cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ልብ ወለድ 2❤💞💝💖

ልብ ወለድ የተለያዩ ግጥሞች እና አዝናኝ ቀልዶች አጫጭር ታሪኮች የፍልስፍና ዳራ ድምፀ መረዋዎች For any comment or Cross @Eduka19 @Jemal911 @Mahidanii @Ssarone

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
747
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

💦የሀሜት ጥገኛ ብዙ ሰዎች በሕይወታችሁ አስተውላችሁ ከሆነ ነብስ ያለው ሀሳብ ይዘው ቀርበው ሊረቷችሁ ካልቻሉ ወይ በስድብ ሊያሸማቅቋችሁ ይሞክራሉ ወይም ። ከኋላችሁ በማውራት ያሸነፏችሁ ሊያስመስሉ ይጥራሉ ። ይሄ የብዙዎቻችን ሕይወት ተግዳሮት ይመሥለኛል ። ለጊዜው ማንነትቱን የዘነጋሁት ደራሲም ይህንን ብሎ ነበር... " በክርክር ማሸነፍ የማይችል ሰው የሀሜት ጥገኛ ይሆናል ። " " ደካማ ሰዎች ካንተ ጋር ማውራት ሲያቆሙ፤ ስላንተ ማውራት ይጀምራሉ ። "
إظهار الكل...
ጋዜጠኛ-በወላጆቻችንና በእኛ በልጆቻቸው መካከል ፣ በልጅነትዎ የታዘቡት ዛሬ ጎልቶ የሚታይዎት የስነ-ልቦና ልዩነት ወይንም የትውልድ ዘንቆ (Generational gap) አለ ? ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን - አለ! ግልጥ ነው ፤ ልጅ ሆኜ ታላላቆቼ በተግባራቸው እንዳስገነዘቡኝ ፣ ለምሳሌ አንድ ሰው በአንድ ውል ተፈጣጠመ ፣ ቃሉን ሰጠ ፣ መሀላ ገባ ከተባለ ስጋ ወደሙን እንደተቀበለ ይከብዳልና ፤ ያ ሰው ለገባለት መሀላ ህሊናውን ያስገዛል ፤ በቃሉ ይታሰራል ፤ በቃሉ ይከበራል ፤ በቃሉ ይፈረጃል ። ትንሽ ልጅ ሆኜ አምቦ ከተማ አማራውም "ቃሌን አልከዳም ቃል ገብቻለው"ይላል ፤ ኦሮሞውም "ሴሪ ሴሩማ" ወይንም "ሴራ ቁርጥ ነው"ይላል ፤ አማራውም "የተናገሩት ከሚሞት የወለዱት ይሙት"ይላል ፤ ኦሮሞውም"ቃልን ነገር አይሰብረውም ፣ ጦር አይመልሰውም"ይላል ። ስለዚህም ህዝቡ ከባህላዊ ስነምግባሩና ፤ ከስነ-ልቦናዊ ባህሪ ጽናት የተነሳ እከሌ ቃሉን ሰበረ ሲሉት ይደነግጣል ።ዛሬ ግን አንድ ጮሌ ወይንም አንድ ካድሬ ወይንም አንድ የስልጣን ልክፍተኛ ፣ ከአንድ መሀላ ወደሌላ መሀላ ፤ ከአንድ ድርጅት ወደሌላ ድርጅት እንደ ቅሪላ ዘጠኝ ጊዜ ሲንፏቀቅ ፣ ጎበዝ! ነው ብለን እናደንቀው ይሆናል እንጂ ነውር ነው ብለን አንደነግጥም ። አዎን በእኛና በወላጆቻችን መሀል ጉልህ የሆነ የትውልድ ዘንቅ (Generation gap) አለ ይላል @yetbgb
إظهار الكل...
ሰላም ውድ የቻናሌ ተከታዬች እንደምን ቆያቹኝ እኔ አለው በፈጣሪ እርዳታ በቻናሌ አንዳንድ ነገሮች እንደተናደዳቹ ይገባኛል የምትፈልጉትን ነገር በአግባቡና በጊዜው ላቀርብላቹ አልቻልኩም ለሱም ደግሞ ከወገቤ ጎንበስ ከጉልበቴ ዝቅ እያልኩ ይቅርታ ጠይቃለው🙏🙏 እናም ሁሉንም ነገር ልክሳቹ በአዲስ አቀራረብ አዲስ ቻናል ከፍቻለው እዛ ውስጥ በመቀላቀል ብዙ ነገርን እንድታገኙ ከልቤ እያከበርኩ እንድትገቡ ጋበዝኳቹ የቻናሏ ሊንክ @Fkrkemnet እዚ በመግባት ሁሉንም ያግኙ ከዚ በኋላ ልብ ወለድ፪ ላይ ስለማይለቀቅ አሁኑኑ ይቀላቀሉን
إظهار الكل...
Nuhamin: " መቅደላዊት " ምዕራፍ ፪ ( ሁለት ) ክፍል ፴፯ ( ሰላሳ ሰባት ) በአምባዬ ጌታነህ ( @adwa1888 ) ወዲያው ሁሉም ነገር መጣላት..... እሷ 5ኛ አመት እያለች ነው። ሴቶች ስለ አንድ ሲኒየር ልጅ ያወራሉ። አንድኛዋ ተነስታ " ሴትን ልጅ በጣም ነው የሚያናንቀው። ሴት ፍጡር አትመስለውም። ስለ ሴት ሲያወራ እኮ ብታዩት ፊቱ እንዴት እንደሚቀያየር በቃ ብቻ ምን ልበላችሁ የሆንን አስፈሪ እንሰሳት ነው የምንመስለው ብቻ የሆነ ቀን ባገኘው እንጃ ብቻ ምን እንደማደርገው" አለች " ሌላኛዋ ተቀበለቻት " አዎ እሷ ልክ ናት በየ አንዳንዱ ምሽቱ ስለ ሴት ልጅ ድክመት ስለ ሴት ልጅ መጥፎነት ሳይናገር አይወርድም። ከሴት ያልተገኘ ነው የሚመስለው ። እኔም በበኩሌ ወይ ከተማ ወይ የሆነ ብታ ባገኘው አልለቀውም። " እያለች ትፎክራለች ሌላኛዋም ትቀበላትና የእራሷን የጥላቻ ረቂቅ ታረቃለች። አንድ ላይ ባሩክን ስለመደብደብ የሆነ ነገር ስለማድረግ ሴራ ይጎነጉናሉ። " ይሄ ሁሉ በምናቧ መጣባት አጠገቧ ያለው ልጅ ነው በእነዛ ሴቶች አፍ ሴትን የሚያጥላላው ተብሎ የተከሰሰው። አሁንም እነዛ ሴቶች ያሉት ነገርን በአይኗ የተወሰነ ፍንጭ እንኳ ባገኝ ብላ የምትመለከተው ይመስላል። ባሩክ በአንድ ጊዜ ስትቀየርበት ግራ ገባው ሁለት ጊዜ ጠይቋት ዝም ስትለው ትቷት ወደ ራሱ የሀሳብ አዙሪት ተመለሰ። ባሩክ ለማይሆን ነገር ጊዜ ማጥፋት አይፈልግም አንድ ሀሳብ ላይ ብቻ የሙጥኝ ብሎ አይቀመጥም። በሀሳብ ይከፋፈላል ወዲህም ወዲያም እንደ ገባር ወንዞች ተነጥሎ ያስባል ይመረመራል። "እሽ አቶ ዲዮጋን !" አለች ልጅቷ ከትውስታ አለሟ ስትነቃ ።ባሩክ አሁን ገባው ለምን በዝምታ እንደተዋጠች ለምን እንዳልመለሰችለት። ለምን በንቀት እና በጥላቻ ስትመለከተው እንደነበር።ባሩክ የሰጣት ምልሻ የድንጋጤም የፍርሃትም የምንም ሳይሆን ዝም ብሎ ፈገግ አለና " ማነሽ እህቴ አእምሮሽ ውስጥ ምን ሲመላለስ እንደነበር አላውቅም ግን በእኔ ሲመላለስ እንደነበር ለመረዳት ችያለሁ! እኔ አንቺን አላውቅሽም ስለማላውቀው ሰው ማንም ሰው ምንም ቢለኝ አልቀበልም እኔ እያንዳንዷን ነገር መርምሬና አረጋግጨ ነው የምሰራው። ዝም ብየ በአንድ አሳቢ ብቻ እንደሚመራ ስብስብ አልነዳም ። የራሴ የሆነ የሀሳብ መፍጫ መሰለቂያ መጅና ወፍጮ ያለኝ ሰው ነኝ። በምን ምክንያት እንደዚህ እንደሆንሽ አላውቅም ማወቅም አልፈልግም ማስረዳትም አይጠበቅብኝም ግን አኔቺን የምነግርሽ ለአእምሮሽ የሰጡሽን ሳይሆን ያገኘሽውን ያወቅሽውን የመረመርሽውን መግቢው። ያኔ በአመክንዮ የተሞላ በእርግጠኝነት የታጀበ አእምሮ ይኖርሻል። ከወገንተኝነት ፈቀቅ ብለሽም ስታወሪ ትደመጫለሽ። እኔ ዲዮጋን ሳልሆን የዲዮጋን አድናቂ ነኝ። ዲዮጋን በጣም ሲበዛ ግድየለሽ ለእውነቱ ብቻ የሚጨነቅ ድንቅ ፈላስፋ ነው።