ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
إظهار المزيد602
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-87 أيام
-1630 أيام
أرشيف المشاركات
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፳፬ (24) ቀን።
✝ እንኳ #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ነድያንን ለሚወዱ #ለአቡነ_ብርሃነ_መስቀል (አብርሃም) በሚያደርጉት ድንቅ ድንቅ ተአምራት #አባ_ዘግሩም ለተባሉት ሙሴ ጽላትን እንደተቀበለ ሁሉ #የእግዚአብሔር_መልአክ ከሰማይ አመጥቶ የብርሃን መስቀልና #የመድኃኔዓለምን_ታቦት_ለተሰጡበት_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #መፍቀሬ_ነዳያን_አባ_ዘግሩም፦ አባታቸው ገርዜነ ጸጋ የተባለ ደገኛ ካህን ሲሆን እናታቸው ደግሞ ነፍስተ እግዚእ ትባላለች፡፡ እነዚህም ደገኛ ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው ብዙ ዘመን ሲኖሩ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ይለመኑት ነበር፡፡ ልዑል እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ የተባረከ ልጅ እንደሚወልዱ አበሰራቸው፡፡ አባ አብርሃምም በመልአኩ ብሥራት ግንቦት ሃያ አራት ቀን በተወለዱ ጊዜ ወላጆቻቸው ብርሃነ መስቀል ብለው ጠሩት፡፡ በኋላ የተጠራበት ስመ ጥምቀቱ ግን ማኅፀንተ ሚካኤል ነው፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
📣📣ኑ እንምከር 📣📣
የወጣት ማሕበራት የአንድነት ጉባኤ
📆 እሁድ ጥቅምት 25/02/2016
🕒 ከ5:00 ሰአት ጀምሮ
⛪ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
✥✥✥በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው መሰባሰባችንን አንተው እርስ በእርሳችን እንመካከር እንጂ ዕብራውያን 10÷25 ✥✥✥
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፳፫ (23) ቀን።
✝ እንኳን #ለእስክንድርያ_አገር_ኀምሳ_ሁለተኛ #ሊቀ_ጳጳሳት_ለአባ_ዮሴፍ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ፣ በዐላውያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቆሮንቶስ_አገር_ኤጺስቆጶስ_ለቅዱስ_ዲዮናስዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለከሀዲ ንጉሥ ለዱድያኖስ ለሚስት #ለቅድስት_እለእስክንድርያ መታሰቢያዋ በዓልና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ኢላርዮስ_ከጣንቅያቅ፣ #ከቴዎደስዮስ_ከቴዎላስ_ከዮሳብና_ከገድላ ከሰማዕት እስክድርያም ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ #ለደብረ_ሊባኖስ_ሁለተኛ_መምህር (እጨጌ) #ከአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ዕረፍት በኋላ ለተሾሙ #ለእጨጌ_አቡነ_ኤልሳዕ ለዕረፍት መታሰቢያቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
"#ሰላም_እብል_ለሊቀ_ጳጳሳት_ዮሴፍ። ዘእምሀገረ መኑፍ። ዘተውህበ ሎቱ አእምሮ መጽሐፍ። ወሰላም ካዕበ ለተልእኮቱ ዕስቁፍ። እንተ ክሣዶ መቲረ ዘኢይክል ሰይፍ"። #ሊቀ_አርከ_ሥሉስ_አርኬ #የጥቅምት_23።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፳፪ (22) ቀን።
✝ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነ ለብልሁና ለጥበበኛው #ለወንጌላዊው_ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ሉቃስ በንጉሥ ኔሮን ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለየዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ሉቃስ_ጋር_በሰማዕትነት_ከዐረፋ_ከአራት°መቶ ሰባ ሰባት ሰዎች ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥1-5። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቈላ 4፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 1፥4-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥1-6። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥1-5። የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የወንጌላዊው የቅዱስ ሉቃስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፳፩ (21) ቀን።
