ar
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

الذهاب إلى القناة على Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

إظهار المزيد
4 374
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
ሀለዉ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ወተቀበልዋ ኲሎሙ ነፍሳተ አበው እለ አዕረፉ እምአዳም እስከኔሁ ወሰገዱ ላቲ እንዘ ይብሉ ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘፈጠረ ለነ ኪያኪ ሥጋ እምሥጋነ ወዐፅመ እምዐፅምነ” ይላል መላእክት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉበትን የጻድቃን የማረፊያቸውን ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ ወደ ገነት አሳረጓት፤ በዚያም ከአዳም ዠምሮ እስከዚያው ያረፉ ያባቶች ነፍሳት ተቀብለዋት “ከዐፅማችን አንቺን ዐጥንት ከሥጋችን አንቺን ሥጋ ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባው” እያሉ የአክብሮት ስግደት ሰግደውለታል፡፡ ❖ ከዚያም መላእክት የጻድቅ ሰው ነፍስ ከሥጋው ሲለይ ያለውን ፍጹም ክብርና የሚወርሰውን የገነት ርስቱን መላእክት ካሳዩዋት በኋላ፤ ኃጥኣን ነፍሳቸው ከሥጋቸው ሲለይ ያላቸውን ጭንቅ ነፍሳቸው በሲኦል የምትቀበለውን ከፍተኛ መከራ አሳዩዋት፤ “ወሶበ ተስእኖሙ አምስጦ ይቤሉ እንዘ ይኬልሑ ኦ እግዝእትነ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን ንዒ ኀቤነ ከመ ትፍትሕነ እማእሰሪሁ ለሰይጣን ወኢትኅድግነ” ይላል ለማምለጥ ባልተቻላቸውም ጊዜ “የመድኅን እናቱ የብርሃን መገኛ እመቤታችን ሆይ ከዚኽ ከዲያብሎስ ቊራኝነት ታላቅቂን ዘንድ ድረሺልን ቸል አትበዪ” እያሉ ምልጃዋን ሽተው በታላቅ ጩኸት ያለቅሱ ዠመር፡፡ ❖ ያን ጊዜ ርኅርኅት የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ወይ ሎሙ ወአሌ ሎሙ መኑ እምዜነዎሙ ለውሉደ ሰብእ ኢይምጽኡ ዝየ” (ወዮላቸው ወዮታ አለባቸው ወደዚኽ እንዳይመጡ ለሰው ልጆች ኹሉ ማን በነገራቸው) እያለች ስታለቅስ፤ መላእክትም ለርሷ “ኢትፍርሂ ኦ ማርያም እስመ እግዚአብሔር ምስሌኪ ወምስለ እለ የአምኑ ብኪ” (እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ስለኾነና ባንቺ አማላጅነት ከአመኑት ኹሉ ጋር ስለ አለ አይዞሽ) በማለት ነገሯት፡፡ ❖ ርሷም “እስእለከ እግዚኦ ወአስተበቊዐከ በእንተ ኲሉ ዘየአምን ብየ ረስዮ እግዚኦ ግዑዘ እምሲኦል ተዘኪረከ ረኃበ ወጽምዐ ወኲሎ መከራ ዘረከበኒ ኀቤከ ወምስሌከ” (አቤቱ በኔ ቃል ኪዳን ስላመነ ኹሉ እማልድኻለኊ እለምንኻለኊ፤ መራቤን መጠማቴንም ካንተ ጋር በምድረ ግብጽ ያገኘኝን ረኃብና ጥም ኹሉ አስበኽ አቤቱ ወደ ሲኦል ከመውረድ ነጻ አድርገው) በማለት ወደ ልጇ ፍጹም ልመናን አቀረበች። ❖ ጌታችን ተገልጾላት “ይኩን በከመ ትቤሊ እፌጽም ለኪ ኲሎ መፍቅደኪ አኮኑ ተሰባእኩ በእንተ ዝንቱ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ከመ ኢይሔሱ ኪዳንየ” (የለመሺዉን ኹሉ ይደረግልሽ፤ የምትፈቅጂውን ኹሉ እፈጽምልሻለኊ የለመንሺዉን ኹሉ ላደርግልሽ ሰው ኹኜአለኹና፤ መሐላዬን እንዳላፈርስ አማንየ በርእስየ ብዬ በራሴ ማልኹልሽ) ሲል ለእናቱ የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳንን ገብቶ ገብቶላታልና በዓሉ “ኪዳነ ምሕረት” በመባል ይታሰባል:: ❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በዝማሬው ላይ ጌታ ለእናቱ ስለገባላት ቃል ኪዳን፡- ✍ “ይቤላ ለእ ማርያም እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተካየድኩ ምስሌኪ ኪዳነ ምሕረት ከመ አድኅን ዘተአመነኪ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ ዘመሐልኩ አነ ለኖኅ ገብርየ ወለአብርሃም ፍቁርየ፤ ዘመሐልኩ አነ ለዳዊት ኅሩይየ ብእሲ ምእመን ዘከመ ልብየ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ በቅዱስ ሥጋየ ወበክቡር ደምየ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ ከመ ኢይሔሱ ማእኰትየ” ✍(ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያምን እንዲኽ አላት በምልጃሽ ያመነብሽን አድን ዘንድ ካንቺ ጋራ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተጋባኊ፤ ለአገልጋዬ ለኖኅና ለወዳጄ ለአብርሃም ቃል የገባኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ እንደ ልቤ ለምለው ለታመነው ለዳዊት የማልኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ በቅዱስ ሥጋዬና በክቡር ደሜ የማልኊ እኔ ምዬ እንደማልከዳ ማልኹልሽ) በማለት ጽፎታል፡፡ [በቀራንዮ ከፈጣሪያችን የተቀበልንሽ ስጦታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን] ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ኪዳነ ምሕረት ✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ቃል ኪዳን” የሚለው ቃል 257 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፤ ኪዳን ማለት ቃል “ተካየደ” ከሚለው ከግእዝ ቃል የወጣ ሲኾን “ተዋዋለ፣ ተስማማ፣ ተማማለ” ማለትን ሲያሳይ እግዚአብሔር ሰውን ከማፍቀሩ የተነሣ ለሰው ልጅ እንደ ባልንጀራ አድርጎ መሐላን ይምላል፣ ቃል ኪዳንም ይገባል፡፡ ❖ ክቡር ዳዊት በመዝ 88፡2-3 ላይ “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” እንዳለ ከኹሉም ቅዱሳን በላይ ኾና ሰማይ ምድር የማይወስኑትን አምላክ በማሕፀኗ ለመሸከም፣ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚሸከሙትን ሰማያዊ መለኮትን በዠርባዋ ለማዘል፣ በክንዷ ለመታቀፍ፣ ሰማይ ምድር ከፊቱ የሚሸሹትን የባሕርይ አምላክን በከናፍሮቿ ለመሳም፣ ፍጥረታትን ኹሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሓይ አብስሎ የሚመግበውን፤ ለቅዱሳን መላእክት ርሱ የገለጸላቸው ምስጋና ምግብ ኹኗቸው እንዲኖሩ ያደረገውን ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለውን እግዚአብሔር ወልድን የድንግልና ጡቶቿን ለማጥባት ከተመረጠች ከእናቱ ጋር የገባው ጽኑዕ የምሕረት ቃል ኪዳን እጅግ ልዩ እና ለኃጥኣን ኹሉ ተስፋ የሚኾን ነው፡፡ ❖ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤልም በአምላክ እናት ፊት ቆሞ “ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝተሻልና አትፍሪ” በማለት ከፍጡራን ወገን ማንም ሊያገኘው የማይችለውን ይኸውም በልዑል እግዚአብሔር ዘንድ መወደድን በማግኘት ከባለሟልነት ኹሉ የላቀ ባለሟልነት ይኸውም የአምላክ እናት የመኾንን የማማለድ ልዩ ጸጋና ክብር እንደተሰጣት ነግሯታል፡፡ ❖ መልአኩ በዚኽ ምስጋናው ላይ “ሞገስን አግኝተሻልና” አለ እንጂ “ወደ ፊት ታገኛለሽ” አለማለቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንቱኑ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተጠበቀችና በልዑል የተመረጠች መኾኗን የሚያረጋግጥም ነበር፡፡ ከዚኽ ከተሰጣት ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ልጇን በማሳሳብ ውሃው ወደ ወይን እንዲለወጥ አስደርጋለች (ዮሐ 2፡1-10)፡፡ ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እንደምናነብበው በአምላካቸው ፊት ባለሟልነትን ያገኙ ብዙዎች ቅዱሳን ቢኖሩም ቅሉ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ግን ለነዚኽ ኹሉ ቅዱሳን ሰማያዊ ክብርን ቃል ኪዳንን የሰጠውን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና በመውለዷ “ወላዲተ አምላክ” የመባል ታላቅና ልዩ ባለሟልነት ተሰጥቷታልና የርሷ ክብር ከማንም ቅዱሳን ክብር ጋር ፈጽሞ የማይነጻጸር ነው፡፡ ❖ ከ 432-447 ዓ.ም ሴሌኡሲያ ላይ ጳጳስ የነበረው ሊቁ ባስልዮስም እግዚአብሔር ለእናቱ የሰጣት ልዩ ባለሟልነትን ከቅዱሳን ጋር በማነጻጸር ሲጽፍ “What encomiums can we offer her as she deserves, when everything of this world is beneath her merits?...” (የሚመጥናትን ምን ዐይነት ልዩ ምስጋና እናቅርብላት? የዚኽ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር “ዓለም አልተገባቸውም” (ዕብ ፲፩፥፴፰) ካላቸው፤ ለአምላክ እናትማ ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሓይ ለኾነችው ለርሷ ምን ልንል