አንድ ነገር ልንገርሽና ሀሳቤን ልቋጭ ምክንያቱም እኔና አንቺ የተለያዬ የርዕዮተ ዓለም ስለሆነ ያለን መግባባት አንችልም። አንድ ጊዜ በታላቋ ግሪክ እንዲህ ሀሆነ የግሪክ ህዝብ ውጭ ላይ መመገብ ነውር ነው ብሎ ያምናል። ውጭ ላይ አይመገቡም ሁሉም ነገር ውስጥ እንዲሆን ነው የሚፈልጉት ነገር ግን ይሄን ህጋቸውን ዲዮጋንን ስላላሳመነው የነሱንም ህግ ይሽርና ውጭ ላይ መመገብ ያዘወትራል። የዲዮጋንን ምግባር እና የሀገሬውን ህዝብ ህግ አለማክበሩ ያበሳጫቸው ግሪካውያን አኔዴ ቀን ዲዮጋን ወደሚበላበት ቦታ በመሄድ ዲዮጋን እንደለመደው ውጪ ላይ ሲመገብ ዙሪያውን ይዞሩና በአንድ ላይ " ውሻ ውሻ ውሻ " ይሉታል። ዲዮጋንም ጩኸታቸውን ከመጤፍ ከምንም ሳይቆጥር ምግቡን በዝግታ ይበላል " ውሻ ውሻ ውሻ " የሚለው ድምፅ እየበረከተ መጣ ።ግሪካውያኖቹ ዲዮጋንን እንዲህ የሚሉት በስድባቸው ተሸማቆ ውጭ ላይ እንዳይመገብና ህጋቸውን እንዲያከብር እንዲቀበል ነበር። ነገር ዲዮጋን " ውሻ ውሻ " በሚለው ድምፃቸው ታጅቦ ምግቡን ከጨረሰ በኋላ ከተቀመጠበት ተነሳና " በሉ እናንተ ግሪካውያን አሁን እኔ በልቼ ጨርሻለሁ ወደ ቤታችሁ መሄድ ትችላላችሁ ።ውሻ የሚባለው ሰው ሲበላ የሚጮህ ነው። " ብሏቸው ትቷቸው ሄደ ።በንግግሩም በታተናቸው። ይሄን ያሌኩሽ ያለ ነገር አይደለም በሁኔታሽ ተገርሜ ነው። በእርግጠኝነት አሁን እኔ ምን አድርጌሻለሁ ብየ ብጠይቅሽ መልስሽ ምንም ነው። ወይም የተወሰኑ ልጆች ስለ እኔ ሲያወሩ የነበረውን ወሬ እንደማስረጃነት ታቀርቢልኝ ይሆናል። ግን ይሄ አኔቺነትሽን ሰውነትሽን ያሳጣሻል። እጌዜር የእህቴን ልጅ ገድሎብኝ እሱን ጠልቼ ሌላ አምኛለሁ። እንደማለት ነው የሚቆጠረው በራሱ ላይ ባልደረሰ ያልደረሰን ሰው ተጠያቂ ማድረግና መጥላት። አየሽ አንቺ በማታውቂው ነገር ባልደረሰሽ ነገር ደስታሽን አጥተሻል። ይሄኔ የጓደኞችሽን አለዚያም የዶርም ሜቶችሽን ወሬ ባትሰሚ ከእኔ ጋር በጥሩ ጨዋታ አሪፍ ጊዜ እናሳልፍ ነበር። በእርግጥ አንቺ ነሽ እንጅ እኔ ጥሩ ጊዜ እያሳለፍኩ ነው። የምወደውን ሀሳቤን እየነገርኩሽ ስለሆነ። እና አኔቺ ወጣት ነሽ ብዙ ነገር ይጠበቅብሻል የጥላቻሽን ሥንጭ አድርቂ ባልሆነ ነገር የተተበተበውን አእእምሮሽን ቀስ ብለሽ ፍቺው።" አለና ፊቱን ወደ መስኮቱ አዞረ። ኮረዳዋ ግራ በተጋባ ሁናቴ ባሩክን ትመለከተው ጀመር። ለብዙ ደቂቃዎች በሁለታቸው የነበረውን ዝምታ ለመስበር " በጣም ይቅርታ! ይሄን ያህል ካስከፋውህ?" አለች ባሩክ ፈገግ አለና " ኧረ እህቴ እኔን አላስከፋሽኝም እኔ በሰዎች ጥሩ ያልሆነ አመለካከት ወይም ጥሩ ያልሆነ አተያይ አልበሳጭም በመነፀራቸው ግን እበሳጫለሁ። የሚያዩበትን የሚያስተውሉበትን መነፅራቸውንም እተቻለሁ። አንቺም ላይ ያደረኩት ይህንኑ ነው እንጅ በአንቺ ተናድጄም ተከፍቼም አይደለም! በዛ ላይ እኔ ለእራሴ ለመናደድ ካልፈለኩ በቀር አልናደድም ማንም ሰው እኔን የማነደዱ መብትም ብቃትም የለውም" አለ። ዝም አለች በተናገረችው ነገር ሳታፍር የቀረች አትመስልም። ባሩክ መፅሀፉን ገለጥ አደረገ። ካቆመበትም ማንበቡን ቀጠለ። ይቀጥላል .... @Lboledoch ለአስተያየት @adwa1888
إظهار الكل...
👍 2
ለው ጥያቄ ጥያቄውን ማዳመጥ የማይችል ልብ ዝም ብሎ ይመታል። ልቡ ባሩክ የሚለውን ጥያቄ ማዳመጡን ትቶ ይመታል። ለትንሽ ጊዜ ራሱን ቆም ብሎ ካስተካከለ በኋላ ጉዞውን ቀጠለ የሕብስት ሆቴል መግቢያ በር ጋ ሲደርስ ግራ ገባው። ቤቱ በተለያዩ ዲም ላይቶች አጊጧል። በዝግታ ወደ ውስጥ ቀስ እያለ ገባና የሆቴሉን የእንግዳ መቀበያ ቦታ ካለፈ በኋላ ቆም ብሎ ግራ ቀኙን አማተረ ምንም ሰው የለም። ትንሽ ከተራመደ በኋላ ወዲያ ማዶ የተወሰኑ ልጆች ክብ ሰርተው ሲጫወቱ ተመለከተ። ወደ እነሱ እየተጠጋ ሲሄድ ናሆምን ተመለከተው። አጠገቡ ያሉትን ሴቶች በተራ ለያቸው። መቅደላዊት ላይ ፈዝዞ ቀረ። ሁሉም ባሩክን አልተመለከቱትም እሱ ግን እያያቸው ነው። ሁሉም እየተጫወቱ ነው። ድንገት የሆነ ነገር ተወራና መቅደላዊት አይኖቿን ጨፍና በረጅሙ ሳቀች። በበረሃ እንደጠወለገች እንኮይ ምንጭ የደረቀባት ተክል ፣በፀሀይ እንደጠነዘለች ፅጌሬዳ አበባ መስላለች። ስትስቅ ውበቷ ጎልቶ ይታያል። " ውብ " አለ ባሩክ በለሆሳስ። መቅደላዊት ሳቋን ቀነስ እያደረገች አይኖቿን ገለጥ አድርጋ የሳቅ እንባዋን እየጠራረገች ፊቷን ዘወር ስታደርግ ባሩክ እየተመለከታት ነው። "ባሩክ " ብላ ጮኸች እነ ናሆምም የመቅደላዊትን የአይን አቅጣጫ ተከትለው አፈጠጡ ባሩክ ቆሞ ነበር። መቅደላዊት ተነስታ ተንደረደረች ሩጫዋ ለጉድ ነበር በፍጥነት ካልሮጠች ከፊቷ የሚሰወርባት መስሏት ወንበሩን እየረጋገጠች ሮጠች። ደርሳ ተጠመጠመችበት እቀፋት እግሮቿን አጥፋ ወገቡ ላይ ወጥታ ቀረች። እዛው ወገቡ ላይ ሆና እያገላበጠች ትስመው ጀመር። አንገቱን፣ ጆሮውን፣ አይኑን፣ ጉንጩን፣ አገጩን፣ ከንፈሩን፣ ትከሻውን፣ ፀጉሩን እየቀያየረች ሁሉንም ከሳመችው በኋላ ከእንደገና እነዚህን የሰውነቱን ክፍሎች ደግማ ትስመዋለች። ለብዙ ደቂቃ ያህል እየሳመችው እንባዋ ይወርድ ነበር። አትናገርም ማልቀስ ብቻ። ባሩክ ትንፋሿን እንደ ናርዶስ በፍቅር ያሸተው ነበር። ጠረኗ ናፍቆት ነበር ይህን ጠረኗን ለማሽተት እየቀረበ ሲሄድ ነበር ልቡ ያለ ቅጥ ሲመታ የነበረው። በዚህ ምክንያት ነበር። ወደ ዘሐህ የናርዶስ ሽታ እየቀረበ ሲሄድ ነበር ሲፈራ የነበረው ። ሁሉም ጥያቄዎቹ ተመለሱለት። ከእቅፉ እንዳለች በደንብ እያቀፋ ይስማትና ያያት ነበር። መቅደላዊት ምንም ትንፍሽ ሳትል ስሜቷን በእንባዋ ብቻ ስትገልፅ ነበር።