✝ እንኳን #ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ተአምራት አድርጋ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ማትያስን ከእስራት ቤት ላአዳነችበት በዓል፣ ለነቢዩ #ቅዱስ_ኢዩኤል ለዕረፍት በዓል፣ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ላስነሣው #ለቅዱስ_አልዓዛር_ሥጋው_ከቆጵሮስ_አገር ወደ #ቊስጥንጥንያ_ለፈለሰበት፣ እግዚአብሔር በሚወድ #የንጉሥ_ሰይፈ_አርዕድ_ደግሞ_ቈስጠንጢኖስ ለሚባል ልጁ በሆነ #በንጉሣችን_በዳዊት ዘመን ለዐረፈው ለከበረች አገር #ኢየሩሳሌም_ሊቀ_ጳጳሳት ለሆነ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ቀን ከምትታሰበው፦ አምላክ ከወለደች #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም ከወራዊ በዓሏ መታሰቢ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ "#ሰላም_ለኪ_ገነተ_ሚዓ_ወሰሊክ። ዘኢያይበሰኪ ነፋሰ መርቄ ወደደክ። እማእሠረ ጌጋይ ፍትሐኒ #ወላዲተ_ክርስቶስ_አምላክ። እምነ ሙቃሔ ጽኑዕ ወእማእሠር ድሩክ። ከመ ፈታሕኪዮ ዮም ለማትያስ ላእክ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ)
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ውድ የፍኖተ ብርሃን ቤተሰቦች በደብራችን ልዩ የሆነ የበገናና የክራር ስልጠና ስለተዘጋጀ መማር የምትፈልጉ ከላይ ባስቀመጥነው ስልክ እየደወላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።
✨✨✨እንዲሁም ትምህርቱን መማር ለሚፈልጉ ሁሉ በማጋራት የበረከቱ ተካፋይ ሁኑ ✨✨✨
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
እንኳን #ለታላቁ_ለትሕትናና_ለትዕግስተኛው አባት ለክቡሩ፤ ለገናና ለሆነ #ለአባ_ዮሐንስ_ሐጺር_ለዕረፍት በዓልና የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ ለሆነ #ለታላቁ_ነቢይ_ለቅዱስ_ኤልሳዕ_ለልደቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
11. በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት አህጉረ ስብከት ሥር የተቋቋሙት አብያተ ክርስቲያናት የሚተዳደሩበት እራሱን የቻለ ሕግና ደንብ ባለመኖሩ በመዋቅራዊ አስተዳደራችን ላይ ከፍተኛ ክፍተት ሲፈጥር የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ ለውጭው ክፍለ ዓለማት አህጉረ ስብከት እና አብያተ ክርስቲያናት እራሱን የቻለ መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ የፀደቀ በመሆኑ በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት ሁሉም አህጉረ ስብከትና አብያተ ክርስቲያናት በጸደቀው መተዳደሪያ ደንብ ብቻ ሥራቸውንና አገልግሎታቸውን እንዲያከናውኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12. የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ኮሌጆች ወጥ የሆነ የጋራ መተዳደሪያ ደንብ እንዲኖራቸው በማሰብ ጉባኤው አስቀድሞ ተዘጋጅ እንዲቀርብ ባዘዘው መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ መርምሮ በማጽደቅ በሁሉም በተቋቋሙትም ሆነ ወደፊት በሚቋቋሙት ኮሌጆች ሥራ ላይ እንዲውል ጉባኤው ወስኗል፡፡
13. ገዳማትና ገዳማዊ ሕይወት፣ የአብነት መምህራን እና ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአጠቃላይ ክብረ ክህነት እና ትምህርተ ኖሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡
14. የቤተ ክርስቲያናችን ሕጋዊ፣ ተቋማዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ መብቶች መከበርና የእምነት ነጻነታችንን እና የምእመናንን ደኅንነት በሕግ አግባብ ማስከበር ይቻል ዘንድ ልክ እንደ ዋናው መሥሪያ ቤት በሁሉም ክልሎች ውስጥ ባሉት አህጉረ ስብከት የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ጉባኤው ወስኗል፡፡
15. ወጣቱ ትውልድ በእምነቱ ጸንቶና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ በእውቀትና በሥነምግባር ይታነጽ ዘንድ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር እና አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡
16. የ2016 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀትን አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል ተዘጋጅቶ የቀረበውን የበጀት ድልድል ጉባኤው መርምሮ በማጽደቅ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
17. የቤተ ክርስቲያናችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈቱት እና የልማት ተቋማት የሚጠናከሩት ዘመኑን የዋጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር እና በእቅድ ተደግፎ በእውቀት ላይ የተመሠረተ የሀብትና የንብረት አስተዳደር ማስፈን ሲችል መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡
በመሆኑም በባለፈው ጉባኤ የጸደቀው የ10 ዓመት የመሪ እቅድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት የመሪ ዕቅዱ አፈጻጸም እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ
ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 19 ቀን 2016፮ ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
*
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ላይ በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻውን ሥርዓተ ጸሎት ከፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
በመሆኑም ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዲሁም ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. የ2016 ዓ.ም. የመንበረ ፓትርያርክ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ያሳለፈውን የጋራ የአቋም መግለጫ በመመርመርና አስፈላጊውን ማሻሻያዎች በማድረግ የበጀት ዓመቱ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ መመሪያ እንዲሆን ጉባኤው አጽድቆታል፡፡
2. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀቱን የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን መወጣት ትችል ዘንድ በአዲስ እንዲደራጁ ተጠንተው የቀረቡትን የአህጉረ ስብከት ይደራጅልን ጥያቄዎችን በመመርመር፡-
ሀ. የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣
ለ. የሰሜን ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት
ሐ. የጎፋና ባስኬቶ ዞን ሀገረ ስብከት
መ. የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሀገረ ስብከት እራሳቸውን ችለው ሀገረ ስብከት ሆነው ተደራጅተው እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3. ቤተ ክርስቲያናችን የመንፈሳዊ ኮሌጆቿን ቁጥር ከፍ በማድረግ የአገልጋይ መምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ባላት እቅድ መሠረት ተጠንተው ከቀረቡት መካከል በ2016 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ፣ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ደብረ ታቦር ከተማ ላይ ሁለት መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲቋቋሙ፣ በማዕከላዊ ጐንደር ሀገረ ስብከት ርእሰ ከተማ ውስጥ ለሚገኙት የምስክር ጉባኤ ቤቶች በኮሌጅ ደረጃ በጀት እንዲመደብላቸው እና በከንባታ ሐድያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሆሣዕና ከተማ ላይ አንድ የካህናት ማሠልጠኛ እንዲከፈት ጉባኤው ወስኗል፡፡
4. ቤተ ክርስቲያናችን ከውስጥና ከውጭ እየደረሱባት ያሉት ከፍተኛ የሆኑ ፈተናዎችን ተቋቁማ ሕልውናዋን አስከብራ መቀጠል ትችል ዘንድ ፡-
ሀ. ውስጣዊ ችግሮቻችን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በጠበቀ በውይይት እንዲፈቱ፣
ለ. ውጫዊ ችግሮችንና የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ በችግሮቹ ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመነጋገር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና የቤተ ክርስቲያናችን መብትና ሕልውና ተጠብቆ እንዲቀጥል እንዲደረግ፣
ሐ. ለቤተ ክርስቲያናችን ሕልውና አደጋ የሆኑና ሊሆኑ የሚችሉ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን አስመልክቶ በአግባቡ ተጠንተውናበማስረጃ ተተንትነው ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
5. ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ሳንጽናና ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና አለመግባባቶች እያስከተሉት ያለው የንጹሐን የሰው ሕይወት መጥፍትና የንብረት ውድመት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን በእጅጉ አሳዝኖታል፡፡ በመሆኑም ችግሩ በውይይትና በስምምነት እንዲፈታ የፌዴራልን የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በግጭቱ ተሳትፎና ድርሻ ያላችሁ በሁሉም አካባቢ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ የበኩላችሁን ሚና በመወጣት እናት አገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟና አንድነቷ ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአደራ ጭምር በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
6. በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተከሠተ ያለው ችግርና ፈተና የሚወገደው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በሕብረት ለችግሮቹ መፈታት ድርሻ እንዳለን አውቀን እንደየእምነታችን አስተምህሮ በጸሎትና በምሕላ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር በንስሓ መመለስ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም ስለ ሀገራችን ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸምና መላው ሕዝበ ክርስቲያንም በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
7. የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክና ለሀገረ መንግስት ምሥረታና እድገት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በማዕከል ደረጃ በማስረጃ አስደግፎ በመጻፍና በማደራጀት ትውልዱ እንዲረዳው በማድረግ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሕልውና አደጋ የሆነውን የሐሰት ትርክት መከላከል ይቻል ዘንድ የዝግጅት ሥራው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል በሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ተቆጣጣሪነት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና የታሪክ ተመራማሪዎችን በማሳተፍ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡
8. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎና ሚና በተመለከተ ጉባኤው በስፋት የተወያየ ሲሆን ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ ችግራችንን እንደሚፈታና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚነገሩትን የሐሰት ትርክቶች ሁሉ የሚታረሙበት እንደሚሆን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖረን ተሳትፎና ሚና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ እንዲፈጸም ሆኖ የምክክር ኮሚሽኑም ይህን የቤተ ክርስቲያናችን እቅድ በመርሐግብሩ በማካተት ቤተ ክርስቲያናችን የድርሻዋን እንድትወጣ እድሉን እንዲያመቻችልን ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡
9. የመረጃ ቋት መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሁሉም ክልል አህጉረ ስብከት ደረጃ በማቋቋም እና እለት እለት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚከሰቱትን ችግሮችና የመብት ጥሰቶች በመረጃና ማስረጃ አስደግፎ ለዋናው ማዕከል የመረጃ ቋት በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ በአንዱ ቦታ ችግር ሲደርስ በመላ ሀገሪቱ እና በውጭው ክፍለ ዓለማት ባሉት አህጉረ ስብከት በአንድነት ድምፅ መሆን ይቻል ዘንድ ተጠሪነታቸው ለዋናው ማዕከል የሆኑ የመረጃ ቋት ማዕከላት በሁሉም አህጉረ ስብከት ተቋቁመው ወደሥራ እንዲገቡ ጉባኤው ወስኗል፡፡
10. የቤተ ክርስቲያናችን ሀብትና ንብረት የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ የሚዳሰሱና እና የማይዳሰሱ ቅርሶችንና በአጠቃላይ ንዋየ ቅድሳቶቻችን ግለሰቦች እና ተቋማት በሕገወጥ መንገድ አትመውና አሳትመው በማሠራጨትና ትክክለኛ ቅጅውን አዛብቶ በማተም ቤተ ክርስቲያናችን ለሐሰተኛ ትርክት እንድትዳረግ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ በደል እየተፈጸመባት መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በኩል የተጀመረው የአዕምሯዊ ንብረት ምዝገባ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ጥቅም እንዲከበር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፲፱ (19) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ኤርትራ_አገር የሚገኘውን በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ አስደናቂውን #ፃዕዳ_ዓምባ_ቅድስት_ሥላሴ_ገዳምን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
እንኳን ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ_ክህነት_ከንግሥና ጋር አስተባብሮ ለያዘው #40_ዓመት_ሙሉ_ሰማያዊ_ኅብስትና_ጽዋ ከሰማይ እየወረደለት ለቀደሰው #ለጻድቁ_ለቅዱስ_ለይምርሐነ_ክርስቶስ ለዕረፍት በዓል፣ ለታላቁ አባት ከመቃብራቸው በሚወጠው #በእምነታቸውና_በጠበል_ፈዋሽነታቸው ለመታወቁት #ለአቡነ_ሐራ_ድንግል_ለልደታቸው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ለቅዱስ_በርተሎሜዎስና_ለሚስቱ ለዕረፍታቸው በዓል፣ #ስለ_ጳውሎስ_ሳምሳጢ በአንጾኪያ የቤተ ክርስቲያ አንድነት ስብሰባ ለተደረገበትና #ለጸይለም አገር ለሆነ ለከበረ አባት #አቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ እንደ በግ ከታረዱ #ከመጥራ_ጻድቃ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌹🌹🌹🌹✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹
ማሕሌተ ጽጌ በግራር ደብረ ዓባይ ቤተክርስቲያን ጥቅምት 17 / 2016 ዓ.ም
የሳምንት ሰው ይበለን!!!
✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨
🌹🌹🌹🌹✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹
ማሕሌተ ጽጌ በግራር ደብረ ዓባይ ቤተክርስቲያን ጥቅምት 17 / 2016 ዓ.ም
የሳምንት ሰው ይበለን!!!
✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨
🌹🌹🌹🌹✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹
ማሕሌተ ጽጌ በግራር ደብረ ዓባይ ቤተክርስቲያን ጥቅምት 17 / 2016 ዓ.ም
የሳምንት ሰው ይበለን!!!
✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨
🌹🌹🌹🌹✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹
ማህሌተ ጽጌ በግራር ደብረ ዓባይ ቤተክርስቲያን ጥቅምት 17 / 2016 ዓ.ም
የሳምንት ሰው ይበለን!!!
✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፲፰ (18) ቀን።
✝ እንኳን #ለእስክድርያ_ሃያ_ሦስተኛ_ሊቀ_ጳጳስ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቴዎፍሎስና ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፈ ለከበረ #ለመነኰስ_ቅዱስ_ሮማኖስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሰማዕት_ቅዱስ_ዮሐንስ፣ #ከቅዱሳን_አድራኒ_ከአርቴማዎስ_ከአርስጦስ #ከሉዲኖስ_ከአስማኒትና
_ከሰባቱ ልጆቿ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "አንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኀ። ወአንተ ገበርከ አድባረ ወምድረ ኵሎ። ክረምተ ወሐጋየ ዘአንተ ፈጠርከ"። መዝ 73፥16-17። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 7፥1-14፣ ራዕ.ዮሐ 21፥21-ፍ.ም፣ የሐዋ.ሥራ 22፥1-6። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 6፥25-34። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ቴዎፍሎስ፣ የቅዱስ ሮማኖስ የዕረፍት በዓልና የማኅሌተ ጽጌ አራተኛ ሳምንት (ሰንበት)ና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ !
ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም
የጥቅምት 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለተከታታይ 6 ቀናት ማኅበራዊ ፣ መንፈሳዊ እንዲሁም አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ በማሳለፍ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
ጉባኤው በዛሬ በ 6 ተኛ ቀን ውሎው አስተዳደራዊ ጉዳይን የያዘ የመሪ ዕቅድ ተመልክቶ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ተጨማሪ ግብዓት ተጨምሮበት ለግንቦት ርክበ ካህናት እንዲቀርብ ወስኗል፡፡
በጸደቁ አጀንዳዎች ላይ ላለፈው አንድ ሳምንት ሲወያይ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ በማድረግ መግባባት በሰፈነበት ሁኔታ ጉባኤውን ማጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን በማጠናቀቂያው በሕግ ፣ በመሪ ዕቅድ ትግበራ እና በልዩ ልዩ ጉዳዮች ጥናት ላቀረቡ እና ማብራሪያ ለሰጡ ባለሙያዎች ብፁዕ ወቅዱስ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ማቅረባቸውን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን አስመልክቶ ቅዱስነታቸው ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫ እንደሚሰጡ ተገልጿል።
©EOTC TV
ያጋጠማቸውን መከራ የተደረገውን ተአምራት ሁሉ መዘርዘር እመቤታችን እንዳለችው ምን ወረቀት ሊበቃ ይችላል? ጦጣና ዝንጀሮ ስለሆኑት እነ ትእማን ዘመዶች ወይስ መሬት ተክፍታ ስለዋጠቻቸው ትእማንና ኮቲባ ታሪክ እንተርክ ተራሮችና ኮረብቶች የሰገዱለትን ወይስ ግመሎቹ ሐውልት የሆኑበትን ታሪክ እንጻፍ የግብጽን ጣዖታት ስለመሰባበሩ ወይስ ዕረፍት እስኪያጣ ስለፈወሳቸው ሕሙማን እንተርክ በዚያች መንገድ ለማለፉ ምልክት ትሆን ዘንድ ተክሎ ስላጸደቃት የዮሴፍ የወይራ በትር ወይስ የተጠለሉበትን ጨለማ ቤት እንዴት በብርሃን እንደሞላው እንናገር የቱ ተነሥቶ የቱ ይቀራል እንዲያው አድንቆ ማለፍ እንጂ፡፡
ውድ አንባብያን አንድ ግን ሳንተርክላችሁ የማናልፈው ታሪክ አለና እርሱን ብቻ በጥቂቱ እንተርከው፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው እመቤታችንን ካስጨነቁ ገጠመኞች መካከል የሁለቱ ሽፍቶች ነገር ዋነኛው ነው፡፡ አንድ ግብጻዊና አንድ ዕብራዊ ሽፍቶች በጋራ ነፍስ እየገደሉ ቋንጃ እየቆረጡ ሀብት ንብረት እየዘረፉ ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህ ሽፍቶች እመቤታቸንን በስደቷ ገጥመዋታል፡፡ ስለ እነዚህ ሽፍቶች እንዲህ ትላለች ግብጽ እንደገባን ከበጋው ፀሐይ እናርፍ ዘንድ ከከተማው ውጭ ከዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጥን ይህም ግንቦት ፳፬ ቀን ነው፡፡ ሁለት ሽፍቶችም በመንገድ አለፉ አንዱ ግብጻዊ አንዱ ዕብራዊ ነው፡፡ ዕብራዊው ግብጻዊውን የዚህችን ሴት ልብስ የልጇንም ልብስ ልወስደው እሻለሁ የነገሥታቱን ልብስ ይመስላልና አለው፡፡ ግብጻዊውም ከተፈጠርኩ ጀምሮ እንደዚህ ያለ ሕፃን አላየሁምና ተው አለው፡፡ ውኃ ፍለጋ ሄጄ ስመለስ የልጄን ጫማ ወስደውት አገኘሁ፡፡ እነ ዮሴፍንም ቀስቅሼ የልጄን ጫማ ወስደውታል የልጄን ጫማ ከማጥፋት በቀር የተጠቀምኩት ነገር የለም ብዬ አለቀስኩ ትላለች፡፡
