ar
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

إظهار المزيد
601
المشتركون
-124 ساعات
-87 أيام
-1830 أيام
أرشيف المشاركات
🌼🌼🌼🌼🙏🙏🙏🙏🌼🌼🌼🌼 "ሰላም ለሥዕልኪ ሓፈ ማኅየዌ፥ በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሳዌ፥ ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ፥ ይኩነነ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵ
🌼🌼🌼🌼🙏🙏🙏🙏🌼🌼🌼🌼 "ሰላም ለሥዕልኪ ሓፈ ማኅየዌ፥ በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሳዌ፥ ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ፥ ይኩነነ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵሉ ምንሳዌ፥ ዓቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ኀላዌ፡፡ ትርጓሜ በጼዴንያና በግብፅ ያለ ሐሰት ፈዋሽ ወዝን ላፈሰሰ ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ቀራጭ ማቴዎስን ወንጌላዊ ያደረግሽው ማርያም ሆይ ጸሎትሽ ከጥፋት ዘመን ሁሉ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት ቋሚ ጠባቂ ይሁነን፡፡" ሰዓታት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 🌴🌴🌴🌴🌼🌼🌼🌼🌴🌴🌴🌴

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲ (10) ቀን። እንኳን #ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም #በፄዴንያ_አገር_በማርታ_ቤት ሥጋ የለበሠች ከምትመስል #ከእመቤታ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።            መስከረም ፲ (10) ቀን። እንኳን #ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም #በፄዴንያ_አገር_በማርታ_ቤት ሥጋ የለበሠች ከምትመስል #ከእመቤታች_ሥዕል ከሠሌዳዋ #ቅባት_እየተንጠፈጠፈ ተአምር ለሠራችበት ቀን መታሰብያ በዓል፣ #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን #ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ለተወለደችበት_ለልደቷ በዓል መታሰቢያ (ይህም የአስቄጥስ ገዳም የከበረ አባ መቃርስ በጻፈው መጽሐፈ ግጻዌ ተጽፎል እንዲሁም ደግሞ በላዕላይ ግብጽ በሚገኝ መጽሐፈ ግጻዌ የከበረች ድንግል እመቤታችን የከበረች ሐና በታኅሣሥ ወር በዐሥራ ሰባት እንደፀነሰቻትና መስከም በዐሥር ቀን እንደወለደቻት ተጽፍአል)፣ ለከበረች  ሰማዕትነት ለተቀበለችበት #ለቅድስት_መጥሮንያ_ሰማዕትነት ለተቀበለችበት በዓል ዕረፍት፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #የጌታችን_የአምላካችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ #ቅዱስ_መስቀል_ወደ_አገራችን_ኢትዮጵያ ድንበር ከደረሰበት (ተቀጽል ጽጌ) አፄ መስቀል) ቀን ለመታሰቢያ በዓልና ከከሀዲው #ሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ካዳነቻቸው ከጥበበኛ ከከበረች #ከቅድስት_ዮዲት በዓለ ዕረፍትና #ከቅድስት_አትናስያና_ሦስት_ልጆቿ_ከመታሰቢያቸው በረከትና ረድኤትን ያሳትፈን።                          "#ሰላምለ_ሥዕልኪ ሀፈ ማኅየዌ። #በፄዴንያ_ወኢትዮጵያ በአውኀዘት በኢሕሳዌ። ለመፀብሐዊ #ማቴዎስ_ማርያም እንተረሰይኪዮ ወንጌላዌ። ይኩነነ ወትረ ፀሎትኪ እምዘመነኵሉ ምንሳዌ። ዓቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ሀላዌ"። #መልክዐ_ሥዕል።

Repost from N/a
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፱ (9) ቀን። እንኳን በሮሜ_አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ #በመላእክት_አለቃ_በቅዱስ_ሚካኤል በስሙ በተሠራ ቤተ ክርስቲያን #ላ
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።             መስከረም ፱ (9) ቀን። እንኳን በሮሜ_አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ #በመላእክት_አለቃ_በቅዱስ_ሚካኤል በስሙ በተሠራ ቤተ ክርስቲያን #ላደረገው_ተአምር መታሰቢያ በዓል፣ ከኃላፊው #ከዚኽ_ዓለም_መንግሥቱ_መንኖ ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ኹኖ ለፈጸመ፤ የደረቀውን ግንድ ላለመለ፣ ለጽጌ፣ ለፍሬ ለአደረሰ ላሳየ እግዚአብሔርን ደስ ላሰኘ #ለንጉሥ_ለቅዱስ_ለአባ_ያሳይ ለዕረፍት በዓልና ለመጺል ለምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_ቢሶራ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ፋሲለደስ_ጋር_ዐሥራ_አራት_ሺህ_ሰባት መቶ #ሠላሳ_ወንዶችና_ሰባት_ሴቶችም በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ሰላም_ለአባ_ያሳይ_ብእሴ_ሰማይ፤ ለአምላኩ ቀናኢ፤ ሐራይ መዋኢ"። ትርጉም፦ ድል ነሺ ጭፍራ ለአምላኩ ቀናተኛ የሰማይ_ሰው_ለኾነ_ለአባ_ያሳይ ሰላምታ ይገባል።

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፰ (8) ቀን። እንኳን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ አባት ለበራክዩ ልጅ ለካህንና ለነቢዩ ለሆነ ለከበረ #ለቅዱስ_ዘካርያስ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።            መስከረም ፰ (8) ቀን። እንኳን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ አባት ለበራክዩ ልጅ ለካህንና ለነቢዩ ለሆነ ለከበረ #ለቅዱስ_ዘካርያስ_በንጉሥ_ሄሮድስ_እጅ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለእግዚአብሔ_ሰው ለሆነ፣ ለየዋሁ፣ ለቅኑ፣ ለጻድቁ፣ ለነቢያት አለቃ #ለቅዱስ_ሙሴ_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከከበረ_ቅዱስ_ዲማድዮስ ከግብጽ ደቡብ ደንጡ ከሚባ አውራጃ በሰማዕትነት ከዐረፈ፣ ምግቡ የአጋዝን ወተት ከሆነ በዕረፍቱም ጊዜ ብዙ ተአምራትን ከአደረገ ከከበረ #ከገዳማዊ_ከቅዱስ_ቂርቆስ ዕረፍት፣ #ከሰማዕቱ_ቅዱስ_ሉክዮስ ከመታሰቢያው፣ #ከቅዱስ_ኤርምያስና_ከቅዱስ_ዮሐንስ፣ #ከቅዱስ_አንዲዎና_ከቅዱስ_ኤልያኖስና ከመነኰስ #አሞንም_ከመታሰቢያቸወ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           በዚች_ቀን_የዓመቱ_ወሮች_መቊጠራያ የሚሆን የመጀመሪያ ኮከብ ይወጣ ይኸውም መናዝል የሚለው ነው የዐሥራ ሁለቱ ወር ኮከቦች ከእልሐመል እስከ ሑት ያሉ መገብተ አውኅራ አሉ ምግብናቸውን ፈጽመው በዚች ቀን እንደገና አንድ ብለው የሚጀምሩበት ነው።      "ሰላም_ለዘካርያስ_ካህን_ወነቢይ ዘርእዮ ለካህን ዐቢይ #ዘስሙ_ዮሴዕ ዘይነብር ውስተ ምሥዋዒሁ ለእግዚብሔር"። ትርጉም፦ በእግዚአብሔር መሠዊያ ውስጥ #ስሙ_ዮሴዕ የሚባል ታላቁን ካህን ተቀምጦ ላየው #ለካህኑና_ለነቢዩ_ለቅዱስ_ዘካርያስ ሰላምታ ይገባል።

