cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Hakim

Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
49 672
المشتركون
+4024 ساعات
+3297 أيام
+1 91730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

"ልጆች እየተጫወቱ የባዕድ ነገር ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን?" - ዶ/ር አቤል ግደይ ፤ የህፃናት ሐኪም ባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦ ሲገባ ትንታን ያስከትላል። ይህ የአየር ወደ ሳንባ መግባትን በመከላከል እና ትንፋሽን በመቁረጥ የአተነፋፈስ ስርዓትን በማቆራረጥ ለአዳጋ ያጋልጣል። ለየት የሚያደርገው የአየር መግባት በመከልከል በአጭር ጊዜ ለሞት ሊያደርስን ስለሚችል ነው። ለምሳሌ፦ አጥንት ፣ ክኒን ፣ ውሃ ፣ ኦቸሎኒ ፍሬ ፣ ስንዴ… ሌሎችን ጠጣር ነገሮች ወደ አየር ቱቦ ሊገቡ እና ትንታን ሊያስከትሉ የሚችሉ ናቸው። የትንታ ምልክቶች ልክ ባዕድ ነገሮች ወደ መተንፈሻ አካላት ሲገቡ የሚኖሩ ምልክቶች እነዚህ ናቸው 1. በሃይል ማሳል 2. መናገር አለመቻል 3. ጮክ ያለ ድምፅ 4. መጥቆር 5. ትንፋሽ ማጠር 6. ማላብ 7. ድንጋጤ 8. አንገት ማሳከክ 9. መፍጨርጨር 10. ቀልብን መሳት 11. ማንቀጥቀጥ ግዜ ከወሰደ •ተደጋጋሚ ሳል •ሽታ ያለው ዓክታ •ክብደት መቀነስ •ትንፋሽ ማጠርና መድከም የትንታ የመጀመርያ እርዳታ አሰጣጥ 1. ሁኔታውን መታዘብ 2. መጠየቅ 3. ሰዎች እንዲረዱን መጣራት 4. ጀርባ መምታትና ሆድን መጫን አንድ ከእናንተ ጋር እየተመገበ የነበረ ሰው ድንገት ትን ቢለው በእነዚህ ከላይ በተዘረዘሩ መንገዶች ማገዝ ይቻላል። ልጆች እየተጫወቱ ቆይተው ክኒን ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን? 1. ሁኔታን መታዘብ • ምን እንደዋጡ መታዘብ • ይህም ህክምና ሂደን ለማስረዳት ይረዳናል • እርዳታ ሰጪ የአደጋ ምስክር እንደሆነ አስቡ። 2. መጠየቅ • ምን እንደዋጠ መጠየቅ ለምሳሌ ፍሬ ፣ ምግብ ፣ ድንጋይ 3. ሰዎች ለእርዳታ መጣራት • እሪ ብሎ መጮህ እና ሰዎችን እርዳታ መጠየቅ 4. ጀርባ መምታትና ሆድ መጫን • ሁኔታውን በፍጥነት በመረዳት ወደ እርዳታ መግባት ያስፈልጋል። ሀ. ጀርባ መምታት ትልልቅ ሰዎች እንዲያጎነብሱ በማድረግ ከታች ከሚታየው ስዕል አድርገን 5 ግዜ ጀርባቸው መምታት ደጋግመን መተን ተስፈንጥሮ ከወጣ ጥሩ ካልሆነ ወደ ሆድ መጫን መቀጠል። ለ. ሂልማች ማኑቨር / ሆድ መጫን ጀርባ ደጋግመን 5 ግዜ ከመታን በኃላ ቀጥለን ሆድን መጫን ያስፈልጋል። ይህ መቆም በሚችሉ ሰዎች ጀርባ ከመምታት በኃላ የምንፈፅመው ይህ ባዕድ ነገር መውጣት አለመውጣቱን ማየትና ካልወጣ እንዲወጣ እየመላለስክ መሞከር ወሳኝ ነው። ትንታ በማይቆሙ ህፃናት ልክ ባዕድ ነገር ሲገባባቸው ቁልቁል ደፍተን ጀርባቸውን 5 ግዜ በመምታት ከዛም ደረታቸውን እየደጋገምን ሌላ ጉዳት በማያስከትል መልኩ መጫንና መጠፍጠፍ ይጠበቅብናል። 5. ህክምና መሄድ አንድ ባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦው የገባበት ሰው ወደ ህክምና መሄድ አለበት። ሳንባ ቁስለት እንዳይፈጥርበት ሃኪም ሊያየው ይገባል። የመጀመርያ እርዳታ የመጨረሻ አይደለም! @HakimEthio
إظهار الكل...
