cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

_____________✔✿❀✔__________ ✍... እንኳን ደህና መጣችሁ "ኑ እናንብብ አብረን በእውቀት ከፍታ እናብብ!" _____________✔❀✿✔___________ መልካም መስራት ክፉ ከማሰብ ይልቅ የበለጠ ደስ ይላል፡፡ ✍ ለማንኛውም፦ ✔ መልዕክት ✔ጥቆማና ቅሬታ @Ayuma

إظهار المزيد
Ethiopia4 656Amharic4 109الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
1 696
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-87 أيام
-3130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል 4 ከወራቶች በኀላ #ወገን እንዳናግራት አደፋፈረኝና ላናግራት ወሰንኩ፡፡ በሰዓቱ እንደሷ የምፈራው ሰው አልነበረም፡፡ በሆነ አጋጣሚ ሳያት ከያዘችኝ የምገባበት ነበር የሚጠፋኝ፡፡ ነገር ግን የሚሰማኝን በውስጤ አምቄ ከምሰቃይ ልተንፍሰውና ይለይለት ብዬ ወሰንኩ፡፡ እንደነገ ላወራት እንደዛሬ አዳር ላይ የምላትን እና ከእሷ ሊመጡ ይችላሉ የምላቸውን ምላሾች በመገመት በድጋሚ የምላትን ከእራሴ ጋር ስለማመድ አደርኩ፡፡ አይነጋ የለም ነግቶ ት/ት ቤት ገባን፡፡ ላናግራት የወሰንኩት ምሳ ሰዓት ስለነበር እስከዛ ያለው ሰዓት በጣም እራቀኝ። ሙሉ ሰውነቴን የፍራት ካባ ሲለብሰኝ ተሰማኝ፡፡ ምሳ እንደበላን ከትምርት ቤታችን ባለ 4 ፎቅ ህንፃ እራሱን እንደሚያጠፋ ሰው 4ኛው ላይ ሁኜ አስጠራዋት፡፡ ቦታውን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ተማሪዎች በምሳ ሰዓት ስለማይበዙበት ነበር። ሌላው ደሞ በሰዓቱ ሴትን ቀጥሮ ስለማውራትም ሆነ ምቹ ስለሆኑ ቦታዎች እውቀቱ ስላልነበረኝ ነው፡፡ ከትንሽ መንቆራጠጦች በኀላ በደም ፈንታ በደም ቧንቧዎቼ የምትዘዋወረው ቆንጆ ከህንፃው መወጣጫ ደረጃዎች በአንዱ በኩል መጣች፡፡ ልክ እንዳየዋት ውስጤ ይረበሽ ጀመር፤ ማታ የተዘጋጀውበት በሙሉ እንደ ጉም ተኖ ጠፋ፡፡ አጠገቤ እንደደረሰችም ልብን በሚያቀልጠው ፈገግታዋ ሞቅ ያለ ሰላምታ ከሰጠችኝ በኀላ እንዳላወቀ ሰው "ለምን ነበር የፈለከኝ?" አለች ትኩር ብላ እያየችኝ፡፡ አይኖቼ ከአይኖቿ ጋር ሲላተሙ ይባስ እፈራትና እረበሽ ጀመር፡፡ ትንፋሽ እንዳጠረው ሰው እያቃሰትኩ "እየውልሽ #ፀጊ አፍቅሬሻለው፤ ጓደኛ እንሁን" አልኳት አንዴ እሷን አንዴ መሬቱን እያየው፡፡ "አይ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር ማሰብ አልፈልግም፤ አልችልም፡፡" አለች እጥር ምጥን ብሎ ለጆሮ በሚከብድ አማርኛ፡፡ "እሺ፤ ቻው" ብያት እኔ በአንዱ ደረጃ እሷ በሌላኛው ዳግም ላንገናኝ በሚመስል መልኩ እየተጣደፍን ሄድን፡፡ ቀጥታ ክላሴ ገባውና እራሴን ካረጋጋው በኀላ ለምን ልናገር ያሰብኩትን እንዳልተናገርኩና "አልችልም" ስትለኝ "ለማስረዳት በመሞከር ፈንታ ለምን "እሺ" የምትለው ቃል ከአፌ እንደወጣች እራሴን ጠየኩት፡፡ ለካ ከሚያፈቅሩት ሰው ፊት መቆም ለሞት ፍርድ ከመቆም ባልተናነሰ ልብን ሰልቦ በፍርሀት ይለውሳል፡፡ .....👉 ይቀጥላል
إظهار الكل...
