ar
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

إظهار المزيد
606
المشتركون
-224 ساعات
-57 أيام
-1430 أيام
أرشيف المشاركات
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ነሐሴ ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮያዊው_ጻድቅ በኤርትራ አገር በሐማሴን አውራጃ ከአስመራ ከተማ በስተምሥራቅ 25ኪ.ሜ ርቀት የሚገኝ አስደናቂ ገዳም #ዘደብረ_ቢዘን ለመሰረቱት እንደ ሐዋርያው #ቅዱስ_ጴጥሮስ በጥላቸው ድውያንን ይፈውሱ ለነበሩት ለአንዳዴ ባሕር ለአባታችን #ለአቡነ_ፊልጶስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ፊልጶስ_ዘደብረ_ቢዘን፦ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ የተመረጡና እንደተወለዱ ነው ሰማንያ አንዱን የብሉይ መጻሕፍትን አጠናቀው ያወቁት ናቸው፡፡ በ12 ዓመታቸውም ለመመንኰስና ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን "አሰናብቺኝ" በማለት ጠይቀዋል፡፡ ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደሚገኘውና ደብረ ጸራቢ ወደሚባለው ገዳም ገቡ፡፡ የገዳሙ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስም የምንኵስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ ከባድ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢመክሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኵስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነገሯቸው፡፡ ከብዙ ፈተናም በኋላ አመነኰሷቸው፡፡ ❤ በገዳሙም እንጨት እየለቀሙና እየፈለጡ፣ ውኃ እየቀዱ፣ የክርስቶስን ሕማሙን ሞቱን እያሰቡ በጾምና ጸሎት ሲጋደሉ ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦላቸው ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ነገራቸውና ሽሬ አደያቦ ወደሚባለው ስፍራ ሄዱ፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራት እያደረጉ ወንጌልን በሀገሩ ዞረው ሰበኩ፡፡ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላቸው ድውያንን ይፈውሱ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእርሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡ 16 ደጋግ መነኰሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ፡፡ ይኸውም በኤርትራ ክፍለ ሀገር በሐማሴን አውራጃ ከአሥመራ ከተማ በስተምሥራቅ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው አስደናቂው ገዳም ነው፡፡ ❤ ጻድቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባሕር በተአምራት ያቃጠሉት አባት ናቸው፡፡ በንጉሡ በዐፄ ዳዊት ዘመን ሰንበትን አንድ ብቻ ናት እያሉ በአንደኛዋ ሰንበት ሥራ ሲሠሩ ጻድቁ አቡነ ፊልጶስ ይህን ሰምተው አንዲት ሰንበት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው፡፡ ከግብፅ የመጡት ጳጳስም ቀደም ብሎ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አሁንም ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ ዐፄ ዳዊት አከራክረዋቸው ጳጳሱም በክርክሩ ተረቱ፡፡ ክፉዎችም በአቡነ ፊሊጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው፡፡ በአቁማዳ ጠቅልለው ሐይቅ ባሕር ውስጥ ጣሏቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባሕር በእሳት ተቃጥሎ ጽድቃቸውን መስክሮላቸዋል፡፡ ❤ ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባሕር ዳርቻ ላይ የተቃጠለው ድንጋይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡ በወቅቱ የንጉሡ ሚስት በዋናተኛ አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አስወጣቻቸው፡፡ እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው፡፡ ወዲያውም "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ነገሯት፡፡ በትንቢታቸውም መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልዱ፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው አለመግባባትና ክፉዎችም በባሕር ውስጥ ስለጣሏቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያው ታርቀዋል፡፡ በዘመናቸውም ርኃብ ስለነተሳ ጻድቁን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማክረዋቸዋል፡፡ አቡነ ፊልጶስም "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው መከሯቸው፡፡ ❤ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም በአቡን ፊልጶስ ምክር መሰረት ከኢየሩሳሌም፣ ከቍስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዐሥሩን ታላላቅ ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉን ያመጡት ዓሥሩ ቅዱሳንም የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊልጶስ ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን በታላቅ ተጋድሎ ኖረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል። ከአባታችን አቡነ ፊሊጶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱስ ከሚለው መጽሐፍ።                           ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለፊልጶስ_እንተ_ክህለ_ያዕዱ። ለዘጸውዖ ብእሲ ለውኂዘ ክረምት እምነ ሞገዱ። ወእምኔሁ አብ እለ መንፈስ ተወልዱ። እንዘ ይዜንው ኃይሎ ወምግባረ ጽድቁ ይንዕዱ። ስሙዓቲሁ ወጽአ ለዓለም በዐውዱ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_5።

✨✨✨        አቤል እንየው✨✨✨✨ ✨ 📌በወርቅ ልብስ ተጎናፅፋና ተሸፋፍና ንግስቲቱ በቀኝ ትቆማለች መዝ 44:9 📌እንኳን  ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። ጾሙ የይቅርታ የፍቅር የመተሳሰብ የአንድነት እንዲሁም ለጥያቄያችን መልስ ምናገኝበት በፈተና ሊጥለን የማይተኛውን ዲያብሎስ ድል የምናደርግበት ጾም ያድርግልን።           ✍️ኪነ-ጥበብ ክፍል

ለሚነሡ ልጆቻችሁም አስተምሯቸው። ❤ ከዚህም በኃላ የአራዊትን ጠባይ ከእነርሱ ያርቅ ዘንድ እግዚአብሔርን ለመኑት ክብር ይግባውና ጌታችንም ይህን የአራዊት ጠባይ አራቀላቸው። ሰዎች የሚመገቡትንም የሚመገቡ የዋሆች ሆኑ። አባቶቻችን ሐዋርያትም ብዙ ተአምራትን አደረጉ በሽተኞችን ሁሉ ፈወሱ ከዚህም በኃላ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ግሪክ አገር ተመለሰ።  ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁንእኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ቅዱስ እንድርያስና በቅዱስ ማትያስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእርሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁሉም ኤጲስ ቆጶሳት ከክርስቲያን ወገኖችም ሁሉ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ብልጽግናን_ንቆ_የተወ_አባ_ጳውሎስ፡- ይህም ቅዱስ ባለ ጸጋ ነበር። ደግ የሆነች ሚስትና የተባረኩ ልጆችንም ነበሩት፡፡ መነኰስ ሊሆን ወደደ ሚስቱንና ልጆቹንም ጠርቶ "እነሆ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ፍቅር እሸጣችሁ ዘንድ ወደድኩ" አላቸው እነርሱም "አሳዳሪያቸን ነህና የወደድከውን አድርግ" አሉት። ❤ ከዚያም በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች በተነ ሚስቱንም ወደ ደናግል ገዳም ወሰዳት አመ ምኔቱንም ጠራትና እንዲህ አላት "ለገዳምሽ አገልጋይ ትሆን ዘንድ ሚስቴን ልሸጥልሽ  አወዳለሁ" እርሷም "እሺ" አለችው የመሸጫዋንም ደብዳቤ ጻፈ የሺያጭዋን ዋጋ ተቀብሎ ለድኆች ሰጠ ልጆቹንም ወደ አበ ምኔቱ ወስዶ እንደ እናታቸው ሸጣቸው ለአበ ምኔቱም አሳልፎ ሰጣቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ ራሱንም ለገዳሙ አለቃ ሸጠ አለቃውንም "ወደ ቤተ ክርስቲያን  ልገባ እሻለሁ" አለው፡፡ በገባም ጊዜ በሩን በላዩ ዘጋ። እጆቹን ዘርግቶ ቆመ በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብሎ ጮኸ "አቤቱ በፍጹም ልቡናዬ ወዳንተ እንደ መጣሁ፣ አንተ ታውቃለህ"  ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "ሀሳብህን ሁሉ አወቅሁ በፍጹም ልቤም ተቀበልሁህ" ❤ ከዚህም በኋላ ከመነኵሶ አስጨናቂ የሆኑ የገዳሙን ሥራዎች ሁሉ እንደ ባሪያ እየሠራ ኖረ ራሱንም ከሁሉ እጅግ አዋረደ ነገር ግን ስለ መዋረዱ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው። ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ከዚህም በኋላ ሐምሌ 30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጳውሎስ ጸሎት ይማሰን ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕታት_ቅዱሳን_መርቆሬዎስና_ኤፍሬም፡- እሊህም ከአክሚም ከተማ የመጡ የሚዋደዱ በመንፈስ ቅዱስ ወንድማማቾች  በሥጋም ዘመዳሞች ነበሩ መንፈሳዊ ስምምነትንም ተስማምተው በላይኛው ግብጽ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም መነኰሱ፡፡ በጾም በጸሎትና በስግደት በታላቅ እየተጋደሉ በገዳሙ ውስት ሃያ ዓመት ዓመት ያህል ኖሩ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ጠላት ሰይጣን በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ከአርዮሳውያን ችግርን በአመጣ ጊዜ አርዮሳውያኑ በአርዮሳዊ ንጉሥ ትእዛዝ መሥዋዕት ሊሠው ወደ ኦርቶዶክሳዊ  ቤተ ክርስቲያን ሊሠዉ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገቡ፡፡ እኒህ ቅዱሳንም አምላካዊ ቅንአትን ቀንተው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡና አርዮሳውያን ያኖሩትን መሥዋዕት በተነኑት። እንዲህም አሏቸው "በሥሉስ ቅዱስ ስም ያልተጠመቀ መሥዋዕትን ያሳርግ ዘንድ አይገባውም"። ❤ ያን ጊዜም አርዮሳውያን ይዘው ደበደቧቸው ታላቅ ግርፋትንም ገረፏቸው ዐጥንቶቻቸውም እስኪሰበሩ ድረስ በምድር ላይ ጥለው ረገጧቸው ነፍሶቻቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ ምእመናንም