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ከተማ ከተማውን እንሂድ ሲል እመቤታችን ግን የሰውን ክፋት ተረድታለችና ልጄን ይገሉብኛል፤ ጫካ ጫካውን እንሂድ ትላለች፡፡ የሆነውንም እንዲህ ስትል ትቀጥላለች፡፡ ፀሐይ ሲገባ ወደ ተራራው ሄድን ስንጓዝም ለመንጋት ትንሽ ቀረው፡፡ በሌላኛይቱ ሀገር ቀደም ሲል ያየናቸው ሁለቱ ሽፍታዎች እስከዚህች ቦታ ድረስ ተከተሉን፡፡ በዚያ ቦታ በተመለከቱን ጊዜ ዕርቃናቸውን ወደ እኛ እየሮጡ መጡ፡፡ በእጆቻቸውም የተመዘዙ ሰይፎች ነበሩ፡፡ ስንከተላችሁ ብዙ ጊዜ ደከምን ነገር ግን ከዛሬ በቀር የምንይዛችሁን ቀን አላገኘንም አሁን ግን በእጃችን ወድቃችኋልና እንበቀላችኋለን አሉን ድርሳነ ማርያም፡፡
ከዚህ በኋላ ዘለው የተወደደ ልጇን ከእቅፏ ወሰዱባት፡፡ ልብሶቹንም ገፈፉት የእርሷንም መጎናጸፊያ ከላይዋ ላየ ገፈፏት አረጋዊ ዮሴፍም እንደ በግ ሆነላቸው ልብሱንም ከላዩ ላይ ቀደዱት ሰሎሜም ይህንን በተመለከተች ጊዜ በድንጋጤ መጎናጸፊዋን ጣለች፡፡ በዚህ አላበቁም ልብሶቻቸውን ከወሰዱ በኋላ እርስ በርስ ቆመው ሲነጋገሩ እንዳልሄዱ ባየች ጊዜ ጽኑ ፍርሃትን ፈራች ልጄን ሊገድሉብኝ ነው እንጅ ሌባ ቀማኛ ከቀማ በኋላ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ይሄዳል ብላ እጅግ አለቀሰች፡፡ እንዲህም አለች ተወዳጅ ልጄ ሆይ ወዮልኝ በዚህች ሰዓት የት እሄዳለሁ ወደየትስ እሸሻለሁ እንዳይገድልህ ርጉም ሄሮድስን በመፍራት ከኢየሩሳሌም ሸሸሁ ከሀገሬ ብቀመጥ ኖሮ ይህንን ሁሉ ድካም ባላወቅሁም ነበር፡፡ የዐይኖቼ ብርሃን ሆይ ከዚህ ሀገር ማንን አውቃለሁ? ያለሁት በምድረ በዳ ነው፤ ዛሬ ከእኔ ጋር ያለቅሱ ዘንድ የሚያውቁኝ የት አሉ? ተወዳጅ ልጄ ሆይ፥ ከአንተ ጋር በመሸሽ አንድ ቀን እንኳ ባልደከምሁ ነበር፤ በዚህ ቦታ አንተን ሲገድሉህ ከማያቸው ቀድመው ቢገድሉኝ በተሻለኝ ነበር፤ ሄሮድስ ልጆቻቸውን የገደለባቸውን ሴቶች ባያቸው ኖሮ ከእኔ ጋር ያለቅሱ ዘንድ በወደድሁ ነበር ብላ አለቀሰች፡፡
እነዚያ ወንበዴዎች ግን ይጨቃጨቁ የነበረው ግብጻዊው ለዕብራዊው “እባክህ ልብሳቸውን እንመልስላቸው” እያለው ስለነበር ነው፡፡ ‹‹እለምንሃለሁ፤ በፊታቸው ከሰው ሁሉ ይልቅ ታላቅ ብርሃንን እመለከታለሁና፤ ሕፃኑም የንጉሥ ልጅ ይመስላል፤ የሚመስለውም አላየሁምና›› አለው፡፡ አይሁዳዊውም “አልሰማህም? የነገሥታት ልብሶች ናቸውና›› አለው፡፡ ግብጻዊውም ማሳመን እንዳልቻለ ባየ ጊዜ ከቤተ ልሔም ጀምሮ የዘረፉትን ብዙ ሀብት እንደሚለቅለት ለመነው፤ በዚህም ተስማምቷል፤ ያ ግብጻዊ አዝኖላቸው ልብሳቸውን መልሶላቸው ጌታንም በትከሻው ተሸክሞ ሸኛቸው፡፡
