cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ማትሪክ

ትኩስ የፈተና መረጃዎች.....ቀልዶች..... ስኮላርሺፕ..... ቴክኖሎጂ.... Pdf መፀሀፍት....ትምህርት ነክ ቁምነገሮች .....ብዙ ብዙ ነገሮች ይዳሰሳሉ.... Join @Ethio_Matric @Ethio_Matric

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
1 612
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የሀገረ አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከነገ ጀምሮ የ2012 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን አስመልክቶ የሚያቀርቡትን አቤቱታዎችን ማስተናደገድ ይጀምራል። ኤጀንሲው አቤቱታዎችን የሚያስተናግደው ከነገ መጋቢት 28/2013 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ነው። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ከግምት በማስገባት ኤጀንሲው አቤቱታዎችን የሚያስተናግደው በድህረ ገፁ www.neaea.gov.et ላይ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ፤ አቤቱታ ያላቸው ተፈታኞች ዘውትር በስራ ሰዓት በድህረገፁ በመግባት 'compliant' የሚለውን በመጫን በሚፈጠረው ቅፅ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል። @Ethio_Matric
إظهار الكل...
የ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ ፦ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ (ሰኔ አካባቢ) ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል። በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ። ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል። የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል። tikvah @Ethio_Matric
إظهار الكل...
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ተገለፀ ! የትምህርት ሚኒስቴር የ 2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል። የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒኤችዲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12ሺ ህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአካባቢው የትምህርት መሰረተ-ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናቸውን በአካባቢያቸው በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ትምህርት ቢሮዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡ በሚቀጥሉት ሳምንታትም ተፈታኞችን በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማጓጓዝ ስራዎች እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ተፈታኞቹ ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም መቐለ ፣ አክሱም ፣ አዲግራት እንዲሁም ራያ የኒቨርስቲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ምንጭ፦ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር #share @ETV_57
إظهار الكل...
የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት ይሰጣል። ትምህርት ሚኒስቴር በኦንላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ዛሬ አስታውቋል። #በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ነው በወረቀት ለመስጠት የታሰበው ብሏል ሚኒስቴሩ። ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ተገልጿል። በዚህም መሰረት የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል። #tikvah #Share @Ethio_Matric
إظهار الكل...
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት ! የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦ • በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ። • ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። • ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል። • ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል። • 2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል። • በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ። • ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል። tikvah @Ethio_Matric
إظهار الكل...
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል ! የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዎስ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ፈተናን በተመለከተ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል። የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የህግ ማስከበርና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል ብለዋል። ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ አሳስበዋል። ምንጭ:- ትምህርት ሚኒስቴር @Ethio_Matric
إظهار الكل...
ለማትሪክ ጥናት ማገዣ የተዘጋጀ t.me/StGeorge_Gibi_Gubae
إظهار الكل...
MATRIC PREP SCHEDULE.pdf5.57 KB
#UPDATE ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን #የ12ኛ ክፍል ፈተና #በኦላይን ለመፈተን የሚያስችለውን አስፈልጊ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ለባለሙያዎች ስልጠናዎችን መስጠት መጀመሩ ሚኒስቴሩ አሳውቋል። በትምህርት ቤቶች ውስጥ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ የመብራትና የኔትዎርክ አቅርቦት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡ የኦንላይ ፈተና #ኩረጃን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ከመሆኑም ባሻገር ለወረቀት እና ፈተናውን ለማረም የሚወጣውን ወጪና ጊዜ ይቆጥባል ነው የተባለው፡፡ ተማሪዎች ፈተናውን በሚወስዱበት ጊዜ #የራሳቸው_ታብሌት_ላይ_ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲስተም አለው ተብሏል። ፈተናው የሚሰጥባቸው ታብሌቶችም በቅርቡ ለተማሪዎች እንደሚሰራጩ ተገልጿል። ተማሪዎች ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲተዋወቁ ከሶስር ሣምንት ያላነሰ ጊዜ የሚሰጣቸው ሲሆን ምንም ሳይጨናነቁ ለፈተና እንዲዘጋጁ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል - #MoE @tikvah @Ethio_Matric
إظهار الكل...
ከኮቪድ ወረርሽን ጋር  በተያያዘ የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን እንደሚካሄድ የትምህርት  ሚኒስቴር አስታወቋል! ተማሪዎች ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊትም  የ45 ቀን የማካካሻ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም እንደሚሰጣቸው በትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ተናግረዋል። ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት እና ፈተናም የሚሰጠው  ትምህርት ቤቶች የኮቪድ  ወረርሽኝን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ ብቻ መሆኑን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ መቅረቡን ሚኒስቴሩ  አስታወቋል። Via ኢብኮ @Ethio_Matric
إظهار الكل...
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የተሻለ ዝግጅት እንዲኖራቸው መሥራት እንደሚገባ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳስቧል። በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ጌታቸው ቢያዝን ለክልሉ ቴሌቪዥን (አማራ ቲቪ) ከተናገሩት የተወሰደ፦ - የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገር ዓቀፍ ፈተና በተሟላ መልኩ አስፈላጊውን ቅጽ (ፎርም) አልሞሉም ሆኖም የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ90 ሺህ በላይ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። - ትምህርት ቤቶች በተለይ 8ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል። - አብዛኛው በሚባል መልኩ የአማራ ክልል ተማሪ ገጠር አካባቢ እንደመኖሩ በሚፈለገው ልክ ጥረቱ ውጤት አስመዝግቧል ማለት አይቻልም። - ተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍቶቻቸው በእጃቸው ስላሉ እንዲያነብቡ፣ የ11ኛ ክፍል ትምህርቶችን መልሰው እንዲከልሱና ወላጆች ለልጆቻቸው አጋዥ መጻሕፍትን እንዲገዙላቸው መልእክት ተላልፏል። - ሀገር አቀፍ ፈተናው በኢንተርኔት በመታገዝ በቀጥታ (ኦንላይን) እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተገልጿል ፤ ተማሪዎች “ታብሌት” ተሰጥቷቸው እንዴት ጥያቄዎችን መሥራት እንዳለባቸው ከቴክኖሎጂ ውጤቱ ጋር የመለማመጃ ጊዜ ይኖራቸዋል። - ሀገር አቀፍ ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴርም ይሁን በሀገር ዓቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ ይፋ አልተደረገም። - ትምህርት ከተጀመረ የመጀመሪያዎቹ 45 ቀናት ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የክለሳ ጊዜያቸው ይሆናል። @Ethio_Matric
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.