cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

MENZUMA TUBE

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
187
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Ezu Al Hadra: Ezu Al Hadra: Ezu Al Hadra: ❤️❤️ተለቀቀ ተለቀቀ ❤️❤️shar shar Watch "አሕመድ የመዲናው || ኢዘዲን ኸድር (ቅመም) || AHMED YEMEDINAW || EZEDIN KHEDIR (Ezu ALHADRA) || Vol_4" on YouTube https://youtu.be/-W8CaKM3fJ4
إظهار الكل...
አሕመድ የመዲናው || ኢዘዲን ኸድር (ቅመም) || AHMED YEMEDINAW || EZEDIN KHEDIR (Ezu ALHADRA) || Vol_4

አሕመድ የመዲናው || ኢዘዲን ኸድር (ቅመም) || AHMED YEMEDINAW || EZEDIN KHEDIR (Ezu ALHADRA) || Vol_4_____________________አሁኑኑ ይቀላቀሉYoutube || Subscribe Now

https://www.you...

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወጣት ሙሀመድ አብዱሏህ (ያዘይነል ዓለሙ ) የተሠኘው ምርጥ የመንዙማ ክሊፕ ተለቀቀ ተለቀቀ ተለቀቀ!!! ''ያዘይነል ዓለሙ'' አዲስ መንዙማ 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/s-NMd15oiKg https://youtu.be/s-NMd15oiKg https://youtu.be/s-NMd15oiKg **
إظهار الكل...
ያዘይነል ዓለም || ሙሐመድ አብዱሏህ || አዲስ መንዙማ YAZEYNEL ALEM || @iNaya Records ዒናያ ሪከርድስ

ያዘይነል ዓለም || ሙሐመድ አብዱሏህ || አዲስ መንዙማ || YAZEYNEL ALEM _____________________አሁኑኑ ይቀላቀሉYoutube || Subscribe Now

https://www.youtube.com/iNayaRecordsTelegram

:iN...

#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ! እንኳን እናቴ ሞታ እንዲሁም አልቅስ አልቅስ ይለኛል እንደሚለው ተረት ሙሒቡ እንኳን ናፍቆቱ እንደዚህ ልብ በሚያሸብር ዜማ ተዚሞለት ወትሮም ቅኝቱ እህህ እህህ ነው! የኡስታዝ ኢድሪስ ነሽዳ ይጥመኝ ይጣፍጠኝ ነበር። ገና ዘንፋላዬን በሚያወድሰው በዚህ ሥራ ላይ ቀድሞ ሳገኘው ነበር ደስታዬ የጀመረው..! ያሰይዲ ያ ሙሐመድ፣ ያሰይዲ ያ ሙሐመድ፣ የፍጡር ምሳሌ ያ’ላህ ቢትወደድ፣ ሰላትና ሰላም ባንቱ ላይ ይውረድ። ይላል። ነጎድጓዳማው የሙአዝ ደምጽ ከተል ይልና