Our Side of the Story
الذهاب إلى القناة على Telegram
"To those who hurt and hunger” Since Oct 14, 2019 Here to help @DebbieTesfaye
إظهار المزيد1 683
المشتركون
-124 ساعات
+167 أيام
+330 أيام
أرشيف المشاركات
I love love honest writers. When you choose to write, a tad bit of vulnerability if not more is asked of you. ግን ከዛ ውጪ it’s about your vocabulary and how you express what you want to say. ሁሉም ኩልል ያለ እውነት አይደለም እንዲመስለን ይደረጋል እንጂ። Yes I’m very well aware fiction የሚባል ነገር እንዳለ እሱ አይደለም ነጥቤ።
አሉላችሁ አንዳንድ…their words storm to your heart and make themselves known of how honest they are. ተፈጥረው ቢመስሉም you can tell they come from the pits of the writer’s deepest corners. እኔ አልችልም እንደዛ መፃፍ or perhaps it’s something I’m learning to do. On my wrist 24/7 on duty የሆኑ ግብረገብ police officers አሉ…ኧረ እፈሪ እንደዚህ አይባልም የሚሉኝ። እያንዳንዷን ፅሁፌን እየሰነጠቁ ከዚህ ምን እንማር የሚሉ ጨቅጫቃ ተማሪዎች ደግሞ ጣቴ ጫፍ ላይ ይቆጠቁጡኛል። እኔ አስተማሪ ነኝ አልኩ? የ ተርም ክፍያ ተቀበልኩ? ልጣፍ ስለሚወዱ እንጂ። አንደኛው ተማሪ TikTok comment section’ኤ ስር “የማይጠቅመንን ነገር ባታሳዪን” ብሎኝ እንዴት እንደሳኩ፣ የሰው ልጅ አንድ label ከተሰጠው ከዚያ ውጪ መኖር አይችልም አይደል? ነውር ነው? ቀልደኞች።
ይኸው አሁንም እጅ እጄን እያሉኝ ነው፣ ምን ላስቀርላቸው እያልኩ እየተጨነኩ lmao. Go read a book or something ለዛሬ theme እና ነጥብ የለንም።
(a very mediocre attempt to become an honest writer, ድንቄም)
It’s been six years since I was 18, time has stretched and bled so much since then. I come back to Noah and John Mayer whenever I need to feel the bittersweet comfort of being 18 again.Today’s that day.
I discovered Noahዬ (my favourite coping mechanism) at 18, I remember wondering if it was allowed to be so vulnerable in a song. I could tell he was the “ምንድነው ምታካብዱት” dude from his songs, like he realised life wasn’t that deep before all of us and decided to write songs about it. I wished more people listened to him, even though I wanted him to be my little secret. People instantly became my favourite if they listened to him. I learned vulnerability from his little songs, that you didn’t need big words and metaphors to make something so magical as long as you truly felt and lived through it. I love how he grows more joyful and real through his albums. If nostalgia is your enemy but you still chase it, this is your song (artist lol).
I hate to admit that life has actually gotten to me, found my lil optimistic, live in the moment self trapped in jobs and responsibilities that I forgot to write, breathe and consciously do all the things that I love. ለካ the point is to find the melody of tizita amidst the chaotic rhythm of the life around you. Like speeding down the walks of people and tuning out their conversations just subtly enough so you wouldn’t go crazy. I’ve actually realised this a lot of times over the years but it’s something I’ll have to teach myself over and over again. ደግሞ ደጋግሞም አዲስ የሚሆንብኝ ይመስለኛል።
Third year I didn’t perform well in class, for a lot of reasons I’ve learned to give myself grace on. ጭንቅላቴ ሽንቁር ያለው ያህል ነበር የሚሰማኝ…literally.
A time when I realised, emotions እምብዛም ነገሮች እንደሆኑ እና ከ ፍቅር፣ ስሜት፣ ትካዜ፣ ደስታ ምናምን በላይ በ logic የሸበተ አፍንጫው ላይ መነፀር ደግፎ የሚዞር
አዐምሮ ተብዬ ለመኖር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ።
Reality from whatever hole your emotions sent you to እስክትወጡ አይጠብቃችሁም። እንዴ እንዲህ ሆኜ ነበር እኮ ምናምን ለ reality a big fat joke ነው።
To live sanely, I beg! find the balance between being in your little giddy days and those you should let the duo of reality and brain cells take over.
Be soft when you need to, have edges to protect your softness too.
May you realise you’re going the wrong way before you’re far too gone.
ከቀልባችሁ እንዲመልሳችሁ ከጅምሩም ቀልባችሁን እስክታጡት አትሁኑ። አሜን።
Third year I didn’t perform well in class, for a lot of reasons I’ve learned to give myself grace on. ጭንቅላቴ ሽንቁር ያለው ያህል ነበር የሚሰማኝ…literally.