T҉ e҉ s҉ h҉ e҉  ......: #የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል3 ከዛን ቀን ጀምሮ በእየቀኑ ስለሷ ማሰብና መጨነቅ ስራዬ ሆነ፡፡ ት/ት ቤት፣ ሰፈር፣ ማታ አልጋዬ ላይ ተኝቼ የማስበውም የማልመውም እሷኑ ሆነ፡፡ በሰዓቱ ገና የ14 አመት ልጅ ስለነበርኩ በተጨማሪም ለእንደዚህ አይነት ስሜት አዲስ በመሆኔም ስሜቱ ምን እንደሆነ አላቅም ነበር፡፡ ነገር ግን ህንድ ፊልም ላይ እንደምናየው ነገሩ ቀስ በቀስ ፍቅር መሆኑ እየገባኝ መጣ፡፡ በእየቀኑ ምሳ ስትበላ፣ ስትጫወት፣ ወደ ቤቷ ስትሄድ በቅርብ ዕርቀት እከታተላታለው፡፡ ነገር ግን በዛ በልጅነት አንደበት ማን ቀርቦ ያውራ? ዝም ብቻ፡፡ ይህ ስሜት ቀስ በቀስ የውስጥ መንፈሴን እየጎዳኝ መጣ፡፡ ለወትሮው ተጫዋች የነበርኩ ልጅ አሁን መቆዘም ትልቁ ስራዬ ሆነ፡፡ ትምርቴንም እየደከምኩ መጣው፡፡ በፍቅሯ መነደፌን ከጓደኛዬ #ወገን በስተቀር ማንም እንዳያውቅብኝ ብጥርም የማሳያቸው ያልተለመዱ ባህሪያት ሚስጥሬን አደባባይ አወጡት፡፡ አብዛኞቹ የክላሴ ልጆች እንዲሁም የፀጊ ጓደኞች እና እራሷ ፀጊ ጭምር እሷን ማፍቀሬን ደረሱበት፡፡ ይህ ደሞ ይበልጥ ኑሮን አከበደብኝ፡፡ ማንኛውም ሰው እኔን እያየ ከተጫወተና ከሳቀ በፍቅሬ ያፌዘና ያላገጠ መስሎ ይሰማኝ ጀመር፡፡ በቃ በሰዓቱ እራሴን ሙሉ በሙሉ እሷን በማለምና በመፈለግ ውስጥ አጣውት፡፡ ከወገን ውጪ ቀርቤ የማወራውም የማማክረውም ጓደኛ አልነበረኝም፡፡ ት/ት ቤት ስሆን ከእሱ ጋር እቤት ስሆን ከግጥም ደብተሬ ጋር ሆነ ግዜዬን የማሳልፈው፡፡ በሰዓቱ የግጥም ደብተሬ የምለው አሁን ላይ ግጥም የሚለውን መጠሪያ ለመያዝ ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በእዛን ወቅት ስለሷ የሚሰማኝን እና ለእሷ መንገር አለብኝ ብዬ የማስበውን በሙሉ ለእኔ ብቻ ትርጉም በሚሰጡ ቃላት የማሰፍርበት፣ የምተነፍስበት ጓደኛዬ ነበር፡፡......4 ❤ 🌹@Yewqetabugida67
إظهار الكل...