እነ ናሆም ሜላትና ዮርዳኖስ የነ ባሩክንና ሁናቴ በልቅሶ እያዩአቸው ነው። ሁሉም ያለቅሳሉ። ናሆም ሆዱ ባር ባር አለው እንባውን ጠረጌ አደረገና እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ " አመሰግንሀለሁ አምላኬ ሆይ እኔን ኤድለኛ አድርገኸኛልና ምስጋናየ ይድረስህ " አይኑ ላይ ያለውን እንባ ከእንደገና አበሰና ሜላትንና ዮርዳኖስን አቀፋቸው። እንዲቀመጡ አደረጋቸውና አንድ ላይ ተቀመጡ። ሁሉም ነገር ከቃላት በላይ ሆነባቸው። ሁኔታውን ዝምብሎ ከመመልከት ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም። ባሩክና መቅደላዊት ለአምስት ወር የተለያዩ ሳይሆን ለአምስት አመት የተለያዩ ፍቅረኛሞች ነበር የሚመስሉት። እስካሁን አልተላቀቁም መቅደላዊት ከብዙ ቆይታ በኋላ ከወገቡ ላይ ወረደችና አንገቱ ላይ ተጠግታ " ባትመጣ ልመጣ ነበር ካለ አንተ መኖር እንደማልችል አምኛለሁ የኔ ጌታ " አለች በተሰረቀረቀና በሰለለ ድምፅ። ባሩክ " እኔም የሆነ ነገሬ ጎድሎኝ ነበር በነፃነት ማሰብ አልችልም ነበር። በነፃነት የማስበው ደግሞ በአንቺ እንድሆን ሆኛለሁ።" አላት መቅደላዊት አቀፈችው። ባሩክም አቀፋትና ወደነ ናሆም ይዟት ተጠጋ። እነሱ ጋ ሲደርሱ መቅደላዊት ባሰባት ባሩክን ልትለቀው አልቻለችም። ሁሉም እየተንሰፈሰፉ ያይዋት ነበር። የመቅደላዊትን ስቃይ በደንብ ያውቁና ያዩ ስለነበር በሁኔታዋና በድርጊቷ አልተገረሙም እንደውም በጣም አዝነው ነበር።ባሩክ አቅፏት ተቀመጠ። አይኖቹን እያየች ፂሙን እያሻሸች ጠረኑን እያሸተተች ትስመዋለች። ከብዙ ቆይታ በኋላ መቅደላዊት ከባሩክ ጭን ተነስታ ናሆምን አቀፈችው። እያለቀሰች " አንተ ያደረክልኝን ነገር መቼም አረሳውም እናንተ ወንድሜና እህቶቼ ናችሁ ሜሊዬ ዮርዲ በጣም ነው የምወዳቸው። ያለፈውን አስቀያሚ ጊዜየን አብራችሁኝ ነበራችሁና እጅግ አድርጌ ነው የማመሰግናችሁ። እናንተ ከምንምና ከማንም በላይ እኔን አስቀድማችሁ ስታደርገለልኝ ነበር።" አለች ሜላቴሜ ሆነ ዮርዲ ከማልቀስ ውጪ ምንም የመለሱላት ነገር የለም ናሆም ዝም ብሎ የምትናገረውን አቋርጦ አቀፋት። ባሩክ አኔገቱን አቀርቅሮ ሁሉንም ካየና ከሰማ በኋላ ተነስቶ ሁሉንም በተራ አቀፋቸው ናፍቆቱ ምን ያህል እንደኘበር እየገለፀ። በመጨረሻም ሁላቸውም ተቀመጡ ለተወሰነ ደቂቃ ይህል ዝምታ ሰፈነ። መቅደላዊት የባሩክ ደረት ላይ ጋደም አለች። ባሩክ ፊት ለፊት ላይ ሲመለከት በዲም ላይት ከለር " እንኳን ደህና መጣህ ባሩክ ኢትዮጵያዊው ዲዮጋን " የሚል አነበበ የናሆም ስራ እንደሆነ ገባውና ፈገግ አለ። " በምን ጊዜ ነው እንደዚህ ስትዘጋጅ የነበረው? በጣም ደክመሀል እኮ " አለው ባሩክ ናሆምን ወደ ዲም ላይቱ እያሳየው። ናሆምም ዲም ላይቱን አየውና ሳቅ ብሎ " ያው እንዲሁ ዲያስፖራ ከምንቀበል ብዬ ነው። በዛ ላይ እንዲህ እንድናደርግ የአሜሪካ መንግስትም ጫና አሳድሯል። " አለ ባሩክ ፈገግ አለና አይ የሚገርም ነው። ይህን ሁሉ ወጪ በተማሪ አቅም ይከብዳል እኮ መቸገር አልነበረብህም እንዲሁ የሚያንስብኝ ሆኖ ነው አሁን ለእኔ? " አለ ባሩክ " እሱን እንኳ ተወውማነስና መብዛቱን ግን ይሄን ሁሉ ወጪ እኔ አይደለሁም ያወጣሁት ዶክተር ወንድማገኝ ነው። ከመጀመሪያው ጀምሮ አብሮን ሲደክም ነበር በኋላም ከኪሱ አውጥቶ ነው ይህን ሁሉ ያደረኩት።" አለ ናሆም ።ባሩክ ራሱን ነቀነቀና" ህም ዶክተር ወንድማገኝ" ብሎ ዝም አለ። ከዛ በኋላ ባሩክ ከነ ዮርዲና ከነሜላትም ጋ የባጥ የቆጡን ሲያወራ ከቆየ በኋላ እራት በልተው ወይን አንድ ላይ ጠጥተው። ወደየ ማደሪያ ሩማቸው ጋ ሄዱ ። መቅደላዊት ና ባሩክ ናፍቆታቸውን በጥሩ ሁኔታ ተወጡ ።እየተሳሳሙና ፍቅር እየሰሩ አደሩ። ፀሀይን መቀስቀስ የሚወደው ባሩክ 12:00 ላይ ከእንቅልፉ ተነስቶ ፀሀይ የምትወጣበትን ስአት ይጠባበቅ ነበር። መቅደላዊትም ወደ 12:30 ላይ ነቅታ ጡት ማስያዤዋን ከደረገች በኋላ ሰፋ ያለ ቁምጣ ለብሳ ባሩክ ወደተቀመጠበት ስፍራ ሄደች። ከኋላው ስታቅፈው። " መቅዲ ነቃሽልኝ እንዴ?" አለ ባሩከ አኔገቱን ወደ ኋላ እየጠመዘዘ እዛው አንገቱን እንዳዞረ ከንፈሩን ሳም አደረገችውና አወንታዋን በራሷ ነቅንቃ ገለፀችለትና ። "ህልም ከሚመስል እውነት ትላንት ነቃሁ። " አለች። ባሩክ ለማለት የፈለገችው ስለገባው ዝም አለች። እንዲህ እያወሩ ፅሀይ ቀይ ሰጋጃዋን ዘርግታ ወጣች። በፈገግታ ተቀበላት መቅደላዊትም አብራው ፈገግ አለች። ፅሀይን ካስወጡ በኋላ መቅደላዊትን ሲያያት ከእንደገና ልዩ ሆና ታየችው አቅፏ አልጋው ላይ አስተኛት እያገላበጠም ሳማትና ቁምጣዋን አውልቆ ተከመረባት። የንጋት መነሻ ወሲብም አደረጉ በፍቅር አብረው የተነፋፈቁ ትንፋሾች በአንድ አፍንጫም ተነፈሱ። በመጨረሻም ልብሳቸውን ለብሰው ወደ ሬስቶራንቱ ወጡ። እነ ናሆም ቀድመዋቸው ደርሰው ነበር። እሽ እንዴት አደራችሁ ተባብለው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ተቀምጠው ቁርስ አዘው አንድ ላይ በልተው እየተጫወቱ እያለ። የናሆም እናት ደወለች። " አቤት እማ ደረሽ እንዴ " አለ " አዎ ደርሻለሁ " አለችው ናሆምም ያሉበትን የሆቴል አድራሻ ነግሯት ስልኩን ዘጋው። " እንዴ ማዘር መጡ?"አለ ባሩክ " አዎ ወንድሜ ባሩክን ማግኘት አለብኝ ብላ መጣች። እንግዲህ እ
إظهار الكل...
ኔ እምቢ አትምጭ ብዬ መንገድ አልዘጋ " አለ ናሆም ገና ከመጀመሪያው ባሩክን ወቀሳ ለመቋቋም እንዲህ ሲሊው ባሩክ ምን እንደሚለው ቀድሞ ስለተረዳ ።ባሩክ ራሱን እየነቀነቀ " እዚህ ድረስ መንገላታት አልነበረባቸውም አይይ " አለ። " ተዋት ትምጣ ባክህ በዛውም ይሄን የመሰለ አገር ታያለች።" አለ ናሆም ። " ቢሆንም በዚህ መልኩ አልነበረም " አለ ባሩክ። ባሩክ ዶክተር ወንድማገኝ ይመር ያደረገለትን ነገር ለማመስገን ስለፈለገ ቢሮው ድረስ ሄደ ላደረገለት ነገር እጅ ነሳ አመሰገነ። ቅኑ ዶክተር ወንድማገኝም ያደረገው ነገር ቀላል እንደሆነ በትሁት አንደበቱ ነገረው። ባሩክም " ዶክተር እርሰዎ ከሚጠበቅበዎት በላየሸ ዝቅ ብለዋል። እንደ ኤርሰዎ አይነት ሰው ማግኘት ይከብዳል። ከእርሰዎ የተማርኩት ነገር ብዙ ነው። እርሰዎን መሆን መታደል ነው። ዝቅ ብሎ ወደ ተማሪው የሚሰራ የሚያዳምጥ የአስተዳደር ሰራተኛ ያስፈልጋል። እርሰዎ ደግሞ ከዛም በላይ ከደረጃዎ ወርደው ረድተውኛልና በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ለመቅደላዊም ላደረጉላት ነገር በእኔም ስም አመሰግናለሁ ። ብሎት ዝቅ አለ " አይገባም " አለና ዶክተር " ይልቅ አንተ ጋ ተማሩ ያመጣችው ውጤት አመርቂ ነው እጅግ ሲበዛ ጎበዝ ናት