cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
978
المشتركون
-424 ساعات
-47 أيام
+330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ አርዋ ቅድስት +"+ =>እናታችን ቅድስት አርዋ በስነ ገድላቸው ከደመቁ የቀደመው ዘመን ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: በሕጻንነቷ የሚገባውን የክርስትና ትምሕርት ተምራለችና ምርጫዋ ሰማያዊው ሙሽርነት ሆነ:: +ለሰዎች ሕይወት እንቅፋት እየሆኑ ከሚያስቸግሩ ነገሮች አንዱ መልክ ነው:: እግዚአብሔር የፈጠረውን ደም ግባት (ቁንጅና) በማይገባ ተጠቅመው የአጋንንት ራት የሆኑ: ሌሎችንም አብረው ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው:: አርዋ ግን ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ብትሆንም እርሷ ለዚሕ ቦታ አልነበራትም:: በለጋ እድሜዋ በክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር ተጠመደች እንጂ:: +ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግስተ ሰማያት ሁሉን ንቃለች:: በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል ዘንድ ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ "መዋኢተ ፍትወት" (የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች) አስብሏታል:: +የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን መሆን የቻለ የደግነት: ርሕራሔ: የፍቅርና የምጽዋት ሕይወትም ነበራት እንጂ:: +አንድ ቀን በተንኮለኞች የሐሰት ምስክር ያለ ጥፋቷ ለፍርድ ቀረበች:: ፍርደ ገምድል ዳኛ ሞት ፈረደባት:: በአደባባይ በጭካኔ ቅድስት እናታችንን ገደሏት:: እግዚአብሔር ግን ድንቅ ነውና ከሞት አስነስቷት ገዳዮቿ እንዲጸጸቱ አድርጓል:: ከዚሕ በኋላም በንጹሕ አኗኗሯ ቀጠለች:: +አንድ ቀን ግን ከባድ ፈተና መጣባት:: አንድ በደም ግባቷ ተማርኮ ሲፈልጋት የኖረ ጐልማሳ አሳቻ ሰዓትና ቦታ ላይ አገኛት:: የሥጋ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አስገደዳት:: +እርሱን መታገሉ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት እርሱ ልብሱን እያወለቀ እርሷ ከወደቀችበት ሆና ወደ ፈጣሪዋ ለመነች:- "ጌታየ ሆይ! የእኔንም ድንግልና ጠብቅ: እርሱንም ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አትተወው:: ስለዚሕም ነፍሴን ተቀበላት" ብላ አለቀሰች:: +እመቤታችን እንደ ዐይን ጥቅሻ ወርዳ ነፍሷን አሳረገች:: ጐልማሳው ወደ ጣላት ቅድስት ዘወር ቢል ሙታ አገኛት:: እርሱም ተጸጸተ:: ወገኖቿ በዝማሬ እናታችን ቅድስት አርዋን ቀብረዋታል:: ✞ ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ ✞ =>ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ አርፏል:: +ቅዱስ ቆሮስ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር የተማረ: ለስብከተ ወንጌል ብዙ ሃገራትን የዞረ ታላቅ ሐዋርያ ነው:: ባስተማረባቸው ቦታዎች ብዙ ሕማማትን ተቀብሏል:: +ብዙ አሕዛብንም ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሷል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለዓመታት አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲታሠር መልዕክቶችንም ይወስድለት ነበር:: ❖ወርኀ ግንቦትን በሰላም ላስፈጸመን እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን:: አምላካችን ከወዳጆቹ በረከትን ይክፈለን:: ❖ግንቦት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት አርዋ እናታችን 2.ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት 4.አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ 2፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ 3፡ አባ ሣሉሲ ክቡር 4፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት 5፡ ቅድስት ሶፍያና ሰማዕታት ልጆቿ ++"+ መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው:: እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥረዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት:: +"+ (ምሳሌ. 31:29) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
إظهار الكل...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

Photo unavailableShow in Telegram
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ አሳለፈ ? ➡️ በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗና በመንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ሰይሟል። ➡️ ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁም #ከመጽደቁ_በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡ ➡️ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ #የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገልጿል። ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ወስኗል። ➡️ #ከሀገር_ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ ፦ - በሙያ ብቃታቸው፣ - በምግባራቸው - በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት #በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ወስኗል፡፡ ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88105?single @tikvahethiopia
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ወሰነ ? ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ፦ ➡️ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ➡️ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ #የተከለከለ፣ ➡️ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ➡️ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ➡️ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ #እንደሚያወግዝ ገልጿል። #የተመሳሳይ_ጾታ_ጋብቻ እና #የግብረ_ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል። @tikvahethiopia
إظهار الكل...
#Update የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በአጽንኦት ጥሪ አቅርቧል። በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካሄድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል። " ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል " ብሏል። ይሁን እንጅ " ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅር አሰኝቶናል " ብሏል። በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አሳውቋል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ አባ አፍፄ ወአባ ጉባ +"+ =>አባ አፍፄና አባ ጉባ ቁጥራቸው ከተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን ነው:: +"+ አባ አፍፄ +"+ =>ጻድቁ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ:: ገና በሕጻንነታቸው ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው ወደ ግብፅ ወርደዋል:: በዚያም በአባ መቃርስ እጅ መንኩሰዋል:: አባ አፍፄ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአልዐሜዳ ዘመን ከ8ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው:: +ጻድቁ ጸበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል:: ትግራይ ውስጥ የሐ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር:: ❖ለጻድቁ በጥቂቱ እነዚሕን እንጠቅሳለን:- 1.ከ100 ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት ገዳማቸው በፍጹም ትጋት: በጾምና በጸሎት አገልግለዋል:: 2.በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን 366 ደቀ መዛሙርት ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ ሕይወትን አስፋፍተዋል:: 3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ተርጉመዋል:: 4.በስብከተ ወንጌል ለሃገራችን ብርሃን አብርተዋል:: ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር "አፍፄ (አፈ-ዐፄ)" ብሏቸዋል:: "የዐፄ (የንጉሥ) አንደበት ያለው" ወይም "ንግግር አዋቂ" ማለት ነው:: +ጻድቁ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው በዚሕች ቀን በ684 ዓ/ም ተሠውረዋል:: እግዚአብሔርም በስማቸው ለተማጸነ: ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: +"+ አባ ጉባ +"+ =>ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ 29 ቀን በ336 ዓ/ም በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ: እናታቸው ቴዎዶክስያ ደጐች ነበሩ:: +አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ) በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው አመስግነዋል:: +በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው: ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ ሒድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን መጥተዋል:: በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ140 በላይ ነበር:: +ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል: መጻሕፍትን በመተርጐም: ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት የእርሳቸው ናት ይባላል:: +ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ ጸበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም አንስተዋል:: እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል:: +በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው:: (በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር: ጥዑመ- ልሳን" ማለት ነው) ❖ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት ያድለን:: በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን:: ❖ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ አፍፄ (ከዘጠኙ ቅዱሳን) 2.አባ ጉባ (ከዘጠኙ ቅዱሳን) 3.አባ ስምዖን ገዳማዊ (በ7 ዓመታቸው መንነው ለ81 ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ) 4.አባ ይስሐቅ ጻድቅ ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ በዓለ ልደቱ ለክርስቶስ 2፡ ቅድስት አርሴማ ድንግል 3፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4፡ ቅዱስ ማርቆስ ዘሮሜ 5፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ 6፡ ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ 7፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ 8፡ ጉባኤ ሰማዕታት ++"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: +"+ (ማቴ. 10:41) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