እንችል ይኾን? (ራእ ፲፪፥፩)... ምን ምስጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናንና አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነ አስተውል፤ ታዲያ የአምላክን እናት ታላቅነት ኹሉም ሰው እንደምን አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ላገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፤ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፤ ጴጥሮስ በጥላው ካደነ (የሐዋ ፭፥፲፭)፤ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ (የሐዋ ፲፱፥፲፩)፤ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? ✔ ለቅዱሳኑ ይኽነን ያኽል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሰደገችው እናቱማ ምን ያኽል ይሰጣት ይኾን? በምን ዐይነትስ ስጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ “ክርስቶስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ” ስላለው ብፁዕ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቊልፍ ከተሰጠው (ማቴ ፲፮፥፲፮-፲፱)፤ ርሷ ከኹሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች (ብፅዕት) አትኾን? (ሉቃ ፩፥፵፭)፤ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ “ምርጥ ዕቃ” ከተባለ (የሐዋ ፱፥፲፭)፤ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች ርሷ ምን ዐይነት ልዩ ዕቃው ትኾን? ✔ ነገር ግን ስለርሷ ብዙ እናገራለኊ ብዬ ስለክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኊ ስለዚኽ ካኹን ወዲኽ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጬአለኊ) በማለት በእግዚአብሔር ፊት የተሰጣት ባለሟልነት ፍጹም እንደኾነና ከቃላት በላይ እንደኾነ አስተምሯል፡፡ ❖ ዳግመኛም ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን ካገኙት ሞገስ የተነሣ ወደ ፈጣሪያቸው እንዲያማልዱን ስንማጸናቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ግን የአምላክ እናት ናትና ካገኘችው ከዚኽ ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ወደተወደደው ልጇ እንድታማልደን እንማጸናታለን፤ ከዚኽም የተነሣ ነው ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬምም በእሑድ ውዳሴ ማርያም ላይ፦ ✍ “ለኪ ይደሉ ዘእምኲሎሙ ቅዱሳን ትሰአሊ ለነ ኦ ምልእተ ጸጋ…” (ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ኹሉ ይልቅ ትለምኚልን ዘንድ ላንቺ ይገባል፤ አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጪያለሽ፤ ከነቢያትም ከመምህራንም ትከብሪያለሽ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ፤ በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ) በማለት ያመሰገናት፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ካገኘችው ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ፭ሺሕከ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ያለ ዘርዐ ብእሲ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በኅቱም ድንግልና የፀነሰች፤ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በኅቱም ድንግልና የወለደች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በጀርባዋ ያዘለች ርሷ ብቻ ናትና፤ በርሷ አማላጅነት የምናቀርበው ጸሎት ምን ያኽል ታላቅ እንደኾነ በሰዓታት መጽሐፉ ላይ፡- ✍“ወፈድፋደሰ በእንተ ማርያም እምከ እንተ ይእቲ ትምክህተ ዘመድነ …” (ይልቁንም የባሕርያችን መመኪያ ስለምትኾን ስለ እናትኽ ስለ ማርያም አንተን በመፅነስና አንተን በመውለድ ዕድፍ ጒድፍ ስላላገኘው ስለ አልተለወጠ ድንግልናዋና ስለ ተሸከመኽ ማሕፀኗ፤ ስለ ታቀፉኽ ስለ ክንዶቿና፣ ስለ ዳሰሱኽ ስለ እጆቿ፤ ስለ ሳሙኽ ስለ ከንፈሮቿ ስለ አሳደጉኽ ስለ ጡቶቿ፤ ከአንተ ጋር ስለ ተመላለሱ ስለ እግሮቿና፤ ስለ ዐዘለኽ ስለ ጀርባዋ፤ ብሩሃት ስለሚኾኑ ስለ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ስላላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች ስለሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ስለ ተበሠሩ (ብሥራትን ስለ ሰሙ) ስለ ጆሮቿ፤ ከርሷ ስለነሣኸው ሥሮችና ጸጒር፣ ደምና፣ ዐፅም ስለ ነፍስና ሥጋ፤ አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮትነትኽ ጋራ አንድ ያደረግኸው) በማለት እንዳስተማረ፤ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ባለሟልነት እንዳገኘች በብርሃናዊዉ መልአክ የተመሰከረላት የአምላካችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ታማልደን ዘንድ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያልን እንማጸናታለን፡፡ ❖ ይኸውም ታላቁ የነገረ ማርያም መጽሐፍ እንደሚያስረዳን ጌታችን ካረገ በኋላ እመቤታችን ጌታችን ወደ ተቀበረበት ጎልጎታ እየኼደች ትጸልይ ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸው በየካቲት ፲፮ ዕለት ስትጸልይ “አዕረግዋ ውስተ ሰማይ ከመ ያርእይዋ መካነ ዕረፍቶሙ ለጻድቃን ኀበ

✞✞✞ #እመቤታችን_ለልጇ_በቤተልሔም_ያቀረበችለት_ድንቅ_ዝማሬ_በቅዱስ_ኤፍሬም_መጽሐፍ ✞✞✞ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል አንድ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ) ✞❖ አምላክን በኅቱም ድንግልና በቤተልሔም የተወለደች ቅድስት ድንግል ማርያምን በአድናቆት 400 መጻሕፍት የጻፈው ቅዱስ ኤፍሬም አመስግኖ፤ ቅድስት ድንግል በቤተልሔም ልጇን ዐቅፋ በፍቅር እንዴት እንዳመሰገነችው እንደዘመረችለት በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ እንዲኽ ሲል በተመስጦ ገልጾታል፡- ✞❖ ☞ “I was full of wonder at Mary as she gave suck to the provisioner of all races…” (ከርሷ ሕፃን ኾኖ የተወለደውን የኹሉንም ዘር መጋቢ ወተት ስታጠባ በማርያም ላይ ሙሉ በሙሉ ተደንቄ ነበር፤ በዓለሙ ምሉዕ የኾነው ርሱ በብላቴናዋ ማሕፀን ውስጥ ኖሯል፡፡ የድኻ ወላጆች ብላቴና ልጅ በፍቅሩ በርሷ ውስጥ የተወሰነውን የባለጸጋው እናት ኾናለች! በድንግል ማሕፀን ውስጥ እሳት ነበር ግን ነበልባሉ አላቃጠላትም፡፡ ✞❖ የሚያቃጥለውን ፍሕም በፍቅርም ብታቅፈውም፣ ርሱን በክብር ስትይዘው ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰበትም፤ የሚያቃጥለው እሳት ሥጋን ተውሕዶ በማርያም እጆች ውስጥ ታቀፈ፡፡ ከአንድ ብቸኛ ደማቅ ደመና ዠርባ ታላቁ ፀሓይ በጨረሮቹ ተሰብስቧል (ኢሳ ፲፱፥፩)፣ አዳምንና መላውን ዓለም ያስገኘውን ብላቴናዋ እናት እናቱ ኾናለች፡፡ በዕቅፎቿ ውስጥ ይዛው በፍቅር ቃላቶች መዝሙሮችን ትዘምራለች፣ እመቤታችን ልጇን በማምለክ እንዲኽ አለችው፡- ✞❖ “ውድ ጌታ እንዳቅፍኽ ፍቀድልኝ” አለችው፡፡ “አንተ ልጄ በመኾንኽ፣ ለአንተ እዘምርልኻለኊ እናትኽ በመኾኔ ምክንያት አከብርኻለኊ አንተን ወንድ ልጄን ወልጃለኊ ኾኖም ግን አንተ ከእኔ ቀዳማዊ ነኽ፤ እኔን የምትሸከመኝን ጌታ አንተን ተሽክሜኻለኊ፡፡ ✞❖ “አእምሮዬ በአንተ ውስጥ በመደነቅ መደመም ይዞኛል፤ አንተን ላመሰግንኽ እንዲቻለኝ ዐሳቤን አንድ አድርግ፤ እንዴት እስከአኹን አንተ እንደኾንኽ ተደንቄአለኊ በአንተም ውስጥ የተደበቀ ነጐድጓድ አለን፡፡ “ከእኔ ውስጥ እንደ ሕፃን አበራኽ ግን አንተ ከኀሊ ብርቱ ነኽ፤ በትክክል ኢሳይያስ ዐውጆልኽ “ድንቅ” በማለት ጠራኽ (ኢሳ ፱፥፮)፡፡ ✞❖ “አንተ በዚኽ በእኔ ውስጥ ሙሉ ነኽ፤ የአንተ ሙሉ ማንነት በሕፃን አካልኽ ውስጥ ተሰውሮ ዐርፏል፤ ከፍታዎች በመሉ በአንተ ተመልተዋል ግን ጡቶቼ ለአንተ በጣም ትንሽ አይደሉም፡፡ “የአንተ መኖሪያ በእኔ እና በሰማያት ውስጥ ነው፤ ጌታን ስለምወድደው ምስጋና አቀርብለታለኊ፤ ከፍታዎች በእኔ ላይ ይደነቃሉ፤ ኹሉም የተባረክሽ ብለው ይጠሩኛል (ሉቃ ፩፥፵፰)፡፡ ✞❖ “ሰማይ በራሷ በፍቅር ትሸከመኛለች ምክንያቱም ከርሷ የበለጠ ክብር ተቀብዬአለኊ፤ ሰማይ በጭራሽ እናትኽ አልኾነችም ነበር ግን በዚኽ ፈንታ ዙፋንኽ አደረግኻት (ኢሳ ፷፮፥፩)፡፡ የንጉሥ እናት ከዙፋኑ የበለጠ ምን ያኽል የተከበረች እና ሞገስ አላት! እናትኽ እንደመኾኔ እንድዘምርልኽ ፈቃድኽ በመኾኑ በአንተ ለጌታ ምስጋናዬን አቀርባለኊ፡፡ ✞❖ “ምድርን የተሸከምኽ አንተ ከኀሊ የኾንኽ ሆይ ግን አንተን እንድሸከምኽ ፈቃድኽ ኾኗልና ምስጋና ለአንተ ይገባል፤ ባለጸጋው ሆይ ከድኻ ቤተሰብ ከተወለደች ልጅ ወንድ ልጅ ኾነኻልና ምስጋና ለአንተ ይገባኻል፡፡ “ብሉየ መዋዕል ቀዳማዊ የኾንኽ ሆይ ወደ እኔ በሕፃንነት ስለመጣኽ፤ አገንንኻለኊ፤ በጒልበቶቼ ላይ ዐረፍኽ ከፍታዎች ጥልቆች መላው ዓለማት ባንተ የተወሰኑ (የተደገፉ) ሲኾኑ፡፡ ✞❖ “ጡቶቼን ያዝኽ- ግን መሬት፣ ባሕር እና በውስጣቸው ያለው በሙሉ በአንተ ቊጥጥር ውስጥ ነው፤ ሠረገላኽ በአየር ላይ ከፍ ያለ ምጡቅ ነው ግን አንተን ተሸከምኹኽ አንተም በእኔ ላይ ዐረፍኽ፡፡ “ከእኔ ጋር እያለኽ፣ የመላእክት ነገዶች በሙሉ ያመልኩኻል፣ በክንዶቼ ውስጥ ታቃትፈኽ እንዳረፍኽ በመላእክት ትታጀባለኽ፡፡ ✞❖ “ሰማይ ከላይ በአንተ ሙሉ ነው፣ ግን እጆቼ እዚኽ ከታች ተሸክመውኻል፤ ከላይ በእሳት መኻከል ትኖራለኽ፣ ግን ከምድር ያሉትን አታቃጥላቸውም፡፡ “ሱራፌል “ቅዱስ” እያሉ ወዳንተ ይጮኻሉ (ኢሳ ፮፥፫)፤ ስለዚኽ ጌታ እኔ እንዴት ልዘመርልኽ? ኪሩቤል በመደነቅ ውስጥ “ቡሩክ” ብለው የሚጮኹልኽ እንዴት አንተ በመዝሙሮቼ ትከብራለኽ ትመሰገናለኽ? ✞❖ “የእኛ አረጋዊቷ እናት ሔዋን አኹን እኔ ስናገር ሰምታ እንድትመጣ ይኹን? በገነት ውስጥ በጊዜው በራቊት ኹኔታዋ ራሷን የደፋችው ከፍ እንድትል ይኹን (ዘፍ ፫፥፯)፡፡ “ፊቷን ገልጣ ለአንተ ትዘምርልኽ ምክንያቱም በኀፍረት የተከደነ ፊቷ በአንተ ዐልፏልና፤ ሰላምን የመላ ሰላምታ ሰምታ የርሷ ልጅ ዕዳዋን ከፍላላታለችና (ሉቃ ፩፥፳፰)፡፡ “ርሷን ወደሌላ ጐዳና የወሰደው እባብ ከእኔ ማሕፀን ባበራኸው ባንተ ሥር ቊልቊል ተረጋገጠ (ተሰባበረ) (መዝ ፸፫፥፲፪-፲፫)፤ ኪሩብ የያዘው ሰይፍ ባንተ ተወገደ (ዘፍ ፫፥፳፬)፤ የተባረረው አዳምም ዳግመኛ የሚመለስ ኾነ፡፡ ✞❖ “አዳምና ሔዋን አንተን መጠጊያ ያደርጋሉ እና ከእኔ የሕይወት ዛፍ አብቧልና፤ መራራ መኾኗን ባረጋገጠችላቸው ፍሬ ፈንታ ባንተም ላንቃቸው ጣፋጭን አግኝቷልና፡፡ “ወርሰዋት ከተለይዋት በቅጣት የወጡት አገልጋዮች ባንተ ተመልሰዋል (ዘፍ ፫፥፳፫)፤ አንተ ለእነርሱ የክብር ልብስ ኾንኻቸው እነርሱም በዚኽ ዕርቃናዊ ኹኔታቸውን ከደኑ (ሸፈኑ) (ገላ ፫፥፳፯)፡፡ ✞❖ “በሲኦል ተጥተለው ዐዝነው ለነበሩት አንተ ታበራላቸዋለኽ ጨለማውንም ከእነርሱ ትገፍፍላቸዋለኽ፤ ከእኔ ያበራኽ ቀዳማዊዉ ብላቴና ሆይ ባንተ ወጣት ብላቴኖች ኹሉ ይባረካሉ፡፡ “ባንተ የሲኦል እስረኞች ይወጣሉ፤ ባንተ ጨለማው ይበራል፤ ጌታ ሆይ ድኾች ባንተ ይበለጽጋሉ፤ ባንተ ችግረኞችም መትረፍረፍን (በረከትን) ያገኛሉ፡፡ “ባንተ የተራቡ ይጠግባሉ (ሉቃ ፩፥፵፱-፶፫)፤ ባንተ ድምፅ ሙታን ይነሣሉ፤ ሰማይና ምድር ላንተ ያንጐደጒዳሉ፤ የኹሉ ጌታ አንተን የላከ ርሱ አብ ቡሩክ ነው) ብላ የአምላክ እናት ለልጇ ዘመረችለት፡፡ (በረከቷ ከኹላችን ጋር ይኹን አሜን) ምንጭ፦ (Ephraem des Syrers Hymnen de Nativitate, Soghita 2) ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል አንድ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ የታተመ፨ 🙏የቅዱስ ኤፍሬም እመቤት ትባርከን🙏

✞ #ጌታን_በማሕፀኗ_የያዘች_የአምላክ_እናት_እና_ዮሐንስን_በማሕፀኗ_የያዘች_ኤልሳቤጥ_በቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ_መጽሐፍ ✞ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ✞ የእነዚኽ ዘመዳሞች (የኤልሳቤጥና የእመቤታችንን) መልካም ገጠመኝ አኹንም ያስደንቀኛል፤ ውበቱን እገልጥ ዘንድም አንድ ዐሳብ ይጎነትለኛል፡፡ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) እና አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) አንድ አስደናቂ ታሪክ አስተምረውኛል፤ እየተደነቅኊ ስለ ርሱ እናገር ዘንድም ፍቅር ይወተውተኛል፡፡ ድንግሊቱ በፍቅርዋ መካኒቱም በደስታዋ፤ ስለ ኹለታቸውም እሰብክ ዘንድ ፈልገውብኛል፡፡ ርስ በርስ የተያዩት አጽናፋት በተከሥቷቸው እንደሚተያዩት ነበር፣ ✞የየራሳቸው የጊዜ ኹኔታ ቁልጭ ብሎ እንደሚታይባቸው እንደ ምሥራቅ እና እንደ ምዕራብ፡፡ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ምሽት የሚታይበትን፤ በዕድሜው ብዛት (በርጅናው) ብርሃንን የሚሸፍነውንና የሚቀብረውን አጽናፍ ትመስላለች (ዮሐ ፭፥፴፭)፡፡ ብላቴናዪቱም (እመቤታችን) ቀኑን በዕቅፏ ተሸክማ ወደ ምድር የምታመጣውንና፤ የንጋት እናት የኾነችውን ምሥራቅን ትመስላለች (ሕዝ ፵፬፥፪) ፡፡ ✞ በወጣትነት እና በእርጅና ጊዜ የመደነቅ ስሜት ይበዛ ዘንድ ንጋት እና ምሽት የሚተያዩት በፍቅር ነው፡፡ ታላቁን የጽድቅ ፀሓይ (ጌታን) የምትሸከመው ንጋት (እመቤታችን) (ሚልክ ፬፥፪)፣ እና ብርሃንን (ጌታን) የሚያበሥረው ኮከብ (ዮሐንስ) የሚወጣባት ምሽት፡፡፡ ታላቁ ንጉሥ ጌታ በብላቴናዪቱ (በእመቤታችን) ዐድሮ ዘውዶችን ያበጃል፣ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) መንግሥቱን የሚያውጀውን አገልጋይ ትሸከማለች፡፡ ✞ በድንግልና የፍጥረታት ጌታ ይከበራል፤ በመካንነት የሌዋውያን (ወንድ) ልጅ ከፍ ይደረጋል፡፡ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) አዳምን የፈጠረው ቀዳማዊዉን ሕፃን ትሸከማለች፤ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ዛሬ በጋብቻ ውስጥ የተፈጠረውን ሕፃን ትሸከማለች (ሉቃ ፩፥፳፬-፳፭)፡፡ የይሁዳ ብላቴና ውስጥ ያዕቆብ ስለ ርሱ የጻፈው ያ የአንበሳ ደቦል አለ (ዘፍ ፵፱፥፱)፤ በሌዋዊቱ ውስጥ ደግሞ ጥምቀትን የመሠረታት ካህን (ሉቃ ፫፥፫)፡፡ ✞ ከአረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ጋር ስለዚኽ ዐዲስ ፅንስ ሐሤት ታደርግ ዘንድ፤ ድንግል በቅድስና ልቃ እና ተመልታ መጣች (ሉቃ ፩፥፴፱)፡፡ በረከትን (ጸጋን) የተመላችው (እመቤታችን) እና የሌዋውያን ሴት ልጅ የኾነችው (ኤልሳቤጥ)፤ እንዲኹም ምድር በመላ የበለጸገበት የከበረ ሀብት የመሉባቸው ኹለቱ ጀልባዎች ርስ በርስ ተገናኙ (ተያዩ)፡፡ ✞ ኹለት ወላዶች፡- አንደኛዋ ተበሣሪና አንደኛዋ አብሣሪ ኾና፣ የዚያኑ የአንዱን (ተመሳሳዩን) ለዓለም ኹሉ የኾነ የመዳን መልእክት ይዛ፡፡ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) ጐበኘቻት፣ እና አንጸባራቂ በኾነ ሰላምታ ተናገረቻት፤ ወዲያውም በርሷ (በኤልሳቤጥ) ውስጥ ተሸፍኖ ያለው ሕፃን አውቆ በደስታ መዝለል ዠመረ (ሉቃ ፩፥፵፩)፡፡ ✞ ማርያም ሰላምን መናገርዋ ያማረ ነበረ፣ በቅርብ እና በሩቅ ላሉት ሰላምን ዘርታለችና (ሉቃ ፩፥፵)፡፡ ርሷ ለሰው ዘር በሙሉ የኾነ ሰላም እንደመላበት ክቡር ስጦታ ነበረች፣ በጠላትነት ለነበሩት የሚኾን ታላቅ ሰላም (ወሀቤ ሰላም ጌታ) በርሷ ውስጥ ተሰውሮ ነበርና፡፡ ርሷ ራሷ ከላይ ሰላምን እንደተቀበለች፣ እንዲኹ ደግሞ ለዓለም ኹሉ ሰላምን ሰጠች (ሉቃ ፪፥፲፬)፡፡ በርሷ አፍ ሰላም በብዛት ተትረፍርፎ ይነገር ነበር፣ ይኽች ቡርክት የኾነች እንዲኽ ሰላምን ታውጅ ዘንድ የተገባት ነበር፡፡ ሰላም በውስጧ (በማሕፀኗ) ነበረና በከንፈሯ ሰላምን ሰጠች፣ ይኽነን የሰማው ሕፃን ዮሐንስም በደስታ ይፈነድቅ ዠመር (ሉቃ ፩፥፵፩)፡፡ ✞ ገና ሳያየው በፊት ያውቀው እንደነበር በማሳየቱ፣ ሲያየውና “ይኽ ርሱ ነው” ብሎ ሲናገር ነገሩን የሚጠራጠረው አይኖርም (ዮሐ ፩፥፳፱-፴)፡፡ ገና ሳይወለድ ርሱን (ጌታን) ለዓለም አስተዋወቀው፣ ከተወለደ በኋላ ርሱን ሲያውጀው ማንም ከምስክርነቱ እንዳይሸሽ፡፡ በተፈጥሮ ላይ ጌታ የኾነው በብላቴናዪቱ ማደሩ ይገለጥ ዘንድ፣ ተፈጥሮን በማሸነፍ ከተፈጥሮ ውጪ (ዮሐንስ) ስለ ወልድ መሰከረ፡፡ ✞ ስለ ወልድ የኾኑት ነገሮች ኹሉ ለመግለጽ እጅግ ከባድ ናቸው፣ በእምነት ዦሮ ካልኾነም በቀር አይሰሙም፡፡ እነዚኽ ነገሮች ኹሉ ዐዲስ ነበሩና ሰው አልተረዳቸውም ነበር፤ ፍቅር ባለው ሰው በአድናቆት ካልኾነ በቀርም አይታዩም፡፡ ለማርያም አድናቆት ለኤልሳቤጥም ታላቅ ሙገሳ ይገባል፣ ማስተዋል ለሚችል ሰው በኹለቱም ውስጥ ዐዳዲስ መገለጦች አሉባቸውና፡፡ ✞ ስለኹለቱም ለመናገር ቃላት በቂዎች አይደሉም፣ አንደበትም (ንግግርም) ዝም ይላል፤ ከአድናቆት የተነሣ ዝምታ ንግግርን ይውጠዋል፡፡ ቃላት ስለማንኛዪቱ ለመናገር ይበቃሉ?፣ እነሆ ኹለቱም ከንግግር (ከአንደበት ገለጻ) በላይ ናቸውና፡፡ ማርያምን በቀረብናት ጊዜ አንደበት በዝምታ ይዘጋል፣ ምክንያቱም የድንግልናን ማስረገጫዎች (ምልክቶች) በርሱም ያደረውን ሕፃን ይመለከታልና፡፡ ወደ ኤልሳቤጥም ስንመጣ ትንታኔ ይከዳናል፣ ከርሷ ማሕፀን ውስጥ አስደናቂውን ብሥራት ይሰማልና፡፡ ድንግሊቱ ፀንሳለችና እነሆ የመካኒቱም ልጅ በደስታ ይዘልላል፤ ስለ ታላላቆቹ ሕፃናት ዕጥፍ ድርብ መደነቅ ይይዘናል፤ ኧረ በማንኛቸው እንደመም? አንደኛዪቱ (እመቤታችን) ያላገባች ኾና ሳለች ወንድ ሳያውቃት ፍሬ በውስጧ አለ፤ በሌላኛዪቱም (በኤልሳቤጥ) ማሕፀን ውስጥ ገና ያልተወለደ ሕፃን በደስታ ይዘልላል፡፡ ✞ ማንኛዪቱን እናድንቅ፡- ልጅዋ የምሥራች ነጋሪ የኾነውን በዕድሜ የገፋችውን ሴትን፣ ወይንስ ድንግል ኾና ግን ደግሞ ሕፃን በውስጧ የተሸከመችዪቱን ብላቴና? ይኽችኛዪቱ (እመቤታችን) ወንድን ፈጽማ አታውቅም ግን ደግሞ ማሕፀኗ ሙሉ ነው (ማቴ ፩፥፲፰)፣ ያቺኛዪቱም (ኤልሳቤጥ) ልጇ ገና ሳይወለድ በፊት መንገድ ያዘጋጃል (ሉቃ ፩፥፵፬)፡፡ ✞ ያለጋብቻ ውሕደት የኾነችው ርሷ (እመቤታችን) ከንፁሕ ፅንሷ የተነሣ እጅግ ታስደንቃለች፣ ያልወለደችዪቱም (ኤልሳቤጥ) ደግሞ ልጇ ዮሐንስ ብሥራትን ለማብሠር ይላወሳል (ይዘላል)፡፡ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናና ወላዲተ አምላክነት በቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ድርሳን በሚል ርዕስ ካሳተምኹት መጽሐፌ በጥቂቱ ከገጽ 96-97 የተወሰደ [የቅዱስ ኤልሳቤጥና የዮሐንስ በረከት ይደርብን]

✍✍✍ትንቢተ ዮናስ✍✍✍ ምዕራፍ አራት 1.👉 ነበዩ በከተማይቱ መዳን እንዳልተደሰተና እግዚአብሔርም ቅልን ምሳሌ በማድረግ ምህረት መልካም እንደሆነ ያስረዳበት ምዕራፍ ነው፡፡ እ ነ ሆ ዝርዝሩ (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 4) ---------- 1፤ ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፥ እርሱም ተቈጣ። 2፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየና። አቤቱ፥ እለምንሃለሁ፤ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር። 3፤ አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ አለው። 4፤ እግዚአብሔርም። በውኑ ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለ። 5፤ ዮናስም ከከተማይቱ ወጣ፥ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፤ ከተማይቱንም የሚያገኛትን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ተቀመጠ። (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 4) ---------- 6፤ እግዚአብሔር አምላክም ቅል አዘጋጀ፥ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው። 7፤ በነጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፥ እርስዋም ቅሊቱን እስክትደርቅ ድረስ መታቻት። 8፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ ዮናስ እስኪዝል ድረስም ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ሞትን ፈለገና። ከሕይወት ሞት ይሻለኛል አለ። 9፤ እግዚአብሔርም ዮናስን። በውኑ ስለዚች ቅል ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለው። እርሱም። እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል አለ። 10፤ እግዚአብሔርም። አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል። 11፤ እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው። እስካሁን ያቀረብኩላችሁ የዮናስ መጽሐፍ ሲሆን በአራት ምዕራፎችና በአርባ ዘጠኝ የተወሰኑት ቁጥሮች የነበሩት እነዚሁ ነበሩ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ፡፡ .......ተፈፀመ..... ፨፨፨ወስብሐት ለእግዚአብሔር፨፨፨

✍✍✍ትንቢተ ዮናስ✍✍✍ ምዕራፍ ሦስት 1.👉ነብዩ በነነዌ ያሰማውን የንስሐ ስብከትና በዚህም የነነዌ ሰዎች በጾም በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመመለሳቸው የተደረገላቸው ምህረት ተገልጿል፡፡ እ ነ ሆ ዝርዝሩ (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3) ---------- 1፤ የእግዚአብሔርም ቃል ሁለተኛ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ። 2፤ ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ የምነግርህንም ስብከት ስበክላት አለው። 3፤ ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች። 4፤ ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም። በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ። 5፤ የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። 6፤ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3) ---------- 7፤ አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ። ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤ 8፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። 9፤ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? 10፤ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም። ይቀጥላል.......