በገባነው ቃል መሰረት አሁን ቪዛዋን እና አኔዳንድ ነገሮችን ታስጨርስና ስትመለስ አብረመችሁ መሄድ ትችላላችሁ በእናንተ በሁለታችሁ ትልቅ እምነት አለኝ በአለም አደባባይ ሀገራችሁንና ሰንደቀመችሁን ከፍ እንደምታደርጉ። ስለዚህ የሚጨረሰውን አብራችሁ ጨርሱ " ብሎት ተለያዩ። የናሆም እናት ባሩክን እንዳየችው " የኔ ልጅ ብላ አንተ ነህ " ብላ ሳመችው " አንተ የኔ ባለውለታ " አለችው። ባሩክ እንደ መቅለስለስ ርያለ " ኧረ እኔ ያደረኩት ነገር የለም ሁሉንም ነገር የልጅሽ መልካም ፈቃድ ቅን ልቦና ታግዞበት ነው። ልጅሽ ነው የአንቺ ባለውለታ " አለ " ቢሆንስ ከማን ጋ ውሎ ልጄን እንደሰጠኸኝ ፈጣሪ ጨማምሮ ይስጥህ" አለች " አሜን!" ተባረክ ብሩክ ሁን ለነገሩ ስምህስ ብሩክ የተባረከ ማለት አይደል ስምህን ነው የሆንከው። ስም በምግባር ላይ ታላቅ ተፅዕኖ አለው እንደሚባለው የአንተም ሰናይ ምግባር ከስምህ የተቀዳ ነው እና እደገልኝ" አለች " አሜን " ባሩክ አንገቱን ደፍቱ ምርቃቱን ይቀበል ጀመር። ሁሉም በአንድ ላይ ተቃቀፉ ዮርዳኖስ እና የናሆም እናት ሜላትና ናሆም መቅደላዊትና ባሩክ። ጠረንጴዛቸው ላይም አንድ ሞሰብ ቀረበ።የፍቅር ሞሰብ። " ይህ አንድ አመት ያልሞላ ታሪክ ነው ከእነዚህ ውብ የታሪክ አምባዎች ስር የተደረገ ታሪክ። የአድዋ ጀግኖች አፅም ላይ የትውልድ እጣፈንታ ሲበየን ፍቅር ይህ ነው። እዚህ ቦታ ላይ የተጀመረ ፍቅር መቋጫ እንደማይኖረው አምናለሁ ምክንያቱም። መሰረቱ የአያቶች የቃልኪዳን አጥንትና ደም ስላለበት። እኔ መቅደላዊትን አገባታለሁ ከእሷም ጋ እስከመጨረሻው እኖራለሁ እወዳተመለሁ አፈቅራታለሁ። እነ ናሆም ሜላትና ዮርዳኖስም ጋ ቤተሰብ እሆናለሁ እዚህ የጀመርኩት ታሪክ በሌላኛው የታሪክ ምዕራፍም እንዲቀጥል እፈልጋለሁ! አድዋ ዩኒቨርስቲ ዕውቀት ብቻ አይደለም የሰጠኝ እውነትን ታሪክን ባህልን ወግን የሀገር ፍቅርን እንዲሁም ነገን ነው። ከሁሉም ስጦታወች የመቅደላዊት ስጦታ ትልቃለች እሷ የኔ ነገ ናት። ወደ ጥልቁ የደስታ አለም የምታስገባኝ ስጦታዬ መቅደላዊት። መቅደላዊት እንዲህ የምትጥም ስጦታ ላደረክልኝ መንገዴ ናታኔምም ምስጋና ይግባህ እንኳንም ያን ጊዜ ለናሆም ጉዳይ ወዳቀዳችሁት ኦፕሬሽን ከመቅደላዊት ጋ አስተዋወከኝ። እንኳንም ያን ሁሉ ውሸት ዋሸተህ ለራስህ ለማድረግ ሞከርክ። አመሰግናለሁ መቅደላዊትን አብስለህ አብቅተህ ስለሰጠኸኝ!!!!!!!!" አለ ባሩክ መቅደላዊትን ትኩር ብሎ እያየ። መቅደላዊት ተጠናቀቀ!! :/// ይህን ድርሰት የፃፍኩት እኔ " አምባዬ ጌታነህ " @adwa1888 ነበርኩ!! ከመቅደላዊት ጋ ለነበረን ጊዜ አመሰግናለሁ !!! እያቆራረጥኩ በማቅረቤ ዝቅ ብየም ይቅርታ እጠይቃለሁ ያው ምክንያት እንዳለኝ ሆኖ! እናም ላሳያችሁኝ ተሳትፎና እና ለሰጣችሁኘ አስተያየትም ከልቤ አመሰግናለሁ!!!! በዚህ ድርሰት ላይ ሀሳብ አስተያየት ማንኛውንም ጥያቄም ሆነ ሂስ ካላችሁ በዚች አድርሱኝ @Nuhamin19 @adwa1888 በ "መቅደላዊት " ታሪክ ላይ አስተያየት ካላችሁ 👇👇👇 @Lboledoch Mekdelawitn mn yahlochachu wededachut kewededachut❤️
إظهار الكل...
" መቅደላዊት " ምዕራፍ ፪ ( ሁለት ) ክፍል ፵ ( አርባ ) በአምባዬ ጌታነህ ( @adwa1888 ) መቅደላዊት " የናሆም ዝግጅት ምን ይሆን?" በሚል የውስጥ ጥያቄ ታጅባ ፈተናዋን ጨረሰች ፈተናዋን የጨርሰችው ከስአት በመሆኑ አስራ ሁለት ስአት ገደማ ለናሆም ደወለችለት። ናሆም እንደጨረሰች ያውቃል። ነገር ግን ስልኳን አላነሳውም ስራ እየሰራ ነበር። መቅደላዊት ደግማ ደወለች። አሁን ባያነሳው እንደበቀደሙ ልትረበሽ እንደምትችል ስላሰበ ስልኩን አነስቶ ማውራት ጀመረ። " እሽ ጨርሻለሁ ምንድን ነው?"አለች መቅደላዊት በመጓጓት " ጥሩ እንኳን ደስ አለሽ። በቃ ዶርም ጠብቂያት ሜላት ትመጣለች። እኔ ጊቢ ውስጥ አይደለሁም " ብሎ ከመጨረሱ የመቅደላዊት ዶርም ተንኳኳ።ስልኩን አልጋዋ ላይ አስቀምጣ ዶርሙን ከፈተች። ዮርዳኖስ ነበረች። ከዮርዳኖስ ጋ ተሳሙና " ዮርዲየ ደህና ነሻ?" አለች መቅደላዊት " ደህና ነኝ መቅዲ " አለች ዮርዲ "ደግሞ አምሮብሻል" አለች መቅዲ ዮርዳኖስን በደንብ እያየች። " አመሰግናለሁ መቅዲ " አለች።በዚህም ጊዜ በሩ ተንኳኳ ። መቅደላዊት ከፈተችው። ሜላት ነበረች። "ዋው " አለች መቅደላዊት ሜላትን አይታ ሜላት ረጅም ቀሚስ ለብሳለች። አረንጓዴ ቢጫ ቀይን ጥለት ያደረገው ቀሚሱ የሜላትን ውበት አግዝፎታል። ሜላት አሁን በለበሰችው አለባበስና ልብስ እንኳን ወንድን የሴትን አፍ የሚያስከፍት ነው። ለዚህም ነው መቅደላዊት " ዋው " ብላ አፏን የዘጋችው " ምንድን ነው ዛሬ እንዲዝ ያማረባችሁ?" ብላ መቅደላዊት አንዴ ሜላትን ሌላ ጊዜ ዮርዳኖስን እያየች ጠየቀች። " ምንም በቃ ዝም ብለን ዛሬ ወጣ ብለን እንዝናና በሚል ሀሳብ ነው። እስከ መቼ ድረስ ተጨናንቀን በፈተና በሀሳብ። " አለች ሜላት ወደ ዮርዳኖስ እያየች። " አዎ ሜሊ ልክ ነች አልፎ አልፎ እንዲህ ወጣ ብሎ ጥሩ አየር መቀበሉም ትልቅ ነገር ነው" አለች ዮርዳኖስ የሜላቴን ሀሳብ አፅንኦት በመስጠትና የራሷንም ማብራሪያ በመጨመር። " እና አንቺም ልበሺ እና ባሩክ ማለቴ ናሆም ከተማ እየጠበቀን ስለሆነ " አለች ሜላት። መቅደላዊት ሜላት የባሩክን ስም ስትጠራ እንደመደንገጥ ብላ ነበር ነግር ግን ማለቴ የናሆም ስትል ሜላት ናሆም ለማለት ባሩክ እንዳለች አምና ያላትን ልብስ እንዲሁም ቆንጆ የሚያደርጋትን ልብስ ከሻንጣዋ መበርበር ጀመረች። መቅደላዊት ሞዴል ሆና ብዙ ጊዜ ስለቆየች የተለያዩ ልብሶችና አልባሳት አሏት። " እስኪ ኑና ምረጡልኝ ጓደኞቼ " ብላ ዮርዲንና ሜላትን እርዳታ ጠየቀች። ግብዣዋን ተቀብለው አብረዋት የሚያስውባትን ልብስ ማመስ ጀመሩ ። አኔዱን ልብስ ያነሱና የእሷ ደረቴ ላይ አድርገው እያዩ ከቀየሩ በኋላ ከስንት ፍለጋና ሙከራ በኋላ አንዲት ቀሚስ ተገኘች። ቀሚሷ አሁን መቅደላዊት ያለችበትን የሰውነት ክብደት ቅጥነትና ርዝመት ያማከለች በመሆኗ ከመቅደላዊት ጋ ልክክ አለች። " ይቺ አንደኛ!" አሉ ዮርዳኖስና ሜላት በአንድ ድምፅ። ሜላቴ በምርጫቸው ተስማምታ እሷም ወዳት ነበር ለብሳ አንድ ላይ ከዶርም ወጡ። ሶስት ሆነው ሲወጡ የተመልካችን አይን ይስቡ ነበር። በየ መንገዱ ዳር ብዙ ለከፋዎች ነበሩ ። " ሶስቱ ወንዶች የት ሄደው ነው?" " ሶስቱ ወንዶች እኛ እንሁን ወይ?" "እንዲህ አምሮባችሁማ ብቻችሁን እግዜርም አይቀበለውም። ........" የሚሉ ለከፋዎች ተሰነዘሩ። እነ መቅደላዊት ምንም ባለማለት ወጡ። አንዳንዶች ደግሞ መቅደላዊትን እንደዛ አምሮባት ሲያዩ " አየሀት አሁን ባለፈው ባሩክ ናፈቀኝ ጥሎኝ ሄደ ምናምን እያለች። ስታለቅስ እነበር። ሴቶችን አትመን ይሄው ያን ሁሉ ለቅሶ ረስታ ይሄ ሌላ ወኔድ ለማግኘት ነው እንዲህ ሽክ ብላ የምትወጣው። ሴት ልጅ አንዳንዴ የአዞ እንባ ነው ያላት። በፍፁም እንዳታምናት ምንም ቢሆን አትጎዳም። አየህ እሷን ምንም አልሆነችም ባሩክ ግን ከአገር አገር ተንከራተተ እሷን ለመርሳት ለመተው ላለማየት። እሷ ግን ረሳችው አየ ሴት " አለ ለጓደኛው። ** ባሩክ የናሆምን ስልክ እየጠበቀ ሩሙ ውስጥ ተቀምጧል። ትንሽ ወደ ራሱ መለስ ሲል የምትሳልበት መቅደላዊት ናት። አድዋ ከመጣ ወደ ሶስት መፅሐፍ አንብቦ ጨረሷል። ወደ ውጪም ብዙ ጉዳዮችን ወደ ሚማርበት ዩኒቨርስቲ ኢሜል አድርጓል። ከእህቱም ጋር በየቀኑ ነው ሲያወራ የነበረው። የናሆም እናት ባሩክ አድዋ እንደመጣ ናሆም ሲነግራት በጣም ተደስታ " ልጄ ባሩክን ማግኘት እፈልጋለሁ እና እሱ ጋ ልምጣ " ብላ ስትጠይቀው ናሆምም ደስ ስላለው " እሽ እማዬ ደስ ካለሽ ነይ ግን ባትደክሚ አሪፍ ነው ወይም ቤት ይዤው እመጣለሁ " አለ ናሆም " ብዙ ጊዜ ነው እንዴ የሚቆየው? " አለች የባሩክ እናት። ናሆም ይህን ጥያቄ ስትጠይቀው ባሩክ የሚቆይበት ጊዜ አጭር እኝደሆነ ትዝ አለውና " ውይ ረስቼው እማዬ አጭር ጊዜ ነው ያለው በቃ በፕሌን ነይ " አለ " እሽ ልጄ " አለች። ናሆም ደስ ብሎት ዝግጅቱን ማዘጋጀት ጀመረ። አብረውት በርከት ያሉ ልጆች ሆቴሉን እያዘጋጁ ነው። በዚህ ጊዜ ሜላት ደወለችለት። ስለኩን አነሳውና " ሜሊ ወደ መነን ሆቴል ሂዱና እዛ ዘና በሉ ትንሽ ቆይቼ እደውላለሁ " ብሏት ወደ ስራው ተመለሰ። መቅደላዊት ዮርዲና ሜላት መነን ሆቴል ተቀምጠው ኮካቸውን እየጠጡ ያወራሉ። ናሆም አብረውት ከሚሰሩት ልጆች ጋ ሆኖ ደፋ ቀና ይላል ጠረምጴዛውን እያስተካከለ ወንበሮቹንም በደንብ እያስቀመጠ። *** ባሩክ ግራ ገባው ናሆም እደውላለሁ ብሎት እስካሁን አልደወለም።ምን አስቦ ነው? ምን እያደረገ ነው።" አለና አይኑን ወደ ሰማይ ልኮ በዝምታ ተዋጠ። ባሩክ አላስችልህ ሲለው ለናሆም ደወለ። ናሆም ግን ስልኩን አላነሳም ነበር። ናሆም ደግሞ እነ ሜላትን እያወራ ነበር ። ናሆም እነ መቅደላዊትን ሲያዘጋጀው ወደ ነበረው ሕብስት ሆቴል ጠርቷቸው ተቀምጠዋል መቅደላዊት ሆቴሉን ለአፍታ ስትቃኘው ቆየች። ሆቴሉ በተለያዩ የኢትዮጵያ ነገስታት ፎቶ ያሸበረቀ እንዲሁም ኢትዮጵያዊነትን የሚገልፁ የተለያዩ ብሔሮች ልብስ እንዲሁም አገልግሎች ሞሰቦች የተለያዩ ከለር ያላቸው ሌማቶች ተሰቅለውበታል። ከሁሉም ግን "ዓድዋ የእኛነት ምስጢር " የሚል ፅሁፍ በሆቴሉ ቢም ላይ በፍየል ቆዳ ተፅፎ ተሰቅሏል። ከፅሁፉ በታች ፊታውራሪዎቹንና እቴጌ ጣይቱን አስከትሎ ምንሊክ ከነፈረሱ በትልቅ ሸራ ላይ ሰፍሯል። ቤቱ አስገራሚ ድባብ ያለው ቤቴ ነው።ታዲያ ከቤቱ ውበት በተጨማሪ እነ ናሆም ሆቴሉን አስውበውት ነበርና። ይሄ ሁሉ ውበትና ዲኮር ያስገረማት እንዲሁም ያሰደነቃት መቅደላዊት ተደንቃ ና ተገርማ ብቻ አልቀረችም ጠየቀች " ይሄ ሁሉ ሽር ጉድ ምንድን ነው? በሆቴሉ ውበት ላይ ሌላ ውበት?" አለች ። ናሆምም ፈገግ እያለ እንግዲህ በጥያቄ የሚጀምር ምሽትና ያማረ ምሽት እንድናሳልፍ ነው!" ብሎ መልሶላት ዘወር አለ። የሚጠጣና የሚበላ አዞ አብሯቸው ተቀመጠ። " አሁን በደንብ እናውራ " አለና ናሆም ተደላድሎ ተቀመጠ። ባሩክ ከላይ ግሬይ ሸሚዝ ከታች ያልደመቀ ጥቁር ሱሪ ለብሶ ረጅም ቡትስ ጫማ ተጫምቶ አንገቱ ላይ ስካርፕ ቢጤ ጣል አድርጎ ከያዘበት አልጋ ወጥቶ ወደ ሕብስት ሆቴል የሚወስደውን መንገድ በእግሩ ተያያዘው ። እነ ናሆም ደግሞ በጨዋታ ጨዋታን እየወለዱ እየተሳሳቁ ለፍቅራቸው ለወዳጅነታቸው ፅዋቸውን እያነሱ ጨዋታቸውን ማድራቱን ተያያዙት።ባሩክ ወደ ሕብስት ሆቴል አቅራቢያ ሲደርስ ልቡ በፍርሃት ራደ ተሰምቶት የማያውቀው ስሜት ተሰማው።ቆም አለና ልቡን ደገፍ አድርጎ " እንዴ ምን ሆኜ ነው? ለምንድን ነው እንዲህ ልቤ ያለቅጥ የሚመታው? " ሲል ራሱን ጠየቀ መልስ የሌ
إظهار الكل...
👍 4
" መቅደላዊት " ምዕራፍ ፪ ( ሁለት ) ክፍል ፴፱ ( ሰላሳ ዘጠኝ ) በአምባዬ ጌታነህ ( @adwa1888 ) "ለምንድን ነው እንደዚህ ያለኝ? ምን ሆኖ ነው ባሩክ? ምን ሆኖ ይሆን? ራስ ምታት ያዛት ባሩክማ የሆነ ነገር ሆኗል ለዛ ነው ይህን ሳምንት ሰውንቴን ያለቅጥ ሲሰማኝ የነበረው ። ምን ሆኖ ይሆን ራሷን በሁለት እጇ ግጥም አድርጋ ያዘችው። የታክሲው ረዳት " የመጨረሻ " የሚለውን መቅደላዊት አልሰማችውም ነበር። " ወጣቷ የመጨረሻ ነው እያልኩኮ ነው " አለ መቅደላዊት ከእንደገና ብርግግ ብላ " እሽ " አለችና ቀስ ብላ ራሷን ደግፋ ወረደች። ትንሽ ረፍት ካደረገች በኋላ በሌላኛው መስመር ወደ ዩኒቨርስቲ የሚመልሳትን ታክሲ ይዛ ተመለሰች። ጊቢ እንደደረሰች ለናሆም ደወለች። " አቤት መቅዲ " አለ " ናሆም ወደ ጊቢ ተመልሻለሁ ላገኝህ እፈሌጋለሁ!" አለች በቀዘቀዘ አነጋገር " አይ ዛሬ አይደለም የምንገናኘው ፈተና ሲያልቅ ነው!!" አለ ናሆም " በናትህ ናሆም ሳትደብቅ ንገረኝ ባሩክ የሆነው ነገር አለ? እ ምንድነው የሆነው እ? ናሆም ንገረኛ " አለች መቅደላዊት እያለቀሰች ። " ኧረ ምንም አልተፈጠረም መቅዲ ለሌላ ነገር ነው ለሌላ ዝግጅት ነው ባሩክ ምንም አልሆነም በቃ ቆይ መጣሁ ጊቢ መግቢያው በር ላይ ያለው ካፌ ጠብቂኝ " ብሎ ናሆም ደንግጦ የያዛውን ሀንድ አውት ጥሎ በፍጥነት ተነሳ። ናሆም ይሄን ስጋቷን ቀደም ብሎ አለማሰቡ አበሳጨው " ሆደ ቡቡ እንደሆነች እያወቅሁ ሌላ ዘዴ መፍጠር ነበረብኝ አሁን እሷ የሚመስላት የመሰላት ከፈተና በኋላ የምናረዳት ነገር እንዳለ ነው። ነገር ግን የምናረዳትም ነገር እንዳለ ሆኖ ግን የምናበስራት የሀዘን መርዶ ሳይሆን የደስታ ነው እኔ ያሰብኩት እሷ አሁን አስባ የተረበሸችበትን ሀሳብ ሳይሆን ከፈተና በኋላ ባሩክን እንድታገኘው ማድረግ እና በሩቅ ያሰበችውን በቅርብ እንድታገኘው ነው። ሌላ አላሰብኩም። ይሄ ያሰብኩትን ሀሳብ የምገልፅበት አንዳች ነገር ግን ሊኖር ይገባል የመጥፎ ጥርጣሬዋን ማስወገጃ መላ ግን ልዘይድ ይገባል " በማለት ከራሱ ጋር ያወራ ጀመር። ይሄን እያሰበ ናሆም የዩኒቨርስቲው መግቢያ በር ላይ ካለው ላውንች ደረሰ። መቅደላዊት ጉንጮቿ በእንባ ርሰዋል። አይኖቿ ቀልተዋል ፣ አፍንጫዋም ደም መስሏል። ናሆምን እንዳየች ተነስታ አንገቱ ስር ተወሸቀች እንዳዲስ ታለቅስ ጀመር። ናሆም በራሱ በጣም በሸቀ " ኧረ መቅዲ በማርያም አታልቅሺ አባቴ ይሙት አንቺ እነደምታስቢው አይደለም። መቼም አባቴ ይሙት ብየሽ እንደማልዋሽሽ ታውቂያለሽ። በሆነ ባልሆነውም አባቴ ይሙት አልልም። ስለዚህ በእናትሽ ተረጅኝ በቃ ምንም አልተፈጠረም ይሄ እኔ ደግሞ አትቁረጭ ያልኩሽ አንቺ የምትወጅውን ነገር ሀማድረጌ ነው የሚያስደስትሽን ነገር እኛንም የሚያስደስተንን " አለ ። መቅደላዊት ፊቷ ላይ ያለውን እንባዋን በሶፍት እያጠራረገች ለመረጋጋት ሞከረች። ናሆም በአባቱ ከማለ እውነቱን እንደሆነ ና በስህተት እንኳ ለምንም ነገር ብሎ በውሸት በአባቱ እንደማይምልም ታውቃለች። " እሽ ናሆም አምንሀለሁ። ምን ላድርግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በዚህ ሳምንት በተደጋጋሚ ያየሁት ጊዜ የለም ይህን ሳምንት ባሩክ በጣም ቀርቦ ነው የታየኝ እና አንተ ቅድም እንደዛ ስትለኝ ምን ላስብ በጣም ደነገጥሁ ጥሩ ያልሆነ መልዕክት ወደ አእምሮየ ገባ ለዛ ነው። እኔ ባሩክ ምንም እነዲሆን አልፈልግም " አለች መቅደላዊት " አውቃለሁ መቅዲ ግን ደግሞ እንደዚህ አይነት እሳቤ መልካም አይደለም። የምትወጅው ሰው በአንቺ እጅ አይደለም የሚጠብቀው ፈጣሪ ነው። ከአንቺ ስራ በላይ በሆነ ነገር ራስሽን መጥመድ የለበትም በቃ እሱን ፈጣሪ ይጠብቀዋል። አኔቺ ይሄን ያህል መጨነቅም ሆነ ማሰብሽ ረፍት አልባ ኑሮ ያደርግብሻል። ደግሞም በፈጣሪ ስራም አይገባም ። ስለዚህ መልካም ነገር ማሰብሽ ተገቢ ሆኖ እያለ ግን ደግሞ አለፍ ያለ ሀሳብም ጥሩ አይደለም። ደግሞም እንዲህ ቢሆንስ ኤያልሽ ከምታስቢ ጥሩ ጥሩውን ብታስቢ ለአንችም በጎ ነው ለሱም መልካም እድል መመኘት ነው።" አለ ናሆም መቅደላዊትን እያባበለ አይኖቿን በመዳፉ እየጠራረገ። " እሽ ናሆም ስላስጨነኩህ በጣም ይቅርታ " አለች " አይ ይቅርታማ መጠየቅ ያለብኝ እኔ ነኝ እንደዚህ እንድታስቢ በማድረጌና ባላሰብሽው ጊዜ በማለቴ " ብሎ አቀፋት መቅደላዊትም አቀፈችው። " እ አሁን ምን ትጠጫለሽ ወይስ የሚበላ ነገር?" አለ ናሆም ፈገግ እያለ መቅደላዊትም በስሱ ፈገግ አለች። ፈገግታዋ ከፅሌመት አለም የሚያስወጣ የብርሀን ፈገግታ ይመስላል። ስቴስቅ ፅሀይ በምትወጣበት ጊዜ ምዴርም ብቻም ሳትሆን ሰማይም እንደሚፈታና እንደሚፈካዉ ሁሉ የመቅደላዊትም ፈገግታ ከማለዳዋ ፀሀይ የማይተናነስ ወገግታ ነው። የናሆም ግብዣ ምንጩ ጥፋት እንደሆነ ማሰቡ እንደሆነ ስለገባት " እሽ ስፕራይት ልጠጣ አዛዥ አንተ ብትሆንም ጋባዥ ግን እኔ ነኝ " አለች። ናሆም ሳቅ አለና " ምነው ብር አለኝ ትኬት ልቆርጥ ነበር አልሽ " አለ " አዎ እውነት ነው እኮ ታዲያ " አለች " እና እኔ ባሰብኩት እኔ ባዘዝኩት ነው አንቺ ምትከፍይው ምን አይነት ንቀት ነው። ነው አንተ ብር የለህም ነው " ብሎ ሳቀ ። " አልወጣኝም በቃ እሽ ትከፍላለህ ምን አይነት ጊዜ ነው ልክፈል ማለት ሆሆሆ " አለችና መቅደላዊት የፈገግታውን አፀፋ በፈገግታ መለሰችለት። ናሆምና መቅደላዊት እንዲህ እየተሳሳቁ ያለፈውን እኔደመርሳት አድርገው ናሆም ኮካ መቅደላዊት ደግሞ ስፕራይት ጠጥተው ናሆም ሂሳቡን ከፍሎ ወጣ። ተቃቅፈው ወደ ላይ ወጡ። ናሆምም እሷን ወደ ዶርሟ የሚያስገባው መገንጠያ መንገድ ላይ ተሰናብቶ ወደ ዶርሙ ሄደ። **** ባሩክ አድዋ ላይ ከትሞ መቅደላዊትን የሚያገኝበትን ቀን እየቆጠረ ነው። ብቻውን ስለሷ ያሰላስላል። "መቅደላዊት የፍቅር የርህራሄ ሁሉ ጥግ ናት እሷን ማፍቀር መታደል ነው። ስትስቅ ጠፈርን ታደምቃለች አእምሮዋ የዘመኑን የስነፈለክ ተመራማሪዎችን ያስንቃል። እሷ ልክ እንደ እነ ኢትዮጵያዊቷ ልዕልት አንድሮሜዳ እንደ ኢትዮጵያዊ ንጉስ ሴፊወስ እንደ ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ካሴዮፕያ ኮከብ ሊመራላት ይገባል። ስታወራ አንጀትህን ታርሰዋለች የውስጥህኔ ትረዳዋች ቀፈገግታህ በአይኖችህ በዝምታህ ውስጥህ ላይ ያለውን አለም ትረዳዋለች። ምንም ሳትናገር አይኖችህን ብቻ አይታ መፅሀፍ ሙሉ ስለ አንተ ትፅፋለች። እሷ ከሁሉም የዘመናቼኔ ሴቶች ትለያለች። እሷ ብቻዋን የፍቅር ከተማ ናት ልክ እንደ ፓሪስ። አሁን ላይ ግን ደስታዋን ሸርሽሬዋለሁ። ግን እኔ ምን ላድርግ መቅደላዊት የደስታዋን ጠርዝ ያገኘች መስሎኝ ነበር። በናታኔም የምትደሰት መስሎኝ ነበር። እኔን ከመጤፍም አትቆጥረኝም ብየ ነበር። እኔን ድልድይ ለማድረግ ያሰበች መስሎኝ ነበር ከሷ የራኩት ። በእኔ ምክንያት እንደዚህ ትሆናለች የሚል እሳቤም አልነበረኝም። እኔ ሁሉንም ሳሌናገራት በዝምታ ያለፍኳት ዝምታየን እንድትሰማው እና እንድትረዳው እንጅ እንድትጎዳበት አልነበረም። ቢሆንም ግን እሷ የኔ ልክ ናት አሁን ያለፈው የትዝታ ሀይቅ ውስጥ ከማይታይ ከማልገልጠው ብራና ላይ አስቀምጨዋለሁ። አሁን እስከፈለገችኝ ድረስ አለሁ። እስከምትፈልገኝ ርዝመት ድረስ። የምሄደው በሷፍላጎት ብቻ ነው። እኔ የራሴ ፍላጎት የለኝም ፍላጎቴ ፍላጎቷን መሰረት ያደረገ ነው። አሁንም ያለፈውን እንደማትደግመው አሜናለሁ። ምክንያቱም ከችግርህ ለመዳንና ከስጋትህ ለመራቅ ያለህ ብቸኛ አማራጭ ማመን ብቻ ነው። ማፍቀር መውደድ ማመን ነው። ከተጠራጠርክማ ከሰርክ ሳትጠራጠር ከምትከስረው ተጠራጥረህ የምትከስ
إظهار الكل...
