cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ፅርሀ አርያም

Yekechna ljoch

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
203
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖መጋቢት ፯ (7) ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞ ሰማዕትነት በቅዱስ ቴዎዶጦስ ሕይወት ✞ +*" ቅዱስ ቴዎዶጦስ "*+ =>በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ጊዜው ለክርስቲያኖች ሁሉ ፍጹም የመከራ ከመሆኑ የተነሳ "ዘመነ-ሰማዕታት" ሲባል በወቅቱ ከ47 ሚሊዎን በላይ ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈዋል:: +የዘመኑ ክርስቲያኖች ለመሞት የሚያደርጉትን እሽቅድምድም እያዩ አሕዛብ "ወፈፌዎች" እያሉ ይጠሯቸው ነበር:: (ዓለም እንዲህ ናትና!) እብዶቹ ጤነኞችን "እብድ" ማለታቸውኮ ዛሬም አለ:: (ለነገሩ "ግደልና ጽደቅ" ከሚል መመሪያ በላይ ጤና ማጣት አይኖርም) =>ታዲያ በወቅቱ አንድ #ቴዎዶጦስ የሚሉት ወጣት በምድረ ግብጽ ይኖር ነበር:: ወጣቱ እጅግ ብርቱ ክርስቲያን ነበርና እንደ ዘመኑ ልማድ ተከሦ በነፍሰ ገዳዮች ፊት ቀረ:: ክሱ አንድ ብቻ ነው:: "ክርስቶስን አምልከሃል" የሚል:: +ከሥጋ ሞት ለማምለጥ ደግሞ መንገዱ ያው አንድ ብቻ ነው:: ፈጣሪውን ክርስቶስን ክዶ ለአሕዛብ አማልክት (አጋንንት) መገዛት:: #ቅዱስ_ቴዎዶጦስ በገዳዮቹ ፊት ቆሞ ተናገረ:- " #እኔ_ክርስቲያን_ክርስቶሳ ዊ_የክርስቶስ_ነኝ:: ምንም ብታደርጉኝ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለዩኝ አትችሉም"(ሮሜ. 8:35) አላቸው:: +እነሱ ግን ነገሩ እውነት አልመሰላቸውምና ሊያሰቃዩት ጀመሩ:: *ገረፉት *አቃጠሉት *ደበደቡት *ሌላም ሌላም ማሰቃያዎችን በእርሱ ላይ ተጠቀሙ:: የሚገርመው ግን እሱ ሁሉን ሲታገሥ ገዳዮቹ ግን ደከሙ:: +በመጨረሻም ወደ ገዢው ዘንድ አቅርበው "ብዙ አሰቃይተነዋል:: ግን ሊሳካልን አልቻለም" በሚል ሰይፍ (ሞት) ተፈረደበት:: በአደባባይ ሊሰይፉት ሲወስዱት ግን ትንሽ አዘኑለት መሰል ጨርቅ አምጥተው "ፊትህን ሸፍን" አሉት:: (ያኔ ትንሽም ቢሆን ሰብአዊነት ሳይኖር አይቀርም) +ቅዱስ ቴዎዶጦስ ግን ገዳዮቹን በመገረም እየተመለከታቸው ተናገረ:- "እኛ ክርስቲያኖች ሞትን አንፈራም:: ሞት ለእኛ ወደ ክርስቶስ መሸገጋገሪያ ድልድያችን ነውና የምንፈራው ሳይሆን የምንናፍቀው ነው::" "ኢትፍርሕዎሙ (አትፍሯቸው)" (ማቴ. 10:28) +ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ጌታውን አመሰገነ:: ፊቱ ላይ ደስታ እየተነበበ ጨካኞቹ አንገቱን ሰየፉት:: በብርሃን አክሊልም ቅዱሳን መላእክት ከለሉት:: *መሠረታዊው ነገር ቅዱስ ቴዎዶጦስ ለምን አልፈራም? ነው:: +አጭር መልስ ካስፈለገን ቅዱሱ ያልፈራው ከልቡ ክርስቶሳዊ በመሆኑ ነው:: ትኩረት እንድንሰጠው የሚያስፈልገው ግን የሰማዕታት ምስጢራቸው:- 1.በጽኑ የክርስትና መሠረት ላይ መመሥረታቸው 2.ዕለት ዕለት የክርስቶስን ፍቅር መለማመዳቸው 3.ከወሬ (ንግግር) ይልቅ ተግባርን መምረጣቸው 4.በንስሃ ሕይወት መመላለሳቸው 5.ሥጋ ወደሙን የሕይወታቸው ዋና አካል ማድረጋቸው 6.ከእነሱ የቀደሙ ቅዱሳንን ዜና ሕይወት ከልብ ማንበባቸው 7.በቃለ እግዚአብሔር መታነጻቸው . . . መጠቀስ የሚችሉ መገለጫዎቻቸው ናቸው:: <+>" ዛሬስ "<+> =>ዓለማችን ከጠበቅነው በላይ ነፍሰ በላነቷ እየጨመረ ነው:: ዛሬ የክርስትና ጠላቶች ከጉንዳን በዝተዋል:: *የራሳችን ማንነት *ክርስትናችን በአፋችን ላይ ብቻ መሆኑ *እረኞችና በጐች መለያየታቸው . . . ሁሉ እኛ ልናርማቸው የሚገቡ ናቸው:: *አሸባሪዎች *አሕዛብ *የመዝናኛው ዓለም *ሰይጣን አምላኪ ዝነኞች (Celebrities) *ሚዲያው *ማሕበራዊ ድረ ገጾችና መሰል ነገሮች ደግሞ ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡና እኛን ውስጥ ለውስጥ በልተው የፈጁን የሰይጣን መሣሪያዎች ናቸው:: +ስለዚህም ከዛሬ ጀምረን ባለ መታወክ ክርስትናችንን ከአፋችን