cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Tikvah-University

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 094
المشتركون
+1124 ساعات
+337 أيام
+1730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#Update በፀጥታ ችግር ምክንያት ምዝገባ ማድረግ ላልቻሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ አካባቢዎች ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል። በዚህም የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል። በትግራይ ክልል ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በሁለት ዙር ፈተናው ይሰጣል ብለዋል። ዘንድሮ 701,489 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚወስዱ ተናግረዋል። የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በተለይም በአማራ ክልል የሚገኙና ምዝገባቸውን ማድረግ ላልቻሉ በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅ ገልፀዋል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ክረምት ለሚሰጠው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን የአሰልጣኞች ስልጠና 224 አሰልጣኞች እየወሰዱ ነው ተብሏል፡፡ በ28 የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አማካይነት ለ60 ሺህ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሒሳብ፣ ሳይንስ እና እንግሊዝኛ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና እንደሚሰጥ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ተናግረዋል። በሐምሌ እና ነሐሴ ወራት የሚሰጠው ስልጠናው፤ የቅድመ አንደኛ፣ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የማስተማር ስነ-ዘዴ አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
ዛሬ በመላ ሀገሪቱ መሠጠት የጀመረው የ8ኛ ክፍል ክልላዊና ከተማ አቀፍ ፈተና በአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ እየተሠጠ አይደለም። በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች ፈተናው እየተሰጠ አለመሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል። "ወቅታዊ የፀጥታ ችግር በተፈጠረባቸው የምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች አንድም ተማሪ እንደማይፈተን" የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ 32 ትምህርት ቤቶች ብቻ የመማር ማስተማር ሥራቸውን እያከናወኑ በሚገኝበት ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በርካታ ተማሪዎች ለፈተናው አለመቀመጣቸው ታውቋል፡፡ “ምንም ዓይነት ተማሪ የማያስፈትኑ ሁለት ዞኖች አሉ፡፡ ሰሜን ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ምንም ተማሪ አያስፈትኑም፡፡ 6ኛም፣ 8ኛም፣ 12ኛም አያስፈትኑም፡፡ ምስራቅ ጎጃም የተወሰነ ያስፈትናል" ነበር ያሉት ኃላፊዋ፡፡ ፈተናው በሚሰጥባቸው ሌሎች ዞኖች ደግሞ ከ350 ሺህ በላይ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል፡፡ ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኔ 13 እና 14/2016 ዓ.ም በአማራ ክልል ይሰጣል፡፡ ምስል፦ ደሴ፣ ባህርዳር እና ሰቆጣ @tikvahuniversity
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር❗️ @samcomptech ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እና ለሌሎችም አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ ያገኛሉ! ሱቃችንን ይጎብኙ! 🔔 የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ! ይዘዙን ያሉበት እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
إظهار الكل...
የ8ኛ ክፍል ክልል/ከተማ አቀፍ ፈተና በመላ ሀገሪቱ በመሰጠት ላይ ይገኛል። ፈተናው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎችም መሰጠት ጀምሯል። በከተማዋ 86,672 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚሰጥ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወቃል። ተማሪዎች በጠዋቱ የፈተና ክፍለጊዜ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ፈተናዎችን የሚወስዱ ይሆናል፡፡ የፈተናውን አሰጣጥ የሚያስፈፅሙ ፈታኞች፣ ተቆጣጣሪዎች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች መመደባቸው ተገልጿል። ምስል፦ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ @tikvahuniversity
إظهار الكل...
👍 1
ሰላም ሚኒስቴር ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የክረምት በጎ ፊቃድ ስልጠና ለተማሪዎች መስጠት ጀምሯል። አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ መቐለ ዩኒቨርሲቲ እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ስልጠናውን ለተማሪዎቻቸው ትናንት መስጠት ጀምረዋል። ተማሪዎቹ ትምህርታቸውንና ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ ለአንድ ወር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ይሰማራሉ። ምስል፦ አምቦ፣ መቐለ እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች @tikvahuniversity
إظهار الكل...
👍 1
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን ፈተና ዛሬ ይሰጣል። የማኅበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች የጂኦግራፊ ትምህርት ፈተና በአራት ክፍለጊዜ ተከፍለው በኦንላይን ይወስዳሉ። ትናንት በነበረው የመጀመሪያ ቀን ፈተና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ተማሪዎች በተፈጠረ የቴክኒካል ችግር ምክንያት በቂ የፈተና ሰዓት እኖዳልነበራቸው በርካታ ተማሪዎች አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል። የማኀበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች እስከ ሐሙስ ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል። ምስል፦ አምቦ፣ ቡሌ ሆራ፣ ዳምቢ ዶሎ እና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች @tikvahuniversity
إظهار الكل...
👍 1
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ዛሬ መሠጠት ጀምሯል። የማኅበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች የሒሳብ ትምህርት ፈተና ሙሉ ቀን በአራት ክፍለጊዜ ተከፍለው በኦንላይን ሲወስዱ ውለዋል። የማኀበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች እስከ ሐሙስ ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል። 78 ሺህ የሚሆኑ የሪሚዲያል ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከታህሳስ ጀምሮ ሲከታተሉ የቆየ ሲሆን፤ ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑ ይታወቃል። ምስል፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና እንደማይቀመጡ ተገለፀ። በክልሉ የተፈጠረው ግጭት በተለይ በምስራቅ ጎጃም ዞን በርካታ ትምህርት ቤቶች እንዳያስተምሩ ማድረጉን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገልጿል። በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙ 996 አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የመማር ማስተማር ሥራቸውን እያከናወኑ የሚገኙት 32 ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው። በትምህርት ዘመኑ ከአንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ539,996 በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንደሚመጡ ቢታቀድም፣ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት ከ13,000 የሚበልጡ አይደሉም ብሏል መምሪያው። በዞኑ 791 ት/ቤቶች 41,944 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ፈተና እንደሚያስፈትኑ ቢጠበቅም፤ 12 ትምህርት ቤቶች በሁለት ዙር 506 ተማሪዎችን ብቻ ያስፈትናሉ ተብሏል። በተመሳሳይ በዞኑ በ593 ትምህርት ቤቶች 38,203 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ ቢታቀድም፣ በ10 ትምህርት ቤቶች 431 ተማሪዎች ብቻ በሁለት ዙር ፈተና የሚወስዱ ይሆናል። በዞኑ በ65 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 19,657 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ ቢታሰብም፤ 5 ትምህርት ቤቶች 577 ተማሪዎችን ብቻ በሁለት ዙር የሚያስፈትኑ ይሆናል። የሰላም ዕጦት ችግሩ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ያደረገ፣ ተማሪዎችንና ማኅበረሰቡን በስነልቦና ያኮሰሰ እና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የትምህርት ማኅበረሰብ አባላትን ከመደበኛ ሥራቸው ውጭ ያደረገ መሆኑን መምሪያው ገልጿል። በአማራ ክልል ዘንድሮ 184,393 የ8ኛ ክፍል እንዲሁም 170,470 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወቃል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር❗️ @samcomptech ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እና ለሌሎችም አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ ያገኛሉ! ሱቃችንን ይጎብኙ! 🔔 የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ! ይዘዙን ያሉበት እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
إظهار الكل...