👍 2
የረቲና ካንሰር ምንድን ነዉ? የረቲና ካንሰር (በእንግሊዝኛዉ አጠራር ‹‹ረቲኖብላስቶማ/Retinoblastoma›› በህጻናትና በልጆች ዓይን ላይ የሚከሰት የካንሰር ዓይነት ሲሆን ካንሰሩ የሚጀምረዉ ከረቲና (የዉስጠኛው ዓይን ክፍል) በመሆኑ የረቲና ካንሰር ተብሎ ይጠራል። ይህ ካንሰር የሚከሰተዉ በ13ኛዉ የዘረ-መል ግንድ (‹‹ክሮሞዞም››) ላይ በሚገኝ ዘረመል ላይ በሚደርስ ጉዳት ነዉ። ዐሥር ከመቶ (10%) የሚሆነዉ የዘረ-መል ጉዳት በቤተሰብ የሚተላለፍ ሲሆን ዘጠና ከመቶ (90%) የሚሆነዉ የዘረ-መል ጉዳት ደግሞ ባልታወቀ ምክንያት በድንገት የሚከሰት ነዉ። ከሚታወቁ የካንሰር አጋላጭ ነገሮች ለምሳሌ ሲጋራ ማጨስ፣ ወዘተ ጋርም ምንም ዓይነት ግንኙነት የለዉም። የረቲና ካንሰር ችግሩ እንደተከሰተ ብዙም ሳይዘገይ ቢቻል ደግሞ ወዲያዉኑ በምርመራ ታዉቆ ተገቢ ሕክምና ካልተደረገለት ዕይታን ካንሰሩ ወደ ሰዉነት ከተሰራጨ ደግሞ ሕይወትን ያጠፋል። የረቲና ካንሰር በአንድ ወይንም በሁለት ዓይን ላይ ሊከሰት የሚችል ሲሆን በብዛት (ዘጠና ከመቶ) እስከ አራት ዓመት የእድሜ ክልል ዉስጥ በሆኑ ልጆች ላይ ይታያል። ሰባ ከመቶ ገደማ (70%) የሚሆነዉ የረቲና ካንሰር በአንድ ዓይን ላይ ብቻ የሚከሰት ሲሆን ሠላሳ ከመቶ (30%) የሚሆነዉ ደግሞ በሁለት ዓይን ላይ ይከሰታል። ዐሥር ከመቶ (10%) የሚሆኑት የረቲና ካንሰር ሕሙማን ደግሞ ከቤተሰቦቻቸዉ ውስጥ አስቀድሞ በዚሁ ካንሰር የተያዘ ሰዉ ይኖራል። ይህ የረቲና ካንሰር በአደጉ ሀገሮች በሕክምና የመዳን ዕድሉ ከ95 በመቶ በላይ ሲሆን በታዳጊ ሀገሮች ግን የግንዛቤ እጥረት፣ የሰለጠነ የሰዉ ኃይል እና የሕክምና መድኃኒት አቅርቦት ችግር ስላለ ህጻናትና ልጆችን ለሞት በመዳረግ ላይ ነዉ። ይህ ችግር ሲከሰት በአብዛኛዉ የዓይን ብሌንን (‘Pupil’) በከፊል ወይንም በሙሉ የሚሸፍን ነጭ ነጸብራቅ የሚመስል ነገር (‘Leucocoria') ይታያል። በነጭ ነጸብራቅ በከፊል ወይንም በሙሉ የተሸፈነ የዓይን ብሌን የድመት ዓይን ስለሚመስል ወላጆች የልጄ ዓይን እንደ ድመት ዓይን ያበራል (የድመት ዓይን ይመስላል) በማለት ይገልጹታል (ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ የቀረበውን ምስል 16.2.1-2.2 ይመልከቱ) በተጨማሪም ይህ የረቲና