ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
إظهار المزيد610
المشتركون
-124 ساعات
-37 أيام
-1130 أيام
أرشيف المشاركات
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን ##ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ ለከበረና ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_እንድራኒቆስ ለዕረፍቱ በዓል፣ #በደብረ_ምጥማቅ_ለእመቤታችን መገለጥ #ለሁለተኛ_ቀን መታሰቢያ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከምሥራቃዊ_ከቅዱስ_ያዕቆብ ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_እንድራኒቆስ፦ ይህንንም ሐዋርያ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው። እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታ ከመከራው በፊት ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።
❤ በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ መንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ። በኒውብያ አገር ላይም ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ሰበከ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙዎች አረማውያንንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ቅዱስ ዮልዮስን ወሰደው በአንድነትም በብዙ አገሮች ዙረው አስተማሩ። ብዙ ሰዎችንም አጠመቁ ተአምራትንም በማድረግ ከሰዎች ላይ አጋንንትን አባረሩ። ብዙዎች በሽተኞችንም ፈወሱአቸው የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሰው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትን አነፁ። አገልገሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ።
❤ ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ቅዱስ እንድራኒቆስ ታመመና በዚች ቀን ግንቦት 22 ቀን ዐረፈ ቅዱስ ዮልዮስም ገንዞ በመቃብር አኖረው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 22 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ሰላም_ለእንድራኒቆስ ዕብሎ። ውኂዝ መንፈስ ዘሰትየ ምስለ ሐዋርያት በአመ ድብሎ። ኀበ ሖረ ይስብክ አህጉራተ አድያም ኵሎ። አብያተ ክርስቲያን ሐኒፆ ወአብያተ ጣዖት አንሒሎ። ዕሴተ ተስፋሁ አድምዐ በሰማይ ዘሀሎ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_22።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "በትርከ ወቀስታምከ አማንቱ ገሠፀኒ። ወሠራዕከ ማእደ በቅሜየ። በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ"። መዝ 22፥4-5 የሚነበበው ወንጌል 27፥27-31።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 16፥6-10፣ 1ኛ ዮሐ 2፥27-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 21-15-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ እንድራኒቆስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን፡፡
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።❤
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለብርሃነ_ዕርገቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የጌታችን_የአምላካችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ+ክርስቶስ_ዕርገት፦ እርሱም በረቀቀ ጥበቡ በመከራው በሞቱና በመነሣቱ ሥራውን ከፈጸመ በኋላ አርባው ቀን ሲፈጸም በነፋሳት ክንፍ ላይ ሁኖ ዐረገ። ያን ጊዜ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ወጣ በነፋሳትም ክንፎች ላይ ሁኖ ወጣ ያለው የዳዊት ትንቢት ተፈጸመ።
❤ በዚህም ዕርገቱ የሚያምኑበት በልዕልና ወደሚኖሩበት የሚዐርጉ መሆናቸው ተረዳ ተረጋገጠ ራስ በአለበት ሕዋሳት ሊኖሩ ይገባልና። አዳም አስቀድሞ በምድራዊ ርስቶች በሲኦልም እንደኖረ መኖርንም እንደቀደመ እንዲሁ ዳግማዊ አዳም ጌታ በመንግሥተ ሰማያት ርስት መኖርን ቀደመ።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ። ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሽብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ።
❤ በጌታችንም ዕርገት የቅዱስ ዳንኤል ትንቢት ተፈጸመ እንዲህ የሚል "ሌሊት በራእይ አየሁ እንሆ ታላቅ እንደ ሰው ልጅ የሆነ መጣ ዘመናትን ወደሚያስረጃቸው ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት። የዘላለም አገዛዝ፣ ጌትነት፣ መንግሥት፣ የዘላለም ሥልጣን ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የሚያልፍ የማይጠፋ ነዋሪ ነው"። ለእርሱም ምስጋና ይሁን ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት8 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ። ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ። ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል"። መዝ 67፥32-33። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 24፥45-ፍ.ም።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ። ወእግዚእነ በቃለ ቀርን። ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ"። መዝ 46፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 1፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥18-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ማር 16፥14-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም የብርሃነ ዕርገቱ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን #አምላክ_ለወለደች_ለእናታች ለእመቤታችን #ለቅድስት_ድንግል_ማርያም #በደብረ_ምጥማቅ በስሟ በተሰራች ቤተ ክርስትያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ #ለአምስት_ተካታታይ_ቀን_ለታየችበት ዓመታዊ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #በዚች_ዕለት_አምላክን_የወለደች_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_በደብረ_ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስመታየቱ የክርስቲያ ወገኖች ሁሉም በታላቅ በዓልን ያደርጋሉ።
❤ እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕርጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥናዋ ገናናነት ይሰግዳሉ ስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል "አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ"።
❤ ሁለተኛም ሰማዕታትም በየማረጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል። ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጠው ይህ ቅዱስ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋና ያቀርብላታል።
❤ ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ። ኄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመታቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰብትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር።
❤ እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልጀራው "ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጅዋ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል።
