cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የና/ደ/አ/አ/ተ/ሃይማኖት ቤ/ክ/ፈ/አሚን ሰ/ት/ቤት

ይሕ የናዝሬት ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተክርስቲያን ፈለገ አሚን ሰንበት ትምህርት ቤት ለአባላቱና ለምእመናኑ ወቅታዊ መረጃዎችንንና ትምህርቶችን የሚሰጥበት channel ነው።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
185
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ             አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"       📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ      ቀናችንን በጸሎት እንጀምር     ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥           ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)      ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥ እንኳን ለጾመ ነቢያት አደረሳችሁ፤ አደረሰን! 🔔 የ2014 ዓ.ም የገና (የነቢያት) ጾም፤ ቅበላው ማክሰኞ ኅዳር 14 ድረስ ብቻ ነው፤ ጾሙ ኅዳር 15 ዕረቡ ይጀመራል ❖ ጾም ማለት ጥሉላት መባልዕትን (የፍስክ ምግቦችን) ፈጽሞ መተው ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ፣ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ፣ መግዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብና እርሱንም ደጅ መጥናት፤ ማረኝ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበርከክ ምሕረተ አምላክን ለመቀበል መዘጋጀት ነው፡፡ ❖ ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህንን ሁሉ በመገንዘብ በዓመት ውስጥ ሰባት አጽዋማትን በማወጅ ልጆቿ እንዲጾሙ ታዛለች፡፡ ❖ ከእነዚህም ሰባት አጽዋማት መካከል አንዱ የነቢያት ጾም/የገና ጾም/ በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ ❖ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል ጾሙ ከኅዳር 15 ጀምሮ ለአርባ ሦስት ቀናት ይጾማል፤ በቤተክርስቲያንም የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ ፩. ጾመ አዳም ❖ ለአዳም የተነገረው ትንቢት ስለተፈጸመበት፤ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ፤ በፍጥረቱ ገዥ አድርጎ በገነት ያኖረኝን ፈጣሪዬን ትቼ የፍጡርን ቃል ሰምቼ ትእዛዙን አፍርሼ አሳዘንኩት ብሎ በፈጸመው በደል አዝኖ ተክዞ አለቀሰ ጾመ፣ ጸለየ፤ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም አይቶ እግዚአብሔር ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ✍‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ›› የሚል ነው፡፡ ❖ ነጋዴ ስንቁን ይዞ እየበላለት ከዚህ እስከዚያ ያደርሰኛል እያለ እንዲጓዝ በአፀደ ሥጋም በአፀደ ነፍስም ሳለ ጌታዬ እንዲህ ብሎኛል ይምረኛል እያለ ተስፋውን አጽንቶ ሲጠባበቅ ኖረ፡፡ ❖ ለልጆቹም ሁሉ ነገረ ሱባኤ ተቆጠረ 5500 ዘመን ሲፈጸምም የማያደርገውን የማይናገር የተናገረውንም የማያስቀር ጌታ ‹‹ቀን ቢደርስ አምባ ይፈርስ›› እንዲሉ ከዘመኑ ዘመን፣ ከወሩ ወር፣ ከዕለታቱ ዕለት፣ ከሰዓቱ ሰዓት ሳያጎድል በጽኑ ቀጠሮው የአዳም የልጅ ልጅ ከምትሆን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፤ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡ 📖ገላ 4፥4 ፪. ጾመ ነቢያት ❖ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት፤ ይህም የጌታ ከእመቤታችን ስለመወለዱ፣ ስለመጠመቁ፣ … ፫. ጾመ ሐዋርያት ❖ ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዓቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን 43 ዕለታት ጾመዋልና፤ የጾሙ መጨረሻ  /መፍቻ/ በዓለ ልደት ስለሆነ ጾመ ልደት ይባላል። ፬. ጾመ ፊሊጶስ ❖ ሐዋርያው ፊሊጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር 16 ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፤ የጾመ ነቢያት መግቢያው ኅዳር 15 ቢሆንም ማቢቂያው ልደት ነው፤ ስለዚህ ‹‹ጾመ ፊሊጶስ›› ይባላል፡፡ ፭. ጾመ ማርያም ❖ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጾማዋለችና፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ትሑት ናትና ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ጸንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለው ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡ ፮. ጾመ ስብከት ❖ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡ ❖ ውድ አንባቢያን እኛ በሐዲስ ኪዳን ያለን ክርስቲያኖች ታዲያ ለምን እንጾማለን ጌታ ተወልዶ፣ ተጠምቆ … የነቢያት ትንቢት ፍጻሜ አግኝቷል ሲል አዕምሮአችሁ ጥያቄን ጫር አድርጎባችሁ ይሆናል፤ ለዚህም ጥያቄ አባቶቻችን ሲመልሱ ነቢያት ይወርዳል፣ ይወለዳል ብለው የተናገሩት ቃል ይፈጸም ዘንድ የሰው ልጆችም ድኅነት ማረጋገጫ እውን ይሆን ዘንድ እንደጾሙ፣ እንደጸለዩ በልደቱም እንሳስት፣ ሰዎች እንዲሁም መላእክት በአንድነት በደስታ እንደዘመሩ የእኛም ደስታ የተረጋገጠበት ነው ስንል እንጾማለን፤ አንድም ነቢያት በጾሙ በረከት እንዳገኙ እኛም ከእግዚአብሔር በረከት እናገኛለን ስንል እንጾማለን፤ ሌላው ትኩረት እንድትሰጡ የምፈልገው ይህ ጾም ጋድ የለውም፡፡ 📌 ዕለተ ምሪያ ❖ ዕለተ ምሪያ ማለት ዕለተ መድኃኒት ማለት ሲሆን ነቢያት ገልጸውታል፤ የጌታ ልደት በዘመኑ በታህሳስ 29 ቀን ሲሆን አባቶች በሠሩልን ሥርዓት መሠረት በዘመነ ዮሐንስ በታህሳስ 28 ቀን ይከበራል፡፡ 📖በኢሳ 12፥1-4 ❖ ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት ልደት የሚውለው ዕለተ ምሪያ በዋለችበት ነው፤ ዕለተ ምሪያ የምትውለው ምንጊዜም ጳጉሜ 5 ቀን ነው፡፡ ❖ ጳጉሜ 5 ቀን ሰኞ ቢውል ልደት መዋል ያለበት ሰኞ ቀን ነው፤ ይህን በዘመነ ዮሐንስ ስንቆጥረው ዕለተ ምሪያ የሚውለው ታህሳስ 29 ሳይሆን ታህሳስ 28 ስለሚሆን ልደት በዚያ ቀን ይከበራል፡፡  ❖ ለልደት በዓል ጋድ /ልዋጭ/ የለውም፤ ረቡዕ ወይም ዓርብ ቢውል እንኳን ፍሥክ /የሚበላባቸው/ ቀናት ሆነው እንዲከበሩ ሐዋርያት አዘው ቢሆንም በዋዜማው የሚገኙት ማክሰኞ ወይም ሐሙስ ከጾመ ነቢያት ጋር የተያያዙ ስለሆኑ መጾማቸው ግድ ነው እንጂ እንደ ጥምቀት በዓል ሳይጾሙ ቆይተው ለዋዜማው ብቻ ጋድ ነው ብሎ የዚያን ቀን ብቻ መጾም ተገቢ አይደለም፡፡ ❖ ስለዚህም እግዚአብሔር በእኛ ይደሰት ዘንድ እኛም በረከትን እናገኝ ዘንድ ጾሙን ለመጾም እግዚአብሔር ይርዳን ጾመን ለመፈሰክ ያብቃን፡፡ መልካም ፆም ይሁንል፤ በጾሙ ሰይጣን ድል የምንነሳበት ንስሐ ገብተን ተስፋ የምናደርጋት መንግስተ ሰማያት የምንወርስበት ያድርግል፤ እንዲሁም ስለ ሀገራች ሰላም ፍቅር የምንጸልይበት መልስም የምናገኝበት ያድርግልን 📌ምንጭ ✍በዲያቆን ቃኘው ወልዴ 📚ጾምና ምጽዋት 1995 ዓ.ም ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ ✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"  📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ        ወስብሐት ለእግዚአብሔር                ይቆየን   ───────────           Channel   🧲 https://telegram.me/Tewahedo12     FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)   🧲 http://facebook.com/Tewahedo12        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)  🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw  ───────────
إظهار الكل...
✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ" መዝ 118 (119) ፥ 71 ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ http://t.me/OrthodoxTewahedo12 ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ ለአስተያየት 📥 ➩ @Tewahedo12_bot

✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✞ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ምስጢረ_ሥላሴ_በጥቂቱ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• እኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የእግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ በሆነው በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡ #አንድ_ሲሆን_ሦስት_ሦስት_ሲሆን_አንድ_በአካል_ሦስት_ሲሆን_በመለኮት_በአንድ_አምላክ_በሆነው_በልዑል_እግዚአብሔር ብቻ ነው የምናምን፡፡ ይህ ምስጢር ሥጋን በለበሰ ኅሊናችን ተመራምሮ ማወቅ አይቻልም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ካልሆነ በስተቀር፡፡ ለዛም ነው ቤተ ክርስቲያናችን አምስቱ አዕማደ ምስጢራትን ስታስተምር በመጀመሪያ ምስጢረ ሥላሴን መማር እንዳለብን ያስቀመጠችልን፡፡ ምስጢር ማለት፦ እጅግ ጥልቅ፣ የተሰወረ፣ የረቀቀ፤ ከመሆኑ የተነሳ #ምስጢር ይባላል፡፡ #ሥላሴ ማለት ደግሞ "ሠለሰ" ወይም ሦስት አደረገ ማለት ሲሆን ትርጉሙም፦ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ✞✞✞ #የሥላሴ_አንድነትና_ሦስትነት፦ ✞✞✞ ☞✞ #የሥላሴ_አንድነት ፦ በአገዛዝ፣ በስልጣን፣ ይህን ዓለም በመፍጠርና በማሳለፍ፣ በህልውና፣ በመለኮት፣ በልብ፣ በቃል፣ በእስትንፋስ፤ በእነዚህ ሁሉ የመለኮት ባህርይ #አንድ ነው፡፡ #የእግዚአብሔር_ሦስትነት_ስንል፦ እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነትም፦ በስም፣ በግብር፣ በአካል ነው። ☞✞ እግዚአብሔር #በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍ፡1፥2 ፣ ምሳ፡30፥4" ። ☞✞ እግዚአብሔር #በግብር ሦስት ነው ስንል፤ ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦ መውለድና ማስረጽ =የአብ፤ መወለድ=የወልድ፤ መስረጽ =የመንፈስ ቅዱስ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝ፡2፥7" ☞✞ እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ #ለአብ፦ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው። #ለወልድ ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ። #ለመንፈስ_ቅዱስ ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው። ☞✞ የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም፦ #አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው። #ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድኅረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝ፡2፥7" #መንፈስ_ቅዱስ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። "እዮ፡26፥13" ✞በመጽሐፍ_ቅዱስም ከበቂ በላይ ሁኖ ተገልፆልናል፡፡ ዘፍ፡1፥26 ፣ ዘፍ፡11፥7 ፣ ኢሳ፡6፥1-3 ፣ ኢሳ፡48፥16 ፣ ማቴ፡3፥16 ፣ ማቴ፡28፥19 ሉቃ፡1፥35 ፣ ዮሐ፡14፥25 ፣ ማቴ፡21፥18 ፣ 1ኛ ቆሮ፡12፥3 ፣ 2ኛ ቆሮ፡13፥14 ፣ ዘፍ፡3፥22 ፣ ማር፡10፥6 ፣ ማር፡10፥18 ፣ ዘፍ፡1፥3 ፣ ዘፅ፡5፥1 ፣ ዘፅ፡7፥17 ፣ ኢያ፡3፥17 ፣ ሐዋ፡1፥23 ወዘተ.... ከዚህም በላይ ስለአንድነትና ሦስትነታቸው እናገኛለን፡፡ 🌾✞✞✞ #​​ቅድስት_ሥላሴ ✞✞✞🌾 #ሥላሴን_ቅድስት_ሥላሴ_እያልን_የመጥራታችን_ምስጢር_ምንድን_ነው❓❔❓ 💠 አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም። 💠 አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ። 💠 አንድም ሴት አዛኝ ናት፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ፥ ይራራሉ፥ ምህረት ይሰጣሉ። 👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል። ምሕረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ በማለት ያመሰጥራል። ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው፥ ርኅራኄያቸውና፥ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን። 💠 አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም፥ አይፈቅዱም በመሆኑም ቅድስት ይባላሉ። 💠 አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም። ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተዉ ለንስሐ ያደርሱታል። 💠 ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀጽ ቅድስት እንላቸዋለን። 💠 አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው። በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ ቅድስት ይባላሉ። የእግዚአብሔር አብ በረከት፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞ ✞ የና/ደ/አ/አ/ተ/ሃይማኖት ወቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤ/ክ ፈ/አ/ሰ/ት/ቤት ገጽ።✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/falg_amine ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
إظهار الكل...
