ar
Feedback
ከግጥም ማዕድ

ከግጥም ማዕድ

الذهاب إلى القناة على Telegram

#አሁንም_እላለሁ_በህይወት_እያለሁ_ውቀሱኝ_በህይወት_እያለሁ_አበረታቱኝ_የግድ_እስክሞት_መጠበቅ_የለባችሁም_እና_ዛሬ_ጀምሩ_ቻናሌን_በመቀላቀላቀል_ደግፋኝ join 👇👇👇👇👇 @getemk2g @getemk2g @getemk2g @getemk2g

إظهار المزيد
425
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

القنوات المماثلة
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
مايو '24
مايو '240
في 0 قنوات
أبريل '24
+23
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '24
+29
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '24
+50
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '24
+22
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '23
+28
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '23
+15
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '23
+33
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '23
+16
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '23
+26
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '23
+31
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '23
+34
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '23
+16
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '23
+15
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '23
+19
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '23
+124
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '230
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '220
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '220
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '220
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '220
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '220
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '220
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '220
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '220
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '22
+7
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '22
+28
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '22
+3
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '22
+1
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '21
+201
في 0 قنوات
التاريخ
نمو المشتركين
الإشارات
القنوات
06 مايو0
05 مايو0
04 مايو0
03 مايو0
02 مايو0
01 مايو0
