ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
إظهار المزيد602
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-87 أيام
-1630 أيام
أرشيف المشاركات
🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️✨✨✨🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️✨✨✨🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️
የሰማይና የምድር ንግሥት ድንግል ማርያም
✨ማኅሌተ ጽጌ ተፈፀመ።
✨✨✨
ናሁ ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ ስሙር
አስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማያት ወምድር
ከመ በህፅንኪ ያሰምክ ፍቁር።
ንግስተ ሠማያት ወምድር ማርያም ድንግል { ፪ }
ተፈፀመ { ፬ } ማህሌተ ፅጌ
ይህ መልካም፣ ያማረ፣ የተወደደ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 26 ጀምሮ እስከ ኅዳር 6 መድረሻ የመጨረሻዋ ሰንበት የሚደረሰው ይህ ድንቅ ማሕሌተ ጽጌ “እነሆ የተወደደ (መልካም) ማሕሌተ ፅጌ ደረሰ ተፈጸመ”
የእመቤታችን ፍቅሯና አማላጅነቷ በረከቷም አይለየን
✨🙏✨የዓመት ሰዉ ይበለን ✨🙏✨
🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️✨✨✨🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️✨✨✨🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️✨✨✨🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️✨✨✨🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️

"አመ አተውኪ ውስተ ታቦት ምስለ ቈጽለ ዘይት ሐመልምል ከመ አብሠርኪዮ ለኖኅ ትእምርተ ጊዜሁ ለሣህል አብሥርኒ ጽድቀ በጸዊረ ጽጌ ጽዱል ማርያም ርግብ ቁስቋም ዘአክናፍኪ መስቀል።"
ትርጉም ፦✨✨✨
"ከለመለመ የወይን ቅጠል ጋር ወደ መርከብ የገባሽ ጊዜ ለኖኅ የይቅርታ ጊዜው ምልክት እንደነበርሽው ንጹሕ አበባን በመያዝ ጽድቅን አብሥሪኝ ክንፎችሽ መስቀል የኾኑ የቁስቋም ርግብ ማርያም።"
✨✨✨
ናሁ ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ ስሙር
አስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማያት ወምድር
ከመ በህፅንኪ ያሰምክ ፍቁር።
ንግስተ ሠማያት ወምድር ማርያም ድንግል { ፪ }
ተፈፀመ { ፬ } ማህሌተ ፅጌ
ይህ መልካም፣ ያማረ፣ የተወደደ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 26 ጀምሮ እስከ ኅዳር 6 መድረሻ የመጨረሻዋ ሰንበት የሚደረሰው ይህ ድንቅ ማሕሌተ ጽጌ “እነሆ የተወደደ (መልካም) ማሕሌተ ፅጌ ደረሰ ተፈጸመ”
የእመቤታችን ፍቅሯና አማላጅነቷ አይለየን
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፪ (2) ቀን።
✝ እንኳን #ከአባ_ጢሞቴዎስ በኋላ ለተሾመ አረማውያን ስለቀናች ሃይማኖቱ ብዙ መከራ ላደረሱበት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ሃያ_ሰባተኛው_ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጴጥሮስ_ለዕረፍቱ_በዓል መታሰቢያና ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ስልሳ_አምስተኛ ለሆነ ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_ሱንትዩ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከእስክንድርያ ነቢዪት ከሆነች #ከሴቴንዋ_ከቅድስት_አንስጣስያና #ከአባ_ሊባኖስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ "#ሰላም_እብል_ለብፁዕ_ሱንትዩ። #ወለጴጥሮስ ዓዲ ሱታፌ ዕበዩ። ኪያሆሙ ሕዝብ በከመ ሠምሩ ወኀርዩ። ሤሞሙ አብ ጳጳሳተ ቤተ ክርስቲያኑ ይርዐዩ። እንተ አጥረያ በደሙ ወማዩ"። #ሊቁ_አርከ ሥሉስ (አርኬ) #የኅዳር2።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የምሥራቅና የሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የብዙኃን መገናኛ ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት የበላይ ኃላፊ በዩጋንዳ ኢፌዴሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የሆኑትን ክብርት አምባሳደር እጸገነት በዛብኅ ጋር ተወያዩ፡፡