❤️ 2
" መቅደላዊት " ምዕራፍ ፪ ( ሁለት ) ክፍል ፴፰ ( ሰላሳ ስምንት ) በአምባዬ ጌታነህ ( @adwa1888 ) አውሮፕላኑ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ለማረፍ ወደ ሰማይ ሲቀዝፍ ያስገባቸውን ጎማወቹን አውጥቶ ፍጥነቱን በመቀነስ አኮበኮበ። ከብዙ ዝግጅትና ጥንቃቄ በኋላ አውሮፕላኑ ምድር ላይ አረፈ። መቐለ ውቧ ከተማ ከነባህርዳር ናዝሬት ሐዋሳ ጋር በጥራትም በንፅህናመም የተስተካከለች ድንቅ ከተማ። ነዋሪዎቿ እንግዳ ተቀባይ ናቸው።ብዙውን ጊዜ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክፍለሀገሮች ለመሄድ በመቀለ ናቸው መቀሌን ሳይደረስ አይሄድም። ምን አልባት በሀገር አቋራጭ ከሆነ ነው እንጅ በፕሌን መቀሌን ሳይነካ የሚሄድ የለም። የመቀሌ ነዋሪ ልክ እንደሌላኛው የኢትዮጵያ ክፍል ህዝብ አኗኗር አበላል እንግዳ ተቀባይነት ያየለበት ህዝብ ነው። ባሩክ መቀሌን እጅግ በጣም ይወዳታል። መሸሌን ሳይነካ ወደ አድዋ መሄድ አይፈልግም። መቀሌ ላይ የተወሰኑ ቀናትን ወስዶ ተዘዋውሮ ከተመለከታት በኋላ ነው ወደ ዓድዋ የሚሄደው።የያዛትን አነስተኛ ሻንጣ ጀርባው ላይ አዘለና በቀስታ ከፕሌኑ ወረደ። አጠገቡ የነበረችው ልጅ ተከተለችውና " እባክህ ወንድሜ ባሩክ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ስላልሆነ አንድ ነገር እንዳደርግ ያሰብኩትን ነገር እንዳደርግ እርዳኝ " አለች።ባሩክ ቆም ብሎ እንደማሰብ አደረገና " መጀመሪያ የምትይውን ልስማ?" አለ " ራት " ልጋብዝህ? " አለች ። ባሩክ ዝም አለ ለአንድ ደቂቃ ያህል " እ በቃ ራሴ ላይ ቅሬታ ስላለብኝ መካሻ እንዲሆን ብየ ነው " አለች። ባሩክ ፈገግ አለና " ግን ስለ እራት ግብዣ ምንነት ታውቂያለሽ? " አላት። ድንግጥ አለችና " ምን በቃ የተለየ ነገር የለውም ራት መብላት ነዋ!" አለች " አዎ እኔም በዚህ አስተሳሰብሽ እንደሆነ ራት ልጋብዝህ እንዳልሽኝ የገባኝ ለዛም ነው የጠየኩሽ፡ ለማንኛውም ራት ስትጋብዥ በጣም አስበሽ መሆን አለበት። አንድን ወንድ ራት ልጋብዝህ ስትይው ከእራት በኋላም ስላለው ነገር አስበሽ መሆን አለበት። ብዙ ወንዶችም ሆነ ሴቶች ስለ ራት ግብዣ ይጨነቃሉ ከአለባበስ ጀምሮ ከምንም ጀምሮ ያ ጭንቀታቸው ደግሞ አንዳች ቴርጉም ይሰጠናል። ትርጉሙም ከእራት በኋላ የሚኖረው ምሽትና አዳር ነው። ስለዚህ ግብዣሽን አስተካክይ እኔ ለእራት ግብዣ ለየት ያለ አመለካከትና ፍቅር ነው ያለኝ። እራት ሌላኛው የደስታየ መለኪያ መስፈሪያ እንቅብ ነው። ፍቅርን የምቋደስበት ከጨረቃዬ ጋ ከዋክብትን የምናሳጅብበት። አእዋፋትን የምንሰማበትን ዜማዎችን የምንቀዳበት። ትርጉም ያላቸውን ሹክሹክታችንን የምንሰማበት፤ በትንፋሽ የምንግባባበት፤ በፍቅር የምንሳሳምበት፤ ጊዜ ቢኖር ያ ነው። በዚህም መሠረት እራት ግብዣሽን ሳልቀበለው ቀርቻለሁ። እራትሽን እራት ለሚገባው ለእኔ ግን ፍላጎትሽ ብቻ አጥግቧኛል የይቅርታሽን ልክ ለክቼበታለሁ አመሰግናለሁ " አለና ፈጠን ፈጠን ብሎ ትቷት ወደ ታክሲዎች መቆሚያ አመራ። ልጅቷ እንደ ፀሀይ በሚያብረቀርቁት አይኖቿ ባሩክን ተከተለችው። ባሩክ ለመጨረሻ ጊዜ እንኳ ወደ ኋላ ሳይመለከታት መንገዱን ወደ ሰማዕታት ሀውልት አቅጣጫ ሄደ። **** ጥሩ ያልሆነውን ውስጧን በሙዚቃ ለማረሳሳትና ለማዝናናት የሙዚቃ ፋይሏን ስትጎረጉር የጂጂን ሙዚቃ አገኘች። የጂጂ ሙዚቃ ላይ ለደቂቃ ቆም አለችና ብዙ አሰበች። ከአሰበች በኋላ ከፈተቻት። በእርግጥ የከፈተችው ሙዚቃ ከትዝታዋ የሚያነቃት የሚያስወጣት ሳይሆን መልሶ የሚዘፍቃት ነበር። ጁጁን እንደ ባሩክ ሆና ለማዳመጥ ሞከረች። የምትለው ነገር ትንሽ ይከብዳታል። "ጂጂን ሊረዳት እና ሊያዳምጣት ሊሰማት የሚችለው ባሩክ ብቻ ነው። እሷን ከሱ ውጭ ምንም ነው " ብላ ታምናለች ትከራከራለችም። መቅደላዊት ። የጂጂ አቦሸማኔን፣ ገራገሩን፣ ሳላየው አላድርምን ሁሉንም በየተራ ካዳመጠች በኋላ የጀሯ ማዳማጫዋን ከስልኳ ነቅላ ወደ ኪሷ አስገባችው። " ፍቅር ግን ምን አይነት ሀይል ነው? እየወደድከው መኖ፤ እንደሚመጣም እንደማይመጣም ሳታውቅ መጠበቅ፤ እሱን መናፈቅ የሚያስችል ትልቅ መግነጢሳዊ ሀይል፤ ዋውውውው ይህ በጣም ይለያል። እኔ ለፍቅር እስረኛ ነኝ ፍቅር እንደፈለገ እያደረገኝ ነው። እያወራኝ ነው ብቻየን ሲፈልግም እያፈላሰፈኝም ነው። " አለችና መቅደላዊት ትኬት ለመቁረጥ ወደ አድዋ ከተማ ተነሳች። የፈተና ጊዜ ለመጨረስ አንድ ፈተና ነበር የቀረው። እሱ እንዳለቀ ቶሎ ወደ ቤተሰቦቿ ሄዳ እነሱ ጋ የተወሰነ ጊዜ በመጫወት ከዛ በኋላ ከእንደገና ወደ አድዋ መጥታ ወደ ውጪ ነው ለመሄድ ያቀደችው በዚህ ፕሮግራም ነው ለመንቀሳቀስ ያሰበችው። ***** ባሩክ መቀሌ ትንሽ ሲዟዟር እና ትንሽ ሲዝናና ከቆየ በኋላ ውሎ አዳሩን አድዋ ካደረገ የተወሰኑ ቀናትን አስቆጥሯል። ለናሆም ደወለ " አቤት ባሩክ ደህና ነህ? " " እኔ ደህና ነኝ ወዳጄ አንተ እንዴት ነህ ፈተና እንዴት ነበር?" አለ ባሩከ " ቆንጆ ነበር!" " መች ነው የምትጨርሱት?" አለ ባሩክ " እኛ ከ አራት ቀን በኋላ እነ መቅደላዊት ደግሞ ነገ ይጨርሳሉ።" አለ ናሆም " ኧረ ? ጥሩ አጋጣሚ ነው። ለማንኛውም አድዋ ነኝ እሽ ፈተናችሁን እንዳላዘናጋችሁ ብየ ነው እስካሁን ያልነገርኳችሁ። " አለ ናሆም ደስ አለው " እንኳን በሰላም መጣህ ወንድሜ እና የት ነው ያለኸው እንምጣ!" አለ ናሆም " አይ ፈተናህን ጨርስ ከተገናኘን ፈተና እንዳለብህም እረሳዋለሁ አንተም ትረሳዋለህ። ስለዚህ ጨርስና በሰፊው ነው ተገናኝተን ናፍቆታችንን የምንወጣው። " አለ ባሩክ " እ...ሽ እሽ ካልክ እንግዲህ " አለ ናሆም በባሩክ ሀሳብ ለጊዜውም ቢህን ተስማማ። ናሆም ባሩክን አውርቶ ከጨረሰ በኋላ ለመቅደላዊት ደወለ። መቅደላዊት በመጀመሪያ ጥሪ አነሳችው።" እጅሽ ላይ ኘበርጨስልክሽ መቅደላ?" አለ ናሆም ያነራችበትን ፍጠነት ስልኩ እጇ ላይ እንደነበር የገመተውን ግምት ልክ ለመሆን። " አዎ ጎግል እያደረኩኮ አሜሪካ ላይ የተሻለ የሚባለውን ዩኒቨርስቲ " አለች ናሆም ራሱን ነቅነቅ አድርጎ " ጥሩ አድርገሻል አሁን የት ነሽ? " አለ " እ አሁን ታክሲ ውስጥ ወደ ከተማ እየሄድኩ " አለች " እንዴ ፈተና ጨረሽ እንዴ ገና መስለሽኝ እኮ ነው?" አለ ናሆም ግራ ገብቶት ።" አይ ገና አልጨረስኩም ግን ከነገ ወዲያ ያልቃሌ ስለዚህ ትኬት ላላገኝ ስለምችል ቀድሜ ልቁረጥ ብየ ነው። ፈተና በጨረስኩ ማግስት ወደ ቤት እሄዳለሁ።" አለች " ኧረ ቆይ መቅደላዊት አትቁረጭ መጀመሪያ ከእኔ ጋር እንገናኝ የሆነ ነገር አስበናል እኔ አንቺ ሜሊና ዮርዲ እና እኛ ያሰብነው ደግሞ ከአንቺ ፈተና በኋላ ነው ያሰብነው። እና ትኬቱን አትቁረጭ በኋላ አላገኝም ይሞላል ብለሽ አስበሽ ከሆነ እኔ እቆርጥልሻለሁ። " አለ ናሆም " ማለት አልገባኝም ምን ዝግጅት ነው ያለው ነውስ ያልነገርከኝ ሌላ ነገር አለ?" አለች መቅደላዊት " ነይና እናውራ "ብሏት ስልኩ ዘጋ። መቅደላዊት ልቧ ከሁለት ተከፈለ። ይቀጥላል ........ @Lboledoch ለአስተያየት @adwa1888
إظهار الكل...