منشورات القناة
ገጣሚ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g

2
#በሬን_ስበር ፧ አይደክምህም? ማንኳኳቱ የማይከፈት ቁልፍልፍ በር፤ እስከምከፍት አትጠብቅ እጅ የለኝም በሬን ስበር፤ እጅ የለኝም ለመክፈቻ ተገንጥሏል በሀጢአቴ፣ እስከምከፍት አትጠብቅ ሰብረህ ግባ ወደቤቴ፣ ስታንኳኳ ብሰማህም ብፈልግም ልከፍትልህ፣ እግር የለኝም ለመነሳት ምናባቴ ልሁንልህ፣ ወዳጄ ነው ብለህ ናፍቀኸኝ ብትመጣም፣ የቆለፍኩት በሬ ወዳንተ አያስወጣም፣ ኳ ኳ ኳ... አይደክምህም? ማንኳኳቱ የማይከፈት ቁልፍልፍ በር፤ እስከምከፍት አትጠብቅ እጅ የለኝም በሬን ስበር፤ ባክህ ግባ የኔ ጌታ እስከምከፍት አትጠብቅ፣ በተዘጋ መግባት ታውቅ የል? ወዳጅህን ስትናፍቅ፣ ካሻህም ስበረው በር አይኑረው ግቢው በር አይኑረው ቤቴ፤ አንተ ካለህልኝ የድንግል ማርያም ልጅ ይገደላል ሞቴ፤ ኳ ኳ ኳ... አይደክምህም? ማንኳኳቱ የማይከፈት ቁልፍልፍ በር፤ እስከምከፍት አትጠብቅ እጅ የለኝም በሬን ስበር። ገጣሚ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
579
3
#ታድላ_ግን ፧ ምን አለባት እሷ? ዝም ብላ ትሳቅ፤ መናፈቅ ይደንቃል የማብሸቋን ስላቅ፤ ታድላ ግን... ስትስቅ ጉንጯ ስርጉድ ይላል፤ ድርብ ጥርሷ ለቅሶ ይገላል፤ ታድላ ግን... አይንም አላት የሚያሳሳ፤ ለቅፅበትም የማይረሳ፤ አላት አላት ሁሉም ነገር፤ ከጥላቻ ክፋት በቀር። ገጣሚ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
322
4
#እጅ_ለሌለው ፧ መጥቼልሻለሁ ሁለት እጄን ትቼ፤ ቆሚያለሁ ከበርሽ ማንኳኳት ፈርቼ፤ "ለምን ፈራህ?" ካልሺኝ፣ አማላይ ቁመና ማራኪ ደም ግባት፤ እግርና ጭንቅንላት ልብና ኩላሊት፤ እጅ ለሌለው ሰው ትርጉም የላቸውም፤ እንኳን ለአንቺ ለበሩ አይመቸውም፤ ስለዚህ ተመለስኩ በረዘመው እግሬ፤ እጅ አጥሮ እንደገፋኝ ለልቤ ነግሬ፤ ሄጃለሁ ከበርሽ መንገዱን አልይዝም፤ ለኔም ቀን ወቶልኝ እጄ እስከሚረዝም። #መታሰቢያነቱ_ለገንዘብ_ሲሉ_ፍቅርን_ለረገጡ_ሰዎች_ይሁንልኝ ገጣሚ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
467
5
ገጣሚ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ join👇 @getemk2g
353
6
ውድ ቤተሰቦች በቅርቡ ከላይ የለቀኩት ግጥሜ☝☝☝በቅርቡ በድምፅ ይለቃል✍️
13
7
#ልኑር_እየፈሰስኩ ፧ የማይገኝ ዕድል ታውቂያለሽ መክሊቴ፤ የምድር ገነት ነው በፍቅርሽ መሞቴ፤ ካጠገብሽ ሳልሄድ ከጎኔ ሳትርቂ፤ ፍቅርሽ መቼ አነሰኝ ናፍቆት አትመርቂ፤ ተይ ግን እዘኚልኝ፣ እያለሽ አትናፍቂኝ፣ ስመሽ እያቀረብሽ ስቀሽ አትራቂኝ፤ ከማህተብሽ ስር ዘላለም ደብቂኝ፤ የመኖር ጉጉቴ ከፀሀይ ዕድሜ እኩል፤ ሲመሽ እንዳልጠፋ..... ቆሜ ተማከርኩኝ በጨረቃ በኩል፤ በክረምት እንዳልሸሽ ደመናን ተጠጋው፤ ካንቺ እንዳልለያይ.... ዘላለም ለመኖር ተፈጥሮን አወጋው፤ ጨረቃና ፀሀይ ኮከብም ደመና፤ አልጨከኑም በኔ ስላንቺ ነውና፤ ሁሌም አለሁ አልኩኝ አንቺጋ ለመድረስ፤ ዘወትር ኖርኩልሽ ናፍቆት ለመቀነስ፤ ናፍቆት መቀነሻ መፍትሄ ሰብስቤ አስቤ እንደጨረስኩ፤ ፀሀይ ጨረቃና ደመናን ስጠብቅ ዝናብ ሆኜ ፈሰስኩ፤ ግን ደሞ አላዘንኩም እንደሰው አሮጥሽም፤ ታድያለሁና ከኔ ለመጠለል ጥላ አልዘረጋሽም፤ ልዩዬ የኔ አለም፥ ከፀሀይ ጨረቃ ከኮከብ ደመና እየተቀናነስኩ፤ ካንቺ ሳልለያይ በፀአዳ ገላሽ ልኑር እየፈሰስኩ። ገጣሚ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
881
8
#ኖረዋል ፧ ከኔ ጋራ ሆነሽ፥ ለምን ትስቂያለሽ? መጀመሪያ ሳውቅሽ..... ፈገግ ብለሽ ነው ልቤን የማረክሺው፤ ለማን ነው ምትስቂው? ከንፈርሽ ይከደን ጥርስሽን መልሺው፤ ከኔ ጋራ ሆነሽ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ተክዘሽ እኮ ነው ሆዴን የበላሽው፤ ላባብልሽ ብዬ ልቤን የረታሽው፤ ዝም በይ ከኔጋ ማንም እንዳይመኝሽ፤ መሳሳቱ አይቀርም ከሳቅሽ ወይ ካለቀስሽ፤ አትሳቂ አታልቅሺ የዛኔ አይሟገቱም፤ ዝም ብለው ዝም ያሉ ኖረዋል አልሞቱም። ገጣሚ ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