Repost from N/a
photo content

Repost from N/a
✝ ታላቁም ጾም ሳይደርስ የፋርስ ሰዎች አፍረው ከእነርሱ ዘንድ ተመልሰው ሔዱ። ስለ ዮሐንስ አፈወርቅም ከኤጲስቆጶሳት ጋር በአመጡት ጊዜ ንግሥት አውዶክስያን በምክሩ ሁሉ መክሮዋትና ገሥጿት ነበር። ስለ ዮሐንስ መሰደድም እርሱ ምንም ምን ያደረገው ስምምነት የለም ንግሥቲቱም ምክሩን ባልሰማች ጊዜ ወደ አገሩ ተመለሰ። ✝ ብዙዎች ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደረሰ እሊህም ሃይማኖታቸው የቀናች ሰዎች በአሉባቸው አብያተ ክርስቲያናት እስከ ዛሬ ይኖራሉ። ቅዱስ ሳዊርያኖስም ሸመገለ ዕድሜውም መቶ ዓመት ሆነው ከሥጋውም ከመለየቱ በፊት በዐሥር ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት ከዚህ ዓለም ከድካምም ወደ እረፍት እንደ ሚወጣ ነገረው። ✝ ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ጠራቸው ክብር ይግባውና የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቅ ጸንተው እንዲኖሩ አዘዛቸውና በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ነፍሱንም በፈጣሪው ክርስቶስ እጅ ሰጠ። ዕረፍቱም የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ ኤጲፋንዮስ በዐረፈ በሁለት ዓመት ዮሐንስ አፈወርቅ በዐረፈ በአንድ ዓመት ነው። ሥጋውንም እንደ ሚገባ በንጹሕ ልብስ ገነዙ ብዙ መዝሙራትንና ምስጋናዎችን አድርገውለት በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሳዊርያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ✝ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_አጋቶን_ጴጥሮስ_ዮሐንስ #አሞን_እናታቸው_ቅድስት_ራፊቃ፦ እሊህ ቅዱሳንም በላይኛው ግብፅ ቊስ ከሚባል አውራጃ ከቆንያ ከተማ ናቸው። ለእርሳቸውም ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ተገልፆላቸው። ከእነርሱ የሚሆነውን ስብራ በምትባል ከተማ እርሷም ወደ እስክንድርያ ክፍል ናት በዚያ የምስክርነት አክሊል እንደሚቀበሉ ሥጋቸውንም ወደ ግብፅ ደቡብ ነቅራሀ ወደሚባል አገር እንደሚወስዱ አስረዳቸው ቅዱሳኑም በዚች ራእይ ደስ አላቸው። ✝ በማለዳም ተነስተው ገንዘባቸውን ሁሉ ለድሆችና ለችግረኞች ሰጡ ከእነርሱም የሚበልጥ ወንድማቸው አጋቶን በሀረጉ ሹም ነበር በሁሉም ዘንድ የተወደደ ነው ራፊቃ እናታቸውም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ በመከራ ስቃይ ላይ የሚፀኑና የሚታገሱ እንዲሆኑ ታበረታታቸው ነበር። ✝ ከዚህም በኋላ ቊስ ወደ ሚባል አገር ሲደርሱ በመኰንኑ በዲዮናሲዮስ ፊት ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። ከእነርሱም አስቀድሞ እናታቸው ራፊቃን አሰቃያት እርሷም በስቃይ ውስጥ በመታገስ ደስተኛ ነበረች ከዚህም በኋላ አራቱን ልጆቿን አሰቃያቸው። ✝ እነርሱንም በማሰቃየት በሰለቸ ጊዜ ወደ እስክንድርያ እንዲልካቸው ወገኖቹ መከሩት በእነርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ህዝቡ እንዳያምን ፈርተዋልና። እነርሱ በሁሉ ዘንድ የተወደዱ ስለሆነ በእርሳቸውም ምክንያት ከዚህ በፊት ብዙዎች ሰዎች በክብር ባለቤት በክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሙተዋልና የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀብለዋልና። ✝ ወደ እስክንድርያም ገዥ ወደ አርማንዮስ ቅዱሳኑን በአመጡአቸው ጊዜ በዚያን ወቅት ስሟ ስብራ በምትባል አገር በዚያ ነበር። የተጋድሎአቸውንም ፅናት አውቆ ፅኑ ስቃይን አሰቃያቸው ሥጋቸውንም ቆራርጦ ከመንኰራኩር ውስጥ ጨመራቸው። ዳግመኛም ዘቅዝቀው ሰቀሉአቸው በዚህም ሁሉ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መኰንኑና የርሱ ሰዎች ሁሉ እስቲአፍሩ ያለ ምንም ጥፋትና ጉዳት የሚያነሳቸው ሆነ። ✝ ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን ይቆርጡ ዘንድ ሥጋቸውንም በባሕር ሊጥሉ በታናሽ ታንኳ ጫኑአቸው። በዚያንም ጊዜ ከግብፅ በስተደቡብ መፂል ከሚባል አውራጃ ነቅራሀ ከምትባል መንደር ወደ አንድ ባለ ፀጋ እግዚአብሔር መልአኩን ላከ። ✝ የቅዱሳኑንም ሥጋ እንዲወስድ አዘዘው። እርሱም ወሰዳቸው "የፃድቃን ማደሪያቸው ይህ ነው" የሚል ቃልን ሰማ የመከራውም ወራት እስከሚአልፍ በዚያ አኖሩአቸው። ✝ ከዚህም በኋላ ገለጡአቸው ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንንም ሰርተውላቸው ስጋቸውን በውስጧ አኖሩ። እግዚአብሔርም ከሥጋቸው ድንቆች የሆኑ ታላላቅ ተአምራትን ገለጠ በዚያም ወራት ሥጋቸውን ስሙንጥያ ወደሚባል አገር አፈለሱ።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም፦ 7 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ✝ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወጸልሐዉ በልሳናቲሆሙ። ኰንኖሙ እግዚኦ ወይደቁ በውዴቶሙ። ወበከመ ብዝኅ ሕብሎሙ ስድዶሙ። መዝ 5፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 20፥1-9።                                                         ✝ ✝ ✝ ✝ #የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝጰ83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 13፥13-22፣ 1ኛ ጴጥ 3፥ 14-18 እና የሐዋ ሥራ 16፥16-22። የሚነበበው ወንጌል ማር 1፥23-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች ማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል የቅድስት ሐና የልደት በዓልና የአባ ዲዮስቆሮስ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