A time when I realised, emotions እምብዛም ነገሮች እንደሆኑ እና ከ ፍቅር፣ ስሜት፣ ትካዜ፣ ደስታ ምናምን በላይ በ logic የሸበተ አፍንጫው ላይ መነፀር ደግፎ የሚዞር
አዐምሮ ተብዬ ለመኖር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ።
Reality from whatever hole your emotions sent you to እስክትወጡ አይጠብቃችሁም። እንዴ እንዲህ ሆኜ ነበር እኮ ምናምን ለ reality a big fat joke ነው።
To live sanely, I beg! find the balance between being in your little giddy days and those you should let the duo of reality and brain cells take over.
Be soft when you need to, have edges to protect your softness too :).
Yesterday’s commute to work was so bright. Ran into ሱቅ የተላኩ playful kids, the sun was a beautiful yellow, the trees were a soothing shade of green (I was also wearing green) , and ሾላ ነጋዴs were ready with their ዶሮs. In a very long time ያልተሰማኝ excitement filled my insides.
ደግ ደጉን ወዲህ፣ 2018።
እንኳን አደረሰነ🌻
Struggle እያደረገ፣ እርግብግቢቱ ከአቅሙ በላይ በሆኑ tragedies ለጋሉበት ሰው “አይዞህ ከእግዜር ተጠጋ፣ ፀልይ” ምናምን ማለት ነውር ነው የሚመስለኝ። እቺ እውነት ለ እኔና experience ላደረጓት፣ ለሚያምኑባት ሰዎች ብቻ ነዋ የምትሰራው። “I’ll pray for you” is my go to. የምችላት እሷ ሰለሆነች፣ ልብ ስብራት አስክሮት፣ ከማስከርም አልፎ አደንዝዞት ሰሙን ለረሳ ሰው አይዞህ ነውር ነው፣ ሊያበረታው? ቁስሉን ሊያደርቅ? እምነት እና ተስፋ ሊሰጠው? እንደውም መሳለቅ ይመስለኛል…እኔ የተሻልኩ ነኝ እያልኩ አይነት ነገር።
ሳቅፍ ጎበዝ ነኝ፣ ስቀልድ፣ ቀባጥሮ ነገር ማረሳሳት፣ ፊልም እና አልበም recommend ማድረግ ላይ። ሌላ ማፅናኛ እስክናገኝ “I’ll pray for you” እንላለን ፈቅደው ከእግዜር እንዲጠጉ ፣ guitar solo እና ሰበብ ሆኖ ብሶት እያላቀሰ የሚያስወጣ film recommend እናደርጋለን። በቃ።
From a buffet of topics to write and wail about “በእንጨትም አልነካው ኧረ” የምል የሚመስለኝ is romantic love፣ እንዲያ እንደ ጅል ቀን ሌት ጉሮሮህ ድምፅህ ጠጉርህ ምናምን እያልኩ እንዳላላዘንኩ ምፅ!
The things we outgrow are so bizarre. I was having a conversation about it with someone and mid conversation I realised that experiencing life’s different shades intensely besides romantic love lessened it’s significance for me. It’s not that I hate it (I hope so lol), just that I’d rather be more excited and inspired by literally anything else.
ምናልባት ደግሞ it’s the need to be in control. All the days I wrote about love, I witnessed my control slowly ebbing away in my words and I was a walking open wound liable for more damage. Random thoughts I can tailor however I want to, I shape and carve them however I want them to sound. ያኛው ሶዬ ግን፣ the words immediately go “sorry debs, boss is here” and turn their backs to tell on me. ፅፌ ካበቃሁ ኋላ ነው the deep water I’m in የሚታወቀኝ። Yeppp maybe that’s it. As usual psychoanalysis አይፈቀድም ቴንክስ :).
Repost from Brown Empire
Day 4
መስታወት መስታወቴ…
መስታወቴ ፊት ስቆም ሶስት ነገር አስባለሁ።
አንድ
እህቶቼ የምላቸውን የአክስቴን ልጆች። ትንሽ ሆነን ቃል የተገባባነውን “ሳገባ ሚዜዎቼ እናንተ ናችሁ’ን” የምርም አግብቼ ሚዜዎቼ እስኪሆኑ የቆዩትን።
