ar
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

الذهاب إلى القناة على Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

إظهار المزيد
4 374
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
#የአምላክ_እናት_ልደት____ልደታ_ለማርያም በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ♥ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መተርጒማን እንዳስተማሩንና እንደጻፉልን በእናቷ በሐና በኩል ያሉ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ጴጥሪቃ ቴክታ ሲባሉ “ወኮኑ ክልኤሆሙ ጻድቃን ወፈራህያነ እግዚአብሔር ወይትአመንዎ ለአምላኮሙ በጥቡዕ ልብ እንበለ ኑፋቄ” ይላል (ኹለቱም ሰዎች ደጋጐችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ያለምንም መጠራጠር በፍጹም ልቡናቸው በአምላካቸው የሚተማመኑ ነበሩ)፤ እነርሱም በጊዜው ይኽ ቀራችኊ የማይባሉ ባለጠጎች ነበሩ፤ ከሀብታቸው ብዛት የተነሣ ወርቁን ብሩን እንደ ዋንጫ እያሠሩ በላሙ በበሬው ቀንድ ላይ ይሰኩት ነበር፤ ይኽን ያኽል አቅርንተ ወርቅ፣ አቅርንተ ብሩር እየተባለ ይቈጠር ነበር፤ የዕንቊ ጽዋ እንኳ ፸፣ ፹ ያኽል ነበራቸው ይላል፡፡ ♥ ከዕለታት ባንዳቸው ጴጥሪቃ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ የሀብቱን ብዛት አይቶ ሚስቱ ቴክታን “ለመኑ ዘዘገብነ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ አንቲኒ ወአነሂ መካን ንሕነ” (የሰበሰብነው ገንዘብ ስንኳን ለኛ ለልጅ ልጅ ይተርፍ ነበር አንቺም እኔም መካኖች ነንና የሚወርሰን ልጅ የለንም) በማለት ተናገራት፤ ርሷም እንዲኽ ማለቱ ወላድ የፈለገ መስሏት በሐዘን ኾና “አምላከ እስራኤል ከኔ ልጅ ባይሰጥኽ ከሌላ ይሰጥኽ ይኾናልና ሌላ አግብተኽ ውለድ” አለችው፤ ርሱም “አነሂ ኢይፈቅድ የአምር አምላከ እስራኤል ከመ ኢየሐስቦ ለልብየ” (ይኽንስ እንዳላደርገው በልቤም እንዳላስበው የእስራኤል አምላክ ያውቃል) በማለት ተናገረ፡፡ ♥ ርሷም ዐዝና ሳለ ራእይ ታያለች፤ ነጭ እንቦሳ ከማሕፀኗ ስትወጣ እንቦሳዪቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባት ስትደርስ ሰባተኛዋ ጨረቃን ስትወልድ፤ ጨረቃ ፀሓይን ስትወልድ አይታ በአድናቆት ለባሏ፦ ❖ “ግሩም ግብሩ ለእግዚአብሔር ትማልም ርኢኩ በሕልምየ ጸዐዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርሥየ ይእቲኒ ወለደት ጸዐዳ ጣዕዋ እስከ ሰብዐቲሆን ወሳብዕታኒ ወለደት ወርኀ ወወርኅኒ ወለደት ፀሓየ” ♥ (የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ትናንትና ማታ በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማሕፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ደግሞ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንደዚኽ እየኾነ እስከ ሰባት ትውልድ ሲደርሱ ሰባተኛዪቷም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየኊ) በማለት አስረዳችው። ♥ ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ሕልም ወደሚፈታ ሰው ዘንድ በመኼድ የሚስቱን ራእይ ነገረው፤ ያም ሕልም ተርጓሚ ምስጢር ተገልጾለት ሰባት አንስት ጥጆች መውለዳችኊ ሰባት ሴቶች ልጆች ይወለዳሉ፤ ነጭ መኾናቸው ደጋጎች ልጆች መኾናቸው ሲኾን “ወሳብእታኒ ትከብር እመላእክት ወትትሌዐል እምኲሉ ሰብእ ወበእንተ ፀሓይኒ ኢያእመርኩ” (ሰባተኛዪቱ ጨረቃን መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ናት፤ የፀሓይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም) በማለት ተረጐመለት፤ ርሱም ለሚስቱ ነገራት፤ ርሷም “የእስራኤል አምላክ የሚያደርገውን ርሱ ያውቃል” በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ♥ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔሜን አሏት፤ ሔሜን → ዴርዴን ወለደች፤ ዴርዴም → ቶናን፤ ቶናም →ሲካርን ወለደች፤ ሲካርም→ ሴትናን፤ ሴትናም →ሔርሜላን ወለደች፤ ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ኹሉ ለፈጠረ ጌታ አያት ለመኾን የበቃች ሐናን ወልዳለች። ♥ ሐናና ኢያቄምንም “ወክልኤሆሙ ኄራን ወሥሙራን እሙንቱ ወየሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር እስመ እግዚአብሔር ኀረዮሙ ወአፍቀሮሙ ትካት” ይላቸዋል እግዚአብሔርን የሚወድዱ በሕጉ የሚኖሩ ደጋጎችና አምላክም የመረጣቸው ሲኾኑ ሐና መካን በመኾኗ ምክንያት ኹለቱም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት በመኼድ ለዐይናቸው ማረፊያ ለልባቸው ተስፋ የሚኾን ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ እንደነበር፤ “Protoevangelium of James” (ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስ) የሚለው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊዉ መጽሐፍ በስፋት ይገልጻል፡፡ ♥ ከዕለታት ባንደኛው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ሲመለሱ “ወርእዩ አርጋበ እንዘ ይትፌሥሑ ምስለ ውሉዶሙ” ይላል ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ አይተው ሐና “አቤቱ ጌታዬ ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠኽ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሣኸኝ” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፤ ወዲያው ሱባዔ ይገባሉ፤ ኢያቄም ወደ በረሓ ኼዶ ሲጸልይ ሐና ደግሞ በቤቷ ዙሪያ ባለው የተክል ቦታ ሱባዔ ያዘች። ♥ በሱባዔያቸው ፍጻሜ ኹለቱም ራእይ አይተው ተነጋግረዋል፡፡ “ይቤላ ኢያቄም ለሐና ብእሲቱ እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ” ይላል ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዎፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ብሎ የተገለጸለትን ለሐና ነግሯታል። ♥ ይኸውም የራእዩ ምስጢር፡- ወፍ የተባለው አካላዊ ቃል ክርስቶስ ሲኾን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፤ ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ ሲያጠይቅ ሲኾን፤ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ምልአቱ፣ ስፍሐቱ፣ ርቀቱ፣ ልዕልናው፣ ዕበዩ ናቸው፡፡ ♥ ሐናም ተገልጾላት “ትቤሎ ሐና ለኢያቄም ብእሲሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ” ይላል ለባሏ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ብላዋለች። ♥ ይኽ የራእይ ምስጢር፡- ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትኾን፤ ነጭነቷ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ ወደ ዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በዦሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መኾኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ♥ ኢያቄምና ሐናም ይኽነን ራእይ ሐምሌ ፴ ቀን ካዩ በኋላ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ይኾናል፤ ሴትም ብንወልድ ለቤተ እግዚአብሔር መጋረጃ ፈትላ ትኑር” ብለው ስእለት ከተሳሉ በኋላ ራእይ አየን ብለው ዕለቱን አልተገናኙም፤ አዳምንና ሔዋንን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት” ብሎ የተናገረው አምላክ ለእኛም ይግለጽልን ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ እየብቻቸው ሰነበቱ። ♥ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን “ከሰው የበለጠች ከመላእክት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችኊ" ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት እሑድ ተፀንሳለች፤ በእናቷ ማሕፀን ሳለችም “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ” እንዲል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥንተ አብሶ ባመጣው መርገም እንዳትያዝ ጠብቋታል፡፡ ♥ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም መፀነስ ከሊቃውንት መኻከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፦ ✍ “ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ” ♥ (ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) በማለት ዓለምን ኹሉ በደሙ ፈሳሽነት ያዳነ ንጉሣችን፣