ወደ ልባችን: ከብዕራችን ወደ አንጀታችን እንድናወርደው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላለች:: +ዛሬ ነገሮችን ረስተን ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮችን ከጀመርን እጅግ አሳፋሪ መሆኑ አይቀርም:: በጐውን ጐዳና ተከትለን በሃይማኖትና በፍቅረ ክርስቶስ ከጸናን ግን ማንም ቢመጣም ፈጽሞ አንናወጥም:: +ይልቁኑ "አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን: ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው:: ስለዚህም ምድር ብትነዋወጥ: ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም::" (መዝ. 46:1) እያልን ከቅዱስ ዳዊት ጋር እንዘምራለን:: << ለዚህ ደግሞ ደመ ሰማዕታት ይርዳን:: በረከታቸው ይድረሰን:: የጌታ ፍቅርም አይለየን >> +*" ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ "*+ =>በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል:: በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው:: በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ነው:: +ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ግማደ መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው ፅዮን ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው:: በኢትዮዽያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን- *ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጉዋደል ይታትር የነበር:: *ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር:: *ወገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ:: *ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር:: +ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር:: በነገሠ በ3 ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል:: ከመቃብሩም ላይ ጸበል ፈልቁዋል:: =>ዘለዓለም ሥላሴ ደግ መሪና ሰላማዊ ዘመንን ያድሉን:: =>መጋቢት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ጻድቁ ኢትዮዽያዊ ንጉሥ ዐፄ ቴዎድሮስ 2.ቅዱስ ቴዎዶጦስ ሰማዕት 3.ቅዱስ ፊልሞን ሰማዕት 4.ቅዱስ አብላንዮስ ሰማዕት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) =>+"+ ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ:: ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና:: ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው:: ስለዚህ ባ ለሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል:: . . . ለሁሉ እንደሚገባው አስረክቡ:: ግብር ለሚገባው ግብርን: ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን: መፈራት ለሚገባው መፈራትን: ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ:: +"+ (ሮሜ. 13:1-8) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
إظهار الكل...
ከበረሐውያን ሕይወትና አንደበት ክፍል ፮
إظهار الكل...
1.49 MB
ከበረሐውያን ሕይወትና አንደበት ጥበብ ወምክር ዘአበው ቀደምት ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ እንደጻፈው። ፫.የፍትወት ጾር ስለሚያስነሣው ፈተና
إظهار الكل...
إظهار الكل...
የካቲት ፳ ፰ -28 የዕለቱ ቅዱሳን ታሪክ