ብፁዕነታቸው ዩጋንዳ ሲያቀኑ በኢንቴቤ አየር ማረፊያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ተቀብለዋቸው የመድኃኔዓለምን ክብረ በዓል በካምፓላ መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አክብረዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በዩጋንዳ ቆይታቸው የሀገረ ስብከቱን የሥራ ኃላፊዎች በማነጋገር የሥራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤምባሲን በመጎብኘት በዩጋንዳ ኢፌዴሪ አምባሳደር ከሆኑት እጸገነት በዛብኅ ጋር ተወይይተዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ከቅዱስ ሲኖዶስ የተጻፈላቸውን የምደባ ደብዳቤ ቅጂ ለክብርት አምባሳደሯ የሰጡ ሲሆን፤ አምባሳደር እጸገነት በዛብኅ የብፁዕነታቸውን ደብዳቤ በክብር ተቀብለው ብፁዕነታቸው በኤምባሲው ተገኝተው ስለጎበኟቸውና ስለባረኳቸው ምስጋናቸውን በመግለጽ ከቤተክርስቲያኗ ጋር አብሮ ለመሥራት ያላቸውን ተነሳሽነት ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በቀጣይ በካምፓላ መንፈሳዊ ትምሕርታቸውን በመከታተል የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነት በመከተል ሥርዓተ ጥምቀት የሚፈጸምላቸው ዩጋንዳውያንን የሚያጠምቁ ሲሆን መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ለተከታተሉ ታዳጊዎችም ማዕረገ ዲቁና ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል EOTC TV ዘግቧል።
✝ "በስመ አብ ወወል ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #የተባረከ_የኅዳር_ወር_ቀኑ_ዐሥር_ሰዓት ሲሆን ከዚህም ይጎድላል።
✝ #ኅዳር ፩ (1) ቀን።
✝ እንኳን #አፍራቅያ_አገር_ለሆኑ_ለቅዱሳን_ሰማዕታት #ለመክሲሞስ_ለማንፍዮስ_ለፊቅጦርና_ለፊልጶስ በከሀዲው ንጉሥ በዳኪዎስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያው በዓልና #ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ_ለጻድቁ_ለቅዱስ_ነአኵቶ ለመታሰቢያው በዓሉ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ "#ሰላም_ለመክሲሞስ_ወለአኃዊሁ_በጽድቅ። እለ አበዩ ሰጊደ ለስብኮ ወርቅ። ሐራ ዳኬዎስ ዓላዊ ኰናኔ ሰብዓቱ ደቂቅ። በዘአርሐስዎ በብሂእ ወበፄው ድቁቅ። ቊስላቲሆሙ መዝመዙ በሠቅ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የኅዳር_1።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገለጹ፡፡
ብፁዕነታቸው ቅርሱ ከሥጋት ቀጠና ነጻ እንዲሆን ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ መ/ር ኃይሉ በላይ
(#EOTC TV ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም )
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን ተሻግረው የጣሊያን ወረራን አልፈዋል እንዲሁም በየዘመናቱ በተፈጠሩ የእርስበርስ ጦርነቶች ጉዳት ሳያደርሱባቸው እዚህ ደርሰዋል ።
ይሁን እንጂ አሁን ባለበንበት ዘመን ግን በአካባቢው በተፈጠረው ከፍተኛ የሰላም እጦትና ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለ EOTC TV (ኢኦተቤ ቴቪ) ገልጸዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ቅዱሱን ቅርስ ከስጋት ነጻ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል ወደ ሰላም መድረክ መምጣት እንዳለበት በቅድሚያ የጠቆሙ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት ብለዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ላሊበላ ቅርስና የአምልኮ ቦታ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ቅዱሱ ቅርስ ከአደጋ ስጋት ውጭ እንዲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት የመንግስት አካላት እንዲሁም የቅዱሱ ቅርስ የጋራ ሀብትነት የሚያሳስበው ሁሉ በጉዳዩ ላይ በጎ ተጽእኖ በማሳደር ድምጽ እንዲሆን ብፁዕነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ዓመታዊ የሠራተኞች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።
ዘጋቢ መ/ር አቤል አሰፋ
+++++++++++++++++++++++++++++++++
(#EOTCTV/ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም)