❤ እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም አምላክ በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 21 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን። በዘአዝፋረ ወርቅ ዑፅፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ሰወረከኒ በዕለተ ቀትል መልዕልተ ርእስየ። ኢትመጥወኒ እግዚኦ እምፍትወትየ ለኃጥአን። ተማከሩ ላዕሌየ ኢትኅድገኒ ከመ ኢይዘኀሩ"። መዝ 139፥7-8 ወይም መዝ 140፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥9-ፍ.ም፣ ራእ.ዮሐ 12፥1-5 እና የሐዋ ሥራ 7፥44-51። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥6-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የደብረ ምጥማቅ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለአሮን ዕጓላተ ርግብ ዘአሥረረ። ድኅረ ተበስሉ በእሳት ከመ ይኩኑ ድራረ። ኢያንጥሙ ፍኖቱ ወኢያድክሞሙ ወትረ። ማየ ታሕቲት ኀበ ሐነፀ ማኅደረ። በማዕተበ እዱ ስሒቦ አዕረገ ደብረ። ትርጉም፦ እራትን እንዲኾኑ በእሳት ከተበሰሉ በኋላ የርግብ ልጆችን እንዲበርሩ ላደረገ ለአሮን ሰላምታ ይገባል፤ ጎዳናው አስቸግሮ ዘወትር እንዳያዳክማቸው በታች ያለ ውሃን ወዳነጸው በኣቱ በእጁ ማማተብ ስቦ ወደ ተራራ አወጣ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_21::
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ለከበሩ #በአንድ_ገዳም_ስልሳ_ሰባት_ዓመት ለተጋደሉ አባት ገሃነመ እሳት በማሰብ በዝሙትም ላለመውደቅ ብለው ሰውነታቸውን የሚነድ እሳት ውስጥ በመጨመር ዘማዊቷን ሴት ለንስሓ ላበቋት #ለአባ_መርትያኖስና #አንበሶች_ውሃ_ይቀዱላቸው ለነበረ፤ ሊፈታተናቸው የመጣውንሰይጣንበዓታቸው ውስጥ አስገብተው በላዩ ዋሻውን ደፍነው ታላቅ የቋጥኝ ደንጊያም ለዘጉበት #ለአባ_አሮን_ሶርያዊ ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ከሚታሰቡት፦ #ከነቢዩ_አሞጽ_ከመርዶላ ከመታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_መርትያኖስ፦ ይህም አባት በልጅነቱ ከአንድ ቅዱስ የሆነ አረጋዊ አባት ዘንድ መንኵሶ ታላቅ ገድልን ተጋደለ። ከዚህም በኋላ ሐመረ ኖኅ ወደምትባል በቂሣርያ ወደአለች ገዳም ሔደ በዚያም እጅግ በጣም የበዛ ገድልን ተጋደለ። በጸሎት በጾም በስግደትም በሌሊትና በመዓልት በመትጋት እየተጋደለ ስልሳ ሰባት ዓመት በኖረ ጊዜ የገድሉና ትሩፋቱ ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ።
❤ እንሆ አንዲት በክፉ ሥራዋና በዝሙቷ የታወቀች ኃጢአተኛ አመንዝራ ሴት ሰማች። ጽድቁንና ቅድስናውን በመናገር የሚያመሰግኑትን እንዲህ አለቻቸው "እናንተ ታመሰግኑታላችሁ እርሱ የሚኖረው በዱር ነው የሴት ገጽ ከቶ አያይም እኔን ቢያይ ድንግልናውን አጥፍቼ ቅድስናውን በአረከስኩት ትኅርምቱንም ባፈረስኩት ነበር"። እነርሱ ግን ጥንክርናውን ስለ ሚያውቁ ተከራከሩዋት። ስለዚህም በመካከላቸው ክርክር ሆነ "ሒጄ ከእኔ ጋራ በኃጢአት ብጥለው ምን ትሰጡኛላችሁ" አለቻቸውና ገንዘብ ሊሰጡአት ተስማሙ።
❤ ያን ጊዜም ተነሥታ ጌጦቿን ልብሶቿንና ሽቱዎቿን ያዘች መልኳም እጅግ ውብ ነበረች ፊቷንም ተከናንባ ጨርቅ ለብሳ ወደ በዓቱ ሔደች። ልብሷንና ጌጦቿንም ለብቻቸው በከረጢት አሥራ ያዘች። ከበዓቱም ቅርብ በሆነ ቦታ ተሠውራ እስከ ሚመሽ ቆይታ የበዓቱን ደጃፍ አንኳኳች። "አራዊት እንዲበሉኝ በውጭ አትተወኝ እኔ መጻተኛ ነኝና መንገድንም ተሳስቼ ወደዚህ ደረስኩ" አለችው። እርሱም በልቡ አሰበ "በውጭ ብተዋት አራዊት ይበሏታል ባስገባትም ስለርስዋ ጦር በኔ ላይ ይነሣብኛል" አለ።
❤ ከዚህም በኋላ ከፈተላት በዚያች በዓት ውስጥ ትቷት ወደ ሌላ ቦታ ፈቀቅ አለ። እርሷ ግን ልብሶቿን ለብሳ ጌጦቿንም ተሸልማ ሽቱዎቿን ተቀብታ ወደርሱ ገባች ከርሷ ጋራም እንዲተኛ ፈልጋ "ከዚህ ማንም የሚያየን የለም" አለችው። ቅዱሱም የሰይጣን ማጥመጃው እንደሆነች አውቆ "ጥቂት ታገሺኝ መንገድን እስታይ እግዚአብሔርን የማንፈራው ከሆነ እንደእኛ ያሉ ሰዎችን ላንፈራቸው ይገባናል" አላት። ይህንንም ብሎ ከእርሷ ዘንድ ወጣ ታላቅ እሳትም አንድዶ እግሩን ከውስጡ ጨምረ ነፍሱንም "የሲዖልን እሳት የምትችዪ ከሆንሽ ኃጢአትን ሥሪያ" አላት። በዘገየ ጊዜ ወደርሱ ሔደች በእሳት ውስጥም እግሩን ሲያቃጥል አይታው እጅግ ደነገጠች። ከእሳትም ውስጥ ጐትታ አወጣችው ልቧም ወደ ንስሓ ተመለሰ። ልብሷንና ጌጦቿን ከላይዋ አውጥታ ጣለች ከእግሩ በታች ሰግደች ስለነፍሷ ድኅነትም እንዲረዳት ለመነችው። እርሱም ይህ ዓለም ፍላጎቱ ሁሉ ኀላፊ እንደ ሆነ ያስተምራትና ይመክራት ልብ ያስደርጋትም ጀመር እርሷም በጨከነ ልብ ንስሓ ገባች።
❤ ከዚህም በኋላ "በአንድነት መኖር አግባብ አይደለም" ብሎ ወደ ደናግል ገዳም ወሰዳት ትጠብቃትም ዘንድ እመ ምኔቷን አደራ አላት። በቀረው ዕድሜዋም በገድል ተጠምዳ እግዚአብሔርን አገለገለችው ወደ በጎ ሽምግልናም ደረሰች የመፈወስ ሀብትም አድሮባት ብዙዎች በሽተኞችን አዳነች።
❤ የከበረ አባ መርትያኖስ ግን ሌላ ሴት እንዳያመጣበት ፈርቶ በባሕር መካከል ወዳለች ደሴት ገብቶ በዚያ የሚኖር ሆነ። አንድ ባለ ታንኳም የእጅ ሥራውን እየሸጠ ምግብ ያመጣለት ነበር። ከብዙ ዘመናትም በኋላ መርከብ ተሰብራ ሰጠመች አንዲት ሴትም በመርከብ ስባሪ ተጣብቃ አባ መርትያኖስ ወደ አለበት ደሴት የባሕሩ ማዕበል አደረሳት በአያትም ጊዜ ደነገጠ አደነቀም። ከእርሷ ጋራ በአንድነት ስለ መኖሩም አዘነ የእግዚአብሔርንም ቃል አስተምሮ የምንኵስና ልብስ አለበሳት ምግቧንም አዘጋጀላትና "ለእኛ በአንድነት መኖር አግባብ አይደለም" አላት። ያንንም ደሴት ትቶላት ወደ ባሕሩ ተወርውሮ ገባ አንበሪም ተሸክሞ ወደ የብስ አወጣው። መቶ ስምንት አገሮችንም እስቲአዳርስ በአገሮች በአሉ ገዳማት ሁሉ ከዚያች ቀን ጀምሮ የሚዞር ሆነ በአንድ ቦታ እንዳይቀመጥ አስቦ ነው።
❤ ከዚህ ኋላም የዕረፍቱ ጊዜ እንደ ቀረበ አውቆ በበዓት ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደረገ። ኤጲስቆሱንም ጠርቶ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ገድሉን ሁሉ ነገረው ኤጲስቆሱም ከጸጋው ገናናነት የተነሣ አደነቀ። ከዚህም አስቀድሞ የእግዚአብሔር መልአክ ለኤጲስቆጶሱ ስለ አባ መርትያኖስ ሥጋ እንዲአስብ ነግሮት ነበር። ከዚህም በኋላ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ግንቦት21 ቀን ሰጠ ኤጲስቆጶሱም በታላቅ ክብር ገንዞ ቀበረው።
❤ ያቺ ሴት ግን እስከ ዕረፍቷ ቀን ባለ መርከብ የሚጐበኛት ሆነ በዐረፈችም ጊዜ ሥጋዋ እንደ በረዶ ነጥቶ አገኛት ሥጋዋንም ወደ አገሩ ተሸክሞ ወስዶ ቀበራት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በአባ መርትያኖስ እና ለቅድስና ባበቃቸው ቅዱሳን ሴቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለአባ_አሮን_ሶርያዊ ዘአሰረ ሰይጣን ወአጾሮ እብነ፤ በንጹሕ ዘተክህነ"። ትርጉም፦ በንጹሕ ያገለገለ ሰይጣንን አስሮ ደንጊያን ያሸከመ ለኾነ #ለሶርያዊው_ለአባ_አሮን_ሰላምታ_ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_አሮን_ሶርያዊ፦ ለዚህ ቅዱስም የመፈወስና ድንቆች ተአምራትን ማድረግ ሀብት ተሰጥቶታል። ይኸውም እግዶች መነኰሳት ወደ ርሱ በመጡ ጊዜ የርግብ ግልገሎችን አብስሎ አቀረበላቸው። ሥጋ አንበላም ባሉት ጊዜ በላያቸው አማትቦ ርግቦቹን አድኖ እንዲበሩ አደረጋቸው። ደግሞ በተራራ ላይ ገዳም ሠራ ውኃው ከተራራው በታች የራቀ ነበረ በጸለየና በእጁ ባማተበ ጊዜ ስቦ ከተራራው ላይ አወጣው።
❤ በአንዲት ቀንም ሰይጣን በክፋቱ ሊአስጠፋው ወደርሱ መጣ እርሱ ግን በላዩ በአደረ መንፈስ ቅዱስ ተንኰሉን አውቆ "ና ወደ በዓት ግባ" አለው። በገባ ጊዜም በላዩ ዋሻውን ደፈነው ታላቅ የቋጥኝ ደንጊያም ጫነበት ሰይጣንም አፈረ። ደግሞም ሁለተኛ የአካ አገረ ገዥ በሞተ ጊዜ በጸሎቱ አስነሣው። ደግሞ ውኃ የሚቀዳባቸውን አራት እንስራዎችን በአንበሳ እየጫነ በመውሰድ ዐሥር ዓመት ያህል ኖረ። ከዚህም በኋላም ግንቦት21 ቀን ወደ ዘላለም ሕይወት ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረች በአባ አሮን ሶርያዊ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት21 ስንክሳር።
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፳ (20) ቀን።
❤ እንኳን #ለጻድቁ_ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ የመን አገር ድረስ ዘምቶ በናግራን ያሉ ክርስቲያኖችን ከአይሁዳዊው ንጉሥ ከፊንሐስ ነጻ ላወጣቸው፤ የነገሠበት ዘውድ በጌታ መቃብር በጎልጎታ አስቀምጦ ንግሥናውን ትቶ ለመነነ #ለዐፄ_ለቅዱስ_ለካሌብ ለዕረፍት በዓልና #ለደብረ_ሊባኖስ ዐሥራ ስድስተኛ #አበ_ምኔት (እጨጌ) #ለአባ_ዘትረ_ወንጌል ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤#ኢትዮጵያዊው_ጻድቁ_ንጉሥ_ዐፄ_ቅዱስ_ካሌብ፦ ይህም ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚፈራውና በፍጹም ልቡ የሚወደው ሃይማኖቱም የቀና ነው።