#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል 2 በሰዓቱ እረፍት አልቆ ተደውሎ ስለነበር እሷ ከጓደኞቿ ጋር እየሮጠች ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡ እኔም በወደኩበት ከእይታ እስክትርቅ ድረስ በአይኔ ሸኘዋት፡፡ ክላስ ገብቼ ልክ እንደሌሎቹ ደብተር አውጥቼ እስክርቢቶ በእጄ ይዣለው፡፡ ነገር ግን በአእምሮዬ ከደቂቆች በፊት አይኔን ስለወጋኝ ውበት እያሰላሰልኩ ነው፡፡ "ስንተኛ ክፍል ናት? የት ነው ሰፈሯ? ስሟ ማነው? እንዴት እስከዛሬ አላየዋትም? " በዛች ቅፅበት ፍቅርን አዝለው ወደ አእምሮዬ የመጡ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ እንዳያልቅ የለም ቀሪው የት/ት ክፍለ ግዜ አልቆ ምሳ ተደወለ፡፡ ምሳ አብሬው ምበላ፣ ወደቤት የሆነ መንገድ ድረስ አብሬው የምሄድ፣ አብዛኛውን ግዜዬን አብሬው ማሳልፈው #ወገን የሚባል ጓደኛ ነበረኝ፡፡ እናም ምሳ እየበላን "ስማ ቅድም አባሮሽ ስንጫወት እኔ እንዳባራት የተሰጠችኝን ልጅ ታቃታለህ እንዴ?" ብዬ ጠየኩት፡፡ "እእእእእ ፀገነትን ነው? አዎ" በማለት መለሰ፡፡ "ፀገነት ነው ስሟ! ማለት ስንተኛ ክፍል ናት? የት ነው ሰፈሯ? የነማን ጓደኛ ናት? ምሳ የት ነው ምትበላው?" በማለት ስለሷ ለማወቅ እንደጓጓው በሚያሳብቅ መልኩ የጥያቄ ናዳ አወረድኩበት፡፡ እሱም "እንደኛው ሰባተኛ ነች፡፡ ሰፈሯ ከእኔ ሰፈር ብዙም አይርቅም፤ ቅርብ ለቅርብ ነን፡፡ እና ቆንጆ ነች፡፡" አለ እየሳቀና በእጁ መታ እያደረገኝ፡፡ ወዳው እንዴት እንደሆነ በማላውቀው መልኩ ውስጤ እሷን እሷን ሲለኝ ተሰማኝ፡፡ "ምሳ የት ነው ሚበሉት?" አልኩት፡፡ እሱም በልተን እንጨርስና እወስድሀለው ብሎ የሚበሉበት ቦታ ወሰደኝ፡፡ የመማሪያ ክላስ ሲሆን ግድግዳው በጠፍጣፋ ጣውላ ተደርድሮ የተሰራ ነው፡፡ በጣውላና ጣውላው መካከል ባላው ቀዳዳ አጮልቄ እንዳይ ጠቆመኝ፡፡ አዎ #ፀጊ ከሶስት ጓደኞቿ ጋር ምሳዋን እየበላች ነበር፡፡ በሰውነት ሁሉም ይበልጧታል፡፡ በመልክ ግን አዳላህ አትበሉኝ እንጂ ትቦንሳቸዋለች፡፡ ስትስቅ ደሞ ላለመሳቅ ቀጠሮ የያዘ ሰውም ቢሆን ፈገግ ይላል፡፡ በቃ እንዴት እንደሆነ ባላቅም ገና በ14 አመቴ ፍቅር ይዞኛል፡፡ ግን ፍቅር ምንድን ነው? አላቅም!!!....... ፫
إظهار الكل...
አዲስ የፍቅር ታሪክ ሊጀመር ነው።
إظهار الكل...