በ21ኛውመቶ ክፍለ ዘመን ሚዲያ ዋነኛው የግንኙት መሣሪያ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው በየቀኑ በሚለዋወጥበት በዚህ የዲጂታል ዘመን ሚዲያ ለኢኮኖሚ እና ርዕዮተ ዓለማዊ መሣሪያነት ከመዋል አልፎ በመንፈሳዊው ዘርፍም ከፍተኛ እመርታ እያሳየ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያን የሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ( Users of radio/TV/Internet) እኤአ 2021 2 ቢሊየን 340 ሚሊዮን ሲሆን ይህ ቁጥር በ2025 2ቢሊየን 460 ሚሊየን በ2050 ደግሞ 2ቢሊየን 930 ሚሊየን እንደሚደርስ የስታስቲክስ ጥናቶች ያሣያሉ (Status of Global Christianity, 2021, in the Context of 1900–2050)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚዲያን በመጠቀም ረገድ በኢትዮጵያ ቀደምት ከሚባሉት ተቋማት አንዷ ናት፡፡ ሊቃውንቶቿ በህትመት ሚዲያው ዘርፍ ቀዳሚዎቹን የሀገራችንን መጽሔቶችና ጋዜጦች በማዘጋጀት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በዘመናችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሁለት የሳተላይት ቴሌቪዥን ማሠራጫ እና በጥቂት የህትመት ዘርፍ ምእመናኗ ጋር ለመድረስ እየተጋች ትገኛች፤፤
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የመገናኛ ብዘኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ትውፊት፣ ቀኖና እና መዋቅራዊ አሠራር መሠረት በማድረግ ብቃትና ጥራት ያሏቸውን መርሐ ግብራት በብዙኃን መገናኛ ማሠራጫዎች በመደበኛነት ለማቅረብ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመ ሲሆን በመገናኛ ብዙሃን ዐዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 6(1)፣(5) እና 40(3)(ለ)፤ መሠረት በኢፌዴሪ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዕውቅና ያለው ተቋም ነው::
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ያለፈውን የበጀት ዓመት በመገምገም በ2016 የበጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር ዓመታዊ የሠራተኞች ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ ድርጅቱን በማዘመን የቅድስት ቤተክርስቲያን እና የቅዱስ ሲኖዶስ ልሣን ሆኖ እንዲደራጅ ከፍተኛ ሥራ መሠራቱን ጠቁመዋል። በቤተክርስቲያን ባለፈው የበጀት ዓመት ከተከሰተው ችግር ጋር ተያይዞ የድርጅቱ ሠራተኞች በቁርጠኝነት ሥራቸውን ማከናወናቸውን በማስመልከት ምስጋና አቅርበዋል።
ድርጅቱ በቴክኖሎጂ እና በይዘት ልቆ ከፍ ያለ አገልግሎት ማበርከት እንደሚገባው የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ ለዚህም ሥልጠናና ውይይቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የድርጅቱ የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት ክንውንን አስመልክቶ በድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አስቻለው ሺፈራው ሪፓርት ቀርቧል።
በመድረኩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሥራ መመሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
በተለይም ደግሞ በኤዶም ገነት የነበሩትን ዕፀዋት የመጠበቅና የመንከባከብ ሓላፊነትን ሰጥቶታል፡፡
ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን አምላካዊ አደራ ተገንዝባ ለዘመናት በዙሪያዋ አገር በቀል ዕፅዋትን እየተከለች በመንገድ የደከሙ የሚያርፉበት ጥላ፤ ለተራቡት ምግበ ሥጋ፤ መኖሪያ የሌላቸው የሚያድሩበት መጠለያ ይሆኑ ዘንድ ጠብቃና አስጠብቃ ቆይታለች፡፡
ለአብነትም ያህልም በሀገራችን ረጅም ዘመናትን ያስቆጠሩና ለአካባቢ አየር ጥበቃ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው አገር በቀል ደኖች የሚገኙት በቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ነው፡፡
እነዚህ ደኖች ቅዱሳን ባሕታውያን የሚጸልዩባቸው ብቻ ሳይሆኑ በየዘራቸው፣ በየዓይነታቸው፣ በየወገናቸው፣ በየመልካቸው፣ እግዚአብሔር የፈጠራቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንስሳትና አራዊትም ደኑን ዓለማቸው አድርገው የሚኖሩበትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚገለጽበት ነው ደን ማለት፡፡
ዓለመ ደን ጥቅሙ ለሰብአዊ ፍጡር ብቻ አይደለም ለፍጥረቱ ሁሉ ነው እንጂ፡፡
ከጥንት ጀምሮ ቤተክርስቲያን በረሃማነትን ለመቀነስ በደን ጥበቃ በኩል ያበረከተችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም በአለንበት ዘመን ከሕዝብ ቁጥር መጨመር እና ከልዩ ልዩ ምክንያቶች ጋር ተያይዞ የደን መመናመን ይታያል፡፡
ስለሆነም እግዚአብሔር አምላክ ለሕይወታችን እንደሚያስፈልገን አውቆ አስቀድሞ ፈጥሮ አዘጋጅቶ የሰጠንን ሀብት እንዳናጣ መንከባከብና ባረጁት ዕፅዋትም ምትክ አዳዲስ ችግኞችን መትከል ይገባናል፡፡ ይህን ስናደርግ ምድራዊ ሕይወታችን የተስተካከለና የተደላደለ ይሆናል፡፡