722
9
#አውቃለሁ ፧ እሾህ በሞላው ማሳ አውቃለሁ ማራኪ አበባ፣ በጦርነት ሜዳ ላይ አይቻለሁ አንጀት ሲባባ፣ ከብዙ ክፉዎች መሀል ደጋግ ልብ ይበቅላል፣ እንደው ምናልባት አንዳንዴ... ከብዙ ድመቶች መሀል አይጥ በሰላም ይውላል፣ ይገላል የተባለ መርዝ መድሀኒት ሆኖ ያድናል፣ ቆሻሻ መሀል ተጥሎ ሲፈተሽ አልማዝ ይሆናል፣ እንደው ምናልባት አንዳንዴ... ሀጥአን በሞሉት ዓለም እንደ ኖህ ፃድቅ ይገኛል፣ በክህደት የደማው ልቤ "እሷ ታማኝ ነች" ይለኛል። ገጣሚ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
749
10
#ቀንቼኮ_አይደለም            ፧ የሳመሽን ሁሉ "አትሳሟት" እያልኩኝ የምሟገትልሽ፤ ዘመድ ጓደኛሽን "እንዳትነኳት" እያልኩ ካንቺ ማርቅልሽ፤      ..............   ቀንቼ'ኮ አይደለም      .............. ላንቺው አስቤ ነው የሚያገኙሽ ሁሉ ጉንጭሽን ሲያለፉ፤ ስለምሳሳ ነው እየደጋገሙ በሳቅሽ ስር ሲያልፉ፤       ..............   ቀንቼ'ኮ አይደለም      .............. አትሳሟት እያልኩኝ ካገኘሁት ሁሉ ከሰው የምጣላው፤ ስለምፈራ ነው፥ ፈገግ ስትዪ ስርጉድ የሚለውን ከንፈር እንዳይሞላው።                ገጣሚ✍️             #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
663
11
#ላግባሽና ፧ እኔን የጠበቅሺኝ እየሰጠሽ የፍቅር ጥግ፣ በዓለም ላይ ስኖር በፍቅርሽ የማድግ፣ በየቀኑ የምታከም ከአይኖችሽ ነፀብራቅ፣ አይችልም አካሌ ከአካልሽ ለመራቅ፣ በፈገግታሽ መሀል ሲሰረጉድ ጉንጭሽ፣ ደስታዬ እጥፍ ነው አቅፌ ስስምሽ፣ የማፈቅርሽ ስጦታዬ ከኔ አትራቂ፣ ከአጠገቤ እያለሽ ጎኔ ሆነሽ ተናፋቂ፣ እኔ አፍቃሪሽ በየሰከንድ የምናፍቅ፣ ላግባሽና ልገላገል ለደቂቃ ካንቺ እንዳ'ርቅ። ገጣሚ✍️ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
621
12
#ድፍረት ፧ አይሰለችህ እኔን መማር በየለቱ፤ አይሰበርም? በቃልህ ሀይል ልቤ አለቱ፤ ማረኝ ብዬ የምበድል፤ እያዳንገከኝ የምገድል፤ ስትፈልገኝ፥ የማልገኝ አንድ ግልገል፤ ኮብልያለሁ አንተን ትቼ ሀጢያቶቼን ለማገልገል፤ ሳገለግል ኖሬ ሀጢአትን በብዙ፤ ለሞት አስረከበኝ ይህ ነበር ደሞዙ፤ ወዮ የኔ ጌታ በምን አንደበቴ ማረኝ እልሀለሁ፤ አስገባኝ ከቤትህ ብዬ አልጠይቅህም በደሌን አውቃለሁ፤ ባክህ አባቴ ሆይ ባክህ የኔ ጌታ፤ ከገነት በሩ ላይ ይኖር ይሆን ቦታ፤ ማን ፈራጅ አረገኝ በየትኛው ሀይሌ፤ እዛስ በምን ፅድቄ ድፍረት ነው ይህ ቃሌ። ገጣሚ✍ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
781
13
#መድሃኒቴ ፧ አለች ደሞ መድሃኒት አንገት ስማ የምታክም፤ ቃል ከአንደበት የምትሰውር ስቃ ምታደክም፤ *** ግልፅ የሆነች ለኔ ምንም የማትደብቅ፤ አጠገቤ ሆና እያየችኝ የምትናፍቅ፤ መጨነቄ የሚጨንቃት መደሰቴ ለሷ ደስታ፤ ቀን ሞላ ጎደለ አትርቀኝም ሁኔታ አይታ፤ የሆነችኝ ለኔ ፅናት ያቆመችኝ ተንበርክካ፤ ከፀሐይ ፍም ያዳነችኝ አስጠልላኝ እንደ ዋርካ፤ *** አለች ደሞ መድሀኒት አንገት ስማ የምታክም፤ ቃል ከአንደበት የምትሰውር ስቃ ምታደክም፤ *** ተቀብታ የፍቅር ናርዶስ ፍቅር ፍቅር የምትሸት፤ አለች ደሞ አንቺን አይነት የምትማርክ እንቡጥ እሸት። ገጣሚ #ካሳሁን_ክንፈ አሪፍ ግጥሞችን ከፈለጋችሁ Join👇 @getemk2g
842
14
#ስልክ_መግዛት_የምትፈልጉ ዋጋ 7,800 ብር INFINIX SMART 6 RAM 2 Storage 32 GB Android 10 0902414335 ሳያመልጣችሁ ደውሉልኝ ወይም በውስጥ አናግሩኝ 👉 @kases+1