ካንሰር ሌሎች ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል (ምስል 16 2.1-2.8 ይመልከቱ)። ዋና ዋና ምልክቶቹም፡- • የዓይን መንሸዋረር፣ • የዓይን መቅላት፣ • የዓይን ማበጥና ወደ ዉጭ መጎልጎል፣ • የዓይን መጠን ማነስ፣ • የዓይነ መስታወት (‘Cornea’) መተለቅና መዳመን ናቸዉ። ስለሆነም ወላጆች እነዚህን ምልክቶች ሲያዩ ወዲያዉኑ ሐኪም ሊያማክሩና ካንሰር እንዳልሆነ ሊያረጋግጡ ይገባል። የዚህ ካንሰር እዉቀቱና ልምዱ የሌላቸዉ የጤና ባለሙያዎች ለምልክቶች በቂ ትኩረት ላይሰጡ ስለሚችሉ በተቻለ ዐቅም እነዚህ ምልክቶች ያሉባቸዉን ህጻናትና ልጆች በዓይን ስፔሻሊስት ሐኪም እንዲታዩ ማድረግ ተገቢ ነዉ። ለረቲና ካንሰር የሚደረጉ ሕክምናዎች ምንድን ናቸዉ? የረቲና ካንሰር ሕክምና ዋና ዓላማ ሕይወትን ማዳን ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ካንሰር ያለበት ዓይን በቀዶ ሕክምና (በኦፕራስዮን) ተጠርጎ እንዳይወጣና ከተቻለም ጠቃሚ ዕይታ እንዲኖረዉ ማድረግ ነዉ። የሚደረጉ ሕክምናዎች እንደ ካንሰሩ ደረጃና እንደ ጤና ተቋሙ ልምድና አቅርቦት የሚለያይ ቢሆንም ዋና ዋና የሕክምና ዓይነቶች የሚባሉት፡- 1. የ’ሌዘር’ (‘LASER’) ሕክምና 2. በደም ሥር የሚሰጥ የካንሰር መድኃኒት እና 3. የጨረር ሕክምና ናቸዉ። ካንሰሩ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰና ወደ ሰዉነት የመሰራጨት ዕድሉ ከፍተኛ ሆኖ ሲገኝ ካንሰር ያለበትን ዓይን በቀዶ ሕክምና ጠርጎ ማዉጣት የግድ ይላል። ስለሆነም ዓይኑ በቀዶ ሕክምና ተጠርጎ እንዲወጣ ከተወሰነ ወላጆች (አሳዳጊዎች) ሳይዘገዩ ሊስማሙ ይገባል። ቅድሚያ የሚሰጠዉ ሕይወትን ማዳን ነዉና!! ከዚህ ጋር ተያይዞ ወላጆች የዉሳኔው ክብደት ከሚፈጥረው ጫና አንፃር የሐኪም ምክርን ወደ ጎን በመተው የባሕል መድኃኒት እና ሌሎች ፍቱን ያልሆኑ ነገሮች በሞከር ረጅም ጊዜ ያጠፋሉ:: ካንሰሩ ገፍቶ እና ተሠራጭቶ አጠቃላይ ዓይኑ ቆስሎ እና መርቅዞ ለጊዜያው እፎይታም ቢሆን በቀዶ ሕክምና ዓይኑን ማስወጣት አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጥር ብቻ የመስማማት ሁኔታ ብዙ ጊዜ ይከሰታል:: የረቲና ካንሰርን በባሕላዊ ዘዴ መፈወስ እንደማይቻል አውቆ ተባባሪ መሆን የግድ ይላል:: አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ከአንድ በላይ የሕክምና አይነቶች ለአንድ ታካሚ ይሰጣሉ። ካንሰሩ እስኪጠፋም ተደጋጋሚ ሕክምና ማድረግን ይጠይቃል። ካንሰሩ ከዳነ በኋላም እንደገና ተመልሶ ሊከሰት ስለሚችል ከሕክምና በኋላ ለረጅም ዓመታት (ከአምስት እስከ ዐሥር ዓመት) ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል። የረቲና ካንሰር በዘር ሊተላለፍ ይችላልን? አርባ ከመቶ (40%) የሚሆነዉ የረቲና ካንሰር በዘር ሊተላለፍ ስለሚችል በቤተሰብ ዉሥጥ ችግሩ እንዳለ የሚታወቅ ከሆነ ህጻናትና ልጆች ተገቢ ምርመራና ክትትል ሊያደርጉ ይገባል። በቤተሰብ ዉሥጥ ችግሩ ያለባቸዉ ሰዎች ልጅ ሲወልዱ የህጻናት ቅድመ ጥንቃቄ ምርመራዉን ከወለዱበት ሳምንት ጀምሮ ሊያደርጉ ይገባል። በዘር የረቲና ካንሰር ችግር ያለባቸዉ ሰዎች እንዲሁም የረቲና ካንሰር ያለበት ልጅ ያላቸዉና የረቲና ካንሰር ሕክምና አድርገዉ የዳኑ ሰዎች ወደፊት ስሚወልዷቸዉ ህጻናት የካንሰር ተጋላጭነት በአግባቡ መረዳት እንዲችሉ የዘረ-መል ዉርስ የምክር አገልግሎት ሊያገኙ ይገባል። ለግንዛቤ እንዲረዳ ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰንጠረዥ 16.1 የተገለጸዉን የካንሰር መተላለፊያ መንገድና የመያዝ ዕድል መረጃ ይመልከቱ። ጠቅለል ባለ መልኩ የህጻናትና ልጆች የዓይን ብሌን ነጭ ሆኖ ከታየ የችግሩ መንስኤ የረቲና ካንሰር ሊሆን ስለሚችል ወዲያዉኑ የዓይን ምርምራ ማድረግ የግድ ይላል። በመጨረሻም ችግሩ ያለባቸዉን ህጻናትና ልጆች ቶሎ በማሳከም ተገቢ ያልሆነ የህጻናትና የልጆች ሞትን ለመቀነስ የድርሻችንን እድንወጣ አደራ ማለት እወዳለሁ። ምንጭ መጽሐፍ:-“የዓይን ጤናና እንክብካቤ” በፕ/ር የሺጌታ ገላዉ ብርሃኑ (በደራሲው ፈቃድ መረጃው ተደራሽ ይሆን ዘንድ ከመጽሐፉ ገጽ 171-176 በከፊል ተወስዶ የተለጠፈ) @HakimEthio
إظهار الكل...
👍 4
To post your papers on the channel, use this link t.me/HakimAds to send your PDF @HakimEthio
إظهار الكل...
Pdf of our Case
إظهار الكل...