በአንጻሩ ዕፅዋትን በአግባቡ ካልተንከባከብን አፈራችን በጎርፍ ተጠራርጎ፣ በአውሎ ነፋስ ተሸርሽሮ የምድሪቱን ልምላሜ የምናጣ ከመሆኑም ባሻገር ፀሐይና ድርቅ ይበረታል፤ የአካባቢያችን አየር ይለወጣል፤ ድርቅ እና ረሃብ ይበዛል፤ ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ ለከፋ ችግር ይጋለጣሉ፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር እንድንጠቀምባቸው የሰጠንን ዕፅዋት የመጠበቅና የመንከባከብ ሓላፊነታችንን በአግባቡ እንድንወጣ ለመወያየት እንዲሁም አለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ይቻል ዘንድ ይህ መርሐ ግብር እንዲዘጋጅ ለደከሙ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ የዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች የሆናችሁ በሙሉ ሰላም የሰፈነባት፣ ልምላሜ የሞላበት፣ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት፣ ሰው በሰውነቱ ብቻ ተከብሮ በነፃነት የሚኖርባት ሀገርን ለትውልድ የማስተላለፍ የታሪክ አደራ የሚጠብቃችሁ መሆኑን በማስታወስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አስተባባሪነት የተዘጋጀው የቤተክርስቲያን ደን ልማት ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በይፋ መከፈቱን በእግዚአብሔር ስም እናበስራለን፡፡
እግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የብፁዕ ወቅዱስነታቸው ቡራኬ ይድረሰን !
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ባዘጋጀው የደን ልማት ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው።
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
•ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ፤
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት፤
•የተከበራችሁ የኃይማኖት መሪዎች፤
•የተከበራችሁ የመንግስት ኃላፊዎች፤
•የተከበራችሁ አምባሳደሮች፤
•የተከበራችሁ የሲቪል ማህበራት አመራሮች፤
•የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፤
•ክቡራንና ክቡራት፤
እንኳን ደህና መጣችሁ፤
“ወነሥአ እግዚአብሔር ለእጓለ እመሕያው ወሤሞ ውስተ ገነት ከመ ይትገበራ ወይዕቀባ፡-እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም፤ ይጠብቃትም ዘንድ በኤዶም ገነት አኖረው” (ዘፍ 2፡15)
ከዚህ ጥቅስ እንደምናስተውለው እግዚአብሔር አምላካችን በማይመረመር ጥበቡ ከምድር በላይ ከሰማይ በታች የሚገኙትን ፍጥረታት አስቀድሞ ፈጥሮ የሥነ ፍጥረት መደምደሚያ (ጉልላት) የሆነው ሰው ይገለገልባቸው ዘንድ ፈቃዱን ገልጦለታል፡፡
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፴ (30) ቀን።
✝ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነ #በእስክንድርያ_በግብፅ ያለቱ አምልኮ ጣኦታት (ላሕም) ላጠፍ ወንጌልን ለሰበከ ለወንጌላዊው #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ማርቆስ_ለልደቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #ሐዋርያው_ወንጌላዊው_ቅዱስ_ማርቆስ ዘአንበሳ፦ የቅዱስ ማርቆስ ወላጆች ስም የአባቱ ስም ቅዱስ አርሰጡጳውሎስ ሲሆን የእናቱ ስም ቅድስት ማርያም ይባላል፡፡ አባቱ ባለፀጋና ያላገባ ነበር የአባቱ ስም ስምዖን ይባል ነበር፡፡ ስምዖንም አርስጡጳውሎስን እንዲያገባ ይገፋፋው ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ በቤቷ እንግዶችን የምትቀበልና የምታስተናግድ ማርያም የተባለችውን የወንጌላዊ የቅዱስ ማርቆስ እናት አገኘ፡፡ እሱም እሷመ ሳያስቡት ባዩት ሕልምና በመፈክራነ ሕልም (በሕልም ፈቺዎች) በተነገራቸው መሠረት ተገናኝተው የትዳር ሕይወትን መሠረቱ፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት ምክንያት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተሚማ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የላሊበላ አካባቢ ነዋሪዎች ከተሚማ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ በአብያተ ክርስቲያናቱ ዙሪያ ያለው ተኩስ የጥንታውያኑን አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አደጋ ላይ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
ለደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት መጠለያነት የተሠሩ የብረት ሽፋኖች በተባራሪ ጥይቶች መመታታቸውን ፤ ሁሉንም ዓይነት የጦር መሳሪያዎች እየተጠቀሙ መሆኑን እና "የተኩሱ ንዝረት ይሰማኛል” በማለት ውጊያው በከተማዋ ውስጥ የፈጠረውን ስጋት እና የደቀነውን አደጋ የሮይተርስ የዜና ወኪል ያናገረው አገልጋይ ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነትን ብንጠይቅም ከሀገረ ስብከቱ መረጃው እንዳልደረሰው የተገለጸልን ሲሆን ወደ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ያደረግነው የስልክ ሙከራም አልተሳካም።