ጌታም ለተወዳጅ እናቱ እንዲህ አላት፤ ‹‹እነዚህን ሁለት ወንበዴዎች ታያለሽን? በኢየሩሳሌም አይሁድ አንዱን በቀኜ አንዱን በግራዬ አድርገው ይሰቅሏቸዋል፡፡ ይህ በልቡናው ቸርነት ያለውም የቸር አባቴ ነው፤ እርሱ በመስቀል እያለሁ ያምንብኛል፤ አዳምና ዘሮቹን ቀድሞም መንግሥተ ሰማያት ይገባል›› አላት፡፡ እነዚህ ሽፍቶች ጥጦስና ዳክርስ ናቸው፡፡ (ማቴ፳፯፥፴፰) ፈያታዊ ዘየማንና ፈያታዊ ዘጸጋም ተብለው በኋላ ከክርስቶስ ጋር በግራና በቀኝ የተሰቀሉት እነዚህ ሽፍቶች ናቸው፡፡
እንደ እውነቱ ቢሆን ከግብጻዊው ይልቅ ዕብራዊው ሊያዝንላቸው በተገባ ነበር፡፡ ነገር ግን ጨከነባቸው፤ ግብጻዊው ግን ቸርነት አሳይቷልና ቸርነት ተደረገለት፡፡ በመንግሥተ ሰማያትም አዳምን በመቅደም የገነት ጠባቂዋ ሱራፊን አስደመመው፡፡ ከባለ ተስፋው አዳም ቀድሞ ገነት ገብቷልና፡፡ ተወዳጆች ሆይ! መቼም የስደቷን ነገር ተናግሮ መጨረስ፣ ተመራምሮ መድረስ የሚቻለን ሆኖ አይደለም፤ እንዲያው ለመዘከር ያህል እንጂ፡፡
ቸር እንሰንብት!!!
ይቆየን!
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨
"ሰሚዖ ሕፃን ለእሙ ገዓራ ባረከ ኰኩሐ ወአንቅዐ ማየ እምታሕተ እግራ ወእምኔሃ ለጽምኣ ትስተይ አመራ"ሕፃን ልጇ ክርስቶስ የእናቱን ጭንቀት ሰምቶ ዓለቱን ባረከው ከእግሯ ሥርም ውኃን አፈለቀ ከዚያችም ለጥሟ ትጠጣ ዘንድ አመለከታት እንዳለ ደራሲ ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቆ በእሳት ዓምድ መርቶ በደመና መሶብ መና አዘግኖ እስራኤልን የመራ የስደተኞች ተስፋ የራብተኞች ምግብ ልጇ ለእናቱ አዘነላት፡፡ሰቆቃወ ድንግል እንባዋንም በእጆቹ ጠረገላት ተጠምታለችና ውኃ ፍለጋ ሄዳ አንድም ሰው ስላላዘነላት አዝናለችና አዘነላት እንደ መዓር ጣፋጭ እንደ ወተት ነጭ ለሚጠጡት ሁሉ ፈውስና ጤና የሚሆን ውኃ ከቆመችበት ምድር ከእግሯ ሥር አፈለቀላት፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ያ ምንጭ የማርያም ምንጭ እየተባለ ይጠራል፡፡ እመቤታችንም በዚያ ውኃ የልጇን ልብስ አጥባ በደፋችበት ቦታ ቅብዓ ሜሮን የሚዘጋጅበት ዕፅ በቅሎበታል፡፡
በዚህ ታሪክ ውስጥ አንድ የሚያሳዝን ነገር ተከስቷል፡፡ ከእናቱ አገር የፈለቀው ለሕሙማን ፈውስ የሆነው ውኃ ለሀገሩ ሰዎች ግን እንደ እሬት መራራ ሆኖባቸዋል፡፡ ለነጋድያን ለፈላስያን ግን እንደ ማር የሚጣፍጥ ፈውሰ ሥጋ የሚያሰጥ አድርጎታል፡፡ ከሀገሩ ሰዎች አንዳቸው እንኳን አይዳን ብሎ ረግሞታል፡፡ ያሳዝናል መራራውን የሚያጠፍጠውን ለተጠሙት ሁሉ የሕይወት ውኃ የሚሰጠውን ለሕሙማን ፈውስ ለስዱዳን ሞገስ የሆነውን ክርስቶስን እና እናቱን አልተቀበሉምና ትንሽም አልራሩላቸውምና ርግማን ሆነባቸው፡፡
🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹🌹✨🌹✨🌹🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹
