ar
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

الذهاب إلى القناة على Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

إظهار المزيد
4 374
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
••• እርሱም ያንን ሠሌዳ የእመቤታችንን ሥዕል አሳምሮ ይስልበት ዘንድ ለሰዓሊ ወስዶ ሰጠው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን በራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጠችለትና ከአመፀኛ ሰው የተገኘ ነውና በዚያ ሰው ሠሌዳ ሥዕሏን እንዳያስል ከለከለችው፡፡ ሥዕሏ የተሳለበትን ሠሌዳም የት እንደሚገኝ ነገረችውና ሄዶ በታላቅ ክብር አምጥቶ በቤተ ክርስቲያኑ አስቀመጠው፡፡ ከሥዕሉም ሥር ድውያንን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት መፍሰስ ጀመረ፡፡ በዚህም ብዙዎች ድንቅ የሆነ ፈውስን አገኙ፡፡ ይህም የተፈጸመው ሰኔ 21 ቀን ነው፡፡   + ሌላም እንዲሁ ቅዱስ ባስልዮስ ያደረገው ተአምር የሰይጣንን የጽሕፈት ደብዳቤ በጸሎቱ የደመሰሰ መሆኑ ነው፡፡ አንድ ጎልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ወደ አንድ ሥራይኛ ዘንድ ሄደ፡፡ ሥራይኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠውና ወደ አረሚ መቃብር ሄዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ በመቃብሩ እንዲቆ ላይ አዘዘው፡፡ ወጣቱም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ከሰይጣናትም አንዱ መጥቶ ወደ ወደ አለቃቸው አደረሰው፡፡ ያችንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰዳት፡፡ ሰይጣንም "የፈለከውን አደርግልሃለሁ ነገር ግን አምላክህን ክርስቶስን ትክደዋለህ ፈቃድህን ከፈጸምኩልህ በኋላም ወደ እርሱ አትምለስም" ሲለው ወጣቱም በልጅቷ ፍቅር አብዶ ነበርና "አዎን ጌታዬ ያዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለው፡፡ ሰይጣኑም "ይህን ልታደርግ በእጅህ ጻፍልኝ" አለውና አጻፈው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰይጣን በጌታው ሴት ልጅ ልብ ውስጥ አደረና ያንን ወጣት እጅግ ወደደችው፡፡ የፍትወት እሳትንም በልቧ ላይ ስላነደደባት መታገስ አልቻለችምና ወደ አባቷ ቀርባ ልጁን አጋባኝ አለችው፡፡ የልጁም ፍቅር በየዕለቱ ይጨምርባት ነበርና ራሷን እንዳታጠፋ ቤተሰቦቿ አጋቧት፡፡ ከእርሱ ጋር መኖር ከጀመረች በኋላ ሲያማትብ እንኳን አይታው አታውቅም ነበርና ስትመረምረው ክርስቲያን አለመሆኑንና ያደረገውንም ሁሉ ነገራት፡፡ ይህንንም ስትሰማ እጅግ ደንግጣ ወደ አገሯ ሊቀ ጳጳስ ወደ ባስልዮስ ዘንድ ሄዳ ከእግሩ ሥር በመውደቅ የደረሰባትን በመንገር ከሰይጣን እጅ እንዲያድናት ለመነችው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም በሏ የሆነውን የአባቷን ባርያ አስመጣውና በንስሓ ተመልሶ ክርስቲያን መሆን እንደሚፈልግ ጠየቀው፡፡ ወጣቱም ፈቃደኝነቱን ሲገልጥለት በአንድ ቦታ ውስጥ አስገብቶ ዘጋበትና ከላይ በመስቀል ምልክት አተመበት፡፡ እንዲጸልይም አዘዘው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ስለ ወጣቱ ብዙ ጸለየ፡፡ ከሦስት ቀንም በኋላ ጎበኘውና በ3ቱ ቀን የደሰበትን ጠየቀው፡፡ ወጣቱም በላዩ በመጮህ ሰይጣናት ሲያስፈራሩት ያንንም ደብዳቤ ሲያሳዩትና በእርሱ ላይ ሲቆጡ በመከራ ውስጥ እንደኖረ ነገረው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም "ከሰይጣናቱ ቁጣ የተነሣ አትፍራ አይዞህ እግዚአብሔር ይረዳናል" ብሎ ጥቂት ከመገበው በኋላ መልሶ ዘጋበትና ሄዶ ይጸልይለት ጀመር፡፡  + ዳግመኛም ከ3 ቀን በኋላ መጥቶ ጠየቀው፡፡ ወጣቱም "የአጋንንቱን ጩኸታቸውን እሰማዋለሁ ነገር ግን አላያቸውም" አለው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ አሁንም ጥቂት ከመገበው በኋላ መልሶ ዘጋበትና እስከ 40 ቀን ድረስ እንዲሁ አደረገ፡፡ ከ40 ቀንም በኋላ መልሶ ሲጠይቀው ወጣቱ "ቅዱስ አባቴ ሆይ ስለ እኔ ሰይጣንን ስትጣላውና ድል አድርገህ ጥለህ ስትረግጠው በዛሬዋ ሌሊት አየሁ" አለው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ይህን ሲሰማ እጅግ ደስ አለው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችንም ጠርቶ እግዚኦታ አደረሱና ከእግዚኦታው በኋላ ያ ወጣት ጽፎ ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ ተወስዶ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ፡፡ ሁሉም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ይኸውም የተደረገው መስከረም 13 ቀን ነው፡፡   + አንዲት ሴት ኃጢአቷን ሁሉ በዝርዝር ጽፋ በክርስታስ አሽጋ እንዲጸልይላት ቅዱስ ባስልዮስን ለመነችው፡፡ እርሱም ከአንዲት ኃጢአቷ በቀር ሁሉንም በጸሎቱ ደመሰሰላት፡፡ ስለ አንዲቱም ኃጢአቷ ወደ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲትሄድ አዘዛት፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም "ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሳይሞት ፈጥነሽ ተመለሽ የካህናት ሁሉ አለቃ ስለሆነ የቀረች ኃጢአትሽን የሚደመስስልሽ እርሱ ነው" ብሎ መለሳት፡፡ በተመለሰችም ጊዜ ቅዱስ ባስልዮስ ዐርፎ ሊቀብሩት ሲወስዱት አገኘችው፡፡ እርሷም መሪር ልቅሶን ካለቀሰች በኋላ በእምነት ሆና ያንን ክርስታስ ከአስክሬኑ ላይ ጣለችው፡፡ ስለ እምነቷም ጽናት ያች የቀረች በደሏ ተደመሰሰችላት፡፡ + ይህም የከበረ ቅዱስ ባስልዮስ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከጻፍነው ሌላ ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶችን አድርጓል ብዙዎችንም ተግሣጻትንና ድርሳናትንና ለመነኰሳትም ትምህርቶችን ደርሷል፡፡ ከብሉይና ከሐዲስም አምላካውያን የሆኑ ብዙ መጻሕፍቶችን ተርጒሟል ሥርዓቶችንም ሠራ እነርሱም በሁሉ ቦታ ይገኛሉ ከዚህም በኋላ ጥር6 በሰላም ዐረፈ በክብር በብዙ ምስጋና ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ባስልዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር6 ስንክሳር።                            +++ + የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወይከውን ቡሩከ ስሙ ለዓለም። እምቅድመ ፀሐይ ሀሎ ስሙ። ወይትባረኩ ቦቱ ኵሎሙ አሕዛብ ምድር። መዝ71፥17-18።  የሚነበበው ወንጌል ሉቃ2፥8-22።                                              +++ + የዕለቱ ምስባክ፦ "ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ104፥14-15። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ4፥24-33። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የኢየሱስ ክርስቶስ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

••• + ከመቶ ሃምሳ ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አስቦ ነፋስን በምድር ላይ አመጣና ውኃውን አጎደለ፡፡ ምንጮች ተደፍነው የሰማይ መስኮት ተዘጋ፡፡ መርከቢቱም በ7ኛው በ12ው ቀን አራራት ተራራ ላይ አረፈች፡፡ ከጊዜም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን ከነቤተሰቡ አንድ ላይ ከመርከቡ እንዲወርዱ አዘዘው፡፡ ኖኅም መሠዊያን ሠርቶ ንጹሕ ከሆኑት ሁሉ ወስዶ መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር መልካም መዓዛን አሸተተ፡፡ ዳግመኛም ምድርን በንፍር ውኃ እንዳያጠፋ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ምድር ፀንታ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ዘር መከር፣ ቅዝቃዜና ሙቀት፣ በጋና ክረምት፣ መዓልትና ሌሊት እንደማይቋረጥ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፡፡ ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉዋት ግዟት አላቸው፡፡ ኖኅም ምድርን ያርሳት ይቆፍራም ጀመር፡፡ ወይንም ተክሎ ከእርሶ ፍሬውን አድርሶ ወይን ጠጥቶ በሰከረና ራሱን በሳተ ጊዜ የከነዓን አባት ካም የኖኅን ራቁትነት አይቶ ሳቀ፣ ሄዶም ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ያፌትና ሴምም ልብስ ወስደው የአባታቸውን ርቃን ሸፈኑ፡፡ ኖኅም ከስካሩ በነቃ ጊዜ ሁሉም ያደረጉትን ዐወቀ፡፡ "ከነዓን የተረገመ ይሁን፣ ለወንድሞቹም ተገዥ አገልጋይ ይሁን" ብሎ ከረገመው በኋላ "የሴም ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔርም የያፌትን አገር ያስፋ፣ በሴም ቤትም ይደር ከነአንም አገልጋይ ይሁን"። + አባታችን ቅዱስ ኖኅም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሦስት መቶ ኅምሳ ዓመት ኖረ የኖኅም መላ ዕድሜው ዘጠኝ መቶ ኃምሳ ሆነ በሰላምም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን በጻድቁ ኖኅ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                         +++ + "ሰላም ለኤልያስ ነቢይ ቴስብያዊ ኮሬባዊ ታቦራዊ ሰማየ ዘለጐመ ወከልአ ዝናመ፤ ቃለ ጸሎቱ ዘተሰምዐ ውስተ ዕዝኑ ለአዶናይ ወአውረደ እሳት እምሰማይ እስከ በልዖ ለማይ፤ ዘዐደወ ብሔረ ተድላ ተጽኢኖ ዘእሳት ሠረገላ። ትርጉም፦ ቴስቢያዊ (የቴስቢያ ሰው)፤ ኮሬባዊ (ወደ ኮሬብ ተራራ የወጣ)፤ ታቦራዊ (በታቦር ተራራ የተገኘ) ፤ ዝናብ እን ዳይዘንብ ሰማይን የለጐመ ለኾነ፤ የጸሎቱ ቃልም በአዶናይ ዦሮ ውስጥ ለተሰማ፤ ውሃውን እስካበላ ደርሶ እሳትን ከሰማይ ያወረደ ለኾነ፤ በእሳት ሠረገላ ተጭኖ ወደ ተድላ ደስታ ቦታ ለገባ ለነቢዩ ለኤልያስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።                           +++ + የነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ ዕረገት፦ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ኤልያስን ወደ ሰማይ በሚወጣባት ጊዜ ኤልሳና ኤልያስ ከገልገላ ተነሥተው ሔደወሰ ወደ ዮርዳኖስ ደረሱ ኤልያስም መጠምጠሚያውን አውርዶ ጠቅሎ የዮርድያኖስ ውኃ መታበት ውኃውም ተከፍሎ ወዲያና ወዲህ ቆመ ሁለቱም ሁሉ በደረቅ ተሻገሩ ወጥተውም በምድረ በዳ ቆመ። + ኤልያስ ኤልሳን "ካንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳልወጣ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ" አለው ኤልሳዕም ኤልያስን "በአንተ ያደረ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ዕጥፍ ሁኖ ይደርብኝ" አለው። ኤልያስም ኤልሳን "ድንቅ ነገርን ለመንከኝ ነገር ግን ካንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳርግ ብታየኝ ይሁንልህ ባታየኝ ግን አይሆንልህ" አለው። በዚያንም ጊዜ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረስ መጣ ወደ መካከላቸውም ገብቶ አራራቃቸው ኤልያስም እንደዚህ በንውጽውጽታና በጥቅል ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ። ኤልሳዕም አይቶ "የእስራኤል ኃይላቸውና ጽናታቸው አባ አባ ብሎ ጮኸ ከዚህ በኋላ ዳግመኛ አላየውም ልብሶቹንም ለሁለት አድርጎ ከፈላቸው ኤልያስም ለኤልሳዕ መጠምጠሚያውን ጣለለት በኤልሳዕም ራስ ላይ ወረደ የኤልያስም ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በኤልሳዕ ላይ ዕጥፍ ሁኖ አደረ ኤልያስም የሠራውን ተአምራት ኤልሳዕ ዕጥፍ አድርጎ ሠራ። + ይህም ኤልያስ በኋላ ዘመን ከኄኖክ ጋር ይመጣ ዘንድ አለው ሐሳዊ መሢሕንም ይቃወሙታል እርሱም ይገድላቸዋል በድናቸውም በአደባባይ ተጥሎ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይቆያል ከዚህም በኋላ ይነሣሉ የሙታን ትንሣኤም ይሆናል ይህም ኤልያስ እውነተኛ ነቢይ አስቀድሞ የነበረ በኋላም የሚገለጽ ነው በብሉይ ዘመንም ኑሮው በበረሃ ውስጥ ነበር። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢይ በቅዱስ ኤልያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                          +++ + ሰላም ለጎርጎርዮስ ወለባስልዮስ ዘተናገሮሙ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤ ዘከመ ቀተሎ ለዑልያኖስ"። ትርጉም፦ ዑልያኖስን እንዴት እንደገደለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕሉ የተናገራቸው ለኾነ ለጎርጎርዮስና ለባስልዮስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።                           +++ + ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ኤስድሮስ ይባላል እርሱም ከአንጾኪያ አገር ሰዎች ንጹሕና ቅዱስ የሆነ ቄስ ነው አምስት ልጆችንም ወልዶአል እነርሱም ባስልዮስ፣ ጎርጎርዮስ፣ ጴጥሮስ፣ ኬርዮን፣ መክርዮን ናቸው ሁሉም ከፍጹማንነት የደረሱ ቅዱሳን ናቸው። + በዚህም በከበረ ባስልዮስ ላይ መንፈስ ቅዱስ መልቶበት በሁሉ ዘንድ የታወቀች ቅዳሴውን ደረሰ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊሠርቁ የመጡትን ሌቦች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ በጸሎቱ በሩን ዘግቶባቸዋል፡፡ በኋላም ምእመናን ሲመጡ በሩን ከፍቶላቸዋል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ መሆኑን ነው፡፡ የታላቁ አባት የቅዱስ ኤፍሬምም መምህሩ ነው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ያደረጋቸው ተአምራት ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ + ወንድሙ የስብስጥያ ኤጲስቆጶስ ከሚስቱ ጋር በድንግልና ሲኖር ሕዝቡ ግን ያሙት ነበርና ቅዱስ ባስልዮስ መላእክት ሲጠብቋቸው እንደተመለከተ ለሕዝቡ ገልጦላቸው ሕዝቡ ከሐሜት ርቀው ንስሓ እንዲገቡ አድርጓቸዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ በተመለከተ ጊዜ "ይህ የቂሳርያው የባስልዮስ ነው" የሚል ቃልን ሰምቷል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ወደ ቂሳርያ ሄዶ ከቅዱስ ባስልዮስ ዘንድ ዲቁናና ቅስና ተቀብሏል፡፡ ቅዱስ ባልዩስም በቅዱስ ኤፍሬም በላዩ ጸልዮለት የማያውቀውን አዲስ የዮናኒን ቋንቋን እንዲናገር አድርጎታል፡፡   + ቅዱስ ባስልዮስ ሰው ሁሉ የሚያምንበትና በአቆጣጠሩም የሚታወቀውን ጠንቋይም በተአምሩ አሳምኖታል፡፡ ይኸውም ቅዱስ ባስልዮስ በታመመ ጊዜ የሚሞትበትን ጊዜ ዐውቆ ይህን ጠንቋይ ጠርቶ "ንገረኝ እስቲ መቼ እሞታለሁ?" አለው፡፡ ጠንቋዩም "ማታ ነፍስህ ከሥጋህ ትለያለች" አለው፡፡ እርሱም "እስከ ጠዋት ካልሞትኩ ክርስቲያን ትሆናለህ?" በማለት ቃል አስገባው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ወደ ጌታችን በመጸለይ በዕድሜው ላይ ሦስት ቀናት አስጨመረ፡፡ ያም ጠንቋይ ሥራው ከንቱ እንደሆነ ታወቀበትና እርሱም አምኖ ከነቤተሰቦቹ ተጠምቆ ክርስቲያን ሆነ፡፡   + ሌላው ተአምር ለቅዱስ ባስልዮስ እመቤታችን ስለ ሥዕሏ የነገረችው ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ባስልዮስ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ከሠራ በኋላ በውስጧ የሚያኖረውን የእመቤታችንን ሥዕል ሊያሠራ መሳያ ሠሌዳ ፈለገ፡፡ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ቤት ጥሩ ሠሌዳ እንዳለ ነገሩትና ሄዶ ባለጸጋውን ሠሌዳውን እንዲሰጠው ለመነው፡፡ ባለጸጋውም የልጆቼ ነው አልሰጥም አለው፡፡ በትዕቢትም ሆኖ በታነጸቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብን ነገር ተናገረ፡፡ ወዲያውም ወድቆ ክፉ አሟሟት ሞተና ልጆቹ ፈርተው ሠሌዳውን አምጥተው ለባስልዮስ ሰጡት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።              ✞ ጥር 6 ቀን ✞ + እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ ለግዝረት (ለኢየሱስ) ዓመታዊ በዓል፣ ለአባታች ለቅዱስ ኖኅ ለዕረፍቱ መታሰቢያ፣ ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ኤልያስ በሕይወት ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ለዐረገበት (ከሞት ለተሰወረበት) በዓል፣ ለታላቋ ሰማዕት ለቅድስት አርሴማ ለልደቷ በዓልና ለከበረና ለታላቁ አባት ለቂሣርያ ኤጲስቆጶስ ለአቡነ ባስልዮስ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ ከአባ ወርክያኖስ ዕረፍትና በበረሀ ስልሳ ዘመናት ከኖረ ከአባ ሙሴ ዕረፍት እርሱም የቅዱሳንን ልቡና ከማየቱ የተነሣ አደነቀ ፊቱም ተለውጦ እንደ እሳትፍም ሆነ። ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           +++ + የዕለቱ ዓራራይ ዜማ፦ "ወአመ ስሙን ዕለት ወሰድዎ ለሕጻን ከመ ይግዝርዎ በሕገ ኦሪት ሰመይዎ ስሞ አማኑኤል በከመ ሰመዮ መልአክ እምቅድመ ትፀንስ"፡፡ ትርጉም፦ በኦሪትሕግ መሠረት ይገዝሩ ዘንድ በስምንተኛው ዕለት ሕፃኑን ወሰዱ ስሙን አማኑኤል ብለው አወጡለት (ሰየሙት) ከመፀነሷ አስቀድሞ መልአክ እንደሰየመው (እንደተናገረው)።                          +++ +የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ፦ "ተወልደ እምድንግል ሰከበ ውስተጐል እሙነ ኮነ ልደቱ ለክብረ ቅዱሳን ወለቤዛ ብዙኃን አብ ፈነዎ ለበኲሩ ውስተ ዓለም"። ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።                           +++ + በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ ልሳነ ዕረፍት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ" ብሎ እንደተናገረ። ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር እነርሱ እንዳሰቡት ሁኖ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር ጌታችን ግን ግዝረትን ሕግ ፈጸመ ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ በላ በእርሱም ፈንታ ሥጋውንና ደሙን ሰጠን። + የከበረ ወንጌል "ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለት ስሙን ኢየሱስ አሉት" እንዳለ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን "እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የሆነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ" አለችው። ዮሴፍም ሔዶ የሚገርዝ ባለሙያ አመጣ ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው "እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቆ ያዙት" አላቸው። ሕፃን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መልሶ እንዲህ አለው "ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዚያች ዕለት ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኃና ደም ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆች መድኃኒት ይሆናል"። + የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችን ማርያም "ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው" አላት። + ሕፃኑም ለዚያ ባለሙያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው "እኔ ነኝ ትገዝረኛለህ ወይስ ተውክ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ" ያም ባለሙያ "የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?" አለው ሕፃን ጌታችንም "አብርሃም፣ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው" ባለሙያውም "እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና" አለው። በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ "አባት ሆይ ለአብርሃም፣ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ" አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች። + ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማሕፀን እንደ መውጣቱ የጌታችን ግዝረቱ የማይመረመር ሆነ እንዲሁ ወደ ሐዋርያት በተዘጋ አዳራሽ መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እንዲሁ እንደ ፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ። አዳምንና ልጆቹን ያድናቸው ዘንድ በፈቃዱ ከጐኑ በመስቀል ላይ የሚፈሰው ደምና ውኃ ካልሆነ በቀር ብዙም ሆነ ጥቂት ሊሆን አይችልም እርሱ በፈቃዱ ሕጉ እንዲፈጸም አስቀድሞ አዘዘ እንጂ። + ያም ባለሙያው ገራዥ ይህን ተአምር ባየ ጊዜ የሕፃኑንም ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ሦስት ጊዜ ሰገደና "በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ" አለው። ከዚህም በኋላ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተአምራቱ ያየውንና የሰማውን እየተናገረ ወደ ቦታው ሔደ ለእርሱም ለጌታችን ከቸር አባቱ ጋራ ማሕየዊ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋራ ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።                           +++ + "ሰላም ለኖኅ ዘተካየደ ምስለ እግዚአብሔር ከመ ኢይሥርዋ ለምድር በአይኅ፤ ዘረሰየ ዘርዖ ከመ ኆፃ ብዙኅ"። ትርጉም፦ ምድርን በንፍር የጥፋት ውሃ እንዳያጠፋት ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳንን የተገባባ፤ ዘሩንም እንደ አሸዋ ብዙ ያደረገለት ለኾነ ለኖኅ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።                           +++ + አባታችን ጻድቁ ኖኅ፦ እርሱም ከአባታችን አዳም ዐሥረኛ ትውልድ ነው። እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ኃጢአት እንደሚበዛ ክፋትም እንደሚመላ ደጋጎች እንደሚያንሱ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደሚመሰስ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያይ ሆነ ስለዚህም ፊቱ የተቋጠረ ሁኖ ፈጽሞ ያለቅስ ነበር። + አምስት ዓመት ድንግልናውን ጠብቆ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግል ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ሚስት እንዲያገባ እግዚአብሔር አዘዘው፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ እንደሚደመሰስ ከእርሱ ዘር በቀር የሚተርፍ እንደሌለ ነገረው፡፡ ጻድቁ ኖኅም የአቡዚር ልጅ የሆነች ሐይከል የምትባል ሴት አግብቶ ወደ እርሷ ሦስት ጊዜ ቢገባ ሦስት ልጆችን ሴም ካም ያፌትን ወለዳቸው፡፡ + ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅ ከደብር ቅዱስ ዕንጨት ቆርጦ መርከብን እንዲያሠራ ካዘዘው በኋላ አሠራሯን በዝርዝርና በጥልቀት አስረዳው፡፡ የቃየል ልጆችም ኖኅን መርከብ ሲሠራ አይተው ዘበቱበት፡፡ የአዳምንም ሥጋ ወስዶ በውስጡ አኖረ፡፡ ሴም ወርቁን፣ ካም ከርቤውን፣ ያፌት ዕጣኑን ወስደው ወደ መርከብ አስገቡ፡፡ ኖኅም ከልጆቹና ከሚስቶቻቸው ጋራ ወደ መርከቡ ገባ፡፡ ንጹሐን የሆኑት እንስሳትና አእዋፋት ሴትና ወንድ ሰባት ሰባት፣ ንጹሐን ካልሆኑት ደግሞ ሁለት ሁለት ሴትና ወንድ አስገባ፡፡ ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ የምድርም ምንጮች ሁሉ ተነድለው ራጃጅም ተራራዎችም እስኪሸፈኑ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ዘነመ፡፡ ውኃውም በላያቸው 15 ክንድ ከፍ አለና ሥጋ የለበሰ ሁሉ ሞተ፡፡

