕ ለሕዝብ ያደረስኩኝ፤ ቃላትን ሰድሬ ቀለምን ጨምቄ፤ ስሜቴን የገለጽኩ ዋዜማ አድምቄ፤  ለካስ ገጣሚ አይደለሁም። ልከትብ አስቤ ቃላት ያልቅብኛል፤ ላንቺ ያለኝን ፍቅር ምን ይገልጽልኛል? ገጣሚ አይደለሁም ቃላት አጥረውኛል።  ገጣሚዎቹማ.......... ታላቁ ገጣሚ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ አርጋኖን ደረሱ ፍቅርሽን መግለጫ። ሲያወድስሽ ዋለ ቅዱስ ኤፍሬም ታጥቆ፤ በዳዊት በገና በእዝራ መሰንቆ። ገጣሚዎቹማ.............. ስላንቺ ልናገር በማብዛት አይደለም ብሎም በማሳነስ፤ ቅዳሴን አዜመ አባ ህርያቆስ፤ ያሬድም አረገሽ የዜማው መሠረት፤ ለቁስለኛው ዓለም የድኅነት መሠረት ኪዳነ-ምሕረት። ገጣሚ ባልኾንም ልሞክረው መሰል ባሕርን በጭልፋ፤ አንቺ የወለድሽው ከዓለም የሚሰፋ። ኾነሽ የተገኘሽ ንጽሕት በኹሉ፤ በአንቺ ይማጸናል ዓለማት በሙሉ። ድንግል በሀልዮ ንጽሕት በገቢር ቅድስት በነቢብ፤ መድኃኒት እንዲኾን ተዓምርሽ ይነበብ፤ ተዓምሪያ ብሎ ሲወጥን ካህኑ፤ ልባቸው ይፈካል የምዕመናኑ፤ ውዳሴሀ ተብሎ ምልጃሽም ሲደረስ፤ ድንግል ትገኛለሽ ከእግዜር ቤተ-መቅደስ። ገጣሚ ባልኾንም........ የእናትነትሽ ወዝ ከእኔ ባይጣጣም፤ ልጅሽ በሰጠኝ ቃል ማመስገን አይከፋም።                                      __ ልባዊት _ ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት 🏆🏆🏆 ለመቀላቀል 👇👇👇 t.me/zemaritnsae 🏆🏆🏆🏆🏆 ግጥም ለመላክ .   👇👇👇 .    @Tins7
إظهار الكل...
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መረጃ ትምህርት መዝሙር ግጥም ይገኝበታል በተጨማሪም ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🙏1) የመዝሙር ግጥምና ዜማ ለምትፈልጉ በፈለጉት አይነት እና ቋንቋ 2) ቪዲዮ ክሊፕ መስራት ለምትፈልጉ (የመ

2🥰 2👏 1
👍
👎