"የእብድ ውሻ" በሽታ ሬቢስ በሽታ ምንድን ነው? - በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) የምንለው ሬቢስ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ከእንስሳት ወደ የሰዉ ልጅ የሚተላለፍ በሽታ ነው። - የእብድ ውሻ በሽታ የተባለበት ምክንያት በአበዛኛው የቫይረሱ ተሸካሚዎች በአካባቢያችን የሚገኙ ውሾች በመሆናቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ የለሊት ወፍ ፣ ፈረስ ፣ ላም ፣ የቫይረሱ ተሸካሚ ሊሆኑ ይችላሉ። - ከዉሻ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የሬቢስ በሽታ በአብዛኛው ታዳጊ ሀገራትን የሚያጠቃ ሲሆን በተለይ ህጻናት ለጆችን ስለበሽታው እና ከትባቱ በቂ ግንዛቤ በሌላቸው የሀገራችን ክፍሎች ላይ በብዛት ይስተዋላል። መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው? - በቫይረሱ ከተጠቁ እንስሳት በተለይ ከውሾች ወደ የሰው ልጅ በንክሻ ወይም በመቧጨር ከአፉቸው በሚወጣ ፈሳሽ (saliva) በቀጥታ ቆዳን ዘልቆ የሚገባ ከሆነ ወይም በሰወነታችን ትኩስ ቁስል (fresh skin wounds) ካለ ሊተላለፍ ይችላል። - በተለይ የተነከስነው ወይም የተቧጨርነው አንገት እነ ከአንገት በላይ ከሆነ ቫየረሱ በፍጥነት ወደ ማእከላዊ የነርቭ ስርአት (central nervous system) ቅርብ ስለሆነ በፍጥነት ወደ አንጎል (brain) በመድረስ ለሞት ሊዳርገን ይችላል። - የሬቢስ በሽታ theroetically ከቫይረሱ ተሸካሚ ሰው ወደ ሰው በንክሻ ይተላለፋል ተብሎ ይታሰባል። ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? -አንድ ሰው በቫይረሱ ከተጋለጠ በኃላ ምልክት እስከሚያሳይ (incubation period) ከ3ሳምንት እስከ 3 ወር ሊቆይ ይችላል። - ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች የተነከሰበት ቦታ ለይ መጠዝጠዝ አና መደንዘዝ ፣ ትኩሳት ፣ እራስ ምታት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ጡንቻ አካባቢ የህመም ስሜት ፣ ፍራቻ ፣ ከመጠን በላይ ምራቅ መኖር ፣ ለመዋጥ መቸገር ፣ ቅዠት ፣ ግራ መጋባት ፣ ዉሃን መፍራት (hydrophobia) ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ የከፉ ደረጃ ሲደርስም ለኮማ ከዛም ለሞት ሊዳረግ ይችላል። - ምልክቶቹን ማሳየት የጀመረ ሰው የመዳን አድሉ እጅግ በጣም ጠባብ ነው። እንዴት መከላከል እንችላለን? - የቤትም ሆነ የዱር እንስሳ ካለን ማስከተብ -ሌላው መርሳት የሌለብን ነገር ክትባቱን ባልተከተቡ እንስሳት ከተነክሰን ወይም ጥርጣሬ እንኳን ቢኖርብን ግዜ ሳንሰጥ ወዲያውኑ የህክምና ባለሙያ በማማከር የተጋላጭነት ክትባቱን (post exposure prohpylaxis) መዉሰድ አለብን። ህክምናውስ? - የሬቢስ በሽታ ይሄ ነው ሚባል ህክምና የለውም። ምክነያቱም የሬቢስ ቫይረስ ሰውታችን ውስጥ ከገባ እራሱን ስለሚደብቅ በጸረ ቫይረስ (Anti viral) አንኳን መዳን አይችልም። - ስለዚህ ማንኛውም አይነት ቁስል በሰውነታችን ለይ ካለ በአግባቡ መታከም እና ተጋላጭ ከሆንን ጊዜ ሳነሰጥ የህክምና ቦታ በመሄድ ከትባቱን መከተብ ብቸኛ አማራጮች ናቸው። - በአጠቃላይ የሬቢስ በሽታ ችላ የማይባል ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ በመሆኑ ሁሉም ከውሻ በሽታ መጠበቅ ይገባል ያሰፈረውን አቅርበናል ። መልካም ቆይታ! Dr. Tewdros Adisu @HakimEthio
إظهار الكل...
