cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

مشاركات الإعلانات
767
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

እውን እመቤታችን ከኢየሱስ ውጪ ሌላ ልጅ አላትን? ግልጽ መልስ። " ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?"(ማቴ13:55) ቅዱስ ስምዖን ( የጌታችን ወንድም ) የቅዱስ ዮሴፍ ወንድም የቀለዮጳ ልጅ ሲሆን እናቱ ደግሞ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እህት የምትባላዋ የቀለዮጳ ሚስት ማርያም ናት። የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሃፊ አውሳብዮስ እንደተናገረው ቅዱስ ስምዖን #የተወለደው ከጌታችን መወለድ 13 ዓመት አስቀድሞ ነው። ይህም ማለት ጌታችን ማስተማር በጀመረበት ዓመት የ43 ዓመት ጎልማሳ ነበር ማለት ነው። ቅዱስ ያዕቆብ ( የጌታችን ወንድም ) ይህም ሰው የቅዱስ ስምዖን ታናሽ ሲሆን የተወለደውም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1BC ነው። ይህም ማለት ከክርስቶስ ልደት( ውልደት) በፊት ባሉት በመጨረሻዎቹ መቶ አመታት ውስጥ ነው። 1 ክፍለ ዘመን መቶ አመት ነውና። እንዲገባን ይህን ተመልከቱ 👉....., 9BC, 8BC, 7BC, 6BC, 5BC, 4BC, 3BC, 2BC, 1BC, 1AD, 2AD, 3AD,...2009, 2010,2011,2012.... BC ማለት ዓመተ ዓለም - AD ማለት የጌታ አመት ዓመተ ምህረት ማለት ነው። #ማስታወሻ ዮሳና ይሁዳም የትውልድ ዘመነኛቸው ከጌታችን ልደት በፊት ነው። ይህም የሚያሳየው ጌታችን በእድሜ ከ4ቱም የሚያንስ መሆኑን ነው። አብሯቸው ስላደገና የእናቱ እህት የምትባል ለማርያም ልጆችም ስለሆኑ በዝምድና ወንድሞቹ ተባሉ። አንባቢያን ሆይ : እንግዲህ ይሁዳ ስምዖን ዮሳና ያዕቆብ በእድሜ ከጌታችን ከበለጡ በምንም መልኩ የእመቤታችን የስጋ ልጆች ሊሆኑ አይችሉም። እመቤታችን የመጀመሪያና የመጨረሻ የበኩር ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ኢየሱስንም ከመውለዷም ከወለደችም በኃላ በድንግልናና በንጽሕና ጸንታ የኖረች ሰው ናት። ወንድሞች የተባሉት በትክክል ወንድሞች ከሆኑ ታናናሽ ወንድሞች ናቸው ማለት ነው ፡፡ እነዚህ ታናናሽ ወንድሞች ጌታን በአደባባይ ገስጸዋል፣ መክረዋል። /ዮሐ. 7፡2-5/ ፡፡ በአይሁድ ባህል ታናናሾች ታላቅ ወንድማቸውን በአደባባይ አይገስጹም ፣ አይመክሩም ፡፡ ወንድሞች መባላቸው ታናናሾች አለመሆናቸውን የሚያሳይ ነው ፡፡ ስለዚህ የድንግል ማርያም ልጆች አይደሉም ፡፡
إظهار الكل...
አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፡፡ እንዲል ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ስቅለቱን በዲሜጥሮስ ቀመር አውጥተን የጌታን መከራውን አስበን በስግደት ህማማቱን እናስባለን በዝክረ ጥንተ ስቅለቱ በጥቅምት ፳፯ ደግሞ በመስቀል የተደረገልንን አስበን እናመሰግነዋለን፡፡ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ ጋር ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መ.ክ.ዘ የነበሩትን አቡነ መብዓ ጽዮንን ታስባለች፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮንን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ በዕለተ ዓርብ የተቀበልከውን መከራ ግለጽልኝ ››ብለው በጸለዩ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተቀበላቸውን መከራዎች ሁሉ አሳያቸው፡፡ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስን መከራ ካዩበት ቀን ጀምሮ ሕማሙን መከራውን ግርፋቱን እስራቱንበጠቅላላ አስራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በማሰብ ጀርባቸውን በአለንጋ ይገርፉ ፤ ራሳቸውን በዘንግ ይመቱ ነበር፡፡ የጌታችንን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ዘወትር ስለሚያለቅሱ ዐይናቸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ነገር ግን እመቤታችንቅድስት ድንግል ማርያም የብርሃን ጽዋ ይዛ መጥታ ዐይናቸውን ቀብታ አድናቸዋለች፡፡ በዚህ የተነሳ ‹‹በትረ ማርያም›› እየተባሉ እንደሚጠሩ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ በዚህ መሰረት ጥቅምት ፳፯ ቀን ለአቡነ መብዓ ጽዮን ቃልኪዳን የገባበት ቀን በመሆኑ በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱ ጋር ይከበራል፡፡ የጻድቁ አቡነ መብዓ ጽዮን በረከትና ረድኤት ይደርብን፡፡
إظهار الكل...
👍 1
ጥቅምት ፳፯ "ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ" ⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜⚜ ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም (ጅማ፤ ኢትዮጵያ) @የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን!! በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን! ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መመስከር እንዲገባ “ ከመዝ ነአምን ዘአልቦቱ እም በሰማያት፤ ወአብ በዲበ ምድር ” በሰማይ ያለእናት ከአብ መወለዱን፣ በምድርም ያለ አባት ከድንግል ማርያም መወለዱን እናምናለን። ይህንንም አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት፣ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል ፤ ድኀረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት፣ መለወጥ ሳያገኛት ዘር ምክንያት ሳይሆን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደ፤ ወልደ እግዚአብሔር በመለኮቱ ወልደ ማርያም በትስብእቱ ብለው አምልተው እንዲያስተምሩን “ከመ አሐዱ ውእቱ ባሕቲቱ ውእቱ አምላክ ወሰብእ ኅቡረ” ትርጉሙም እርሱ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮስ ፴፭፥፳፩ መጋቢት ፳፯ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሠቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን አርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርአት ሠርተዋል፡፡መጋቢት ፳፯ ቀን በዓቢይ ጾም ስለሚውል በዓቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርታለች ። ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተክርስቲያናችን ጌታችን በመስቀሉ ስለፈጸመልን የማዳን ስራ “ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” ። በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው እያለች እየዘመረች ታስበዋለች። ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯ በወርኀ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ “ …እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋህድ ዘምስለ ምህረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች ። “እስመ አንተ ትክል አንጽሖትየ እግዚኦ ወበቃልከ እለ ለምፅ አንጻሕከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጐከ ወበመስቀልከ ለጻድቃን አብራህከ ” ልታነጻኝ ይቻልሃል አቤቱ ለምጻሞቹን በቃልህ እንጽተሃልና እያሉ አባቶቻችን በመስቀሉ ለጻድቃን ማብራቱን እያሰቡ በዓሉን በመዝሙር በደስታ ያከብሩታል “ወበከመ ሙሴ ሰቀሎ ለአርዌ ምድር በገዳም ከማሁ ሀለዎ ለወልደ ዕጓለ እመሕያው ይሰቀል” ዮሐ ፫፥፲፬ ሙሴ እባብ በምድረ በዳ እንደሰቀለ የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው ብሎ እንደተናገረ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ነው ። ክርስቶስ ስለስቅለቱ ሲናገር ምሳሌ የሚሆነውን፣ ሙሴ በምድረ ባዳ የሰቀለውን፣ የነሐሱን እባብ “ሙሴ እባብ በምድረ በዳ እንደሰቀለ የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው” ብሎ ምሳሌውን ተናግሯል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ከጭንጫ ውሀ አፍልቆ ቢመግባቸው ከዚህ ምድሩ ብቅ፣ሰማዩ ዝቅ ቢልለት፣ ከደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበጀ፣ ውሀውን እያረጋ፣ መና መገብኳችሁ ይላል እንጅ ይክልኑ እግዚአብሔር ሠሪዓ ማዕድ በገዳም። ቆላ በሆነማ ባልተቻለውም ነበር ብለዋል ።ጌታም ሊያስተምራቸው ፣ የርሱን ከሃሊነት ሊያሳያቸው፣ የእነርሱንም ሀሰት ሊገልጥባቸው ፣ ሙሴን ነቅዓ ማይ የሌለበት በርሐ ይዘሀቸው ውረድ ብሎት ቢሄዱ መናው ወርዶላቸዋል፣ ውሀውም ፈልቆላቸዋል ።ነገር ግን ነዘር የሚባል እባብ እየነከሰ ይፈጃቸው ጀመር።ከዚህ በኋላ እስራኤል ሙሴ ዘንድ ሂደው ከጌታ ምህረት ቸርነት ከሰው ስሕተት ኃጢአት አይታጣም በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ተናግረን በድለናል እባቦችን ከኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን አማልደን አሉት።ሙሴም ስለሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ ጽሩዩን ብርት አርዌ አስመስለህ ሠርተህ ከሚገናኙበት አደባባይ ከእንጨት ላይ ስቀልላቸው አለው። ሙሴም እባብን ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። (ኦሪ ዘኁ ፳፩ ፥፩፡፱) ይህንም ምሳሌ አባቶቻችን በትርጓሜ ወንጌል ቅዱስ እንዳስቀመጡልን አርዌ ምድር የዲያብሎስ፤አርዌ ብርት የጌታ ምሳሌ ነው ። በአርዌ ምድር(እባብ) መርዝ እንዳለበት በዲያብሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት።በአርዌ ብርት መርዝ እንደሌለበት በጌታም ፍዳ ኃጢአት የለበትም ።አርዌ ብርት በአርዌ ምድር አምሳል መሰቀሉ ጌታ በአምሳለ እኩያን እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ ለመሰቀሉ ምሳሌ ነው። ዳግመኛም “ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን” ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና ኢሳ ፶፫፥፲፪ የሚለውን ትንቢት ፈጽሟል። ምሳሌውን አውቆ አስመስሏል ትንቢቱንም አውቆ አናግሯል ። ጲላጦስ አይሁድን ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ ቢላቸው በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው አሉ ።ጲላጦስም በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው። ማቴ ፳፯ ፥፳፭ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ “ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢያትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት” ፡፡ እንዲል ክርስቶስን አይሁድ ስቀለው ብለው ፈረዱበት አክሊልን የሚያቀናጀውን የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን አነገስንህ ብለውታልና ጭፍሮች በፍና ተሣልቆ የእሾህ አክሊል ታተው ደፉለት “ወጸፈሩ ሐራ አክሊለ ዘሦክ ወአስተቀጸልዎ ዲበ ርእሱ” ዮሐ ፲፱፥፪ ። ኢየሱስ ክርስቶስ የእሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ዕፀ በለስን በልቶ “ምድር እሾኽንና አሜከላን ታበቅልብኻለች” ዘፍ ፫፥፲፰ ብሎ የፈረደበትን አዳም ስለርሱ ክሶ መርገሙን ደምስሶለታል ። መጋቢት ፳፯ ቀን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯ )፡፡ ኦ አእዳው እለ ለሐኳሁ ለአዳም ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል ፤ ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል
إظهار الكل...
ከዘረኝነት አስተሳሰብ ነጻ ሳንወጣ እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሊሰማ አይችልም። ክርስቶስ ዘርን፤ መልክን ለይቶ አልሞተልንም። ክርስቲያን ነኝ የምንል ክርስቶስን እንምሰለው። ክርስቶስ ፍቅር ነው። እንዋደድ። (1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕ. 2) ---------- 8፤ ዳግመኛ አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም ነገር በእርሱ በእናንተም እውነተኛ ነው፤ ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን ይበራል። 9፤ በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ። 10፤ ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤ 11፤ ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና። እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ሰላም ያድርግልን።
إظهار الكل...
2👍 1
ሶስቱ እግዚአብሔር ጸሎትን በቶሎ የሚሰማበት መንገዶች። 1. ስግደት ሰግደህ ላብህ በፈሰሰበት ቦታ ( መስገጃው ) ላይ መተኛት - ያኔ እግዚአብሔር በህልም ወይም በራእይ የምትፈልገውን ነገር ያሳይካል።  2. ጸሎት ጸልየህ አልቅሰህ እንባህ በፈሰሰበት ቦታ ላይ መተኛት - ያኔ እግዚአብሔር በህልም ወይም በራእይ የምትፈልገውን ነገር ያሳይካል።  3. የተመረጡና ቅዱስ ተብረው ከሚጠሩ እጽዋቶች አንለ የወይራ እንጨት ነው። የእሱን እንጨት ቆርጠህ በፊትህ አስቀምጠህ ጸሎት መጸለይ ለ3 ቀን ወይም ለ1ቀን ስትጨርስ እንጨቱን ማቃጠል አመዱንም በአልጋህ ላይ መበተን በዛም አልጋ ላይ መተኛት - ያኔ እግዚአብሔር በህልም ወይም በራእይ የምትፈልገውን ነገር ያሳይካል።  @WwEotc
إظهار الكل...
