cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🏘Alenbeza charity family❤️

#ሩህሩህ_ልብ ያላቸው ሰዎች #ብዙ_ገንዘብ ካላቸው ሰዎች በእጅጉ ይበልጣሉ #For_more_contact +251954724868 #For_support CBE:1000353714884 Birhan bank:1601660042923

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
Advertising posts
195المشتركون
لا توجد بيانات24 hour
لا توجد بيانات7 يوم
لا توجد بيانات30 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

📔🔟የማንበብ ጥቅሞች፦📚 1⃣መጽሐፍት የበለጠ ጠቢብ ያደርጋል ። 2⃣አንባቢዎች ከፍተኛ የውስጥ ሰላም አላቸው ። 3⃣መጽሐፍት ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳሉ። 4⃣ መጻሕፍትን ማንበብ የንባብ ቅልጥፍናን ይገነባል። 5⃣ማንበብ አጠቃላይ እውቀትዎን ያሳድጋል እርስዎ የተሻለ የውይይት ባለሙያ ያደርጎታል ። 6⃣ማንበብ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባርን ይጠብቃል ። 7⃣ማንበብ የአልዛይመር በሽታን ይከላከላል። 8⃣ማንበብ የበለጠ ሳቢ ያደርግልዎታል። 9⃣ማንበብ ውስጣዊ ሃይሎን ያነቃቃል ። 🔟 📈ትኩረትዎን እንዲያሻሽሉ ይረዳዎታል ። 📒📕📗 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ። 📔📓 👩‍🏫ያላየነውን አለም ፣ ህይወት ያሳየናል 👨‍🏫። #donate_1book #Share #Join 📚@allenbezacharity📚
إظهار الكل...
ስማኝ ልጄ!!!!!!! 1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!! 2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!! 3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!! 4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!! 5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!! 6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!! 7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!! 8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!! 9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!! 10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!! 11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!! 12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!! 13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!! 14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!! 15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!! 16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!
إظهار الكل...
#Share #share
إظهار الكل...
አለንቤዛ በጎ አድራጎት ማህበር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በአል እንዲሆንላችሁ ይመኛል መልካም አውደአመት wishes all chriatianity followers a happy easter celebration happy holiday @allenbezacharity
إظهار الكل...
☎️📞መጸሐፍ ለማበርከት እነዚህን ስልኮች ብቻ ይጠቀሙ 👉0934774973/መስ 👉0923999383/ረዲ 👉0964158596/ሙሌ 👉0979913944/ዮኒ ☎️📞ሀዋሳ ለምትኖሩ 👉0954724868/ካሌብ 👉0930520535/ማሩሻ እናመሠግናለን!!
إظهار الكل...
ሰላም ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ መጽሐፍ አሰባሰቡ አሁንም እንደቀጠለ ነው። እየሰጣችሁ ላላችሁ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን እኛ ለምንከፍተው መጽሐፍት መደብር ብዙ መጽሐፍት ያስፈልገናል ይህ ማለት የናንተ አብሮነት በእጅጉ ያስፈልገናል። የምትችሉ ከአንድ መጽሐፍ ጀምሮ በመግዛትና በማዋጣት ካልሆነም ደግሞ በእጆ የሚገኘውን መጽሐፍ በማበርከት በዚህ ታልቅ ስራ ላይ አሻራዎን እንዲያሳርፉ እንጋብዛለን። አሁኑኑ ይደውሉልን ያሉበት ድረስ መተን እንቀበሎታለን። ይህ የኔ ያንተ ያንቺ የኛ የሁላችንም ጉዳይ ነው። ስለቀና ትብብራችሁ እናመሠግናለን።
إظهار الكل...
🗣መጽሐፍ ማሰባሰቡ እንደቀጠለ ነዉ🔊🔊 ውድ ቤተሰቦች መጽሐፍ ማሰባሰቡ እንደቀጠለ ነዉ በዲላና በሀዋሳ ብዙዎች እየተሳተፉ ነው #ቢኒና_ጓደኞቹን(ከሀዋሳ) እጅግ አድርገን እናመሠግናለን በዲላም እየተሳተፋችሁ ላላችሁ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።🙏🙏🙏 🔊🔊 አንድ መጽሐፍ ለኛ ትልቅ ዋጋ አላትና አዲስም አሮጌም መጽሐፍ በማበርከት እንዲሁም ሌሎችን በማስተባበር አብረውን ይቁሙ 📚📚💚💛❤️ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ያስተውሉ "የምንፈልገውን ለውጥ እኛው ነን ማምጣት የምንችለው"ዛሬ አንባቢ ወጣቶችን እያበረታታን ምክንያታዊና የሚጠቅሙ ባለራዕይዎችን እናፈራለን። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ አብረውን ስለቆሙ እናመሠግናለን!!🙏🙏 @allenbezacharitygroup @allenbezacharitygroup #Alenbeza_Charity Dilla/Ethiopia🇪🇹
إظهار الكل...
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ!! መልካም ፈተና ይሁንላችሁ ያነበባችሁትን ማስታወስ እንድትችሉ ፈጣሪ ይርዳቹ
إظهار الكل...
ስጦታችሁን እየሠጣችሁን ስላላችሁ እያመሠገንን አሁን ደግሞ ይህንን pic share and profile በማድረግ ለሁሉም እንዲደርስ እናድርግ። አብራችሁን ስለቆማቹ እናመሠግናለን!! graphics_design_#miki_design @Miki_Design እናመሠግናለን!! join @allenbezacharitygroup @allenbezacharitygroup
إظهار الكل...