የና/ደ/አ/አ/ተ/ሃይማኖት ቤ/ክ/ፈ/አሚን ሰ/ት/ቤት

ይሕ የናዝሬት ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተክርስቲያን ፈለገ አሚን ሰንበት ትምህርት ቤት ለአባላቱና ለምእመናኑ ወቅታዊ መረጃዎችንንና ትምህርቶችን የሚሰጥበት channel ነው።

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ጥቅምት ስምንት የማኅሌተ ጽጌ ሁለተኛው ሳምንት። ማኅሌተ ጽጌ ጥቅምት 7 #ነግሥ፦ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድስ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፣ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኩሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል። ማኅሌተ ጽጌ ጥቅምት 7 ፩. ነግሥ (ለአፉክሙ ) ሰላም፡ ለአፉክሙ፡ ዘማዕፆሁ፡ ሰላም፤ ጽጌያቲሁ፡ ሥላሴ፡ ለተዋሕዶ፡ ገዳም፤ መንገለ፡ አሐዱ፡ አምላክ፡ ንዋየ፡ መጻኢ፡ ዓለም፤ ወልጡ፡ አምልኮትየ፡ በጸጋክሙ፡ ፍጹም፤ እምአምልኮ፡ ጣዖት፡ ግሉፍ፡ አሐዱ፡ ድርኅም። #ዚቅ፦ ለሥሉስ፡ ቅዱስ፡ ጥዑም፡ ቃሎሙ፤ ናርዶስ፡ ጸገየ፡ ውስተ፡ አፉሆሙ፡፡ ፪. ተፈሥሒ ድንግል (ማኅሌተ ጽጌ ) ተፈስሒ፡ ድንግል፡ ዘኢተአምሪ፡ ብእሴ፤ ዘጸገይኪ፡ ለነ፡ አሐደ፡ እምነ፡ ሥላሴ ፤ እንዘ፡ ትዘብጥ፡ ከበሮ፡ ቅድመ፡ አዕላፈ፡ ኤፍሬም፡ ወምናሴ፤ ለተአምርኪ፡ ትነግር፡ ውዳሴ፤ ማርያም እኅቱ ለሙሴ፡፡ #ወረብ፦ ተፍሥሒ፡ ድንግል፡ ዘኢተአምሪ፡ ብእሴ፡ ዘኢተአምሪ፤ ዘጸገይኪ፡ ለነ፡ አሐደ፡ እምነ፡ ሥላሴ፡ እምነ፡ ሥላሴ፡ ዘጸገየኪ፡ ለነ፤ #ዚቅ፦ በህየ፡ ማርያም፡ እኅቱ፡ ለሙሴ፡ በዕብራይስጥ፤ በይባቤ፡ ዘበጠት፡ ከበሮ፤ በዝየ፡ ማርያም፡ ቅድስት፤ በሥምረተ፡ መለኮት፡፡ ፫. እንበለ ትሣረር እንበለ: ትሣረር: ምድረ: ገነት: ወሥነ: ጽጌያት: ያስተርኢ፤ በኅሊና: ሥሉስ: ዘሀሎ: ተአምርኪ: በቋዒ፤ ኦ: መዋዒት: እመ: አምላክ: መዋዒ፤ ንዒ: ንዒ: እምርእሰ: ኤርሞን: ንዒ፤ ከመ: ትንስቲዮ: ለጸላዒ: ሕዝበኪ: ገፋዒ፡፡ #ወረብ፦ ኦ: መዋዒት: እመ: አምላክ: ንዒ: ንዒ: እመ: አምላክ እምርእሰ: ኤርሞን: ንዒ: ለፀላኢ: ለፀላኢ: ከመ: ትንሥቲዮ /፪/ #ዚቅ፦ ዘእንበለ፡ ይትፈጠር፡ ሰማይ፡ ወምድር፤ ወዘእንበለ፡ ትሣረር፡ ምድረ፡ ገነት፤ ሀለወት፡ ስብሕት፡ ቅድስት፡ ወቡርክት፡ ይእቲ፡ ማርያም፤ ፬. እንዘ ተሐቅፊዮ እንዘ ፡ ተሐቅፊዮ ፡ ለሕጻንኪ ፡ ጽጌ፡ ፀዓዳ ፡ ወቀይሕ፤ አመ ፡ ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ቦእኪ ፡ በዕለተ ፡ ተአምር ፡ ወንጽሕ፤ ንዒ ፡ ርግብየ ፡ ትናዝዝኒ ፡ እምላህ፤ ወንዒ ፡ ሠናይትየ ፡ ምስለ ፡ ገብርኤል ፡ ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ፡ ከማኪ ፡ ርኅሩኅ ፡፡ #ወረብ፦ ንዒ፡ ርግብየ፡ ንዒ፡ ርግብየ፡ ምስለ፡ ሚካኤል፤ ወንዒ፡ ሠናየት፡ ወንዒ፡ ሠናይትየ፡ ምስለ፡ ገብርኤል፡ ፍሡሕ፤ #ዚቅ፦ አንቀጸ፡ አድኅኖ፡ ረሰያ፤ ኀደረ፡ ቃል፡ ኀበ፡ ሠምረ፡ አብ፤ ወይቤላ፡ ንዒ፡ ርግብየ፡ ሠናይትየ፤ አግአዚት፡ ንባብኪ፡ አዳም፡፡ ፭. ክበበ ጌራ ወርቅ ክበበ፡ ጌራ ወርቅ፡ ጽሩይ ፡ እምዕንቈ ባሕርይ ፡ ዘየኃቱ፣ ዘተጽሕፈ ፡ ብኪ ፡ ትእምርተ ፡ ስሙ ፡ ወተዝካረ ፡ ሞቱ፣ አክሊለ ጽጌ ፡ ማርያም ፡ ለጊዮርጊስ ፡ ቀጸላ መንግሥቱ፣ አንቲ ፡ ኵሎ ፡ ታሰግዲ ፡ ሎቱ፣ ወለኪኒ ፡ ይሰግድ ፡ ውእቱ፡፡ #ወረብ፦ ክበበ፡ ጌራ ወርቅ፡ ዘየኃቱ፡ ጽሩይ፡ እምዕንቈ ባሕርይ፤ ማርያም፡ አክሊለ፡ ጽጌ፡ ለጊዮርጊስ፡ ቀጸላ፡ መንግሥቱ፡፡ #ዚቅ በወርቅ፡ ወበዕንቊ፡ ወበከርከዴን፤ ሥርጉት፡ ሥረጉት፡ በስብሐት፤ ወነገሥት፡ ይትቀነዩ፡ ለኪ፤ ትርሢተ፡ መንግሥቱ፡ አንቲ፡ መድኃኒቶሙ፡ ለነገሥት፡፡ ፮. ስብሐት ለኪ (ሰቆቃወ ድንግል ) ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ አብ፡ ፈናዊ፤ ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ ወልድ፡ ተፈናዊ፤ ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ ማኅየዊ፤ ቃለ፡ ስእለትነ፡ በአዕዛነ፡ መንፈስ፡ ጽልዊ፤ ወዲበ፡ ዛቲ፡ ማኅሌት፡ ሰላመ፡ ከዓዊ፡፡ #ወረብ፦ ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ አብ፡ ፈናዊ፡ ስብሐት፡ ለኪ ፤ ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ ወልድ፡ ወመንፈ፡ስ ቅዱስ ፤ #ዚቅ ስብሐት፡ ለኪ፡ ኦ፡ ወላዲተ፡ እግዚአ፡ ኲሉ፡ አኰቴት፡ ወክብር፤ ለአብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ይእዜኒ፡ ወዘልፈኒ፡ ወለዓለመ፡ ዓለም፡ አሜን፤ ወልድኪ፡ ሣህሎ፡ ይክፍለነ፤ ሰአሊ፡ ለነ፡ ቅድስት። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ኑ ቅዳሜ ማታ ከ4:00 ጀምሮ ሌሊቱን በሙሉ እግዚአብሔርን እያመሰገንን እንደር። እርሶም በየትም ቦታ በምስጋናው ለሚካፈሉ ወንድምና እኅቶች ይላኩላቸውና ከማኅሌታውያኑ ጋር በሕብረት እናመስግን። ለመቀላቀል እንግሊዝኛውን ተጭነው ጆይን ያድርጉኝ። 👇👇👇👇👇👇 @falg_amine @falg_amine @falg_amine
إظهار الكل...
*እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ አመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: *የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ *መልካም ቀን ይሁንልን።
إظهار الكل...
ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ልጠይቃችሁ፦ አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የኾነ ቦታ ላይ ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደዚያ ቦታ ለመሔድ አስፈላጊ ነው የምትሉትን ኹሉ አታደርጉምን? ቀኑን ሙሉም ቢኾን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁምን? እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያላችሁ ግን አንዲት ወይም ዐሥር ወይም ሃያ ወይም መቶ ወይም አንድ ሺሕ ቅንጣት ወርቅ አይደለም፤ ወይም ምድርን ኹሉ አይደለም፡፡ ከዚህ ኹሉ የምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት እንጂ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ ታዲያ ምን አለ? ይህንን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ ሰዎችስ እንደምን ያሉ ምስኪናን ናቸው? #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
إظهار الكل...
​​እንኳን #አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን! አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል። አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ። አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው። በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር። በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል። ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል። ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል። ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል። ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ። #ምንጭ - ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ
إظهار الكل...
††† እንኩዋን ለቅዱሳን ነገሥታት "አብርሃ ወአጽብሃ" እና ለቅዱስ "ሐናንያ ሐዋርያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† +"+ ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ +"+ =>እነዚህ ነገሥታት ሞገሶቻችን: ብርሃኖቻችን ናቸውና ደስ እያለን እንወዳቸዋለን: እናከብራቸዋለን:: ሥላሴ ቢመርጧቸው ዛሬ ላለንበት ሕይወት መሠረቱን ጥለው አልፈዋልና:: +2ቱ ቅዱሳን ነግሥታት መንትያዎች ሲሆኑ ወላጆቻቸው ንጉሥ ታዜር / አይዛና / ሠይፈ አርዕድ እና ንግሥት አሕየዋ / ሶፍያ ይባላል:: ንጉሡና ባለቤቱ ልጅ ቢያጡ ወደ እግዚአብሔር ለመኑ:: ፈጣሪም በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት 2 ዕንቁዎችን አስረከባቸው:: +ንግስት አሕየዋ (ሶፍያም) መጋቢት 29 ቀን በ311 ዓ/ም ጸንሳ: ታሕሳስ 29 ቀን በ312 ዓ/ም 2ቱን ቅዱሳን ወልዳቸዋለች:: "አምላክ ሽሙጥን አራቀልኝ" ስትልም "አዝጉዋጉ" ብላቸዋለች:: እነዚህ 2 ፍሬዎች በልጅነታቸው ከወቅቱ ሊቀ ካህናት እንበረም ኦሪቱን ጠንቅቀው ተምረዋል:: +ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸውና በ12 ዓመታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ገብተዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን አባታቸው ታዜር በማረፉ ሕዝቡ 2ቱን ቅዱሳን "ንገሡልን" አሏቸው:: እነርሱም "እኛ የፈጣሪ አገልጋዮች ነንና አንችልም" በማለታቸው ለተወሰነ ጊዜ እናታቸው አስተዳደረች:: +ቆይቶ ግን ቅዱስ ሚካኤል ለሊቀ ካህናቱ እንበረም "የፈጣሪ ፈቃዱ ስለ ሆነ አትዘኑ:: 2ታችሁም በአንድ ዙፋን ላይ ንገሡ: ታላቅ ጸጋ ለሃገሪቱ ይሆናል በላቸው" አለው:: +ሊቀ ካህናቱም የታዘዘውን ተናግሮ: በ19 ዓመታቸው: 2ቱንም በአንድ ዙፋን ላይ "ነገሥተ ኢትዮዽያ" ሲል አስቀምጦ ቀባቸው:: ስማቸውን "ኢዛና" እና "ሳይዛና" አላቸው:: ቅዱሳኑ እንደ ነገሡ ቀዳሚ ሥራቸው የቀናችውን ሃይማኖት መፈለግ ሆነ:: +በወቅቱ ፍሬምናጦስ (የሁዋላው አቡነ ሰላማ) በቤተ መንግስቱ ውስጥ የቅርብ አማካሪ ነበርና ጠርተው ተጨዋወቱት:: "አንተ ወንድማችን! ክርስቶስ ይወርዳል: ይወለዳል ተብሎ የተቆጠረው ሱባኤ እኮ አልፏል:: ምነው ቀረሳ? በርግጥ ምሥጢሩ ንገረን" አሉት:: +እርሱም አትቶ: አመሥጥሮ: ከ300 ዓመታት በፊት አምላክ ሰው መሆኑንና ዓለምን ማዳኑን አስተማራቸው:: "አጥምቀን?" ቢሉት "አልችልም" አላቸው:: እነርሱም ከብዙ ስጦታ ጋር ወደ ግብጽ ላኩት:: +ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "አቡነ ሰላማ" ብሎ ከብዙ መጻሕፍት ጋር ላከው:: በመጀመሪያ ኢዛናና ሳይዛና ተጠመቁ:: ስማቸውም "አብርሃ ወአጽብሃ" ተባለ:: ቀጥሎም ሠራዊቱና ሕዝቡ ተጠመቀ:: +ሃገራችንም በእነዚህ ቅዱሳን አማካኝነት ከጨለማ ወደ ብርሃን መጣች:: የክርስትና