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 👉💟እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ፤ ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽሸ💟👈 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ✍ልጄ ጸጉርህ ወጣት ሳለህ ጥቁር፣ ጐልማሳ ስትሆን ገብስማ፣ ስትሸመግል ነጭ ይሆንልሃል። በወጣትነት ማስተዋል ያጥርሀልና ፀጉርሕ ጥቁር፣ በጎልማሳነትህ ጉልበትና ጥበብ ተዋህደውሃልና ገብስማ በሽምግልናህ እውቀትህ በዝቷልና ነጭ ይሆንልሃል። 👉ጉልበት ያለው ወጣት ማስተዋል ያጥረዋል። ማስተዋል ያለው ሽማግሌ ጉልበቱ ይከዳዋል። ጉልበትና ጥበብ የተዋሃዱት ጎልማሳ ስትሆን ግን ብዙ መስራት ይጠበቅብሃል። 👉ሀኪም ታማሚ ታካሚውን አስቀምጦ ወይም አስተኝቶ እንጂ በቁሙ እንደማያክመው ሁሉ እግዚአብሔርም አሳምሞ ወይም ጥሎ ያስተምርሃል። ደግሞም ያክምሃል። ሲያስተኛሕና ሲጥልህ "ጌታ ሆይ የምታስተምረኝ ምንድን ነው?" በለው እንጂ አትዘን አትማረር። ለሰው በቁሙ መማርና መለወጥ ብዙ ጊዜ ጭንቅ ነውና እግዚአብሔር ጥሎ ያስተምርሃል። ያነሣሃል። 👉ልጄ ሽምግልናን እንድታያት ወጣትነትህ ሽምግልናን ታክብራት። የናቅኸውን ነገር እግዚአብሔር አይሰጥህምና ሽማግሌ እንድትሆን ሽምግልናን አክብራት። 👉ልጄ አምስት አይነት ዘውዶች አሉ። አምስተኛው ግን ከሁሉም ይበልጣል። ✟ የመጀመሪያው የንግስና ዘውድ፣ ✟ ሁለተኛው የትምህርት ዘውድ፣ ✟ ሦስተኛው የተክሊል ዘውድ፣ ✟ አራተኛው የክህነት ዘውድ ሲሆኑ ✟ አምስተኛው ግን የሽበት ዘውድ ናቸው። አራቱም ዘውዶች ሲመሽ ይወልቃሉ። የማይወልቀው የተፈጥሮ ዘውድ ሽበት ግን ከሁሉም ይበልጣል መብለጡም በኑሮ ማስተዋልን መውለዱ ነው። 👉ልጄ የክብር ኑሮ አድካሚ ነውና አትመኘው ሀብትም ርካታ የለሽ ያደርጋልና ፍቅርን ምረጥ። አፈር ሥጋዬን ካላከበሩልኝ ብለህ ጠብ አታብዛ የምትረግጣት መሬት አንድ ቀን ትረግጥሃለችና አረማመድህ በዝግታ ይሁን። ገንዘብ ካለኝ ወዳጅ ይኖረኛል ብለሕ አታስብ። ገንዘብ ከድህነት እንጂ ከሞት አያስጥልም። ፍቅር በፍቅር እንጂ በገንዘብ አይገዛምና በገንዘብሕ ሀሰተኛ ወዳጅና እውነተኛ ጠላት እንደምታተርፍ እወቅ። ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ የተባለው ለአውሮፕላን እንጂ ለፅድቅ አይደለምና ገንዘብሕን ተማምነህ የድንግልን አማላጅነት የክርስቶስን ቤዛነት አትርሳ። 👉ልጄ እኔ ብቻ በችግር እኖራለሁ ብለህ ሌላው ባለመቸገሩ አትቅና። ሁሉም ለማኝ ሲሆን ደግ (ጥሩ) አይደለምና። ዛሬ ዓለም የተጨነቀው ሁሉም ሀገር በመቸገሩ ነው። ሁሉም ሲቸገር ደግ አይደለምና ይሕን አትመኝ። 👉ሲነጋ ወደ ዓለም ሲመሽ ወደ እግዚአብሔር አትገስግስ። መከራህን ለጌታ ደስታህን ለዓለም አታድርግ። እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ።ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽ። ሕፃን ልጅ ሲቆሽሽም የሚሸሸው ወደ እናቱ ነውና አንተም (ኃጢያትህ ሲበዛ) ወደ እናት ቤተክርስቲያንህ ሽሽና ንስሀ ግባ። ንስሃ ደግሞ ያጣኸውን ለማግኘት የብልጠት መንገድ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ስጦታ በትዕቢት ስለመያዝህ የምትፀፀትበት ሊሆን ይገባዋል። 👉ልጄ የወጣህበት ሰረገላ በመሬት ላይ ቆሟል! መሬት ደግሞ በእግዚአብሔር እጅ ላይ ተቀምጣለች። የተሸከመንን የተሸከመ እርሱ እግዚአብሔር ነው። የኮራንባቸው ነገሮች ሁሉ የእርሱ ናቸው። ከእርሱ በቀር የሚችለን ማንም የለም። ብዙ ዘመን ግን ያለ እግዚአብሔር በራሳችን ለመኖር እቅድ አውጥተናል፤ ያለ እግዚአብሔር መኖር ግን አይቻልም። ያለ እርሱ መኖር ፍፃሜው ሞት ነውና። 👉ልጄ ሆይ ከእግዚአብሔር ተለይተሕ መኖር አይቻልም። እርሱ በነፍስም በሥጋም ገዢሕ ነውና ከእርሱ ጋር ተጣበቅ። መንግስት ችግር ሳይመጣ ወታደሩን በችግር ያሰለጥናል፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን መቆም እንድንችል በትግል ውስጥ ያሰለጥንሃልና አትመረር። 👉ልጄ አንተ የሠማይ ኮኮብ ነህ። የተደበቅህ ቢመስልህም ሁሉ ያይሃል። የክዋክብት ሕልውናቸው ብርሃናቸው ነው። የአንተም ክርስትና ሕልውናው የተለወጠ ሕይወት መሆኑን አስተውል። አዎ የሰማይ ኮኮብ ነህ አገርህም በሰማይ እንደሆነ እወቅ። ስምህ ክርስቲያን አገርህ በሰማይ ዘርህ ክርስትና እናትህ ድንግል ማርያም ንጉስህ ክርስቶስ ነው። 👉ልጄ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል። ብዙዎች ስለጠሉህም ይጠላሃል። አንተ ግን የብዙሃን እውነት ነው ሳይሆን እግዚአብሔር እውነት ነው በሚል መመሪያ ተመራ። ለመልካምነትህ ክፉ ምላሽ ለወሮታህ ከሳሽ ቢነሳብህ የመልካም ነገር ደሞዝ ሰጪ እግዚአብሔር መሆኑን አምነህ ሥራህን ሥራ። 👉ልጄ መልካም ነገርህ ነገ ሊረሳ ይችል ይሆናል መልካም መሆንህንም ሰዎች ላይረዱልህ ይችላሉ እውነተኛ መልካምነት ግን ምስጋናን ሳያደምጡ የሚፈፀም መሆኑን እወቅ። 👉ልጄ ታማኝ ስትሆን ያለፈብሕ ትመስል ይሆናል፤ ግልፅ ስትሆን በቀላሉ ልትጠቃ ትችላለህ፤ ታማኝና ግልፅ መሆንህን ግን እግዚአብሔር ስለሚወደው ብቻ አጥብቀህ ያዘው። 👉ልጄ ልጅነት የለሰለሰ መሬት፣ ወጣትነት ያዝመራ ዘመን፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል። በሽምግልናሕም የምታጭደው የወጣትነትሕን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ። "ምክር ከእማሆይ ፅጌ አሌልቱ ደብረ ሰዋሰው አደሬ ኪዳነ ምሕረት የሴቶች ገዳም 🌻💐🌹 #Join us...🌹💐🌻 #Share #Share #Share #Share 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የኢትዮጲያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን_14ቱ_ቅዳሴያት (The 14 anaphoras) #1) ቅዳሴ ሐዋርያት (anaphora of the Apostles) #2) ቅዳሴ እግዚእ (anaphora if the lord) #3) ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (anaphora of st.John the son of thunder) #4) ቅዳሴ ማርያም (anaphora of st.mary) #5) ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት (anaphora of the 318 orthodox fathers) #6) ቅዳሴ አትናቴዎስ (anaphora of Athanasius) #7) ቅዳሴ ባስልዮስ (anaphora of Basil) #8) ቅዳሴ ጎርጎርዮስ (Anaphora of Gregory of Nyssa) #9) ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ (Anaphora of Epiphanius) #10) ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ (Anaphora of John Chrysostom) #11) ቅዳሴ ቄርሎስ (Anaphora of Cyril) #12) ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Anaphora of Jacob of sarug) #13) ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ (Anaphora of Dioscoros) #14) ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ (Anaphora of Gregory of Nazianzus)

ዓለመ፡፡ ✍ቸር እረኛ እስራኤልን የሚጠብቃቸው ታዛዥ የሆነ ክርስቶስ ለአሕዛብ የመጣ፡፡ እሺ ብሎ ታዛዥ ሆኖ ዓለምን ይቤዥና ያድን ዘንድ ከሰማይ ወረደ፤ መጣ፡፡›› (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ገጽ)፡፡ በማለት ሁሉን የሚገዛ አምላክ ዓለሙን ሊቤዥና ሊያድን እሺ ብሎ በፈቃዱ መምጣቱን መሰከረ፡፡ ሁሉን የሚመግብ፣ የሕይወት እንጀራንና የሕይወት መጠጥን የሚሰጥ ጌታ ወደ ሰርግ ተጠራ፡፡ ለፍጥረቱ ማዕድን የሚያዘጋጅ ጌታ በፈሪሳዊው ስምዖን ቤት ለግብዣ ተጠራ፡፡ ዮሐ 2፤2፣ ሉቃ ፤36-37፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በፈሪሳዊው ማዕድ ላይ የቀረበው የጌታ ማዕድ በሚለው ስብከቱ ‹‹ ንስሓ ስለምትገባው ስለዚያች ኃጢአተኛ ሴት ሲል ከግብዣው ቤት ተገኘ፤ ጌታ ርሀቡ ሥጋዊው ምግብ ሳይሆን የዚያች ኃጢአተኛ እንባ እንጂ… ወደ ፈሪሳዊው ስምዖን ቤት የሄደው በምግብና በመጠጥ ለመዝናናት አልነበረም ሕይወት መድኃኒት የሆነውን ትምህርቱን በማዕዱ ለማቅረብ በመሻቱ ነበር እንጂ፡፡ … ክፉ የተባለው ሰይጣን በመብል ምክንያት አዳምና ሔዋንን ሞትን የሚያመጣ ምክርን እንደመከራቸው እንዲሁ ቸሩ ጌታችን ደግሞ በማዕድ ቦታ ተገኝቶ ሕይወት ሰጪ የሆነ ትምህርቱን ለአዳም ልጆች በማዕዱ አቀረበ፡፡ እርሱ ጌታችን የጠፉትን ነፍሳት ለማጥመድ አሳ አስጋሪ ነበር፡፡ ቀራጮችና አመንዝሮች ወደ ስካርና ሥርዐት አልበኝነት ሲፋጠኑ ተመለከታቸው፤ ሥጋንም ከሚያወፍር የማዕድ ቦታ እነርሱን በማስገር ነፍስን ወደሚያወፍር ጾም ሊያሻግራቸው የቃሉን መረብ በማዕዱ ውቅያኖስ ላይ ጣለው፡፡››በማለት ገለጸው፡፡"ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም" 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 #JOIN #JOIN #JOIN #JOIN 🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻 🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻 🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻

✍☞⛪️ ነገረ ክርስቶስ ⛪️☜✍ 🌼💓 @EOTC2921 💓🌼 ✍ብርህት፣ ንጽህት፣ ጽድልት፣ የሆነች ቤተክርስቲያናችን ከምታስተምራቸው ትምህርቶች አንዱና ዋነኛው ነገረ ክርስቶስ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ትምህርት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል ወልድ ሲሆን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ ሲሆን በኋላኛ ዘመን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው ሆነ፡፡ እንዲህ እናምናለን፤ እንዲህም እናስተምራለን፡፡(ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ)፡፡ ✍ነገረ ክርስቶስ ማለት ስለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምናምነውን እምነት የምናስተምረውን ትምህርት የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህ ክፍለ ትምህርት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ስለ ጌታችን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚታመነው፣ የሚነገረው፣ የምንመራበት ምንድነው የሚለውን በሚገባ ለመረዳት በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በሊቃውንት፣ በትውፊት የተላለፈውን አስተምህሮ የምናቀርብበት ነው፡፡ አግዚአብሔር አምላካችን የሚታየውን ዓለም ከማስገኘቱ በፊት እስከ ዘላለም ድረስ በአንድነቱና በሦስትነቱ፣ በመለኮቱ፣ በመንግሥቱ አለ፡፡ ከጎሕና ከጽባሕ በፊት፣ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፣ መላእክት ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር አለ፡፡ ሰማያት ሳይዘረጉ፣ የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ፡፡ ከሚንቀሳቀስ እንስሳ በፊት ከሚበሩም አዕዋፍ በፊት፣ ከባሕር አራዊት በፊት፣ እግዚአብሔር በመንግስቱ ነበረ፡፡ አዳምን በእርሱ አምሳልና አርአያ ሳይፈጥረው፣ ትእዛዙንም ሳያፈርስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ ማርያም ሥግው ከአምላክ የተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከባሕርይ የተገኘ ባሕርይ፣ ከሕይወት የተገኘ አዳኝ ከመድኃኒት የተገኘ መድኅን፣ ከገዥ የተገኘ ገዢ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ህላዌ እንደሆነ እናምናለን (መዝገበ ሃይማኖት)፡፡ ከአብ መወለዱም በዚህ ዘመን፣ በዚህ ወቅት፣ በዚህ ሰዓት ተብሎ ዘመን አይቆጠርለትም፤ በሰውና በመላእክት አእምሮም ሊመረመር አይችልም፡፡ ሰውንም ስለማዳን በአባቱ ፈቃድ በእርሱም ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር በድንግልና ተወለደ፡፡ ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠም፡፡ በሚያስደንቅ ትሕትና ሰው ሆነ፤ በሚያስደንቅ ዙፋኑ ለደቀመዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት ጊዜ አገልጋዮች መላእክት ደነገጡ፡፡ ትሕትና ወዳለበት ፍቅር የአሕዛብን እግረ ልቡና ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ መላእክት ደነገጡ (ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘስሩግ)፡፡ ፍጥረቱን ሁሉ ሰብስቦ የያዘና ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግብ ጌታቸው በብብቷ (በክንዷ) ተቀምጦ ጡቷን ሲጠባ ባዩ ጊዜ በአርያም ፈለጉና በዚህ ዓለም እንደ ቀድሞው ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አገኙት፡፡ የጌታን ትሕትና ባዩ ጊዜም ዓይኖቻቸውን ወደ ላይ ወደ አርያም ከፍ ከፍ አደረጉ ክንፋቸውንም ዘርግተው ለሁሉ ጌታ ለአንተ ምስጋና ይገባሃል እያሉ ጌታቸውን አመሰገኑ፡፡ (አንቀጸ ብርሃን) አዳምን ካልታረሰች መሬት የፈጠረው ሔዋንንም ከአዳም ያለእናት የፈጠራት እርሱ ከንጽሕት ድንግል ያለ ወንድ ዘር ተወለደ፡፡ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና ስለዚህ የአዳምን ብድራት ትከፍለው ዘንድ አዳም ያለ እናት ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት ክርስቶስን ወለደች ይህም ድንቅ በሚሆን አንድነት የፍጥረት ሁሉ እኩልነት ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡ (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ከአዳም አጥንት ጎድን ሲነሳ ምንም አካል እንዳልጎደለው እንዲሁ ከድንግል የምትናገር ነፍስን ሲነሳ ማኅተመ ድንግልናዋ አልተለወጠም፡፡ አዳም የጎድን አጥንት ከእርሱ ከተነሳ በኋላ አካል ሳይጎድለው ፍጹም ሆኖ እንደኖረ እንዲሁ ድንግልም ሕጻን ክርስቶስ ከእርሷ ከተወለደ በኋላ በድንግልና ጸንታ ኖረች›› አለ፡፡ ሕዝ 44፤1-3፣ መኃ 4፤12 ነቢያት ስለእርሱ ሰው መሆን ተነበዩ፡፡ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው›› አለ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።›› በማለት ትንቢት ተናገረ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ›› አለ፡፡ (ኢሳ 14 ፣ 9፤6፣ 8፤4)፡፡ ጌታችን በመወለዱ በዲያብሎስ የተያዙትን ማርኳል፣ ሲኦልን በዝብዟልና ስሙ ‹‹ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ›› ተብሎ ተጠራ፡፡ የማይደፈር ግሩም ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን ትሑት ነው፡፡ የማይደረስበት ልዑል ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን የባርያውን መልክ ነሳ፡፡ የማይዳሰስ እሳት ነው፡፡ እኛ ግን አየነው፣ ዳሰስነው፣ ከእርሱም ጋር በላን ጠጣንም (ቅዳሴ ማርያም)፡፡ ሁሉ በእርሱ የተፈጠረና ሁሉን ሚመግብ ሁሉ በእጁ የተያዘ መላእክት የሚታዘዙለትና የሚያገለግሉት፣ እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል ነኝ አለ (ሉቃ 22፤27)፡፡ በአዳም ምክንያት የጨለመውን ልቡናችንን ለማብራትና በእርሱ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኖ የመጣ (ዮሐ 12፤16)፡፡ ጨለማን ያስወገደ ብርሃን የሃይማኖትና የጽድቅ ጣሪያዋ (ጠፈሯ)፣ ሃይማኖትም ወንጌልም፣ በብዙ ድካም እርሱን ደስ ያሰኙት የሚወርሱት፣ የሃይማኖት ገንዘብን ይዘው በሠርክ የሚገቡበት መንግስተ ሰማያት እርሱ ነው (ሉቃ 17፤21፣ መልክአ ኢየሱስ)፡፡ ክብርና ምስጋና ይግባውና የእኛን ሞት ሞቶ የእርሱን ሕይወት የሰጠን፡፡ ድዳ ለነበሩት ቃል፣ ለተሰበሩት ምርጉዝ፣ ለዕውራን ብርሃን፣ለሐንካሶች መሄጃ፣ ለለምጻሞች የሚያነጻቸው ሆነ፡፡ በዴዌ የተያዙትን አዳነ፣ ደንቆሮዎችን ፈወሰ፣ ሞትን ዘለፈው ጨለማንም አሰቃየው፡፡ ብርሃን ኅልፈት የሌለበት፣ ፀሐይ፣ የማይጠፋ ፋኖስ፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ፣ በተወሰነ በቁርጥ ፈቃድ ለዓለም ጌጥ ሁሉን የፈጠረ፣ ሰውን ለማዳን ለሁሉ የተገለጠ፣ ነፍሳችንን የመለሳት እርሱ ነው (ኪዳን ዘነግህ)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ምንስ እላለሁ ምንስ እናገራለሁ ከዘመን በፊት የነበረ እርሱ ትንሽ ሕጻን ሆኗልና ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ›› በማለት የጌታን ትሕትና አደነቀ፡፡ ነፋሳት የሚታዘዙለት፣ መላእክት የሚላላኩት እርሱ ለእናቱና ለዘመዶቹ እየታዘዘ አደገ፡፡ ሁሉን አዋቂ ሲሆን አልአዓዛርን የት ቀበራችሁት ብሎ ጠየቀ፤ እርሱ የሕይወት ውሃ ሲሆን ከሳምራዊት ሴት ውሃ ለመነ፡፡ ምራቅ ከጭቃ ጋር ለውሶ እውር ያበራ እርሱን አይሁድ ምራቅ ተፉበት፡፡ ጠባቂ አጥተው ለባዘኑት መልካም እረኛ ሆኖ መጣ ስለበጎቹም ነፍሱን ሰጠ፡፡ (ዮሐ 1፤11) ቅዱስ ያሬድ ‹‹ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለእስራኤል ዘመጽአ ውስተ ዓለም ተአዛዚ ከዊኖ ክርስቶስ ለአሕዛብ፡፡ ኦሆ ብሂሎ ተአዛዚ ከዊኖ ወረደ ወመጽአ ለአድኅኖ… ከመ ይቤዙ ወያድኅን

መድኃኔዓለም_ክርስቶስ_-_Medhanialem_Kiristos.3gp1.28 MB

#መድኃኔዓለም_አዳነን መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/ ደስ ይበለን /2/ እልል በሉ /2/ አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/

መድሀኒአለም_ስምህ_ገናና_ዘማሪ_ዩሐንስ.3gp3.34 MB

✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✞ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ምስጢረ_ስላሴ_በጥቂቱ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• እኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የእግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ በሆነው በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡ #አንድ_ሲሆን_ሦስት_ሦስት_ሲሆን_አንድ_በአካል_ሦስት_ሲሆን_በመለኮት_በአንድ_አምላክ_በሆነው_በልዑል_እግዚአብሔር ብቻ ነው የምናምን፡፡ ይህ ምስጢር ስጋን በለበሰ ህሊናችን ተመራምሮ ማወቅ አይቻልም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ካልሆነ በስተቀር፡፡ ለዛም ነው ቤተ ክርስቲያናችን አምስቱ አዕማደ ምስጢራትን ስታስተምር በመጀመሪያ ምስጢረ ስላሴን መማር እንዳለብን ያስቀመጠችልን፡፡ ምስጢር ማለት፦ እጅግ ጥልቅ፣ የተሰወረ፣ የረቀቀ፤ ከመሆኑ የተነሳ #ምስጢር ይባላል፡፡ #ስላሴ ማለት ደግሞ "ሰለሠ" ወይም ሦስት አደረገ ማለት ሲሆን ትርጉሙም፦ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ✞✞✞ #የስላሴ_አንድነትና_ሦስትነት፦ ✞✞✞ ☞✞ #የስላሴ_አንድነት ፦ በአገዛዝ፣ በስልጣን፣ ይህን አለም በመፍጠርና በማሳለፍ፣ በህልውና፣ በመለኮት፣ በልብ፣ በቃል፣ በእስትንፋስ፤ በእነዚህ ሁሉ የመለኮት ባህርይ #አንድ ነው፡፡ #የእግዚአብሔር_ሦስትነት_ስንል፦እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነትም፦ በስም፣ በግብር፣ በአካል ነው። ☞✞ እግዚአብሔር #በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍ፡1፥2 ፣ ምሳ፡30፥4" ። ☞✞ እግዚአብሔር #በግብር ሦስት ነው ስንል፤ ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦ መውለድና ማስረጽ =የአብ፤ መወለድ=የወልድ፤ መስረጽ =የመንፈስ ቅዱስ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝ፡2፥7" ☞✞ እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ #ለአብ፦ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው። #ለወልድ ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ። #ለመንፈስ_ቅዱስ ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው። ☞✞ የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም፦ #አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው። #ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝ፡2፥7" #መንፈስ_ቅዱስ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። "እዮ፡26፥13" ✞በመጽሐፍ_ቅዱስም ከበቂ በላይ ሁኖ ተገልፆልናል፡፡ ዘፍ፡1፥26 ፣ ዘፍ፡11፥7 ፣ ኢሳ፡6፥1-3 ፣ ኢሳ፡48፥16 ፣ ማቴ፡3፥16 ፣ ማቴ፡28፥19 ሉቃ፡1፥35 ፣ ዮሐ፡14፥25 ፣ ማቴ፡21፥18 ፣ 1ኛ ቆሮ፡12፥3 ፣ 2ኛ ቆሮ፡13፥14 ፣ ዘፍ፡3፥22 ፣ ማር፡10፥6 ፣ ማር፡10፥18 ፣ ዘፍ፡1፥3 ፣ ዘፅ፡5፥1 ፣ ዘፅ፡7፥17 ፣ ኢያ፡3፥17 ፣ ሐዋ፡1፥23 ወዘተ.... ከዚህም በላይ ስለአንድነትና ሦስትነታቸው እናገኛለን፡፡ የእግዚአብሔር አብ በረከት፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣ የእመቤታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞

🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 #ልብ_ብለህ_አስተውል 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 #አትመኝ፦ እንደ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ትሆናለህ፡፡ ዘፍጥ 3÷1-8 #አትቅና፦ እንደ ቃየል ወንድምህን ትገላለህ፡፡ ዘፍጥ 4÷1- #አትስከር፦ አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ፡፡ ዘፍጥ 19÷30-38 #ዓለምን አትመልከት፦ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ፡፡ ዘፍጥ 19÷22-23 #በአባትህ አትሳቅ፦ እንደ ካም ትረገማለህ፡፡ ዘፍጥ 9÷20 #እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርዖን ትሰጥማለህ፡፡ ዘፀ 14÷28 #በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ ትገባለህ፡፡ መጽ.አስቴ 7÷1 #ትዕቢተኛ አትሁን፦ እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡ 2ነገ:19÷35 #ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ፡፡ መጽ.መሳ 16÷15 #አትዘሙት፦ እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል፡፡ 1ነገ 11÷1-8 #ሥልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም #በአባትህ ላይ ትነሣለህ፡፡ 2ነገ ሳሙ 15÷13-17 #ገንዘብን አትውደድ፦ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል፡፡ ማቴ:26÷14-16 ☞☞☞✞ @EOTC2921 ✞☜☜☜ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 ✞✞#መንፈሳችን_በፀሎት_እንዲበረታ_አበው_እንዲህ_ይመክሩናል✞✞ 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 ☘ 1. ‹‹ጸሎት የማያፈቅር ሰው ብታይ ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ፣ወደ እግዚአብሔር የማይጸልይ ከሆነ በመንፈሳዊነቱ ሞቷል….ህይወትም የለውም›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ☘ 2. ‹‹ጸሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሏል›› የሶሪያው ማር ይስሐቅ ☘ 3. ‹‹ጸሎት አእምሮን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነው ›› የሶሪያው ማር ይስሐቅ ☘ 4. ‹‹ጸሎት ጸጋን ይጠብቃል፣ቁጣንም ያሸንፋል…ትዕቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል›› የሶሪያው ማር ኤፍሬም ☘ 5. ‹‹የመንፈስ ፍሬዎችን ያለ ፀሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ☘ 6. ‹‹ጸሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግበት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ☘ 7. ‹‹በጸሎት ግዜ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገርክ አይደለምን??እንዴት ያለ መብት ነው!!!›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ☘ 8. ‹‹ጸሎትን ለማድረግ አታቅማማ፣ሥጋ ከመብል(ከምግብ) በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች›› አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ ☘ 9. ‹‹ያለ ጸሎት የምናደርገው ወይም የምንናገረው ነገር መጨረሻው ውደቀት ነው፡፡ፍጻሜው ኃጢአት ወይም ጉዳት ነው፡፡በማናውቀው ምስጢራዊ በሆነ መልኩ ሲጎዳን እንመለከተዋለን›› አባ አጋቶን ☘ 10. ‹‹ሰው እራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካልጸለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም›› አባ አጋቶን

#ቅዱስ #ዮሐንስ #አፈ #ወርቅ:- ወዳጄ ሆይ! የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡ አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና #ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#ወዳጄ ሆይ 👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀 🦎እንደ እስስት ጸባይህን አስር ጊዜ አትቀያይር/you have to be a constant fashion, 🦆እንደ እርግብ ለዚህም ለዚያም አትደንግጥ፤ 🐕እንደ ውሻ አትለማመጥ፤ 🦇እንደ ቁራ ዝም ብለህ አትጩህ፤ 🐖እንደ ጅብ ሆድህን ብቻ አትውደድ፤ 🐫እንደ ግመል ሽንት ኀላ አትቅር፤ እንደ ፍየል ጥቅምህን ብቻ አታሳድድ፤ 🐏እንደ በግ የዋህ እንጂ ጅል አትሁን፤ 🐅እንደ አንበሳ ክብርህን ጠብቅ፤ 🐪እንደ አህያ ጠንክረህ ስራ፤ 🐝እንደ ንብ እና ማር ተፈላጊና ጣፋጭ ሁን፤ 🐘እንደ ዝሆን እራስህን አግዝፈህ አትይ፤ ✌️እንደ ሸክላ ተሰባሪ መሆንህንም አስብ/አትዘንጋ፤ 🦋እንደ ቢራቢሮ ሁሉም ጋር አትብረር በአንድ ተወሰን፡፡ ስለሁሉም ነገር እግዚአብሄር ይመስገን። @EOTC2921

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክEOTC2921 #በመንፈሳዊ ሕይወትህ ለውጥ እንዲኖርህ #1ኛ የፀሎትን ህይወት ተለማመድ ተጠቀምበትም፣ #2ኛ ከመንፈሳዊ አባቶችና ሊቃውንት መ/ራን ምክርና ትምህርት አትራቅ #3ኛ ከቅዱሳት መፃህፍት ጋር ያለህን ግንኙነት አዘውትር፣ #4ኛ የምትውልባቸውን ቦታዎች ፥የምታነባቸውን መፃህፍት፥የምትመርጣቸውን ባልጀሮችህን ምረጥ፤ለመንፈሳዊ ህይወትህና ለሌሎች ወንድሞችህና እህቶችህ የሚያሰናክሉ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ፣ #5ኛ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ መሆንህን ዘወትር አትዘንጋ፣ #6ኛ ሃፍረትንና ፍርሃትን አስወግድ፥በራስህ ማስተዋልም አትደገፍ፣ #7ኛ አላዋቂነትህን ተቀበል 'እኔ ብቻ' አትበል ውዳሴ ከንቱንም አትፈልግ፣ #8ኛ ለሰራሃው ሃጢአት ሳትዘገይ ንስሃ ግባ፣ #9ኛ ልበ ደንዳናነትንና አመፀኛነትን ከአንተ አርቃቸው፣ #10ኛ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ለመኖርና የቃሉ ሙላት በውስጥህ ኖሮ ከክርስቶስ ጋር መኖርን ተለማመድ በቃሉም ፀንተህ ተገኝ፣ #11ኛ የቅዱሳንን ተጋድሎና ፍቅር በመመልከት እነርሱን ለመምሰል ትጋ፣ #12ኛ ከዚህ በፊት የነበርክበትን የሃጢአት ህይወት ኮንነው #13ኛ ሰዎችን/ባልንጀራህን አፍቅር ከጥላቻም ራቅ፣ #14ኛ ነገርን ሁሉ ለበጎነው ብለህ ተቀበል። ጌታ ሆይ ይህን እንድናደርግ እርዳን አሜን!!! ☞@EOTC2921

#የልዳው_አንበሳ የቤሩቱ ኮከብ የልዳው አንበሳ ሦስት ጊዜ ሞቶ ጊዮርጊስ ተነሳ/2/ #አዝ........ በተጋድሎ ጸና........ቅዱስ ጊዮርጊስ በእውነት መሰከረ...ቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያሉ ጊዮርጊስ......ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰይፍ ተመተረ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ የልዳው አንበሳ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠላት አይገዛህ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይጣንን ተዋጋው..ቅዱስ ጊዮርጊስ ጎልማሳው ሥጋህ...ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ.......... ዲድያኖስ ተቆጣ....ቅዱስ ጊዮርጊስ ጽናትህን አይቶ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀጣ ተነሳ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ በትዕቢት ተሞልቶ...ቅዱስ ጊዮርጊስ ባንተላይ ወገኑ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታት........ቅዱስ ጊዮርጊስ ከምድረ ገፅ አንተን....ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍፁም ለማጥፋት.....ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ......... በመበለቷ ቤት ..........ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ተአምር ሰራ....ቅዱስ ጊዮርጊስ ምሶሶ አለምልሞ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ እውራን አበራ................ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባት አክሊላትን ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ተቀበለ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ጌታ ፍቅር ..............ቅዱስ ጊዮርጊስ ባደባባይ ዋለ................ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ.......... ዝክርህን ዘክሮ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ስምህን የጠራ......ቅዱስ ጊዮርጊስ በነፍስም በሥጋ....ቅዱስ ጊዮርጊስ የለበት መከራ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ ደራጎንን አጥፋ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ አርቅልን ከኛ........ቅዱስ ጊዮርጊስ በዝሙት በኃጢአት....ቅዱስ ጊዮርጊስ ደርሶብናልና..............ቅዱስ ጊዮርጊስ

🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ተጋድሎ_በኢትዮጵያ_ሊቃውንት 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ❖ የዚኽም ቅዱስ አባቱ በቀጶዶቅያ መስፍኑ አንስጣስዮስ ሲኾን እናቱ ቴዎብስታ ትባላለች፤ የተወለደውም በልዳ በሶርያ ፍልስጥኤም በ፪፻፹ ዓ.ም. ነው፤ ታናሽ ኾኖ ሳለ አባቱ ዐርፏል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ፈረስ ግልቢያን ተምሮ ኻያ ዓመት በኾነው ጊዜ ቢሩት ሀገር በመኼድ በዚያ ሀገር ይመለክ የነበረውን መንፈሰ ሰይጣን ያደረበትን የመኰንኑን ልጅ እንዲበላት የተሰጠውን ዘንዶ በክርስቶስ ስም ከገደለው በኋላ እጅ መንሻ ይዞ ወደ ንጉሠ ፋርስ ኼደ፡፡ ❖ በዚያ ሀገር ግን ነገሥታቱ ጣዖታትን በማምለክ ክርስቲያኖችን ሲያሳድዷቸው አይቶ ዐዘነ፤ ልቡም በክርስቶስ ፍቅር ነድዶ ወደ ሀገሬ አልመለስም ስለ ክርስቶስ ስም እሞታለኊ አለና “ክርስቲያናዊ አነ ወአአምን በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ” (እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው) በማለት መሰከረ፡፡ ❖ ከዚያም ንጉሡ ልብሱን ገፍፈው በዕንጨት ላይ እንዲሰቅሉት፤ ዳግመኛ የዘንባባ እሾኽ የመሳሰሉ ፸ የብረት ችንካሮች ሠርተው በነዚያ እንዲቸነክሩትና ዐጥንቱን ኹሉ እንዲቀጠቅጡት አዘዘ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በትዕግሥት በመኾን “እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል” (ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም) አለ፡፡ ❖ ዳግመኛም በውስጡ ረዣዥም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማን ባጫሙት ጊዜ “ሠጠቅዎ ወመተርዎ ዐሥራዊሁ እስከ ውኅዘ ደሙ ዲበ ምድር ከመ ማይ ወሶበ ስዕነ ሠጊረ ድቡተ ሖረ” ይላል ችንካሮቹ ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ እስኪፈስስ ድረስ እግሩን ዘልቀው ሥሩን በጣጠሱት፤ መኼድም ባልቻለ ጊዜ አጐንብሶ ኼዷል፤ ከዚያም የፈላ የብረት ጋን ውስጥ ከትተው ሰውነቱ በደም እስኪጥለቀለቅ ድረስ ራሱን በመዶሻ ሲመቱት ወደ ጌታችን ጸለየ፤ ያን ጊዜ “ጊዮርጊስ ሆይ ከአንተ ጋር ነኝና ጽና” የሚል ቃል ከሰማይ መጣለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጾ ከሕመሙ ፈውሶታል፡፡ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡ ❖ ንጉሡም ይኽነን ባየ ጊዜ እጅግ የሚያስጨንቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀን አሠርቶ ለቅዱስ ጊዮርጊስ “እመሰ ትሠውዕ ለአጵሎን ትነሥእ ጌራ መንግሥት ወእመሰ ኊልቊ አንተ ከመ ትትልዎ ለክርስቶስ ነጽር ዘንተ መንኰራኲረ ዘግበርኩ ለከ ከመ እግድፍ በውስቴታ ታማስን ሥጋከ” (ለአጵሎን ብትሠዋ የመንግሥትን ዘውድ ትቀዳጃለኽ፤ ግን ክርስቶስን ለማገልገል የቈረጥኽ ብትኾን ሥጋኽን ትፈጭ ዘንድ በውስጧ ልትጣልባት ያዘጋጀኋትን መንኰራኲር ተመልከት) አለው፤ ይኽ ሲኾን ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣሪው ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ እነርሱም ወደ መንኰራኲሩ በመወርወር ፵ ሰዎች ያዞሩት ዠመር ከዚያም ሰውነቱ ለዐሥር ክፍል ተከፋፈለ፤ እነርሱም ሥጋውን በጒድጓድ ውስጥ ቀበሩት፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመምጣት እንደገና ከሞት አስነሣውና ባረከው፡፡ ❖ ርሱም ከሞት ተነሥቶ እንደገና ወደ ከተማ ገብቶ ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ እነርሱም እጅግ ለመስማት የሚከብዱ መከራዎችን አደረጉበትና ሰውነቱን ጨምቀው አንጀቱን ዘረገፉት፤ ከዚያም ሥጋውን አቃጥለው በዕንጨት ቀፎ በማድረግ ይድራስ ወደተባለ ተራራ ወስደው ዐመዱን በትነውት ተመለሱ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመውረድ አራቱን ነፋሳተ ምድር የተበተኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋዎች እንዲሰበስቡ አዝዞ እንደገና ከሞት አስነሥቶታል፤ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በክርስቶስ አምነው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም ብዙ ተጋድሎዎችን ለሰባት ዓመታት ከፈጸመ በኋላ ንጉሡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ በሰይፍ እንዲቈረጥ አዝዞ ወደ መሰየፊያው ቦታ ሲኼድ እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያኖች ጸጥ ይል ዘንድ ጸለየ፤ ወዲያውኑም እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት አቃጥሏቸዋል፤ ከዚያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብዙ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፤ ከዚያም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ራሱን ዘንበል አድርጎ ሚያዝያ ፳፫ በሰይፍ ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል፡፡ ❖ ከአገልጋዮቹ የቀሩት ሥጋውን ወስደው በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ወደ ሀገሩ ልዳ በመውሰድ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በውስጡ አኖሩት፤ ከርሱም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ተገልጠዋል፡፡ ❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌ ድርሰታቸው ላይ፦ “ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ” (የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከኾነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለርሱ ኹሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) ርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል) ይሉታል፨ ❖ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቁ አርከ ሥሉስም የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስን ተጋድሎ፡- “ሰላም ለከ ሰርዌ ሰማዕታት አእላፍ ዘሞገሰ ስምከ በጽሐ መንገለ ኲሉ አጽናፍ በቅድመ ፀሓይ ብሩህ ዘኢየዐርብ ለዘልፍ ሕማምየ ዝሩ ነሢአከ ወጸዊረከ እስትንፋሰ አፍ ጊዮርጊስ ቀሊለ ክንፍ ከራድዮን ዖፍ” (ዘወትር በማይጠልቅ በብሩህ ፀሓይ ፊት በምድር ዳርቻዎች ኹሉ የስምኽ ባለሟልነት የደረሰ የአእላፍ ሰማዕታት አለቃቸው ሰላምታ ለአንተ ይገባል፤ ክንፈ ፈጣን ከራድዮን ዖፍ የተባልኽ ጊዮርጊስ ሆይ የአፍ እስትንፋስን ተቀብለኽና ተሸክመኽ ሕማሜን በትን) እያለ ተማፅኖታል፡፡ ❖ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦ “ሰላም ለጊዮርጊስ ሰማዕት ዘፀሓየ ጽድቅ ዘተአምሪሁ ከመ ኆጻ ባሕር ዘኢይትኌለቊ ኮከበ ክብር ዘማእከለ ሰማይ ወምድር ዘአርአየ ኀይለ በዲበ ሰሌዳ መንበር ብእሲ አዛል ወመስተጋድል ኀያል ዝሕዙሐ ገድል”፡፡ (ገድሉ የበዛ የተትረፈረፈ ኀያል፤ ተጋዳይ ጐልማሳ (ብርቱ) ሰው፤ በተዘረጋ ዙፋን ላይ ኀይልን ያሳየ፤ በሰማይና በምድር መኻከል ያለ የማይቈጠር የክብር ኮከብ፤ ተአምሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ የኾነ፤ የፀሓየ ጽድቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት ለኾነ ለጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፨ ❖ የስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ ደራሲ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ፦ "እምብሩር ወወርቅ ይትበደር ሞገሱ ለጊዮርጊስ ቅዱስ በዲበ ጸዐዳ ፈረሱ ለረዲኦትነ ይምጻእ ወያንሶሱ" (ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም) ይለዋል፨ 👇👇👇👇👇👇👇 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

•••✞ #ባሰማት_ጊዜ_ቃሉን ✞••• •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ስሙ ገብርኤል የተባለ ለድንግል ነገራት መልካም ዜና እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና /2/ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ባሰማት ጊዜ ቃሉን ቅዱስ ገብርኤል በለዛ ድንግል ቀረበች ወደእርሱ ፍፁም ትህትና ይዛ #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ ••• ትጸንሻለሽ ሲላት መላኩ ፍፁም በልቧ ሳትመካ እንደቃልህ ይሁን አለችሁ በቃሉ ተማርካ/2/ #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ ••• የአለም መድኃኒት ነውና ካንቺ እሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ትሰይሚዋለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ/2/ #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ ••• እፁብ ድንቅ ነው ሁልጊዜ ለድንግል ማርያም የተሰጣት ክብር የአምላክ እናት ሆና መመረጥ ከሴቶች መካከል /2/ #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ ••• ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ይገባሻል ላንቺ ክብርና ምስጋና የፍጥረታት ጌታ ሁልጊዜ ካንቺ ጋር ነውና /2/ #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••  •••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••