ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
إظهار المزيد636
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-47 أيام
-1230 أيام
أرشيف المشاركات
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን ክርስቶስ ለሚወዱ #ለቅዱስ_እንድራኒቆስና #ሚስቱ_ቅድስት_አትናስያ_ለመታሰቢያ_በዐላቸው በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከቅዱሳን አባቶቻችን #አብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_እንድራኒቆስና_ሚስቱ_ቅድስት_አትናስያ፦ እነርሱም ከአንጾኪያ ከተማ ነበሩ። በወርቅና በብርም የከበሩ ባለጸጎች ነበሩ ከገንዘባቸውም ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር።
❤ ከዚህም በኃላ አንድ ወንድ ልጅና አንዲት ሴት ልጅን ወለዱ ወንዱን ዮሐንስ ሴቲቱንም ማርያም ብለው ሰየሟቸው ልጆችም አደጉ እንዱራኒቅስና ሚስቱም እንግዳ በመቀበል ለድኆችና ለምስኪኖች በመመጽወት በጎ ሥራን አበዙ እነርሱም መገናኘትን ትተው ሰውነታቸውን በንጽሕና ጠበቁ።
❤ ልጆቻቸውም ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆናቸው ጊዜ የሆድ ዝማ በሽታ ታመው በአንዲት ቀንም ሞቱ እንዲራኒቆስም አይቶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ራሱን ጥሎ እንዲህ ብሎ አለቀሰ "ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ወጣሁ ወደ እግዚአብሔርም ራቁቴን እሔዳለሁ እርሱም ሰጠ እርሱም ወሰደ የእግዚአብሔር የጌትነቱ ስም የተባረከ ይሁን ለዘላለሙ አሜን"። እናታቸውም ለሞት እስከምትደርስ እጅግ አዘነች ልጆቿ ወደ ተቀበሩበት ወደ ዐፀደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች ከኀዘንዋም ብዛት የተነሳ አንቀላፋች በእንቅልፏም ውስጥ "በልጆችሽ ሞተ አታልቅሺ እነርሱ ግን በሰማያት ደስ እያላቸው ናቸው" እያለ በመነኰስ አምሳል ሲነግራት አየች። ይህንንም ሰምታ ሒዳ ለባሏ ነገረችው።
❤ ከዚህም በኃላ ይህን ዓለም ይተዉ ዘንድ ተስማሙ ገንዘባቸውንም ሁሉ ምንም ሳያስቀሩ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጡ በሌሊትም ወጥተው ወደ እስክንድርያ ከተማ ደረሱ ሚስቱንም በዚያ ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በአባ ዳንኤል ዘንድ መነኰሰ። ከዚያም ተመልሶ ሚስቱ አትናስያን ወደ ሴቶች ደናግል ገዳም ወሰዳት በዚያም ተዋት።
❤ ከዐሥራ ሁለት ዓመትም በኋላ እንድራኒቆስ ከቅዱሳት መካናት ይባረክ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ አባ ዳንኤልን ለመነው ፈቀደለትም በመድኃኒታችንም ቸርነት ሚስቱ አትናስያ በወንድ አምሳል በጉዞ ላይ ተገናኘችው ሚስቱ እንደሆነችም አለወቀም እርሷ ግን አወቀችው ነገር ግን ሚስቱ እንደሆነች አልገለጠችለትም።
❤ ወደ ቅዱሳት መካናትም በደረሱ ጊዜ ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አባ ዳንኤል በአንድነት ተመለሱ። አባ ዳንኤልም ሚስቱ እንደሆነች በመንፈስ ቅዱስ አውቆ እንድራኒቆስን "ባልንጀራ ካደረግኸው ከዚህ መነኰስ ጋራ በአንድ ቦታ ኑሩ እርሱ ቅዱስ ነውና" አለው። ዐሥራ ሁለት ዓመትም በአንድነት ኖሩ ማንም የአወቀ አልነበረም።
