cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

دار القرأن والسنة

ኢንሻአላህ በዚህ ቻናል ቁርአንና ሀዲሥ በሰለፎች አረዳድ እንማማራለን። የቴሌግራም ግሩፓችን @atewhidu_awellen

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
169
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🔥🔥እንደው ወላሂ እስቲ እናንተ ፍረዱ የአላህ ቤት ውስጥ ሀሙስ ቀን ለይተው (የኸሚስ) እያሉ ማጫጫስ እንደው ምን ይባላል ።🔥🔥 ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ይህ እየሆነ ያለው የትም አይደለም ጠሮ ኡስማን ኢብኑ አፋን መስጅድ ውስጥ ነው። ልብ በሉ በተደጋጋሚ እዚህ መስጅድ ውስጥ ሁከት ሚፈጥሩ፣ ድብደባ ሚፈፅሙ፣አላህ አርሽ በላይ አይደለም ብለው ሚያምኑ፣እነሱን ያልተከተለ (አህባሽ ያልሆነላቸውን) በግፍ የሚደበድቡ ፣መስጅድ ውስጥ አይቀራም ሚሉ፣ ከነሱ ውጪ ማንም ልክ እንዳልሆነ የሚምግቱ ከመሆናቸውም ጋር አሁን በምስሉ ላይ ምትመለከቱትን (የኸሚስ) እያሉ ማጨስ ጀምረዋል። 🔥🔥🔥ጠሮ ውስጥ እንዲህ ያለ ሰው ነው ያለው አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ መስጅዱንም ለዚህ አላ ማ ለማዋል ነው ጥረት እያደረጉ ያሉት።🔥🔥 ልብ በሉ የአላህ ባሮች አህባሾች ምን ያህል ዲን ላተይ እንደሚጮቱ። አላህ ቀናውን መንገድ ይምራን በመሀይማን ድንበር ማለፍ አላህ አብሮ አያጥፋን።
إظهار الكل...
♻️ተውሒድ ሲባል በቃል የሚመሰከር ሸሃዳ ብቻ አይደለም፡፡ በተግባር የሚኖሩት ሕይወት እንጂ፡፡ የሚያሳዝነው ዛሬም ላይ ከአላህ ይልቅ ሸሆቹን፣ጅኖቹን፣ ቆሌዎቹን .. የሚፈሩ ብዙ ናቸው፡፡ 🚸ወላሂ ይገርመኛል … ስንቶች ናቸው! አላህን ለማግኘት ብለው ከአላህ የራቁ፡፡ ወደ አላህ የሚደርሱት በሸሆቹ እና በወሊዮቹ በኩል ብቻ መሰላቸዉና የአላህን ሥም አንድም ቀን ሳይጠሩ፣ ወደ አላህም አንድ ቀን እጃቸዉን ሳያነሱ፣ ሸሆቹ እግር ላይ ወድቀው፣ ወሊዮቹ በሚሏቸው በር ላይ ተደፍተው እነርሱን ሲያገለግሉና ሲኻድሙ ኖረው ዱንያን የተሰናበቱ፡፡ 🔆ጌታዬን አንተን ከማግኘት ከሚጋርድ ዕውቀት አንተው ጠብቀኝ፡፡ t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan
إظهار الكل...
#እህቴ__ #ሰለፍዩ_ያግባሽ__!! -------------------------- ብዙ እየተባለ ሁሉን ነገር ችሎ፡ ካብሮ አደግ ጓደኛ ከዘመድ ተገሎ፡ በተውሒዱ ፀንቷል በእስልምናው ታግሎ፡ በነገር ትኩሳት በፍም ተፈትኖ፡ አለ ዛሬም ድረስ በመንሀጁ ገኖ፡ ገንዘብም ባይኖረው ባያምርም ህይወቱ፡ ህንፃ ለመገንባት ባይችልም ጉልበቱ፡ ንፋስ ስልክ ቀለም ባይቀባም ቤቱ፡ ልቡ ብርሀን ነው ይሔ ነው ውበቱ፡ ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ሀቁን ከሰማሽኝ እህቴ ልንገርሽ ዱባይ ቪላ ሰርቶ ኢኽዋን ከሚያኖርሽ፡ ቀን ስራ እየሰራ ሰለፍይ ያክብርሽ፡ ፖለቲካ ሰብኮ ገደል ከሚያስገባሽ፡ ልብሽን ከምትሰጭ ለሱፍያ ለአህባሽ፡ የህይወትሽ ቀመር ሚስጥሩ ከገባሽ፡ የተውሒዱ ሞተር፤ የሱናው አርበኛ ሰለፍዩ ያግባሽ፡ ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ በኑረዲን አል አረቢ(ከገጠር)1443 -_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_ https://t.me/nuredinal_arebi https://t.me/nuredinal_arebi https://t.me/nuredinal_arebi -_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-
إظهار الكل...
شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

#ሰለፍያ_ቀጥተኛ_የሀቅ_መንገድ_ብሎም_አይነኬ_ፅኑ_ተራራ_ነው

📌ሙስሊም ሴት ልጅ ሜክአፕ መስራት ትችላለችን? መሠራትስ⁉️ ✅በመጀመሪያ ደረጃ #ሜክአፕ መሰራት #ቆዳን የማይጎዳና #ለባልና ለዘመዶች እንጂ አጂነቢ ወንዶች❗️ ፊት እስካልሆነ ድርሰ የሚከለከል አይሆንም። ሴት ልጅ አደባባይ ይዛው አትውጣ እንጂ ማንኛውንም #የመዋቦያ ነገር መጠቀም ትችላለች። ✅ከዚህ በመነሳት ሜክአፕ መስራትም ከዚህ ውስጥ ይገባል። ማለቴ የምትሰራው ልጅ #አጂነቢ ወንድ ፊት ልታሳየው እንደሆን #እስካላወቀች ድረስ ብትስራ አትከለከልም። ከዚህም በላይ ለምንድን ነው የምትሰሪው ብላ #መጠየቅም ግዴታ አይሆንባትም። ነገር ግን #ከራሷ መጥቶ ለአጂነቢ ነው ምናምን ብላ ከነገረቻት መስራት አትችልም፣ ምክንያቱም በመጥፎ ነገር ላይ #መተባበር ነውና። ♻️ ምንጭ :— 📚 ኢብኑ ዑሰይሚን ★ @hebre_muslim
إظهار الكل...
📚 عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: 🍁 قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: 🍃 ((إن الله تعالى يرضى لكم ثلاثا، ويكره لكم ثلاثا: فيرضى لكم أن تعبدوه، ولا تشركوا به شيئا، وأن تعتصموا بحبل الله جميعا ولا تفرقوا، ويكره لكم: قيل وقال، وكثرة السؤال، وإضاعة المال)). 🌹 رواه مسلم. 🌹 #اللهم_صل_وسلم_وبارك_على_سيدنا_محمد
إظهار الكل...
የልብ ቅርፅ ❌❌  ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ المزة القلب ❤لا يجوز لأنه تشبه بالكفار️ ልብ ቅርፅን መጠቀም የተከለከለና የተወገዘ ነገር ነው በኩፋሮች መመሳሰል ነውና። የማይሳሳት የለምና እኔም ይህን ነገር ተጠቀረሜው ነበር ስለሆነም ተመልሻለሁ። የሰው ልጅ ሆኖ የማይሳሳት የለም ነገር ግን የአንድ ነገር ጥፋትና ችግር ሲነገረው መመለስ ለአላህና ለመልዕክተኛው ተገዥነት ነው። ታላቁ አሊም ሼኽ ሷሊህ አል ፈውዛን እንድህ ይላሉ يقول ‏العلامة صالح الفوزان حفظه الله: ‏ ‏«انظروا إلى سعة فضل الله أنهم عصوا الله وخالفوا أمره لكن لما تابوا تاب الله عليه وأحبهم» ‏ ‏[أسباب محبة الله للعبد] የአሏህን ትሩፋትና ቼርነት ተመልከት አላህን አመፁት ከትእዛዙም አፈነገጡ ነገር ግን ሲመለሱ ሲፀፀቱ አላህ ምህረቱን ለገሳቸው ወደዳቸውም። ነብዩም እንድህ ሲሉ ተመላሽን አሞግሰዋል كل بني آدم خطاء وخير الخطائين التوابين. የሰው ልጆች ሁሉ ተሳሳቾች ናቸው ከተሳሳቾች ሁሉ መልካሙና ጥሩው ግን ተመላሾቹ ናቸው ይሉናል የአላህ ነብይ። ‏لا يجوز استعمال رمز القلب (❤) قال الشيخ ابن باز رحمه الله : " أنه رمز للعشق المحرم ورمز للألهه الاغريقية" اللجنة الدائمة للأفتاء [20950] ⭕ تذكير بخصوص بعض الرموز المستخدمة في برنامج الواتس أب فلابد يا أخي المسلم ويا أختي المسلمة أن نتنبه لخطورة حرب اليهود والنصارى وملل الكفر على الإسلام وأهله ،و مما ينبه عليه هو وجود هذه الرموز الخبيثة المتدوَالة في برنامج الواتس آب وهي مخالفة لدِينِنا الإسلامي الحنيف وعقيدتنا التي هي رأس مالنا ..