❤ ናግራን አገር ያሉ ክርስቲያኖች አይሁድ እንደሚገድሏቸው በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ መንፈሳዊ ቅናትንም ቀና። ከዚህም በኋላ ተነሣ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብቶ በመሠዊያው ፊት ቆመ ዐይኖቹንም ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ ብሎ ጸለየ "ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ሆይ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠርህ መላእክት ሁሉ አእላፈ አእላፋት አንተን የሚያመሰግኑህ ለአንተም የሚገዙ ዐይኖቻቸው ብዙ የሆነ ኪሩቤል ክንፎቻቸው ስድስት የሆኑ ሱራፎልም ጽዕኑ ክቡር ልዩ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር በቅዱሳን የሚመሰገን እያሉ ያለማቋረጥ የሚያመሰግኑህ ብርሃን እንደ ልብስ የሚጐናጸፍ የክብር ባለቤት ለሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔር ሆይ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ። የጠፋ በጎችን ይመለሳቸው ዘንድ ልጅህን ይኸውም ቃልህ ነው ፈቃድህ የላክኸው አንተ ነህ። ተናጋሪ በግ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳትለይ ከሰማይ የወረድክና ስለ እኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆንክ ከጨለማም ከድንቁርናም አውጥተህ ወደ ብርሃን ወደ ሕይወት ወደ ዕውቀት የመራኸን። አሁንም ከሀዲ ወንጀለኛ ፊንሐስ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች እንደ በጎች በማረድ እንደ ገደላቸው እሳትም አቃጥሎ የወገኖችህንና የርስትህን ልጆች እንዳጠፋቸው እይ። እነሆ አብ ሆይ እኔ አመንሁብህ በአንድ ልጅህም በሕያው ቅዱስ መንፈስህም በመሠዊያህ ክብርም ተማፅኛለሁ በሃይማኖትህም ጸንቼአለሁ እንሆ ስለ አምልኮትህና ስለ ምዕመናን ወንድሞቼ ስለ ቀናሁ በአንድ ልጅህ መስቀል ጠላቶችህን ልዋጋቸው እወጣለሁና ከአለኝታዬ እንዳታሳፍረኝ የሚያውቁህም አምላካቸው ወዴት ነው እንዳይሉ። ስለ በደሌና ስለ ኃጢአቴም ጸሎቴን የማትሰማ ልመናዬንም ንቀህ የምትተው ከሆነ በዚህ ቦታ ብትገድለኝ ይሻለኛል። አቤቱ መሐሪ ይቅር ባይ ርኅሩህ ርስትህ የሆኑ ምዕመናንን በከሀድያን ጠላቶችህ እጅ አሳልፈህ አትስጥ። እኛ ወገኖችህና የርስትህ መንጋዎች ስለሆን ለአንተም ምስጋና እናቀርባለን ምስጋና ገንዘብህ ነውና ለዘላለሙ"።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ካሌብ ከአገረ መንግሥቱ ወጥቶ ሔደ የናግራንን አገር ያጠፋአት አይሁድን ገደላቸው ብዙ ተአምራትም አድርጎ ስለ አደረገለት ሁሉ እግዚአብሔር እያመሰገነ ወደ አገረ መንግሥቱ በታላቅ ክብር በታላቅም ደስታ ተመለሰ። "ለእግዚአብሔር ምን ዋጋ እከፍለዋለሁ ለጌትነቱና ፍጹም ለሆነ ገናናነቱ መባ አድርጌ ነፍሴንና ሥጋዬን ከማቀርብለት በቀር" አለ።
❤ ከዚህም በኋላ ይህን ዓለም ንቆ መንግሥቱንም ትቶ ወጣ ደጋጎች መነኰሳት ወደ ሚኖሩበት ወደ አባ ጰንጠሌዎን በተራራ ላይ ወደ አለ ገዳም እስከ ደረሰ በእግሩ ሔደ። ወደ ዋሻ ውስጥም ገብቶ ሰውም እንዳያየው የዋሻውን በር ዘግቶ በዚያ ውስጥ ኖረ ከዚያችም ወጥቶ ዳግመኛ ዓለምን እንዳያይ ማለ። ከእርሱ ጋራም ያገባው ዕቃ የለም ከምንጣፍ ከሸክላ ጽዋ ከለበሳት የምንኵስና ልብስ በቀር ምግቡም አምባሻና ጨው የሚጠጣውም ውኃ ነው።
❤ የክብር ባለቤት ከሆነ እግዚአብሔር ቃል መቃብር መስኮት ላይ ይሰቅልለት ዘንድ የኢየሩሳሌሙን ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስን እየለመነው ወጋው ብዙ የሆነ የነገሠበትን ዘውድ ላከ። ወደ ዋሻውም ከገባ በኋላ ከማንም ጋራ አልተነጋገረም እግዚአብሔር ደስ አሰኝቶ በፍቅር አንድነት ግንቦት 20 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዐፄ ካሌብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ዘትረ_ወንጌል፦ ይህም ቅዱስ የደብረ ሊባኖስ ዐሥራ ስድስተኛ አበ ምኔት የሆነ ነው። ከታናሽነቱ ጀምሮ እንደ መላእክት ንጽሕናን የለበሰ ትሕትናን ቅንነትን የሚወድ ነበረ። የምንኵስናንም ልብስ ከለበሰ በኋላ መልካም ገድልን ተጋደለ በክርስቶስ መንጋ ላይም ጠባቂ ሁኖ ተሾመ ከዚያም በኋላ በበጎ እርጅና ግንቦት 20 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የአባ ዘትረ ወንጌል በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ #የግንቦት_20 ስንክሳር::
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ዮሴፍ_ዘአክሱም፦ እኚህ ጻድቅ ልደታቸውና ዕረፍታቸው በተመሳሳይ ግንቦት 19 ቀን ነው፡፡ ልጅ ሆነው እየተጫወቱ ሳለ መልአክ መጥቶ ለወላጆቻቸው የዓለም ሰው እንዳልሆነ ስለነገራቸው ወስደው ለሊቀ ጳጳሱ ሰጧቸው፡፡ በአክሱም ሲማሩ አድገው በ22 ዓመታቸው መንኰሰዋል፡፡ አንጋፋ ከተባሉት የኢትዮጵያ ቅዱሳን አንዱና ዋነኛው ናቸው፡፡
❤ ጻድቁ በጸሎት ላይ እንዳሉ ጌታችን ተገልጦላቸው እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ "ትወደኛለህን?" ብሎ ሲጠይቃቸው "ጌታዬ ባለወድህማ ኖሮ መች ዓለምን ንቄ እከተልህና ገዳም እገባ ነበር" አሉት፡፡ ቀጥሎም ጌታችን "ከወደድከኝስ ለእናቴ ዓሥራት የሰጠኋት፣ ለወዳጄ ለጊዮርጊስ ዓሥራት የሰጠኋት፣ ለባለሟሌ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓሥራት የሰጠኋት ይህችን ቅድስት ሀገር ቅዱስ ያሬድንና አባ ጊዮርጊስን ያፈራችውን ኢትዮጵያን ጠብቅ" ብሏቸው ተሰወረ፡፡ ጻድቁም ጌታችን ይህን ከነገራቸው በኋላ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ስለ ሀገራችን ቆመው ጸልየዋል፡፡
❤ ሸዋ ቡልጋ ፈጠጋር ውስጥ ለሚገኙት ወንድማቸው ለታላቁ ጻድቅ ለአቡነ ዘካርያስም ስለ ኢትዮጵያ አብዝተው እንዲጸልዩ መልእክት ስለላኩባቸው አቡነ ዘካርያስም ዕድሜ ልካቸውን የጸለዩአት ጸሎት "የኢትዮጵያን ሕዝብ ማር" የምትል ነበረች፡፡ የአቡነ ዘካርያስ ገዳም ቡልጋ ውስጥ ይገኛል፡፡ አቡነ ዮሴፍ ዘአክሱም የሀገራችንን ሊቃውንትና ሕዝቡንም ለብቻ ሰብስበው የሮማውያን የሀሰት ትምህርት ነፍስን ለሲኦል የሚዳርግ ፍጹም ክህደት መሆኑን አጥብቀው አስተምረዋል፡፡ ጻድቁ በአንድ ወቅት ርሀብ በሆነ ጊዜ የገዳሙን ድንጋዮች ባርከው ዳቦ አድርገው ሕዝቡን የመገቡ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ከአባታች ከአባ ዮሴፍ ዘአክሱም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን ፣ በጸሎታቸው ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደና #የግንቦት_19 ስንክሳር፡፡
ያስተማረው ነው፡፡ ጳውሎስ ሳምሳጢን በገዳም ቅጠል እየበላ የሚኖር ተሐራሚ መናኝ ነበር፡፡ በጾም በጸሎት ሲኖር ሰይጣን ራሱን ሰውሮ መጥቶ ተገለጠለትና "ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቶልሃል፤ ነገር ግን አምላክ ያለሩካቤ በድንግልና የተወለደ አይምሰልህ በሩካቤ ተወለደ እንጂ፤ ይህም ልጅ ደግ ሰው ሆነ፣ በ30 ዘመኑ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ተጠመቀ፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ተቀመጠ፣ ያን ጊዜም ይህ ሰው በጸጋ የሥላሴ ልጅ ሆነ" ብሎ አስተማረው፡፡ ጳውሎስ ሳምሰጢንም ሰይጣን የነገረውን ነገር በልቡ አምኖ ለደቀ መዝሙሩ ለተያስሮስ አስተማረው፡፡ ተያስሮስም ለድያድርስ አስተማረው፡፡ ድያድርስም ለንስጥሮስ አስተማረው፡፡ ንስጥሮስም ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንን አምላካችንን "መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ዕሩቅ ብእሲ ነው" ብሎ ለልዮንና ለመርቅያን አስተማራቸው፡፡
❤ ንስጥሮስ ይህን አዲስ የክህደት ትምህርት እንዳመጣ በሰሙ ጊዜ 200 ኤጲስ ቆጶሳት በቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ መሪነት በኤፌሶን ተሰብስበው ሲያስተማሩት እምቢ ቢላቸው አውግዘው ለዩት፡፡ ንስጥሮስም ሰውነቱ መግሎ ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ በኋላም መርቅያን ሲነግሥና ልዩንም የሮም ሊቀ ጳጳስ ሲሆን ሁለቱም አባታቸው ንስጥሮስ ያስተማራቸውን ሃይማኖት ማስፋፋት ቻሉ፡፡ እነ ልዮንም ንስጥሮስ በተወገዘበት ጉባዔ ላይ የነበሩትና አሁን ለሥጋቸው የፈሩ አባቶችን ይዘው ከንስጥሮስ ክህደትና ከቅዱስ ቄርሎስ ትምህርት አወጣጥተው የራሳቸውን የረከሰ ሃይማኖታዊ ድንጋጌ አወጡ፡፡ "ክርስቶስ ሁለት አካል ነው፣ አንዱ የማርያም ልጅ አንዱ የእግዚአብሔር ልጅ በመቀራረብ አንድ ሆኑ ያለውን አውጥተው ከቅዱስ ቄርሎስም ቃልና ከንስጥሮስ ክህደት ቀላቅለው መለኮት የመለኮትን ሥራ ይሠራል፣ ትስብእትም የትስብእትን ሥራ ይሠራል፤ በሁለት መንገድ አንዱ ተአምራትን ያደርጋል ሁለተኛው መከራን ይቀበላል ስለዚህም ትስብእት ከመለኮት ያንሳል" ብለው ጻፉ፡፡ ይህንንም የክህደት ጽሕፈታቸውን ለቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላኩለት፡፡ እርሱም ሄዶ ከክህደታቸው እንዲመለሱ አስተማራቸው፡፡ "በአንዱ ክርስቶስ ላይ ለምን የሁለትነት ነገር ትናገራላች? ወደ ሠርግ ቤት ተጠርቶ የሄደው ውኃውንም የወይን ጠጅ ያደረገው እርሱ አንዱ ክርስቶስ ነው…" እያለ በብዙ ምሳሌ ካስተማራቸው በኋላ ልዮንንና መርቅያን የጻፉትን የክህደት ጽሕፈት በፊታቸው ቀደደው፡፡ እነርሱ ግን አንድ ጊዜ ክደዋልና የቅዱስ ዲዮስቆሮስን ፂሙን ነጭተው ጥርሱን አውልቀው ብዙ አሠቃዩት፡፡ እርሱም የነጩትን ፂሙንና ያወለቁትን ጥርሱን ሰብስቦ "እነሆ የሃይማኖቴን ፍሬ ተቀበሉ" ብሎ ለእስክንድርያ ክርስቲያኖች ላከላቸው፡፡ ከሃዲያኑም ወደ ጋግራ ደሴት አጋዙትና በዚያው ዐረፈ፡፡