إظهار الكل...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

✝✞✝ እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ገዳማዊት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ +*" ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ "*+ =>ቅድስቷ እናታችን በነገድ እሥራኤላዊ ስትሆን የተወለደችው ኢየሩሳሌም ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው በሚገባው ፈሊጥ አሳድገው ወደ ትምሕርት አስገቧት:: +አስተማሪዋ ገዳማዊ መነኮስ ነበርና ከተማ ውስጥ አያድርም:: አስተምሯት ዕለቱኑ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር እንጂ:: ዓመተ ክርስቶስ ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቃ ተማረች:: +አንድ ቀን እንደ ልማዷ ልትማር ብትጠብቀውም መምሕሯ ሊመጣ አልቻለም:: ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ መነኮሱን ልትጠይቅ : አንድም ልትማር ወደ በዓቱ ሔደች:: +በሩ ላይ ደርሳ ብታንኩዋኩዋም መልስም : የሚከፍትም አልነበረም:: ከውስጥ ግን ምርር ያለ የለቅሶ ድምጽ ተሰማት:: "ጌታ ሆይ! ይቅር በለኝ?" እያለ በተደጋጋሚ ይጮሃል:: ያ ደጉ መነኮስ ነበር:: +ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ በቅጽበት አንድ ሐሳብ መጣላት:: "እርሱ በንጽሕና እየኖረ ስለ ነፍሱ እንዲሕ ከተማጸነ እኔማ እንደምን አይገባኝ!" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች:: የለበሰችውን ልብስ አልቀየረችም:: ቤተሰቦቿን አልተሰናበተችም:: ከቤቷ አተር በዘንቢል እና ውሃ በትንሽ እቃ ይዛ ወደ ጐልጐታ ገሰገሰች:: +ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ወድቃ አለቀሰች:: ጸለየችም:- "ጌታ ሆይ! ነፍሴን ወደ ዕረፍት አድርሳት? ከክፉ ጠላትም ጠብቀኝ? ይሕንን አተርና ውሃ ለእድሜ ዘመን ሁሉ ባርክልኝ::" +ይሕን ብላ እየፈጠነች ከኢየሩሳሌም ተነስታ በእግሯ ቃዴስን : ሲናይ በርሃን አቁዋርጣ ግብፅ ደረሰች:: ምርጫዋ ብሕትውና ሆኗልና ልምላሜ ከሌለበት : ፀሐዩ እንደ ረመጥ ከሚፋጅበት በርሃ ገባች:: +በዚያም ከያዘችው አተር ለቁመተ ሥጋ እየበላች : ከውሃውም በጥርኝ እየተጐነጨች : ማንንም ሰው ሳታይ : በፍጹም ተጋድሎ ለ38 ዓመታት ቆየች:: የቀኑ ሐሩር : የሌሊቱ ቁር (ብርድ) ልብሷን ቆራርጦ ቢጨርሰው እግዚአብሔር ፀጉሯን አሳድጐ አካሏን ሸፈነላት:: +ጊዜ ዕረፍቷ ሲደርስ የቅዱሳንን ዜና የሚጽፈው ታላቁ አባ ዳንኤል ወደ እርሷ ደረሰ:: እንዳያት ተከተላት:: እርሷ ግን በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ገብታ ተደበቀች:: አባ ዳንኤል በውጪ ሆኖ ተማጸነ:- "እባክህ አባቴ! ውጣና ባርከኝ" አለ:: ሴት መሆኗን አላወቀም ነበርና:: እርሷ ግን "ራቁቴን ነኝና አልወጣም" አለችው:: +ልብሱን አውጥቶ ሰጥቷት ወጥታ ተጨዋወቱ:: በፈቃደ እግዚአብሔር ዜናዋን ሁሉ አወቀ:: ወደ በዓቷ ዘወር ሲል በዘንቢል የሞላ አተር ተመለከተ:: ለ38 ዓመታት ተበልቶ ዛሬም ሙሉ ነው:: አባ ዳንኤል ይፈትነው ዘንድ ከአተሩ በደንብ በላለት:: ከውሃውም ጠጣለት:: ግን ሊጐድል አልቻለም:: +እያደነቀ "እናቴ ሆይ! ልብሴን ውሰጂው" ቢላት "ሌላ አዲስ አምጣልኝ" አለችው:: ይዞላት በመጣ ቀን ግን ተሠውራለችና አላገኛትም:: +አንድ ቀን ግን (ማለትም ግንቦት 28) አረጋውያን መነኮሳት መጥተው የገጠማቸውን ነገር ነገሩት:: እንዲሕ ሲሉ:- "ሰው ተመልክተን ወደ በዓቱ ስንገባ አተር በዘንቢልና ውሃ በመንቀል አገኘን:: ስንበላው ወዲያው አለቀ::" አባ ዳንኤል ነገሩን ገና ሳይጨርሱለት አለቀሰ:: +አተሩ አለቀ ማለት ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ አርፋለች ማለት ነውና:: አረጋውያኑ ግን ቀጠሉ:- "ከበዓቱ ስንወጣ በጸጉሯ አካሏ ተሸፍኖ ወደ ምሥራቅ ሰግዳ አርፋ አግኝተን ከሥጋዋም ተባርከን ቀበርናት" አሉ:: አባ ዳንኤል ዜናዋን ጽፎላት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታከብራታለች:: =>አምላካችን በቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን:: ከበረከቷም ያድለን:: =>ግንቦት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት (ገዳማዊት) 2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ሥጋው ቆዽሮስ የደረሰበት) 3.አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ 4.አባ ጌርሎስ (ጻድቅና ሰማዕት) 5."45" ሰማዕታት (የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት) 6.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት =>ወርኀዊ በዓላት 1.አማኑኤል ቸር አምላካችን 2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ) 3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ 4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት) =>+"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
إظهار الكل...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

3👍 2