كثير منا يَستعملها في بعض رسائِلِه وهو لا يعلم معناها ولا يعلم مدى خطورتَها علي عقيدتِنا فعَلى سبيل المثال لا الحَصْر : ወንድሞች ልንነቃ ይገባል ይህ ድርጊት ከኩፋሮች የመጣ ነው ቀጥታ ከአቂዳ ጋር ግንኙነት አለው ስለዚህም ከዲናችን ጋር የሚቃረን ነገር መጠቀምን እንጠንቀቅ። ለምሳሌ አንዳን ነገሮችን እንመልከት 1⃣ هذه ✳ ❇ 💠✨⚓ ترمز للديانة النصرانية وهي أشكالٌ مِن الصُّلْبان . ይህ ምልክት የክርስትና የመስቀል ምልክት ነው። 2⃣ وأمَّا هذا 💖 فرمْـزٌ على أنَّ الصليب في القلب . ይህ ምልክት ደግሞ መስቀል ከልቤ ውስጥ ነው እወደዋለሁ ማለት ነው። 3⃣ وأمَّا هاذان الرمزان ⛪ 💒 فهما للكنيسة وأنها في القلب. እነዚህ ሁለት ምልክቶች ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ምልክት ነው ይህም ማለት ቤተክርስትያን ከልቤ ውስጥ ነው ማለት ነው። 4⃣ وأمَّا هذه 🙏 فتحيةٌ في الديانة البوذية عُبَّاد بُوذا . ✅✅✅✅ 5⃣ وأمَّا هذا🗿فرمْـزٌ َلِوَثَن أو صنم . ይህ ደግሞ የጣኦት ምልክት ነው። 6⃣ وأمَّا هذه ♦ ♣ ♥ ♠ فهي لأوراق اليانصيب . 7⃣ وأمَّا هذا 🔯 فرمْز للصهيونية اليهودية . 8⃣ وأمَّا هذه 🍻🍺 دعاية لشَرَابٌ الخَمْر . እነዚህ ምልክቶች ደግሞ የአስካሪ መጠጥ ምልክቶች ናቸው። 9⃣ وهذا 🎄 يرمُز لِِتَزُيين الأشجار في بعض الأعياد النصرانية وما يسمى [الكريسمس] . 🔟 وهذه لِآلآت الموسيقى المُحرَّمة 🎺 🎸 🎻 🎼 🎶🎵🎷 እነዚህም ምልክቶች የሙዚቃ መሳሪያ ምልክቶች ናቸው። 1⃣1⃣ وهذه ♍ لفظ الجلالة بالمقلوب اقلبو الجهاز. ይህ ደግሞ እጅግ የሚገርምና ከሁሉም እስልምና ላይ ለመጫወት ሆን ብለው የሰሩት ነው። ይህማ ካልሆነ እንደት የአላህን ስም ገልብጠው ይፅፋሉ!!? ይህ ከላይ የምትመለከቱት ምልክት የአሏህን ስም ገልብጠው ፅፈው ነው። 2⃣1⃣ وهذه 👐 🙌 ليست للدعاء لاحظ أصابع الإبهام للداخل و ليس إشارة للدعاء الله أعلم بمقصودها.. 3⃣1⃣ وهذه رموز عبدة الشيطان كما يسمون أنفسهم ♈♉♋♌♑♓. ይህ የሰይጣን አምላኪዎች ምልክት ነው። وغيرها كثير ... وكثيرون منا لا يعلمون والله المستعان . እናም ሌላም ሌላም ከዲናችን ጋር ሊቃረን የሚችሉ ነገሮችን አይሁዶች አዘጋጅተው አቅርበውልናል። ለምሳሌ እስቲከሮች ✅✅ 😂😘😭😜☺️🙊👻🤡👿👽😹☠🧑‍🍳👨‍🌾👮‍♀👮🧕👳‍♂👳👨‍👧‍👧🦊🐻 እና ወዘተ እንጠንቀቅ✅✅✅ በጌታዬ ይሁንብኝ ይህን አንድ ሙስሊም ሊጠቀመው አይገባም።።።። ¤ لذا نرجو التَنَبُّه لها وعدم استعمالها ، ونشر هذا التنبيه على أوسع نطاق والدال على الخير كفاعله __ ⛔⛔⛔⛔⛔⛔ إلي من يستعمل هذه العلامة 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 هل تعلم لما ترمز؟ هذه العلامة شعار لعيد قديسهم بتريك ونحن نستعملها ونزين بها الفوائد والرسائل !!! والأن تبين ماذا تعني ولمن ترمز هذه العلامة فالواج وتداولها 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Kitabu_all_twuhiyd https://t.me/Kitabu_all_twuhiyd
إظهار الكل...
📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነው🌹كِيتَ بَ أل تَوُحِيد

ኑእንተዋወስ መልካሙን እንጋራ ዲናችን እንወቅ አለብን አደራ 📚ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 📚ከቁርዓንና ከሐዲሥ [በሰለፎች አረዳድ 📚ከታማኝ ዑለማዎች የሚሰጡ 📚ሙሃደራወችና ኢስላማዊ ግጥሞች 📚የነብያትና የሶሀባ ታሪኮች 📚ለእናቶቻችናለእህቶቻችንአስደሳች 📚ዲናዊ ንግግሮችና ፈትዋ ይቀርቡበታል እዲሁም ወቅታዊ ኢስላማዊ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ ለማንኛዉም ጥያቄና አስተያየት ካላቹ @iA_MusLim

የወር አበባ ላይ ያለች ሴት መስጂድ ውስጥ መግባት ትችላለች? ~~~~~ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት መስጂድ መግባቷን በተመለከተ በዑለማእ መካከል ልዩነት መኖሩ የሚታወቅ ነው። አብዛኞቹ የሚከለክሉ ቢሆኑም የሚፈቅዱት ዓሊሞች አቋም ከመረጃ አንፃር የበለጠ ጥንካሬ እንዳለው ስላመንኩኝ እሱን አቀርባለሁ። እዚህ ላይ ተርጉሜ ያቀረብኩት የሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልባኒን ረሒመሁላህ ፈትዋ ሲሆን ለተጨማሪ ማብራሪያ የሸይኽ ፈርኩስን ፈትዋ ሊንክ አያይዣለሁ። ወደ ፈትዋው:– ጥያቄ:— የወር አበባ ላይ ያለች ሴት መስጂድ ውስጥ መግባት ትችላለች? መልስ:– አዎ ይፈቀዳል። ምክንያቱም የወር አበባ ሴትን የእውቀት ማእዶችን— በመስጂዶች ውስጥ ቢሆኑ እንኳ— እንዳትካፈል አይከለክልምና። በወር አበባ ጊዜ የሴት መስጂድ ውስጥ መግባትን የሚከለክል ማስረጃ የለምና። ይልቁንም ከዚህ በተቃራኒ መፈቀዱን የሚያመለክት ነው ያለው። ከነዚህም ማስረጃዎች ውስጥ ሁለት የእመት ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ሐዲሦች ናቸው። አንደኛ:— ከነብዩ ﷺ ጋር ሐጅ ስታደርግ ለመካ በቀረበ ‘ሰሪፍ’ የሚባል ቦታ ስትደርስ የወር አበባ ገጠማት። ነብዩ ﷺ ሲገቡ እያለቀሰች አገኟት። "ምን አገኘሽ? የወር አበባ አየሽ?" አሏት። "አዎ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" አለች። "ይሄኮ አላህ ዐዘ ወጀል በሴት ልጆች ላይ የደነገገው ነው። ጦዋፍ እንዳታደርጊ እንዲሁም እንዳትሰግጂ እንጂ ሐጅ የሚያደርግ ሰው የሚያደርገውን ሁሉ ፈፅሚ" አሏት። በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ማስረጃችን ነብዩ ﷺ ከመስጂዶች ሁሉ በላጭ በሆነው መስጂድ እንዳትገባ አልከለከሏትም። እርሱም አልመስጂደል ሐራም ነው። ይልቁንም የከለከሏት ሶላትንና በቤቱ መዞርን (ጦዋፍን) ነው። ይህም ነብዩ ﷺ መስጂደል ሐራም ውስጥ እንድትገባ እንደፈቀዱላት ማስረጃ ነው። ነገር ግን ሶላትንና በቤቱ መዞርን (ጦዋፍን) ከልክለዋታል። … ይ እንግዲህ የወር አበባ ላይ ላለች ሴት መስጂድ ውስጥ — የትኛውም መስጂድ ቢሆን— መግባቷን የሚፈቅድ ሐዲሥ የመጀመሪያ ሐዲሥ ነው። ከመስጂደል ሐራም ውጭ ያለ ሲሆን ደግሞ ብይኑ ይበልጥ የተፈቀደ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እመት ዓኢሻን የወር አበባ ላይ እያለች መስጂደል ሐራም እንድትገባ ፈቅደውላታልና። ከሶላትና በቤቱ ከመዞር (ከጦዋፍ) በስተቀር አልከለከሏትም። ስለሆነም ከመስጂደል ሐራም ውጭ ያሉ መስጂዶች ብይን በበለጠ የተፈቀደ ነው። ሁለተኛው ሐዲሥ ደግሞ አሁን እንደጠቆምኩት እርሱም የእመት ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ዘገባ ነው። የመጀመሪያው ሐዲሥ ሶሒሕ አልቡኻሪ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ሁለተኛው ሐዲሣችን ደግሞ ሶሒሕ ሙስሊም ውስጥ የሚገኝ ነው። "ነብዩ ﷺ ‘መስገጃዋን አቀብይኝ’ ሲሉኝ ‘የወር አበባ ላይ ነኝ’ አልኳቸው። ‘የወር አበባሽኮ እጅሽ ላይ አይደለም’ አሉ።" እዚህ ላይ የወር አበባ ሲባል የተፈለገው የወር አበባውን ደም ነው። የወር አበባ ደም ያለ ጥርጥር ነጃሳ ነው። የወር አበባ ላይ ያለችዋ ሴት ግን ነጃሳ (የከሰች) አይደለችም። ከየትኛውም ሰው ነጃሳ መውጣቱ ሰውየውን እራሱን ነጃሳ አያደርገውም። ደግሞም የወር አበባ ላይ ያለች ሴት የዒልም (እውቀት) ጉባኤዎች ላይ መሳተፍ ትችላለች። ሌላ ጠያቂ:– አሰላሙ ዐለይኩም ሸይኽ:— ወዐለይኩም አሰላም። እነዚህ ጉባኤዎች በአላህ ተባረከ ወተዓላ ቤቶች (መስጂዶች) ውስጥ ቢሆኑ እንኳ ማለት ነው። በነዚህ ሁለት ትክክለኛ ሐዲሦች መሰረት ብይኑ የተፈቀደ ይሆናል። በዚህ ላይ የሚጨመረው "በነገሮች ላይ መሰረቱ ፍቁድነት ነው" የሚለው እና "መሰረቱ ከተጠያቂነት ነፃ መሆን ነው" የሚሉት ዑለማዎች ዘንድ ታዋቂ የሆኑት መርሆዎች ናቸው። ይህም እነዚህን ሁለት መርሆዎች የሚፃረር ማስረጃ እስከሚኖር ድረስ ነው። ከነዚህ ሁለት መሰረቶች ጋር የሚገጥም ማስረጃ ሲኖር ግን እንዴት ሊሆን ነው? በዚህም የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ለመከታተል፣ ቁርኣን ለማዳመጥ እና ለመሳሰሉት መስጂድ መግባታቸውን አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ "ይችላሉ" የሚል እንደሆነ ምላሹ በዚህ ይጠናቀቃል። ጠያቂ:— ሶሒሕ ሙስሊም ውስጥ በሚገኝ ሐዲሥ ላይ ነብዩ ﷺ "(የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች) ከመስገጃው ገለል ይበሉ" እንዳሉ ኡሙ ዐጢያህ ጠቅሳለች። (እንዴት ነው?) ሸይኽ:— አዎ። "እንዳይሰግዱ" ማለት ነው። ይሄ "ሐጅ ላይ ያለ ሰው የሚያደርገውን ሁሉ አድርጊ። ባይሆን ጦዋፍ እንዳታደርጊ ። እንዳትሰግጂም" የሚለው የመጀመሪያው የዓኢሻ ሐዲሥ አይነት ነው። የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች የሙስሊሞች መስገጃ ዘንድ እንዲገኙ፣ ትምህርታቸውንና ህብረታቸውን እንዲታደሙ ታዘዋል። ነገር ግን በሶላታቸው ላይ አይጋሯቸውም። ጠያቂ:– አላህ መልካምን ይመንዳችሁ። ሸይኽ:— እናንተንም። ምንጭ:— [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑ፞ር: ካሴት ቁጥር 623] ለተጨማሪ ማብራሪያ በዚህ ሊንክ ገብተው የሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ ፈርኩስን በሳል ትንታኔ ይመልከቱ። في حكم دخول الحائض المسجدَ | الموقع الرسمي لفضيلة الشيخ أبي عبد المعز محمد علي فركوس حفظه الله https://ferkous.com/home/?q=fatwa-35 ~ Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ። https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

🌸ሒጃብ የሴቶች ራስ ላይ የተደፋ አክሊል፤ የንፅህና፣ የጥብቅነትና የልዕልና ምልክት! በቂያም ቀን ዙሪያቸውን በብርሃን የሚያፈካ ጌጥ ነው።🌸🌸🌸
إظهار الكل...
