EECMY - School (online class)
الذهاب إلى القناة على Telegram
This channel is created with the thought of teaching students by supplying important files. Please pay attention.
إظهار المزيد487
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
+230 أيام
أرشيف المشاركات
ተማሪዎቻቸን የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተናን አጠናቀው ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ከመምህራኖቻቸው ጋር የተመለሱ ሲሆን የእረፍት ጊዜያቸውን እንዴት ማሳለፍ እንዳለባቸው ፤ የፈተናቸውን ውጤት እንዴት በተረጋጋ ሁኔታ መጠባበቅ እንደሚገባቸው ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ምክር ተሰጥቷቸዋል፡፡ ተማሪዎችም በበኩላቸው ለትምህርት ቤቱ ያላቸውን ገንቢ አስተያየት በግልጽ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም በራስ ተነሳሽነት የመማሪያ ክፍላቸውን አዋጥተው ለማደስ ቃል ገብተዋል፡፡ በመጨረሻም ከትምህርት ቤቱ ቢርቁም የትምህርት ቤቱን ቴሌግራም አካውንት እንዲሁም የመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ስልክ በመጠቀም ከትምህርት ቤት የሚለቀቁ መረጃዎችን እንዲከታተሉ ማሳሰቢያ ከተሰጣቸው በኋላ የፎቶ ፕሮግራም ተካሂዶ ወደ ቤታቸው ተሸኝተዋል፡፡
መልካም ውጤትና የእረፍት ጊዜ ለተማሪዎቻችን!
እንወዳችኋለን !
የትምህር ቤቱ ማህበረሰብ
ዛሬም ሰኔ 5/2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን የሚኒስትሪ ፈተናውን በሰአቱ በተረጋጋ ሁኔታ መጀመራቸውን ርዕሰ መምህሩ በመፈተኛ ጣቢያው እንደተለመደው በመገኘት አረጋግጠዋል የዛሬው ፈተና ከቀኑ 5፡00 ሰአት ላይ ይጠናቀቃል፡፡
መልካም ውጤት ለተማሪዎቻችን
ዛሬ ሰኔ 4/2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን የሚኒስትሪ ፈተናውን የጠዋት ፈረቃ በሰላም ተፈትነው አጠናቀዋል የከስዓቱ ፈተና 8፡00 ሰአት ስለሚጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
መልካም ውጤት ለተማሪዎቻችን