🌾✞ ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የተለያዩ ጥያቄዎችን ከእናንተው ተጠይቀው ነበር፤ እናም ጥያቄዎችና መልሶቻቸውን እነሆ ብለናል፡፡ ✞🌾 1. ከ12ቱ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ ገንዘብ ያዥ ነበር ታድያ በልቡ ስስት ነግሶ ጌታውን ሸጠ፡፡ ቃሉን አፍርሶ አባትነቱን ክዶ በእራሱ ላይ ጫነ የኃጢአት ነዶ፤ ይህ ከኃዲ ሰው ማነው? A. ማቴዎስ B. ይሁዳ C. በርተለሚዮስ D. ፊልጶስ #መልስ ✔B 2. ለመጀመርያ ግዜ እግዚአብሔር ይፍታ ያሉት አባት ማን ይባላሉ? A. አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሀን B. አባ ጳውሊ C.አባ በርናባስ D. አባ እንጦንስ #መልስ ✔B 3. ለመናብርት አለቃ ሆኖ የተሰየመው መልአክ ማን ነው? A. ቅዱስ ሚካኤል B. ቅዱስ ራጉኤል C. ቅዱስ ገብርኤል D. ቅዱስ ሩፋኤል #መልስ ✔D 4. ረጅም ዘመን በመኖር አንደኛው ሰው ማቱሳላ ነው። የኖረውም 969 ዓመት ነው። ሁለተኛው ማን ነው? A. ሄኖክ B. ሙሴ C. ያሬድ D. ዕዝራ #መልስ ✔C 5. የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉስ ሳዖል ነው። ሁለተኛው ማን ነው? (ጥቆማ፦ ዳዊት አይደለም) A. ኢያቡስቴ B. ሰሎሞን C. ናቡከደነጾር D. መልስ የለም #መልስ ✔A 6. በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ሰማዕት እስጢፋኖስ ነው። ሁለተኛው ማን ነው? A. ጴጥሮስ B. ያዕቆብ ወልደዘብዴዎስ C. ጳውሎስ D. ማርቆስ #መልስ ✔B 7. የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል ነው። ሁለተኛው ማን ነው? A. ስምዖን B. ይሁዳ C. ዮሴፍ D. ብንያም #መልስ ✔A 8. በመጽሃፍ ቅዱስ ስማቸው ከተጠቀሱት ሴቶች የመጀመሪያዋ ሔዋን ናት። ሁለተኛዋ ማን ናት? (ጥቆማ፦ የቃየል ሚስት ስም አልተጠቀሰም) A. ሳራ B. ሲፓራ C. የላሜህ ሚስት አዳ D. ቤርሳቤሕ #መልስ ✔C 9. የቤተክርስቲያናችን ሊቅ የዜማው ደራሲ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያ ዜማው ምን በመባል ይጠራል? A. በግዕዝ B. እዝል C. አራራይ D. ሁሉም መልስ ናቸው #መልስ ✔C 10. በመፅሐፍ ቅደስ የተጠቀሰው የመጀመሪያው መልዓክ ማነው? A. ኪሩቤል B. ሚካኤል C. ገብርኤል D. መልሱ አልተሰጠም #መልስ ✔A 11. ከመፅሐፍ ቅዱስ ከተጠቀሱት ሴት ነብያቶችን መካከል ያልሆነችው ማን ናት? A. የሙሴ እህት ማርያም B. ዲቦራ C. ኤልሳቤጥ D. ሐና #መልስ ✔C 12. ከአምስቱ እኅት ቤተክርስቲያናት የማትመደበው የማን ቤተክርስቲያን ናት? A. የግሪክ B. የአርመን C. የሶርያ D. የህንድ #መልስ ✔A 13. ከግቢ ጉባኤ ክፍላት የማይመደበው የቱ ነው? A. ሙያ እና ተራድዖ B. ኦዲት እና ኢንስፔክሽን C. መዝሙር እና ኪነጥበብ D. መረጃና መዛግብት #መልስ ✔D 14. ከአራቱ ወንጌላውያን መካከል ወንጌላዊው ዮሐንስ በንስር ይመሰላል ወንጌላዊው ማርቆስ በምን ይመሰላል? A. በላም B. በአንበሳ C. በሰው D. መልስ የለም #መልስ ✔B 15. ማህሌተ ጽጌን የደረሰው አባት ስሙ ማን ይባላል? A. ቅዱስ ኤጲፋንዮስ B. ቅዱስ ያሬድ C. አባ ጽጌ ድንግል D. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #መልስ ✔C 16. ከሚከተሉት አንዱ ከተስዓቱ ቅዱሳን አይመደቡም? A. አባ ኢየሱስ ሞአ B. አባ አፍጼ C. አባ ጽሕማ D. አባ ይምአታ #መልስ ✔A 17. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ከ አምስቱ አዕማደ ምስጢራት መካከል አይመደብም? A. ምስጢረ ሥላሴ B. ምስጢረ ቁርባን C. ምስጢረ ሜሮን D. ምስጢረ ስጋዌ #መልስ ✔C 18. አብርሃም ማለት ምን ማለት ነው? A. እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው B. ክብር ከእስራኤል ለቀቀ C. ከባህር የተገኘ D. የብዙሃን አባት #መልስ ✔D 19. አምስቱን አዕማደ ምሥጢር የያዘ ፀሎት የቱ ነው? A. ሰሊም ለኪ B. መልክዓ ማርያም C. ጸሎተ ሃይማኖት D. ስብሐት ለአብ #መልስ ✔C 20. ከሚከተሉት አንዱ በስርዓተ ቅዳሴ ጊዜ ከሚነበቡ ቅዱሳን መፃህፍት ውስጥ አይመደብም? A. የጳውሎስ መልዕክታት B. የሐዋርያት ስራ C. የዮሐንስ ራዕይ D. 4ቱ ወንጌላት #መልስ ✔መልስ የለም ሁሉም ይነበባሉ። 🙏 ለተሳተፋችሁ በሙሉ ቃለ ሕይወት ያሰማለን ተስፋ መንግስተ ሠማያትን ያውርስልን ፍጻሜአችሁን ያሳምርልን፡፡ አሜን፡፡ 🙏

☞✞ አንድ ንጉሥ መዝሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታዘዘውን ሃያ እና ሰላሳ መዝሙር ማድረስ ባንችል እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ ይገባናል። አንድ ንጉሥ የሚባለው፦ ✔አስር መዝሙር ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ከሰኞ አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ1–10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ30–40 ያውን የመጀመሪያውን አስር መዝሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡ ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው ግን የተወሰኑ መዝሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡ ፪. #ውዳሴ_ማርያም ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው። የዘወትር ጸሎት ካደረስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን ደግመን ከእመቤታችን በረከት ተሳታፊ መሆን ተገቢ ነው፡፡ ✔በዋልድባ የሚኖሩ መነኮሳት ውዳሴ ማርያም ከቅዳሴ ማርያም ሳያደርሱ ውለው አያድሩም፡፡ ✔በየአብነት ትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎችእና በየገዳማት ያሉ መነኮሳት ሁሉ ውዳሴ ማርያምን በየዕለቱ ያደርሳሉ፡፡ ✔እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡ ፫. #ወንጌል_ዘዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው ጸሎት ነው፡፡ ✔አባቶች ይህንንጸሎት በየእለቱ እያደረሱ ብዙ ተጠቅመውበታል። ፬. #ሌሎች_ጸሎታት ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም፣ በመዝገበ ጸሎት እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣ እንዲሁም ገድላት፣ ተአምራትን፣ እንደ ችሎታችን በየዕለቱ እናደርሳለን፡፡ ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን የመዝሙረ ዳዊትና ውዳሴ ማርያምን ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡✔አጭር ጸሎት በተቻኮልን እና መጻሕፍትን ለማንበብ ጨርሶውን ጊዜ በማይኖረን ሰዓት ይህንን እንድንጸልይ አንዳንድ አባቶች ይመክሩናል። አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ ሃይማኖት፣ ሰላም ለኪ /ስለውዳሴ ማርያም ፈንታ/፣ አቡነ ዘበሰማያት፣ አንድ ከመዝሙረ ዳዊት(መዝሙር 150) /በመዝሙረ ዳዊት ፈንታ/ በመጨረሻም አቡነ ዘበሰማያት ማድረስ ብንችል መልካም ነው። ✔ጸሎተ ሃይማኖት የህይማንት መግለጫ በምሆኑ እንጸልየዋለን። በመካከል ሰላም ለኪ በመድገማችንም የውዳሴ ማርያም በረከት ይደርሰናል። መዝሙረ ዳዊት 150 ስናደርስ ደግሞ ሁሉንም መዝሙራት የደገምን ያህል ይሆንልንና የዳዊቱን በረከት እናገኛለን፡፡ ይህንን ሁሉ ማድረስ ካልተቻለን ግን ቢያንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ከቤታችን ልንወጣ ይገባናል። ✔አጭር ጸሎት ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል፡፡ ዘጠኝ ሰላም ለኪ፣ አስራ ሁለት አቡነ ዘበሰማያት በገዳማት ያሉ አበው ያደርሳሉ። ✔አጭር ጸሎትን እነደ መደበኛ ማድረግ ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ✔አጭር ጸሎት የምንጸልየው በጣም በተቸገርንበት፣ ጊዜ ባጣንበት ሰዓት ነው። ይህንን ጸሎት እንደመደበኛ ይዞ በየእለቱ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብቻ መድገም ግን ስንፍና እንዳይሆን ያስፈራል። ይልቁንም በክርስትና ሕይወት ጅማሬ ላይ ያሉ ምእመናን/ወጣንያን/ክርስትናውን እስኪላመዱ ጸሎታቸው አጭር ሊሆን ይችላል። እየቆዩ ሲሄዱ ግን በጸሎት እየበረቱ ወደ መደበኛው ጸሎት መድረስ አለባቸው። ሁልጊዜ ወተት መመኘት ሁልጊዜ አልበረታውም እያሉ አጭር ጸሎት እያደረሱ መተኛት ተገቢ አይደለም። ይህ አይነቱ አካሄድ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለስንፍና ምክንያት አድርጎ መጠቀምም ነው። ✔ከዚህ ጋር በቤተክርስቲያን አገልገሎት ላይ ያለንም ዳዊት መድገም ውዳሴ ማርያም ማድረስ ይጠበቅብናል። የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ መዘምራን ወዘተ እነዚህን ጸሎታት መጸለይ ይጠበቅባቸዋል። አልያ ግን እያወቅን ጸሎት ማድረስ እንዳለብን ብዙ ጊዜ ተምረን እንዳልተምርን ቸል ብንል ለፈተና መጋለጥ ይመጣል። ከእግዚአብሔርም ቸርነት እንድንርቅ ያደርገናል። ✔አቡነ ዘበሰማያት የጸሎታችን መነሻና መድረሻ ጸሎት ስናደርስ የጸሎታችን መነሻ (መጀመሪያ) አቡነ ዘበሰማያት ነው፡፡ ✔በመካከል ጸሎት አቋርጠን ከሰው የምንነጋገርበት ጉዳይ ቢገጥመን በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር ተገቢ ነው፡፡ በአቡነ ዘበሰማያት አስረን የገጠመንን ጉዳይ ፈፅመን እንመለሳለን፡፡ ከዚያም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ካቆምንበት እንቀጥላለን። ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት ሳናስር በመሃል እንዳሻን እንዳናቋርጥ አበው ያስተምሩናል፡፡ ✔የማህበር ጸሎት በቤታችን ከምንጸልየው ጸሎት በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ተገኝተን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንደመሆኗ በእርሷ የሚጸለይ ጸሎት ከጸሎታት ሁሉ የላቀ ነው። በካህናት እየተመራ፣ በሕብረት ሆነን የምናደርሰው በመሆኑ ታላቅ ኃይል አለው። እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ የምንጸልየውን ጸሎት እንደሚሰማ ሲያመለክተን እንዲህ በማለት ነግሮናል። "አሁንም በዚህ ሥፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ፣ ጆሮቼም ያደምጣሉ። ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ዓይኖቼ እና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።"/2 ዜና መዋ 7-15/ ከዚህ አንጻር በቤተ መቅደስ እየተገኘን መጸለይ ተገቢ ነው። በሰንበት ቀን ኪዳን ማድረስ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ተግባራችን መሆን አለበት። በሰንበት ያለ በቂ ምክንያት ቅዳሴ የሚያስታጉል በቀደሙ አባቶች /አባ ሚካኤል ወአባ ገብረኤል/ ቃል መወገዙን የተአምረ ማርያም መቅድም ይነግረናል። ከዚህ ጋር በሰዓታት፣ በማኅሌት ጸሎታት ላይ በመገኘት ቤተ ክርስቲያናችን ካዘጋጀችልን የማይጠገብ ማእድ ልንሳተፍም ይገባናል፡፡ ✔የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሐይማኖታችን ፍጹም ፍቅር የሚኖረን ከእነዚህ ጸሎታት ጋር ስንተዋወቅ ነው። አልያ የእንጀራ ልጅ መሆን ይመጣል። የመናፍቃንን አዳራሽ መናፈቅ ይመጣል። ✔ከላይ በተመለከተው የጸሎት ጊዜ እየተጠቀምክ፣ የጸሎት ዓይነቶችንም በምትችለው መልኩ እያደረስህ፣ በቤተ መቅደስ እየተገኘህ ኪዳን እያደረስህ፣ ቅዳሴ እያስቀደስህ ከፈጣሪህ ጋራ እለት እለት ተነጋገር ጸሎት ከሌለ መንፈሳዊነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ ከጄነሬተሩ ተቋርጦ ገመዱ ተበጥሶ ብቻውን እንደተንጠለጠለ አምፖል መሆንይ መጣል፡፡ ስለዚህ በርታና ጸልይ ፈጣሪ ለሁላችንም ብርታቱን ያድለን፡፡ አሜን፡፡ 🙏✞ የእግዚአብሔር አብ በረከት፤ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፤ የጻድቃን የሰማዓታት ፀሎት፤ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖታችን ይጠብቅልን፡፡ አሜን ለዘላለሙ፡፡ ✞🙏

❀♣✞ #ጸሎት ✞♣❀ #ምን_ዓይነት_ጸሎት_ልጸልይ? #ሊነበብ_የሚገባው_ድንቅ_አስተምሮ ☞✞ ጸሎት በክርስትና ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በጥያቄዎቻችሁ መሠረት የምንጸልይባቸውን ጊዜያት፣ የምንጸልየውን የጸሎት ዓይነት፣ ምን መምሰል እንዳለበት ለማየት እንሞክራለን፡፡ #1. የጸሎት ጊዜያት ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት”ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ፣ ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ 118-164/ ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡ ➊. #ጸሎተ_ነግህ ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” መዝ 62÷11 እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡ ✔ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን። ✔የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ ✔የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁ መላእክት ለተልዕኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት ነው፡፡ ✔የሌሊቱ መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡ ✔ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን። ➋ #ጸሎተ_ሠለስት ከነግህ በመቀጠል የምንጸልየው ጸሎት ጸሎተ ሠለስት (የሦስት ሰዓት) ጸሎት ይባላል፡፡ ይህ የጸሎት ጊዜም የምናስበው፦ ✔ሔዋን የተፈጠረችበት ✔እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት ✔ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት ✔ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት/ ሰዓት ነው፡፡ ➌. #ጸሎተ_ቀትር በእለቱ እኩሌታ(6 ሰዓት) ላይ የምናገኘው ይህ የጸሎት ጊዜ ነው፡፡ ይህንም ጊዜ የምናስበው፦ ✔ሰይጣን አዳምን ያሳተበት ✔በዕፀ በለስ ምክንያት ለስሕተት የተዳረገውን አዳምን ለማዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ የዋለበት ✔የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበት የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት በዚህም ምክንያት አጋንንት የሚበረታቱበት ጊዜ ነው። ✔ስለዚህ የአዳምን ስሕተት፣ የዳግማዊ አዳም የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልና መሞት፣ እያሰብን የቀን እኩሌታ በመሆኑ መዳከማችንን ተገን አድርጎ አጋንንት እንዳይሰለጥንብን እየለመንን እንጸልያለን፡፡ ➍. #ጸሎተ_ተሰዓተ ዘጠኝ ሰዓት ላይ አራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን። በዚህ ጊዜ የምናስበው፦ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነጻ ለማውጣት በፈቃዱ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው። ✔ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ተግባር ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት ነው፡፡ ✔ቆርኖሌዎስ የተባለ መቶ አለቃ በጸሎት ጸንቶ ደጅ ሲጠና ከሰነበተ በኋላ ከፈጣሪው ምላሽ ያገኘበት ሰዓት ነው፡፡(ሐዋ 10÷9) ✔በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳት መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንን የቆርኖሌዎስ እድል እንዲገጥመን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡ ➎. #ጸሎተ_ሰርክ አምስተኛው የጸሎት ጊዜ(11 ሰዓት) የሠርክ ጸሎት ነው፡፡ ✔ስለዚህ የጸሎት ሰዓት ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡ "ጸሎቴን እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን" (መዝ 140÷2) ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡(ማቴ. 27÷57) ➏. #ጸሎተ_ንዋም ይህ የመኝታ ጊዜ ጸሎት ዕለቱን በሰላም ስላሳለፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንዘጋጅበት ነው፡፡ እኛ ተኝተን የሚሆነውን አናውቅም እርሱ ግን የማያንቀላፋ እረኛ ስለሆነ ይጠብቀናል። ስለዚህ ከመተኛታችን በፊት ሊሌሊቱን እንዲባርክልን እንጸልያለን። በዚህ ጊዜም የምናስበው፦ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡ ✔ቀኑ አልፎ በሌሊቱ ይተካል ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ ✔ሰላም አሳድረንም ብለን ለፈጣሪ ራሳችንን በእምነት አደራ እናስረክባለን፡፡ ➐. #ጸሎተ_መንፈቀ_ሌሊት ይህ እኩለ ሌሊት እንደ ቀናቱ የጸሎት ሰዓታት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። ቅዱሰ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ” “ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ”/መዝ 118-62/ በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት ሰዓት ነው። ✔ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሳው በሌሊት ነው። ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም ሰዓት ነው። ከዚህ የተነሳ ለእኛ ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን በማሰብ ሞትን ድል እንደነሳልንም አስበን በማመስገን ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ከሚያቆማቸው ወገን እንዲያደርገን እየለመንን በዚህ ሰዓት እንጸልያለን፡፡ ☞✞ሰባቱን የጸሎት ጊዜያት ጠብቀን መጸለይ ካልተቻለንስ? በሰባቱ የጸሎ ሰዓታት የታቻለንን ያህል እንድንጸልይ ታዘናል፡፡ እነዚህን የጸሎት ሰዓታት በገዳም ያሉ መነኮሳት በየበረሃው የሚዞሩ ባሕታውያን ይጠብቋቸዋል፡፡ ይጸልዩባቸዋልም፡፡ በከተማ በሥራ ምክንያት ሩጫ በዝቶበት በሁሉም ሰዓት መጸለይ የማይችል ክርስቲያን ግን ቢያንስ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነሳ እና ማታ ወደ መኝታው ሲያመራ መጸለይ ይገባዋል። ጠዋት እና ማታ በመጸለይ ከፈጣሪ ጋራ ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡ ☞✞ ምን ዓይነት ጸሎት እንጸልይ? በመደበኛነት ልንጸልያቸው የሚገቡ ጸሎታት /በቤተክርስቲያናችን አባቶች በገዳማቱ በአድባራቱ የሚዘወተሩ እለታዊ ጸሎታት/ እነኚህ ናቸው፡፡ ፩. #መዝሙረ_ዳዊት መዝሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት ባህታውያን ጀምሮ በካህናት፣ ምእመናን በሁሉም ዘንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው። አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዚህ ጊዜ ጀምረው እየደገሙት፣ እየጸለዩበት ይኖራሉ። ዳዊት ሳይደግሙ ወደ ዕለታዊ ተግባራቸው አይሰማሩም። መዝሙረ ዳዊት እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው። ቀጥለን እንመልከት፦ ሰኞ (ከ1–30)፣ ማክሰኞ (ከ31–60)፣ ረቡዕ(ከ61–80)፣ ሐሙስ (ከ81– 110)፣ አርብ (ከ111–130)፣ ቅዳሜ (ከ131–150)፣ እሁድ (ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) ይጸለያል፡፡

👉“የእግዚአብሔርን ኃይል አታዉቁም እና ትስታለችሁ” ማቴ 22፥22 ➎✝#አምላክ ➏✝#የዘላለም_አባት ➐✝#የሰላም_አለቃ { ትንቢተ ኢሳያስ (ምዕራፍ 9፥6:7) } 👉"ሕፃን ተወልዷልና ወንድ ልጅም ተሰቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ሀያል አምላክ፡ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፡ ለአለቆች ሰላምን ለዕርሱም ህይወትን አመጣለሁና፡ ከዛሬ ጀሞሮ እስከ ዘልአለም ድረስ በፍርድና በፅድቅ ያፀናውና ይደግፈው ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፡ በዳዊት ዙፋን መንግስቱም ትፀናለች ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንነት ይህንን ያደርጋል።" 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 ውድ የተዋህዶ ቤተሰቦች የሆናችሁ የእናቱ የእናታችን የቅድስት ቅዱሳን የንፅሕይት ንፁሐን የድንግል ማርያም ያአስራት ልጆች የሆናችሁ እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ/ሰን በአሉ የሰላም~የደስታ~የፍቅር~የጤና~የመተሳሰብ የመተዛዘን~የበረከት~የእረድኤት~የስኬት~የቅንነት ይሆንልን ዘንድ የፈጣሪ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን!!!!

✞#ሕፃን_ተወልዶልናልና✞ 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 በስመ አብ ወወለወድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 👉ልደታትን ስንመለከት ብዙ አሉ፦ ልደተ አዳም ከምድር፣ ልደተ ሔዋን ከአዳም ፣ልደተ ሙታን ከመቃብር፣ ልደተ ሕፃናት ከእናታቸው ማህፀን የሚጠቀሱት ናቸው፡፡የእነዚህ ሁሉ ልደት ለራሳቸው እንጂ ለእኛ አይደሉም። 👉#ህፃን_ተወለልዶልናልና የሚለው ግን ለእኛ ነው፡፡ የአምላክን መወለድ ብዙ ነቢያት በብዙ ሕብረ ትንቢት ተናግረዋል በብዙ ሕብረ አምሳል መስለዋል፡፡ 👉ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ አይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ዳግምም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን።ዕብ፡1፥1 በብዙ ሕበረ አምሳል በብዙ ሕብረ ትንቢት እግዚአብሔር ከተናገረባቸው ነቢያት አንዱ ኢሳይያስ ነው። ኢሳይያስ ከነቢያት ወንድሞች በተለየ መልኩ የአምላክን ሰው መሆን የተናገረ ነቢይ ነው። መወለዱን፣ስሙን፣ከማን እነደሚወለድ ፣ለሰው ልጆች ያደረገውን የቤዛነት ስራ መከራ መቀበሉን ፣በጎል መወለዱን በግልፅ ከተናገሩ የተነሳ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ወንጌላዊ ነቢይ የሚል ቀጽል ሰጥተው ይጠሩታል፡፡የትንቢት መጽሐፉንም ደረቅ ሐዲስ በማለት ሰይመውታል፡፡ይህም ማለት ስለክርስቶስ መወለድ በምሰሌ ያይደለ በቀጥታ የተናገረ በመሆኑ ነው ለምሳሌ የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡ 👉"ጌታ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"ኢሳ፡7፥14 ከላይ ባጭሩ እንዳየነው ከማን እንደምትወልድ ስሙን ማን አንደሆነ በግልጽ እስቀምጧል፡፡ 👉"በስድስተኛው ወር ገብርኤል መላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ ከዳዊት ወገን የሆነ ስሙ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ከታጨች ከድንግል ዘንድ የዚህች ድንግል ስሟ ማርያም ነው"ሉቃ፡1፥26 በማለት ወንጌለዊው ገልጧል። 👉"በነቢይ ከጌታ ዘንድ እነሆ ድንገል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለውን ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። ማቴ፡1፥22 ኢሳይያስ "ሕፃን ተወልዶልናል" ብሎ ለእኛ መዳን የተወለደው ነገረን ቀጥሎም ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል።" ይላል። ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን መድኃኒት ለሆነን እንደመጣ ሊያሳይ፡፡ ከዚህ በመቀጠል እርሱን ለመግለጥ የተጠቀማቸው ቃላት በጣም የሚደንቁ ናቸው፡፡ #ስሙ_ድንቅ_መካር_ኃያል_አምላክ_የዘላዓለምአባት_የሰላምአለቃ በሚሉ #ሰባት ቃላት ገልጾታል ቁጥሩ በእብራዊያን ዘንድ ፍጹም ነው። ከላይ ኢሳይያስ የተጠቀማቸው ሰባት ቃላት ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን የሚያስረዱ ናቸው፡፡ ሕፃን ብሎት ነበር ሕፃን የሚለው ስም ታህታዊ ማንም በሥጋ የወለደ ሰው ሲወለድ የሚጠራበር ነው ፡፡ ሰው መሆኑን ለመግለጥ ሕጻን አለው አምላክነቱን ለማስረዳት ስሙም ብሎ ጀምሮ በሰባት ቃለት አስረድቶናል፡፡ ➊✝#ስሙ ስለ ስሙ ቅዱሳት መጻፍት ሲናገሩ ኢየሱስ ፣አማኑኤል፣ ክርስቶስ ፣መድኃኔዓለም የሚባሉት ስመ ስጋዌ ናቸው። ሰው በመሆኑ የተጠራባቸው ኢየሱስ፦ማለት መድሐኒት ማለት ነው፡፡ አማኑኤል፦ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። ከእኛ ጋር፦ ሲባል ከስጋችን ሥጋ ከደማችን ደምን ነስቶ ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው። ክርስቶስ፦ማለት መሲህ ፣ሹም፣ንጉሥ ፣አለቃ ማለት ነው፡፡ መድኃኔዓለም፦ማለት የአለም መድኃኒት የዓለም ቤዛ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቆርሶ በደሙ ዓለምን የዋጀ ማለት ነው፡፡ 👉"ልጅም ትወልዳለች እርሱም ሕዝቡን ከኃጢያታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለች" ማቴ፡1፥21 👉"ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ እርሱ በመጣ ጊዜ ሁሉን ይነግረናል አለችዉ ኢየሱስም የምትናገሪዉ እርሱ እኔ ነኝ አላት።"ዮሐ፡1፥42 👉"እኛ ራሳችን ሰምተነዋል አርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን።"ዮሐ፡4፥42 ከላይ የተመለከትናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስሙንና ግብሩን የሚገልጡ ናቸው፡፡ ትርጉሙ ከተግባር ጋር የተያያዘ ነውና ይህንን ነው ኢሳይያሰ “ሕፃን ተወለደልን” በማለት የተነገረለት ኢሳይያስም ሕጻን ብሎ የጠራዉ ሰዉ ሲሆን አምላክነቱ አልተለወጠምና አምላክነቱን መግለጥ የሚችሉ ቃላት ከስሙ ጀምሮ ተጠቅሟል ስሙ አዳኝ ነው። 👉"አቤቱ በስምህ አድነኝ።"መዝ፡53፥1 👉ስሙ ቅዱስ ነው፤ እርሱ ለእኔ ታላቅ ስራ አድርጎል እና ስሙም ቅዱስ ነው።"ሉቃ 1፥50 👉ስሙ፦ አጋንንትን ይገዛል "አጋንንት በስምህ ተገዙልን።"ሉቃ 10፥17 👉ያመኑትን እነዚህን ምልክቶች ይከተሏቸዋል በስሜ አጋንትን ያወጣሉ እባቦችን ይይዛሉ የሚያሰክር መርዝ ቢጠጡ አይገድላቸውም።ማር 16፥17 👉ስሙ፦ ስግደት የሚገባው ነው ?"እግዚአብሔር/እግዚአብሔርነቱ/ ያለልክ ከፍ ከፍ አድርገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለዉን ስም ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከኩ ዘንድ።" ቆላ 2፥9-11 👉ስሙ፦ ምስጋና ይገባዋል 👉"በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ.."ማቴ 6፥9 ➋✝#ድንቅ ድንቅ፦ማለት ቃል እነደሚገባው አድርጎ የማይገልጠዉ ቃላት ላጣንለት ነገር የምንጠቀመዉ ነዉ በህቱም ድንግልና ተጸንሶ በህቱም ድንግልና መወለዱን ሲደንቅ የሚኖር ነውና በኪሩቤል ላይ የሚገለጥ ስጋን ለብሶ መወለዱን የማይወስነዉ መወሰኑ የማይዳሰሰው መዳሰሱ የማይታየው መታየቱ የማይጨበጠው እሳተመለኮት በጨርቅ መጠቅለሉ በጎል መጣሉ የሚደንቀን ነው እነኳን ለኢሳይያስ ለመላእክትም ድነቅ ነው። ሰማይ ዙፋኑ የሆነ አምላክ በትህትና መገለጡ ድሆች እንኳ ባልተወለዱበት የከብቶቸች በረት መወለዱ ድንቅ ነው፡፡ 👉"በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ"(እግዚአብሔርን ስራህ ድንቅ ነው በሉት) መዝ፡65፥3 ሕፃናትን በእናታቸው ማህጸን የሚጠብቃቸው ሕጻን ሆነ ይህ እንዴት አይደንቅ 👉"ስራህ ድንቅ ነው ነፍሴም እጅግ ታዉቀዋለች።"መዝ 138፥12 በላይ በሰማይ በኪቤል ጀርባ በምድር በእናቱ እቅፍ መታየቱ ድንቅ ነው? "ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ ለዓይናችን ድንቅ ነው።"መዝ 117፥22 ማቴ 22፥42 ➌✝#መካር ሰው ለመሆን መወሰኑን በልብ የመከረውን በነብያት ያናገረውን ያን የፈጸመ ምክረ ከይሲን በምክሩ የሻረ ዲያብሎስን ያሣፈረ በልቡ ጥበብ ከሰው ልጆች በተለየች ምክሩ አዳምን ነጻ ያወጣ መካር ነው፡፡👉"ግሩም ምክሩ እምጎለመኸያው (ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ልዩ ነው)"መዝ 65፥5 በዚህ በልዩ ምክሩ ዲያብሎስ የመከራቸውን የነፍስና የስጋ ተዋህዶ በሥጋ ተወለደ ይህ የዲያብሎስን ስራ ያፈርስ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። 1ኛ ተሰ 3፥7👉"ውዕቱ ጥበቡ ወምክሩ ያድኅነነ መጸአ (እርሱ የአብ ጥበቡና ምክሩ ሊያድነን መጣ)" ይለዋል ቅዱስ ያሬድ ➍✝#ኃያል ኃያልነት የበሕርይ ገንዘቡ ነው "ኀይሉ ለአብ ወጸጋ ለአህዛብ…”የአብ ኃሉ እርሱ ነው ለአህዛብም ጸጋን የሚሰጥ “ እነዳለ መጽሐፈ ኪዳን፡፡ መንግሥትህ ያንተ ናትና ኃይል ምስጋና ክብር ለዘላለሙ” ማቴ 6፥13 በኃይሉ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃዉን ሊነጥቀዉ እንዴት ይቻላል።ማቴ 12፥29👉“ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም /ደካማ/አይደለም ነገር ግን በእናንተ ኃለኛ ነው በድካም ተሰቅሏልና ነገር ግን በእግዚአበሔር /በእግዚአብሔር/ኃይል በሕይወት ይኖራል 1ኛ ቆሮ 13፥3-5 👉“የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው” 1ቆሮ 1፣24-26 ሰዎች ይህንን የእግዚአብሔር ኃይል አላወቁም ነበር።

#ጌታችን_ስለተወለደባት_ምሽት_ሶርያዊው_ቅዱስ_ኤፍሬም_አንዲህ_አለ፦ 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 👉‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ! 👉ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! 👉ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት! ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡ 👉ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ! የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!›› #የገና_አባት (ቅዱስ ኒቆላዎስ) ለድኆች ሥጦታ ይለግስ የነበረ ቅዱስ አባት ነው። ታሪኩም በስንክሳር ታኅሣሥ 10 ላይ ተጽፎአል። "የገና ዛፍ ባሕላችን አይደለም እነርሱ ክረምታቸውን የሚያስታውሱበት ነው ከእኛ ጋር አይገጥምም" "የተወለደውን ክርስቶስ የበዓሉ ማዕከል እንዳናደርግ ያደርገናል" ማለት ትክክለኛ ነገር ነው። Pagan Origin (የባዕድ አምልኮ መነሻ) አለው ብሎ ጣዖት አምልኮ ነው ማለት ግን ከገደብ ያለፈ ድምዳሜ ነው። በከዋክብት ያመልኩ የነበሩት የጥበብ ሰዎች በሚያመልኩት ነገር ወደ ክርስቶስ ተጠርተዋል ፣ የዙሐል ጣዖት ይከበርበት የነበረውን ዕለት ከክርስትና በኋላ በእስክንድርያ የቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን ሆኗል። 👉የራሳችንን የገና ባሕላዊ አከባበሮች የገና ጨዋታን ፣ ቀጤማ መጎዝጎዝ የመሳሰሉትን ማክበር ይገባናል። ከዚያ ውጪ በክርስትና መንፈስ እስከተቃኘና የጌታን በበረት መወለድ ፣ የሰብአ ሰገልን ጉዞ ፣ ከዋክብቱን ፣ የመላእክትን ዝማሬ ፣ የእረኞችን ደስታ ፣ የሰብአ ሰገልን እጅ መንሻ የሚያሳይ እስከሆነ ድረስ የኛ ባሕል ያልሆነውን ሁሉ ጣዖት ነው ብሎ ማንቋሸሽ ፣ የሚያምር ነገርን ሁሉ ማውገዝ ያስመስላል። ቅዱስ ኒቆላስም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምትዘክረው ቅዱስ ስለሆነ አጋጣሚውን ጻድቁን ለማስተዋወቅም ልንጠቀምበት ይገባል። ሥጦታም የምንሠጣጠው የሰብአ ሰገልን ሥጦታ መነሻ አድርገን ሲሆን ልግስናውን ለነዳያን ብናደርገው የበለጠ በረከት እንቀበልበታለን።"በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ"

•✞✞✞ #ግን_መቼ_ነው ? ? ? ✞✞✞• ☞መቼ ነው ፣ እውነተኛ ክርስቲያን የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔርን መፍራት የምጀምረው? ? ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔርን ማመስገን የምጀምረው? ? እስከመቼስ ነው በዋዛ በፈዛዛ ጊዜየን የምጨርሰው? ? ☞በከንቱ ጊዜዬን እጨርሳለሁ እፍፍፍ መቼ ነው ፣ እግዚአብሔር በሰጠኝ ነገር ደስተኛ የምሆነው ? ? ሁልግዜ አማርረዋለሁ ግን ለምን? ☞ኦ አምላኬ እዳስተውል እርዳኝ መቼ ነው ፣ ሰውን እደራሴ አድርጌ የምወደው? ? ☞መቼ ነው ፣ ለጠሉኝ ሁሉ መልካም የማደርገው ? ? እኮ መቼ? ☞መቼ ነው? እግዚአብሔር ለምን እደፈጠረኝ የምረዳው? ? ☞እኔማ ሁሌም በአለም ከንቱነት ጠፋሁ አለም አታለለችኝ ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔር እንደፈለገው መኖር የምጀምረው ? ? ☞እኮ መቼ? እድሜዬን አንድም ቀን መልካም ሳልሰራበት..? ☞መቼ ነው፣ ክፉ ንግግር ከመናገር ተንኮል ከመስራት የምቆጠበው ? ? ☞መቼ ነው ፣ለፆም ለፀሎትና ለስግደት በሙሉ ልቤ ሆኘ የማገለግለው እኮ መቼ? ? ☞መቼ ነው፣ ለመልካም ስራ ምሳሌ የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ ይህን ከንቱ አለም ከልቤ የማወጣው ? ? ? እኮ መቼ ? ☞መቼ ነው ፣ እኔ ማለት ትቼ እህት ወንድሞቼ ወገኖቼ ማለት የምጀምረው ? ሁሌም እራስ ወዳድ እፍፍፍፍ.... ☞መቼ ነው ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማከብረው ? ?? ☞እኮ መቼ ነው እንደ ቃሉ የምኖረው ? ☞እስከመቼስ ነው የሚፈልገውን ነገር ትቼ የሚጠላውን ነገር የምከተለው እፍፍፍ.... ☞መቼ ነው ፣ ጥሩ እና ለጋሽ አዛኝ የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ በፍቅር መኖር የምጀምረው ? ? ? ሁልጊዜ ልቤ በጥላቻ ተሞልቷል... ☞መቼ ነው ሰውን ከመበደል ከማስቀየም የምቆጠበው? ?? ☞መቼ ነው ከራስ ወዳድነት የምላቀቀው ? ? ? ☞መቼ ነው ተመስገን አምላኬ የምለው? ? ? ☞ኦ አምላኬ አንተ እርዳኝ እኔስ ግራ ገባኝ ??? አምላኬ ሆይ ጥበብና ማስተዋሉን፤ ልብና ልቦናውን፤ ጥንካሬና ብርታቱን እምነትና የዋህነቱን፤ ትግስትና ፍቅሩን•••ለኛ ለባሮችህ ትሰጠን ዘንድ አማላጅ በምትሆን በቅድስተ ቅዱሳን በእመአምላክ በንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም፤ እንዲሁም አንተ ባከበርካቸው ቅዱሳን ፀሎትና ቃልኪዳን ማረን ይቅር በለን፡፡ አቤቱ ሆይ እኛ ሀጢያተኛ ባሮችህን ለንሰሀ ሞት አብቃን፡፡ •••✞ አሜን ✞ አሜን ✞ አሜን ✞•••

#የልዳው_አንበሳ የቤሩቱ ኮከብ የልዳው አንበሳ ሦስት ጊዜ ሞቶ ጊዮርጊስ ተነሳ/2/ #አዝ........ በተጋድሎ ጸና........ቅዱስ ጊዮርጊስ በእውነት መሰከረ...ቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያሉ ጊዮርጊስ......ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰይፍ ተመተረ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ የልዳው አንበሳ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠላት አይገዛህ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይጣንን ተዋጋው..ቅዱስ ጊዮርጊስ ጎልማሳው ሥጋህ...ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ.......... ዲድያኖስ ተቆጣ....ቅዱስ ጊዮርጊስ ጽናትህን አይቶ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀጣ ተነሳ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ በትዕቢት ተሞልቶ...ቅዱስ ጊዮርጊስ ባንተላይ ወገኑ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታት........ቅዱስ ጊዮርጊስ ከምድረ ገፅ አንተን....ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍፁም ለማጥፋት.....ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ......... በመበለቷ ቤት ..........ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ተአምር ሰራ....ቅዱስ ጊዮርጊስ ምሶሶ አለምልሞ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ እውራን አበራ................ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባት አክሊላትን ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ተቀበለ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ጌታ ፍቅር ..............ቅዱስ ጊዮርጊስ ባደባባይ ዋለ................ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ.......... ዝክርህን ዘክሮ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ስምህን የጠራ......ቅዱስ ጊዮርጊስ በነፍስም በሥጋ....ቅዱስ ጊዮርጊስ የለበት መከራ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ ደራጎንን አጥፋ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ አርቅልን ከኛ........ቅዱስ ጊዮርጊስ በዝሙት በኃጢአት....ቅዱስ ጊዮርጊስ ደርሶብናልና..............ቅዱስ ጊዮርጊስ

🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ተጋድሎ_በኢትዮጵያ_ሊቃውንት 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ❖ የዚኽም ቅዱስ አባቱ በቀጶዶቅያ መስፍኑ አንስጣስዮስ ሲኾን እናቱ ቴዎብስታ ትባላለች፤ የተወለደውም በልዳ በሶርያ ፍልስጥኤም በ፪፻፹ ዓ.ም. ነው፤ ታናሽ ኾኖ ሳለ አባቱ ዐርፏል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ፈረስ ግልቢያን ተምሮ ኻያ ዓመት በኾነው ጊዜ ቢሩት ሀገር በመኼድ በዚያ ሀገር ይመለክ የነበረውን መንፈሰ ሰይጣን ያደረበትን የመኰንኑን ልጅ እንዲበላት የተሰጠውን ዘንዶ በክርስቶስ ስም ከገደለው በኋላ እጅ መንሻ ይዞ ወደ ንጉሠ ፋርስ ኼደ፡፡ ❖ በዚያ ሀገር ግን ነገሥታቱ ጣዖታትን በማምለክ ክርስቲያኖችን ሲያሳድዷቸው አይቶ ዐዘነ፤ ልቡም በክርስቶስ ፍቅር ነድዶ ወደ ሀገሬ አልመለስም ስለ ክርስቶስ ስም እሞታለኊ አለና “ክርስቲያናዊ አነ ወአአምን በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ” (እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው) በማለት መሰከረ፡፡ ❖ ከዚያም ንጉሡ ልብሱን ገፍፈው በዕንጨት ላይ እንዲሰቅሉት፤ ዳግመኛ የዘንባባ እሾኽ የመሳሰሉ ፸ የብረት ችንካሮች ሠርተው በነዚያ እንዲቸነክሩትና ዐጥንቱን ኹሉ እንዲቀጠቅጡት አዘዘ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በትዕግሥት በመኾን “እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል” (ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም) አለ፡፡ ❖ ዳግመኛም በውስጡ ረዣዥም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማን ባጫሙት ጊዜ “ሠጠቅዎ ወመተርዎ ዐሥራዊሁ እስከ ውኅዘ ደሙ ዲበ ምድር ከመ ማይ ወሶበ ስዕነ ሠጊረ ድቡተ ሖረ” ይላል ችንካሮቹ ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ እስኪፈስስ ድረስ እግሩን ዘልቀው ሥሩን በጣጠሱት፤ መኼድም ባልቻለ ጊዜ አጐንብሶ ኼዷል፤ ከዚያም የፈላ የብረት ጋን ውስጥ ከትተው ሰውነቱ በደም እስኪጥለቀለቅ ድረስ ራሱን በመዶሻ ሲመቱት ወደ ጌታችን ጸለየ፤ ያን ጊዜ “ጊዮርጊስ ሆይ ከአንተ ጋር ነኝና ጽና” የሚል ቃል ከሰማይ መጣለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጾ ከሕመሙ ፈውሶታል፡፡ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡ ❖ ንጉሡም ይኽነን ባየ ጊዜ እጅግ የሚያስጨንቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀን አሠርቶ ለቅዱስ ጊዮርጊስ “እመሰ ትሠውዕ ለአጵሎን ትነሥእ ጌራ መንግሥት ወእመሰ ኊልቊ አንተ ከመ ትትልዎ ለክርስቶስ ነጽር ዘንተ መንኰራኲረ ዘግበርኩ ለከ ከመ እግድፍ በውስቴታ ታማስን ሥጋከ” (ለአጵሎን ብትሠዋ የመንግሥትን ዘውድ ትቀዳጃለኽ፤ ግን ክርስቶስን ለማገልገል የቈረጥኽ ብትኾን ሥጋኽን ትፈጭ ዘንድ በውስጧ ልትጣልባት ያዘጋጀኋትን መንኰራኲር ተመልከት) አለው፤ ይኽ ሲኾን ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣሪው ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ እነርሱም ወደ መንኰራኲሩ በመወርወር ፵ ሰዎች ያዞሩት ዠመር ከዚያም ሰውነቱ ለዐሥር ክፍል ተከፋፈለ፤ እነርሱም ሥጋውን በጒድጓድ ውስጥ ቀበሩት፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመምጣት እንደገና ከሞት አስነሣውና ባረከው፡፡ ❖ ርሱም ከሞት ተነሥቶ እንደገና ወደ ከተማ ገብቶ ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ እነርሱም እጅግ ለመስማት የሚከብዱ መከራዎችን አደረጉበትና ሰውነቱን ጨምቀው አንጀቱን ዘረገፉት፤ ከዚያም ሥጋውን አቃጥለው በዕንጨት ቀፎ በማድረግ ይድራስ ወደተባለ ተራራ ወስደው ዐመዱን በትነውት ተመለሱ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመውረድ አራቱን ነፋሳተ ምድር የተበተኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋዎች እንዲሰበስቡ አዝዞ እንደገና ከሞት አስነሥቶታል፤ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በክርስቶስ አምነው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም ብዙ ተጋድሎዎችን ለሰባት ዓመታት ከፈጸመ በኋላ ንጉሡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ በሰይፍ እንዲቈረጥ አዝዞ ወደ መሰየፊያው ቦታ ሲኼድ እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያኖች ጸጥ ይል ዘንድ ጸለየ፤ ወዲያውኑም እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት አቃጥሏቸዋል፤ ከዚያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብዙ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፤ ከዚያም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ራሱን ዘንበል አድርጎ ሚያዝያ ፳፫ በሰይፍ ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል፡፡ ❖ ከአገልጋዮቹ የቀሩት ሥጋውን ወስደው በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ወደ ሀገሩ ልዳ በመውሰድ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በውስጡ አኖሩት፤ ከርሱም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ተገልጠዋል፡፡ ❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌ ድርሰታቸው ላይ፦ “ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ” (የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከኾነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለርሱ ኹሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) ርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል) ይሉታል፨ ❖ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቁ አርከ ሥሉስም የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስን ተጋድሎ፡- “ሰላም ለከ ሰርዌ ሰማዕታት አእላፍ ዘሞገሰ ስምከ በጽሐ መንገለ ኲሉ አጽናፍ በቅድመ ፀሓይ ብሩህ ዘኢየዐርብ ለዘልፍ ሕማምየ ዝሩ ነሢአከ ወጸዊረከ እስትንፋሰ አፍ ጊዮርጊስ ቀሊለ ክንፍ ከራድዮን ዖፍ” (ዘወትር በማይጠልቅ በብሩህ ፀሓይ ፊት በምድር ዳርቻዎች ኹሉ የስምኽ ባለሟልነት የደረሰ የአእላፍ ሰማዕታት አለቃቸው ሰላምታ ለአንተ ይገባል፤ ክንፈ ፈጣን ከራድዮን ዖፍ የተባልኽ ጊዮርጊስ ሆይ የአፍ እስትንፋስን ተቀብለኽና ተሸክመኽ ሕማሜን በትን) እያለ ተማፅኖታል፡፡ ❖ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦ “ሰላም ለጊዮርጊስ ሰማዕት ዘፀሓየ ጽድቅ ዘተአምሪሁ ከመ ኆጻ ባሕር ዘኢይትኌለቊ ኮከበ ክብር ዘማእከለ ሰማይ ወምድር ዘአርአየ ኀይለ በዲበ ሰሌዳ መንበር ብእሲ አዛል ወመስተጋድል ኀያል ዝሕዙሐ ገድል”፡፡ (ገድሉ የበዛ የተትረፈረፈ ኀያል፤ ተጋዳይ ጐልማሳ (ብርቱ) ሰው፤ በተዘረጋ ዙፋን ላይ ኀይልን ያሳየ፤ በሰማይና በምድር መኻከል ያለ የማይቈጠር የክብር ኮከብ፤ ተአምሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ የኾነ፤ የፀሓየ ጽድቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት ለኾነ ለጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፨ ❖ የስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ ደራሲ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ፦ "እምብሩር ወወርቅ ይትበደር ሞገሱ ለጊዮርጊስ ቅዱስ በዲበ ጸዐዳ ፈረሱ ለረዲኦትነ ይምጻእ ወያንሶሱ" (ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም) ይለዋል፨ 👇👇👇👇👇👇👇 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች፦ ☞በዕለተ ሠሉስ/ማክሰኞ ለሚከበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከአሁኑ የተለያዩ መዝሙሮችን እናጠናለን፡፡ እናንተም ያጠናችሁትን ወይም ማጥናት የምትፈልጉትን መዝሙሮች እና ወረቦች በኦዲዮ እና በቪዲዮ እንዲሁም በፅሁፍ መላክ ትችላላችሁ፡፡ ✔✞ እግዚአብሔር አምላክ የሰላም በዓል እንዲያደርግልን ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ከቅዱሳን፣ ፃድቃን፣ ሰማዕታት፣ ከሀዋርያት ደናግል መነኮሳት ምልጃና ጸሎት ጋር እኛም በጾም፣ በጸሎትና በስግደት እየበረታን ለልደተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰላም ያደርሰን ዘንድ የእርሱ ቅዱስ መልካም ፈቃድ ይሁንልን ፤ አሜን፡፡ ☞ቻናላችን @EOTC2921 ☞ግሩፓችን @Ethio_Orthodox1 ይህ ነው ማንኛውንም መንፈሳዊ አስተያየትና ጥያቄ በግሩፑ ማድረስ ትችላላችሁ፡፡

031-Bekeme Semaene.mp35.71 MB

030-Yom Tewolde.mp37.20 KB

029-Beza kulu alem.mp31.54 MB

028-Yitfesiha adbare Tsion.mp31.29 MB

027-Reyiwo nolot.mp31.28 MB

026-Tewolde Iyesus.mp31.35 MB