አሰላምዓለይክ ያረሱለሏህ አሰላምዓለይክ የሙላው ጥላ አሰላምዓለይክ የኔ ዘንፋላ ሲል ልብ መናወጥ ይጀምራል። አጅሬ ፍቅር ሀለቱ ላይቻል ላይለመድ፣ ሲያጽፈኝ ያድራል ሌሊቱን እያስነከረ ከመድ፣ ወይ አልተቀምጥኩ አርፌ እግር ኖሮኝም አልሄድ፣ ነገር ዓለሙን ያስጠፋል እሩቅ ያለን ሰው መውደድ፣ አላስተረፈም ሲጋረፍ የናፍቆትሁ ነዲዱ፣ ቢለየው አይደል ገላዎ እንስቅስቅ ያለሎት ግንዱ። እያለ ሲቀጥል የደም ዝውውር እጅጉን የፈጠነ፣ ቆዳ የተለጠጠ ዓይነት ስሜት ይሰማል። የስማቸው ወራሽ ሙሐመዱልዓሚን የሚያምረው የሚያምረው እያለ እንጉርጉሮውን ሲጀምርማ ጸጉር ተነቅሎ ሊወድቅ እስኪመስል ይቆማል፣ በቆዳ ላይ እየተርመሰመሰ የሚቆነጥጥ ነፍሳት ያለ ይመስልም ይነዝራል፣ የሰውነት ከተማ በደስታ ጁንድ ይወረራል! የዘይኔ የፊት ፀዳሉ ይመሰክራል በቃሉ፣ ሂዳያን ለሚታደሉ ሙእጂዛ‘ኮነው ጀማሉ፣ በዩሱፍ በኩል ያለፉ ጣቶቻቸውን ሲከትፉ፣ የቁንጅናው ወጨፉ አላስችል ቢል ነበር ወስፉ፣ የነዛን ወይዛዝርት ኸበር ለአዒሸቱ ቢወራ፣ እንደዚህ በማለት ነበር ጀማሉን የምታብራራ። እያለ የትልቁን ሰው ውበት የማብራራቱን ስልጣን ለወጣቱ ማዲሕ ኢድሪስ ያስረክባል። ኢድሪስም ቀበል አድርጎ ከነብዩላህ ዳውድ ዓ.ሰ የወረሰው በሚመስለው ቃናው የእናታችንን ገለፃ ይቀጥላል። ያጀማል ያጀማል ያጀማሉል ዓለም፣ የኔን ባል ግንባር ቢያዩማ ወይዛዝርቱ በሞላ፣ ልባቸውን ነበር ሚቆርጡ በ‘ጃቸው በያዙት ቢላ፣ መች ሚታይ ሆኖ እንደ ቀላል ውበቱ ልብ ይገድላል፣ አንሰፈሰፈኝ ናፍቆቱ ሳላዬው በሩቁ ያን ጀማል። ዘይንዬ ናፍቆትሁ በ‘ኔ ካ‘ቅሜ በላይ በረታ፣ ከእህል ከውኃ አጣላኝ ከፌሽታ ከሳቅ ጨዋታ። መቼም ውዴታው ኸልቁን እህህ ማሰኘት ያውቅበታል እህህ ብሎ ይቀጥላል ፉዓድ በናፍቆት በተረታ፣ በሸውቅ በተዳበሰ ድምፀት! እህህ ወዳጄ እህህ ወዳጄ፣ በፍቅር መያዜ ይፋ እንዳይወጣብኝ ታምቆ፣ ተናገረብኝ እንባዬ ሚፈሰው ወዳጁን ናፍቆ፣ ቢጫወትም ቢዘነቅም፣ ልቡ በሀዘን ታርዞ በጥርሱ ዳኢም ቢስቅም፣ ፍቅር ኃይል አለው አንተዬ በዋዛ አይደበቅም። አጃቢዎቹ በለሆሳስ አሰላሙዓለይክ እያሉ ማዲሖቹም በዬተራ በዬመሃሉ አሰላሙዓለይኩም አሕመድ ያሐቢቢ፣ አሰላሙዓለይኩም ያሚስኪ ወጢቢ፣ አሰላሙዓለይኩም ጦሓ ያጦቢቢ ሲሉ የሰማ ናፍቆት ልቡን ቢረግጠውም ለአፍታ ረውዷው ላይ የደረሰ፣ ከሐውዱም የቀመሰ ይመስለዋል፤ ሙሒቡ የውዴታ እንባውም ሰርግና ምላሹ፣ ሕመሙም ፈውሱ ነውና! #ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ! አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ዓላ ሰይዱና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊ ሰይዲና ሙሐመድ!💚💚💚
إظهار الكل...