❤ ሰይጣን ለመጀመሪያ ጊዜ ለጳውሎስ ሳምሳጢን ያስተማራትን ያችን ክህደት በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሰይጣን የሚያድርባቸው ሰዎች እየተቀባበሏት እስከ ንስጥሮስንና እስከ ልዮን ድረስ ከደረሰች በኋላ የልዮን ልጅ በሆነው በአውፍንስ አማካኝነት በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ገባች፡፡ አውፍንስም ክህደቱን ለሁለት የሀገራችንን መነኰሳት አስተማራቸው፡፡ ለአንደኛው "ወልድ ሦስት ልደት አለው፣ በመጀመሪያ ከአብ ተወለደ ዳግመኛም በመንፈስ ቅዱስ ሥጋ ከድንግል ተወለደ ሦስተኛም በቤተልሔም ተወለደ" ብሎ ካስተማረውና ካስካደው በኋላ ስሙን "ተክለ ሃይማኖት" ብሎ ጠራው፡፡ ሁለተኛውንም መነኩሴ ለብቻው ጠርቶት "ልጄ ሆይ ስማኝ ልብ አድገህም ዕወቅ፣ ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ቅብዐት የከበረ ነው፣ ይኸውም ሳይዋሃድ ማደር ነው" ብሎ ካስተማረውና ካስካደው በኋላ ስሙን "ኤዎስጣቴዎስ" ብሎ ጠራው፡፡ እነዚህም የካዱ ሁለቱ መነኰሳት በየሀገሩና በየአውራጃው እየዞሩ ሀገራችን ኢትዮጵያን በክህደት ትምህርታቸው አጥፍተዋት ነበር፤ ነገር ግን ብዙ ቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ይህን ክህደት በትምህርታቸውና በተአምራታቸው እንዲገታ አድርገውታል፡፡
❤ አቡነ ብስጣውሮስም እነዚያን ከሃዲዎች አውግዘው ለዩአቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ከሃዲያኑ አባታችንን ከሰሷቸውና ከጎንደሩ ንጉሥ ጋር አጣሏቸው፡፡ ንጉሡም የእነዚያን ካሃዲዎች እምነት አምኖ ተቀብሎ ነበርና አባታችንን ወደ ጎንደር እንዲያመጧቸው ጭፍሮቹን ላከ፡፡ አቡነ ብስጣውሮስም ነገሩን አውቀው ስለ ቀናች ሃይማኖት ይመሰክሩ ዘንድ አንደበት እንዲሆናቸው ጌታችንን በጸሎት ሲጠይቁ ጌታችንም "ልጄ ብስጣውሮስ ሆይ አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ እኔ ስለመሠረትኳት አንዲት ሃይማኖት ጽና" አላቸው፡፡ አባታችንም ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄዱና ንጉሡ ሰዎቹን ስለማውገዙ ጠየቃቸው፡፡ አባታችንም ንጉሡን ስለ ቀናች ሃይማኖት እየመሰከሩለት አስተማሩት፡፡ ንጉሡም በብዙ ስጦታና ሽንገላ ሊያታልላቸው ሞከረ ነገር ግን አባታችን አጥብቀው ተቃወሙት፡፡ ንጉሡም ዕውቀታቸውንና ጽናታቸውን ባየ ጊዜ አባታችንን በእግር ብረት አሳስሮ አሥር ቤት ውስጥ ጣላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ የእግር ብረቱ እንደሰም ቀልጠ፡፡ ወታደሮቹም ይህንን ተአምር አይተው ፈርተው ሄደው ለንጉሡ ነገሩት፡፡ ንጉሡም ሰምቶ ደነገጠ፤ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ወደ አባታችን መጥቶ ሰገደና "አባቴ ሆይ ይቅር በሉኝ የሃይማኖትንም ነገር እንደገና አስተምሩኝ" አላቸው፡፡ እሳቸውም አስተምረው ባረኩት፡፡ በመከራቸውም ታግሰው ለልጆቻቸውና ለእኛም የሐዋርያትን ሃይማኖት አጸኑልን፡፡ ዕድሜአቸውም 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ዕረፍታቸው እንደደረሰ ዐውቀው የቀናች ሃይማኖት በሀገራችን ለዘለዓለም ጸንታ ትኖር ዘንድ ጌታችንን አጥብቀው ለመኑት፡፡ ጌታችንም በደሙ የመሠረታት የቀናች ሃይማኖት በሀገራችን ጸንታ እንደምትኖርና ሌላም የምሕረት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ግንቦት 19 ቀን ዐረፉ፡፡
❤ በዚያችም ዕለት ሐይቅ አለቀሰች፤ የሐይቅም ባሕር ሦስት ዓመት በኃይል ስትታወክ አቡነ አላኒቆስ ይህ ሁሉ የሆነው ስለ አባታችን ስለ ብስጣውሮስ ማረፍ መሆኑን ዐውቀው ወደ ንጉሡ ሄደው የአባታችንን ዐፅም እንዲሰጣቸው ጠየቁት፡፡ ንጉሡ ግን "በረድኤታቸው ይጠብቁኛልና አልሰጥም" አላቸው፡፡ ንጉሡ ስለከለከላቸው አቡነ አላኒቆስም ቊስቋም ወደምትባል በወርቅና በከበረ ዕንቁ ወደተሸለመች ወደ እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ሄደው በእመቤታችን ሥዕል ሥር ወድቀው አለቀሱ፡፡ ሥዕሏም በሰው አንደበት አናግራ ካጽናናቻቸው በኋላ የአባታችን ዐፅም ከመሠዊያው በስተቀኝ በኩል እንደሚገኝ ነገረቻቸው፡፡ አቡነ አላኒቆዎም ዐፅማቸውን አፍልሰው ወደ ሐይቅ በተመለሱ ጊዜ የመዓዛው ሽታ የንጉሡን አገር ሁሉ መላው፤ መቃብሩ በነበረበት ቦታም የብርሃን ዓምድ ተተክሎ ታየ፡፡ ንጉሡም መነኲሴው የአባታችንን ዐፅም እንደወሰዱ ባወቀ ጊዜ መነኲሴውን ይዘው ከአባታችን ዐፅም ጋር ያመጡለት ዘንድ ብዙ ፈረሰኛ ወታደሮቹን ላካቸው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በጥበቡ ሰውሯቸዋልና አቡነ አላኒቆስን ሊያገኟቸው አልቻሉም፡፡ አቡነ አላኒቆስም የቅዱስ አባታችንን ዐፅም ወስደው በሐይቅ በመሠዊያው በስተቀኝ በኩል በቀበሩት ጊዜ በፊት ያስቸግር የነበረው የባህሩ ኃይለኛ ንውጽውጽታ በአንድ ጊዜ ጸጥ አለ፡፡ ሌላም ብዙ ተአምራት ተደርገው ታዩ፡፡ ይኸውም ፍልሰተ ዐፅማቸው የካቲት 8 ቀን የተፈጸመ ነው፡፡ ከአባታችን ከአቡነ ብስጣውሮስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ብስጣውሮስ_ዘሐይቅ፦ ሙሉ ስማቸው ዓቃቤ ሰዓት አቡነ ብስጣውሮስ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን የትውልድ ሀገራቸው መቅደላ ነው፡፡ አባታቸው ፍተ ድንግል እናታቸው ጽዮን ሞገሳ የሚባሉ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ አቡነ ብስጣውሮስ በ17ኛው ምዕት ዓመት የነበሩ ታላቅ ጻድቅ ሲሆኑ የታላቁና የጥንታዊው ትምህርት ቤትና የሥርዓተ ገዳም ተቋም የደብረ ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም አበምኔት ነበሩ፡፡ በልጅነታቸው ትምህርት ቤት ገብተው የሐዋርያትን ሥርዓትና የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጓሜ በሚገባ ተምረዋል፡፡
❤ በዘመናቸው የሃይማኖት ስደት ስለነበር አባታቸው ፍተ ድንግል ስለ ሃይማኖታቸው በዐላውያን ሰማዕት ሆነው ሲገደሉ አቡነ ብስጣውሮስ የአባታቸውን ዐፅም ይዘው በመሸሽ ወደ ላስታ ሄደው በእመቤታችን ስም በተሠራች ገዳም በደብረ ዠመዶ ወስደው ቀበሯቸው፡፡ በኋላ በዐፄ ፋሲል ዘመን ሃይማኖት ሲመለስ ዐፅማቸውን አፍልሰው አምጥተው አገራቸው ቀብረዋቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ እናታቸው በግድ ሚስት አጭተውላቸው የነበረ ቢሆንም ብዙ ሳይቆዩ ሚስታቸው ስለሞተች ቀድሞም የተመኙትን የምንኩስና ሕይወት ለመኖር ወሰኑ፡፡
❤ አንድ ቀን አንዱ የደብረ ሐይቅ መነኲሴ የገዳሙን ምርት ገበያ ለመሸጥ ይዘው እንደሄዱ አንድ ቀማኛ ወንበዴ አግኝቶ ሊቀማቸው ሲል አቡነ ብስጣውሮስ ደርሰው አዳኑት፡፡ መነኵሴውንም ወደ ቤታቸው ወስደው በመልካም መስተንግዶ አሳደሯቸው፡፡ መነኲሴውም በዚያች ሌሊት ስለ አቡነ ብስጣውሮስ ብዙ ነገር ከተመለከቱ በኋላ አቡነ ብስጣውሮስን ስለ ምንኩስና አስተማሯቸው፡፡ መነኩሴው በማግስቱ ሲሄዱ ወደ ሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም መጥተው እንዲጎበኟቸውና እንዲባረኩ ነግረዋቸው ሄዱ፡፡ አቡነ ብስጣውሮስም እግዚአብሔር መንገዳቸውን ይመራቸው ዘንድ ብዙ ከጸለዩ በኋላ ወደ ሐይቅ ገዳም ገቡ፡፡ በገበያ ያገኘውና በቤቱ ያሳደረውም መነኲሴ ሲያያቸው ደስ ተሰኝነቶ የገዳሙ አበምኔት ዓቃቤ ሰዓት አባ ዘወልደ ክርስቶስ ዘንድ ወሰዳቸው፡፡ አበምነቱም አቡነ ብስጣውሮስን ገና እንዳዩአቸው ጸጋ እግዚአብሔር እንዳደረባቸው አይተው በጣም ደስ ተሰኙ፡፡ አቡነ ብስጣውሮስም መመንኰስ እንደሚፈልጉ ለአበምኔቱ ሲነግሯቸው አበምኔቱ "የምንኲስና ሥራ ቀላል አይምሰልህ፣ ብዙዎች ወደ እኛ መጡ ነገር ግን መታገስ ተስኗቸዋል…" በማለት የምንኲስና ሕይወት ከባድ ፈተና እንዳለበት ነገሯቸው፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ብስጣውሮስም "በልዩ ልዩ ዓይነት ፈተናዎች ፈትኑኝና ሥራዬን ካዩ በኋላ ያመነኲሱኛል" አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ብስጣውሮስ በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት እየተጋደሉ ገዳሙን በጉልበት ሥራ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ከገዳሙ አበምኔት ከዓቃቤ ሰዓት አባ ዘወልደ ክርስቶስ እጅ ምንኲስናን ተቀበሉ፡፡ ተጋድሎአቸውንም ከበፊቱ ይበልጥ በማብዛት መኖር ጀመሩ፡፡
