cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

"ይህ ቻናል የጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ ሲሆን በጅማ ዋና ግቢ ለሚማሩ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተማሪዎች በግ/ጉ ሚትላለፉትን መልዕክት፣ት/ቶች፣ስነ ጽሁፎች እና ሌሎችም ለማድረስ የተከፈተ ቻናል ነው።" ለማንኛውም አስተያየት 👉 @natidula 👉 @MeronW_BAHIRAN 👉 @Mek_J 👉 @AsegidT

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 905
المشتركون
+524 ساعات
+157 أيام
+5130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🔔🔔🔔ተንሥኡ ለጸሎት 🔔🔔🔔 "ጸሎት፦ በሕይወት ማዕበል ውስጥ መጠጊያ ወደብ፤ ማእበል ለሚያንገላታቸው መልሕቅ፤ የድሃው ሐብት፤ የባለጸጋው ደህንነት፤ የታማሚው መዳኛ ወይም ጤና ማግኛ ነው። ጸሎት መጥፎ ነገሮችን ያስወግዳል መልካሙን ይጠብቃል።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) ➱ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እደምን ቆያችሁ? በግቢ ጉባኤው የሚደረገው የዓርብ ጸሎት እንደቀጠለ ነው። ሀላችንም እህት ወንድሞቻችንን ቀስቅሰን እንገኝ! ⏰ሰዓት - ዓርብ ጠዋት 12:15 🏠ቦታ - ታች ቤት (ጽርሐ ጽዮን) 🔔🔔🔔Kadhannaaf ka'aa 🔔🔔🔔 "Kadhannaa: Buufata baqannaa obomboleettii jireenyaa keessatti; Warra obomboleettiidhaan dararamaniif dhabannadha.   Qabeenya hiyyeessaa.  Nageenya warra dureeyyii.   Fayyisaa dhukkubsata ykn fayyina argachutti.   Kadhannaan waan badaa ni buqqisa, waan gaarii ni eega." (Qulqulluu Yohaannis Afaan warqee) ➱Jaalatamtoota maatii waaqayyoo akkam turtan? Yaa'ii mooraatti kadhannan taasifamu akkuma itti fufeetti jira. Hundi keenyaa obbollewwan keenya walin wal waamne haa argamnu. ⏰Sa'aatti : Ganama 12:15 🏠Iddoo : Taachi beeti
إظهار الكل...
🔔🔔🔔ተንሥኡ ለጸሎት 🔔🔔🔔 "ጸሎት፦ በሕይወት ማዕበል ውስጥ መጠጊያ ወደብ፤ ማእበል ለሚያንገላታቸው መልሕቅ፤ የድሃው ሐብት፤ የባለጸጋው ደህንነት፤ የታማሚው መዳኛ ወይም ጤና ማግኛ ነው። ጸሎት መጥፎ ነገሮችን ያስወግዳል መልካሙን ይጠብቃል።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) ➱ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እደምን ቆያችሁ? በግቢ ጉባኤው የሚደረገው የዓርብ ጸሎት እንደቀጠለ ነው። ሀላችንም እህት ወንድሞቻችንን ቀስቅሰን እንገኝ! ⏰ሰዓት - ዓርብ ጠዋት 12:15 🏠ቦታ - ታች ቤት (ጽርሐ ጽዮን) 🔔🔔🔔Kadhannaaf ka'aa 🔔🔔🔔 "Kadhannaa: Buufata baqannaa obomboleettii jireenyaa keessatti; Warra obomboleettiidhaan dararamaniif dhabannadha.   Qabeenya hiyyeessaa.  Nageenya warra dureeyyii.   Fayyisaa dhukkubsata ykn fayyina argachutti.   Kadhannaan waan badaa ni buqqisa, waan gaarii ni eega." (Qulqulluu Yohaannis Afaan warqee) ➱Jaalatamtoota maatii waaqayyoo akkam turtan? Yaa'ii mooraatti kadhannan taasifamu akkuma itti fufeetti jira. Hundi keenyaa obbollewwan keenya walin wal waamne haa argamnu. ⏰Sa'aatti : Ganama 12:15 🏠Iddoo : Taachi beeti
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
❖እንኳን አደረሳችሁ!❖ “እያዩት ወደሰማይ ዐረገ”(ሉቃ 24÷50 የሐዋ 1÷9) ምስባክ፦ ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ፤  ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤  ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ለሰላሳ ዘጠኝ ቀናት ያህል ለሐዋርያቱ በተለያየ ጊዜ እየተገለጠ ለአገልግሎት ሲያዘጋጃቸው እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምስጢር እያስተማራቸው ከቆየ በኋላ በ፵ኛው ቀን በሐዋርያቱ ፊት አርጓል።  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው የጌታችንን አበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው።  ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣ በ፵ኛው ቀን ወደ ሰማይ አረገ ያረገበትም ቦታ ቢታንያ አጠገብ የሚገኘውደብረ ዘይት የሚባለው ተራራ ነው። አሥራ አንዱ ሐዋርያትን እዚያ ድረስ ከወሰዳቸው በኋላ ባርኳቸው እያዩት ዐረገ። ደመናከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።  ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሩ፤ በመለኮታዊ ክብሩ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ ተቀመጧል። ጌታችን ያረገውም በለበሰው ሥጋ በመሆኑ እና ለሁለተኛ ጊዜ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ ይህን ክብር እኛም  እንድናገኝ ምሳሌ ሲሆነን ነው። በሚመጡ ዘመናትምበክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣንበክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ኤፌ . ፪፡፮ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕርገቱ አስመልክቶ ከተናገራቸው  ሦስት ነገሮች ውስጥ፦ 📌 የመጀመሪያው፤ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። ዮሐ . ፲፪፡፴፪ 📌 ሁለተኛው ደግሞ፤  ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሐ . ፲፬፡፲፰ 📌 ሶስተኛው፤ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። ዮሐ . ፲፮፡፯   የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ለእኛ ትልቅ ተስፋ ነው ስለዚህም ሐዋርያት ጌታችን ሲያርግ ወደሰማይ ትኩር ብለው ይመለከቱት እንደነበር እኛም በታላቅ ተስፋ የጌታን ነገር ልናስብ ይገባል። ነቢዩ ዳንኤል ስለ ጌታችን ዕርገት እና በአብ ቀኝ ስለመቀመጡ እንዲህ ሲል በትንቢት ተናግሮ ነበር፤ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅየሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥መንግሥቱም የማይጠፋ ነው። ዳን . ፯፡፲፫ - ፲፬   ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በአብ ቀኝ ተቀመጠስንል ጌታ ከአብ ጋር እኩል ነው ማለታችን ነው። ከ፬ቱ ወንጌላት ውስጥ ይህን የዕርገቱን ታሪክ የመዘገቡት የማርቆስ ወንጌልና የሉቃስ ወንጌል ናቸው።  ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤ እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደታያት ሲሰሙ አላመኑም። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤ እነርሱም ሄደውለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም። ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶምያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ። እንዲህም አላቸው። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንምለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶችይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥ የሚገድልም ነገር ቢጠጡአይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። ማር. ፲፮፡፱-፲፱  እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ። እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየወደ ሰማይም ዐረገ። ሉቃ. ፳፬፡፵፰-፶፩  ቅዱስ ሉቃስ የሐዋርያት ሥራን ሲጽፍ ስለ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት አብራርቶ ጽፎታል።  እንዲህ ሲል፦ ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖለእነርሱ ራሱን አሳያቸው። ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን። ከእኔ የሰማችሁትንአብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤ ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስትጠመቃላችሁ አለ። እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለውጠየቁት። እርሱም አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ ነገር ግንመንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድርዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎችበአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው። ሐዋ. ፩፡፫-፲፩  ክርስቲያኖች በሰማያት ስፍራ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው እንደሚቀመጡ የእርሱ ዕርገትያረጋግጥልናል። ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ጌታችን እርገት እንዲህ ሲል ይመክረናል፤ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና። ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበትጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።  ቆላ. ፫፡፩-፬   ኖርንም ሞትንም የክርስቶስ ነንና ዘላለማዊ ሕይወትን እንወርስ ዘንድ አምላካችን ይርዳን። ልዑል እግዚአብሔር በኑሮአችን ሁሉ ባርኮን፤ ቀድሶን፤ በእርሱ ፈቃድ እንድንኖር ይርዳን። የምንሻትን መንግስተ ሰማያትን ያወርሰን ዘንድ የእናቱ የድንግል ማርያም አማላጅነት፤ ስለ እርሱ ክብር ሲሉ ሕይወታቸውን ሰውተው ያለፉት ቅዱሳን ሰማዕታት ምልጃ እና ጸሎት አይለየን አሜን።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
አስቸኳይ ማስታወቂያ The Inspired Youth Association ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ለግቢ ጉባኤ ምሩቃን ልዩ የሥልጠና እና የሥራ ዕድል አመቻችቷል። በመሆኑም ከሥር የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን። ሥልጠናው ጊግ 101 ወይም የቁርጥ ጊዜ ስራ በመባል ሲታወቅ ሥልጠናውንም ሲያጠናቅቁ ሰርተፍኬትና ባጅ ያገኛሉ ለመመዝገብ: ✅ይህን ሊንክ https://forms.gle/n58myyknKTiQK3xK8 ቴሌግራም ቦቱ ላይ ገብተው የሚከተሉትን ጥያቄዎች ሲጠየቁ ከዚህ በታች የተሰጠውን መልስ ያስገቡ መረጃውን ከየት አገኙት ? መልስ👇👇👇👇 ከዘ-ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሲዬሽን ሪፈራል ኮድዎን በ IEYA**** ቅርጸት ያስገቡ:- መልስ👉👉 0102 ሳይቀደሙ በቶሎ ይመዝገቡ! በነፃ ተምረው ተፈላጊነትዎን ይጨምሩ! ✅ በነፃበስልክዎ ብቻ ✅የአጭር ጊዜ ሥልጠና መሥራት በተሰኘው በገበያ ማስተር ካርድ ፋውንዴሽና በ አጋሮቻቸው ጥምረት ለተመሰረተው ይህ ፕሮግራም ከ ዘ ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሲዬሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ
إظهار الكل...
