cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts

ይህ በአቡ ጁነይድ ሳላህ አህመድ የቀረቡ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክቶች የሚሰበሰቡበት ቻነል ነው። አላህ ጠቃሚ እውቀትን ከመልካም ስራ ጋር ያግራልን! You can contact me here @salehom100

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 730
المشتركون
-224 ساعات
+97 أيام
-1030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ኡድሂያ ለማረድ ካቀዱ ከወዲሁ ጥፍርና ጸጉርዎን ከመቁረጥ ይቆጠቡ! ------------------- ☞ እንድ ሙስሊም ሀጅ የማያደርግ ከሆነና በዒድ አል አድሀ እለት ኡድሂያን ለማረድ ካሰበ የዙልሂጃ ወር ከገባበት የምጀመሪያዉ ቀን ጀምሮ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም፤ ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህም ተከታዩን የኡሙሰለማ ሀዲስ መሰረት ያደረገ ነው። عن أم سلمة رضي الله عنها أن النبي صلى الله عليه وسلّم قال : " إذا رأيتم هلال ذي الحجة ، وفي لفظ : "إذا دخلت العشر وأراد أحدكم أن يضحي فليمسك عن شعره وأظفاره ". رواه أحمد ومسلم ، وفي لفظ : " فلا يأخذ من شعره وأظفاره شيئاً حتى يضحي ". وفي لفظ : "فلا يمس من شعره ولا بشره شيئاً ". ከኡሙ ሰለማ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «የዙልሂጃ ወርን ጨረቃ ካያችሁና ከናንተ መካከል አንዱ ኡድሂያ ለማረድን ካቀደ፤ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል። በሌላም ዘገባም «ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩና ከጥፍሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል። እንደዚሁ፤ «ከሰውነቱ ቆዳ ወይም ከፀጉሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል። ይህ ማንኛውም ሙስሊም እራሱን በሀጅ ላይ ካሉ ሰዎች ጋር የሚያመሳስልበት እና የተወሰኑ የኢህራም ክልከላዎችን ከነሱ ጋር የሚጋራበት ዲናዊ ስርአትና ነብያዊ ትዕዛዝ ነው። ☞ ጸጉርንና ጥፍርን ከመቁረጥ የሚከለከለው ለራሱ ወይም ለሰው በራሱ ገንዘብ የሚያርድ ሰው ብቻ ነው። ህጉ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው ሲባል፤ በወኪልነት ለሌላ ስው የሚያርድን ሰው አይጨምርም። ☞ እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም ማካካሻ ከፋራም የለበትም። አንዳንዶች እንደሚያስቡት ሳይሆን ወንጀሉን ቢፈፅምም ኡድሂያ ማረዱን መተው የለበትም። ☞ በስህተት ወይም በመርሳት ፀጉሩን ወይም ጥፍሩን የቆረጠ ሰው ምንም ወንጀል የለበትም። በተመሳሳይ መልኩ በጣም አስፈላጊ ሲሆን ቢቆርጥ ችግር የለውም። ለምሳሌ የተጎዳን የሰውነት ቆዳ ለማከም ወይም የተሰበረ ጥፍሩን ለማስተካከል መቁረጥ ይፈቀድለታል። ፠ ስለ ኡድሂያ ጥቂት ተጨማሪ ነጥቦች 1 - በዙልሂጃ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደ አላህ መቃረብ አንዱ ነው። 2- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱናዎች መካከል ነው። ኡድሂያ የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረግ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው። 3- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ ተቅዋና ታዛዥነት ግልጽ ማድረጋችንን ብቻ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፤ {ﻟَﻦ ﻳَﻨَﺎﻝَ اﻟﻠَّﻪَ ﻟُﺤُﻮﻣُﻬَﺎ ﻭَﻻَ ﺩِﻣَﺎﺅُﻫَﺎ ﻭَﻟَٰﻜِﻦ ﻳَﻨَﺎﻟُﻪُ اﻟﺘَّﻘْﻮَﻯٰ ﻣِﻨﻜُﻢْ ۚ ﻛَﺬَٰﻟِﻚَ ﺳَﺨَّﺮَﻫَﺎ ﻟَﻜُﻢْ ﻟِﺘُﻜَﺒِّﺮُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﻫَﺪَاﻛُﻢْ ۗ ﻭَﺑَﺸِّﺮِ اﻟْﻤُﺤْﺴِﻨِﻴﻦَ} الحج 37 አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት፡፡ በጎ ሠሪዎችንም አብስር፡፡» አል ሐጅ 37 4- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል። 5- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል። 6- ወንድም ይሁን ሴት ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል ለኡድሂያ ይታረዱሉ። 7- የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ ወይም የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም። 8- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋራትም ይቻላል። 9- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል። 10- የኡድሂያውን ስጋ፣ ለቤት፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ ሶስት ቦታ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም። አቡጁነይድ Http://www.t.me/abujunaidposts
إظهار الكل...
🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts

ይህ በአቡ ጁነይድ ሳላህ አህመድ የቀረቡ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክቶች የሚሰበሰቡበት ቻነል ነው። አላህ ጠቃሚ እውቀትን ከመልካም ስራ ጋር ያግራልን! You can contact me here @salehom100

👍 3🤝 1
🗞 ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ✍ ዝግጅት፦ አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ ህዳር 2004 🔗 የፅሁፉ ሊንክ https://d1.islamhouse.com/data/am/ih_articles/single/am_Virtues_of_the_Ten_Days_of_Dhul_Hijjah.pdf 🔗 telegram Share Link https://t.me/abujunaidposts/374 ---------------- 📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች @abujunaidposts
إظهار الكل...
10ቱ የዙልሒጃ ቀናት.pdf3.33 KB
👍 4👌 4
إظهار الكل...
مسألة العذر بالجهل تأصيلاً وتقعيداً || الشيخ وليد السعيدان - حفظه الله

Photo unavailableShow in Telegram
ውድ የኢስላም ወንድሞቼ፤ እንኳን ለዒድ አልፊጥር አደረሳችሁ። አላህ ስራችንን እንዲቀበለንና ለቀጣዩ ረመዳን ዕውቀትና ተግባርን ወፍቆ እንዲያደርሰን እለምነዋለሁ። ወንድማችሁ አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال وأعاده الله علينا ونحن في عز وكرامة وسعادة أخوكم في الله أبو جنيد صالح أحمد T.me/abujunaidposts
إظهار الكل...
👍 13
🌟ይህ ነው ዳዕዋችን 🌟አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ 🔗 Share Link https://t.me/abujunaidposts/551 ---------------- 📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች @abujunaidposts
إظهار الكل...
ይህ ነው ዳዕዋችን.mp318.24 MB
👍 4
🌟ይህ ነው ዳዕዋችን 🌟አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ 🔗 Share Link https://t.me/abujunaidposts/550 ---------------- 📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች @abujunaidposts
إظهار الكل...
ይህ ነው ዳዕዋችን.mp318.24 MB
👍 2
*ረመዳን ሙባረክ!* እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር አደረሳችሁ። አላህ ተቀባይነት ያለው ፆም እና ኢባዳን ይወፍቀን። ለረመዳን ያልደረሱ ወዳጆቻችንን ሁሉ አላህ ይማራቸው። አሚን t.me/abujunaidposts
إظهار الكل...
🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts

ይህ በአቡ ጁነይድ ሳላህ አህመድ የቀረቡ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክቶች የሚሰበሰቡበት ቻነል ነው። አላህ ጠቃሚ እውቀትን ከመልካም ስራ ጋር ያግራልን! You can contact me here @salehom100

👍 8👌 1
Photo unavailableShow in Telegram
💥 ታላቅ የምስራች! ◻️ አልሐምዱሊላህ... የነሲሓ ቲቪን የቀጥታ ስርጭት ከዛሬ እሁድ መጋቢት 1/2016 ጀምሮ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ሆናችሁ ከዌብሳይታቸን https://live.nesiha.tv መከታተል ትችላላችሁ። ለአጠቃቀም ይበልጥ ምቹ እንዲሆን የሞባይል አፕሊኬሽኑን ከስርጭት ፔጁ ላይ ወይም ከቴሌግራም ቻናላችን ማውረድ ትችላላችሁ።  በአላህ ፈቃድ የተጠቃሚዎችን አስተያየት መሰረት በማድረግ ማሻሻያዎች ከተደረጉለት በኃላ በአፕሊኬሽን ስቶሮች ላይ የምታገኙት ይሆናል። ብዙ ወዳጆቻችን ሲጠይቁት የነበረና የጣቢያውን ተደራሽነት በእጅጉ የሚጨምር ስኬት ስለሆነ የተሰማንን ደስታ እየገለፅን ። ለነሲሓ የ አይ ቲ ባለሞያዎች ከፍ ያለ ምስጋናቸነንን እናቀርባለን። ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ ዕውቀት ለሁሉም! @nesihatv
إظهار الكل...
👍 6👌 1
Photo unavailableShow in Telegram
ነሲሓ ኮንፈረንስ የሚታደሙበትን የመግቢያ ትኬት online በመመዝገብ በነፃ ይውሰዱ ታላላቅ ኡለማዎች የሚሳተፉበት ልዩ የነሲሓ ኮንፈረንስ በአላህ ፈቃድ በሚሊኒየም አዳራሽ መጋቢት 1/2016 ይካሄዳል። በተከታዩ ሊንክ ከዌብሳይታቸን በስምዎ ነፃ የመግቢያ ቲኬት ማግኘት ይችላሉ። https://conference.nesiha.tv ለፕሮግራሙ ድጎማ በማድረግ አጋራችን ለመሆን Cbe 444 የሂሳብ ቁጥራችንን ይጠቀሙ። እናመሰግናለን ____ 🕌 ibnu Masoud islamic Center @merkezuna
إظهار الكل...
👍 9