❤ እናታቸው የልጃቸውን መመንኰስ ሰምተው ወደ ሐይቅ መጡ ነገር ግን አቡነ ብስጣውሮስ እናታቸውን ወጥተው ላለማየት ተሠወሩ፡፡ አበምኔቱም በብዙ ፍለጋ አግኘተዋቸው "ልጄ እናትህ አንተን ለማየት ከሩቅ ሀገር መጥታለችና ሄደህ አግኛት" ሲሏቸው አቡነ ብስጣውሮስም "አባቴ ሆይ ጌታችን በወንጌል ያለውን አያስታውሱምን? "እነሆ እናትና ወንድሞችህ በውጭ ቆመዋል ባሉት ጊዜ ጌታችን በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ ከሚፈጽም በቀር እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?" ብሎ ተናግሮ የለምን? ስለዚህ ወደ እናቴ አልሄድም" ብለው ለአበምኔቱ መለሱላቸው፡፡ አበምንቱም "ከመንገዱ ርቀት የተነሣ እናትህ በብዙ ድካም መጥታለችና ልታያት ይገባል" ብለው ግድ አሏቸው፡፡ አቡነ ብስጣውሮስም ሄደው እናታቸውን ካገኟቸው በኋላ እናታቸውም በዛው መንኲሰው በባሕሩ ዙሪያ ካለው ከሴቶች ገዳም ገብተው ማገልገል ጀመሩ፡፡
❤ አቡነ ብስጣውሮስ ከመልካም የጉልበት ሥራ ጋር ቀን ቀን የዳዊትን መዝሙር፣ የነቢያትን መጻሕፍትና መኃልየ መኃልይን ሲደግሙ ይውላሉ ሌሊት ሌሊት ሐይቁ ውስጥ ገብተው እጅግ አብዝተው ሲጸልዩ የብርሃን ዓምድ ተተክሎ ይታይ ነበር፡፡ ጸሎታቸውንም ሲጀምሩ ሰማያት ይከፈቱ ነበር፡፡ ቅዱሳን መላእክትንም ሲወጡ ሲወርዱ ያዩአቸዋል፡፡ አቡነ ብስጣውሮስ በእንደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ ብዙ ሲያገለግሉ ዜና ትሩፋታቸው በሁሉ ዘንድ በዓለም ተሰማ፡፡ አስተዳዳሪው ዓቃቤ ሰዓቱ አቡነ ዘወልደ ክርስቶስም እርጅና ሲጫናቸው ማኅበሩን ሰብስበው "በእኔ ቦታ አባት የሚሆናችሁን ምረጡ" አሏቸው፡፡ እነርሱም "እግዚአብሔር ያመለከተህን አንተ ሹምልን" አሏቸው፡፡ አባ ዘወልደ ክርስቶስም በጸሎት ከጠየቁ በኋላ "እግዚአብሔርና እኔ አባት ይሆኑላችሁ ዘንድ አቡነ ብስጣውሮስን መርጠንላችኋል" አሏቸው፡፡ ቀጥሎ አበምኔቱ ስለ አቡነ ብስጣውሮስ እንዲህ በማለት ትንቢት ተናገሩ፡- "እርሱ ሃይማኖቱ የቀና ምግባሩ ያማረ በተጋድሎም የጸና በጸሎቱ ሀገርን ይጠብቃል፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በነገሥታቱና በመኳንንቱ ፊት ያደርጋል" እያሉ ለማኅበሩ በነገሯቸው ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኙ፡፡ አቡነ ብስጣውሮስ ግን ይህን ሲሰሙ የመረረ ልቅሶን አለቀሱ፤ ከእነርሱም ዘንድ ይሸሹ ዘንድ ወጥተው በመርከብ ተጭነው ሄዱ፡፡ ነገር ግን ደርሰው ይዘው በእግዚአብሔር ፈቃድ ይሾሟቸው ዘንድ ይዘው አሰሯቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ከሰማይ "ብስጣውሮስ የአባትህን የአበምኔቱን ቃል አታስተሐቅር" የሚል ቃል ተሰማ፡፡ ማኅበሩም ይህንን ከሰማይ የመጣውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ተደስተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ብስጣውሮስን እንደ ሕጋቸውና እንደ ሥርዓታቸው የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም አበምኔትና ዓቃቤ ሰዓት በማድረግ ሾሟቸው፡፡
❤ አቡነ ብስጣውሮስም በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ወንበር በተቀመጡ ጊዜ የተሰወረውን ሁሉ የሚያዩ ሆኑ፡፡ ፊታቸውም እንደ ጨረቃ የሚያበራበት ጊዜ ነበር፣ ለአገልግሎትም ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ክንፋቸውን እየጋረዱ ይቀበሉት ነበር፡፡ ጻድቁ ጸሎተ ዕጣን ሲያሳርጉ እያለቅሱ ነበር፤ የጌታችንን መከራ እያሰቡ ሰውነታቸውን በድብቅ ይገርፋሉ፤ ድኆችንና ጦም አዳሪዎችን ሁሉ የሚንከባከቧቸው አባት ሆኗቸው፡፡ ገዳሙንም አፍርሰው ሊዘርፉ የመጡትን ወራሪዎች አባታችን ወደ መቅደስ እየገቡ በጸሎት እያሰሯቸው አሳፍረው ይመልሷቸው ነበር፡፡
❤ አቡነ ብስጣውሮስ በእንዲህ ዓይነት ተጋድሎ ገዳሙንና ሀገራችንን እየጠበቁ ሲኖሩ በመሀል የቅብዐት እምነት ነገር በገዳሙ ተነሣ፡፡ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንን አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን "ከትስብእት ጋር ከተዋሐደ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ተቀባ፣ በዚህም ቅብዐት በጸጋ ልጅ፣ ንጉሥም፣ ነቢይም፣ ሊቀ ካህናትም ተባለ" የሚሉ ከሃዲያን ተነሡና የእግዚአብሔር ሰው ብፁዕ አባታችን ብስጣውሮስ ይህንን የክሕደት ትምህርት ሰምተው እጅግ እያዘኑና እያለቀሱ የካዱትን ሰዎች በብዙ ምሳሌ እያደረጉ ማስተማር ጀመሩ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ቅብዐት በጸጋ ልጅ እንዳልሆነ፣ ነገር ግን በባሕርይው የአብ ልጅ እንደሆነ፣ እርሱ ራሱ ቅብ፣ እርሱም ራሱ ቀቢ፣ እርሱ ራሱ ተቀቢ እንደሆነ በብዙ ምሳሌ እያደረጉ የቀደሙ የአባቶቻችንንም ትምህርት ሁሉ እየጠቀሱ አስተማሯቸው፡፡ ነገር ግን ሰይጣን አንድጊዜ አስክዷቸዋልና አንዳንዶቹ እምቢ አሏቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ሐዋርያት ከመሠረቷት አንዲት ቤተ ክርስቲያን አውግዘው ለዩአቸው፤ ቤተ ክርስቲያንም ሰላም ሆነች፡፡ በዚህም አባታችን ከሃድያንን የሚዘልፉ ዳግማዊ ቄርሎስ ተባሉ፡፡ ይህም ክህደት መጀመሪያ ሰይጣን ለጳውሎስ ሳምሳጢን
❤ ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ የእግዚአብሔርን ከጠሩበት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይልም ነበር፡፡ ከልጆችም ጋር ሲጫወቱ ልጆቹ "ስለ እግዚአብሔር ብለህ ይህን አድርግልን…" ሲሉት ያደርግላቸዋል፡፡ በእረኝነት ሳሉ ምሳውንም ሆነ እራቱን ለምስኪኖች ይሰጣል፡፡ ለእግዚአብሔር ስም እጅግ ቀናተኛ ስለነበሩ ስሙን ይፈሩ ስለነበር ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው "ይህን ክፉ ነገር በራስህ ላይ አድርግ" ባሏቸው ሰዓት እንኳን በራሳቸው ላይ አንዳች ክፉ ነገር ወይም አደጋ ለማድረስ ወደኋላ አይሉም ነበር፡፡ ይህንን ሊፈትኗቸው ብለው አንድ ቀን ስለታማ ጦር አምጥተው "ስለ እግዚአብሔር ብለህ እስቲ ራስህን በዚህ ስለታማ ጦር ትወጋ ዘንድ ና" ባሏቸው ጊዜ አብርሃም ልጁን ይስሃቅን ሊሠዋ በኅሊናው እንደወሰነ እርሳቸውም በቁርጥ ኅሊና ሆነው ራሳቸውን በጦሩ ሊወጉ ሲሉ ዘለው ያዟቸው፡፡
❤ በሌላም ጊዜ እንዲሁ ሊፈትኑት በጭነት ምክንያት ጀርባው የቆሰለ አህያ አምጥተው "ዓቢየ እግዚእ ስለ እግዚአብሔር ብለህ የዚያችን አህያ ቁስሏን ላስ" አሉት፡፡ እርሱም ያን ጊዜ "ርኩስን ብስም ኃጢአት ይሆንብኛል፣ አይሆንም ካልኳቸው ደግሞ ስመ እግዚአብሔርን ጠርተንበት እምቢ አለ ስለሚሉ የፈጣሪዬን ስም መዳፈር ይሆንብኛል ብሎ በልቡ አሰበና ያን ጊዜ ይስም ዘንድ ተመለሰ፡፡ ባልንጀሮቹም በቁርጥ ኅሊናው እንደወሰነ ባወቁ ጊዜ ሊያደርገውም ሲሄድ ተመልከተው ቶሎ ብለው ሮጠው ከኋላው ያዙት፡፡ እርሱም "እኔስ የፈጣሪዬን ስም እፈራለሁ ስሙን ተደፋፍሬ በምድር በሕይወት ከምኖር ሞት ይሻለኛል" አላቸው፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ወላጆቹ ለመምህር ዘርዐ ሚካኤል ሰጡትና ብሉያት ሐዲሳት መጻሕፍትን ሌሎችንም አስተማረው፡፡ ከዚህም በኋላ መምህሩንና ዓቢየ እግዚእን ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወስዶ አክሱም አደረሳቸውና ዓቢየ እግዚእ ከአባ ሰላማ መተርጉም እጅ ዲቁናና ቅስና ተቀበሉ፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ የሃሌ ሉያው አባ ሳሙኤል ቆብንና አስኬማን ሰጠው፡፡ ለአባታችን አንበሶችና ነብሮች አራዊትም ሁሉ እንደ ጓደኛ ሆነው ታዘዙለት፡፡ ቶራዎችም በሰው አንደበት ያናግሩታል፡፡ ቶራዎቹም ከነብሮች ጋር ተስማምተው እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ እርሱም እህልን ሳይቀምስ በቤት ጣሪያም ውስጥ ገብቶ ሳይቀመጥ ተጋድሎውን በማብዛት ብዙ ደከመ፡፡ የመላእክት ክንፍ ተሰጥቶት በሦስት ሰዓት ውስጥ የሕያዋንን መኖሪያ አይቶ ይመለሳል፡፡ በዋልድባ ገዳም ስውር ቤተ ክርስቲያን አለ ነገር ግን የሚያገኘው አልነበረም፡፡
❤ አባታችን ዓቢየ እግዚእ ግን 40 ቀንና 40 ሌሊት ከጾመ ከጸለየ በኋላ አራዊት ተሸክመውትና አጅበውት እዚያች ስውር ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ደረሰ፡፡ በውስጧም የሚንቀሳቀስ ብርሃን አየ ይኸውም የዚህ ዓለም ብርሃን አይደለም፡፡ በውስጧ ያሉ ስውራን ቅዱሳንንም አገኛቸውና ከእነርሱ ተባረከ፡፡ ከዚህም በኋላ የተለያዩ አስደናቂ ተአምራትን እየሠራ ወንጌልን በመስበክ ብዙ አገለገለ፡፡ የተከዜን ባሕር ለሁለት ከፍሎ በመሻገር በአካባቢው ያሉ እስላሞችን በተአምራቱ አሳመናቸው፡፡ ከደረቅ ጭንጫም ላይ ውኃን አፈለቀ፡፡ በተሰጠውም ክንፍ ብሔረ ሕያዋንና የጌታችን መካነ መቃብር ዘንድ እየሄደ ከቅዱሳን ጋር ጸሎት ያደርጋል፡፡ ደቀ መዛሙርቶቹም "እገሌ ሞቷልና የት እንቅበረው?" ባሉት ጊዜ እርሱ ግን ከጸለየ በኋላ ከሞት ያስነሣዋል፡፡ የሐማሴኑ መስፍንም እንዲሁ በጦርነት ወቅት ሞቶ ባለሟሎቹ አስክሬኑን ተሸክመው ወደ ሀገሩ ሲወስዱት ሰላምጌ ከምትባል የላስታ ምድር ደረሱና በመንገድ አባታችንን አገኛቸውና "ይህን በድን ወዴት ትወስዱታላችሁ?" አላቸው፡፡ እነርሱም "ሐማሴን ይባላል በንጉሡ ትእዛዝ ወደ ጦርነት ዘምተን ሳለ እርሱ ሞቶ ወደ ሀገሩ እየወሰድነው ነው" አሉት፡፡ አባታችንም ያስቀምጡት ዘንድ አዘዛቸውና ውኃ አምጡልኝ አላቸው፡፡ ስመ እግዚአብሔርንም ጠርቶ ከጸለየና በውኃው ካጠመቀው በኋላ ሐማሴንን ከሞት አስነሣው፡፡ ሐማሴንንም ስለ አሟሟቱ ሲጠይቁት "መልአከ ሞት ወስዶ ለፍርድ ሳያቆመው በፊት ይህ ጻዲቅ መነኲሴ ስለ እኔ ሲለምን አየሁት፤ በጸሎቱም እግዚአብሔር ማረኝና ነፍሴን ወደ ሥጋዬ እንድትገባ አዘዘ" ብሎ የሆነውን ሁሉ በዝርዝር ነገራቸው፡፡