Repost from N/a
✝ አገረ ገዥ የሆነ አጎቱን በሮሜው ንጉሥ በአኖሬዎስ ዘንድ እንዲህ ሲል ወነጀለው "በከበረ ወንጌል ቃል ኪዳን እነደገባ ከእርሱ ዘንድ ስለ ርሱ መቶ እጥፍ እቀበላለሁና እኔ ገንዘቤን ክብር ይግባውና ለክርስቶስ እሰጠዋለሁ" በማለት ሳዊርያሮስ ገንዘቡን ሁሉ እንደበተነ። ይህም ነገር ለንጉሡ ደስ አሰኘው ፈጸሞም በእርሱ ደስ አለው እጅግም ወደደው ከእርሱም ከቤተ መንግስቱ እንዳይለይ ንጉሡ አኖሬዎስ አዘዘው ከእርሱም ጋር ሁል ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን በመሔድ ሌሊቱን ሁሉ ቁመው ያድራሉ ንጉሥ አኖሬዎስም የመነኰሳትን ሥራዎች ስለሚሠራ ከልብሰ መንግሥቱ በታች በሥጋው ላይ ማቅ ይለብስ ነበር። ✝ በዚህም ወራት ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ የነበረ አባ ዮናክንዲኖስ ነው ለእርሱም ሳዊርያኖስ በብዙ ሕዝብ  ላይ ኤጲስቆጶስ  መሆን እንዲገባው እግዚአብሔር ገለጸለት። ሊቀ ጳጳሳቱም እጅግ የሚወደውና የሚያከብረው ሆነ ከቶ እንድለየውም አይሻም ነበር በሁሉም ዘንድ ተወዳድ ሆነ ዜናውም በቁስጥንያው ንጉሥ በቴዎዶስዮስ ዘንድ ተሰማ። ✝ ሰዎች ሁሉ እንደሚያከብሩት በአየ ጊዜ ድካሙ በውዳሴ ከንቱ እንዳይጠፍ ከዚያች ቦታ በሥውር ሊወጣ ወደደ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ተገለጸለት ወደ ሀገረ ገብሪ ሔዶ ለብዙ ነፍሳት የገዳም አባት እንዲሆን አዘዘው በሌሊትም ወጥቶ ሔደ የምንኰስና ልብስን ከለበሰ በኋላ ደቀመዝሙር ቴዎድሮስ ከእርሱ ጋር ነበር ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ ገብላ ገዳም እስከሚደርስ በፊቱ የምትሔድና የምትመራው በመኰራኩር አምሰል የብርሃን ሠረገላ ላከለት። ✝ በዚያም ገዳም አበ ምኔት የሆነ ጻድቅ ሰው ነበር የቅዱስ ሳዊርያኖስንም መምጣት ጌታችን በራእይ አስረዳው ወደርሱ መጥቶ ተቀበለው ሰላምታም ሰጠውና ስለእርሱ ጌታችን በራእይ ተገልጾለት እንዳስረዳው ነገረው የጌታንም ቸርነት እጅግ አደነቁ። ✝ ዜናውም በሀገሮች ሁሉ ተሰማ የማይቁጠሩ ብዙ ሰዎች ወደርሱ ተሰበሰቡ። ንጉሥ ቴዎዶስዮስም ለከበረ ሳዊርያኖስ ገዳማትን የሚሠሩለት ብዙዎች ሰዎችን ሹሞችንም ከእርሱ ዘነድ ላከ የእግዚአብሔርም መልአክ በውስጣቸው ገዳም የሚሠሩባቸውን ቦታዎች ወሰነላቸው ብዙ ነፍሳትን የሚያጽናና የሚያረጋጋ ሆነ። ✝ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም በእጆቹ ላይ ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ ከእርሳቸውም በሀገር ገብላ መኰንን ልጅ ሰይጣን እንደደረባትና መኰንኑም "ሳዊርያኖስን ከዚህ አገር ካላበረርክ ከልጅህ አልወጣም ያለው ነው"። መኰንኑም ይህን ገነር በሰማ ጊዜ ተነሥቶ ወደ ከበረ ሳዊርያኖስ ሒዶ ሰይጣን ያለውን ነገረው ደሞም ልጅን ያድናት ዘንድ ለመነው። ✝ ቅዱስ ሳዊርያኖስም እንድህ ብሎ ደብዳቤን ጻፈለት "ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሰሱስ ክርስቶስ ስም ከእሷ ወጥተህ ሒድ አባቷም ያንን ደብዳቤ ተቀብሎ ወደልጁ ሰደደ ጊዜም ከመኰንኑ ልጅ ሰይጣን ወጥቶ ሔደ ልጅቷም ዳነች። ✝ ዳግመኛም ታላቅ ሠራዊት እስቲሆኑ ድረስ ብዙዎች ወንጀለኞች ሰዎች ተሰበሰቡ ወደ ከበረ ሳዊርያኖስም ገዳም ገብተው ሊያፈረርሱት ፈለጉ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም በላያቸው ጨለማን አመጣ ምንም ምን ሳያዩ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ኖሩ ቅዱስ ሳዊርያኖስንም ይቅር ይለቸው ዘንድ ብዙ ዕንባ በመፍሰሰ ለመኑት እርሱም ወደ ቦታዎቻቸው መልሶ ሰደዳቸው። ✝ ዳግመኛም በገዳማቱ ውስጥ ያለ በእርሱ የሚተዳደሩ መነኰሳት ሁሉ ከእነርሱ የታመመ ቢኖር በላያቸው በመጸለይ ያድናቸዋው የሚያጸናናቸውና ሁሉም እንደ እግዚአብሔር መላእክት እስቲሆኑ ፈረሀ እግዚአብሔር የሚያስተምራቸው ሆነ። እንዲህም ሆነ ስሙ ፈላታዎስ የሚባል የዚያች አገር ኤጲስቆጶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ እራይ ተገልጦለት ቅዱስ ሳዊርያኖስ በእርሱ ፈንታ ኤጲስቆጶስነት ይሾም ዘንድ እንዳለው አወቀ ያን ጊዜም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ላከ ቅዱስ ሳዊርያኖስንም ኤጲስቆጶስነት እንዲሾሙት አዘዛቸው ለዚች ሹመት እግዚአብሔር መርጦታና። ✝ ወዲያውኑ ደጋጎች ነገሥታት አኖሬዎስና አርቃዴዎስ ወስደው ገብላ በሚባል አገር ላይ ኢጶስቆጶስነት ሹሙት ስለ መንጋዎቹና ስለ ወገኖቹም አጠባበቅ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ። ✝ በዚያችም አገር እጅግ አዋቂ የሆነ የሙሴን ሕግ በማወቁ የሚመካ አንድ ስሙ ስቅጣር የሚባል ይሁዳዊ ነበር። እርሱም ወደ ቅዱስ ሳዊርያኖስ መጥቶ ከእርሱ ጋር ተከራከረ ግን ከቅዱስ ሳዊርያኖስ አንደበት የሚመጣውን ቃል ይሰማ ዘንድ አልተቻለውም። ✝ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ሳዊርያኖስ በራእይ ተገልጦለት ይህ አይሁዳዊ እርሱ ራሱ ክርስቶስ ከአከበራቸውና ከባረካቸው ወገን ውስጥ ሊሆን እንዳለው አስረዳው። ያ አይሁዳዊውም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ አስጨናቂዎች የሆኑ የስቃይ ቦታዎች በሕልሙ በማየት እንዲህ የሚለውን ቃል "ታላቅ በሆነ የዘላለም ሥቃይ ውስጥ የሚኖሩ እሊህን ከሀዲዎች ዘመዶችህ አይሁድን እነሆ እይ እነርሱም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ያላመኑ ናቸው"። በማግሥቱም ያ አይሁዳዊ ወደ ቅዱስ ሳዊርያኖስ መጥቶ ከእግሩ በታች ወድቆ ሰገደለት ክርስቲያንም ያደርገው ዘንድ ለመነው ያን ጊዜም እርሱንና ቤተሰቦቹን የሀገር ሰዎችንም ሁሉ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ✝ የቀሩትም አይሁድ ሁሉ አለቃቸው ክርስቲያን እንደሆነ በሰሙ ጊዜ አምነው ተጠምቀው ክርስቲያኖች ሆኑ። እንዲሁም ኒሞንጦስ የሚባሉ ሌሎች ሥራየኞች ሰዎችን ወደ ክርስቲያን ሃይማኖት እንዲገቡ ቅዱስ ሳዊርያኖስ ለመናቸው እነርሱ ግን በሥራያቸው ስለሚታበዩ ከእርሱ ቃሉን አልሰሙም እነርሱም ባዕድ ወደ እነርሱ የመጣ እንደሆነ በፊቱ አረርን ይበትናሉ ምንም ምን ማየት አይችልም። ✝ ቅዱስ ሳዊርያኖስንም ወደ ቀናት ሃይማኖቱ እሊህን ሥራየኞች ሰዎች ያስገባቸው ዘንድ ዕንባን በማፍሰስ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው እግዚአብሔርም በእርሱ ላይ ብቻ ጽኑዕ ደዌ አመጣ ወደ ክርስቲያን ወገኖች ግን ምንም ምን አልደረሰም። በግብጽ አገር በፈርዖንና በሠራዊቱ በግብጻውያንም ላይ መቅሠፍት ሲታዘዝ ወደ እስራኤል ወገን እንዳልደረሰ እንዲሁ ሆነ። ✝ በዚያም ወራት እንዚያ ሥራየኞች የቅዱስ ሳዊርያኖስን ቃል ሰምተው ትእዛዙን ስለ አልተቀበሉ ስለዚህም ይህ ጽኑ ደዌ በላያቸው እንደመጣ አወቁ። ወደ ቅዱስ ሳዊርያኖስም መጥተው በደላቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ክርስቲያኖችም ያደርጋቸው አስተምሮ አጥምቆ ክብር ይግባውና ከክርስቶስ መንጋዎች ጋር አንድ አደረጋቸው። ያቺ አገር ሁለመናዋ አንድ ማኅበር አንድ መንጋ ሆነች። ✝ ሰይጣንም ልብሱ በተቀደደ ሽማግሌ አማሳል ሆኖ ፈጽሞ የሚጮህ ሆነ እንዲህም አለ። "ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአለው ቦታ ሁሉ ጨነቀኝ በግብጽ አገርም ጠንካሮች መነኰሳት ተመሉባት በሮሜ አገርም ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ በውስጧ ይኖራል ደግሞ በቁስጥንጥንያ ዮሐንስ አፈወርቅ አለ ይህ ቦታ ለእኔ ቀረልኝ ብዬ ነበር እነሆ ሳዊርያኖስ ከእጄ ውስጥ ነጠቀኝ" አለ። ✝ እንዲህም ሆነ የፋርስ ሰዎች ሊወጉአቸው ሽተው ወደ አኖሬዎስና ወደ አርቃዴዎስ መልእክትን ላኩ እሊህ ደጋጎች ነገሥታትም የፋርስ ሰዎች የላኩትን ደብዳቤ ወደ ቅዱስ ሳዊሮያኖስ ላኩት። እርሱም ያቺን ደብዳቤ በአነበባት ጊዜ የደብዳቤውን መልስ ወደ ነገሥታት አኖሬዎስና አርቃዴዎስ እያስረዳ እንዲህ ብሎ ጻፈ "እኛ የክርስቶስ ከሆን መንግሥታችንም የክርስቶስ ነው እንዲህም ከሆነ የጦር መሣሪያን የጦር ሠራዊትንም አንሻም"። እግዚአብሔርም ከቀደሙ ነገሥታት ጋር ሁኖ ያደረገውን እንዴት እንዳዳናቸው ጠላቶቻቸውንም እንዴት ድል እንዳደረጓቸው አስታወሳቸው።

Repost from N/a
✝ "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #መስከረም ፯ (7) ቀን። ✝ እንኳን #ስለ_ተዋሕዶ_ሃይማኖት #በጉባኤ_ኬልቄዶን (ከለባት) #በ_451 ዓ.ም በንጉሥ መርቅያኖስና በሚስቱ በንግሥት ብርክልያ (በሊዮናውያን) #ጢሙን_ለተነጨና_ጥርሱንም ለተነቀለ  #ለእስክድርያ_ሃያ_አምስተኛ_ጳጳስ #ለታላቁ_ሊቅ_ለአቡነ_ዲዮስቆሮስ ለዕረፍት በዓል፣ ለገብላ ኤጴስቆጶስ ለከበረ አባት #ለአባ_ሳዊርያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበሩ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ለአጋቶንና #ጴጥሮስ_ለዮሐንስና_ለአሞን_ለእናታቸው_ራፈቃ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦#ከቅዱስ_ፋሲለደስ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉ #ከሁለት_ሺህ_ሰዎች፣ ከጋንግራ ሰው #ዳሳ #ከአንጾኪያ_ኤጲስቆጶስ_ከናውላ፣ ከመነኵሴውም #ከአባ_ጴጥሮስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                              ✝ ✝ ✝ ✝ #የእስክንድርያ_አገር_ሃያ_አምስተኛ_ሊቀ_ጳጳሳት #ሊቁ_አባ_ዲዮስቆሮስ፦ ስለ ቀናች ሃይማኖትም ታላቅ ተጋድሎን ከተጋደለ በኋላ ዕረፍቱ በተሰደደበት በደሴተ ጋግራ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው ንጉሥ መርቅያኖስ ወደ ሰበሰበው ጉባኤ በጠሩት ጊዜ ሲደርስ ብዛታቸው ስድስት መቶ ሠላሳ ስድስት የሆነ ታላቅ ጉባኤን አየ። እንዲህም አለ "ይህ ታላቅ ጉባኤ እስቲሰበሰብ ድረስ በሃይማኖት ላይ የተገኘው ጉድለት ምንድን ነው"። "ይህ ጉባኤ የተሰበሰበው በንጉሥ ትእዛዝ ነው" አሉት። እንዲህም አላቸው "ይህ ጉባኤ ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆን ኖሮ እኔ ተቀምጬ እግዚአብሔር በሰጠኝ በአንደበቴ እናገር ነበር ግን የዚህ ጉባኤ መሰብሰብ በንጉሥ ትእዛዝ ከሆነ የሰበሰበውን ጉባኤ ንጉሡ እንዳሻው ይምራ"። ✝ ከዚህም በኋላ አንዱን ክርስቶስን ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት ባሕርይ ሁለት ምክር የሚያደርግ የክህደት ቃል በውስጡ የተጻፈበትን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ልዮን የላከውን ደብዳቤ የከበረና የተመሰገነ ዲዮስቆሮስ ቀደደ። በመንፈስ ቅዱስ የሚናገር የከበረ ዲዮስቆሮስም በጉባኤው ፊት እንዲህ ብሎ አስረዳ "ሰው እንደመሆኑ ወደ ሠርግ ቤት የጠሩት ጌታችን ክርስቶስ አምላክ እንደመሆኑ ውኃውን ለውጦ ወይን ያደረገው ከሀሊ ስለሆነ ሰውነቱና መለኮቱ በሥራው ሁሉ የማይለይ አንድ ነው"። ✝ ደግሞ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቄርሎስ ከተናገረው የአካላዊ ቃል ተዋሕዶ እንደ ነፍስና ሥጋ እንደ እሳትና ብረት ተዋሕዶ ነው ያለውን ቃል ምስክር አድርጎ በማምጣትም አስረዳ። "እሊህም የተለያዩ ሁለቱ ጠባዮች ስለ ተዋሕዷቸው አንድ ከሆኑ እንዲሁም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ አንድ መሲሕ አንድ ጌታ አንድ ባሕርይ አንድ ምክር ነው እንጂ ወደ ሁለት አይከፈልም" አላቸው። ✝ ከዚያም ከተሰበሰበው ጉባኤ ውስጥ ማንም ሊከራከረው የደፈረ የለም ከውስጣቸውም የእግዚአብሔር ጠላት ስለሆነው ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በኤፌሶን ጉባኤ አስቀድሞ ተሰብስበው የነበሩ አሉ። ወደ ንጉሥ መርቅያኖስና ወደ ሚስቱ ንግሥት ብርክልያ "ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከአባ ዲዮስቆሮስ በቀር ስለ ሃይማኖት ትእዛዛችሁን የሚቃወም የለም" ብለው ነገር ሠሩበት። ✝ ቅዱስ ዲዮስቆሮስንም ወደ ንጉሥ አቀረቡት ከእርሱም ጋር ታላላቅ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ከጉባኤው የሆኑ ነበሩ ከጥዋትም እስከማታ እርስበርሳቸው ሲከራከሩ ዋሉ። የከበረ ዲዮስቆሮስም የቀናች ሃይማኖቱን አልለወጠም ንጉሡና ንግሥቲቱ በእርሱ ተቆጥተው እንዲደበድቡት አዘዙ ስለዚህም ደበደቡት ጽሕሙን ነጩ ጥርሶቹንም ሰበሩ እንዲህም አደረጉበት። ✝ ከዚህም በኋላ የተነጨውን ጽሕሙን ያወለቁትንም ጥሩሱን ሰብስቦ ወደ እስክንድርያ አገር ላካቸው "እነሆ የቀናች ሃይማኖት ፍሬ ይህ ነው" አላቸው። ለጉባኤውም የተሰበሰቡ ኤጲስቆጶሳት በዲዮስቆሮስ ላይ የደረሰውን መከራ በአዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ በእርሱ የደረሰ በእነርሱ ላይ እንዳይደርስ ስለዚህም ከመናፍቁ ንጉሥ ከመርቅያኖስ ጋር ተስማሙ። ✝ በሲኦል ውስጥ ይቆርጡት ዘንድ ባለው ምላሳቸውም "ለክርስቶስ ሁለት የተለያዩ ባሕርያት" አሉት ብለው በንጉሡ መዝገብ ላይ በእጆቻቸው ጽፈው ፈረሙ። ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ተመልሶ ያን በውስጡ የጻፉበትን ደብዳቤ ያመጡለት ዘንድ ወደእሳቸው ላከ እነርሱም ላኩለት እነርሱ እንደጻፉ በውስጡ እርሱ የሚጽፍ መስሏቸዋልና። እርሱ ግን አባቶቻችን ሐዋርያት ከአስተማርዋት ከቀናች ሃይማኖት በኒቅያ የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጲሳት አባቶቻችን ከሠሩት ሕግ የሚወጣውን ሁሉ በደብዳቤው ግርጌ ጽፎ አወገዘ። ✝ መናፍቁ ንጉሥም ተቆጥቶ ጋግራ ወደም ትባል ደሴት እንዲአግዙት አዘዘ ወደዚያም ወሰዱት። ከእርሱም ጋር የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አብሮ ተሰደደ። ሌሎችም አራት መነኰሳት የሸሹ አሉ። እሊህም ስድስት መቶ ሠላሳ ስድስት ኤጲስቆጶሳት ተቀምጠው በኬልቄዶን ለራሳቸው መመሪያ የሚሆናቸውን ሥርዓት ሠሩ። ✝ የከበረ ዲዮስቆሮስንም በአጋዙት ጊዜ ከዚያች አገር ኤጲስቆጶስ ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት ኤጲስቆጶስ ንስጥሮሳዊ ስለሆነ ታላቅ ጉስቁልናንም አጎሳቁለው በእጆቹ ላይ ድንቆች ታላላቅ ተአምራቶችን እግዚአብሔር እስከገለጠ ድረስ። የደሴቱም ሰዎች ሁሉ ሰገዱለት አከበሩት ከፍ ከፍም አደረጉት እግዚአብሔርም የመረጣቸውን በቦታው ሁሉ ያከብራቸዋልና። አባ ዲዮስቆሮስም አባ መቃርስን "አንተ በእስክንድርያ አገር የሰማዕትነት አክሊልን ትቀበል ዘንድ አለህ" አለው። ከዚህም በኋላ ከምእመናን ነጋዴዎች ጋር ወደ እስክንድርያ ላከው በእርሱ ላይ ትንቢት እንደተናገረ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። ✝ የከበረ አባት ዲዮስቅሮስ ግን መልካም ተጋድሎውን በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርንም አገልግሎ ከዚች ኃላፊት ከሆነች ኑሮው ወጥቶ ሔደ የሃይማኖቱንም ዋጋ አክሊልን ተቀብሎ ወደ ዘላለም ዕረፍት ገባ ያረፈውም በዚያች በደሴተ ጋግራ ነው ሥጋውንም በዚያው አኖሩ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዲዮስቆሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                                                                    ✝ ✝ ✝ ✝ #የገብላ_ኤጲስቆጶስ_የከበረ_አባት #አባ_ሳዊርያኖስ፦ የዚህም ቅዱስ የአበባቱ ስም አብስርያኖስ ይባላል የሀገረ አቴናንም ፍልስፍና ተማረ ከዚያም ወደ ቂሣርያ ሔዶ እውቀታቸውን ሁሉ ተማረ። ዳግመኛም ወደ ሮሜ ከተማ ተመልሶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተማረ ከጥቂት ዘመናት የብሉይንና የሐዲስን መጸሕፍት አጠና። ✝ ከዚህም በኋላ ቁጥር የሌለው ብዙ ገንዘብን ትተውለት ወላጆቹ አረፉ ስለርሱ ፈንታ መቶ ዕጥፍ ይቀበል ዘንድ ወዶ ያንን ገንዘብ ለክብር ባለቤት ለክርስቶስ ሊሰጥ ወደደና ድሆችን መጸተኘኞችን ምስኪኖችን ችግረኞችንም በውስጥ ይቀበል ዘንድ የእንግዳ መቀበያ ቤትን ሠራ። አትክልትም ተከለ ፍሬዎችን ተሸክመው የሚያመጡላቸውን ሠራተኞችን አደረገ እነዚያም ስለ ድሆችና ስለ ችግረኞች የተሠሩ ቦታወች እስከ ዛሬ በስሙ የሚጠሩ ሆኑ።

Repost from N/a
✝ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝                 ✝ #መስከረም ፯ (7) ✝ እንኳን #ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም እናት #ለቅድስት_ሐና ለልደቷ_መታሰቢያ_በዓል፣ #ለመጥምቀ°መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ እናት #ለቅድስት_ኤልሳቤጥ_ለመታሰቢያዋ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                               ✝ ✝ ✝ ✝ #ቅድስት_ሐና፦ ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት። ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥምቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥ ወለደቻት። ✝ ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቆም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው። ✝ የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር። ✝ ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት። ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በቅድስት ሐና በጸሎቷ የሚኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 11 ስንክሳር።                               ✝ ✝ ✝ ✝ #ቅድስት_ኤልሳቤጥ፦ ይህች ቅድስት ከኢየሩሳሌም የሆነች የእናቱዋ ስም ቅድስት ሶፍያ ነው። እርሷም ከሌዊ ነገድ ከአሮን ወገን ለሆነ ለማጣት ልጅ ናት በዝምድና አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የእናቷ እኅት ልጅ ናት። ማጣት ሦስት ልጆችን ወለዷልና የታላቂቱም ስም ማርያም ነው እርሷም ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ እመቤታችንን ያገለገለች ሰሎሜን ወለቻት፣ ሁለተኛዋም ሶፍያ ናት እርሷም የዚች ቅድስት ኤልሳቤጥ እናቷ ናት፣ የታናሺቱም ስም ሐና ነው። እርሷም የከበረች ድንግል እመቤታችንን ማርያምን ወለጀቻት። ሰሎሜ ኤልሳቤጥ እመቤታችን ማርያም የእኅትማማች ልጆች ናቸው። ✝ ይችንም ቅድስት ኤልሳቤጥ ካህኑ ዘካርያስ አገባት የከበረ ወንጌልም ስለርሳቸው፡ ተናግሯልና እነርሱ ሁለቱም ያለ ነውር ያለ ነቀፋ በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው የሚኖሩ ዕውነተኞች ደጎች ሆኑ። ኤልሳቤጥም መካን ስለሆነች ወደ እግዚአብሔር የሚለምኑና የሚሚማልዱ ሆኑ አርጅተውም የመውለጃቸው ዘመን በአለፈ ጊዜ እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ዘካርያስ ልኮ ጸሎታቸው ልመናቸው እንደ ተሰማ ስለ ዮሐንስ መወለድና ከእርሱ ስሚሆነው አስረዳው። ✝ ከዚህም በኋላ ይቺ ቅድስት ኤልሳቤጥ መጥምቁ ዮሐንስን ፀንሳ ወለጀችው ከሰዎችም የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዶ እጅ ደስ አላት። ሕፃኑም በማሕፀኗ እያለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሰላምታ በሰጠቻት ጊዜ እንዲ ብላ ጮኸች "ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ ቡሩክ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ እነሆ እንዴት ነሽ ስትይኝ የሰላምታሽን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ልጁ በማሕፀኔ ውስጥ በደስታ ዘለለ (ሰገደ)"። ✝ ከዚህም በኋላ ጌታችንን አየችው በአምላክነቱም አመነች የሚያምኑበትም በመዳናቸው ደስ አላት ዕድሜዋንም በፈጸመች ጊዜ በበረሀ ውስጥ ሳለች የካቲት16 ቀን በሰላም ዐረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ኤልሳቤጥ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #መስከረም ፮ (6) ቀን። ✝ እንኳን #ከዐበይት_ነቢያት_አንዱ_ለሆነው ለታላቁ ነቢይ #ለአሞጽ_ልጅ_ለቅዱስ_ኢሳይያስ_ለዕረፍት በዓልና በከሀዲ ንጉሥ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለች #ቅድስት_ሰብልትንያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን ። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከመነኰስ_ያዕቆብ፣ ከኤጲስቆጶስ #ከአናቲሞስ_ከባስሊስና_ከአሮጦስ_ከውርዋና፣ #ከሳውልስ_ከሰማዕቱ_ከሰውላስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                    ✝ ✝ ✝ ✝ #የአሞጽ_ልጅ_ታላቁ_ነቢዩ_ቅዱስ_ኢሳይያስ፦ ይህም ነቢይ ለይሁዳ በነገሡ በአምስቱ ነገሥታት ዘመን አስተማረ ትንቢትም ተናገረ እሊህም አዝያን ኢዮአታም አካዝ ሕዝቅያስና ምናሴ ናቸው። ✝ በአካዝ ዘመንም እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ። "እነሆ ስለዚህ እግዚአብሔር ምልክትን ይሰጣችኋል። እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች። ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ አንድ ሆነ ማለት ነው"። እርሱም በኃጢአታቸው ከሚመጣባቸው ፍዳ ወገኖቹን የሚያድናቸው ወደ ሃይማኖቱም የሚአስገባቸው እንደሆነ የእስራኤልንም ልጆች መሥዋዕታቸውንና ክህነታቸውን እንደሚሽር ከሐዲስ ወገኖችም የሚያመሰግኑት ካህናትን እንደሚሾም ተናገረ። ✝ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምም ኢየሩሳሌምን ከቦ የስድብ ቃልን በክብር ባለቤት በእግዚአብሔር ላይ በተናገረ ጊዜ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምን ያጠፋው ዘንድ እግዚአብሔር እንዳለው ለሕዝቅያስ ትንቢትን ተናገረ። በዚያች ሌሊትም እግዚአብሔር የላከው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሠናክሬም ሰፈር መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞችን ገደለ። የለኪሶ ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አዩ ። ✝ ሕዝቅያስም ታሞ ለሞት በተቃረበ ጊዜ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደርሱ መጥቶ "እግዚአብሔር ትሞታለህ እንጂ አትድንም ብሏልና ቤትህን አዘጋጅ" አለው። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመነ ፈጽሞ ጽኑ ልቅሶንም አለቀሰ። ይህን ከነገረው በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኢሳይያስ መጣ "ሒደህ ለሕዝቅያስ "የአባትህ የዳዊት ፈጣሪ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ። እነሆ በዘመንህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨመርኩልህ" አለ በለው"። ✝ ዳግመኛም ስለ እስራኤል መማረክና ከምርኮ ስለ መመለሳቸው ትንቢት ተናገረ የፈሳሽ ውኃን ምንጭ በማፍሰስ በእጆቹ ላይ እግዚአብሔር ምልክትን ገለጠ። ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስ መከራ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ። "እርሱም በመከራው ጊዜ ነገርን አልተናገረም እንደ በግ ይታረድ ዘንድ መጣ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንደ ማይናገር እንዲሁ በመከራው ጊዜ አልተናገረም"። ✝ ከዚህም በኋላ ደግሞ በሕዝቅያስ ልጅ በንጉሥ ምናሴ ላይ ትንቢት ተናገር ጣዖትን ስለማቆሙና ስለማምለኩ ገሠጸው። ስለዚህም ንጉሥ ምናሴ ተቆጥቶ በዕንጨት መሰንጠቂያ መጋዝ በራሱና በእግሮቹ መካከል ሠነጠቀው ምስክርነቱንም በዚህ መስከረም 6 ቀን ፈጸመ ። ✝ ትንቢት እየተናገረ የኖረበትም ዘመን ሰብዓ ዓመት ከዚያም በላይ ይሆናል ። እርሱም ያስተማረው ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሦስት ዓመት ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ✝ #ሰማዕቷ_ቅድስት_ሰብልትንያ፦ ይችንም ቅድስት ዕድሜዋ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን ከሀድያን ያዙዋት እጆቿንና እግሮቿንም አሥረው ከሚነድ እሳት ውስጥ ጣሏት የክብር ንጉሥ በሆነ በእግዚአብሔርም ኃይል ከእሳት ዳነች። ✝ ውኃን በተጠማች ጊዜ እግዚአብሔርን ለምናው ውኃን አፈለቀላትና ጠጣች ክብር ምስጉን የሆነ ጌታችንንም አመሰገነችው። ከዚህም በኋላ ነፍሷን በእግዚአብሔር እጅ አደራ ሰጥታ ራሷን ከእሳት ውስጥ ወረወረች ምስክርነቷንም ፈጸመች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሰብልትንያ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 6 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ✝ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ104፥14-15 ወይም መዝ 28፥8-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 3፥1-7 ወይም ዮሐ 12፥36-ፍ.ም።