❤ አባ ዳንኤልም ይጎበኛቸውና ስለ ነፍሳቸው ጥቅም ያስተምራቸው ነበር። ከዚህም በኃላ አትናስያ በታመመች ጊዜ ለእንድራኒቆስ "አባታችንን አባ ዳንኤልን ጥራልኝ" አለችው ሒዶም ለአባ ዳንኤል እንዲህ ብሎ ነገረው "ባልንጀራዬ ታሞ ለመሞት ተቃርቧልና ትጎበኘው ዘንድ ና"። በደረሰም ጊዜ በታላቅ ሕመም ላይ አገኛት እርሷም "ታቆርበኝ ዘንድ እሻለሁ" አለችው ያን ጊዜም ተፋጠነና ሥጋውንና ደሙን አቀበላት ከዚህም በኋላ አረፈች በሚገንዟትም ጊዜ ሴት እንደሆነች አገኙ ዳግመኛም ታሪኳንና ለባሏ ያወራቻቸውን ምልክቶች አገኙ።
❤ እንድራኒቆስም በአነበበ ጊዜ እርሷ ሚስቱ እንደሆነች አወቀ ደንግጦም ልቡ ተሠወረ ፊቱንም እየጻፈ ጮኸ ያለቅስ ጀመረ። ከጥቂት ቀን በኋላም ታመመ አረጋውያንም መጥተው በረከቱን ተቀበሉ ሥጋውንና ደሙንም ተቀበሉ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ እንድራኒቆስ በሚስቱ አትናስያ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 28 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰአሉ_ለነ_አብርሃም_ይስሐቅ_ወያዕቆብ አበወ ሕዝብ ወአሕዛብ ወዘመሐይምናን መክብብ ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ"። ትርጉም፦ የምዕመናን ሹሞች የአሕዛብና የሕዝብ አባቶች #አብርሃም_ይስሐቅ_ያዕቆብ ፈጽማችሁ ለምኑልን፡፡ #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በሰዓታት_ላይ፡፡
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለእንድራኒቆስ_ለምኔተ_አስቄጥስ ዘሐወጻ። እንዘ ይዘሩ ብዕሎ ዘኢኮነ ብዕለ ዐመፃ። #ወለአትናስያ_ሰላም ለነቢር ዘተባየፃ። ከመ ይእቲ ብእሲቱ እንበለ ይጠይቅ ገጻ። እስመ አዕፅምቲሃ በጽምእ ከመ ሣዕር ነቅጻ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_28።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወአንተሰ ብእሲ ዘከመ ነፍስየ። ማእምርየ ወዐውቅየ። ዘኅቡረ አስተጠዓምከ ሊተ መባልዕተ"። መዝ 54፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ 7፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 7፥1-9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ፊሊጶስ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ጻድቅ ለታላቁ ለጻድቅ ንጉሥ #ለቅዱስ_ላሊበላ_ባለቤት (ሚስት) #ለቅድስት_መስቀል_ክብራ_ለዕረፍቷ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_መስቀል_ክብራ፡- የትውልድ ሀገሯ ትግራይ ሽሬ አካባቢ ነው፡፡ ይኽችም ቅድስት የታላቁ ጻጽቅ ንጉሥ የቅዱስ ላሊበላ ባለቤት ስትሆን ሁለቱን ያጋባቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ዲዛኖችና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር ከመለሰው በኃላ ድጋሚ ተገልጦለት "...እንደ አንተ የተመረጠች ናት እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል፡፡
❤ ቅድስት መስቀል ክብራ ከቅዱስ ላሊበላ ይትባረክን የወለደች ሲሆን በ23 ዓመት ውስጥ ቅዱስ ላሊበላ 11 እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል፡፡ ከዚህም በኋላ ቅድስት መስቀል ክብራን መንና ትግራይ ገባች። ወደ ትግራይ እየመራ የወሰዳት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ እርሷን በትግራይ ቅዱስ ሚካኤል እንዲጠብቃት ከተዋት በኃላ ቅዱስ ላሊበላን ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ መንግሥተ ሰማያት አውጥቶታል፡፡
❤ ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ሆና መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃት ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከ 36ቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል፡፡ ይኽችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች፡፡ ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዲጠመቁ አድርጋለች፡፡
❤ ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ክልል ሽሬ አውራጃ መደባይ ታብር በተባለው ቦታ ላይ በስማ የተሰራ ትልቅ ገዳም አላት። እጅግ ውብ በሆኑ ሰንሰላታማ ትላላልቅ ድንጋዮች መካከል የሚገኝ አስደናቂና ጥንታዊ ገዳም ነው። ገዳሙ ከሽሬ ከተማ በእግር የ 7 ሰዓት መንገድ ያስኬዳል። የቅድስት መስቀል ክብራ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ እግዚአብሔር አምላክ ይማረን፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዐላት።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፳፮ (26) ቀን።
❤ እንኳን #ለእመቤታች_ድንግል_ማርያም_እጮኛዋ (ጠባቂ) ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆን ለተገባው #ለአረጋዊው_ለጻድቁ_ለቅዱስ_ዮሴፍ_ለዕረፍት በዐል፣ #ለኢትዮጵያው_ለመጀመርያው_ሊቀ_ጳጳስ #ለአቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ለዕረፍት በዐልና #ለእስክድርያው_ሊቀ_ጳጳስ በጉባኤ ቁስጥንጥንያ ከሃዲያን (መናፍቃንን) መቅዶንዮስን፣ ሰባልዮስና አቡሊናርዮስንም ተከራክሮ ለረታቸው #ለአቡነ_ጢሞቴዎስ_ለዕረፍት_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከአባ_ሮዲስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የእመቤታችን_ጠባቂ ( እጮኛ) #ጻድቁ_ቅዱስ_ዮሴፍ፦ መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው ነው
❤ እርሱም እምቤታችንን በርሱ ዘንድ ካስጠበቋት ጀምሮ በሁሉ ነገር ያገለግላት ነበር። በመከራዋም ሁሉ አልተለያትም። በወለደችም ጊዜ በቤተ ልሔም ከርሷ ጋራ ነበረ። ወደ ግብጽም በተሰደደች ጊዜ ከእርሷ ጋራ ብዙ መከራ ደረሰበት። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ጊዜው በደረሰ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን ጠርቶ ተሰናበታቸው እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሐምሌ 26 ቀን ሰጠ። የዘላለምንም ሕይወት ወረሰ።
❤ በዐረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃበር አኖሩት። ዕረፍቱም ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዊ በዐሥራ ስድስት ዓመት ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ቅዱስ ዮሴፍ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን (ፍሬምናጦስ)፦ ዜናውም እንዲህ ነው ስሙ ሜሮጵዮስ የሚባል የጥበበኞች አለቃ አንድ ሰው ወደ ሕንድ አገር ሊአልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር መጣ ከእርሱም ጋራ ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ። የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ የሁለተኛውም ኤዴስዮስ ይባላል። ሲድራኮስ የሚሉትም አሉ። በኢትዮጵያ በኩል ወዳለው ወደ አፍሪቃ ባሕር ወደብ ደረሱ ልቡ የተመኘችውን የኢትዮጵያን አገር መልካምነቷን ሁሉ ተመለከተ።
❤ ከዚህም በኃላ በድንገት ወንበዴዎች ተነሥተው በመርከብ ከአሉት ሁሉ ጋር ገደሉት እኒህ ሁለት ልጆች ግን ተረፉ። የአገሩ ሰዎችም አገኙዋቸው ወደ ንጉሥም ወስደው አንድ እጅ መነሻ አድርገው እነርሱን ሰጡት ንጉሡም ተቀበላቸው።
❤ ከጥቂት ቀኖች በኃላም ንጉሡ ኤዴስዮስን በፊቱ የሚቆም ጋሻ ዣግሬ አድርጎ ሾመው ፍሬምናጦስን ግን በገንዘቡ ሁሉ ላይ በጅሮንድ አድርጎ ሾመው ይህም ንጉሥ የአብርሀና የአጽብሐ አባታቸው ስሙ አይዛና የተባለው ነበር። እነርሱ ሕፃናት ሳሉም አረፈ። እኒህም አካለ መጠን እስከሚያደርሱ ድረስ የንጉሡን ልጆች እያሳደጉ ኖሩ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ማመንንም አስተማሩዋቸው።
❤ የንጉሡም ልጆች አድገው በነገሡ ጊዜ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመለሰ ፍሬምናጦስ ግን ወደ ግብጽ ሔደ ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አትናቴዎስም ደረሰ። የደረሰብትንም ሁሉ ነገረው። ስለ ኢትዮጵያውያንም ሃይማኖት ጳጳስ ሳይኖራቸው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳመኑ ነገረው። አባ አትናቴዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ ፍሬምናጦስንም የነጻ ሕዝብ አገር ለሆነችው ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስ ይሆን ዘንድ ግድ አለው። ጵጵስነትንም ሾመ ከታላቅ አክብሮት ጋራ ላከው በአብርሀና በአጽብሐ ዘመነ መንግሥትም ወደ ኢትዮጵያ በደረሰ ጊዜ በክብር ተቀበሉት።
❤ በኢትዮጵያም አገሮች ሁሉ የቀናች ሃይማኖትን ሰበከ አስተማረም ክብር ይግባውና ክርስቶስን የጌትነቱን ብርሀን በሁሉ አገሮች ገለጠ ስለዚህም ብርሃንን ገላጭ ሰላማ ተባለ ሁሉንም አስተካክሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለም አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የእስክንድር_ሊቀ_ጳጳስ_አባ_ጢሞቴዎስ፦ በተሾመ ጊዜም የክርስቶስን መንጋዎች ከአርዮስ ከመቅዶንዮስና ከሰባልዮስ ተኩላዎች ጠበቀ። ይህም አባት በተሾመ በስድስተኛው ዓመት ለክርስቲያን ወገኖች ደግ የሆነ ቴዎዶስዮስ ነገሠ በዚያችም ዓመት ክብር ይግባውና መንፈስ ቅዱስን ስለ ካደው ስለ መቅዶንዮስ በቁስጥንጥንያ የተሰበሰቡ የመቶ ሃምሳ ቅዱሳን ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ተደረገ ይህም አባት ጢሞቴዎስ ሊቀ ጉባኤ ሆኖ መቅዶንዮስንና ሰባልዮስን አቡሊናርዮስንም ተከራከራቸው። ረትቶም አሳፈራቸው። እነሆ የክህደታቸውንና የክርክራቸውንም ነገር የካቲት አንድ ቀን ላይ ጽፈናል።
❤ ከዚህም በኃላ ይህ አባት በሹመቱ ዘመን አብያተ ክርስቲያናትን በማነፅና በሚገባውም ሥራ ሁሉ በእድሳታቸውም አሰበ። ለመጻተኞችም ቤቶችን ሠራላቸው።
❤ መንጋዎቹንም ሁልጊዜ ያስተምራቸው ነበር በመልካም እውቀቱና በትምህርቱ ጣዕም ሁልጊዜም በማስረዳቱ በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ከአርዮስና ከመቅዶንዮስ ወገኖችም ብዙዎቹን መልሶ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሆነች የቀናች ሃይማኖት አስገባቸው።