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ! ያሐቢበሏህ! መውላና ጀላሉዲን ሩሚ (ቀ.ሲ) ‘you are not a drop in the ocean, you are the entire ocean in a drop.’ ይሉት ላንቱ ይመስለኛል! ሠይዲ! አንቱ በውቅያኖስ ውስጥ ያሉ ጠብታ አይደሉም በትንሿ ጠብታ ውስጥ የተገኙ ጥልቅና ሰፊ ባሕርም ኃይቅም ውቅያኖስም እንጂ!! ማዲሑ "ላንቱ‘ኮ ሲባል ነው ከውኑ መኸለቁ!" እንዳሉት ፍጥረተ ዓለሙ ሊያገለግልዎ የተፈጠረ አንድ ጠብታ ነው። ምድር ሰማዩ፣ ተራራው ዛፉ፣ ሸለቆው ጋራው ሁሉ ጠባብና ኢምንት ነው፤ ጭለማ የወረሰው አስፈሪ ነው፤ አውሬ የበዛበት ዱር ነው። አንቱ ታላቁ የእዝነት ምንጭ በፍቅር ስትንቆረቆሩበት ነው ጨለማው የበራው፣ ደረቁ የረጠበው፣ ከባዱ የገራው፣ ትንሹ ያደገው አንቱን ትልቁን ሰው ሲያገኝ!!! ሸፊዒ! ሙሒብ ተቸገረ ጨነቀው ብልሃቱ! መቼም የትልቅን ሰው ቀድር የሚያውቀው ያው ትልቁ ነውና ታላላቅ የወዳጆችዎ አገር ሰዎች አይረቤነታችንን አይተው፣ ከንቱነታችንን ሸሽተውና አንቱን ናፍቀው ወ‘ዳንቱ መጉረፍ ቢጀምሩ ያኔ ባልደረቦችዎ ስትለዯቸው የደረሰባቸው መከራ ያገኘን መሰለን፣ እናቱን እንዳጣ ህፃን፣ ያ‘ባቱ እጅ እንዳመለጠው ብላቴና ፈራን፣ አነባን፣ ጨነቀን፥ አንቱንም ያወቅነው የወደድነው በነሱ ነውና!አውቀንኋል እንደምንለው አውቃችኋለሁ በሉን፣ አውቀናቸዋል እንደምንል ሳዳቶቹም ይወቁን! የኔ ባሕር! መቼስ "በሕሩ መደዲሂ ለይሰ ለሁ ሐድዱን!" አይደል? አዎን የመውደድ ድንበሩ ዳር የሌለው ነው፤ ባሕሩ ሰፊና፣ መርከቡም ዘዋሪ አያጣምና ዛሬም ሶለሏህ በተባለበት ሁሉ አንጠፋም! ስምኩን በበጎ ካነሳ ጋር ሁሉ መወዳጀቱን እናውቅበታለን፤ የስምኩን ፋኖስ እያበራን የማቁን ዳገት ማለፉን ለምደነዋል የቁስላችን መሻሪያ፣ የልባችን ሽንቁር ስፌት!!ደግሞስ ወዳጅ ከወዳጁ መች ይርቅና!? ላደለው በጀሰድ ዝቅ ሲል በሩኅ ካልሆነም በመናም!! የኔ ደዋዕ የኔ ሺፋዕ! #ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ! አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዱና ሙሐመድ ወዓላ አሊ ሐቢቡና ሙሐመድ!💚💚💚 @bilalbinrebah @bilalbinrebah @bilalbinrebah @bilalbinrebah
إظهار الكل...
ኢናሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጅኡን 😢😢 የገታ ሀሪማ ኸሊፋ የሆኑት ሸይኽ ሙሒዲን አርፈዋል አሏህ ይዘንላቸዉ😭😭 ፋቲሀ በሉላቸዉ ያአሏህ ያአሏህ ያአሏህ ከአዱኒያ ላይ ትልቅ ሰወች ሲጠፉ ፊቲናዉ ሲስፋፋ አይ የኛ ነገር ትልቅ ሰወችን ማጣት ዱኒያ እየከበደች መሆኑን ያሳያል😢😢
إظهار الكل...
# ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ ! ሠርክ አዲስ ድንቅ ነሽ ለ‘ኔ አለ እያደር መወደዷ ቢገርመው! የሰይዲ ነገር‘ኮ ሁሌ አዲስ፣ ሙሐባቸው እያደረ የሚጀደድ፣ እዬቆዬ የሚጣፍጥ፣ በጠለቁበት ቁጥር እየተደነቁ የሚሰጥሙበት ነው!! ያረሱለሏሂ ያሚፍታሁ ዱንያ ወልአኸራ! ወዳጅሁ የልቡ ቋጠሮ እንዲፈታለት፣ ከእስሩ እንዲላቀቅ፣ ጨለማው እንዲበራለት፣ የሁለት ዓለም ሰዓዳ፣ የሁለት አገር ንግስናና ክብረት እንዲያገኝ የኔማ ክብረቴ ፊትዎን ማዬቴ እያለ አሸንቁሮ ይፈልግኋል! ደስታዬ ሙስጠፋ ዘይኔ፣ ያየሁኝ ‘ለት ዐይንሁን ባይኔ ነው እኔ የምሻው መኽተም፣ የሚያምረውን ፊቱን ባዬሁት፣ ብዬ ነበር የተመኘሁት፣ አይተነው ብንሞት ግዴለም። እያለ ኑረት፣ ትድረት ማለት አንቱ እንደሆንኩ ከዛ ተቀድሞም አልፎም ያለው ሐያት ምንም እንደሆነ ይገልፃል! መላሽ ያርገኝ ላላህ ገለታ፣ ጀማልሁን ያዬሁኝ ለታ፣ ለጌታ ገሩ ነው መቸም። ይልናም ጌትዬው የተኳለ፣ የተዘዬነ፣ ፀሃይና ጨረቃን የሚያስንቀውን ፊትዎን ያሳዬው ‘ለት ሰርግና ምላሹ እንደሆነ አውቆት ለገለታ ለምስጋና ይቸኩላል መቼም ለርሱ ሁሉ ገር ነውና!! አርሒቡ ነቢ ሐድሩልኝ፣ ብዙ እማዋይሁ ጉዳይ አለኝ። እንዳሉት ጥሪው ሸርጥም ባይሞላ፣ ስንጠራችሁ አትቅሩ። አድለን እንዳደልካቸው፣ መክነን እንደመከንካቸው። ተምኪን ተምኪን!! እንኳን ዛታቸው ታይቶ ስማቸው ተሰምቶ ያሽራል፣ እንኳን በእውን ታይተው የመናም አብሮነታቸው ከአዛ ያላቅቃል፣ መሸቅቃ ያረግፋል፣ በስማቸው፣ በራቀው የመኸለቅ ሚስጥራቸው፣ በሙዕጅዛ ተዓምራቶቻቸው፣ እሳቸው ለወዳጆቻቸው፣ ጌትዬውና ሙሒቦቻቸው ለእርሳቸው ባላቸው ፍቅር ከሚሰማው ከሚወራው ከሚፈራው ሁሉ ነጃ ይበለን፣ አገሩ ሰላም ቀዬው አማን ይሁን የመዲናን እርጋታ ለሚወዷት ለምንወዳት አገራችንም ያድልልን! # ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ ! አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም! @bilalbinrebah @bilalbinrebah
إظهار الكل...
የኢስራእና የሚዕራጅ ለይል!! ✦✦✦ ይሄ ለይል የተባረከ የዱዓ ለይል ነው። ✦✦✦ መቼስ ከቀን እና ከለይል የትኛው ይበልጣል የሚል አይጠፋም።አላህን ሳታምፅ ያሳለፍከው ቀንም ይሁን ለይል ከሁሉም የተሻለ ቢሆንም ደጋጎቹ ግን ከቀን ይልቅ ለይሉን ያስበልጣሉ።በአፈጣጠርም ቢሆን ከቀን ቀድሞ የተኸለቀው ለይሉ ነው።ቀን ላይ የማናገኛት የስቲጀባ ሰአት ሁሌም የሌሊቱ አንድ ሶስተኛ ሲቀረው እናገኛታለን። ✦✦✦ "የንዚሉ ረቡና" የሚለው ሐዲሰ በቀጥታ ከለይሉ ጋር ነው ቁርኝቱ።የንዚሉ ሲል ሙዷፉ ሐዝፍ ሆኖ እንጂ "የንዚሉ መለኩ ረቢና"ለማለት ነው።ይህንንም ታላቁ ሙፈሲር አል ኢማሙል ቁርጡቢይ ተፍሲራቸው ላይ በግልፅ አስቀምጠዋል። ሙዷፍ፣ ሙዷፍ ኢለይሂ እና ሓዝፍ የሚሏቸው ቃላት የነሕው ጉዳዮች ናቸው። ✦✦✦ ታላቁ ሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር አል ዓስቀላኒይ ቡኻሪን ከሚተነትኑበት ፈትሑል ባሪ ላይ "የንዚሉ"ከሚለው ቃል ያለቸው "የ" "ዩ" ተብላ መነበብ እንዳለባት ኢብኑ ፉረክን ጠቅሰው ዘግበዋል።ማለትም የንዚሉ ሳይሆን "ዩንዚሉ"። የንዚሉ ማለት "ይወርዳል" ሲሆን "ዩንዚሉ" ከሆነ ደግሞ ያወርዳል ማለት ነው።ይወርዳል ሲል የተፈለገበት መላኢካ በአላህ ትእዛዝ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል ማለት ሲሆን "ያወርዳል" ከሆነ ደግሞ አላህ መላኢካውን ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ያወርዳል ማለት ነው። የአሏህ መላኢካ የሌሊቱ አንድ ሶስተኛ ሲቀረው ወደ አንደኛው ሰማይ ይወርድና "ሃል ሚን ዳዒን ፈዩስተጃበ ለህ፣ሃል ሚን ሙስተጝፊሪን ፈዩጝፈረ ለህ፣ሃል ሚን ሳኢሊን ፈዩዕጧ....." እያለ እንዲለፍፍ ጀሊሉ ያዘዋል። "ማን ነው የሚለምን ልመናው የሚሰማለት፣ማነው ምህረትን ጠይቆ ምህረትን የሚያገኝ፣ ማነው የሚጠይቅና የሚሰጠው ...." እንደማለት ነው። ወዳጄ! በደንብ የሚገባህ ነሕውን በደንብ ስትቀራው ነውና አትቦዝን። ✦✦✦ እናማ "ያገኘም አገኘ ያጣም ያን ቀን አጣው" እንዳሉት የዘቡራ ልጅ ሰይድ ጫሊ በለይሉ ተነስቶ እጁን አሏህን ለመለመን የዘረጋ በብዙ ማትረፉ አይቀሬ ሲሆን እንዲሁ ተኝቶ ያሳለፈው ደግሞ ይቀርበታል።በለይሉ ጀሊሉን መለመን ብዙ ትርፍ አለውና።እንዴታ! ለይሉኮ የጀግኖች ሜዳ ነው። የሰው ልጅ ቀን ሲባዝን ውሎ ለሊቱን በእረፍት ሊያሳልፍ ጋደም ሲል እንደርሱ ሲባዝኑ የዋሉ ግን ደግሞ የለይሉን ምስጢር የተገነዘቡ ድንቅ የአሏህ ባሮች ገላቸውን ከምንጣፉ አርቀው ሰርክ ዒባዳ ሲያደርጉ ያነጋሉ። ✦✦✦ ወዳጄ! ይሄ ለይሉ የሚሉት ሌላ ተአምርንም አስተናግዷል። ለሰማይ ለመሬት የከበደ "ኢስራእና ሚዕራጅ" የሚሉትን አጃኢበኛ ትእይንት ተንፀባርቆበት አልፏል።ክስተቱ ለኛ ነብይ ብቻ የተሰጠ የልህቀት ማሳያ ምልክት ነው። መገን ለይሉ! ✦✦✦ የክስተቱ መንስኤ የነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ሃዘን ነው።መቼስ ነብዩ እንደኛው ሁሉ የሰው ልጅ ናቸውና በወቅቱ ከመከራ ላይ መከራ ተጨማምሮባቸው በጭንቀት ተከበው ነበር። ﺃﺷﺪ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺑﻼﺀ ﺍﻷﻧﺒﻴﺎﺀ ﺛﻢ ﺍﻷﻣﺜﻞ ﻓﺎﻷﻣﺜﻞ . እንዳለው ሐዲሱ ።ከሰዎች ከባድ በላእ የሚደርስባቸው ቀዳሚዎቹ ነብያቶች ናቸው።አንዳንዱ የኔ ብጤ ትንሽ ነገር ስትነካው እየየውን ያቀልጠዋል።በላኡንም የመጠላት ምልክት አድርጎ ያስበዋል።ነገሩ ግን በተቃራኒው ነው። ✦✦✦ የኛ ነብይ የመከራ ዶፍ ላያቸው ላይ እንደ መብረቅ እያጓራ በነበረበት በዚያ ጭንቅ ሰአት ይባስ ብሎ የቅርብ ደጋፊ የነበሩ በጣም ወሳኝ ሰዎቻቸውን በሞት ተነጠቁ።አቡ ጧሊብን እና እመት ኺዲጃህን[ረዲየሏሁ ዓንሃ] የኛ ነብይ ይሻል እንደሁ ብለው ወደ ጧኢፍ ቢያቀኑም ጭራሽ የወቅቱ የጧኢፍ ሰዎች "ውሻ በቤቱ ይኮራል" እንዲሉ ለአለማት እዝነት የተላኩትን ያን ሰላማዊ ነብይ ከሃገራችን ውጣልን ብለው ድንጋይ ውርውሮሽ ጀመሩ። አሁን በኛ ዘመንም "አንተ የኛ ዘር አይደለህምና ሃገራችንን ለቀህ ውጣ" የሚሉ መንጋዎችን ሳይ በጧኢፍ የነበሩትን ያስታውሱኛል።ጥሎት ለሚሄደው፣ለዛውም ንብረቱ ላልሆነው የአላህ መሬት "ውጣልኝ" ማለቱ መሃይምነት እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?! ✦✦✦ ሐቢባችን በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ሆነው አንድም የማማረር ቃል አላወጡም።ምንም እንኳ በበላእ ባህር ቢዋጡም "የጧኢፍ ህዝቦችን ጠራርገህ አጥፋልኝ" ብለው ግን ዱዓ አላደረጉም።የአለማት እዝነት ተደርገው ተልከዋልና። ጀሊሉ! "ጭንቅን ደስታ ይተካዋል፣ ከመካራ በኋላ ተድላ ይመጣል" እንዳለው ያን ሁሉ ጭንቀት የሚያስረሳ ነገር በዚህች አሁን እኔና አንተ በምናወጋባት ለይል ተመሳሳይ ሰይዱና ጅብሪል ከሰማየ ሰማያት ተልኮ ወደ ምድር ነብዩን ፍለጋ ወረደ።ነብዩ ያኔ በጃዕፈርና በሐምዛ መሃል ተኝተው ነበር።ጅብሪል በጣሪያው በኩል ነበር የገባው።ጅብሪል ጠጋ ሲሉ ጣሪያው በአሏህ ቁድራ ጋ ብሎ ተከፈተ።ጀብሪል ገቡና ነብዩን ይዘው ወጡ። ✦✦✦ በዚያ ውድቅት ለሊት ጀብሪል ነብዩን ከቤት ካስወጣቸው በኋላ ካዕባ ወስዶ ደረታቸውን ሰነጠቀውና በረቀቀ ዘዴ ልባቸውን አውጥቶ በዘምዘም ውኃ አጠበው።ከዚያም "ሒክመተን ወኢማና"የሚባሉ እጅግ ውድ ነገሮች ልባቸው ውስጥ አንዠቀዠቀውና ሞላው።ዑለማኦች ይሔን ነገር ሲተነትኑ ለአስገራሚው ጉዞ ቅድመ ዝግጅት ነው ይላሉ። የትኛውም ነብይ ያልሄደውን አለም ሊጎበኙ ስለሆነ ያንን የሚቋቋም የማይነጥፍ አቅም ያስፈልጋቸው ነበር። ከዚያማ በኋላ .... ለጉዞው ማሳለጫ ይሆን ዘንድ ሰማየ ሰማያትን አቋርጦ የመጣው የተሽቆጠቆጠው ቡራቅ ቀረበ።ውጣበት አላቸው ጀብሪል ለነብዩ .... ነብዩ ቡራቁ ላይ ሊወጡ ሲሞክሩ ቡራቅ ደስታው አስክሮት መቅበጥበጥ አበዛ። ጅብሪል እንዲረጋጋ ነካ አደረጉት ቀጥ አለ።መገን ጅብሪል ባለ ስድስት መቶው አክናፍ! አንዱን ክንፍ ሲዘረጉት ማበይነሰማኢ ወል አርድ ከፀሃይ መውጫ እስከ መግቢያው እፍፍፍን አድርጎት ይሞላል።አጃኢብ ነውኮ። በዚህች ለይል የኛ ነብይ ጅብሪልን በትክክለኛ አፈጣጠሩ አዩት።ባለ ስድስት መቶ ክንፉ አስገራሚ ፍጥረት ሰይዱና ጅብሪል በዚያ አፈጣጠር ማየት አስቡት .... በነገራችን ላይ ነብዩ ጅብሪልን በትክክለኛው አፈጣጠር ያዩት ሁለት ጊዜ ሲሆን በመጀመሪያው ራሳቸውን ስተው ወድቀዋል።በሁለተኛው ግን የተገጠመላቸው ልዩ አቅም ስለነበር አልወደቁም።ተቋቋሙት። ✦✦✦ በጅብሪል የተነካው ቡራቅ መቅጥበጡን አቆመ።ነብዩ ቡራቁ ላይ ወጡ።ጉደኛው ቡራቅ አይኑ ያየበት ድረስ እንዲወነጨፍ ተደርጎ የተሰራ ተአምረኛ ሰንጋ ነው።አሁን ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው። እናም ጉዞው ለይሉ ላይ ጀመረ... ለይሉ!!! እንኳን አደረሳችሁ!
إظهار الكل...
#ሱረቱል_ኻህፍ #መልካም_ጁምዐ!😇 @bilalbinrebah
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.