መጥተው ሥጋቸውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖርዋቸው ከእነርሱም ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን መርቆሬዎስ  ኤፍሬም ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                       ❤ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ጳውሎስ በሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት እንዲሁም በሁላችን በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ይደር ለዘላለሙ አሜን። በሐምሌ ወር የሚነገበብ ንባብ ደረሰ ተፈጸ። እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 30 ስንክሳር።                               ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ዕብል_ለቤትከ_ቅዳሴሃ። ድኅረ ፈጸመ በቊስጥንጥንያ ሕንፄሃ። ሱርያል ገሀደ ተአምሪከ አሜሃ። እምዘይት ማኅቶት ዘሥዕልከ ተቀቢዖ ሶቤሃ። ዐይነ ዕውረሰ በቅጽበት በርህ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_30።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ይቤ ወመጽአ መንፈስ አውሎ። ወተለዓለ ማዕበል። የዐርጉ እስከ ሰማይ"። መዝ 106፥25-26። የሚነበበው ወንጌል ማር 6፥47-53።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እምውኂዝ እምሰጠት ነፍስነ። እምሰጠት ነፍስነ እማየ ሀከክ። ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክነ ዘኢያግብአነ ውስተ መሥገርተ ማዕገቶሙ"። መዝ 123፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ማር4፥35-41። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሐምሌ ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሱርያል (እስራልዩ) ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት (ለቅዳሴ ቤቱ) በዐል፣ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_እንድርያስ አስገራሚ ተአምር በማድረግ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ማትያስን ከእስር አስፈትቶ ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ላዳነበት፣ ክብርንና ብልጽግናን ንቆ ለተወ ራሱን ስለ ጽድቅ ለሸጠ #ለቅዱስ_ጳውሎስ_ለዕረፍት በዐል፣ ለቅዱሳን ለገሊላ ሰዎች  #ለመርቆሬዎስና_ለኤፍሬም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን  ከሚታሰበው፦ ከእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት #ከአባ_ጢሞቴዎስ ከምስር በአስቄጥስ ወደ አለወደ አባ መቃረስ ገዳም ከሥጋው ፍልሰት፣ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትን በረከት ያሳትፈን።                           ✝ ✝ ✝ ❤ በዚችም ቀን #የእስራልዩ_ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ይኸውም #ቅዱስ_ሱርያል መልአክ ነው። የቅዱስ ሱርያል አማላጅነቱና ረድኤቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ በዚችም ቀን #ሐዋርያው_ቅዱስ_እንድርያስ ተአምራትን አደረገ። እንድርያስ በጽርዕ አገር እያለ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ተገልጦ እንዲህ አለው "ማትያስን ከእሥር ቤት ታወጣው ዘንድ ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ሒድ የዚያች አገር ሰዎች ከሦስት ቀን በኃላ ሊበሉት ያወጡታልና"። እንድርያስም ጌታችንን እንዲህ አለው "የቀረው ሦስት ቀን ከሆነ እንዴት እደርሳለሁ ነገር ግን ፈጥኖ የሚያወጣውን ከመላእክት አንድ ላክ እንጂ"።  ❤ ጌታችንም ለእንድርያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት "ስማ ሀገሪቱን ወደዚህ ነዪ ከልዃት በውስጧ ከሚኖሩ ሁሉ ጋር ትመጣለች አንተና ደቀ መዘሙሮችህ ግን ጠዋት በሆነ ጊዜ ተነሥታችሁ ወደ ባሕር ሒዱ የተዘጋጀ መርከብንም ታገኛላችሁ እርሱም ያደርስሃል" ይህንንም ብሎ ከእርሱ ዘንድ በክብር ዐረገ።  በነጋ ጊዜም እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተነሥቶ ወደ ወደብ ደረሰ ጥሩ መርከብንም አየ ጌታችንንም በሊቀ ሐመር አምሳል አየው ጌታችን እንደሆነ አላወቀም "ሊቀ ሐመር ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን" አለው ጌታም "የእግዚእብሔር ሰላም ይደርብህ" አለው እንድርያስም ደግሞ "በዚህ መርከብ ወዴት ትሔዳለህ" አለው "ሰውን ወደ ሚበሉ ሰዎች አገር እሔዳለሁ" አለው እንድርያስም ሊቀ ሐመሩን "ወንድሜ ሆይ ከአንተ ጋር ትጭነኝ ዘንድ እለምንሃለሁ" አለው ሊቀ ሐመሩም "እሺ" ብሎ ወደ መርከቡ አወጣቸው። በባሕሩ ላይም ሲጎዙ ጌታችን እንድርያስን እንዲህ ብሎ ጠየቀው "ጌታህ ምን ኃይል አደረገ" እንድርያስም ጌታችን ከአደረጋቸው ተአምራቶች ይነግረው ጀመረ ጌታችን እንደሆነ አላወቀም ነበርና።  ❤ ከዚህም በኋላ ሊቀ ሐመሩ እነደሚአንቀላፋ ሰው ሆነ ያንጊዜም እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተኛ በዚያን ጊዜም ጌታችን እንድርያስንና ሁለቱን አርድእቱን ይሸክሙአቸው ዘንድ መላእክትን አዘዛቸውና ወስደው በባሕሩ ዳርቻ አኖሩዋቸው።  