❤ በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ መንበርም ላይ ዘጠኝ ዓመት ተኩል ኖረ ከዚያም በኋላ ሐምሌ 26 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጢሞቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 26 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለጢሞቴዎስ_ለጴጥሮስ_እኍሁ። ጳጳሰ ሀገር ዘእምቅድሜሁ። በቊስጥንጥንያ ዘኮነ ሊቀ ማኅበሮሙ ለእሊአሁ። ተክዕወ ለምእመናን እምሁከተ ዐለውት ዘሠርሑ። ሰላም ብዙኅ እስከ የኀልፍ ወርኁ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 26።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዚአከ ውእቱ ሰማያት ወእንቲአከ ይእቲ ምድር። ዓለምኒ በምልዑ ዘአንተ ሣረርከ። ባሕረ ወመስዐ ዘአንተ ፈጠርከ። መዝ 88፥11-12። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 6፥1-15።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ይምጹኡ ተናብልት እምግብፅ። ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር። ነገስተ ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር"። መዝ 67፥31-32። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 6፥3-20፣ 1ኛ ዮሐ 2፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 5፥20-34። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 1፥18-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን ማርያም ወይም የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአረጋዊው የቅዱስ ዮሴፍና የአባ ሰላም ከሳቴ ብርሃን የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፳፮ (26) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያው_ጻድቅ የጌታችን መከራ በማሰብ ከተወለዱ ጀምሮ ተላጭተውት የማያውቁትን ፀጉራቸውን ከትልቅ ዛፍ ላይ እያሠሩ ይጸልዩ ለነበሩ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌሉያ ለዕረፍት በዐል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌሉያ፦ የትውልድ ሀገራቸው ተንቤን ነው፡፡ አባታቸው ይስሐለነ እግዚእ እናታቸው ትቀድሰነ ማርያም ይባላሉ፡፡ አቡነ አቢየ እግዚእ አጎታቸው ናቸው፡፡ እናታቸው እሳቸውን ፀንሳ ሳለ ቡራኬ ለመቀበል ወደ ወንድሟ ስትሄድ አቡነ አቢየ እግዚእ መሬት ላይ ወድቀው ሰግደውላታል፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም "ለዚህች ሴት እንዴት ሰገዱላት?" ብለው ቢጠይቋቸው አቡነ አቢየ እግዚእ ስለ አቡነ ሳሙኤል ክብርና ጽድቅ ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡
❤ አቡነ ሳሙኤል ሲወለዱ እናታቸው ለአቡነ ዐቢየ እግዚእ ሰጠቻቸው፣ እርሳቸውም በሃይማኖት በመግባር ኮትኩተው ሁሉን አስተምረው አሳደጓቸው፡፡ አባታችን የጻድቃንና የሰማዕታትን ታሪክ እያነበቡ ያዝኑና ያለቅሱ ነበር፡፡ እንደ እነርሱ በሆንኩም እያሉ ይመኙ ነበር፡፡ አቡነ አቢየ እግዚእ ሀሳባቸውን በመንፈስ ተረድተውላቸው ነበርና መርቀው ባርከው አሰናበቷቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም በሕፃንነታቸው መንነው ወደ አቡነ እንጦንዮስ ገዳም ገብተው በ14 ዓመታቸው መነኰሱ፡፡