👍 3
የኒው-ዮርክ የውስጥ ደዌ ልዮ ክሊኒክ የስነ-ደዌ ህክምና ክፍል የተለያዪ አገልግሎቶችን ይሰጣል ከእነዚህም ውስጥ የመቅኔ ምርመራ ፣ በአልትራሳውንድ የታገዘ የናሙና መውሰድ እና ምርመራ እንዲሁም በተለያዪ የሰውነት ክፍሎች ላይ ለሚወጡ እብጠቶች በቀጭን መርፌ ናሙና በመውሰድ የስነ-ደዌ ምርመራ እንዲሁም የማህፀን በር ቅደመ ካንሰር ምርመራ እናደርጋለን። Newyork's Internal Medicine Specialty Clinic pathology department serves a fluid cytology, FNAC, Ultrasound guided FNAC, peripheral morphology, bone marrow aspiration and biopsy with histopathology service and Pap-smear test are available. QUALITY CARE WITH COMPASSION! ጥራትን ከርህራሄ ጋር! ☎️ +251462219119 📞 +251925636085 📞 +251916068121 📍 Infront of Hawassa Referral Hospital. 📍ከሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ፊት ለፊት። Telegram - https://t.me/NEWYORKIM
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
Ethiopian Physiotherapy Association are delighted to invite you on upcoming panel discussion "Assistive Device and Technology Integration in Physiotherapy Practice." The event, scheduled for May 25, 2024, from 2:00 PM to 11:00 PM at the Ethiopian Sport Academy, Fill this form to secure your spot https://forms.gle/TGMvTejZuR5ovFNu9
إظهار الكل...
2👍 1
አጣዳፊ የሆነን ያልተጠበቀ (ለምሳሌ በምሽት ለሚከሰት) የጥርስ ህመም ፡ በጊዜያዊነት ለማስታገስ ፡ በቤት ውስጥ እኚህን ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል! 1. የህመም ማስታገሻ መዳኒቶች ፡ መዋጥ (መድኒቶችን ቦታው ላይ መንከስ ተገቢ አይደለም!) 2. ለብ ያለ 1 ብርጭቆ ውሀ ግማሽ ማንኪያ ጨው አሟሙቶ ፡ መጉሞጥሞጥ! 3. ቁሩንፉድ ለንቅጦ (የውስጥ ዘይቱን) ህመም ያመጥው ጥርስ ውስጥ ማስቀመጥ! 4. በረዶ ውሀ በፎጣ ጠቅልሎ ፡ በዙሪያው ማስደገፍ (በተለይ ስፍራው እብጠት ካለው!) 5. ዝንጅብል አድቆ ፡ መንከስ! 6. ህመም ያስከተለውን ነገር ከለዬ ማስወገድ (ቀዝቃዛ ውሀ ፣ ጣፋጭ ወይንም ምግብ ማኘክም ከሆነ መተው) 7. የተቦረቦረ ጥርስ ውስጥ የተሰገረ ምግብ ወይም ጣፋጭ ካለ ፡ በጥንቃቄ ማውጣት! የተጠቀሱት ሁሉም መፍትሄዋች : ጊዜያዊ 'ማስታገሻዋች' ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው እንጂ ፡ ዘላቂ መፍትሄዎች አይደሉም! ሲመቻች ወዲያው ሀኪም ቤት በመሄድ መታየት እና ቋሚ መፍትሄ መፈለግ የግድ ይላል! በቸልታ ህመሙን በተደጋጋሚ እያስታመሙ በሽተኛ ጥርስን በአፍ ወስጥ ሳያሳክሙ ማቆየት : መዘዙ የእትዬ ለሌ ነው! ዶ/ር በረከት ማተያስ : Dental Surgeon https://t.me/beckymatthiasdentalsurgeon @HakimEthio
إظهار الكل...
👍 4