#ውድ_ምክር_ለውድ_እህቴ ቁጥር አንድ ሙዚቃና በሃራም መንገድ ወንዶች ጋር የምትደዋወሉ ክብረ ንፅህናችሁንና ማንነታችሁን አርክሳችሁ በየ ሚዲያውና በየቴሌቪጅኑ በየ ቲክቶኩ... መስኮት የምትወጡ በከንቱ ስሜታ ላይ ላላችሁ ወደዳችሁም ጠላችሁም የሆነ ቀን ትሞታላችሁ ከጀናዛ አልጋ ላይ ትተኛላችሁ በፍላጎታችሁ ሳይሆን በግዳችሁ! አስተውይ እህቴ ከጀናዛ አልጋ ላይ ስተኝ ብቻሽን ነው ጓደኛም ሆነ ሌላ ወዳጅሽ አይከተልሽም ታዲያ ያኔ ለአላህ ምን ልትይው ነው? አላህ የምትሰሪውን እንደሚከታተልሽ እያወቅሽ ግን ከአላህ ይልቅ የሰዎች ሃቅ ያስበለጥሽ እህቴ ያኔ ለአላህ ምን ልትይው ይሆን!? የሆነ ቀን በድንገት ቀንሽ ይደርስና ከጀናዛ አልጋ ላይ ትታጠቢያለሽ ግን አስተውለሽ ታውቂያለሽ ከዛ አልጋ ላይ ተኝተሽ ታጥበሽ በነጠላ ጨርቆች ብቻ ነው ተገንዘሽ ወደ ቀብርሽ የምትገቢው አላህ ያዘነላቸው እህቶች ብቻ ሲቀሩ ብዙዎች በዚህ ሰአት በሰርግ ሰአታቸው ሰውነታቸውን እየተገላለጡ ነው ሚገኙት ረሱላችን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)እንደተናገሩት ከኡመቶቸ ብዙ ሴቶችን ጀሃነም ውስጥ ያየኋቸው በእርቃን ልብስ የሚገላለጡ ነው ብለዋል። ያ አላህ! ውድ እህቴ ለመሆኑ የጀሃነም እሳት ከዱንያዋ እሳት በምን ያክል እጥፍ እንደምትበልጥ አውቀሽ ይሆን? አላህ ሆይ ጠብቀን ከእሳት! በአላህ  ይሁንብኝ ራሳችሁን የምትገላለጡ እህቶች አስቡት በዱንያ አንድም ቀን በስርዓት ሳትሸፈኑ ነገ ሞታችሁ በጀናዛ አልጋ ላይ በነጠላ ጨርቅ ተገንዛችሁ ቀብር ከመግባታችሁ በፉት ራሳችሁን ብትሸፍኑ አይሻልም? አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ በአንድ ዛፍ ላይ ያሉ ቅጠሎች ከዛፉ ላይ ከረገፉ የግንዱ መጨረሻ ምን እንደሚሆን ታውቃላችሁ? ተቆርጦ እሳት ላይ ይማገዳል አይደል? ልክ አንደዛው አንዲት ሴት ራሷን ከገላለጠች ቁጥብነቷን ከራሷ ላይ ከገፈፈችውና በማይረባ ብጥቅጥቅ ልብስ ራሷን ከገላለጠች መጨረሻዋ የዛ ግንድ ነው ሚሆነው።   በአላህ ይሁንብኝ የሴት ልጅ ቁጥብነቷ(ሃያዋ)ለአላህ ያላት እውነተኛ ታማኝነትና ኢማኗ ነው። እባክሽን እህቴ ወደ አላህ ተመለሺ በዚህ ባለንበት ዘመን ሰርጎች የጭፈራ ፕሮግራሞችና መሰል የፊትና መድረኮች የበዙበት ግዜ ላይ ነው ያለነው አላህ ያዘነላቸው እህቶች ሲቀሩ ብዙዎች በዚህ ፊትና ላይ ወድቀዋል   በአላህ ይሁንብኝ ውድ እህቴ ብዙ ሙሸራዎች አሉ በሰርግ ቀናቸው የሰርግ ልብስ ከመልበሳቸው በፊት ከፈን አድርገው ወደ ቀብር የገቡ ውድ እህቶቸ ለዚች ዱንያ አትጨናነቁላት ይህች ዱንያ ረጅም መስላ የምትታያችሁ ካላችሁ አትሳሳቱ በጣም አጭር ናት። ሌላው መልዕክቴ ደግሞ አይናችሁን የምትቀነደቡና ሰውነታችሁን ለባዳ ወንዶች የምትገላለጡ እህቶች ዋ! አላህ ከረገማቸው ሴቶች መካከል ተቀንዳቢዎችንና የሚገላለጡ ሴቶችን ነው ተጠንቀቁ በተጨማሪም የሴቶች የውበት ሳሎን የምትሰሩ እህቶች ከኔ በበለጠ እናንተ በደምብ ነው ምታውቁት ገንዘብ ለማግኘት ብቻ ሲባል ምን ያክል ሸሪአን ያልጠበቁ አላህን የሚያስከፉ ነገሮች በነዚህ ቤቶች እንደሚሰሩ ታውቃላችሁ። በነዚህ የሴቶች ውበት ሳሎን የምትሰሩ እህቶቼ አደራችሁን ይቅርባችሁ እንጂ ሃራም ነገር አትብሉ አላህን ለምኑት ሃላል የሆነ ስራ ይሰጣችኋል። ሌላው ፊታችሁንና ሰውነታችሁን ወይም ኒቃብ ለብሳችሁ አላህን የሚያስቆጣ ስራ የምትሰሩ እህቶቸ ሆይ ተጠንቀቁ አላህ ያያችኋል ስንት ሴቶች ናቸው ማንነታቸውን ሸፍነው በየ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሃራም ነገሮችን የሚሰሩ ውድ እህቴ በሶሻል ሚዲያ ላይ ለወንደሞችሽ ፊትና ከመሆን ተቆጠቢ አይ አልሰማም የምትይ ከሆነ አላህን እያስቆጣሽ ስለሆነ  ምን አልባት መጨረሻሽ ሊበላሽብሽ ይችላል። ውድ እህቴ የዋህ አትሁኚ ሶሻል ሚዲያ ላይ ማንነታቸውን ደብቀው የሰው አውሬ የሆኑ ወንዶች አሉ ምንም ሌላ አላማና ግብ የሌላቸው ዋናው አላማቸው ሴቶችን ብቻ ለስሜታቸው መጠቀም የሚፈልጉ ወጣቶች አሉ ተጠንቀቁ ከነዚህ ወጣቶች እጅ ላይ እንዳትወድቁ ውድ እህቴ ይህ ምክሬ ከልቤ ወንድማዊ ነው በደምብ ተጠቀሙበት አላህን ፍሩ በአላህ ይሁንብኝ አላህ(ሰብሃነ ወተዓላ)ይሄን ሁሉ ጤንነት ሰጦሽ እሱን የምታስቂጪው ከሆነ በደቂቃ ውስጥ ወደ ሞት አልጋ ላይ እንድትተኝ ያደርግሻል የአላህ ቅጣት ከባድ ነው። ወደ አላህ ተመለሺ ከመሞትሽ በፊት ሴቷ ሒጃቧን በአግባቡ ከለበሰች ይህም የሚያስተላልፈው የራሱ መልዕክት አለው፡፡ ይኸውም «እኔ ላንተ የተከለከልኩ ነኝ የሚል ይሆናል፡፡ አዎ! ሴቶች ሒጃባቸውን በአግባቡ ከለበሱ ጨዋ እንደሆኑ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ በባለጌዎችም አይደፈሩም፡፡ በመሠረቱ ሒጃብ ማለት አማኝ ሴቶች ለአስገዳጅ ነገሮች ከቤቶቻቸው ሲወጡ ሰውነታቸውን የሚሸፍኑባቸው ልብሶች ናቸው፡፡ በተቃራኒውም ተቀባብታ ከንፈሯን ሊፒስቲክ አጥግባ፣ ጡቶቿን አሹላ፣ ደረቷ ከፍታ፣ ዓይኖቿን ተኳኩላ፣ ፀጉሯን እያሳየሽ፣እጆቿንና እግሮቿን ገላልጣ ሱሪ ለብሳ፣ ሰውነቷን አጣብቃ፣ አጭር ጉርድ ለብሳ ከቤት የምትወጣ ሴት አለባበሷ የሚያስተላልፈው መልዕክት ሰውነቴ ለናንተ የስሜት መውጫ ለዚና የቀረበ ነው እኔን