👍 1
Nuhamin: " መቅደላዊት " ምዕራፍ ፪ ( ሁለት ) ክፍል ፴፮ ( ሰላሳ ስድስት ) በአምባዬ ጌታነህ ( @adwa1888 ) ዶክተር ወንድማገኝ የፈተና ክፍሎችን እየተዘዋወረ ከጎበኘ በኋላ መቅደላዊትን አገኛት " ይሄ የማጠቃለያ ፈተና ሲመጣ ጥሩ ትዝታ እንደሌለሽ አውቃለሁ ቢሆንም ግን አንዳንድ ጊዜ ከነዛ መጥፎ ከሆኑ ትውስታዎች መራቅ በራሱ ራስን ማብቃት ነውና የባለፈው ፋይናል ላይ የተፈጠረውን ችግር አስታውሰሽ እንዳትረበሽ ፍፁም በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናሽን ስሪ! በተረፈ መልካም ዕድል" ብሏት ሄደ ። "እሽ ዶክተር በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ " አለች በፈገግታ " ምንም ችግር የለም አንቺ ብቻ አስደምሚኝ እንጅ ሌላው ነገር ቀላል ነው ። ከዛ በኋላም የምትፈልጊው ነገር እንዲደረግልሽ መጠየቅ ትችያለሽ " አለ ዶክተር " እንግዲህ የቻልኩትን አደርጋለሁ በተረፈ እግዚአብሔር ይጨመርበት! " " በይ በርቺ " ብሏት ሄደ። መቅደላዊት ውጤቱን ማምጣቷ እያጠራጠራት መጥቷል። በትክክል እያነበበች እንዳልሆነም ይሰማታል። ነገር ግን የቻለችውን እያደረገች ነው! እሷ ግን በዝግጅቷ እየረካች አይደለም። በዛ ላይ የባሩክ ናፍቆት ያናውዛታል። መቅደላዊት ከነ ብዙ ችግሯ ሆና ትምህርቷ ላይ ለማተኮር አማራጭ የሌለው ነገር እንደሆነ አስምራበታለች። መቅደላዊት የምታነበው ነገር ቶሎ ሲገባት ራሷን መጠራጠር ትጀምራለች። " እንዴት ለምን? አሁን ፈተና ላይ ይመጣል " የሚል ጥያቄ ራሷን ትጠይቅና በብዙ መልሶች ራሷን ታሻማዋለች። ይሄንን ችግሯንም ለዮርዳኖስ አማክራት የመለሰችላት መልስ " አንቺ በጣም ጎበዝ ና ፈጣን አእምሮ ስለሆነ ያለሽ ቶሎ ይገባሻል ስለዚህ ብዙ መገረም መጨነቅ የለብሽም አለቀ ፈተናው የሚመጣው አንቺ ከምታነቢውና ስታነቢው ቶሎ ከገባሽም ብዙ ቆይቶ ከገባሽም ጭምር ነው። ስለዚህ በማይሆን ጥያቄ ና ሀሳብ መስራት የሚችለውን አእምሮሽን አታጨናንቂው። ዝም ብለሽ አንብቢ በአንቺ ማንበብ ነው የውጪ እድልሽ የሚከናወነው " የሚል ነበር። ከዛን ጊዜ በኋላ የዮርዳኖስን ምክር ለመቀበል ብትሞክርም ሙሉ በሙሉ ግን ከጥርጣሬዋ ልትወጣ አልቻለችም። ቢሆንም ግን አሁን ላይ የተሻለ አቀባበል ነው ያላት። በዚህ ውጥንቅጥ መሀል ሆና ወደ ፈተናው አመራች። ናሆም ሜላትን " ሜሊ እኔ አሌቻልኩም መቅደላዊትን ሳያት እያፈርኩ ነው የሆነ ከባድ ነገር ነው የደበኳት በዚህ መሀል የሆነ ነገር ብትሆንስ እ? ፀፀቱን የምችለው ይመስልሻል ሁሌም ቢሆን ራሴን ስጠላው ነው የምኖረው ግዴለሽም የፈለገው ነገር ይምጣ ምርጫውን ለእሷ እንተወውና ልንገራት ነግረናት የራሷን ውሳኔ ትወስን? አይመስልሸም? እኔ አልቻልኩም እንዴ እሷን ሳገኛት የምታወራኝ ስለ ባሩክና ስለባሩክ እንዴት እሱን እንደምታገኘው እና ደግሞ ሰሞኑን የሆነ ነገር እንደተፈጠረ ስሜቷ ነግሯታል። ባሩክ እንደቀረባትና አብሯት እንዳለ ። እናም ውዴ በጣም ተጨነኩ ምን ላድርግ እሽ ግራ ገባኝ እኮ? አለ ባሩክ ፊቱ ክርትት እያለ " እረዳሀለሁ እኮ የኔ ማር ሳልረዳህ ቀርቼ አይደለም ህመምህም ያመኛል ግን ሳትነግራት ቀርተህ ከምትጎዳው በላይ ነግራሃት የምትጎዳው ስለሚበልጥ ነው። ስለዚህ አለመንገርህ ከመንገርህ አንፃር ጎልቶ ከታየ ይሄ ይሻላል ብየ ነው! በእርግጠኝነት ብትነግራት ወይ አዲስ አበባ ልሂድ ትላለች ወይም ደግም እዚሁ ይመጣል ጠብቂ ብንላት እንኳ ደህና ሆና የምትጠብቀው ይመስልሃል በቃ እሱን እያሰበች አታነብም።አሁን ግን ስላልነገርናት እሱን ለማግኘት አጥብቃ ትምህርቷን እያጠናች ፈተናዋን እየተፈተነች ነው ስለዚህ ካለችበት ጥሩ ማዕድ እንደማንሳት ስለሚሆንብን እንተዋት ጊዜው ሲደርስ ፈተናው ሲያልቅ ባሩክም ስለሚመጣ ያኔ ታውቃለች። ስታስበው ባሩክስ ፈተና መች ነው የምትጨርሱት ያለው ለምን ይመስልሀል? እ? ስለዚህ አይዞህ መጨረሻ ላይ ደስ ይልሃል እሽ የኔ ፍቅር " አለችና ከንፈሩን ቀስ አድርጋ ጎረሰችው። ሳብ አድርጎ እሱም አፀፋውን ሰጣት ደረቱ ላይ አቀፈና አጣደፋት ።ሜላት ለአመታት የተራበችው ፍቅረኛዋ እስኪመስላት ድረስ እያዟዟረች ሳመችው። ናሆም አቅፏት ተቀመጠ ጭኑ ላይ አስቀምጦ ሜላትን አግኝቷት እንደማያውቅ እያዟዟረ ሳማት እሷም የዋዛ አሌነበረችም። ብዙ ጊዜ ሜላት ለናሆም ፍቅሯን የምትገልጥለት በአሳሳሟ ነው! አይኖቿን ጨፍና አንድ ጊዜ ታችኛውን ከንፈሩን ሌላ ጊዜ ላይኛውን ከንፈሩን እያቀያየረች ትስመዋለች ትመጠዋለች በአኔዳች የሀሴት መንፈስ በአየር ሊይ የሚያቀዝፋት ይመስላታል። ከናሆም ከኔፈር የሚነጥላትን ምንም ነገር ትጠላለች አንድ ጊዜ እሱን መሳም ስትጀምር ሁሉም ነገር እንዲጠፋ ይሉኝታ ትዝብት የሚባሉ ነገሮች እንዳይኖሩም ትሻለች። ሜላት ናሆምን በደንብ ታፈቅረዋለች! ** ባሩክ ፕሌን ውስጥ ሆኖ አንዴ የያዘውን የ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት "the Ethiopian history " የሚለውን መፅሐፍ እያነበበ በሌላኛው ደግሞ አድዋ ሲደርስ ከመቅደላዊት ጋ ሊኖረው የሚችለውን የደስታ እና የመናፍቅ ስሜት እያሰበ ከምድር በውል ባልታወቀ ከፍታ ላይ እየበረረ ነው። አጠገቡ አንዲት ወጣት ቀይ ቆንጆ ተቀምጣ በዝምታ ትመለከተዋለች ከብዙ ተመስጦ በኋላ የአስተናጋጇን የምን ላምጣልህ ጥያቄ ለመመለስ ዘወር ሲል አጠገቡ ያለችው ቆንጆ እንደምትመለከተው አጤነ። በዚህን ጊዜ ፊቷን በደንብ ሲመለከታት የትግራይ ቆንጆ እንደሆነች አሰበ። በትንሹም ቢሆን በሚችላት ትግርኛ ሊተዋወቃት ስለፈለገ " ከመይ ደኃን ደኁ "አለ ልጅቷም ሳቅ አለችና ከአነጋገሩ ትግረኛ እንደማይችል እንዲሁም የሚችለውን ትግረኛ እንኳ የንግግር ለዛውን እንደማያውቀው አውቃ " ደህና ነኝ አንተስ እንዴት ነህ ትግረኛ ትችላለህ ?" ብላ እየሳቀች ጠየቀችው ባሩክም አለማወቁን ስላወቀችበት እንደማፈር ብሎ በእርግጥ ትግረኛ አልችልም ግን መልመድ እፈልጋለሁ እ ለዚህም እጥራለሁ የተወሰነም ቢሆን ለማወቅ ችያለሁ! " አላት " ጎበዝ ነህ አንዳንዶች እንደ አንተ አይጥሩም ማወቁ አይከፋም በቀላሉ ሰው ጋ ያላምድሃል ራስሄኔ ቀለልም ያደርገልሃል። እኔም እንደ አንተ የትግረኛ አለማመድ ነው አማረኛን የለመድሁት እናም ይሄው በደንብ አቀላጥፌ መናገር ችያለሁ አንተም ያለምንም መሰላቸት በደንብ ከተለማመድክ በትግረኛም ቅኔ ልትዘርፍ ትችላለህ " ብላ ሳቅ አለች " ኧረ ቅኔው ቀርቶብኝ ቀኔን በዘረፍኩበት " አለ ባሩክ " ወደየት እየሄድክ ነው?" አለችው ኮረዳዋ ቆኔጆ በደንብ ለማውራት ራሷን ለተለያዩ ጥያቄዎች እያዘጋጀች " አድዋ ነው የምሄደው " እ ? አድዋ ? አድዋ ዩኒቨርስቲ ?" አዎ ምነው ? " አለ ባሩክ ጥያቄዋ አስገርሞት " አይ ምንም እዛ ነው የተማርኩት አምና ነው የጨረስኩት " አለችው " ዋው ደስ ይላላ የኔ ሲኒየር ነሽ እኔ ሶስተኛ አመት እያለሁ ነው የተመረቅሽው " አላትና ባሩክ እባላለሁ " ብሎ እጁን ዘረጋላት " ማን?" ደግማ ጠየቀችው " ባሩክ " ደገመላት ። በአንድ ጊዜ ፊቷ ክስም አለ ገፅታዋ ተቀያየረ አይኗ በርበሬ መሰለ ።ባሩክ በሁኔታዋ ደነገጠ። " ምነው ችግር አለ እናት?" አለ ። ዝም አለችው ደግሞ ጠየቃት ዝም አለችው ።ወዲያው ሁሉም ነገር መጣላት...... ሼር @Lboledoch ለአስተያየት @adwa1888
إظهار الكل...
👍 7
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.