❤ አባታችንም ሐማሴንን "በሰላም ወደ ሀገርህ ሂድ" ብሎ አሰናበተው፡፡ ያ ሹም ግን ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች መጽውቶ ወደ አባታቸን ዘንድ መጣ፡፡ የአባታችንን ጽድቁንና ትሩፋቱን የሰሙ ሁለት ሺህ ሰዎችም አብረውት ከሹሙ ጋር መጡና አባታችንን "የምንኲስና ልብስ ልንለብስ እንወዳለን" ባሉት ከፈተናቸው በኋላ አመነኰሳቸው፡፡ ያንንም መስፍን ፍኖተ ሕይወት-የሕይወት መንገድ ብሎ ሰየመው፡፡ የአባታችንም ያችን ደብር ሰጠውና አበ ምኔት ሆኖ ብዙ አገልግሎ ዘመኑን ጨረሰ፡፡ ዳግመኛም አባታችንን በደብረ መድኃኒት በምትባል ደብር ሳለ ስሟ ቡሩክት ማርያም የምትባል ልጁ ሞታ አባታችን አለቀሰላት፡፡ ተነሥቶም ወደ ዋሻ ገብቶ በሩን ዘግቶ አመድ ነስንሶ ደረቱን እየደቃ እየጸለየ ሳለ ቡሩክት ማርያም ከሞት መነሣቷን ደቀ መዛሙርቱ ሮጠው መጥተው ነገሩትና ሄዶ አገኛት፡፡ "ምን አየሽ?" ቢላት እርሷም "ስለአገልጋዬ ዓቢየ እግዚእ ልቅሶና መቃተት ይህች ነፍስ ወደ ሥጋዋ ትመለስና እስከምታረጅ ትኑር" የሚል ቃል ሰማሁ" አለችው፡፡ እርሷም አባታችን ካረፉ በኋላ በምድረ ዠመዶ ኖራ በኋላ በሰላም ዐረፈች፡፡
❤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ብፁዕ አባታችን ከ6 መነኰሳት ልጆቻቸው ጋር ይሰግዱ ዘንድ ሲሄዱ ርዝመቱ 120 ስፋቱ 12 ክንድ የሆነ ዐይኖቹ እንደሚነድ እሳት የሆኑ ከአፉም ነበልባል የሚወጣ እንደንስርም ክንፍ ያለው ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ መጠኑም ተራራ የሚያክል አውሬ በቁጣ ሊውጣቸው አፉን ከፈተ ምላሱን አውለበለበ፡፡ መነኰሳቱም እጅግ ደንግጠው ሳለ አባታችን ግን በስመ ሥላሴ አማትበው በአውሬው ላይ የተገለጠውን ያንን ከይሲ ለሁለት ሰነጠቁት።
❤ አባታችን አንድ ቀን ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብቶ ሳለ ገዳማውያኑ "አንድ መነኰስ ብናገኝ ሥጋወደሙ በተቀበልን…" ሲባባሉ አገኛቸውና ባረካቸውና "ዛሬ የተዘጋጀ ቁርባን አለን?" አላቸው፡፡ እነርሱም "አዎን" አባሉት ጊዜ አዘጋጂተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ አዘጋጅተው አመጡና አባታችንን "ገብተህ ቀድስ" አሉት፡፡ እሱም "ባርኩኝ" አላቸውና "እንደ መልከጼዴቅ፣ እንደ አቤል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ…" ባሉት ጊዜ ሚመጠን አለ፡፡ ይህንንም ባለ ጊዜ ኅብስትና ጽዋ ከፃሕል ጋር ተዘጋጅቶ ከላይ ከሰማይ ወረደ፡፡ ይህንንም ያዩና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሁሉ "ይህ ኅብስትና ጽዋ ከየት መጣ" እያሉ አደነቁ፡፡ አባታችንም የሐዋርያትን ቅዳሴ ቀድሶ አቆረባቸው፡፡ አባታችንም ወጣና ደመናውን ጠቅሶ በደመና ተጫነ፡፡ እነርሱም "አቤቱ ስለ እግዚአብሔር ብለህ ስምህን ንገረን" አሉት፡፡ እርሱም "ስሜ ዓቢየ እግዚእ ይባላል የምንኩስና ስሜ የመረታ ሀገር እንጦንስ ነኝ" አላቸውና ባረኳቸው ሄደ፡፡ ያም ፃሕልና ጽዋ ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ቅዱስ አባታችን በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የተለያዩ አስደናቂ ተአምራትን እየሠራ ወንጌልን በመስበክ እገዚአብሔርን ካገለገለ በኋላ ከፈጣሪው ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብሎ በግንቦት 19 ቀን በክብር ዐርፏል፡፡ ከአባታች አቡነ ዐቢየ እግዚእ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት_፲፱ (19 ) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ለዓለም ብርሃን ለሆኑት እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ላጠኑት #ለአቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት፣ በጸሎታቸውም ውኃውን ደም ላደረጉት ለታላቁ ለተአምረኛው አባት #ለአቡነ_ዓቢየ_እግዚእ፣ ጸሎት ማድረግ ሲጀምሩ ሰማያት ተከፍተው የመላእክትን አገልግሎት በግልጽ ይመለከቱ ለነበሩትና #ለአቡነ_ብስጣውሮስ_ዘሐይቅና ጌታችን ተገልጦ "ለእናቴ ዓሥራት የሰጠኋት፣ ለወዳጄ ለጊዮርጊስ፣ ለባለሟሌ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓሥራት የሰጠኋት ይህችን ቅድስት ሀገር ቅዱስ ያሬድንና አባ ጊዮርጊስን ያፈራችውን ኢትዮጵያን በጸሎትህ ጠብቅ" ብሎ ላዘዛቸው #ለአቡነ_ዮሴፍ_ዘአክሱም ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት፦ አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊት እናታቸው ዳግም ሞገሳ ይባላሉ፡፡ ትውልድ ሀገራቸው ወሎ መቄት እንጂፋ ነው፡፡ ሲወለዱ በርካታ ሙታን ተነሥተዋል፡፡ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲያደንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት።
❤ የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለትና "ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወድዋለህን አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለ ሁሉ" አለው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ እግዚአብሔር እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ።
❤ ከወለቃ አውራጃም ስሙ አባ ዘካርያስ የሚባል ነበረ እርሱም ለዮሴፍ ዘመዱ የሆነ በጭልታም ዮሴፍን ወስዶ የምንኵስና ልብስ አለበሰው። ወደትግራይ ምድርም ወስደውና በዚያ ተግባረ እድ ለምንኵስና ሥራ የሚገባ ጽሕፈትን ስፌትን ተማረ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ በረሀ ዱር ገብተው የእንጨት ፍሬ እየበሉ ከዝኆኖች ከአንበሶችና ከዘንዶዎች እየተፈተኑ በየአይነቱ በሆነ ተጋድሎ በመድከም ኖሩ። በጽድቃቸውም ኃይል ብዙ ተአምራትን አደረጉ አባ ናትናኤልም የጋለ ምንቸት በመሐል እጁ ይዞ በመነኰሳቱ ፊት ዞረ። አባ ዮሴፍም የሚያበስሉበት ማሰሮ በተሰበረ ጊዜ ወጡ ሳይፈስ አገናኝቶ እንደ ቀድሞው አደረገው። ገብረ ኄርም ሕዝባዊ ሲሆን በሞተ ጊዜ ሊአጠምቁት ሲሉ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኤጲስቆጶስነት ሹሞኛልና እኔ በእጄ አጠምቃችኋለሁ" አላቸው። እሊህም ቅዱሳን የትሩፋታቸውንና የጽድቃቸውን የአማረ ሥራቸውን አሳዩ።
❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ወደ ጳጳስ ወሰዱትና ቅስና ተሾመ። አባ ዘካርያስም በዐረፈ ጊዜ አባ ዮሴፍ ወደ ሌላ ገዳም ሒዶ ሳይቀመጥ ቁሞ አርባ መዓልትም አርባ ሌሊት ጾመ። ከድካም ጽናትም በወደቀ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል አነሣው። ሁለተኛም ከገደል አፋፍ እጁን ዘርግቶ ሳይሰበስብ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ቆመ። ሰይጣንም መጥቶ ወደ ቆላ ወረወረው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ተቀብሎ ወደ መቆሚያው መለሰው። ደግሞም ከደንጊያ ወሻ ውስጥ ገብቶ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ኖረ። ሰይጣናትም ወደርሱ እየመጡ በየራሳቸው ምትሐት በማሳየት ያስፈራሩት ነበር መላእክትም ያበረቱትና ያጸኑታል። ናላው በአፍንጫው እስቲፈስ ድረስ በየእልፍ እልፍ እየሰገደ ኖረ።
❤ ከዚያም የትራይን አውራጃዎች ሁሉ ዞረ። ወደ ሰሜንም ምድር ተሻግሮ ከቅዱስ ያሬድ መቃብር ገባ በደጃፉም ላይ ተቀርጾ አግኝቶ አንቀጸ ብርሃን ተማረ። ሲመለስም ሽፍቶች አግኝተውት በደንጊያ ወገሩት በበትርም ደበደቡት በጦርም ወግተው ጥለውት ሔዱ። አምላክን የወለደች እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ወደርሱ መጥታ አዳነችው። አንዲት ቀንም የሴት በድን አግኝቶ በላይዋ ባማተበ ጊዜ ተነሣች።
❤ ወደ ኢየሩሳሌምም ሦስት ጊዜ ሒዶ ከከበሩ ቦታዎች ተባርኳል ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት መቃብም እስከ አገረ ባርቶስና ሕንደኬ ደረሰ። ውኃው ከመላበት ወንዝም በሚደርስ ጊዜ በላዩ አማትቦ እንደ የብስ በእግሩ እየረገጠ ይሻገረዋል። አንበሶችና ነብሮች ይከተሉታል ምግብ በአጡ ጊዜ ድንጊያውን ባርኮ ሥጋ አድርጎ ይሰጣቸዋል።
❤ ከዚህ በኋላም ወደ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ደብረ ሊባኖስ ሔደ። ከአባ ተወልደ መድኅንም እጅ አሰሰኬማ ተቀበለ። አባ ተወልደ መድኅንም ሊፈትነው ወዶ ሰባት የጽድ ቅርንጫፍ ሰብሮ ትከለው ብሎ ሰጠው በተከላቸውም ጊዜ ወዲያውኑ በቅለው አደጉ እስከ ዛሬም አሉ። ብዙዎችም ወደርሱ መጥተው በእርሱ እጅ መነኰሱ እግዚአብሔር አብና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ድንግል ማርያም ስም በአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በአንድነት ኖሩ።
❤ በአንዲት ዕለትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕጣንን ሰጠችውና ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋራ የአሸናፊ የእግዚአብሔርን መንበር አጠነ። ብዙ ጊዜም ወደርሱ ሐዋርያት እየመጡ ይባርኩታል። በአንዲት ዕለትም ነብር ከእናቱ እጅ ሕፃንን ነጥቆ ወሰደ በአባ ዮሴፍም ስም በአማጸነችው ጊዜ በሦስተኛው ቀን መለሰላት።
❤ ለልጆቹም ገንዘብም ሆነ የእንስሳ ጥሪት እንዳያደርጉ ሥጋ እንዳይበሉ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ትሕትናን ቅንነትን እንዲማሩ ከንቱ ነገር ቧልትን እንዳይናገሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይስቁ ይህ ሁሉና የመሳሰለውን ሥርዓትን ሠራላቸው።
❤ ከዚህም በኋላም ሩጫውን በፈጸመ ጊዜ ግንቦት19 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ ደብረ ታቦር ብሎ በሰየማት ቤተ ክርስቲያንም ተቀበረ ከእርሱም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሴፍ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑረሰ ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት19 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ዓቢየ_እግዚእ፦ አባታቸው ያፍቅረነ እግዚእ እናታቸው ጽርሐ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ሃይማኖታቸው የቀና ምግባራቸው ያማረ በእግዚአብሔር የተወዱ ናቸው፡፡ በወርቅ በብር የከበሩ ቢሆኑም ልጅ ግን አልነበራቸውም፡፡ በእመቤታችን ስም ለተቸገሩ ምጽዋትን በመስጠት ዘወትር ይማጸኑ ነበር፡፡
❤ አንድ ቀን ድንቅ የሆነ ራእይ አየና ፈቃደ እግዚአብሔርን ሲጠባበቁ ነሐሴ 7 ቀን ጽርሐ ቅዱሳን ፀነሰችና ግንቦት አንድ ቀን እንደ ፀሐይ የሚያበራ ልጅ ወለደችና በ40 ቀኑ ሲጠመቅ ስሙን ዓቢየ እግዚእ አሉት፡፡ ያጠመቁትም የአክሱሙ ሊቀ ጳጳስ መተርጉም ሰላማ ሲሆኑ እሳቸውን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሕጻኑን እንዲያጠምቁት በማዘዝ በክንፎቹ ተሸክሞ ከአክሱም ወደ ተንቤትን ምድረ መረታ አመጣቸውና አጠመቁት፡፡ እርሳቸውም "ይህ ሕጻን ድውይ የሚፈውስ ሙታንን የሚያነሣ ቅዱስ ይሆናል" ብለው ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅዱሳን እንግዳን መቀበል ልማዳቸው ነበርና አንድ ቀን ሦስት አጋንንት በሽማግሌ አምሳል ሆነው በእንግድነት እቤታቸው ገቡና "ልጃችሁን የሐዋርያትን መጻሕፍትን መዝሙረ ዳዊትንና አርጋኖንን እንድናስተምርላችሁ ስጡን" አሏቸው፡፡ ወላጆቹም ገና ሕጻን መሆኑን በመናገር ሲከራከሩ ቅዱስ ሚካኤል ደርሶ እነዚያን አጋንንት አጠፋቸው፡፡ አጋንንቱም ይህንን ዘዴ ተጠቅመው ሕጻኑን ዓቢየ እግዚእ ወስደው ሊገድሉት ነበር ምክንያቱም በእርሱ ምክንያት ነፍሳት እንደሚድኑ ዐውቀዋልና፡፡
❤ ሰው የሆነበትንም ሥራ በፈጸመ ጊዜ "ሒዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ። ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ። ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ" አላቸው። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱ አዳኝና ሕይወት ከሆነ ቅዱስ መንፈሱ ጋራ ጌትነት ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአባ_አብርሃም_ጓደኛ_አባ_ገዐርጊ፦ ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው። በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ። ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር።
❤ ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ። እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኋላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ። ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና "ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህ ልብ ልታአጽናና ይገባሃል። የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና" አለው። አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኋላ የከበረ ወንጌል "ከእኔ ይልቅ አባቱንና እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም" ብሏል ብሎ አሰበ። ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ። አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ።
❤ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለ የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው። አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥ ሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም። ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው "ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት። ሁል ጊዜም እስከ ሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ። በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ ጌታ ተገልጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው። ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት። ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ። እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል።
❤ ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረደባት ናት። እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ። በዚያችም ጌታችን በወረደባት መስኮት ብርሃን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች።
❤ እሊህ ቅዱሳንም ለመነኰሳት የሚሆኑ ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ። ለአባቶቹ የሚታዘወውንና የሚገዛውን አመሰገኑት። ከዚህም በኋላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን ዐረፈ። ከእርሱ በኋላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን ዐረፈ። መላ ዕድሜው ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኵስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ገዐርጊ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር አሜን። ምንጭ፦ #የግንቦት_18_ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለገዐርጊ_በኀዲገ_መርዔት_ውስተ ተሐግ። ድኅረ ዐምደ ብርሃን መርሖ ፍኖተ ፈለግ። ከመ አለበዎ መልአክ ኵነኔ ሥርዓት ወሕግ። ፈጸመ ገድሎ ምስለ አብርሃም በደርግ። ውሣጤ በዐት ዘስማ በግቢግ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_18።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ትፌኑ መንፈሰከ ወይትፈጠሩ። ወትሔድስ ገጸ ለምድር። ለይኩን ስብሐቲሁ ለእግዚአብሔር ለዓለም"። መዝ 103፥30-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 16፥1-8።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "መንፈቀ ሌሊተ እትነሣእ። ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ። ወእለ የዐቅቡ ትእዛዘከ"። መዝ 118፥30-31። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 11፥1-16፣ 1ኛ ጴጥ 5፥6-12 እና የሐዋ ሥራ 10፥44-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥23-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የጥንት ጰራቅሊጦስና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፲፰ (18) ቀን።
