cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

✍✍✍✍ዮቶር✍✍✍✍✍

ትልቁ ትምህርት ቤት በዚህ channel የኢትዮጵያን ታላቅነት እንመሰክርበታለን። እንማርበታለን።እናስተምርበታለን።እናንተም የምታውቁትን ታሪክ፡ባህል፡ቅርስ እንድናስተዋውቅ በዚህ ይላኩልን @honeanimut። እኛ ተቀብለን ለሁሉም እናደርሳለን። ማንበብን ልምድ እናድርግ። እያንዳንዷ ማክሮ ሴኮንድ እኛን ልታስተምር እየዞረች ነው። እኛ ከሰዓቱ ተመሳሳይ አቅጣጫ እኩል መጓዝ አለብን እንጅ ተቃራኒ አንጓዝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
128
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🙏እንኳን ወደ Offical RIDE BIRR ቦት በደህና መጡ. በRide Birr ቦት ለዘመድ አዝማድ እና ለጓደኛዎ ሼር በማድረግ በCBE BIRR / ሞባይል ባንኪግ እና በ AIR TIME / ሞባይል ካርድ ገንዘብ መስራት ይችላሉ! ♻️1 ሰው ሲጋብዙ 5.00Birr ያገኛሉ 🔻ራይድን ይቀላቀሉ ➡️https://t.me/Ride_br_Bot?start=r0766953364
إظهار الكل...
🙏እንኳን ወደ Offical RIDE BIRR ቦት በደህና መጡ. በRide Birr ቦት ለዘመድ አዝማድ እና ለጓደኛዎ ሼር በማድረግ በCBE BIRR / ሞባይል ባንኪግ እና በ AIR TIME / ሞባይል ካርድ ገንዘብ መስራት ይችላሉ! ♻️1 ሰው ሲጋብዙ 5.00Birr ያገኛሉ 🔻ራይድን ይቀላቀሉ ➡️https://t.me/Ride_br_Bot?start=r0766953364
إظهار الكل...
በምንችለው መልኩ እያደረስን፣በቤተ መቅደስ እየተገኘን ኪዳን እያደረስን፣ቅዳሴ እያስቀደስን ከፈጣሪን ጋራ እለት እለት እንነጋገር ጸሎት ከሌለ መንፈሳዊነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ከጄነሬተሩ ተቋርጦ ገመዱ ተበጥሶ ብቻውን እንደተንጠለጠለ አምፖል መሆን ይመጣል፡፡ስለዚህ በርቱ ጸልዩ ፈጣሪ ለሁላችንም ብርታቱን ያድለን፡፡አሜን 𝕒𝕟𝕚𝕞𝕦𝕥 𝕙𝕠𝕟𝕖
إظهار الكل...
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘለአለም ትኑር ሰባቱን የጸሎት ጊዜያት ጠብቀን መጸለይ ካልተቻለንስ? በሰባቱ የጸሎ ሰዓታት የታቻለንን ያህል እንድንጸልይ ታዘናል፡፡እነዚህን የጸሎት ሰዓታት በገዳም ያሉ መነኮሳት በየበረሃው የሚዞሩ ባሕታውያን ይጠብቋቸዋል፡፡ይጸልዩባቸዋልም፡፡በከተማ በሥራ ምክንያት ሩጫ በዝቶበት በሁሉም ሰዓት መጸለይ የማይችል ክርስቲያን ግን ቢያንስ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነሳ እና ማታ ወደ መኝታው ሲያመራ መጸለይ ይገባዋል።ጠዋት እና ማታ በመጸለይ ከፈጣሪ ጋራ ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡ ምን እንጸልይ? በመደበኛነት ልንጸልያቸው የሚገቡ ጸሎታት /በቤተክርስቲያናችን አባቶች በገዳማቱ በአድባራቱ የሚዘወተሩ እለታዊ ጸሎታት/ እነኚህ ናቸው፡፡ 1.መዝሙረ ዳዊት መዝሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት ባህታውያን ጀምሮ በካህናት፣ምእመናን በሁሉም ዘንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው።አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዚህ ጊዜ ጀምረው እየደገሙት፣እየጸለዩበት ይኖራሉ።ዳዊት ሳይደግሙ ወደ ዕለታዊ ተግባራቸው አይሰማሩም።መዝሙረ ዳዊት እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው።ቀጥለን እንመልከት ሰኞ ከ 1 - 30፣ማክሰኞ ከ 31 – 60፣ረቡዕ ከ 61 – 80፣ሐሙስ ከ 81 – 110፣አርብ ከ 111 – 130፣ቅዳሜ ከ 131 – 150 እሁድ- ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ይጸለያል፡፡ አንድ ንጉሥ መዝሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታዘዘውን ሃያ እና ሰላሳ መዝሙር ማድረስ ባንችል እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ ይገባናል። አንድ ንጉሥ የሚባለው፡-አስር መዝሙር ነው፡፡ለምሳሌ ሰከኞ አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ 1 – 10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ 30 -40 ያውን የመጀመሪያውን አስር መዝሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው ግን የተወሰኑ መዝሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡ 2. ውዳሴ ማርያም ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው።የዘወትር ጸሎት ካደረስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን ደግመን ከእመቤታችን በረከት ተሳታፊ መሆን ተገቢ ነው፡፡በዋልድባ የሚኖሩ መነኮሳት ውዳሴ ማርያም ከቅዳሴ ማርያም ሳያደርሱ ውለው አያድሩም፡፡በየአብነት ትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎች እና በየገዳማት ያሉ መነኮሳት ሁሉ ውዳሴ ማርያምን በየዕለቱ ያደርሳሉ፡፡እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡ 3. ወንጌል ዘዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው ጸሎት ነው፡፡አባቶች ይህንን ጸሎት በየእለቱ እያደረሱ ብዙ ተጠቅመውበታል። 4.