#ስልክ_መግዛት_የምትፈልጉ      ዋጋ 7,800 ብር INFINIX SMART 6 RAM 2 Storage 32 GB Android 10    0902414335 ሳያመልጣችሁ ደውሉልኝ ወይም በውስጥ አናግሩኝ 👉 @kaseshart
90
15
#ገለሽኛል ፧ በታመንኩኝ ዝቅ ባልኩኝ ለፍቅር ስል፤ አደማሽው ያዳንሺውን ክፉ ቁስል፤ ፍቅር እውር ነው ተታለልኩኝ፤ በሙሉ ልብ ካንቺ ዋልኩኝ፤ ቁልቋል ሆኜ ኖሬ ካ'ጋም፤ ምርጫ ያለው ለካ አይረጋም፤ አንቺ ምን አለብሽ ሁለት እናት አለሽ፤ አንዱ ሲሞትብሽ በአንዱ ታለቅሻለሽ፤ የሞትኩት እኔ ነኝ ሳምንሽ ክደሽኛል፤ ለመኖር ስጓጓ ዋሽተሽ ገለሽኛል፤ አመሰግናለሁ በክደት ቢላ ስለገደልሺኝ፤ ብሞትም እንኳን ወደተሻለው የፍቅር ገነት ስላስገባሺኝ። ገጣሚ✍ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
720
16
#ስብራት ፧ አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ናት ተሰብረህ መቆም ይከብዳል፤ ተማምነህ የተደገፍከው እየሸረፈህ ይወርዳል፤ አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ናት ምንም ምህረት የሌላት፤ በቁምህ ትገልሃለች መሞትህ ካል
#ስብራት ፧ አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ናት ተሰብረህ መቆም ይከብዳል፤ ተማምነህ የተደገፍከው እየሸረፈህ ይወርዳል፤ አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ናት ምንም ምህረት የሌላት፤ በቁምህ ትገልሃለች መሞትህ ካልተሳካላት፤ እኔ ግን መኖር አላቆም ትንፋሼ እስካልተዘጋ፤ ምናልባት ቢዘገይ እንጂ ጭለማ አይኖርም ሲነጋ። ገጣሚ✍ #ካሳሁን_ክንፈ join👇 @getemk2g
565
17
ገጣሚ #ካሳሁን_ክንፈ Jion👇 @getemk2g
334
18
#በእንባዬ_እንዳጠፉ ፧ ትላንትናን እያሰብኩኝ ለምን ብዬ እንባ ላፍስስ፤ በሀዘኔ ለሚያለግጡ የጠላቴን አንጀት ላርስ፤ በሆዴ ቻል ዋጥ አድርጌ ህመሞቼን ሽፍንፍንፍን፤ በመድማቴ ስቄ ቁስሎቼን ሽፍን፤ ለምን ሲባል ተሰንሰቅስቄ ደም ማንባቴ፤ ለምን ሲባል ወዳጆቼ ይታመሙ በጉዳቴ፤ ከላይ በፈገግታ በሳቅ ስንከተከት፤ ጥርሶቼ እስከኖሩ አይኔን አይመለከት፤ ተከትሮ የቆመ እንባ ተጠራቅሞ ዓይኖቼ ስር፤ ቅርቡን እንጂ ጨልሞብኝ ሩቅ አላይም እንደንስር፤ እንባዬ ጎርፍ ሆኖ ሀገር እንዳይጠፋ፤ ወንዝ ዳር አቁሙኝ እጅጉን ስከፋ፤ የዛን ጊዜ ይውረድ ከውሃው ይደብለቅ፤ ጨው ካለው ባህር ላይ በውቅያኖስ ይጥለቅ፤ ውሃ ጣዕም የለውም እስከነፃ ድረስ፤ እንደኔ የከፋው የአንድ ሰው እንባ ነው ጨዋማ ውቅያኖስ፤ ሲቀላቀል የኔ የተገደበ እንባ መውረድ ከጀመረ፤ ሊቀጥል አይችልም የተዋበው ሁሉ ሰርክ እንደሰመረ፤ በሳቅ የታጀበ የታመቀ እንባ የደቀቀ ተስፋ፤ ድጋሜ እንዳቶጉኝ አቅቶኝ አልቅሼ ዓለም እንዳጠፋ። ገጣሚ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
929
19
የምወዳችሁና የማከብራችሁ ውድ የግጥም አፍቃሪያን የምትወዱኝና የምታደንቁኝ ቤተሰቦቼ ስለምትደግፉኝና ስምታበረታቱኝ ከልብ አመሰግናለሁ🙏 ይህን የግጥም ቻናሌን👉@getemk2g @getemk2g @getemk2g ☝☝☝ ጎደኞቻችሁን በመጋበዝ ቢያንስ 2 ሰው join አድርጎ እንዲቀላቀል አድርጉልኝ ስለምትደግፉኝ አመሰግናለሁ🙏
593
20
#ገጣሚው_የት_ጠፋ ፧ ብዕሩ ጠፋበት ብራና አለቀበት? ብርሀን ሲጠብቅ ጨልሞ ቀረበት? ወይስ ቃላት አጣ? በሀሳብ ገረጣ? ገጣሚው የት ጠፋ? አጥቶ ይሆን ተስፋ? አቅሙ ደቃቆ ተሰባብሮ ይሆን? ሕይወት ሰነከለው መሆን አለመሆን? ከራሱ ተጣላ? ወይንስ ከሌላ? ወይ ስራ ቀየረ? በግጥሙ አፈረ? የት ጠፋ ገጣሚው ምንስ ተፈጠረ? ግጥምን ከራቃት ቀናት ተቆጠረ፣ ይህ ሁሉ ጥያቄ ተፈጥሮ ሲያበቃ፣ የገጣሚው ግጥም እንዲ ነበር በቃ። ገጣሚ✍ #ካሳሁን_ክንፈ Join👇 @getemk2g
851