cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኢልም ለሁሉም

#አቂዳህን ውሠድ ሚነል ኪታብ ወሱና ከትክክለኛዋ አሷም መነሀጂ አሠለፍ ናት ፊርቀቱን ናጂያህ #ማንኛውንም አስተያዬት ፣ ምክር ፣ ባጠቃላይ ቻናሉን በተመለከተ ወሳኝ #ጥቆማ ካለዎት ...በዚህ ይጠቀሙ !! ሥህተትም ባያችሁ ጊዜ እርሙኝ ! ጀዛኩሙሏህ ኸይራ! @SualihMuhammed @bintYahyaAselefiya

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
626
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ተውሒድ የሁሉም ነብያት መንገድ። YouTube ቻናሌን Subscribe ያድርጉ። https://youtube.com/watch?v=r7HnXjlnRCM&feature=share
إظهار الكل...
ተውሒድ የሁሉም ነብያት መንገድ። YouTube ቻናሌን Subscribe ያድርጉ።

15 ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች ~ · ① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። መምህር "አስተማሪ" የተባለው ስለሚያስተምርህ ነው። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ። "አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።" "ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።" ② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚገድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የሃንዳውት፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ። ③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው። "ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።" ④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው። "ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።" ⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ እራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ እንዳለው ተረዳ። "Education is a better safeguard of liberty than a standing army." ⑥ እራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ እንጂ። አንተ'ኮ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም። "እራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።" ⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም ። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሐብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል። እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮች ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው። "ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።" "አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ እራስህ እያለፍክ ነው።" ⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ እራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ። "ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።" ⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። አትንበጣረር፤ ግን አትጥመስመስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ። ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ። "ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።" (10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ እንደ ቴኳንዶ ያሉ ራስን መከላከያ ሥልጠና፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ። "ሰው ማለት፣ ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት።" (11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን። "ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።" "ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።" (12) የት/ቤት ክበባት አብዛኞቹ ቁም ነገር የማይሰራባቸው ትርኪ ምርኪ ናቸው። ካልተገደድክ በስተቀር አትግባባቸው። ከተገደድክ መርጠህ ለመግባት ሞክር። ከገባህም ሸሩን ለመቀነስ፣ እሴት ለመጨመር ጣር። "ህይወት መቀለጃ አይደለም።" "ብልህ ሰው በሚወረወርበት ድንጋይ ቤት ይሰራል።" (13) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነት ዋጋ የሚሰጥ ሰው ለቆሻሻ ነገሮች አይንበረከክም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ኣ? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። እራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም። "እራስን በሱስ በመጉዳትና እራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"
إظهار الكل...
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