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ።
ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት ምክንያት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተሚማ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የላሊበላ አካባቢ ነዋሪዎች ከተሚማ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ በአብያተ ክርስቲያናቱ ዙሪያ ያለው ተኩስ የጥንታውያኑን አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አደጋ ላይ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
ለደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት መጠለያነት የተሠሩ የብረት ሽፋኖች በተባራሪ ጥይቶች መመታታቸውን ፤ ሁሉንም ዓይነት የጦር መሳሪያዎች እየተጠቀሙ መሆኑን እና "የተኩሱ ንዝረት ይሰማኛል” በማለት ውጊያው በከተማዋ ውስጥ የፈጠረውን ስጋት እና የደቀነውን አደጋ የሮይተርስ የዜና ወኪል ያናገረው አገልጋይ ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነትን ብንጠይቅም ከሀገረ ስብከቱ መረጃው እንዳልደረሰው የተገለጸልን ሲሆን ወደ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ያደረግነው የስልክ ሙከራም አልተሳካም።
በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የተከዜ ምዕራፈ ቅዱሳን ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም መነኮሳት ልኡክ የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንን ጎበኘ፡፡
መነኮሳቱ ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋስይሁን በላይና የተቋሙ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱም ብሮድካስት አገልግሎት ተቋሙን የተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።
ጉብኝቱ 150 መነኮሳትን ከተከዜ ምዕራፈ ቅዱሳን ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም በቅርቡ ወደተገደመው በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት የአቡነ ዜና ማርቆስ ወአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንድነት ገዳም አድርሰው ሲመለሱ ነው የተከናወነው፡፡
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ ጥቅምት ፳፱ (29) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ታዴዎስ_ዘጽላልሽ_ግመልን_በመርፌ_ቀዳዳ አሳልፈው ሙት አስነስተው ብዙ ሕዝብ ላሳመኑበት ለተአምራት በዓላቸው፣ በምዕራብ ሐርጌ በሜኤሶ ወረዳ የሚገኘውን #ታላቁ_ገዳም_አሰቦት_ደብረ_ወገግ_ቅድስት_ሥላሴ ለመሰረቱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ ለዕረፍታቸው በዓልና ለተመሰገነና ለከበረ ለዘኸኝ መምህር #ለቅዱስ_ጸቃውዐ_ድንግል ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።
እንኳን በከሀዲው በመክስምያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_ድሜጥሮስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም የተወለደበት #ከልደቱ_ከበዓለ ወልድ ወራዊ በዓል መታሰቢያ፣ #ከድሜጥሮስ_ወዳጅ_ከሰማዕቱ_ስቅጣር ዐረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፳፰ (28) ቀን።
✝ እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን_አንዱ_ለሆኑት በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በቅዱሳን መላእክት እጅ ለተከናወነው ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ይምዓታ_ዘጎሕ_ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
እንኳን #ለቅዱስ_አማኑኤል_ዓመታዊ_በዓል፣ #አባቱ_ኖኅ_እግዚአብሔር_የያፌትን_አገር_ያስፋለት ብሎ ለመረቀው #ለቅዱስ_ያፌት_ለመታሰቢያ_በዓሉ፣ #ለቅዱሳን_ሰማዕታት_ለመርትያኖስና_ለመርቆሬዎስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_መቅብዩ፣ #ከአባቶቻችንም_ከቅዱሳን_ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የአስኮ ደ/መድሃኒት መድሃኒዓለም እና ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል የአመት ሰው ይበለን አሜን !!!!
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