❤ ከየት እንደመጣ የማይታወቅና መላ አካሉ እንደበረዶ ነጭ የሆነ አንበሳ መጥቶ እየመራቸው አሁን ደብረ ሃሌሉያ እየተባለ ወደሚጠራው ገዳማቸው ሄደው በዓታቸውን አጽንተው ገዳሙን መሠረቱት፡፡ አቡነ ሳሙኤል ዘሀለሎም እየተባሉ ይጠራሉ፡፡
❤ ጻድቁ የጌታችን መከራ በማሰብ ከተወለዱ ጀምሮ ተላጭተውት የማያውቁትን ፀጉራቸውን ከትልቅ ዛፍ ላይ እያሠሩ ይጸልዩ ነበር፡፡ እንዲሁ አድርገው ዛፍ ላይ ራሳቸውን ሰቅለው 40 ቀንና 40 ሌሊት ሲጸልዩ በመጨረሻ የታሠሩበት ፀጉራቸው ተነቅሎ ከመሬት ላይ ወደቁ፡፡ ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን አስከትሎ ተገልጦላቸው እጃቸውን ይዞ አንሥቷቸዋል፡፡ "ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?" ቢላቸው ስለ ሀገራችን ሰላም ይልቁንም በዚህ በቆረቆሩት ገዳማቸው የሚኖሩትን ልጆቻቸውን እንዲጠብቅላቸው ለመኑት፡፡
❤ ጌታችንም በገዳማቸው ውስጥ በፍጹም ሕማም፣ ደዌና ተስቦ በሽታ እንደማይገባ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ለመንግሥተ ሰማያትም ያልታጨ ሰው በዚህ ገዳም ገብቶ አይቀበርም፡፡ ጻድቁ ከዛፉ ላይ ወድቀው ሳለ ጌታችንን እጨብጣለሁ ብለው የዘረጓት እጃቸው እያበራች ኖራለች፡፡ እንደ መብረቅም እየጮኸች ለገዳሙ እንደ ደወል ታገለግል ነበር፡፡ በመጨረሻም ሊያርፉ ሲሉ ልጆቻቸውን ሰብስበው ባርከዋቸዋል፡፡ ያ አቡነ ሳሙኤል የባረኩበት ቡራኬም በመጽሐፈ ግንዘት ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ዛሬም ድረስ ሰው ሲሞት "ቡራኬ ዘአቡነ ሳሙኤል" ብሎ ካህኑ ይደግማል፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ በከተማ አካባቢ ግን እየተደረገ አይደለም፡፡ አቡነ ሳሙኤል ብዙዎችን ያመነኰሱ ሲሆን እንደነ አቡነ ተጠምቀ መድኅን፣ አቡነ ዘኢየሱስ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ያሉ ሌሎችንም በርካታ መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡
❤ አባታችንን ያመነኰሷቸው አባት አቡነ እንጦንዮስ ሊጠይቋቸው ወደ ደብረ ሃሌሉያ ሄደው ሲመለሱ እንዲላላካቸው አንድ ትንሽ ልጅ ትተውላቸው ተመለሱ፡፡ አቡነ ሳሙኤልም በጥበብ መንፈሳዊ ኮትኩተው አሳደጉት፡፡
❤ አንድ ቀን ምግባቸው የሚሆን የእንጨት ፍሬዎችን ለመልቀም ከበዓታቸው ሲወጡ ልጃቸው እንዳይደክምባቸው በማሰብ በገዳማቸው ትተውት ለመሄድ አሰቡ፡፡ ብቻውን ስለሆነ አስፈሪ አራዊት እንዳያስደነግጡት በማሰብ ጉድጓድ ቆፍረው በዚያ አኑረውት ሄዱ፡፡ ርቀው ሄደው የእንጨቶችን ፍሬ ሲለቅሙ በጫካው እሳት ተስቶ ገዳማቸውንም ሙሉ በሙሉ አቃጠለው፡፡ ጻድቁ ስለ ልጃቸው ወደ ፈጣሪያቸው ጸልየው ካበቁ በኋላ ወደ ገዳማቸው ቢሄዱ የልጃቸው የራስ ፀጉር እንኳን ሳትቃጠል በሰላም አገኝተውታል፡፡ ያ ልጅም በኋላ አቡነ ገብረ መስቀል የተባለው ገድለኛ አባት ነው፡፡ ከአባታችን ከአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ሃሌሉያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
✨✨✨ልደት ዘፍኖተ ብርሃን ✨✨✨
ባሳለፍነው ሳምንት የሰንበት ት/ቤታችን ፲፫ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል ለዓመቱ በሠላም በጤና ያድርሰን🙏