⏳የመጨረሻው በረራ🚻🚷🚯📵🚫 ┏××××××××××××┓ 👉#የተጓዡ ስም፦የአደም ልጅ 👉#ፆታ፦ ወንድ ወይም ሴት ሊሆን ይችላል 👉#ዕድሜ፦በአማካይ ከ60-70 አመት በተለይ ለነብዩ ﷺ ዑመት 👉#ስራ፦ አላህን መገዛት 👉#ልዩ_መለያው፦ ከሌሎች ፍጥረታት የሚለየው ዐቅል(አዕምሮ) የተባለ ልዩ የማሰቢያ መሳሪያ የተገጠመለት 👉#የመጀመሪያ_መገኛ፦ አፈር 👉#የመኖሪያ_አድራሻው፦ መሬት የተባለች ፕላኔት። 👉#መነሻው፦ አዱኒያ የተባለች ልፋትና ፈተና የበዛባት ለመድረሻው አገር ስንቅ መቋጠሪያ የሆነች አለም። 👉#የትራንዚት_አገር፦ መቃብር የሚባል ሰፈር 👉#በትራንዚት_ስፍራው_የቆይታ_ጊዜ፦ በዐመት ለመግለፅ ይከብዳል። የመቀስቀሻ ጥሩንባ እስኪነፋ ጊዜያዊ የመቆያ ቦታ ይሆናል። 👉#የበረራው_ምክንያት፦ በዱንያ ላይ የቆይታ ጊዜው ስላለቀ 👉#መድረሻ፦ አኼራ የሚባል ዘላለማዊ አገር ሲሆን እሳት እና ጀነት የሚባሉ ስቴቶች አሉት 👉#የማጓጓዣው_ስምና_አይነት፦ ምት የተባለ በአይን የማይታይ ድምፁም የማይሰማ ፈጣን በራሪ 👉#ዋነኛ_አብራሪ፦ መለከተል መውት(የሞት መልአክት) 👉#የበራሪው_ቀንና_ሰዐት፦ አይታወቅም ፤ በየትኛውም ሁኔታና አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። 👉#ልዩ_ማሳሰቢያ፦ ይህ ጉዞ የሚካሄደው በድንገተኛ ሁኔታና ተጓዡም በራሱ በሚመቸው ጊዜ ትኬት ቆርጦ ሳይሆን ሳያስብና ሳይዘጋጅ ተቆርጦለት በመሆኑ ማንኛውም የአደም ልጅ ለዚህ ጉዞ እራሱን ማዘጋጀትና በንቃት መጠበቅ ያለበት ሲሆን ጓዙንም ከወዲህ መሸከም ይኖርበታል። 👉#ለጉዞው_መሣካት_እጅግ_ጠቃሚው_ስንቅ፦ መልካም የተባለና ሸሪዐዊ ድጋፍ ያለው ስራ ሁሉ መስራት። 👉በአሸኛኘት ስነ ስርዐት ላይ ተጓዡን የሚከተሉ አጃቢዎች ፡ 👉ከ 2 ሜትር ያላነሰ ተጓዡ የሚለብሰው ነጭ ጨርቅ 👉#የተጓዡ_ንብረቶች፦ ከመነሻ ስፍራ ወደ ትራንዚት ቦታው ተጓዡን ለማድረስ የሚያገለግሉ የተለያዩ ነገሮች 👉ጥሩ ይሁን መጥፎ ስራው 👉ቤተሰቡ 👉እስከመጨረሻው_ከተጓዡ_ጋር የሚቆይ_ወዳጅ፦ መልካም ስራ 👉በትራንዚሽን ስፍራው የሚቀርቡ ሁሉም የሰው ልጅ ሊዘጋጅላቸው የሚገባ ዋና ዋና ጥያቄዎች 🗣ጌታህ ማነው? 🗣ነቢይህስ ማነው? 🗣ቂብላህስ? 🗣ሀይማኖትህስ? 🗣ኪታብህ/መፅሀፍህ? 👉ከተጓዥ ሽኝት በኋላ ምድር ላይ ቀርተው ሊጠቅሙ የሚችሉ ነገሮች፦ 🎯ቀጣይ የሆነ ሰደቃ(ሰደቀቱል ጃርያ) 🎯ከአላህ ምህረትን የሚለምንለት መልካም ልጅ 🎯ተጓዥ በህይወት ዘመኑ በቅርስነት አኑሮት(ሰዎች አስተምሮ) ያለፈው ጠቃሚ ዕውቀት 👉ከትራዚሽን_በኋላ፦ 🎯ከተወሰነ ቆይታ በኋላ የአደም ልጅ ጌታው ፊት ለመቆም ወደ አንድ የመሰብሰቢያ ቦታ ይነዳል። ሁሉም ከመነሻ ሀገር ይዞ እንደመጣው ስራ ውጤቱ ይሰጠዋል። 👉በጭንቀቱ ወቅት ልዩ መስተንግዶ የሚጠብቃቸው፦ 🎯ፍትሀዊ ኢማም(መሪ) 🎯በአላህ ኢባዳ ያደገ ወጣት 🎯ልቡ ሁሌም በመስጅድ ተንጠልጥሎ ያለ ሰው 🎯ለአላህ ብቻ ሲሉ ተዋደው በዚያው ሁኔታ ኑረው በመዋደድም የተለያዩ 🎯ቆንጆና እጅግ ከተከበረ ቤተሰብ የሆነች ሴት ለዝሙት ጋብዛው አላህን ፈርቶ ስሜቱን የተቆጣጠረ 🎯ለብቻው ባለበት ሁኔታ ሳለ ከአላህ ፍራቻ ያለቀሰ/💡 📔🔊"እያንዳንዱ ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት የስራ. ዋጋችሁን የምትሰጡትም የትንሳዔ ዕለት ነው። ከእሳት እንዲርቅና ጀነት እንዲገባ የተደረገ በእርግጥ ስኬታማ ሆኗል። የዚህች ዐለም ህይወት መጣቀሚያ እንጂ ሌላ አይደለም።"(ቁ.ም 3:185) 📔🔊"የትም ቦታ ብትሆኑ (ሌላው ቀርቶ) ከጠንካራ ህንፃዎች ውስጥም ብትሆኑ (ብትደብቁ) እንኳ ሞት ያገኛችኋል።" 📔🔊"ያ የምትሸሹት ሞት ያገኛችኋል ከዚያም የሩቁንም የቅርቡንም ዐዋቂ ወደ ሆነው (አምላክ) ትመለሳላችሁ ትሰሩት የነበራችሁትንም ይነገራችኋል።"(ቁ.ም 62:8) ──────⊱◈◈◈⊰────── https://t.me/EilmForAll 💡 @ https://t.me/IbnuTeyimiyahMedresa #share_The_خير
إظهار الكل...
ኢልም ለሁሉም