ሌሎች ጸሎታት ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም ፣ በመዝገበ ጸሎት እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣እንዲሁም ገድላት፣ተአምራትን፣እንደችሎታችን በየዕለቱ እናደርሳለን፡፡ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን የመዝሙረ ዳዊትና ፣ውዳሴ ማርያምን ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡ አጭር ጸሎት በተቻኮልን እና መጻሕፍትን ለማንበብ ጨርሶውን ጊዜ በማይኖረን ሰዓት ይህንን እንድንጸልይ አንዳንድ አባቶች ይመክሩናል።አቡነ ዘበሰማያት፣ጸሎተ ሃይማኖት፣ሰላም ለኪ /ስለ ውዳሴ ማርያም ፈንታ/፣አቡነ ዘመሰማያት፣አንድ ከመዝሙረ ዳዊት/ መዝሙር 150/ በመዝሙረ ዳዊት ፈንታ/በመጨረሻም አቡነ ዘበሰማያት ማድረስ ብንችል መልካም ነው ።ጸሎተ ሃይማኖት የህይማንት መግለጫ በምህኑ እንጸልየዋለን። በመካከል ሰላም ለኪ በመድገማችንም የውዳሴ ማርያም በረከት ይደርሰናል። መዝሙረ ዳዊት 150 ስናደርስ ደግሞ ሁሉንም መዝሙራት የደገምን ያህል ይሆንልንና የዳዊቱን በረከት እናገኛለን፡፡ይህንን ሁሉ ማድረስ ካልተቻለን ግን ቢያንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ከቤታችን ልንወጣ ይገባናል።አጭር ጸሎት ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል፡;ዘጠኝ ሰላም ለኪ፣አስራ ሁለት አቡነ ዘበሰማያት በገዳማት ያሉ አበው ያደርሳሉ። የጸሎት ቅደም ተከተል አቡነ ዘመሰማያት: አንድ ከመዝሙረ ዳዊት:ውዳሴ ማርያም: እና ሌሎችም:ቀጥሎም አቡነ ዘመሰማያት በ እንተ እግዘዕትነ ማርያም: ጸሎተ ሃይማኖት በመጨረሻም አቡነ ዘመሰማያት ኪርያላይሶን 41 ግዚ:: አጭር ጸሎትን እነደ መደበኛ ማድረግ ለፈተና ያጋልጣል አጭር ጸሎት የምንጸልየው በጣም በተቸገርንበት፣ጊዜ ባጣንበት ሰዓት ነው።ይህንን ጸሎት እንደመደበኛ ይዞ በየእለቱ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብቻ መድገም ግን ስንፍና እንዳይሆን ያስፈራል።ይልቁንም በክርስትና ሕይወት ጅማሬ ላይ ያሉ ምእመናን/ወጣንያን/ክርስትናውን እስኪላመዱ ጸሎታቸው አጭር ሊሆን ይችላል።እየቆዩ ሲሄዱ ግን በጸሎት እየበረቱ ወደ መደበኛው ጸሎት መድረስ አለባቸው።ሁል ግዜ ወተት መመኘት ሁል ግዜ አልበረታውም እያሉ አጭር ጸሎት እያደረሱ መተኛት ተገቢ አይደለም።ይህ አይነቱ አካሄድ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለስንፍና ምክንያት አድርጎ መጠቀምም ነው።ከዚህ ጋር በቤተክርስቲያን አገልገሎት ላይ ያለንም ዳዊት መድገም ውዳሴ ማርያም ማድረስ ይጠበቅብናል።የሰንበት ት/ ቤት ወጣቶች ፣ዲያቆናት፣ቀሳውስት፣ሰባክያነ ወንጌል፣መዘምራን……እነዚህን ጸሎታት መጸለይ ይጠበቅባቸዋል።አልያ ግን እያወቅን ጸሎት ማድረስ እንዳለብን ብዙ ጊዜ ተምረን እንዳልተምርን ቸል ብንል ለፈተና መጋለጥ ይመጣል።ከእግዚአብሔርም ቸርነት እንድንርቅ ያደርገናል። አቡነ ዘበሰማያት የጸሎታችን መነሻና መድረሻ ጸሎት ስናደርስ የጸሎታችን መነሻ (መጀመሪያ) አቡነ ዘበሰማያት ነው፡፡በመካከል ጸሎት አቋርጠን ከሰው የምንነጋገርበት ጉዳይ ቢገጥመን በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር ተገቢ ነው፡፡በአቡነ ዘበሰማያት አስረን የገጠመንን ጉዳይ ፈፅመን እንመለሳለን፡፡ከዚያም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ካቆምንበት እንቀጥላለን።ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት ሳናስር በመሃል እንዳሻን እንዳናቋርጥ አበው ያስተምሩናል፡፡ የማህበር ጸሎት በቤታችን ከምንጸልየው ጸሎት በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ተገኝተን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው።ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንደመሆና በእርሱአ የሚጸለይ ጸሎት ከጸሎታት ሁሉ የላቀ ነው።በካህናት እየተመራ ፣በሕብረት ሆነን የምናደርሰው በመሆኑ ታላቅ ኃይል አለው።እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ የምንጸልየውን ጸሎት እንደሚሰማ ሲያመለክተን እንዲህ በማለት ነግሮናል።”አሁንም በዚህ ሥፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ ፣ጆሮቼም ያደምጣሉ።ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ዓይኖቼ እና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።”/2 ዜና መዋ 7-15/ ከዚህ አንጻር በቤተ መቅደስ እየተገኘን መጸለይ ተገቢ ነው።በሰንበት ቀን ኪዳን ማድረስ ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ተግባራችን መሆን አለበት።በሰንበት ያለ በቂ ምክንያት ቅዳሴ የሚያስታጉል በቀደሙ አባቶች /አባ ሚካኤል ወአባ ገብረኤል/ቃል መወገዙን የተአምረ ማርያም መቅድም ይነግረናል።ከዚህ ጋር በሰዓታት ፣በማኅሌት ጸሎታት ላይ በመገኘት ቤተ ክርስቲያናችን ካዘጋጀችልን የማይጠገብ ማእድ ልንሳተፍም ይገባናል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሃይማኖታችን ፍጹም ፍቅር የሚኖረን ከእነዚህ ጸሎታት ጋር ስንተዋወቅ ነው።አልያ የእንጀራ ልጅ መሆን ይመጣል።የመናፍቃንን አዳራሽ መናፈቅ ይመጣል። ከላይ በተመለከተው የጸሎት ጊዜ እየተጠቀምን፣የጸሎት ዓይነቶችንም
إظهار الكل...
ተብሎ በ ጸሎቱ ጸ ሲጻፍ “ፈጽሞ፣ ጨርሶ” የሚል ትርጉም ሲኖረው “ፍፁም” ተብሎ በፀሃዩ ፀ ሲጻፍ ደግሞ “ድፍን፣ ዝግ” የሚል ትርጓሜን ይሰጣል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ “ንፁኅ”ተብሎ በፀሃዩ ፀ እና በብዙኀኑ ኀ ሲጻፍ “የተጠላ፣ የወደቀ” ማለት ሲሆን “ንጹሕ” ተብሎ በጸሎቱ ጸ እና በሐመሩ ሐ ሲጻፍ ደግሞ “ንጽሕና” ማለት ነው፡፡ “ጽንስ” የሚለው “ችግር” ማለት ሲሆን “ፅንስ” ማለት ደግሞ “የማሕፀን ፍሬ፣ ሐሳብ፣ ምኞት” ማለት ነው፡፡  በዚህ መልኩ የሞክሼ ሆሄያት አገባብ መስተካከል አለበት፡፡ በተለይም ደግሞ “እግዚአብሄር” ሳይሆን “እግዚአብሔር”፣ “ስላሴ” ሳይሆን “ሥላሴ”፣ “ተዋህዶ”ሳይሆን “ተዋሕዶ”፣ “አለም” ሳይሆን “ዓለም”፣  “ሠው” ሳይሆን “ሰው”፣ “ማሕሌት” ሳይሆን “ማኅሌት”፣  “ማህበር” ሳይሆን “ማኅበር”፣ “ትምሕርት” ሳይሆን “ትምህርት”፣ “ስርዓት” ሳይሆን “ሥርዓት”፣ “ህይወት” ሳይሆን “ሕይወት” በማለት ሌላው ቢቀር እነዚህን የተለመዱትን ማስተካከል ይገባል፡፡  ደብዛቸው እየጠፋ ያለው ፊደሎች በፊደላችን ውስጥ ቀስ በቀስ እየተመነመኑ ሄደው ሊጠፉ የተቃረቡ ድንቅዬ ፊደላት አሉ፡፡ አብዛኛው ሰው እንኳን ሊጽፋቸው አይቷቸውም ባያውቅ አይገርመኝም፡፡ አሁንም የትምህርት ስርዓቱ ተጠያቂ ነው! ለመጥፋት የተቃረቡት ፊደሎች እና ሥርዓት ነጥቦቻችን እነሆ፡፡ “ከ”የወለዳቸው — ኲ(“ክዊ” – ከ+ወ+የ)፣ ኵ(“ክው” – ከ+አ+እ)፣ ኴ(“ክውየ” – ከ+ወ+የ) “ቀ”የወለዳቸው — ቑ(“ቅዊ” – ቀ+ወ+አ)፣ ቖ(“ቅወ” – ቀ+ወ+እ) “ኀ”የወለዳቸው — ኊ(“ኅዊ” – ኀ+ወ+የ) ፣ ኍ(“ኅው” — ኀ+አ+እ) ኌ(“ኀውየ” – ኀ+ወ+የ) “ነ”የወለዳቸው — ኆእና ኇ ስርዓተ ነጥቦቻችን ፡ -ሁለት ነጥብ -በቃላት መካከል የሚለይ ። – አራት ነጥብ – አረፍተ ነገሮችን የሚዘጋ ! – ትእምርተ አጋኖ – የግነት አረፍተ ነገሮች የሚዘጋ “ – ትእምርተ ጥቅስ – ንግግሮችን የሚይዝ ፣ – ነጠላ ሰረዝ – ዝርዝሮችን የሚለይ ፤ – ድርብ ሰረዝ – የሚገናኙ ግን ለብቻቸው የሚቆሙ የሚለይ ፥ – ንዑስ ሰረዝ – ፣የሚለውን የሚተካ ፦ – አስረጂ ሰረዝ – ነገሮችን ለማብራራት  ፧ – ሦስት ነጥብ – በ “?”የተተካው የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ምልክት ፨ – ሰባት ነጥብ – አንቀጾችን የሚለይ ፠ – – የጽሑፍ ክፍሎችን ለመለየት ¡ – ትእምርተ ስላቅ – ሹፈትን(ማሾፍን)ለመግለጽ  አ.ሳሊብ  ዋቢ መጻሕፍት መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ – አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ  የካም መታሰቢያ የኢትዮጵያ ፊደል መሰረትነት መታወቂያ – አቶ አሥረስ የኔሰው ጥንታዊ የኢትዮጵያ ትምህርት – ሊቀ-ሥልጣናት ሃብተማርያም ወርቅነህ  ባሕልና ክርስትናዊ ትውፊት በኢትዮጵያ – አቶ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር ማኅቶተ ጥበብ ዘልሣነ ግዕዝ – ወ/ሮ ኑኀሚን ዋቅጅራ
إظهار الكل...
ራሽ ሳንማረው አልፈናል፡፡ (የትምህርት ስርዓቱም ተጠያቂ ነው!) የኢትዮጵያውያን ጥንታዊ ፊደል “አ፣በ፣ገ፣ደ…” እያለ የሚቀጥለው ነበር፡፡ የሴም ቋንቋዎች ላይ በግሌ ጥናት በማደርግበት ጊዜ ያጋጠመኝ አንድ አስደናቂ ነገር ይህን አይነት ተመሳሳይ የፊደል አካሄድ ከግዕዝ ውጪ በሚገኙ ሌሎች የሴም ቋንቋዎች ላይ መኖሩ ነው፡፡ ለአብነት ያህል በእብራይስጥኛው የፊደል አቆጣጠር(א,ב,ג,ד) አሊፍ፣ ቤት፣ ጊሜል፣ ዳሌት… እያለ ይቀጥላል፡፡ በአረብኛው ብንሄድ ደግሞ (ا،ب،ت،ث) አሊፍ፣ ባእ፣ ታእ፣ ሣእ… እያለ ይቀጥላል፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከሴም ቋንቋ ውጪም ቢሆን በግሪክኛ (α,β,γ,δ…) አልፋ፣ ቤታ፣ ጋማ፣ ዴልታ… ተብሎ ይሰደራሉ፡፡ ይህ የመወራረስ ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ይጠቁማል፡፡ የኢትዮጵያን ቀደምት ፊደል የሆነው “አ፣በ፣ገ፣ደ…” ታዲያ ያለ ትርጉም አልተቀመጠም፡፡ ጹሑፉ እጅግ እንዳይረዝም ለማሳያ ያህል “አ፣በ፣ገ፣ደ፣ወ” የሚሉትን ፊደሎቹ እና የእነርሱን ትርጉም ከስር አስቀምጫቸዋለሁ – ከእስራኤላውያን ፊደል ትርጉም ጋር ለማስማማትም ሞክሬያለሁ ፡፡ ☞ አ(ቀንድ፣ የቀንድ ከብት) – ቅርጹ የከብቶችን ቀንድ መልክ የያዘ ነው፡፡ መለኮታዊ ትርጉሙ “አብ” ማለት ሲሆን የሁሉ ነገር መጀመሪያ በሆነው “አ” የሚጀምረውም ለዚህ ነው፡፡ “አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር – ጌታን ፈጽሜ አመሰግነዋለሁ” የሚለውም አንድምታ ይሰጠዋል፡፡ በእብራይስጡ አለፍ (א) ሲሆን የእብራይስጥ ፊደሎች መጀመሪያ ነው፡፡ የአይሁድ ሊቃውንት ከላይ ያለችው ጭረት አምላክ ከስር ያለው ጭረት አዳም እንደሆነ እና በመሃል ያለው ሰረዝ ደግሞ ሰው እና አምላክን ያገኛኘው የእግዚአብሔር ሕግ መሆኑን ያመሰጥራሉ፡፡  ☞ በ(ቤት) – ቅርጹ በቤት መልክ የተሰራ ነው፡፡ በእብራይስጡ ቤት (ב) ሲሆን አንድምታው ተመሳሳይ ነው፡፡ “በትሕትናሁ ወረደ – ጌታ በትሕትናው ወደኛ ወረደ” የሚለውን አንድምታ ይይዛል፡፡ የአይሁድ ሊቃውንት ፊደሉ የቤት ቅርጽ መያዙ ዓለም መንፈሳዊነትን ጠቅልሎ የመያዙን ምስጢር እንደሚያትት ይገልጻሉ፡፡ ☞ ገ(ግመል) – ግመል “ገብረ ሰማያት ወጥበቡ – ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሰራ” የሚለውን አንድምታም ይይዛል፡፡ ግመል በጽናት ረጅም ጉዞን ስለምትጓዝ ይህንን ጠቅሰው የአይሁድ ሊቃውንት ጊሜል (ג) የሚለውን ፊደላቸውን ይተረጉማሉ፡፡ ☞ ደ(መዝጊያ) – “ደመረ ሥጋነ ምስለ መለኮቱ – ከመለኮቱ ጋር ሥጋችንን ደመረ” የሚለውን አንድምታ ይይዛል፡፡ በእብራይስጥኛ ፊደሉ ዳሌት(ד) ሲሆን በእብራይስጥኛ ዳሌት(דלח) የሚለው ቃል በራሱ ትርጉም “በር፣ መዝጊያ” ማለት ነው፡፡ የአይሁድ ሊቃውንት ፊደሉ ለትምክህት “በሩን ዘግቶ” ትህትናን የተቀበለ ሰውን እንደሚወክል ይናገራሉ፡፡ (የእብራይስጥኛ ፊደሉ በትህትና ያቀረቀረ ሰው እንደሚመስል ልብ ይሏል) ☞ ሀ(ኗሪ) – “ሀለወተ አብ እምቅድመ ዓለም – የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው” የሚለውን አንድምታ ይይዛል፡፡ በአንድ ወቅት “አ” የሚለው መጀመሪያ መሆኑ ቀርቶ “ሀ” መጀመሪያ የሆነበት ምክንያትም “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት” መሆኑን እና “ሀ” የሚለው ፊደልም እጁን ወደላይ ዘርግቶ የሚጸልይ ሰውን ቅርጽ መያዙን ሰምቻለሁ፡፡ በእብራይስጡ ሄይ (ה) ሲሆን ሃያ(היא) የሚለውም ቃል – መኖር፣ አኗኗር – በዚህ ፊደል ስለሚጀምር የአምላክ ለሰው ሚስጥራትን መግለጥን እንደሚገልጽ የአይሁድ ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ☞ ወ(ወገል) – “ወረደ እምሰማይ – ጌታ ከሰማይ ወረደ” የሚለውን አንድምታ ይይዛል፡፡ የቃሉ ቅርጽም ሆነ አንድምታው ውህደትን ያመሰጥራል፡፡ በእብራይስጡ ቫቭ (ך) ሲሆን እንደ መንጠቆ አይነት ቅርጽ እንዳለው በመጠቆም የሰማይ እና የምድርን መገናኘት እና በተጨማሪም በእብራይስጥኛ ኦር ያሻር(אר ישר)ተብሎ የሚታወቀውን የእግዚአብሔር እርዳታ ያመሰጥራል፡፡  ለአብነት ያህል አምስቱን ጠቀስኩ እንጂ ፊደሎቹ ሁሉ ትርጉም አላቸው – አቀማመጣቸውንም ጨምሮ፡፡ ከ “አ፣በ፣ገ፣ደ” ወደ “ሀ፣ለ፣ሐ፣መ” የተደረገውን ሽግግር ታላቁ ሊቅ የሆኑት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ” በሚለው መጽሐፋቸው ላይ “የፊደል ተራ የተፋለሰና አልፍ አ ከርስቱ ከቀዳማዊነቱ ተነቅሎ በርሱ ፋንታ ሆይ ሀ መዠመሪያ ፊደል የሆነ ከፍሬምናጦስ ወዲህ ነው፡፡ አበገደሀ የነበረውንም ሀለሐመሠ ብለው ከላይ እስከ ታች ያፋለሱትም ከርሱ ጋር የነበሩ ጽርኣውያን እና ቅብጣውያን ናቸው ይባላል” ብለው አስፍረዋል፡፡ ይህም ትልቅ ስህተት መሆኑንም ሲገልጹ “በሄኖስ ራእይ ተመስርቶ የታነጸውን የአልፋ ወዖን ምስጢር አፋልሷል” ይላሉ፡፡ በተማሪዎች ዘንድ “አቡጊዳ የተማሪዎች እዳ” የሚባለውም የፊደል አሰዳደራችን ጥልቅ ምስጢራትን በውስጡ የያዘ ነውና ብናጠናው እላለሁ፡፡ እርሱ እንኳን ቢቀር “ሀ፣ለ፣ሐ፣መ” የሚለውን ፊደል እስከመጨረሻ ድረስ በቃላችን እንወቀው፤ አለማወቁ የሚያሳፍር ነውና፡፡  ሞክሼ ሆሄያት – ለአወቃቸው ትልቅ ራስ ምታት ሞክሼ ሆሄያት የምንላቸው በአጠራር አንድ ሆነው በጽሑፍ ግን የተለያዩ ፊደላትን ነው፡፡ እነዚህም ሀ፣ሐ፣ኀ(ሀሌታው ሀ፣ ሐመሩ ሐ፣ ብዙኀኑ ኀ)፣ ሠ፣ሰ(ንጉሡ ሠ፣ እሳቱ ሰ)፣ አ፣ዐ(አልፋው አ፣ዐይኑ ዐ)፣ ጸ፣ፀ(ጸሎቱ ጸ፣ፀሃዩ ፀ) ናቸው፡፡ በጥንት ጊዜ አንድ ሰው ጸሐፊ ለመሆን ፊደሎችን ብቻ ሳይሆን አጻጻፉን እና አገባቡንም ማወቅ ነበረበት፡፡ የታሪክ ድርሳናትን ብንመለከት በአጼ ባካፋ ጊዜ የጽሑፍን አገባብ ሳይጠብቅ የጻፈ ሰው እጁ ይቆረጥ ነበረ፡፡(አዳሜ ሥላሴ ተብሎ መጻፍ ሲገባው ስላሴ ቢል እጁን ደህና ሰንብት ይለው ነበር) ከጊዜ በኃላ ግን ሰዎች በድፍረት እየጻፉ ምስጢርም እያፋለሱ ስለሄዱ “ሌሎቹ ፊደሎች ይቀነሱ” የሚል ንግግር ከተማሩ ሰዎች ጭምር የተደመጠበት ወቅትም ጭምር በቅርቡ ነበር፡፡ ይህ ጥቅማቸውን ለይቶ ባለማወቅ የሚመጣ ነው፡፡  በአሁኑ ዘመን ያሉ ብዙ ተማሪዎች(በተለይም በከተማ) ሞክሼ ሆሄያትን ጠብቀው ሲጽፉ አይታዩም፡፡ የትምህርት ስርዓቱም ለዚህ ዋነኛው ተጠያቂ ነው፡፡ ብዙ ጽሑፎችን ስመለከት የሞክሼ ሆሄያት ነገር በጣም ያበሳጨኛል፡፡ ሞክሼ ሆሄያትን ባልተገባ መንገድ መጻፍ ትልቅ የትርጉም ለውጥ እንደሚያመጣም መታወቅ አለበት፡፡ ግድየለም… ሙሉ ለሙሉ(እኔን ጨምሮ) ይህን ችግር ባንቀርፈው እንኳን ቢያንስ የተቻለንን እንሞክር! ከታች የተወሰኑትን ጠቅሻለሁ፡፡ ሠ እና ሰ – ከመለኮታዊ አጠራሮች ውስጥ ዋነኛው እና ተጠቃሹ “ስላሴ” ተብሎ የሚጻፈው ነው፡፡ ይህ ትልቅ ስሕተት ነው፡፡ “ሠ” የተሰኘው ፊደል “ንጉሡ ሠ” የተባለበት ምክንያት አለው – ቅርጹም ቢሆን የንጉሥን ዘውድ ይመስላል፡፡ በዚህ መሰረት ዘለዓለማዊ ንጉሥ እየጠራን ነውና “ስላሴ” ሳይሆን “ሥላሴ” ብለን እንጻፍ፡፡ ለአብነት ያህል “ሰረቀ” እና “ሠረቀ” አንድ አይደለም፡፡ “ሰረቀ” በእሳቱ ሰ ሲጻፍ “ሳይታይ ወሰደ፣ አነሳ” ሲሆን “ሠረቀ” ደግሞ “ተገለጠ፣ ወጣ፣ አሰረ፣ቋጠረ” የሚል ትርጉም ይኖረዋል፡፡ በግዕዙ “ሠረቀ በሥጋ – በሥጋ ተገለጠ” ይባላል፡፡  “ሠዓሊ” ማለት “የሚሥል” ማለት ሲሆን “ሰአሊ ደግሞ “የሚለምን፣ የሚጠይቅ” ማለት ነው፡፡በውዳሴ ማርያም “ሰአሊ ለነ ቅድስት – ቅድስት ሆይ ለምኚልን“የምንለው ለዚያ ነው፡፡ “ሠርግ” ማለት “የመስኖ ውሃ፣ ኩሬ” ማለት ሲሆን “ሰርግ” ማለት ደግሞ “የጋብቻ በዓል፣ ድግስ” ማለት ነው፡፡ ጸ እና ፀ – ይህም ቢሆን በተደጋጋሚ የሚደረግ ስህተት ነው፡፡ ለአብነት ያህል “ፍጹም” እና “ፍፁም” የሚሉትን እንይ፡፡ “ፍጹም”
إظهار الكل...
