cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የጥበብ ና የፍልስፍና መንደር

የምናብ አለም

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
334
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

1.18 MB
19.70 MB
3.21 MB
23.74 MB
5.66 MB
2.32 MB
6.82 MB
14.04 MB
00:55
Video unavailableShow in Telegram
6.82 MB
9.89 MB
4.64 MB
...የጥንቱ ፈላስፋ ፊሮ🌿 ፨፨፨ የጠርጣሪነት ፍልስፍና (scepticism) ጀማሪ እንደሆነ የሚታመንለት የጥንቱ ፈላስፋ ፊሮ አንድ ቀን ጥበብን ያካፍላቸው ዘንድ ወደጋበዙት ሰዎች በማለዳ አመራ። በቦታው ሲደርስ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ተሰብስቦ ሲጠብቀው ተመለከተና ወደተዘጋጀለት የከፍታ ቦታ በዕርጋታ ወጥቶ ቆመ። ፊሮ ትምህርቱን ከመጀመሩ በፊት ጥያቄ ወረወረ፦ <<ዛሬ እዚህ የተሰበሰባችሁት ከእኔ ልትማሩ ነው?>> ተማሪዎቹ በአንድ ድምፅ አዎንታቸውን ገለፁ። <<እንግዲያውስ ስለምን እንደማስተምር ታውቃላችሁ ማለት ነዋ?>> አለ ፊሮ። <<ኧረ ምንም አናውቅም>> አሉ ተማሪዎቹ አሁንም በአንድ ድምፅ። <<ስለምን እንደማስተምር ካላወቃችሁማ ዝም ብዬ ማውራት አልፈልግም>> አለና ከመድረኩ ወርዶ ወደ ቤቱ አመራ። በነጋታው አሁንም በዚያው ቦታ ህዝቡ ተሰብስቦ ይጠብቀው ጀመር። ፊሮም መጣና በእርጋታ ወደ መድረኩ ወጣ። <<ዛሬስ ስለምን እንደማስተምር አውቃችኋልና?>> በማለት ጠየቀ። የተሰበሰበው ህዝብ በአንድ ቃል አዎንታቸውን ገለፁ። ፊሮም <<ካወቃችሁትማ ወደ ቤቴ ልሂድ....>> በማለት ከከፍታው ላይ ወረደ። በሚቀጥለው ቀን ወደ ቦታው ሲያመራ አሁንም ህዝቡ ተሰብስቦ እየጠበቀው ነው። የዚያን ቀን ግን ህዝቡ መልሳቸውን አዘጋጅተው ነበር የጠበቁት። ፊሮም ወደ ከፍታው ከወጣ በኋላ፦<<ዛሬስ ስለምን እንደማስተምር ታውቃላችሁ..?>> አለ። ህዝቡም፦<<ግማሾቻችን እናውቃለን፤ግማሾቻችን ደግሞ አናውቅም...>> አሉት። ፊሮም፦<<እንግዲያውስ ግማሾቻችሁ የምታውቁት፤ ለግማሾቹ የማያውቁት ንገሯቸው!..>> ምንጭ ፦ ጥበብ ከጲላጦስ ፨፨፨ ፨ አሁን በእናንተ አረዳድ በፈላስፋው ላይ ነው ወይስ በተከታዮቹ ላይ ነው የሚፈረደው...?
إظهار الكل...
🌿ፈጣሪ ሆይ፣ ወደ እኔነቴ መልሰኝ ራስን የመሆን ቁልፍ! የጥንት አፈ-ታሪክ እንዲህ ይነገረናል፡፡ አንድ ጊዜ አንዲት አይጥ በሰላም ስትኖር ሳላች በድንገት ድመት አይታ እጅግ ደነገጠች፡፡ ከዚህ ድንጋጤ ለመዳን ምርጫዋ ብዙ ነው - ለምሳሌ ምናልባት ድመቷ ፈሪ ልትሆን ስለምትችል መጋፈጥና ሁኔታውን ማየት፣ አላዛልቅ ካለ ወደቀዳዳዋ ገብታ ቀን እስኪያልፍ መሸሸግ፡፡ አይጧ ግን የመረጠችው ያልተጠበቀ መንገድ ነው፡፡ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ ድመትን እንዳልፈራ፣ ድመት አድርገኝ” በማለት ጸሎት አደረሰች፡፡ የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ ድመትነት ተቀየረች፡፡ ብዙም ሳትቆይ ግን ውሻ በፊቷ ተደንቅሮ አገኘችው፡፡ የለመደችውን ጸሎት ማነብነብ ቀጠለች፣ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ ውሻን እንዳልፈራ፣ ውሻ አድርገኝ”፡፡ አሁንም የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ ውሻነት ተቀየረች፡፡ ሆኖም ይህኛውም ማንነት ብዙም አላዛለቃትም፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መንገድ ስታቋርጥ አንበሳን አየችና የተለመደውን ጸለቷን አደረገች፡፡ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ አንበሳን እንዳልፈራ፣ አንበሳ አድርገኝ”፡፡ እንደገና የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ አንበሳነት ተቀየረች፡፡ አንበሳነቱም አላዛለቃትም፡፡  ከጥቂት  እርምጃ  በኋላ  አንድ  ለአደን  የወጣ  ሰው  መሳሪያ  ታጥቆ  አየችና እጅግ ደከማት፡፡ “ፈጣሪ ሆይ፣ አንዴ ብቻ ታገሰኝ፡፡ ሁለተኛ ሰውን እንዳልፈራ፣ እባክህን ሰው አድርገኝ” ብላ የተለመደ ጸሎቷን ጸለየች፡፡ አሁንም ምኞትዋ ደረሰና ወደ ሰው ተቀየረች፡፡ በመለዋወጥ የደከመ ማንነቷን ለማሳረፍ እቤቷ ገብታ ቁጭ ባለ ቴሌቭዥን ስታይ አንድን የኮሽታ ድምጽ ሰማች፡፡ ዘወር ስትል፣ አይጥ ወዲህ ወዲያ ስትል አየችና እጅግ ፈራች፡፡ የመጨረሻው ምኞትዋ በጸሎት መልክ በድንገት ከአንደበቷ ወጣ፣ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ አይጥን እንዳልፈራ፣ ወደ እኔነቴ መልሰኝ”፡፡ ወዲያውኑ ይህ የመጨረሻ ምኞቷ ሆነላትና ችግሯን ለማሸነፍ ራስን የመቀየር ጉዞዋን ወደ ጀመረችበት ወደ አይጥነቷ ተመለሰች - ብዙ ቀናትን ካባከነች በኋላ፡፡ ራስን ከመሆን፣ ማንነታችንን ከማሳደግ እና ባደገው ማንነታችን ፍርሃታችንን ከመጋፈጥ ውጪ ድል የማግኛው መንገድ ምንድን ነው? በፊታችን እንደተደነቀረው ገጠመኝና እንደ እለቱ ሁኔታ ራስን እንደመለወጥ ምን አድካሚ ሕይወት አለ? ማንነቴን አውቄና ተቀብዬ፣ ድካሜን በማሸነፍና ብርታቴ ላይ በመገንባት ራሴን ሆኜ መኖር የድሎች ሁሉ ድል ነው! ራስንና ማንነትን ለቅቆ የሚጀመር ጉዞ የማያልቅ፣ አድካሚና፣ ወደተነሳንበት ስፍራና ሁኔታ እንደገና “በዜሮ” የሚያስጀምር ሁኔታ ነው፡፡ ሌሎች የራሳቸው ማንነት በማሳደግና በመበርታት ያሸነፉትን ችግር አንተ እነሱን ለመሆን በመሞከር አታሸንፈውም፡፡ አንተነትህ አንተነትህን ይፈልገዋልና ራስህን ሆነህና ከራስህ ጋር ተስማምተህ ኑር፡፡
إظهار الكل...
🌿ባለም ስንክሳር ላይ እንዳየነው ኖረን የሕይወት ከፍ ዝቅ ቀርጾ እንዳስተማረን ድልን የሚወልደው ሌላ ድል ነውና፣ በ እችላለሁ” አስኳል አእምሮህ ካልጸና፣ የመውደቅን ሃሳብ ልብህ ካገዘፈ፣ #ውድቀትህ_እርግጥ_ነው_ደምቆ_የተጻፈ፡፡ 'እበለጣለሁ' ካልክ ውስጥህ እንዲያ ካለ፡ ብትበልጥም አትበልጥም፣ መብለጥ ለእምነት እንጂ ለሚዛን አትከፍልም፡ የሕይወት ጦር ሜዳ የስኬት እንጎቻ ለፈጠነ አትቀናም ወይ ለባለ ጡንቻ ታሽራለችእንጂ ጊዜ ቀኗን ቆጥራ #እችላለሁን_ብሎ_ድልን_ለሚጣራ!" 🌿 ሰውና_ፍልስፍናው 🌿        🎖 @cekuaa🎖 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊 💫 https://t.me/philoso_phy 💫              
إظهار الكل...
🌿#እኔ_የምፈራው. . . እኔ የምፈራው. . . "ምን አለኝ?" ከሚል ጥያቄ ይልቅ "ሰው ምን ይላል?!" በሚል ስጋት ተውርሮ ሕልምን ማጨናገፍ! አድገው ጽጌረዳ ሳይሆኑ በለጋነት መርገፍ! ዓለም በፈጠረችው ሕግጋት ታስሮ የራስን ዓለም ሳይፈጥሩ ማለፍ! #እኔ_የምፈራው. . . ደስታዬን በሰዎች ላይ መገንባት! ከሰው ሲስማሙ ጮቤ መርገጥ፣ሰው አለኝ ብሎ ደረትን መንፋት! ሰው የጠፋ ቀን ማንነትን ፈልጎ ማጣት፣እውነትን መካድ፣መንገድ አልባ ሆኖ ከንፋስ ጋ መጥፋት! . #እኔ_የምፈራው. . . በሚተኩኝ ሰዎች ዙሪያ ማንዣበብ! "አይተኬ ነኝ" ብለው ሲደነቁ ከርመው፣ ከታች ተወርውሮ አፈር ድሜ መብላት፣እንደ ዘበት. .. እንደ ዋዛ ተዘንግተው መና ሆኖ መቅረት! . #እኔ_የምፈራው. . . ባልተፈጠሩበት መስክ ዕድሜን ማሟጠጥ! የሚወዱትን ሰውተው፣የኔ በማይሉት መስክ ላይ ያለ ሰበብ መረገጥ! በሕሊና ጩኸት፣በፀፀት ረመጥ እየታቀጠሉ በሞት ሽረት ህመም ዕድሜ-ዘመን መራወጥ! . #እኔ_የምፈራው. . . በሰው እጅ መውደቅ! እኔ የምፈራው. . ፍርሃቴን ብቻ እየቆጠርኩ፣ፍርሃቴን ብቻ እየፈራሁ፣!ፍርሃቴን ብቻ እየተመንኩ መኖር!          ••●◉Join us share◉●••           ═════❥━━━❥═════      🌾ነገ መልካም ይሆናል !  🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫              🎖  @cekuaa 🎖
إظهار الكل...