#አቂዳህን ውሠድ ሚነል ኪታብ ወሱና ከትክክለኛዋ አሷም መነሀጂ አሠለፍ ናት ፊርቀቱን ናጂያህ #ማንኛውንም አስተያዬት ፣ ምክር ፣ ባጠቃላይ ቻናሉን በተመለከተ ወሳኝ #ጥቆማ ካለዎት ...በዚህ ይጠቀሙ !! ሥህተትም ባያችሁ ጊዜ እርሙኝ ! ጀዛኩሙሏህ ኸይራ! @SualihMuhammed @bintYahyaAselefiya

🔻ይደመጥ ‼️ ▪️በየሀገሪ ሰሞኑን የተከሰቱ ጉዳዩች 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ▪️በ ሀገራዊ ጉዳይ የተሰደዱ ወንድም እህቶች ላይ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን" 🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ 👇👇👇👇👇👇👇👇 on YouTube https://youtu.be/95ukb8XSqWM
إظهار الكل...
💢የጋብቻ ቀለበት ➖➖➖➖➖➖ ◾️‏قال العلامة الألباني : 🔘ሸኽ አልባንይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል። 【وضع خاتم الخطوبة في يد العروس من عادات النصارى وقد أمرنا بمخالفتهم】 ✅ አንድ ሰው በሚያገባት ሴት ላይ የጋብቻ ቀለበት ማድረጉ የክርስቲያኖች ልምድና ተግባር ነው። እኛ ደሞ እነሱን በመፃረር ላይ ታዘናል። 📗(أداب الزفاف ص ٢١٢) t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1774 t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1774
إظهار الكل...
ኢብኑ ተይሚያ የተውሂድ የሱና ቻናል

💢የጋብቻ ቀለበት ➖➖➖➖➖➖ ◾️‏قال العلامة الألباني : 🔘ሸኽ አልባንይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል። 【وضع خاتم الخطوبة في يد العروس من عادات النصارى وقد أمرنا بمخالفتهم】 ✅ አንድ ሰው በሚያገባት ሴት ላይ የጋብቻ ቀለበት ማድረጉ የክርስቲያኖች ልምድና ተግባር ነው። እኛ ደሞ እነሱን በመፃረር ላይ ታዘናል። 📗(أداب الزفاف ص ٢١٢) t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1774 t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1774