የእናታችን ሐና በረከትና ምልጃ አይለየን።
إظهار الكل...
+ #እይታዬ - ፫ + ብዙ ጊዜ ሰዎች እኛ ኦርቶዶክሳውያንን '' እናንተኮ ለስዕል የምትሰግዱ ስዕል አምላኪዎች ናቹሁ '' ይሉናል። ግን እውነት ነው? አይደለም። እኛ ለስዕሉ ማለትም ስለዕሉ ለተሳለበት ቀለም፣ ስዕሉ ላረፈበት አቡጀዴ( ሸራ)ና ለፍሬሙ አንሰግድም። ግን በስዕሉ በኩል ለስዕሉ ባለቤቱ እንሰግዳለን። ይህም ስግደት የአምልኮ ወይም የጸጋ (የክብር) ተብሎ ይከፈላል። የአምልኮው ስግደት ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ የሚቀርብ ነው። የጸጋ ስግደት ደግሞ ለቅዱሳን መላእክትና ሰዎች የሚቀርብ ነው። ቅዱሳን ስዕላት ከሌሎች ስዕላት የሚለዩት ቅዱስ በሚለው ስማቸው፤ በመንፈሳዊ አገልግሎታቸና ፈውስን በመስጠታቸው ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ በቁስ ላይ አድሮ ተኣምር እንደሚሰራ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ እውነት ነው። ለምሳሌ ጌታችን በልብሱ እንዱሁም ቅዱስ ጳውሎስም በልብሱ በሽተኛዎችን እንደፈወሱ ስንመለከት የእግዚአብሔር መንፈስ በቁስ ላይ እያደረ ተአምራትን እንደሚሰራ እንገነዘባለን። በቁስ ደረጃ ደግሞ ስዕልም ጨርቅም አንድ ናቸው ፤ የተሰሩበት ግብአት ቢለያይም። ስለዚህ የእግዚአብሔር መንፈስ በስዕል ላይ አድሮ ተአምር አይሰራም ማለት ስህተት ነው። ለመሆኑ በስዕል የተፈወሰ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት እንችላለን? አዎ እይታችንን ካስተካከልን እንችላለን። ለምሳሌ እንዲህ የሚል ቃል አለ :-: " ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ #ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን #ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር። ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።" (ሐዋ 5:15-16) ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው በሽተኛ ይፈውስ ነበረ። ጥላ ምንድነው? ጥላ በመሰናክል አካል ምክንያት ብርሀን የማያገኝ ቦታ ነው። ይህ ቦታ ብርሀን አስተላላፊ ካልሆነ አካል በስተጀርባ ይገኛል። #ይህ_ጥላ_የሚፈጥረው_ቅርፅ_ብርሀን_እንዳያልፍ_ያደረገውን_አካል_ግልብጥ_ምስል_ነው ። ማለትም ራስኑን ቅርጽ በጥቁር ቀለም መልክ ማለት ነው። ጥላን ወደ ስነ-ጥበብ ስንመጣው ደግሞ Shadow Art በሚባል የአሳሳል ጥበብ እናኘዋለን። ጥቁር ቀለምን ብቻ በመጠቀም አንድን አካል አስመስሎ የመሳል ጥበብ ነው። የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ ልክ እንደ Shadow art ነው በተፈጥሮ ብርሃን በምደር ላይ የተሳለ ፥ ይህንን ጥቁር ጥላ ከነቅርጹ በደንብ ሙያ ተጨምሮበት በቀለም አሳምሮ በመሳል የባለቤቱን ገጽታ ማምጣት ይቻላል። በመሬት ላይ ያረፈው ጥላ መፈወሱ ፤ በክብር በሸራና በተለያዩ አካላት ላይ ምሥጢርን፥ ሥርአትን ጠብቀው የተሳሉ ስዕላት እንደሚፈውሱ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ነው። ይቆየን።
إظهار الكل...
🔷 ከተወደደችው እመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ነው። ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ሲያበስራት ከእርሷ የሚወለደው እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ነግሯታል። የእግዚአብሔር ልጅ ምን ማለት ነው ካላችሁ የሰው ልጅ ሰው እንደሚባል የእግዚአብሔር ልጅም እግዚአብሔር ይባላል " መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት... ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።" (ሉቃ 1:35)። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስም ስለ ሚወለደው ቅዱስ ሕጻን ድንቅ በሆነ ምሥጢር አሰምቶ ተናገረ " ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" (ኢሳ 9:6) 💠 ከእመቤታችን የሚወለደው 💟 አለቅነት በጫንቃው የሆነ 💟 ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሆነ 💟 የሰላም አለቃ የሆነ ነው። 🔷 በግልጥ ከዚህ የምንረዳው ከእመቤታችን የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን ነው። ቅዱስ ኢሳይያስ ከእመቤታችን የሚወለደው ሕጻን እግዚአብሔር እንደሆነ ሲነግረን አማኑኤል ብሎ ከሩቁ ጠራው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። ከእመቤታችን የተወለደው ከእርሷ ጋር የተሰደደው፣ የተሰበከው፣ ከሐዋርያት ጋር ዞሮ ስብከቱን ያቀናው፣ የሞው የተነሳው የተሰቀለው፣ ወደ ሰማይ ያረገው ተመልሶም የሚመጣው እርሱ ከእኛ ጋር የሆነው እግዚአብሔር/አማኑኤል ነው " እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።" (ማቴ 1:23) ፍቅሩ ይደርብን።
إظهار الكل...
👍 1
[ ትምህርተ ተዋህዶ!] • ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው፡፡ በመለኮቱ የእግዚአብሔር ልጅ ፥ በስጋ የማርያም ልጅ እንደ ሆነ እናምናለን፡፡ ሰው ባልሆነ አካል የሰውነትን ስራ አይሰራም ሥጋን ከርሷ ከእመቤታችን የነሳ፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ሞት የሚሥማማት ስለሆነች ሞት የሚሥማማውን ሥጋ ተዋህዶአልና፡፡ ስለዚህም የተቀበለው ልቅሶ ፣ ሕማም ፣ ሞት ከድንግል የነሣው የሥጋ ገንዘብ ነው፡፡ አዘነ አለቀሠ ሲል ብትሠማ ያዘነ ያለቀሠ አምላክ ቃል እንደሆነ አታሥብ ይህ ሁሉ ሥጋ በመሆኑ ነው እንጂ፡፡ • ይህ ወልድ ለአንዱ የምንሰግድለት ለአንዱ የማንሠግድለት ባህርይ የምንል አይደለም፡፡ ሠው የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ባህርይ አንድ ሥለሆነ ሥጋው ጋር አዋህደን አንዲት ሥግደት እንሠግድለታለን እንጂ፡፡ • ከድንግል በነሣው ሥጋ ሞተ በማለት ፋንታ እግዚአብሔር አምላካችን ሥጋ በሌለው ባህርይ ታመመ ሞተ ይሉት ዘንድ አይገባም፡፡ • ክርስቶሥ ፈጣሪ እግዚአብሔር መሆኑን እናምናለን! ሥለሆነም ፍጡር ነው የሚሉትንና ዛሬም በአብ ቀኝ ተቀምጦ ለእኛ ያማልዳል የሚሉትን እንቃወማለን! እናወግዛለን! • ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱሥ አንድነት ሣይለይ በምልአት ሣለ ሥጋ መሆኑ እንደምን ነው? ቢሉ የዓይን ብርሃን ከአይን ብሌን ሣይለይ ከብርሃነ ፀሀይ ጋር ተዋህዶ ምሉዕ እንደሆነ ጌታም በመልአተ ባሕርዩ ሣለ በመኀፀነ ድንግል አድሮ ከመቅጽበት ዓይን ሠው ሆነ፡፡ የማይለይ የማይነገር የማይመረመር ተዋህዶ ሆነ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመሥቀሉ ክቡር!!!
إظهار الكل...
2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.