ይህ ጽሑፍ ጊዜ ወስጄ በደንብ ጥናት አድርጌበትም የማሰፋው ነው – ለጊዜው ግን መግቢያ ትሆናችሁ ዘንድ በዚህ መልኩ ቀርቧል) የፊደል ነገር በተነሳ ቁጥር የልጅነት ትዝታዬ ይቀሰቀሳል፡፡ ልጅ እያለሁ አባቴን ለምጠይቃቸው ጥያቄዎች መልስ ከሰጠኝ ወይም መልሱን የማገኝበትን ከጠቆመኝ ቦኋላ ሁሌም ንግግራችንን የሚዘጋው ስለ ኢትዮጵያዊነት ተናግሮ ነበር፡፡ ታዲያ ከንግግሮቹ መሃል ‹‹እኛ ኢትዮጵያን እጅግ ከሚያኮሩን ነገሮች አንዱ የራሳችን ፊደል ባለቤት መሆናችን ነው›› የምትለዋ ትዝ ትለኛለች፡፡ በወቅቱ የልጅነት አእምሮ ስለነበረኝ ሙሉ ምስጢሩን ባልረዳውም፤ አሁን አሁን ከነፍስ ማወቅ ጋር ተያይዞ በጥቂቱም ቢሆን “በፊደል” እና “በኢትዮጵያዊነት” መካከል ያለው ግንኙነት በጥቂቱም ቢሆን እየገባኝ ይመስለኛል፡፡ በፊደላት ምንነት፣ አንድምታ እና ምስጢር ዙሪያም ይህንን ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡  ታደሙልኝ! ምርምር ከሰው ልጅ የውስጥ የማወቅ ፍላጎት እንደሚመነጭ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ከዚህ የማወቅ ፍላጎት መንጭቶ የሚደረግ ምርምር ታዲያ ብዙ ጥቅሞች አሉት – ከዚህም መካከል አዲስ እውቀትን ማፍለቅ ዋነኛው ነው፡፡ በተለይም በማህበራዊው ሳይንስ የአንድን ነገር ስያሜ ማጥናት አጽንኦት የሚሰጠው ለዚህ ነው፤ የአንድ ቃል ሐተታ በራሱ ስለነገርየው ብዙ አዳዲስ እውቀትን ማፍለቅ ይችላልና፡፡ በዚህ መሰረት ከርዕሱ ጋር አያይዘን “ፊደል ምንድነው?”የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ አግባብ ይመስላል፡፡ የፊደል ትርጉም በሥነ-ቋንቋ ሊቃውንት  በአገራችን እጅግ የተከበሩ የነበሩት የሰዋሰው አዋቂ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ” በሚለው ግሩም መጽሐፋቸው ላይ “ፊደል ማለት የቋንቋና የቃል ያነጋገር ሁሉ ምልክት አምሳል ወይም መግለጫ ማስታወቂያ ማለት ነው” ይላሉ፡፡ አቶ አስረስ የኔሰው ደግሞ “የካም መታሰቢያ የኢትዮጵያ ፊደል መሰረትነት መታወቂያ” በሚለው መጽሐፋቸው “ፊደል ሐውልት ነው፤ ሐውልትም ፊደል ነው፡፡ ፊደል መልክ ነው፤ መልክም ፊደል ነው፡፡ ፊደል አባት ነው፤ አባትም ፊደል ነው፡፡ ፊደል ልጅ ነው፤ ልጅም ፊደል ነው፡፡ ፊደል ወሰን ነው፤ ወሰንም ፊደል ነው፣ ፊደል አላማ ነው፤ አላማም ፊደል ነው፡፡” ብለው ይገልጹታል፡፡  ሊቀ-ሥልጣናት ሀብተማርያም ወርቅነህ ደግሞ “ጥንታዊ የኢትዮጵያ ትምህርት” በሚለው መጽሐፋቸው  ላይ “ፊደል ማለት መጽሔተ አእምሮ ማለት ነው” በማለት ይጠቅሳሉ – በአእምሮ ያለው ሁሉ የሚሰፍርበት ጥበብን የሚያሳውቅ መሆኑን ሲያስረዱን፡፡ የቤተ-ክርስቲያን ሊቃውንት ስለ ፊደል ብዙ ይናገራሉ – ሲናገሩም “ጥበብ የጠፋበትን የሚመራ ነቅዐ ጥበብ (የጥበብ ምንጭ)፣ ዕውቀት የጠፋበትንም የሚያበራ መራሔ ዕውር (ዕውርን መሪ) ነው” ይሉናል፡፡ በኢትዮጵያውያንም ሆነ በውጭ ሰዎች ብዙ የተባለለትን የፊደላችንን ጉዳይ ቸል ማለት የማይቻለውም ለዚህ ሲባል ነው፡፡ በኢትዮጵያ በዋናነት የሚጠቀሱ እና በብዙኀኑ ዘንድ ተደጋግመው የሚታዩ ሦስት ዋና ዋና ችግሮችን በዚህ ጽሑፍ እናያለን፡፡ እነርሱም የፊደላትን ተርታ አለማወቅ፣ ሞክሼ ሆሄያትን አለመለየት እና ጭራሹኑ አንዳንድ ፊደሎችን እና ስርዓተ-ነጥቦችን አለማወቅ ናቸው፡፡  በጥንታዊው ዓለም የአንድ አገር የሥልጣኔ መጠን የሚለካው በሥነ-ጽሑፍ፣ በፍልስፍና፣ በሥነ-ሕንፃ እና በመሳሰሉት የአስተሳሰብን ጥልቀት እና ምጥቀት በሚጠይቁ ድርጊቶች ነበር፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ከዛሬ ሰባት ሺህ አመታት በፊት በዳዕማት የፅሁፍ ትምህርት መስጠት መጀመሯን ለሚያውቅ ሰው በወቅቱ አገራችን ደርሳበት የነበረውን የሥልጣኔ ደረጃ መገመት አያዳግተውም፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ የምዕራብውያኑ ፊደላት ድምፆችን ከመወከል በዘለለ የተለየ ጥቅም ወይም ደግሞ ምስጢራዊ ፍቺ የላቸውም ፡፡ የግዕዝ ፊደላት ግን እንደዚህ አይደሉም፡፡ የግዕዝ ፊደላት ድምፃትን ከመወከልም አልፈው እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ ምስጢራዊ እና ሃይማኖታዊ ፍቺ ሲኖራቸው በተጨማሪም ደግሞ እንደ ቁጥር መቁጠሪያነት ሆነውም ያገለግላሉ፡፡ የፊደላቱ አንድምታ የመጀመሪያው የፊደላቱ ምስጢራዊ ፍቺ ነው፡፡ በአባ ሰላማ (ፍሬምናጦስ) ጊዜ ሀ፣ለ፣ሐ፣መ እያለ የሚሄደው ተርታ ይውጣ እንጂ ከቀድሞው የነበረው በአሁኑ ጊዜ “አቡጊዳ” ብለን በምንጠራው ተርታ ነበር፡፡ ይሄም ማለት የግዕዙ ፊደል በአልፋው “አ” ይጀምርና አ፣በ፣ገ፣ደ እያለ ይሄድ ነበር፡፡በሁለቱም አደራደር መሰረት ፊደሎቹ የራሳቸው የሆነ ፍቺን ይይዛሉ፡፡ ቀደምት በነበረው የፊደላት አደራደር መሰረት አ(አለፍ – የቀንድ ከብት – የመጀመሪያ) የሚለውን ፍቺ ይይዛል፡፡ በ(ቤት) የሚለውን ትርጉም፣ ገ(ግመል)፣ ደ(ዳልት-መዝጊያ)…ወዘተ እያለ ይቀጥላል፡፡ ይኼም በወቅቱ ኢትዮጵያውያኑ በአካባቢያቸው ከሚያዩት እና ትርጉምን ከሚሰጡ ነገሮች በመነሳት ፊደላቸውን እንደቀረጹ መረዳት ይቻላል፡፡ ሁለተኛው የፊደላቱ ሃይማኖታዊ ፍቺ ነው፡፡ በአባ ሰላማ በተጀመረው የፊደላት አደራደር ይህንን መንገድ ተከትሎ የተሰደረ ነው፡፡ ይህን አደራደር በአሁኑ ወቅት በሰፊው የምንጠቀምበት ሲሆን የፊደላቱ ዝርዝር “ሀ” ብሎ ይጀምራል፡፡ በዚህም መሰረት ሀ(ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም – የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው)፣ ለ(ለብሰ ሥጋ እምድንግል – ከድንግል ሥጋን ለበሰ)፣ ሐ(ሐመ ወሞተ – ታመመና ሞተ)፣ መ(መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር – የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው)…ወዘተ እያለ በምስጢራዊ መንገድ በመጠቀም ከብሉይ እስከ ሐዲስ ኪዳን ድረስ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል ይሰብካል፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ፊደሎቹ ቁጥርን ተክተው ማገልገል መቻላቸው ነው፡፡ ይህም ደግሞ ፊደሎቹን ካላቸው የቁጥር ልኬት ጋር በማድረግ ለማጥናት ከማቅለሉም በተጨማሪ ለምስጢራዊ አገልግሎትም ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ፊደላቶቹ ከ “አ” ጀምሮ ያላቸውን ተርታ በመጠቀም ለእያንዳንዳቸው ቁጥራዊ ልኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡ አ(አሐዱ – አንድ)፣ በ(ክልኤቱ – ሁለተኛው)፣ ገ(ሠለስቱ -ሦስተኛው)፣ ደ(አርባዕቱ -አራተኛው)…ወዘተ እያለ ከቀጠለ በኋላ ከ(ዕሥራ – ሃያ)፣ ለ(ሠላሳ )፣ መ(አርብዓ-አርባ)…ወዘተ እያለ ይቀጥላል፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ በመቀጠል የእ(አእላፍ – መቶ ሺህ)፣ ቀእ(አእላፋት – አንድ ሚሊዮን)፣ እእ(ትእልፊታት – መቶ ሚሊዮን) እንዲያውም እእእ(ምእልፊት-አሥር ቢሊዮን)…ወዘተ እያለ ይቀጥላል፡፡ ፊደላቶቹና ተርታቸው ልጅ እያለሁ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “ሃምሳ ሎሚ” የሚል ጥሩ ፕሮግራም ይተላለፍ እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ በአንድ ወቅት ታዲያ ፊደላትን በተመለከተ ከመድረክ መሪዎቹ ጥያቄ ቀርቦ እጅግ የተማሩ የሚባሉት ሰዎች ሳይቀር ከ “ሀ” እስከ “ፐ” ድረስ በተርታ መቁጠር ሲያቅታቸው ታዝቢያለሁ፡፡ የእውነት ለመናገር  እጅጉን አፍሬያለሁ፡፡ አሁን እስቲ… ስንቶቻችን ፊደሎቻችንን ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻው እንወጣዋለን? ይህንን ጥያቄ ለሁላችሁም ልተወው፡፡ (የማትችሉ ካላችሁ ግድየለም… ዛሬ መማር ይቻላል፡፡ አልረፈደም!) በኢትዮጵያ የፊደል ስርዓት ውስጥ ሁለት አይነት የፊደል ተርታዎች አሉ፡፡ ከላይ እንዳየነው የመጀመሪያው በእጅጉ የተለመደው እና “ሀ” ብሎ የሚጀምረው “ለ፣ሐ፣መ…” እያለ የሚቀጥለው የፊደል አሰዳደር ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አግድም ሲቆጠር “አ፣ቡ፣ጊ፣ዳ…” እያለ የሚሄደው እና ቁልቁል ሲቆጠር ደግሞ “አ፣በ፣ገ፣ደ…” እያለ የሚሄደው የፊደል አሰዳደር ነው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ ቀደምታ የሆነው “አ፣በ፣ገ፣ደ” የሚለው ሲሆን፤ እጅጉን በሚያሳዝን ሁኔታ በከተማ የተማርን ተማሪዎች ጭ