// #ሀያዕ_ነው_ውበታችን !! እውቀት ይኑርሽም አይኑርሽም ሀያዕ ለሴት ልጅ ወሳኝ ነው ወላሂ ደግሞ እውቀት ያለ ሀያዕ ልክ የላጭን ልጅ ቅማል በላው አይነት ነው አባቱ ላጪ ሆኖ ልጁ ቅማል ከበላው ነገሩ አለቀ,ከልብ ሆነሽ ይህን ምሳሌውን አስተንትኚው,..እውቀቱ ኖሮ ሀያዕ ከሌለ አበቃ ምንም አይፈይድሽም ጋን ሙሉ አተላ ተሸክመሽው እዳ ነው የሚሆንብሽ..እውቀቱ ኖሮሽ ሀያዕ ከሌለ ያለ እርሾ የተቦካሽ ሊጥ ብለሽ ውሰጂው ራስሽን..። የሴት ልጅ ውበቷ ሚረግፈው እድሜዋ ሲገፋ አይደለም "ሀያዕ" ስታጣ አደብ ይሉኝታ ሲርቃት ሁለ ገብ እዚያም እዚህም አለቅላቂ ስትሆን ነው። ሀሀሀ፣ቂቂቂ፣ ክክክ፣ የኔ ማር፣የኔ ቆንጆ፣ ውዴ ስወድሽኮ ውድድድድ አንች ማለት ለኔ ወዘተ..ይህ ሁሉ የኛ የሴቶች ስራ ነው.ወንዶቹ አያውቁትም እዚህ ትርኪ ምርኪ ተራ እኛ እንጂ እነሱ የሉም አሁን አሁን ደግሞ ኮሜንት ቂቂ አንች እደዝህ ብለሽ፤ ሀሀሀ አንተ እንደዚህ ብለህ፣ በየኮሜንቱ ውል ውል ለጥቅም አልባ ነገር ያስጠላል። ሀያዕ አጣሽ ማለት ራስሽን አጥር የሌለው ግቢ ብለሽ አስቢው..ለአላፊ አግዳሚው ለወጭ ወራጁ ቅርብ ሲያሻው እዚችው ፌስቡክ ላይ ለግዜው ማረፊያ ሲያሻውም መደበሪያ ያደርግሻል. አልፎም አንች ላይ የአደብ እጦት የድርቅና ቡቃያ ይበቅልብሻል ከዚያ ያድግና መጨረሻሽን ያበላሸዋል። እህቴ ሆይ ልብ በይ ራሴን ፍፁም አድርጌ አይደለም..የፊትሽን ገፅታ በመስታወት ካላየሽው የት ታቂውና.እናማ ያንች ነገርሽ ከብዙው ጥቂቱ እንጂ ስራሽ ሁሉ ጎልቶ አይታይሽም ለዚያም ነው የፃፍኩት..እኔ እደመስታወቱ በዝምታ ራስሽን አላሳየሁሽም ከሱ አልተሻልኩም ይልቁን በፅሁፍ ነው እሱማ ዝም ብሎ ራስሽን እድትመለከቺ ያደርግሻል ለምን,? እሱ ገፅታሽን እኔ ግን ንግግርሽን ነው የማሳይሽ እሱ ስለ አቋምሽ እንጂ ስለ ንግግርሽ ማሳያ ተሰጦ የለውም። ፌስቡክ ላይ እንደምታይው ተወያይዉ ሳይሆን ተነታራኪው በዝቷል ያኔ ገብተሽ ከምትበሻሸቂ ከቻልሽ ለነገሩ ማስረጃ ምላሽ መስጠት ካልቻልሽ መተው ማንን ጎዳ ዝም በይ ትተሽ እለፊ "ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህመልዕክተኛ ፤ለአሸጅ አብዱልቀይም እንዲህ ብለውታል፦ (አላህ የሚወዳቸውን ሁለት ባህርያት አለህ ቻይነትና፤እርጋታ።"(ሙስሊም ዘግበውታል) - ሙስሊም ዘግቦታ" ሀያዕሽ እርጋታን ይሰጥሻል መቻልሽ በማያገባሽ አለመግባትሽን ይይዝልሻል ልትናገሪ ካሰብሽው መጥፎ ቃላት ይልቅ ቻል አድርገሽ ስሜትሽን ገያ አድርገሽ እድታልፊ ያስችልሻል። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:- የማይመለከተውን ጉዳይ መተው ለአንድ ሰው ከእስልምናው መዋብ ነው።ቲርሚዚ እና ኢብኑ ማህጃ ዘግበውታል። ብዙ ማለት ብችል ባልኩኝ ነበር..እህቶቼ አላህን እንፍራ ከኛ አልፎ አሁን አንዳንድ ወንዶች ብቅ ብቅ ማለትን ጀምረውታል ሀሀሀ ቅቅቅ ሆኗል በየቦታው ከባዮች:- ከወንድም ይሁን ከሴቱ ጥቅሙ ተሽለን መገኝቱ ሀያዕ ዋናውና የውስጣችን ሂጃብ ነው አላህ ለኔም ለአንችም ሀያዕ ይወፍቀን !!!!
إظهار الكل...
🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን  አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)   📚 ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች ድምፅ ፋይል ከሚከተለው ቴሌ ግራም ቻናል ያውርዱ             •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈• 🌐 https://t.me/AbumuslimKitaboch     •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
إظهار الكل...
Abumuslim Kitaboch

📚 قناة ينشر فيها دروس التي انتهي تدريسها المتعلقة بالعقيدة وغيرها للأستاذ أبي مسلم عمر العروسي. 📚 ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች በከፊል የሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ጆይን በማለት ተቀርተው ያለቁ ሙሉ የኪታብ ኦዲዬዎችን ዳውን ሎድ ያድርጉ፡፡             🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን  አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ) 

👆👆👆 #የኢማን መሰረቶች ስድስት ናቸው። የሚለው ሐዲሥ ተከታታይ ማብራሪያ ክፍል 1 🔶በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን በምስራቅ ስልጤ ገርቤ በር ወረዳ በቢላል መስጂድ የተደረገ ሙሐደራ። 🎙 በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ) 🌐 https://t.me/shakirsultan
إظهار الكل...
ወጣትነት ከትናንት ጥገኝነት የምንወጣበት፣ ለነገ አሸናፊነት የምንሰንቅበት ዛሬ ነው። ግን አስታውስ! ከስንቆች ሁሉ በላጩ ተቅዋ ነው።
إظهار الكل...