ደሴት ሆነች:: ሃገረ እግዚአብሔርነቷንም አጸናች:: ቅዱሳኑ ከዚህ በሁዋላ በሞገስ ክርስትናን ያስፋፉ ዘንድ ደከሙ:: ከ154 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን ሲያንጹ አብዛኞቹ ፍልፍል ነበሩ:: +በተለይ ግን በአክሱም ከተማ ላይ ያነጿትና 12 ቤተ መቅደሶች የነበሯት የጽዮን ቤተ ክርስቲያን ልናያት ትናፍቀናለች:: ጌጧ: ብርሃኗ ውል ውል ይልብናል:: ይህቺው ቤተ ክርስቲያን በ10 ኛው ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት በእሳት አውድማታለችና:: መሠረቱ ግን ዛሬም አለ:: +ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ ግን ክርስትናን ለማስፋፋትና መንግስትን ለማጽናት ሲሉ ከአክሱም በተጨማሪ በሽዋም ዙፋንን ዘረጉ:: ለብዙ ዓመታትም አምላክ በፈቀደው መንገድ እስከ የመን ድረስ ገዙ:: ክርስትናንም አስፋፉ:: +ቅዱስ አብርሃ በተወለደ በ52 ዓመቱ: በ364 ዓ/ም ጥቅምት 4 ቀን ሲያርፍ ወንድሙ ለ15 ዓመታት ብቻውን አስተዳድሯል:: በ379 ዓ/ም ደግሞ በዚሁ በጥቅምት 4 ቀን ቅዱስ አጽብሃም በተወለደ በ67 ዓመቱ በክብር ዐርፏል:: +ከሁለቱም መቃብር ላይ ለ30 ቀናት የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ ታይቷል:: ጌታችንም በማይታበል ቃሉ "ስማችሁን የጠራውን: መታሰቢያችሁን ያደረገውንም እምርላቹሃለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: +"+ ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ +"+ =>ሐናንያ ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ: በሕገ ኦሪት አድጐ: ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ72ቱ አርድእት ደመረው:: +ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ: ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: (ሉቃ. 10:17) ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ50ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: +በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል (የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ) ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር:: +ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነው የነገረው:: ከ3 ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል:: ሳውል (ዻውሎስ) ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር:: +2ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው: ፈወሰው: አጠመቀው: በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: (ሐዋ. 9:1-19) +ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: =>አምላከ አብርሃ ወአጽብሃ "ድሃ ተበደለ: ፍርድ ተጉዋደለ" የሚል ዳኛ: ሃይማኖቱ የቀና መሪንም ያምጣልን:: የቅዱሳኑን ክብር በእኛ ላይ ያድርግልን:: =>ጥቅምት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሃ 2.ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ባኮስ ሰማዕት 5.ቅዱሳን ባባ እና ማማ 6.ቅዱስ ዮሐንስ ሕጽው =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) =>+"+ እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኩዋንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው:: +"+ (1ጢሞ. 2:1-4) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† @falg_amine 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
إظهار الكل...
​​#ፆመ_ፅጌ / የፅጌ ፆም የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ ለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ጽጌ ጾም መቼ ነው የሚገባው እያሉ የሚጠይቁ ስላሉ ከወዲሁ ለማስታወስ ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡ በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡ ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ "አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ"፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡ እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት "ሰቆቃወ ድንግል" በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር” የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡ ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!!! ይቀላቀሉ 👇👇👇 @falg_amine @falg_amine @falg_amine
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.