إظهار الكل...
إظهار الكل...
ቅኝት music🎧

🖇✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️🖇 📚 💥 መኖርያችን ከሆነችው ዓለም የተሰባሰቡ አስገራሚ አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ እውነት የሆኑ ኩነቶችን የሚያገኙበት ቻናል ነው።

https://telegram.me/kegnetmusics

📚 📚 ለማንኛውም አስተያየት @suraXoXo ይጠቀሙ Share share

#22 ❤️እንኳን ለታላቁ ሊቀመልአክት ለቅዱስ ዑራኤል በዓለ ሲመት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ::❤️ ለከበረ ገናና ስሙ ምስጋና ይድረሰውና ‹‹ዑራኤል›› ማለት ትርጉሙ ‹‹የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን›› ማለት ነው፡፡ ከ፯ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ቅዱስ ዑራኤል ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚገልጸው መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል፡፡ ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ 28፡13፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨው ይኸው ገናና መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ዕውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ለኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን ትእዛዝ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡›› መጽሐፈ ዕዝራ 2፡ 1፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናም በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በመልአኩ አማላጂነት እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሱት መልአኩ ጽዋ ሕይወትን ካጠጣቸው በኋላ ነው፡፡ በመጀመሪያም አባ ጊዮርጊስ የተወለዱት በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት ነው፡፡ በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሠረቱ አብዛኞቹ ቅዱሳት ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የማይጠቅሳቸው የሀገራችን የከበሩ ቅዱሳት ገዳማትና ቅዱሳን ነገሥታት የሉም፡፡ የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስትሰደድ መንገድ እየመራ ወደ ግብጽ እና ወደ አገራችንን ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ እመቤታችንን ከተወደደ ልጇ ጋር በደመና ጭኖ መላ ኢትዮጵያን ካስጎበኛት በኋላ ቅድስት አገራችንን ለእመቤታችን የዓሥራት አገር እንድትሆን ያደረገው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ ሩህሩህ መልአክ የቅዱስ ኡራኤል በረከት ረዳኤቱ ይደርብን፣ ጸሎትና አማላጅነቱም አይለየን ። አሜን።
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.