✝ "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #መስከረም ፮ (6) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ዐፅማቸው #ከዋልድባ_አብረንታንት_ወደ ደብረ_ዓባይ ለፈለሰበት ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።                                                           ✝ ✝ ✝ ✝ #የአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_የሥጋ_ፍልሰት፦ ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ፤ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትውልዳቸው ከካህናቱ ወገን አክሱም ነው አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ። ለመምህር ሰጥተዋቸው ሲማሩ አድገው በኋላም ወላጆቻቸው በሞት ሲለዩአቸው ደብረ በንኰል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኩስናን ከአበው እያጠኑ ለትልቁም ለትንሹም በትሕትና እየታዘዙ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየሰበሩ በትኅርምት በጽሞና በጸሎት ይኖሩ ነበር። ✝ ሰይጣን በውዳሴ ከንቱ ጾር ቢመጣባቸው ከማሕበረ መነኰሳቱ ተለይተው በተባሕትዎ ለመኖር ሽተው ወጥተው ሲሔዱ ተከዜ ደረሱ። ወንዙ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትምህርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉ ሳይበላሽ ተሻግረዋል። ዋልድባ ሲደርሱ ጌታ እዚህ ተቀመጥ ስላላቸው ገዳም መሥርተው ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማሩ ተቀመጡ። ዛሬ በዋልድባ የሚያመሰግኑበት ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያምን ከተከዜ ወዲህ ያመጡ እሳቸው ናቸው። ይህንን እየጸለዩ ሲሔዱ ክንድ ከስንዝር መሬት ለቀው ይታዩ ነበር። ✝ አንድ ቀንም ይህንን ጸሎት ደግመው ውኃውን ቢባርኩት ኅብስተ ሕይወት ሆነላቸው ከነደቀ መዛሙርቶቻቸው ተመግበውታል። እመቤታችንም የፍቅር መግለጫ ዕጣን፣ ወርቅ፣ እንቁ ሰጥታቸዋለች። "ውዳሴዬን ከቅዳሴዬ አንድ አድርጎ የደገመውን አንተ ከገባህበት መካነ ሕይወት አስገባዋለሁ" ብላ ቃልኪዳን ሰጥታቸዋለች። ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታን በስብሐተ መላእክት ተገልጦ "በስምህ የተማጸነውን በጎ የሰራውን፣ ዜና ገድልህን የጻፈውን፣ ያስጻፈውን፣ ያነበበ፣ የተማረ፣ ያስተማረ፣ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ምሬልሃለሁ። በዚህ ቦታ በዋልድባ የሚሰበሰቡ ልጆችህን ከእዳ ከፍዳ እሰውርልሃለሁ" አላቸው። እንኪያስ ቦታዋን ባርክልኝ ብለው እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል ጌታችንም "እህል አይብቀልብሽ ኃጢአት አይሻገርብሽ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላት ለገዳመ ዋሊ። አባታችን አቡነ ሳሙኤል በበዓታቸው ውስጥ ጸንተው ሲኖሩ ታህሣሥ 12 ቀን ያረፉ ሲሆን ዛሬ መስከረም 6 ግን ፍልሰተ አጽማቸው የተከናወነበት ዕለት ነው። ከአባታቸው ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን።

