cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ትምህርት በቤቴ/Timehirtbebet

ትምህርት በቤቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የሚያቀርብላቹ ፕሮግራም ነው።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
210
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ጅማ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ በቆየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የውይይት መድረክ የተነሱ ኃሳቦችን ከመድረኩ ተሳታፊ አካላት ጠይቀን ተከታዩን መርጃ ሰጥተውናል ፦ - ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን የመቀበል ዝግጁነታቸውን እስከ መስከረም 25/2013 ዓ/ም ድረስ እንዲያሳውቁ በመድረኩ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ዝግጁ የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ከመስከረም 25 ጀምሮ መጥራት ይችላሉ፡፡ - በቀድሚያ ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ይደረጋል፡፡ - ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተወጣጣ የዩኒቨርስቲዎችን ዝግጁነት የሚያረጋግጥ ግብረ-ኃይል የተቋቋመ ሲሆን ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ይመለከታል። - ዩኒቨርሲቲዎች በጥሪ ጊዜ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንዳይኖር ዩኒቨርሲቲዎች ተናበው እንዲሰሩ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለተማሪዎች እንዲያመቻቹ ኃሳብ ተነስቷል፡፡ - የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ወደ ግቢ እንዲገቡ ጥሪ እየተደረገ ይገኛል፡፡ - በዚህ ዓመት ሌላው ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው የዲሲፒሊን ጉዳይ ሲሆን ባለፈው ዓመት የተፈጠሩ ክስተቶች እንዳይደገሙ ሁሉም ባለድርሻ አካል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።
إظهار الكل...
ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም ተገኝተዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ስለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ገለፃ አድርገዋል። በዚሁ መሰረት የትምህርት ቤት አከፋፈት ሂደቱ በሶስት ዙር እንደሚከናወን አስታውቀዋል ፦ - በመጀመሪያው ዙር ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በገጠር ወረዳ እና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ፤ - በ2ኛ ዙር ጥቅምት 16 ቀን 2013 በሁሉም የዞን እና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ፤ - በአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።
إظهار الكل...
ተጨማሪ ፦ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው። በተመሳሳይ ደግሞ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁ እና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሚሰጥ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። (MoE
إظهار الكل...
#UPDATE የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ሐረጓ ማሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ እንደገለፁት ፥ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ እያካሄዱት ያለው ውይይት ዛሬ አልተጠናቀቀም ፤ ነገ ጥዋት መግለጫ ይሰጣል ብለውናል።
إظهار الكل...
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ውይይት እያካሄዱ ነው! ውይይት እየተካኔደባቸው እና ውሳኔ ከሚያገኙ ጉዳዮች መካከል ፦ - የመደበኛ ትምሀርት የሚጀመርበት ቀን ፣ - የ8ኛና 12ኛ ክፍል ክልላዊና ሀገራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን - እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች ላይ እየቀረበ ባለ ቅሬታ ላይ ውሳኔ የሚሰጥ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አዲሱ የትምህርት ስርዓት ዝግጅት አካሄድ እና ሁኔታ በውይይቱ ላይ የሚገመገም እና ውሳኔ የሚሰጠው ይሆናል። የጎልማሶች ትምህርት አሰጣጥ እና አፈፃፀምም በውይይቱ ውሳሄ ከሚያገኙ ጉዳዮች መካከል ነው። በውይይቱ ላይ የተደረሰው ውሳኔ ነገ በ9:00 ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል። (MoE) https://t.me/Timehirtbebete https://t.me/Timehirtbebete
إظهار الكل...
ትምህርት በቤቴ/Timehirtbebet

ትምህርት በቤቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የሚያቀርብላቹ ፕሮግራም ነው።

ትምህርት በፈረቃ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ! ትምህርት ሲጀመር የትምህርት አሳጣጥ ሂደቱ በፈረቃ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በፈረቃ የሚሰጠው ትምህርት እንደየአካባቢው ሁኔታ ከ2 እስከ 3 ፈረቃ ተከፍሎ ሊሰጥ እንደሚችልም ተገልጿል። የመማር ማስተማር ሥራው በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደሚጀመር ትምህት ሚኒስቴር አመልክቷል። ሚኒስቴሩ እንዳለው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ተቋርጦ የቆየው መደበኛ ትምህርት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ዳግም ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል። መንግስት በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፣ ውሃ እና የእጅ ማጽጃዎችን በማሟላት እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን በማጽዳት መደበኛው ትምህርት እንደሚጀመር አስታውቋል (ENA)
إظهار الكل...
Maths G.9 Geometry and Measurement Share via https://t.me/Timehirtbebete https://t.me/Timehirtbebete
إظهار الكل...
إظهار الكل...
Biology G.9 – Unit 3 – Human Biology and Health Share via https://t.me/Timehirtbebete https://t.me/Timehirtbebete
إظهار الكل...
PHYSICS GRADE 9 Share via https://t.me/Timehirtbebete
إظهار الكل...