#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል1 በወቅቱ እንደማንኛውም ታዳጊ ጨዋታን አብዝቼ የምወድ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡ በትምርቴ ከ1-10 ባለው ደረጃ እወጣ ነበር፡፡ በብዛት 4ኛ እና 5ኛ የኔ ደረጃዎች ነበሩ፡፡ ከዛ በዘለለ ግን ሙሉ ቀን ሙሉ ለሊት ስጫወት በውልና ባድር ጨዋታ የማልሰለች ልጅ ነበርኩ፡፡ ከቀኖች ሁሉ በቅጡ በማላስታውሰው በአንዱ ቀን ከተወሰነ የት/ት ክፍለ ግዜ በኀላ ለእረፍት ተለቀን ከተወሰኑ ተማሪዎች ጋር ተመራርጠን አባሮሽ እየተጫወትን ነው፡፡ በሰዓቱ እኔ አባርሬ እንድይዝ የተሰጠኝ አንዲት ቀይ ቀጠን ያለችን ልጅ ነበር፡፡ ልጅቷን ከዚህ በፊት ልብ ብዬ አይቻት አላቅም፤ ስሟንም ሰምቼው አላቅም፡፡ ጨዋታው ተጀመረና እኔ ነብር እሷ ሚዳቆ ሆነን በረጅሙ የት/ቤታችን የሳር ሜዳ ላይ ያዝኩሽ አመለጥኩህ ሩጫ ያዝን፡፡ ልይዛት በጣም እቀርብና በድንገት የእኔ ፍጥነት ቀንሶ የእሷ በመጨመር ታመልጠኛለች፡፡ ከብዙ ልብ አፍርስ ሩጫ በኀላ ከነብር እጅ ሚያመልጥ የለምና ሚዳቆዋን ያዝኳት፡፡ ነገር ግን እሷ ልታመልጠኝ እኔም ይዣት ለማስቀረት ስንሞክር እኔ በእሷ ላይ ወደቀን ተገኘን፡፡ ዩኒፎርሟ እንደመገላለጥ ብሎ ነበርና እንደማፈር ብላ ልብን በሚያቀልጥ ሁኔታ በእነዛ ሁለት አይኖቿ ለመጀመሪያ ግዜ አይኖቼን ተመልክታ እየተሽኮረመመች ከመሬት ተነስታ ሄደች፡፡ በዛች ቅፅበት ያቺ ቀጭን ቀይ ቆንጆ የመጀመሪያ ፍቅሬ ልትሆን ሳታስፈቅድ ወደ ልቤ ዘልቃ ገባች። 👇 ክፍል ሁለት ይቀጥላል
إظهار الكل...
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼ቸሩ የእኔ ጌታ መሃሪ ይቅር ባይ 🌼 🌼ከክፉው ወረርሽኝ ከኮሮና ቫይረስ 🌼 🌼ከባህሩ ስጥመት ድልድይ ሆነህ🌼 🌼ከጥፋት ከልለህ ትላንት ካሻገርከኝ🌼 🌼በሰላም በጤና ዛሬ ላይ አኑረህ 🌼 🌼ተመስገን ጌታዬ ነገም አንተ አለህ🌼 🌼የዘመናት ሠሪ የዓመታት አባት 🌼 🌼ሁሉን አሳላፊ አልፋና ኦሜጋ 🌼 🌼ያለፈውን ዘመን ደግሞ እንዳይመጣ 🌼በምሕረትህና በቸርነት ይለፍ 🌼 🌼እውነተኛ መሪ መንጋውን ሰብሳቢ🌼 🌼ከሃሳዊ መሲህ ተዋህዶን ጠባቂ 🌼 🌼አሁንም አድለን እንባ አባሽ መሪ 🌼 🌼 🌼 🌼ዘመነ ማቴዎስ ዘመነ ፍሥሃ ! ፡፡ 🌼 🌻 🌻 🌼 🌻 🌼 🌻 🌻 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌹@Yewqetabugida67🌷🌼
إظهار الكل...