cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

በዚህ ቻናል ላይ ማንኛውንም ☦☦የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአትን የጠበቁ ✥ አስተምሮቶችን ✟ ❖ ስብከቶችን ✟ ❖ መዝሙሮችን ✟ ❖ መንፈሳዊ መጽሐፍቶችን ያገኛሉ።☨☨ "መፅሐፍ ቅዱስን ወዳጅህ አድርገው አንተ የቃሉ ወዳጅ ስትሆን እግዚአብሔር ደግሞ የልቡ ወዳጅ ያደርግሀል።"      /አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ/

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 027
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+47 أيام
+1630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡ እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን? ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ  እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #አንድ አረጋዊ እንዲህ አሉ ፦”ልጆቼ ሆይ፦ ራሳችሁን መለወጥ ሳትችሉ የሌላን ሰው ነፍስ ማዳን ወይንም ሰወችን መርዳት አትችሉም፤ ነፍሳችሁ በልዩ ልዩ ምስቅልቅል ውስጥ ሆናም የሌላውን ሰው መንፈሳዊነት ስርአት ማስያዝ አይቻላችሁም፤ እናንተ ራሳችሁ የውስጥ ሰላም ከሌላችሁ ለሌሎች ሰላምን ማስገኘት አትችሉም ፤ ብዙውን ጊዜ የሰወችን በኛ ምክንያት ለበጎ ነገር መነሳሳትና ነፍሳቸውም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምናየው ወደ በጎ ይቀርቡ ዘንድ በአፍ በምንነግራቸው ነገር ሳይሆን በእኛ ላይ በተግባር በሚገለጥ የመንፈስ ፀጋና ስጦታ ነው፡፡ ሌሎች ሰወችም ህይወታቸው ለበጎ ነገር እንዲነሳሳና እንዲለወጥ በእኛ ህይወት ሲማሩ እኛ እንኳን ላናየውና ላንረዳው እንችላለን፡፡" 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
إظهار الكل...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #በደብረ_ምጥማቅ_ተገለጠች ከግንቦት 21 ጀምሮ እስከ 25 ድረስ ለአምስት ተከታታይ ዕለታት፥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ መገለጥ ይከበራል። በደብረ ምጥማቅ በዘይቱን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በ1968 በግብጽ ተገልጣለች። ይህ በእርግጥ ብዙ መልእክታት ያሉት ጉዳይ መኾኑ ለማንም ግልጽ ነው። ካልኾነማ ደርሶ ለምን ተገለጠች? እንዲሁ ያለ ምንም ዓላማ ነውን? የሚልና መሰል ጥያቄዎችን ያስነሣልና። የአንድን ክስተት መልስ አለማወቅ በራሱ ጉዳዩን ቀሊል ሊያደርገው እንደማይችል ልብ እንበል። መገለጧ ለምን እንደ ኾነ የማይታወቅ ቢኾን እንኳን፡ መልእክት የሌለው የመኾኑ ማስረጃ ሊኾን አይችልም። ስለዚህ የእመቤታችንን መገለጥ ቀለል አድርገን ማለፍ ያለብን መስሎ አይታየኝም። ++++++++  +++++++  ++++++++++ እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ በዘይቱን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ትገለጽ ነበር። የምትገለጥ የነበረውም በብርሃንና አስደናቂ በኾነ ውበት ነው። አንዳንዴ ከመስቀሉ ሥር ስትሰግድ ትታያለች፤ አንዳንዴ ልጇን ወዳጇን ታቅፋው ትታያለች። ቅዱሳን መላእክት ክንፎቻቸውን ዘርግተው፣ ያመሰግኗታል፤ ይጋርዷታልም። ሰማዕታት ይሰግዱላታል፤ ምስጋናና ክብር ያቀርቡላታል። ጻድቃን ደናግላን፣ ቅዱሳን በሙሉ ያደንቋታል። በአጭሩ አማናዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትገለጣለች ማለት ነው። ይህን ኅብረቲዊነት መመልከት እንዴት ያረካ ይኾን! የክርስቲያን ናፍቆቱ ወደዚህ ማኅበር ውስጥ ከመግባት በቀር ምን ሊኾን ይችላል! እንግዲህ ይህን አስደናቂ መገለጥ እንዴት በመጨመጨ ዐይን ልናየውና መልእክቱን ልንዘነጋ እንችላለን? ተስፋችንስ ከንቱ አለመኾኑን ከዚህ በላይ ምን ማሳያ እንሻለን! ይሄን አንድነት ከጥልቅ ልባችን እንድንመኝ ለማድረግና፡ ዓለም ጣዕሟ ከዚህ ኅብረት አንጻር መራራ መኾኑን ተረድተን ወደዚህ ኅብረት ለመግባት መትጋት፣ መውደድና መፈለግ አለብን! ++++  +++++++  +++++++  +++++++ እመቤታችን የተገለጠችው በጉልላቱ ላይ ነው። ይህን ስናስተውል፡ በአእምሯችን ውስጥ የመንፈሳዊነትን ከፍታን ማየት እንችላለን። ወደ ላይ ማየት! እመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምን በምድራዊ አስተሳሰብ ውስጥ መፈለግ የለብንም። በሌላ በማንኛው ዓለማዊ ነገር ውስጥ የምናገኛት አይምሰለን። እመቤታችን ያለችው በጉልላቱ ላይ ነው። ከፍ ባለ መንፈሳዊ ሕይወትና የቀና አስተሳሰብ ላይ እርሷን በእርግጥም እናገኛታለን። ስለዚህ ወደ ላይ እንውጣ! በእርሷ ቤተ ክርስቲያን እርሷን እንያት! በእርሷ ቤተ ክርስቲያን ወስጥ ተገኝተን በኃጢአታችን ምክንያት እርሷን ሳናይ እንደ መቅረት ያለ ምን ጉዳት አለ! ስለዚህ ከፍ እንበል። አልእሉ አልባቢክሙ "ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ" አእምሩ ኀበ ዘትቀውሙ "የቆማችሁበትን አስተውሉ" ተንሥኡ ለጸሎት ወይም ተንሥኡ ለነጽሮተ ምሥጢር "ለጸሎት ተነሡ፡ ወይም ምሥጢር ለማየት ተነሡ" እንግዲህ እነዚህ ወደ ላይ ማንሻዎች ናቸው። እመቤታችንን በእነዚህ መነሻዎች ከፍ ብለን እንመልከታት!! +++++ +++++  +++++   ++++++++++ የእመቤታችን መገለጥ ለኃጥኡም ለጻድቁም፣ ለአማኙም ለከሐዲው መኾኑ ደግሞ ሌላው አስደናቂው ነገር ነው። ርኅርኂተ ሕሊና መኾኗን ያመለክታል። የቆሰሉ ነፍሳትን ሕሊናት ለማከም፣ ለሚያምኑት መጽናኛ ልትኾን ተገለጠች። ከእስላሞችም እንዲያዩአት ፈቀደች። ቅድስና የሌለው ሊያያት የማይገባ ሲኾን፡ መሐሪት ስለ ኾነች ለአሕዛብም ታየች። ለእኛስ መች ታየች ብለው ከማመን እንዳይዘገዩ፣ አንድም አፍቃሪተ ሰብእ መኾኗ እንዲረዳን!! እርሷ ከእኛ የሌለች መስሎን በቀቢጸ ተስፋ እንዳንፍገመገም ጠበቀችን። በእርግጥም የሔዋን ጠበቃ የተባለችው የሔዋን ጠበቃ ብቻ ስለ ኾነች ሳይኾን በእርሷ አንጻር የእኛም ጠበቃ መኾኗን ለማመልከት እንጂ። ብዙዎች ከአሕዛብ ወገን ተደነቁ፡ ወደ እውነተኛው በረትም በጥምቀት በር ገቡ። እርሷን ካዩ በኋላ በውጪ መቅረት አልኾነላቸውምና! እመቤታችን ኾይ ለአሕዛብም ጭምር መገለጥሽ አስደንቆናል! በዚያውም ምንም ኃጥእ ብንኾን ከፈለግንሽ የምናገኝሽ መኾኑ ተረድቶናል። እኛን ኃጥአንንም ሳትንቂን በልባችን ውስጥ ተገለጪ! +++++ ++++    +++++++++  ++++++ በተደጋጋሚ መገለጧ ደግሞ ፍጹም ጊዜ ጥርጣሬን የሚያርቅ። ኹል ጊዜም በቃል ኪዳኗ የምትረዳን መኾኗን እንድንገነዘብ ያደርገናል። አንዴ ታይታን ተጠራጥረን፡ በድጋሚ ታይታን ከጥርጥር የምንወጣ እንኖራለንና። ምልጃዋ ለልጇቿ የማይቋረጥ መኾኑንም እናስተውላለን። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለረጅም ሰዓት (2-3 ሰዓት) መታየቷም በአንድ በኩል የእርሷ መገለጥ ምትሐት አለመኾኑን፡ በሌላ በኩል እኛን የምትፈልገንና ፍለጋዋም ጽኑ መኾኑን ይረዳኛል። እንግዲያውስ እርሷ እየፈለገችን ወዴት እንሮጣለን! እንዴት ከእርሷ ይልቅ ኃላፊ ነገሮችን ልናስቀድም እንችላለን? እንዴትስ በእርሷ ጨክነን ሰዓት የለኝም እያልን ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንቀራለን? ወዳጆች ሆይ ይህ የእመቤታችን መገለጥ አሕዛብ የመለሰ መኾኑን ስትሰማ ከኃጢአት መንገድ መመለስና ንስሓ መግባት እንዳለብህ አይረዳህምን? ኋለኞቹ አሕዛብ በመገለጧ በር በኩል ወደ ጽድቅ ሲገቡ ፊተኞቹ እኛ በኃጢአት መስኮት ስለ ምን እንወጣለን? ++++++  +++++++  +++++++  +++++ የእመቤታችን መገለጥ ውስጥ፡ ከመስቀል ስር ኾና መታየቷ ቀራንዮን በሕሊችን ውስጥ ለመቅረጽ ካልኾነ በቀር ምን ሊኾን ኖሯል! ወዳጄ ነገረ ማርያምን ስታይ በእርሱ ውስጥ ወደ ቀራንዮ ትገሰግሳለህ! የእናትነቷን ፍቅር ከመስቀሉ ስር ዝቅ ብለህ ትጠጣለህ። ቅዱሳን መላእክት ሲያመስግኗት አይተህ፡ በቸልታ ያሳልፍካቸውን ጊዜያት በማሰብ ታዝናለህ! በክንፎቿ ሲጋርዷት አይተህ በልብህ ውስጥ ፍቅሯን ሰውረህ ጣዕሟን በአንደበትህ በአስደናቂ ምስጋና ታጣጥማለህ!! ልጇን ታቅፋው ስትገለጥ አይተህ ያለ እርሷ ልጇን የማታገኝ መኾኑን ትረዳለህ። ስለዚህ ወደ ጉልላቱ እመቤታችን ስትገለጥ ተመልከትና አንተም ጣዕሟን በአንደበትህ ለዓለም ግለጥ። አፍህን በዘፈን አታቆሽሸው፣ በሐሜትም አታዝገው፣ በጫጫታም አታጨቅየው፣ በቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና አስውበው እንጂ። +++++  ++++++   ++++++  +++++++ በጉልላቱ ላይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታይታ አሕዛብን እንዳሳመነች፡ አንተም እርሷን በሕይወትህ ግለጣት፡ እንደ እርሷ ሰውን ሁሉ ያለ አድልዎ ውደድ! ማንንም አትጥላ! የሚጠሉህን ክርስትናን ገልጠህ ወደ በረቱ ሰብስባቸው። ኃጢአትን ፈጽሞ ጥላት፣ ከጠማማ ጋር አትጣመም። በእውነትና በንጽሕና መንገድ በመጓዝ በሰውነትህ ውስጥ ማርያማዊ ጣዕም ያለውን ሕይወት ግለጥ። ሰውነትህ የማርያማዊነት ፍቅር መውጫ ጉልላት ይኹንና እርሷን ባንተ ውስጥ አይተው እርስ በእርስ በክርስቲያናዊ ፍቅር ይፋቀሩ ዘንድ! ክርስትና ማለት የቤተ ክርስቲያንን ፍቅር የመግለጥ ሕይወት ነው። የእመቤታችን ምልጃ ከሁላችን ጋር ይኹን አሜን! 