መስከረም ፩ ስንክሳር.mp33.74 MB

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናንና ምዕመናት ሐዋርያው ብፁዕ ጳውሎስ በመልዕክቱ አሮጌው ነገር አልፎአል እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል (፪ኛ ቆሮ ፭፥፲፯) ሲል የተናገረው በሰው ልጆች ላይ የነበረው እዳ በደላችን በክርስቶስ ኢየሱስ በደሙ ፈሳሽነት የታጠበልንና ከነበረብን ሕመም በእርሱ ቁስል መፈወሳችንን ሲያመለክትና በእርሱ መዳናችንም አዲስ ሆነን እንድንገኝ ማስቻሉን ለማመላከት ነው ፤ ሆኖም እኛ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሮጌው ኃጢአት ያተደመሰሰልን ክርስቲያኖች ከኀጢአት ተግባር በመውጣት አነሆ ሁሉም አዲስ ሆኗል ብለን ወደ ምንመሰክርበት የጽድቅ መንገድ ልንመጣ እና አዲሱንም ዓመት በዚህ መልኩ ልንቀበል ያስፈልገናል። ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከገቢረ ኃጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት ፣ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት ፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም ፤ ነፍሳችን በኃጢአት እየተጨነቀች ፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተከናንባ ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኃጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች ጨዋታ ነው" ሲል አስተምሯል። ስለሆነም በመብልና በመጠጥ መደሰት ሳይሆን የነፍሳችንን ረኃብ እና ጥም መመልከት ግድ ይለናል። መጽሐፍ ቅዱስ አቤቱ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ (ሰቆ. ፭፥፳፩) ያለውም በዘመናት ሂደት እየበደልንና እያጠፋን መኖራችን እሙን በመሆኑ በዘመን መታደስ የሰው ልጅ አእምሮ እንዲታደስ እና ሥራው ሁሉ የተወደደ እና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን ለማድረግ ነው። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናንና ምዕመናት በዚህ ወቅት በተለይም በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭት ፣ ጦርነት እና ሰላምን ማጣት የሚመነጩት ራሳችንን በአዲስ መልክ በእግዚአብሔር ቃል በማደስ የተሰጠንን ተጨማሪ የንስሐ ዘመን እንደ ዋዛ በመቁጠር እና ዘመኑን የምንሻሻልበት ሳይሆን ለተጨማሪ ጥፋት የምንዘጋጅበት በማድረጋችን የተነሳ የሚስተዋል ችግር መሆኑ ሀቅ ቢሆንም ቅሉ ይህ የምንቀበለውንም አዲስ ዓመት አቅማችንን ሁሉ ተጠቅመን የምንተላለቅበት እና ሀገራችንንም ወደ ጥፋት የምናስገባበት ሳይሆን ቆም ብለን በማሰብ ዕድሜ ለንስሐ የተሰጠን መሆኑን በማስተዋል ከሁሉ አስቀድሞ ሰላምና ፍቅርን ፣ ወንድማማችነትንና አንድነትን እንድናገኝ በማስተዋል እንድንመላለስ ነው። በመጨረሻም ፦ አዲሱን ዓመት ስንቀበል በፍፁም ክርስቲያናዊ ፍቅር የተራቡትን በማብላት ፣ የተጠሙትን በማጠጣት ፣ የታረዙትን በማልበስ ፣ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብ ሊሆን ይገባል። እግዚአብሔር አምላካችን አዲሱን ዓመት የፍቅር ፣ የሰላም ፣ የስምምነት እና የተባረከ ያድርግልን። እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ ! አባ ሄኖክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጳጉሜን ፭ ቀይ ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

"ዘመኑን መልካም የምናደርገው በዘመኑ መካከል ራሳችንን ለበጎ ነገር ዝግጁ ስናደርግ እና ከኃጢአት ተመልሰን አዲስ ለመሆን ዝግጁ ስንሆን ነው" ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአ/ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ: “ወኀለፈ
"ዘመኑን መልካም የምናደርገው በዘመኑ መካከል ራሳችንን ለበጎ ነገር ዝግጁ ስናደርግ እና ከኃጢአት ተመልሰን አዲስ ለመሆን ዝግጁ ስንሆን ነው" ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአ/ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ: “ወኀለፈ ዘትካት ወናሁ ኮነ ሐዲሰ ኵሉ ፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”   — ፪ኛ ቆሮ ፭፥፲፯ በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ምዕመናንና ምዕመናት; ጥንት የሌለው ቀዳማዊ ፤ ዘመን የማይቆጠርለት ደኃራዊ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ፳፻፲፮ ዘመነ ዮሐንስ የምሕረት ዓመት በሰላም እና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ! የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት በእግዚአብሔር አጋዥነት በሰሩት የዘመን ቀመር መሠረት ዓመታት በዓመታት እየተተኩ ዘመናት እየተለዋወጡ ላለንበት ዘመን ደርሰናል። ዓመታት ወይም ዘመናት በራሳቸው ኃይል በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ሊወስኑት የሚቻላቸው አንድም የሕይወት ውሳኔ ባይኖርም በርካቶች ዘመናትን ሲያማርሩና ሲነቅፉ ይስተዋላል። መሠረቱ ግን በየዘመናቱ ውስጥ የሰው ልጆች የሚሰሯቸው በጎ ሥራዎች እና የሚፈጽሟቸው መጥፎ ተግባራት ዘመኑን የተለየ ስያሜ እንዲሰጠው ማድረጋቸው አይዘነጋም። በመሆኑም ዘመኑን መልካም የምናደርገው በዘመኑ መካከል ራሳችንን ለበጎ ነገር ዝግጁ ስናደርግ እና ከኃጢአት በንስሐ ተመልሰን አዲስ ለመሆን ዝግጁ ስንሆን ነው።

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 #ስንክሳር ዘጳጉሜ #ስድስት (፮)     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33                         #ስንክሳር                        ዘጳጉሜ #አምስት (፭)                       ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33                         #ስንክሳር                        ዘጳጉሜ #አራት (፬)                       ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33                         #ስንክሳር                        ዘጳጉሜ #ሦስት (፫)                       ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

“ለዓዲስ ዓመት ዋዜማ አብረን ጸሎት እናድርግ” ፡፡ “እንኳን ለ2016 ዓ.ም (ዘመነ ዮሐንስ) ዋዜማ በሰላምና በጤና አደረሰን: አደረሳችሁ”:: 🕯"ጸሎትህ የጎደለውን ይሞላል"🕯 "አምላክ ልብህን ይቀይረው ዘንድ፣ እርሱን ለመከተል ታገል። እንደዚህ በለው "ጌታ ሆይ አድነኝ፤ከሃጢያቴና ከተፈጥሮአዊ ዝንባሌም አድነኝ። ከአንተ በመታረቅ መንገዴ ላይ እነዚህ ነገሮች ሁሉ መሰናክል አይሁኑ። ብዙ ልቦችን ምናልባት ከእኔ በላይ የከፋ ሁኔታ ውስጥ የነበሩትን ብዙ ሰዎችን ቀይረሃል።" [ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ] ልዩ የጸሎት  መርሐ ግብር ጳጉሜ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ዕለተ አርብ ከ11፡30 ጀምሮ በሰንበት ትምህርት ቤታችን  አዳራሽ እንገናኝ!