እንድርያስም ከእነቅልፍ በነቃ ጊዜ መረከብን አላገኘም እጅግም አደገቀ ለደቀ መዛሙርቱም እንድህ አላቸው "ልጆቼ ሆይ በመርከብ ውስጥ ከጌታችን ጋር ነበርን ግን አላወቅንም"።  ❤ ከዚህም በኋላ እንድርያስ ተነስቶ ጸለየ ክብር ይግባውና ጌታችንም በመልካም ጎልማሳ አምሳል ተገለጸለት እንዲህም አለው "ወዳጄ እንድርያስ አትፍራ እኔ ይህን አድርጌአለሁና አንተ በሦስት ቀን አልደርስም ብለህ ነበር ስለዚህ በፍጥረት ሁሉ ላይ ኃይል እንዳለኝ የሚሳነኝምእንደሌለ ታውቅ ዘንድ እንግዲህም ወደ ከተማው ገብተህ ማትያስን ከእሥር ቤት አውጣው ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሁሉ"።  ❤ ከዚህም በኋላ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተነሥቶ ወደ ከተማ ገባ ማትያስ ወዳለበትም እስር ቤት ሔደ። በደረሰም ጊዜ የወሀኒ ቤቱ ደጀ ራስዋ ተከፈተች በገባ ጊዜም ማትያስን ተቀምጦ ሲዘምር አገኘው እርስ በርሳቸውም ሰላምታ ተሳጣጡ እንድርያስም ማትያስን "ከሁለት ቀን በኋላ አውጥተው እንደ እንስሳ አርደው ይበሉኛል አልክ አንተ በጌታችን ዘንድ ያየናትን ያቺን ምሥጢር ረሰሃትን በምንናገርበት ጊዜ ሰማይና ምድርን ይናወጣሉ" አለው።  ማትያስም "ወንድሜ ሆይ እንሆ ይህን አወቅሁ ነገር ግን በዚች ከተማ ውስጥ ሥራዬን እንድፈጽም የጌታችን ፍቃድ እንደ ሆነ እኔ እናገራለሁ እርሱ ራሱ "እንሆ እኔ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እንኳችኋለሁ" ብሏልና ወደ ዚህም እሥር ቤት በጨመሩኝ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ጠራሁት እርሱም ሃያ ሰባት ቀን ሲፈጸም ወንድምህ እንድርያስን ወዳንተ እልከዋለሁ እርሱም ከእሥር ቤት ያወጣሃል ከአንተ ጋራ ያሉትን ሁሉ ያወጣችዋል ብሎ ገለጠልኝ እንሆም ደርሰሃል የምትሠራውን አስተውል" አለው።  ❤ እንድርያስም ወደ እስረኞች በተመለከተ ጊዜ እንደ እንስሳ ሣር ሲበሉ አይቶ አዘነ አለቀሰም ሰይጣንንም ከሠራዊቱ ጋር አሠረው ከዚህ በኃላ አንድርያስና ማትያስ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ማለዱ እጆቻቸውንም በእሥረኞች ሁሉ ላይ ጫኑ አእምሮአቸውም ተመለሰ ከከተማው ውጭ ወጥተው በዚያ በአንድነት እንድቀመጡ አዘዙአቸው። ❤ እኒያ ሐዋርያትም የሚሆነውን ያዩ ዘንድ ወጥተው በሀገሩ ጎዳና ዳር ተቀመጡ የከተማው ሰዎችም እነደ ልማዳቸው የሚበሉትን ከእሥረኞቹ ውስጥ ሊአመጡ መጡ የእሥር ቤቱን ደጅ ክፍት ሆኖ አገኙ እሥረኞችም አልነበሩም ደነግጠውም "በእኛ የደረሰብን ምንድነው ወዮልን" አሉ ያን ጊዜም ሰይጣን በሰው መስሎ ሐዋርያት ይህን እንዳደረጉ ነገራቸው የአሉበትንም አመለከታቸው የከተማው ሰዎችም በመቀዳደም ሮጡ እንድርያስንና ማትያስንም ይዘው በከተማው ጥጋጥግ አስጎተቱአቸው በሌሊትም በእሥር ቤት ያሳድሩአቸው ነበር ሦስት ቀናትም እንዲህ አደረጉባቸው ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ።  ❤ ከዚህም በኋላ ሰለ ከተማዋ ሰዎች ድኀነት ወደ እግዚአብሔር ጸለዪ ጸሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ በላዩ ምስል ወደአለበት የዕብነ በረድ ምሶሶ ቀርበው በመስቀልመ ምልክት አመተቡት እንዲህም አሉት "አንተ ምሶሶ ፍራ ከበታችህም እንደ ጥፋት ውኃ ያለ ብዙ ውኃን በዚች ከተማ ላይና በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ላይ አውጣ" ያን ጊዜም ከምሶሶው ሥር ብዙ ውኃ መነጨ የከተማው ሰዎችንም ያሠጥማቸው ዘንድ ገነፈለ ሰዎችም ከከተማው ወጥተው ሊሸሹ ወድደው ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ያዙ ውኃውም በዝቶ ከበባቸው ማምለጥም አልቻላቸውም ውኃውም እስከ እስከ አንገታቸው ደረሰ ያን ጊዜም አለቀሱ እንዲህም አሉ "ወዮልን ይህ ሁሉ በእኛ ላይ የመጣው በእነዚህ በተመረጡ ሰዎች በእግዚአብሔር አገልጋዮች ምክንያት ነው እኛም በአምላካቸው እናምናለን"። ❤ ቅዱስ እንድርያስም "የዕብነ በረደ ምሰሶ እንግዲህስ በቃህ እነሆ የጥፋት ጊዜ አለፈ" ያን ጊዜም ውኃው ተገታ ውኃውም እንደተገታ የከተማው ሰው አይተው ወደ ሐዋርያት ሔዱ ስለዚያች ከተማ ሰዎች ድኅነትም ቁመው እጆቻቸውን ዘርግተው ወደ እግዚአብሔር ሲጸልዩ አገኙአቸው ሐዋርያትን "ይቅር በሉን" ብለው ለመኑአቸው። ሐዋርያትም "በሕያው እግዚአብሔር እመኑ እንጂ አትፍሩ" አሏቸው ሐዋርያትም ሁለተኛ ጸለዩ በውኃ ስጥመት የሞቱትንም ሙታን አስነሡአቸው በዚያም ውኃ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው። ሥጋውንና ደሙንም አቀበሏቸው ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው። ሕግንና ሥርዓትንም ሁሉ አስተምረው በቀናች ሃይማኖት አጸኑአቸው እንዲህም አሏቸው ያዘዝናችሁን ጠብቁ ከእናንተ በኃላ

ገዳም ሃምሳ ሃምሳ ዓመት በጸሎት ኖረው በአጠቃላይ በ500 ዓመታቸው ነው ያረፉት፡፡ ዐፅማቸው መንዝ ከአርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ ፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡ ከአባታች ከእጨጌ አቡነ ዮሐንስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሐምሌ ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 ለኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት ለተደመሩ ጻድቅ #ለእጨጌ_እጨ_አቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ_ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #እጨጌ_እጨ_አቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ፦ ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ፡፡ አባታቸው ድላሶር እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል፡፡ ወላጆቻቸውም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ፡፡ አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ "በምን አውቀኸኝ ነው?" ብላ አቅፋ ሳመችውና "ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ዓመት ትኖራለህ…" ብላ ባርካው ተሰወረች፡፡ ❤ ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዩሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኋላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኵስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በድብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በጾምና በጸሎት በተጋድሎ ኖዋል፡፡ ከዚኽም በኋላ አባ ዮሐንስ ወደ ተዘጋጀላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ፡፡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኃላ ይገኛል፡፡ ❤ ሕዝቡ በተለምዶ እጨ ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው እጨጌ ዮሐንስ ነው፡፡ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል፡፡ በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ጸበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ጸበሉ ይወርዳል፡፡ እዛው ቆይቶ መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል፡፡ ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው፡፡  ❤ አባታችን በታላቀ ተጋድሎ ሣሉ ሰይጣን የሀገሩን ሰዎች በጠላትነት እንዲነሡባቸው አደረገ፡፡ ሰዎቹም አባታችንን እንዴት እንደሚያጠፏቸው ይማከሩ ጀመር፡፡ ሊገድሏቸው ፈልገው ቅድስናቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና ፈሩ፡፡ ከዚህም በኋላ "ለምን ከመንደራችን ከወንድ ያረገዘች ሴት ፈልገን እሳቸው አስረገዟት ብለን በሐሰት እንከሳቸው?" ብለው ተማከሩ፡፡ ብዙ ወርቅና ብርም ለአንዲት ሴት ሰጥተው በሐሰት ከእርሱ አርግዣለሁ ብላ እንድትመሰክር አደረጓት፡፡ አባታችንም በሕዝብ ፊት በሐሰት ተከሰሱ፡፡ ጻድቁም "አንቺ ሴት ከእኔ ነው ያረገሽው?" አሏት እርሷም "አዎ ከአንተ ነው ልትክድ ነው እንዴ?" አለቻቸው፡፡ አባታችንም በዚህ አዝነው "በአንቺና በእኔ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ" ሲሉ ያች ሴት ወዲያው ለሁለት ተሰንጥቃ ሞተች፡፡ የአገሩ ሰዎችም እጅግ ፈሩ፡፡ አባታችንም ምድሪቱን እረገሟት፡፡ "የተዘራው ዘር አይብቀልብሽ፣ የተተከለው አይፅደቅ፣ ብርድና ውርጭ ይፈራረቅብሽ" ብለው እረግመዋት በደመና ተጭነው ወደ ሰሜን ጎንደር እስቴ ጉንደ ተክለተሃማኖት ሔዱ፡፡ ❤ አቡነ ዮሐንስ በመላው ኢትዮጵያ ወንጌልን እየተዘዋወሩ ያስተማሩ ሲሆን ከቅድስናቸው የተነሣ በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 የኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት የተደመሩ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በይፋት ጠግሮ በዓለወልድ፣ በአፋር አዘሎ፣ በመንዝ ፍርኩታ ኪዳነምሕረት፣ በደብረ ሊባኖስ፣ በጎንድ ተክለ ሃይማኖት በሌሎችም ቦታዎች በመዘዋወር በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ ❤ አባታችን ከሰማይ መስቀል የወረደላቸው ሲሆን ዛሬም በገዳማቸው የሔደ ሰው በወረደው በእጃቸው መስቀል እየተዳበሰ ቆመው በጸለዩበት ባሕር በጠበላቸው ይጠመቃል፡፡ በተጨማሪም ይይዙት በነበረውም  መቋሚያቸው በመዳበስ በረከትን ማግኘት ይቻላል፡፡ ቆመው ከጸለዩበት ባሕር ውስጥ ደረቅ አሸዋ ይወጣል፡፡ አባ ዮሐንስ 500 ዓመት ከኖሩ በኋላ ዕረፍተ ዘመናቸው ሲደርስ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከ15 ነቢያት፣ ከ12 ሐዋርያት፣ ሄሮድስ ያስፈጃቸው ከመቶ አርባ አራት ሺ ሕፃናት፣ ከአብርሃም ከይስሐቅ፣ ከዕቆብ ጋር ሁሉንም ነገደ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ታላቅ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ "ስምህን የጠራ ገዳምህን የረገጠ፣ መባ የሰጠ፣ ቤተ ክርስትያንህን የሠራ ያሠራ የረዳ፣ ገድልህን የሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣ መታሰቢያን ያደረገ እስከ 10 ትውልድ እምርልሀለው፤ ንስሀ ሳይገባ አይሞትም፣ ልጅ መውለድ ባይችል እኔ ልጅ እሰጠዋለሁ፤ ገድልህን በቤትህ ያስቀመጠ እርኩስ መንፈስ፣ ክፉ አጋንንት ቸነፈር ወባ መልአከ ጽልመት አይነካውም፡፡ በገዳምህ መነኵሴ ቢቀበር በሰማይ ክንፍ አበቅልለታለሁ፤ አይሁድም አረማዊም ያላመነ ያልተጠመቀ በገዳምህ መጥቶ ቢያርፍ ይቅር እልልሃለሁ፣ እንደ መቃብሬ ጉልጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ…" የሚል ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ❤ ቅዱስ አባታችንም በ 500 ዓመታቸው ሐምሌ 29 ቀን ዐርፈው በጎንድ ተክለ ሃይማኖት ተቀብረዋል፡፡ በሰሜን ጎንደር የሚገኘውን ይህንን ገዳም ጻድቁ ራሳቸው ናቸው የመሠረቱት፡፡ ነገር ግን የገዳሙን ስያሜ በአባታቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም አድርገውታል፡፡ አቡነ ዮሐንስ ካረፉ በኋላ በእርግማናቸው መሠረት በመንዝና በይፋት ብርዱ ድርቁ ስለበዛባቸው አንድ ብቁ ባሕታዊ ከበዓታቸው ወጥተው "በሐሜታችሁ ምክንያት እጨ ዮሐንስ ስለረገማችሁ ነው የእርሱን ዐፅም ካላመጣችሁ ብርዱ ውርጩ ድርቁም አይጠፋላችሁም" አሏቸው፡፡ ሕዝቡም አባታችን በጉንድ አቡነ  ተክለ ሃይማኖት ከተቀበሩ ከ 134 ዓመት በኋላ በቅዱሳን እየተመሩ ሄደው በሌሊት ግማሽ ዐፅማቸውን አምጥተው በሀገራቸው አምጥተው ስላስቀመጡ ብርዱና ውርጩ በመንዝ እየቀነሰላቸው መጥቷል፡፡ ❤ ዛሬም በሀገሩ ብርዱና ውርጭ ሲበዛ የጻድቁን ታቦት ሲያወጡ ውርጩ ይጠፋል፡፡ ጠገሮ በሚባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘው ጠበላቸው እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ ግማሽ ዐፅማቸውን ከጉንደ ተክለሃይማኖት አምጥተው አርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ በላይ በፍሩክታ ኪዳነምሕረት መጋቢት 18 ፍልሰተ ዐፅማቸው ተከናወነ፡፡ ምድሪቷም ተባረከች፣ የዘሩትንም አበቀለች፣ ውርጩም ብርዱም ቀነሰ፣ ዝናብ አልዘንብ ሲል ወይም ሰብል የሚጨርስ አንበጣ ሲመጣ ታቦታቸው ወጥቶ ምህላ ይያዛል ወድያውም መቅሰፍት ይርቃል፣ ዝናብም ይዘንባል፡፡ ጻድቁ ደመናን፣ ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ ነበር፡፡ በጠገሮ፣ በአዘሎ፣ በፍርኩታና በሌሎቹም ታላላቅ ቦታቦዎች ላይ በእያንዳንዱ

የተከበራችሁ ውድ የሰ/ት/ቤታችን አባላት  እንደሚታወቀው ነገ እሁድ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ስለሚኖረን። በዕለቱ በቦታው በመገኘት  ለደብራችን መልካም የሆነውን አካል በመምረጥ ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ። ማንኛውም ከ18 ዓመት የላይ የሆነ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባል በአካል ተገኝቶ መምረጥ ግዴታው ስለሆነ መቅረት ፈፅሞ አይቻልም። ። ። ፅ/ቤት

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ሐምሌ ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን #ለእመቤታች_ድንግል_ማርያም_እጮኛዋ (ጠባቂ) ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆን ለተገባው #ለአረጋዊው_ለጻድቁ_ለቅዱስ_ዮሴፍ_ለዕረፍት በዐል፣ #ለኢትዮጵያው_ለመጀመርያው_ሊቀ_ጳጳስ #ለአቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ለዕረፍት በዐልና #ለእስክድርያው_ሊቀ_ጳጳስ በጉባኤ ቁስጥንጥንያ ከሃዲያን (መናፍቃንን) መቅዶንዮስን፣ ሰባልዮስና አቡሊናርዮስንም ተከራክሮ ለረታቸው #ለአቡነ_ጢሞቴዎስ_ለዕረፍት_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከአባ_ሮዲስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የእመቤታችን_ጠባቂ ( እጮኛ) #ጻድቁ_ቅዱስ_ዮሴፍ፦ መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው ነው ❤ እርሱም እምቤታችንን በርሱ ዘንድ ካስጠበቋት ጀምሮ በሁሉ ነገር ያገለግላት ነበር። በመከራዋም ሁሉ አልተለያትም። በወለደችም ጊዜ በቤተ ልሔም ከርሷ ጋራ ነበረ። ወደ ግብጽም በተሰደደች ጊዜ ከእርሷ ጋራ ብዙ መከራ ደረሰበት። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ጊዜው በደረሰ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን ጠርቶ ተሰናበታቸው እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሐምሌ 26 ቀን ሰጠ። የዘላለምንም ሕይወት ወረሰ። ❤ በዐረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃበር አኖሩት። ዕረፍቱም ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዊ በዐሥራ ስድስት ዓመት ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ቅዱስ ዮሴፍ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                 ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን (ፍሬምናጦስ)፦ ዜናውም እንዲህ ነው ስሙ ሜሮጵዮስ የሚባል የጥበበኞች አለቃ አንድ ሰው ወደ ሕንድ አገር ሊአልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር መጣ ከእርሱም ጋራ ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ። የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ የሁለተኛውም ኤዴስዮስ ይባላል። ሲድራኮስ የሚሉትም አሉ። በኢትዮጵያ በኩል ወዳለው ወደ አፍሪቃ ባሕር ወደብ ደረሱ ልቡ የተመኘችውን የኢትዮጵያን አገር መልካምነቷን ሁሉ ተመለከተ። ❤ ከዚህም በኃላ በድንገት ወንበዴዎች ተነሥተው በመርከብ ከአሉት ሁሉ ጋር ገደሉት እኒህ ሁለት ልጆች ግን ተረፉ። የአገሩ ሰዎችም አገኙዋቸው ወደ ንጉሥም ወስደው አንድ እጅ መነሻ አድርገው እነርሱን ሰጡት ንጉሡም ተቀበላቸው። ❤ ከጥቂት ቀኖች በኃላም ንጉሡ ኤዴስዮስን በፊቱ የሚቆም ጋሻ ዣግሬ አድርጎ ሾመው ፍሬምናጦስን ግን በገንዘቡ ሁሉ ላይ በጅሮንድ አድርጎ ሾመው ይህም ንጉሥ የአብርሀና የአጽብሐ አባታቸው ስሙ አይዛና የተባለው ነበር። እነርሱ ሕፃናት ሳሉም አረፈ። እኒህም አካለ መጠን እስከሚያደርሱ ድረስ የንጉሡን ልጆች እያሳደጉ ኖሩ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ማመንንም አስተማሩዋቸው። ❤ የንጉሡም ልጆች አድገው በነገሡ ጊዜ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመለሰ ፍሬምናጦስ ግን ወደ ግብጽ ሔደ ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አትናቴዎስም ደረሰ። የደረሰብትንም ሁሉ ነገረው። ስለ ኢትዮጵያውያንም ሃይማኖት ጳጳስ ሳይኖራቸው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳመኑ ነገረው። አባ አትናቴዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ ፍሬምናጦስንም የነጻ ሕዝብ አገር ለሆነችው ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስ ይሆን ዘንድ ግድ አለው። ጵጵስነትንም ሾመ ከታላቅ አክብሮት ጋራ ላከው በአብርሀና በአጽብሐ ዘመነ መንግሥትም ወደ ኢትዮጵያ በደረሰ ጊዜ በክብር ተቀበሉት። ❤ በኢትዮጵያም አገሮች ሁሉ የቀናች ሃይማኖትን ሰበከ አስተማረም ክብር ይግባውና ክርስቶስን የጌትነቱን ብርሀን በሁሉ አገሮች ገለጠ ስለዚህም ብርሃንን ገላጭ ሰላማ ተባለ ሁሉንም አስተካክሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለም አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የእስክንድር_ሊቀ_ጳጳስ_አባ_ጢሞቴዎስ፦ በተሾመ ጊዜም የክርስቶስን መንጋዎች ከአርዮስ ከመቅዶንዮስና ከሰባልዮስ ተኩላዎች ጠበቀ። ይህም አባት በተሾመ በስድስተኛው ዓመት ለክርስቲያን ወገኖች ደግ የሆነ ቴዎዶስዮስ ነገሠ በዚያችም ዓመት ክብር ይግባውና መንፈስ ቅዱስን ስለ ካደው ስለ መቅዶንዮስ በቁስጥንጥንያ የተሰበሰቡ የመቶ ሃምሳ ቅዱሳን ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ተደረገ ይህም አባት ጢሞቴዎስ ሊቀ ጉባኤ ሆኖ መቅዶንዮስንና ሰባልዮስን አቡሊናርዮስንም ተከራከራቸው። ረትቶም አሳፈራቸው። እነሆ የክህደታቸውንና የክርክራቸውንም ነገር የካቲት አንድ ቀን ላይ ጽፈናል። ❤ ከዚህም በኃላ ይህ አባት በሹመቱ ዘመን አብያተ ክርስቲያናትን በማነፅና በሚገባውም ሥራ ሁሉ በእድሳታቸውም አሰበ። ለመጻተኞችም ቤቶችን ሠራላቸው። ❤ መንጋዎቹንም ሁልጊዜ ያስተምራቸው ነበር በመልካም እውቀቱና በትምህርቱ ጣዕም ሁልጊዜም በማስረዳቱ በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ከአርዮስና ከመቅዶንዮስ ወገኖችም ብዙዎቹን መልሶ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሆነች የቀናች ሃይማኖት አስገባቸው። ❤ በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ መንበርም ላይ ዘጠኝ ዓመት ተኩል ኖረ ከዚያም በኋላ ሐምሌ 26 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጢሞቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 26 ስንክሳር።                              ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለጢሞቴዎስ_ለጴጥሮስ_እኍሁ። ጳጳሰ ሀገር ዘእምቅድሜሁ። በቊስጥንጥንያ ዘኮነ ሊቀ ማኅበሮሙ ለእሊአሁ። ተክዕወ ለምእመናን እምሁከተ ዐለውት ዘሠርሑ። ሰላም ብዙኅ እስከ የኀልፍ ወርኁ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 26።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዚአከ ውእቱ ሰማያት ወእንቲአከ ይእቲ ምድር። ዓለምኒ በምልዑ ዘአንተ ሣረርከ። ባሕረ ወመስዐ ዘአንተ ፈጠርከ። መዝ 88፥11-12። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 6፥1-15።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ይምጹኡ ተናብልት እምግብፅ። ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር። ነገስተ ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር"። መዝ 67፥31-32። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 6፥3-20፣ 1ኛ ዮሐ 2፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 5፥20-34። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 1፥18-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን ማርያም ወይም የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአረጋዊው የቅዱስ ዮሴፍና የአባ ሰላም ከሳቴ ብርሃን የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሐምሌ ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያው_ጻድቅ የጌታችን መከራ በማሰብ ከተወለዱ ጀምሮ ተላጭተውት የማያውቁትን ፀጉራቸውን ከትልቅ ዛፍ ላይ እያሠሩ ይጸልዩ ለነበሩ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌሉያ ለዕረፍት በዐል በሰላም አደረሰን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌሉያ፦ የትውልድ ሀገራቸው ተንቤን ነው፡፡ አባታቸው ይስሐለነ እግዚእ እናታቸው ትቀድሰነ ማርያም ይባላሉ፡፡ አቡነ አቢየ እግዚእ አጎታቸው ናቸው፡፡ እናታቸው እሳቸውን ፀንሳ ሳለ ቡራኬ ለመቀበል ወደ ወንድሟ ስትሄድ አቡነ አቢየ እግዚእ መሬት ላይ ወድቀው ሰግደውላታል፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም "ለዚህች ሴት እንዴት ሰገዱላት?" ብለው ቢጠይቋቸው አቡነ አቢየ እግዚእ ስለ አቡነ ሳሙኤል ክብርና ጽድቅ ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ ❤ አቡነ ሳሙኤል ሲወለዱ እናታቸው ለአቡነ ዐቢየ እግዚእ ሰጠቻቸው፣ እርሳቸውም በሃይማኖት በመግባር ኮትኩተው ሁሉን አስተምረው አሳደጓቸው፡፡ አባታችን የጻድቃንና የሰማዕታትን ታሪክ እያነበቡ ያዝኑና ያለቅሱ ነበር፡፡ እንደ እነርሱ በሆንኩም እያሉ ይመኙ ነበር፡፡ አቡነ አቢየ እግዚእ ሀሳባቸውን በመንፈስ ተረድተውላቸው ነበርና መርቀው ባርከው አሰናበቷቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም በሕፃንነታቸው መንነው ወደ አቡነ እንጦንዮስ ገዳም ገብተው በ14 ዓመታቸው መነኰሱ፡፡ ✝ ከየት እንደመጣ የማይታወቅና መላ አካሉ እንደበረዶ ነጭ የሆነ አንበሳ መጥቶ እየመራቸው አሁን ደብረ ሃሌሉያ እየተባለ ወደሚጠራው ገዳማቸው ሄደው በዓታቸውን አጽንተው ገዳሙን መሠረቱት፡፡ አቡነ ሳሙኤል ዘሀለሎም እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ❤ ጻድቁ የጌታችን መከራ በማሰብ ከተወለዱ ጀምሮ ተላጭተውት የማያውቁትን ፀጉራቸውን ከትልቅ ዛፍ ላይ እያሠሩ ይጸልዩ ነበር፡፡ እንዲሁ አድርገው ዛፍ ላይ ራሳቸውን ሰቅለው 40 ቀንና 40 ሌሊት ሲጸልዩ በመጨረሻ የታሠሩበት ፀጉራቸው ተነቅሎ ከመሬት ላይ ወደቁ፡፡ ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን አስከትሎ ተገልጦላቸው እጃቸውን ይዞ አንሥቷቸዋል፡፡ "ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?" ቢላቸው ስለ ሀገራችን ሰላም ይልቁንም በዚህ በቆረቆሩት ገዳማቸው የሚኖሩትን ልጆቻቸውን እንዲጠብቅላቸው ለመኑት፡፡ ❤ ጌታችንም በገዳማቸው ውስጥ በፍጹም ሕማም፣ ደዌና ተስቦ በሽታ እንደማይገባ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ለመንግሥተ ሰማያትም ያልታጨ ሰው በዚህ ገዳም ገብቶ አይቀበርም፡፡ ጻድቁ ከዛፉ ላይ ወድቀው ሳለ ጌታችንን እጨብጣለሁ ብለው የዘረጓት እጃቸው እያበራች ኖራለች፡፡ እንደ መብረቅም እየጮኸች ለገዳሙ እንደ ደወል ታገለግል ነበር፡፡ በመጨረሻም ሊያርፉ ሲሉ ልጆቻቸውን ሰብስበው ባርከዋቸዋል፡፡ ያ አቡነ ሳሙኤል የባረኩበት ቡራኬም በመጽሐፈ ግንዘት ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ዛሬም ድረስ ሰው ሲሞት "ቡራኬ ዘአቡነ ሳሙኤል" ብሎ ካህኑ ይደግማል፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ በከተማ አካባቢ ግን እየተደረገ አይደለም፡፡ አቡነ ሳሙኤል ብዙዎችን ያመነኰሱ ሲሆን እንደነ አቡነ ተጠምቀ መድኅን፣ አቡነ ዘኢየሱስ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ያሉ ሌሎችንም በርካታ መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ ❤ አባታችንን ያመነኰሷቸው አባት አቡነ እንጦንዮስ ሊጠይቋቸው ወደ ደብረ ሃሌሉያ ሄደው ሲመለሱ እንዲላላካቸው አንድ ትንሽ ልጅ ትተውላቸው ተመለሱ፡፡ አቡነ ሳሙኤልም በጥበብ መንፈሳዊ ኮትኩተው አሳደጉት፡፡ ❤ አንድ ቀን ምግባቸው የሚሆን የእንጨት ፍሬዎችን ለመልቀም ከበዓታቸው ሲወጡ ልጃቸው እንዳይደክምባቸው በማሰብ በገዳማቸው ትተውት ለመሄድ አሰቡ፡፡ ብቻውን ስለሆነ አስፈሪ አራዊት እንዳያስደነግጡት በማሰብ ጉድጓድ ቆፍረው በዚያ አኑረውት ሄዱ፡፡ ርቀው ሄደው የእንጨቶችን ፍሬ ሲለቅሙ በጫካው እሳት ተስቶ ገዳማቸውንም ሙሉ በሙሉ አቃጠለው፡፡ ጻድቁ ስለ ልጃቸው ወደ ፈጣሪያቸው ጸልየው ካበቁ በኋላ ወደ ገዳማቸው ቢሄዱ የልጃቸው የራስ ፀጉር እንኳን ሳትቃጠል በሰላም አገኝተውታል፡፡ ያ ልጅም በኋላ አቡነ ገብረ መስቀል የተባለው ገድለኛ አባት ነው፡፡ ከአባታችን ከአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ሃሌሉያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።

Repost from N/a
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 በዛሬው ዕለት የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 በዛሬው ዕለት የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳሴ ቤት ዓመታዊ በዓል በደማቅ ሁኔታ በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ተከብሮ አልፏል። ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን!!

Repost from N/a
photo content
+4

Repost from N/a
photo content
+4

Repost from N/a
photo content
+9

Repost from N/a
photo content
+9

Repost from N/a
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 በዛሬው ዕለት የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳ
+9
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 በዛሬው ዕለት የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳሴ ቤት ዓመታዊ በዓል በደማቅ ሁኔታ በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ተከብሮ አልፏል። ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን!!