መስታወቴ የነሱ ትዝታ አለው። (መስታወቴ የነሱ ነበር።) መኖር ያዘናጋኝና፣ ናፍቆት ብልጭ ያደረገልኝ ሰሞን እንደትልቅ እህት የወደቅኩ ይመስለኛል።
አለ አይደል መቼም የምንራራቅ፣ ብንራራቅም የማንጠፋፋ ይመስለኝ ነበር። እዚህኛው የህይወቴ ክፍል ውስጥ ያሉት ሰዎች ማናቸው ደግሞ ዱቼ እና ቀጮ ሲሉኝ የሆነ ግማሽ ህይወቴ ቻው ሳይለኝ እንደሞተ ያህል ይሰማኛል። ቢሆንም አሁንም ባዶ ቦታ ትቶ እንደመቀመጥ ያህል “ሰው አለ” ብዬ የተውኩላቸው በኋላ የምንሞላው ቦታ ያስቀመጥኩላቸው ናቸው። የማልተዋቸው በመኖሬ ውስጥ ትርጉም ሳፈላልግ አንድ ብዬ የምቆጥራቸው ናቸው።
እናወራለን እኮ፣ የቻት ግሩፕ አለን፣ ርቀት ያፈዘዘው። ምን እየሰሩ ይሆን በዚች ቅፅበት የሚለውን ማወቅ የነበረብኝ ግን የማላውቀው ነገር ልብ ልቤን ሀላፊነቴን በአለመወጣት ይገርፈኛል። ያኔ የተራራቅንባቸውን ዘጠኝ አመታት እንደመስስና እንደአዲስ ካችአፕ እንደራረጋለን።
ከልጆቼ በፊት ልጆቼ፣ ከእህቶቼ በፊት እህቶቼ ፣ከጏደኞቼ በፊት ጏደኞቼ ነበሩ።
ደግሞ እኮ ሁለት በምንም በምንም የምስማማቸው my partner in crime’s ነበሩ። መስታወቴ እና የለጠፍንበት ስቲከሮች እነሱን ያስናፍቀኛል።
*
ሁለት
ፊቴን አየዋለሁ። የሰላሳ ቤቱ ፊቴ ደስ ይለኛል። ቆንጆ ነበርኩ ግን I wasn’t always this beautiful. Millennials understand this glow። ዘመን እና እድሜን የምወደው ለዚህ ነው። ለራስ ብዙ ያውቃል።
beauty is often a fragile illusion, a delicate arrangement of creams, oils, potions, and routines. ቢሆንም ፊቴን ብዙ ጣጣ አላበዛበትም። አለ አይደል ሳልቀባባ እንዳልደነግጥ። ቤት ቤት ሰውዬ፣ ውጪ እመቤት ከመሆን መሀል መሆንን እፈልጋለሁ። በጣም ተቀባብቼ ከአማረብኝ አንዱን መቀባት የምጠርግ፣ ጆሮጌጥ ወይ የአንገት ጌጥ የምመርጥ ለዘብተኛ አጊያጭ ነኝ።
ከውበት ጋ እሰጥ አገባ አልፈልግም። ስንት ችግር በፈላበት ግዜ ከመልክ ጋ አታካራ “የአለ ምንም ምክንያት ነው ድንገት ተነስታ ራሷን የሰዋችውን” ያመጣል። በውበት በኩል የተጫነብንን ቀምበር እንደፆታ የምናውቀው እውነታ ነው።
የእውነት ቆንጆ የሆንኩ የሚመስለኝ ከወንድሜ ሚስት ፍሬ እና ከጏደኛዬ ሰሚራ ጋ ስሆን ነው።
ቁንጅናን ሲገልጡ ከእኔ ፊቸር ይዋሳሉ። እኔም እንደጥኡም ልብወለድ ፈገግ ብዬ ልቤም ስኪፕ እያደረገች እንሰማቸዋለን።
“አፍንጫዋ እንዳንቺ ስልክክ ያለ፣ ከለሯ እንዳንቺ ንፅት ያለ፣ ጠይምምም ፣ ፀጉሯ እንዳንቺ ጫካ… “ምናምን ይሉኛል ሰልሆነች አንዷ ቆንጆ ሲያወሩ። ሳል’ዋሽ ውበቴ የሚነገረኝ በነሱ አፍ ይመስለኛል።
ምርምር እንደሚሻ ሁሉ “ለካ ቆንጆ ነሽ” “ግን እኮ ታምሪያለሽ” ምናምን ሳልባል ስለውበቴ የሰማሁት ከነሱ ነዉ ወይንም ያመንኩት እነሱን ነው። እንደአፍሮዳይት የውበት መለኪያም ስለሚያደርጉኝ፣ መስታወቴ ፊት ስቆም አይኔን ከነሱ እዋሳለሁ።
*
ሶስት
የእድሜ መስመሮች
ማበብና ማማርም እንዳለ ሆኖ የህይወት ቀጣይ የምእራፍ ዳናዋም የሚጀምረው ሰላሳዎቹ ውስጥ እንደሆነ ይሰማኛል። ጆዉ ላይናችን ሞር ዲፋይንድ ይሆናል፣ ጉንጫችን ስር ያለው የሳቅ መስመር ደመቅ ይላል፣ አይናችን ስር በስሱ መነስነስ የጀመሩ የሪንክል ጉዝጏዞዎች ትናንት እንደነበሩ ሁሉ በዝምታ ቦታ ይይዛሉ … አለአይደል እንደኔ ከአላተኮራችሁባቸው የማታይዋቸው አይነት ሆነው።
የአርባዎቼ ጠዋት ላይ ላለመደንገጥ፣ ህይወት በኋላ ልታደምቃቸው ዛሬ በስሱ ንድፍ ያወጣችበትን ፊቴን እዳስሰዋለሁ።
Thirties are quietly magnificent, People might call this the polite excuse we whisper to avoid naming the inevitability of aging. I have friends who extremely glorifies reality, that don’t let me mascara my gray hair on my forehead which makes me more age conscious, and make me want to punch their throats lol and yes, sometimes I feel the pangs, ከመሬት ተነስቼ. But more often, I glide past it, letting the thought pass like a cloud across a sky I do not own.
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