ለማግኜት ብዙ ልፋት አይጠይቅም ቅረቡኝና አላህን እንመፅ የሚል መልዕክት ነው ሚያስተላልፈው ምክንያቱም አላህን አትብቃ ብትይዝና ወንዶችን ለመፈተን ባታስብ እንደዚህ አላህን አምፃ ከቤት ባልወጣች ነበር። እና ዋናው አላማቸው ይሄ ነው ወንዶችን ለማጥመድ የታሰበ ነው በዚህ ምንገድ ያላችሁ እህቶች አላህን ፍሩ የአላህን ቅጣት ፈርታችሁ ወደ አላህ ተመለሱ አላህ ስታምጭው ዝም የሚልሽ ታጋሽ ስለሆነና እድል እየሰጠሽ ነው እንጂ እንዳመፅሽው አንቺን መቅጣት ይችላል ግን ይታገሳል እና ውድ እህቴ ታጋሽነቱ አያዘናጋሽ ሞት ስለማይቀር ሁሌ ያን እድል ላታገኝው ትችያለሽ።   በመጨረሻም እናንተ እራሳችሁን ንፁህ አድርጋችሁ አላህ ያዘዛችሁን እየተገበራችሁ ራሳችሁን ቁጥብ አድርጋችሁ የአላህን ውድ ሃገር የምትጠባበቁ አብሽሩ ፈተናው ቢበዛባችሁም መጨረሻችሁ ግን በምንም የማይገመት ትልቅ ወደሆነው ጀነት ነው! ኢንሻ አላህ። ወንጀል ላይ የምትገኙ እህቶቸ ወደ አላህ ተመለሱ ወላሂ አላህ ወደሱ ተመላሾችን ይቀበላል እንዲሁም ወንጀላችሁን በመልካም አጅር ይቀይርላችኋል ታዲያ ምን ትጠብቃላችሁ። በዱዓችሁ አትርሱኝ ወሰለላሁ አላ ነብይና ሙሃመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ አጅመዒን መልዕክቱን ለአላህ ብላችሁ ሼር አድርጉት የአንድ ሰው ወደ አላህ የመመለስ ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ነው ወደ አላህ ለተመለሱትም ለፅናታቸው ሰበብ ይሆናቸዋል በአላህ ፍቃድ። ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር SHARE SHARE SHARE SHARE ለመልካም ነገር አይደከምም! እንመካከር በመመካከር ህይወት ቀለል ትላለች! #በዝሙት_አንዘምን
إظهار الكل...
⭕️ረመዷን መች ነው⁉️ 🚫ጥያቄ 📌 ብዙ ጊዜ በየማህበራዊ ሚዲያው የሚተላለፍ አንድ ሀዲስ አለ ፣ እሱም ረመዷን መች እንደሆነ #ለመጀመሪያ ጊዜ ለወንድሙ የተናገረ #እሳት ከሱ ሀራም ትሆንበታለች ይላልና ይህ ሀዲስ ትክክለኛነቱ እንዴት ነው⁉️ ✅መልስ✅ ✅ ይህ ሀዲስ #በየትኛውን የሀዲስ ኪታብ ላይ በጭራሽ ሊገኝ #ይቅርና በተቀጠፋ ሀዲሶች መዝገብ ውስጥ እንኳን #የማይገኝ በነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ #የተቀጠፈ ሀዲስ ነው።ይህን ሀዲስ በየትኛውም መልኩ #ማሰራጨትም ሆነ #ማስተላለፍ የተከለከለ ነው። ♻️ ምንጭ: ኢማሙ ሲዩጢይ ፣ ተድሪቡ ራዊ ____
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.