✝✞ከኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ላይ የተገኙ የየዕለቱ የቅዱሳን አባቶቻችን እና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድል ይነገርበታል✝ በ you tube ማግኘት ለምትፈልጉ ሊንኩን ተጫኑት

https://www.youtube.com/channel/UCIY17WqQ1KxefebBlSH...

†††እንኳን ለታላቁ ሊቅና ጻድቅ ቅዱስ አንስጣስዮስ እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ አንስጣስዮስ ሊቅ ††† ††† ቅዱስ አንስጣስዮስ በ4ኛው ክ/ዘመን የተነሳ ሶርያዊ የነገረ መለኮት ሊቅ: ገዳማዊ ጻድቅና የመንበረ አንጾኪያ ሊቀ ዻዻሳት ነበር:: ቅዱሱ ርጉም አርዮስን ካወገዙ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: በወቅቱ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ሱባኤውንና ጉባኤውን የመሩ ሲሆን አንዱ ይህ ቅዱስ ነው:: ከ 5 ዓመታት በሁዋላም ብዙ ድርሳናትን ጽፎ: ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ፈጽሞ በ330 ዓ/ም አርፏል:: ያረፈው ግን አርዮሳውያን ባቀረቡት ክስ በሃሰት ተመስክሮበት በግፍ ተሰዶ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ስለ ውለታው የውዳሴ ድርሳን ጽፎለታል:: ††† አቡነ ዓምደ ሥላሴ ††† ††† እኒህ ታላቅ ጻድቅ ሐዋርያዊ አባት አቡነ ዓምደ ሥላሴ የትውልድ ሃገራቸው ጎጃም ሲሆን የተወለዱት በዚሁ ዕለት (የካቲት 27) ነው:: ጻድቁ በአጼ ሱስንዮስ (በ17ኛው መቶ ክ/ዘ) የነበሩ ድንቅ ሠሪ : ተአምረኛና ገዳማዊ አባት ናቸው:: የካቲት 16 ቀን መንኩሰው ወደ ተጋድሎ ገብተዋል:: በዋልድባ በነበራቸው ቆይታም እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት የካቲት 16 ቀን እንድትከበር ማድረጋቸውም ይነገራል:: ጻድቁ በሌሎች ገዳማትም የነበሩ ሲሆን ዛሬም ድረስ ረድኤታቸው የሚደረግበት : ስማቸው የሚጠራበት ገዳም ግን ማኅበረ ሥላሴ ይባላል:: ገዳሙ የሚገኘው በሃገራችን ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ : በመተማ በርሃ ውስጥ ነው:: ይህንን ቅዱስ ገዳም የመሠረቱትም ራሳቸው አባ ዓምደ ሥላሴ ናቸው:: ገዳሙ ዛሬም ብዙ ምሑራንና መናንያን ያሉበት : በደህና ሁኔታም የሚገኝ ነው:: ግን በርሃውን የኔ ብጤ ደካማ ሰው የሚችለው አይደለም:: ስለ ጻድቁ ዓምደ ሥላሴ ከሚነገሩ ታሪኮች ቅድሚያውን የሚይዘው የተዋሕዶ ጠበቃነታቸው ነው:: በ1603 ዓ/ም ዼጥሮስ (ፔድሮ) ፓኤዝ የሚባል ካቶሊካዊ እሾህ ወደ ሃገራችን ገብቶ ነበርና ንጉሡን ሱስንዮስን አባብሎ ተዋሕዶን አስካዳቸው:: ነገሩ ውስጥ ለውስጥ ሲበስል ቆይቶ በ1609 ዓ/ም በመገለጡ እነ ራስ ዮልዮስ ለሃይማኖታቸው ጠዳ ላይ ተዋግተው ግንቦት 6 ቀን ተሰው:: ይህ ነገር ሲሰማ ወንድ ሴት : ትልቅ ትንሽ ሳይመረጥ በገጠሩም : በከተማውም : በገዳሙም ያሉት ሁሉ የተዋሕዶ ልጆች መንቀሳቀስ ጀመሩ:: 7 ዓመታት እንዲህ አልፈው በ1616 ዓ/ም ግጭቱ በይፋ ተጀመረ:: "ተዋሕዶን ካልካዳችሁ" በሚል በቀን እስከ 8,000 ሰው በሰይፍ ታረደ:: ይህን ያደረጉት ደግሞ አልፎንሱ ሜንዴዝ : ንጉሡ ሱስንዮስና ጀሌዎቻቸው ነበሩ:: በጊዜውም ከቤተ መንግሥት እነ ንግሥት ወልድ ሰዓላ (የሱስንዮስ ሚስት) : ከጻድቃን አበው ዘርዓ ቡሩክ ዘግሺ : ሐራ ድንግል ዘደራ : ምዕመነ ድንግል ዘጩጊ : ዓምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ . . . ከቅዱሳት እነ ፍቅርተ ክርስቶስ : ወለተ ዼጥሮስ : ወለተ ዻውሎስ : እኅተ ዼጥሮስ . . . ለሃይማኖታቸው ተዋሕዶ ጥብቅና ቆመው ሕዝቡን አስተማሩ:: መከራም ተቀበሉ:: ብዙ ኢትዮዽያውያን የመከራ ጽዋን ተጐንጭተው ለክብር ከበቁ በሁዋላ የእግዚአብሔር ፍርድ ተገለጠ:: በጻድቃኑ እነ አባ ዓምደ ሥላሴ ሐዘን ንጉሡ ታመመ:: ምላሱ ተጐልጉሎ ወጣ:: በዚህ ጊዜ አቤቶ ፋሲለደስ ለአባ ዓምደ ሥላሴና ለሌሎቹ ቅዱሳን "አባቴን አድኑልኝ! ተዋሕዶም ትመለስ" አላቸው:: ጻድቁም ከባልንጀሮቻቸው ጋር ጸልየው ንጉሡን አዳኑት:: በፈንታውም ይህንን አሳወጁ:: ††† ፋሲል ይንገሥ! ሃይማኖት (ተዋሕዶ) ይመለስ! የሮም ሃይማኖት ይፍለስ! ††† ከዚህ በሁዋላ በ1624 ዓ/ም ፋሲል ሲነግሥ አባ ዓምደ ሥላሴ ለገዳማቸው ብዙ ቦታ አስከልለው : በተጋድሎ ኑረው በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን በቀናችው እምነት ተዋሕዶ ሁላችንም እስከ ፍጻሜ ዘመናችን ያጽናን:: ከበረከተ ቅዱሳንም ይክፈለን:: ††† የካቲት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ አንስጣስዮስ ርቱዓ ሃይማኖት (ዘአንጾኪያ) 2.አቡነ ዓምደ ሥላሴ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት 2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ 3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ) 4.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት 5.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ 6.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 7.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት ††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" ††† (1ዼጥ. 2:21-25) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
إظهار الكل...