👍 5🥰 1👏 1
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔        የአጽዋማት ማውጫ                 ፳፻፲፮ ❖ጾመ ነነዌ -የካቲት 18 ሰኞ ❖ዓቢይ ጾም- መጋቢት 2 ሰኞ ❖ደብረ ዘይት- መጋቢት 29 እሁድ ❖ሆሳዕና- ሚያዝያ 20 እሁድ ❖ስቅለት- ሚያዝያ 25 አርብ ❖ትንሣኤ- ሚያዝያ 27 እሁድ ❖ርክበ ካህናት- ግንቦት 5 ረቡዕ ❖እርገት- ሰኔ 6 ሐሙስ ❖ጰራቅሊጦስ- ሰኔ 16 እሁድ ❖ጾመ ሐዋርያት- ሰኔ 17 ሰኞ ❖ጾመ ድኅነት- 19 ረቡዕ   
إظهار الكل...
🙏 5👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
💐"ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን!" [፪ቆሮ ፱፥፲፭]💐 እንኳን ደስስስ አላችሁ!🥰 በእውነት እግዚአብሔር ይመስገን🙏 " ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።" (መዝ 117: 26) ⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️ ➛ውድ ኦርቶዶክሳውያን ተመራቂ  ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!💐እነሆ ግቢ ስትገቡ የተቀበለቻችሁ ግቢ ጉባኤ አመስግና አደራ ሰጥታ ትሸኛችኋለች እንዳትቀሩብን።🙏 ➛በልዩ ልዩ ጸጋ ቤ/ክያንንም አኛንም ሲያገለግሉ የቆዩ ዕንቁ አገልጋይ ተማሪዎችን ለመሸኘት፤ መልካም ለመመኘት የሚቀር ተማሪ መቼስ አይኖርም። 🌹ቀን: ሰኔ 8/2016 ዓም 💐ዕለት: ቅዳሜ 🌹ሰዓት: 3:00-6:30 💐ቦታ: ሐ/ኖ/ቅ/ኪዳነ ምህረት አዳራሽ እግዚአብሔር በሠላም ለዕለቱ ያድርሰን🙏 ➡ጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
📣ሰንበትን በቅዳሴ!🥰 ከትንሣኤ በኋላ ስድስተኛው ሰንበት "የበዓላትን በኩር ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት። ኑ እናክብራት። ኑ እናመስግናት። ኑ በዓል እናድርጋት። ይህቺውም ቅድስት ሰንበተ ክርስቲያን ናት። ይህች ቀን እግዚአብሔር ሥራ የሠራባት ናት እንበል። በእርሷም ደስ ይበለን ኀሴትም እናድርግ..." #ቅዳሴ-አትናቴዎስ የዕለቱ ምንባባት፦ ሮሜ ፮÷፩-፲፭ ፩ጴጥ ፬÷፬-፲፪ ግብ:ሐዋ ፳፫÷፲፭-፳፪ የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፳፬÷፲፭-ፍ:ም ምስባክ:- መዝ ፻፮÷ ፲፮ እስመ ሰበረ ኆኃተ ብርት፤ ወቀጥቀጠ መናሥግተ ዘኃፂን፤ ወተወከፎሙ እምፍኖተ ጌጋዮሙ። መዝሙር ዘሰንበት፦ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፋሲካ፤ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ፤ፋሲካ ዛቲ ዕለት ንትፈሣሕ ባቲ፤ፋሲካ ንትፈሣሕ ባቲ ወንትኃሠይ ባቲ፤ፋሲካ ዛቲ ዕለት ናኅይ ወዕረፍት፤ፋሲካ ሰማይ ወምድር ይትፌሥሑ ባቲ፤ፋሲካ ፋሲካ ፋሲካ ፋሲካ፤ተዝካረ ትንሣኤሁ ለመድኃኒነ። ትርጉም፦ ፋሲካ!  ይህች ዕለት ቅድስት ናት ይህች ቀን ፈጽመን የምንደሰትባት ቀን ናት ይህች ዕለት ፍጹም የዕረፍት ቀን ናት ሰማይና ምድር ይደሰቱባታል ፋሲካ የመድኃኒታችን የትንሣኤው መታሰቢያ ናት። 👉 ሰንበትን በታላቁ ድግስ ቅዳሴ ተጠራርተን በጋራ እናስቀድስ። @JuWanaGibiGG @JuWanaGibiGG @JuWanaGibiGG "ለክርስቶስ ከሚኖር ሰው በቀር ነጻ ሰው የለም!”  - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #ጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግቢ ጉባኤ
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram