cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሀላል✌ⓉⓊⒷⒺ☪

🌹ይህን ቻናል አላማው ሱናን የበላይ ለማድረግን ተውሂድን ለማንገሥና የአህባሾችን የሡፍዮችን የኢኽዋን የተብሊግ ባጠቃላይ በቢድአና በሽርክ የተዘፈቁ ቡድኖችን ለማፈራረሥና መሠረታቸውን ለማጥፋት ነው ኢንሻ አላህ☝☝ @WaEish @WaEish ሀላል✌' @WaEish @WaEish

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
179
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...

00:44
Video unavailableShow in Telegram
9.21 MB
00:59
Video unavailableShow in Telegram
12.20 MB
𝚊𝚕𝚕𝚊𝚑 𝚔𝚊𝚕 𝚣𝚊𝚛 𝚜𝚞𝚗, 24 𝚊𝚙𝚛𝚒𝚕 𝚔𝚊 𝚣𝚑𝚞𝚛𝚎 𝚋𝚞𝚑𝚊𝚕𝚊 𝚔𝚊𝚛𝚊𝚗𝚎𝚢𝚘 𝚢𝚎𝚜𝚑𝚒 𝚍𝚎𝚋𝚎𝚕𝚎 𝚋𝚎𝚖𝚎𝚗𝚘𝚍𝚎𝚠𝚗𝚊 𝚋𝚎𝚖𝚊𝚔𝚛𝚋𝚛𝚎𝚠 𝚘𝚜𝚝𝚊𝚣 ❤𝚜𝚊𝚍𝚊𝚝 𝚔𝚎𝚖𝚊𝚕 𝚊𝚋𝚞 𝚖𝚎𝚛𝚎𝚢𝚎𝚖 𝚑𝚊𝚏𝚎𝚣𝚎𝚑𝚞𝚖𝚞𝚕𝚊𝚑❤ 𝚍𝚎𝚛𝚜𝚎 𝚢𝚎𝚗𝚘𝚛𝚎𝚗𝚊𝚕 𝚎𝚗𝚜𝚑𝚊 𝚊𝚕𝚕𝚊𝚑𝚒
إظهار الكل...
🅐🅢🅔🅛🅐🅜 𝙖𝙡𝙞𝙮𝙠𝙪𝙢 𝙬𝙚𝙧𝙖𝙝𝙢𝙚𝙩𝙪𝙡𝙖𝙝 𝚢𝚊𝚓𝚎𝚖𝚊
إظهار الكل...
{አድርሱልኝ} #ዑስታዝ_ሳዳት_ከማል!! <{=============}> የጥመት ሰው ይጥላህ ይስደብህ ምቀኛ፡ ባልዋልክበት ይቅጠፍ ስም ያጥፋ ሴረኛ፡ ለአህባሽ ለሱፍያ በሽታ ነህ ጭራቅ፡ ለኛ ግን ጀግና ነህ የሱና ነፀብራቅ፡ ቢዲዐን ለሚታከክ ሽርክን አድበስብሶ፡ ተውሒድን ለረሳ የዲኑን ምሰሶ፡ በግማሽ ላመነ ግማሹን ቀንሶ፡ አዝጋሚ ለሆነ አፄ በጉልበቱ፡ ሱናን ለመቀበል ላልታደለ ገልቱ፡ ለአህባሽ ለሱፍይ ለተብሊግ ወንበዴ፡ ለሙመይዕ ጭፍራ ለኢኽዋን ነጋዴ፡ ከሰለፍ ጎዳና ሟሙቶ ለወረዴ፡ በደሊል ተውበህ አንተ ነህ ጎራዴ፡ <{==================}> ቃላትህ ቀስት ነው ጥመቶችን አፍራሽ፡ ሀቅን ለፈለገ ቶሎ ፈጥኖ ደራሽ፡ ችሎታህ ግሩም ነው ሰፊ ነው አዳራሽ፡ እንግደለው ብለው ትላንት የዛቱብህ፡ በታጋሽነትህ ዛሬ ግን ቀኑብህ፡ አሏህ አድሎሀል አስተዋይ ችሎታ፡ የአርሹ ባለቤት የአለማት ጌታ፡ በሰለፍ ጎዳና በጠራው ሰንሰለት፡ ሽርክን የነገርከን ብለህ አንድ ሁለት፡ ከአሊፍ ጀምረህ ተውሒድ ያስተማርከን፡ የጌታን ትዕዛዝ የነብዩን ሱና ሀቅን የነገርከን፡ ሽርክና ቢዲዐ ጥመት እንድመረን፡ ሰበብ ሆነኸናል አቋም እንዲኖረን፡ ጥመት ቢሰበሰብ ደጋና ቆለኛ፡ የሒዲያ ሰበብ ፈርጣችን ነህ ለኛ፡ ኢኽዋን ብትዝትብህ ሱፍይ የወለዳት፡ አህባሽ ብትፎክርም የአይሁዶች ማዳት፡ ሙመይዕ በድብቅ ብዙ ብታስብም፡ የውሸት ጥርቅም እውነትን አይስብም፡ <{=====================}> አሏህ በችሎታው ሰጥቶህ ጥንካሬ፡ ኢኽዋንን በደሊል ሰብረህ አከርካሬ፡ ጆሮ ዳባ ብለህ የአሉባልታን ወሬ፡ አቋምህ አንድ ነው ድሮም ሆነ ዛሬ፡ የሰለፍ ተከታይ ጀግና ነህ እውነትም፡ ንፁህ ነው መንሀጂህ፤ በቁርዐን ደሊል እንከን የለበትም፡ የማይቀያየር፤ በገጠር ከተማ የትም ቢሆን የትም፡ የጥመት ቡድኖች ቢያሰሙም ስሞታ፡ በሀቅ ተራመድ በመረጃ ፍረድ ተጓዝ በቀጥታ፡ አሏህ ይጠብቅህ የአርሹ ባለቤት የአለማት ጌታ፡ አብሽር ቀጥልበት አሏህ አይተውህም፡ ወሏህ ባሪያው ነህ ለክፉ አይሰጥህም፡ ደካሞች ነንና ምንም ባንፈይድም፡ ሁሌ አርገዘንሀል መጥፎህን አንወድም፡ በመንሀጀ ሰለፍ ከጎንህ ነን አለን፡ በመልካም ዱዐችን እናስብሀለን፡ የተውሒድ ጀግና ነህ ሁሌ እንወድሀለን፡ <{===========//=========}> የቢዲዐን ኮተት፤ የወንጀልን ክብደት የሽርክን ተራራ፡ በተውሒድ ተውበህ፤ ሱናውን ደርበህ ሀቅን ስታብራራ፡ ከልብህ አስበህ፤ ጀግንነት ደርበህ ሰውን ስትጣራ፡ የአሏህ ፍርዱ ሲቀርብ፤ አህባሽና ኢኽዋን እንደ ጉም ሲበተን፡ ሰለፍይ ጀግና፤ የወጣት ናሙና አሏህ ሰጠን አንተን፡ #ሳዳት__ሆይ!! የሰው የጂኑ፤ የአለም ፈጣሪ እውቀት ይጨምርህ፡ ሐቅን እንደጨበጥክ፤ ደዕዋን እንደቀጠልክ አቦ አሏህ ያኑርህ፡ ለጥመት ቡድኖች፤ እንኳን ንግግርህ ስምህ ልብ ያደማል፡ የተውሒድ አንበሳ፡ ወሏሒ ጀግና ነህ ዑስታዝ ሳዳት ከማል፡ <{=====================}>
إظهار الكل...
👑አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ 🌹 ያ ጀመአ👑
إظهار الكل...
ሰሞኑን ሸይኽ ሷሊሕ ብኑ ሰዕድ አሱሃይሚ እና ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዑመር ባዝሙል የመዲናና የመካ ክፍለ ሃገራት ሙፍቲዎች ተደርገው በመመደባቸው ደስታቸውን የሚገልፁ ዓሊሞችን እያየን ነው። ከነዚህ ዑለማዎች ውስጥ አንዱ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ናቸው። በዚህ በዑለማዎች መካከል ሳይቀር መናቆር በበዛበት ዘመን እንዲህ ለሌሎች መልካም ምስክርነት መስጠት አርአያ የሚሆን ስራ ነውና እዚህ ላይ ላመጣው ወድጃለሁ። بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله رب العالمين، الرحمن الرحيم، مالك يوم الدين، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له ، وأشهد أن محمدًا عبده ورسوله أما بعد በንጉሳዊት፣ ዐረባዊት ሰዑዲያ ጠቅላይ ሙፍቲ የሆኑ ገራገሩ ዐብዱልዐዚዝ ኣሊ ሸይኽ - አላህ ይጠብቃቸውና - በሁለቱ የተከበሩ ሐረሞች ላይ ሁለቱን የተከበሩ ሸይኾች፣ ከተውሒድና ሱና ተጣሪዎች ውስጥ የሆኑትን ሰለፊ ዓሊሞች በፈትዋ ሃላፊነት ላይ መድብዋቸዋል። - አንድኛው፦ የተከበሩ ሸይኽ ሷሊሕ ብኑ ሰዕድ አሱሐይሚ - አላህ ይጠብቃቸውና - በመዲነተ ነበዊያ ላይ ሲሆን - ሌላኛው ደግሞ፦ የተከበሩ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዑመር ባዝሙልን - አላህ ይጠብቃቸውና - በመከተል ሙከረማህ ላይ ነው። ገራገሩ ሙፍቲ - አላህ ይጠብቃቸውና - ምንኛ ያማረ ስራ ነው የሰሩት! ምንኛ ያማረ ምርጫ ነው!! ሁለቱም ምንኛ ያማሩ ተመራጮች ናቸው!! በዚህ ትልቅ ሃላፊነት ላይ ሁለቱንም የላቀው አላህ እንዲያግዛቸው፣ እንዲሁም መቃናትንና ሐቅን እንዲገጥማቸው እንለምነዋለን። والحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على نبيه محمد وآله وصحبه أجمعين. አቡ ዐብዲላህ / ሙሐመድ ብኑ ዐሊይ ብኒ ሒዛም አልፈድሊ አልበዕዳኒ - አላህ ይቅር ይበለው። 15 ጅማደል ኣኺራ / 1443 = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

. ቤ/ክ አደባባዩን አሥተዳድራ ታውቃለችን? . 📌 ቤ/ክ የአደባባዩ ባለቤት እንደሆነች የሚጠቅሱ ሰዎች ቤ/ክ ከ1966 ወዲህ ቦታውን በየትኛውም ወቅት ስለማሥተዳደሯ ማምጣት የሚችሉት መረጃ የለም። አደባባዩ ለ48 ዓመታት ያክል በአ/አ መሥተዳድር ሥር ሲተዳደር ቆይቷል። . 📌 ከማሥተዳደርም ባለፈ ላለፉት 48 ዓመታት ለአደባባዩ እንክብካቤ ወጪ የተደረገው ገንዘብ የወጣው ኦርቶዶክሱም፣ ሙስሊሙም፣ ፕሮቴስታንቱም ግብር ከሚከፍልበት የመሥተዳድሩ ካዝና እንጂ ከቤ/ክ ካዝና አይደለም። ዱሮም ሆነ አሁን ከፓርክ የሚገኘው ገቢ እየገባ ያለው ወደመንግሥት ካዝና ነው። . 📌 ባለፉት 48 ዓመታት በመስቀል አደባባይ ለተካሄዱ ፕሮግራሞች የፍቃድ ደብዳቤ ሲጻፍ የነበረው ለአ/አ መሥተዳድር እንጂ ለቤ/ክ ሆኖ አያውቅም። ይህ አሁንም ድረስ አልተቀየረም። . አንዲት የሃይማኖት ተቋም ለግማሽ ምዕተ ዓመት ወጪ አውጥታበትም ሆነ ገቢ አግኝታበት የማታውቀውን፣ ቢያንስ ለ48 ዓመታት አንድ ቀንም አሥተዳድራው የማታውቀውን የሕዝብ አደባባይ "የእኔ ብቻ መጠቀሚያ ነው" ልትል የምትችልበት ምንም ዓይነት ሕጋዊም ሞራላዊም አሠራር የለም። . እንዳይረዝም ቀሪ ነጥቦች በተከታታይ ይቀጥላሉ! እርስዎ ሼር በማድረግ ለሃይማኖት እኩልነት የበኩልዎን ይወጡ! . #አብዮትአደባባይ #መስቀልአደባባይ #የሃይማኖትእኩልነት #የሃይማኖትነፃነት #እኩልነት #ኢትዮጵያ #ማኅበረቅዱሳን @WaEish @WaEish @WaEish @WaEish @WaEish @WaEish
إظهار الكل...
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ 1)ኢብኑ ተይሚያህ የሱናው አንበሳ ✍በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር 2)አላህን ማወቅ ✍በሳዳት ከማል 3)ተውሒድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ✍በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር 4)ተውሂድ እና ሽርክ ✍በሳዳት ከማል 5)መንዙማ ✍በሳዳት ከማል 6)የኡሱሉ ሰላሳ እና የቀዋዒዱል አርባዓ ትርጉም ✍በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር 7)አርበዒን ሀዲስ ✍በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር እነዚህን መፅሀፎች ከፊሎቹ ውስን ቢሆኑም በጥያቄችሁ መሰረት ከሀገር ውጭ እና ከሀገር ውስጥ ያላችሁ ወንድም እና እህቶች ማገኘት እንድትችሉ እያደረግን በመሆኑ ወደ ቴሌግራም አድራሻችን በመቀላቀል በተጠቀሱት አድራሻዎች አማካኝነት ማገኘት የምትችሉ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን። https://t.me/Okazcom
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.