❤ እንኳን #ለጥንት_ጰራቅሊጦስ በዓልና
#ለአባ_አብርሃም_ጓደኛ ለዐሥራ አራት ዓመታት የላማ የጣመ ሳይመገብና ሳይታኛ ለተጋደለ ለከበረ
#ለአባ_ገዐርጊ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕት_ቅዱስ_ሲኖዳ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ወበ፶ ዕለት ፈነወ ሎሙ #መንፈሰ_ቅዱሰ ከመ ዘእሳት ወተናገሩ በነገረ ኵሉ በሐዉርት"። ትርጉም፦ #በሃምሳውም_ቀን_በእሳት_አምሳል_መንፈስ_ቅዱስን ሰደደላቸው በአገሩ ሁሉ ቋንቋ ተናገሩ። #ቅዳሴ_ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ።
✝ ✝ ✝
❤ #በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ፤ ከትንሣኤ በሃምሳኛ ቀን ለደቀ መዛሙርቱ ከአብ የሚሠርጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።
❤ "እናንተም ከአርያም ኃይልን እስከምትለብሱ በኢየሩሳሌም ኑሩ" አላቸው። ሁለተኛም "ያ እውነተኛ መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል" አላቸው።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው "እርሱም አለቃቸው የሆነ ጌታችን አጽናኚውን ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ነው ሊልክልን ተስፋ አስደርጎናል የምናስበውንና የምናደርገውን ልብ ያስደርገን ዘንድ"። ይህንንም ሲነግራቸው እንሆ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ ሰሙ በዓለም ውስጥ እንደ ርሱ ያለ የማያውቁት ጣፋጭ መዓዛ አሸተቱ። የተከፋፈለ የእሳት ላንቃዎችም በየአንዳንዳቸው ላይ ሲወርዱ ታዩ። በአዲስ ቋንቋም ተናገሩ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ሊሆን አርባ ቀን ጾሙ።
❤ ሁለተኛም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ "በዓለ ኃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ። ድንገት ከሰማይ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ መላው የተከፋፈለ የእሳት ልሳኖችም ታዩአቸው በየአንዳንዳቸውም ላይ ተቀምጡባቸው ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ። በየራሳቸውም በአገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመር መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ሁሉም ተሰበሰቡ በየአገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና። ተደንቀውም በድንጋጤ እንዲህ አሉ። "እንሆ እሊህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን የጳርቴና የሜድ፣ የኤላሜጤም ሰዎች ስንሆን። በሁለት ወንዝ መካከል በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣ በፍርግያም በጽንፍልያም፣ በግብጽም፣ በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነት የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን የእግዚአብሔርን ገናናነት በቋንቋችን ሲናገሩ እንሆ እንሰማቸዋለን። ሁሉም ደግጠው የሚናገሩትን አጡ። እርስ በርሳቸውም እንጃ ይህ ምን ይሆን አሉ ሌሎች ግን እያፌዙባቸው "ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል" አሉ።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው "የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደለም ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና። ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለውነው፦ "እግዚአብሔር አለ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ መንፈሴ አሳድራለሁ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ ጐበዛዝቶቻችሁም ራእይን ያያሉ ሽማግሎቻችሁ ሕልምን ያልማሉ። ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ መንፈስ ቅዱስን አሳድራለሁ ትንቢትን ይናገራሉ። ድንቆችን በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ። ደግሞ እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል ታላቅ የሆነ የጌታ ቀንም ሳይመጣ ፀሓይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል"።
❤ ዳዊትም እንዲህ አለ "ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ደስ የሚያሰኝ ድኅነትህንም ስጠኝ። በጽኑዕ መንፈስህም አጽናኝ ለዝንጉዎች ሕግህን እንዳስተምራቸው"። ሁለተኛም "መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉ" አለ። ደግሞ "ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ምድር ይምራኝ" አለ። ደግሞም "በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በአፉ እስትንፋስ"።
❤ ኢሳይያስም እንዲህ አለ "በእኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለድኆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነትን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠ እለው ዘንድ ላከኝ"።
❤ ጌታችንም እንዲህ አለ "ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ይህን ነገርኳችሁ። ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። እኔ ሰላም እተውላችኋለሁ የአባቴንም ሰላም እሰጣች። እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ስጦታ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አትፍሩም። እኔ እሔዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ"።
❤ ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አለ "እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚገኝ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይምሰክራል። እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና ምስክሮቼ ናችሁ። እንዳትሰነካከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህም በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። እኔም ዕውነት እነግራችኋለሁ እኔ ብሔድ ይሻላችኋል እኔ ካልሔድኩ ግን አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ወደ እናንተ አይመጣምና። ከሔድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሰዋል። ስለ ኃጢአት በእኔ አላመኑምና ስለ ጽድቅም ወደ አብ እሔዳለሁና እንዲህም አታዩኝም ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና" አላቸው። "የምነግራችሁም ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን ዛሬ ልትሸከሙት አትችሉም እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ እኔን ይገልጣል ከእኔም ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋልና ለአባቴ ያለው ሁሉ የኔ ገንዘብ ነውና ስለዚህ ከእኔ ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋል አልኳችሁ። ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና"።
❤ ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ "ምንድነው ይህ ነገር ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁ የሚለን"። ጌታ ኢየሱስ ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐውቀባቸው እንዲህ አላቸው "ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ስለአልኳችሁ። እውነት እውነት እላችኋለሁ እናንተ እንደምታዝኑ እንደምታለቅሱ ዓለም ደስ ይለዋል እናንተ ግን ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ደስታ ይሆናችኋል"።