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
إظهار الكل...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን ? 👉 እንኪያስ በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር       እንዲሰማ አድርጉት ፡፡ 👉 ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን       እንዲያይ አድርጉት ፡፡ 👉 በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ       አድርጉት ፡፡ 👉 ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር       ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት ፡፡ 👉 ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር       መልካም  ንግግርን እንዲናገር አድርጉት ፡፡ #ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው ፡፡ #ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ። ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ ።" (የዮሐንስ ወንጌል 1:48) #ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን ለሁላችንም የሐዋርያው በረከት ትድረሰን ለዘለዓለሙ አሜን !!! #እንኳን ለሐዋርያው ለቅዱስ ናትናኤል ዓመታዊ የእረፍት በዓል አደረሳቹ አደረሰን 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ሩፋኤል ሆይ መንፈሳዊ ሐኪም ነህና ደዌ ኃጢአት እንዳያሰቃየኝ ፍቱን መድኃኒትህን ቀብተህ አድነኝ #መልክአ ቅዱስ ሩፋኤል 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ትጒህ በጸሎት #አቡነ ተክለሃይማኖት እየረዱ (ረድ ሆነው ) ሰባት ሰባት ጊዜ ዳዊትን ያደርሱ ነበር (ማር ይስሐቅ ገፅ 77 / ገድለ ተክለሃይማኖት ) #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው፤ በ1197 ዓ.ም ታኅሣሥ 24 ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በአሥራ አምስት ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ /ጌርሎስ/ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ #አባታችን ከመነኮሱም በኋላ በዳዊት ጸሎት ከነቢያት ምስጋና ሌሊቱን ሙሉ ይተጉ ነበር በያንዳንዱ መዝሙርም አሥር አሥር ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡  ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በጸሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ አባታችን ባረፉ 54 ዓመት  በ1344 ዓ.ም ለአባታችን ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ በረከታቸው በእኛ አድራ ትኑር ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ተወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር እነዚህን መከራዎች ያመጣው የእናንተን ግድየለሽነት ለማራቅና ከእንቅልፋችሁ እንድትነቁ ብሎ ነው #ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
إظهار الكل...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #በዚህችም ዕለት የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት ዮሐንስ አፈወርቅ አረፈ፡፡ ይህም አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎች ወገን ነው የአባቱም ስም አስፋኒዶስ የእናቱም ስም አትናሲያ ነው እሊህም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህንንም ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት ትምህርትንና ጥበብንም ሁሉ አስተማሩት እርሱ ወደ አቴና ሒዶ በመምህራን ቤት ተቀምጦ ትምህርትን ሁሉ ተምሮ በዕውቀቱ ከብዙዎች በላይ ከፍ ከፍ ብሏልና። ከዚህም በኋላ ገና በታናሽነቱ መነኰሰ የዚህንም የኃላፊውን ዓለም ጣዕም ንቆ ተወ ከእርሱም ቀድሞ በዚሁ ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ መንኵሶ ነበር በአንድነትም ተስማምተው ብዙ ትሩፋትን ሠሩ ወላጆቹም በሞቱ ጊዜ ከተውለት ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ እንጂ ከዚያም በምንኵስና ሥራ በመጠመድ ፍጹም ገድልን እየተጋደለ ኖረ። በዚያም ገዳም ሶርያዊ ጻድቅ ሰው ስሙ ሲሲኮስ የሚባል መነኰስ ነበረ እርሱም ወደፊት የሚሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ያይ ነበር በአንዲት ሌሊትም ለጸሎት እየተጋ ሳለ ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ዮሐንስን አያቸው ወደ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብተው ጴጥሮስ መክፈቻ ሰጠው ወንጌላዊ ዮሐንስም ወንጌልን ሰጠው እንዲህም አሉት በምድር ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው ደግሞ በሰማያት የተፈታ ይሆናልና በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ ያደረብህ አዲስ ዳንኤል ሆይ የክብር ባለቤት ከሆነ ከታለቅ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወደ አንተ ተልከናልና ዕወቅ እኔም የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠኝ ጴጥሮስ ነኝ። ሁለተኛውም እኔም በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ። ለአንተም ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወገኖችህ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእምሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል። ጻድቅ ሲሲኮስም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ቸር ታማኝ እረኛ ሁኖ እንደሚሾም ዐወቀ። ከዚህም በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በላዩ ወርዶ አደረበትና ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ዲያቆን ሁኖ ሳለም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ብሉያትንና ሐዲሳትን ተረጐመ። በአንዲት ሌሊትም ቅዱስ ዮሐንስ ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ በድንገት እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታየው ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ አትፍራ ተነሣ አለው የቅዱስ ዮሐንስም ልቡ ተጽናንቶ ጌታዬ አንተ ማነህ ግርማህ አስፈርቶኛልና አለው የእግዚአብሔር መልአክም ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወዳንተ የተላክሁ ነኝ። አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና እልፍ አእላፋትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና በእግዚአብሔር መንግሥትም ውስጥ የጸና የብርሃን ዐምድ ትሆናለህና። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንተ ይመጣል ከእርሱም ጋራ ሁሉም ካህናትና ዲያቆናት በየማዕረጋቸው የሚያዝህንም አድርግ የእግዚአብሐር ትእዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም አለው። ከዚህም በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስን ቅስና እንዲሾመው አዘዘው በማግሥቱም ሊቀ ጳጳሳቱ መጣ ከርሱ ጋራም ካህናት አሉ ይህን ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው። የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳትም በአረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃድዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን በቍስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው አባቶቻችን ሐዋርያት እንደሚአደርጉት በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ላይ ጸና ሕይወትነት በአላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚአስተምር ሆነ። ከኤጲስቆጶሳትም ሆነ ከመንግሥት ወገን ሕግን የሚተላለፉትን ሁሉ ይገሥጻቸዋል ማንንም አይፈራም ፊት አይቶም አያደላም። የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት አውዶክስያም ገንዘብ ወዳጅ ስለሆነች የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች ያቺ መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥታ ንግሥት አውዶክስያ ቦታዋን እንደነጠቀቻት ነገረችው እርሱም የደኃዋን ቦታዋን መልሺላት ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥት አውዶክስያን ለመናት እርሷ ግን እምቢ በማለት አልታዘዘችለትም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት። ቍጣንና ብስጭትንም ተመልታ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች እነርሱም ንግሥቲቱን ስለ ተቃወመ ስደት እንደሚገባው በእርሱ ላይ ተስማምተው ጻፉ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው። ከዚያም በደረሰ ጊዜ የዚያች ደሴት ሰዎች በክፉ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ ከሀድያን ሁነው አገኛቸው ቅዱስ ዮሐንስም አስተማራቸው ገሠጻቸውም በፊታቸው ስለ አደረጋቸው ድንቆች ተአምራት ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው። የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም በመቆጣት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ ከአልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም። መልእክታቸውንም በአነበበ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስን ከስደቱ መለሰው በተመለሰ ጊዜም የቍስጥንጥንያ ሰዎች በመመለሱ ታላቅ ደስታ አደረጉ። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ። ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳት ዮናክኒዶስም በሰሙ ጊዜ መልእክትን ላኩ ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ እስከምትመልሰው ድረስ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል አውዶክስያን አወገዛት። ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስን ይመልሱት ዘንድ ንጉሥ ላከ ግን ሙቶ አገኙት ሥጋውንም ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት። የከበረ ዮሐንስም በተሰደደበት አገር እንደአረፈና ሥጋውንም ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ እንደአመጡ ወደ አባ ዮናክኒዶስ መልእክት ጽፈው አስረዱት። ሁለተኛም የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል ልኮ አውድክስያን አወገዛት እየለመነችውም ስምንት ወር ያህል ኖረች በብዙ ልመናም ፈታት። ነገር ግን ጭንቅ በሆነ ደዌ እግዚአብሔር አሠቃያት ያድኗት ዘንድ ገንዘቧን ለባለ መድኃኒቶች ጥበበኞች እስከ ሰጠች ድረስ ግን አልዳነችም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብርም ሔዳ በእርሱ ላይ ያደረገችውን በደል ይቅር ይላት ዘንድ እየሰገደችና እያለቀሰች ለመነችው እርሱም ይቅር አላት ከደዌዋም ፈወሳት። ጌታችንም ከሥጋው ታላላቅ ድንቆች ታአምራትን ገለጠ። ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን አለው።
إظهار الكل...