✍✍✍ትንቢተ ዮናስ✍✍✍ ምዕራፍ ሁለት 1.👉ዮናስ በዓሣ ሆድ ውስጥ ሳለ ያሰማው ጸሎትና በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ቀድሞው ጥሪ መመለሱ በሰፊው ተብራርቶ ይገኝበታል፡፡ እ ነ ሆ ዝርዝሩ (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 2) ---------- 1፤ እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ። 2፤ ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ። 3፤ በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ። 4፤ ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ። 5፤ እኔም። ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ። 6፤ ውኆችም እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠምጥሞ ነበር። (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 2) ---------- 7፤ ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ። 8፤ ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች። 9፤ ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል። 10፤ እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። 11፤ እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፥ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው። ይቀጥላል.......

✞✞✞ #እንኳን_ለጾመ_ነነዋ_በሰላም_አደረሳችሁ ✞✞✞ ✍✍ትንቢተ ዮናስ ✍✍ ምዕራፍ አንድ የሚከተሉትን ዋና ዋና ታሪኮችን የያዘነው፡፡ 1.👉ወደ ነነዌ እንዲሄድ የቀረበለት ጥሪ 2.👉ወደ ተርሴስ በመኮብለሉ የደረሰበት የጉዞ እክል ተገልፇል፡፡ (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1) ---------- 1፤ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ ። 2፤ ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ። 3፤ ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይኰበልል ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፥ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ። 4፤ እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፥ በባሕርም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች። 5፤ መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር። (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1) ---------- 6፤ የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ። ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደ ሆነ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ አለው። 7፤ እርስ በእርሳቸውም። ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እናውቅ ዘንድ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ። 8፤ የዚያን ጊዜም። ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እባክህ ንገረን፤ ሥራህ ምንድር ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ ወዴት ነው? ወይስ ከማን ወገን ነህ? አሉት። 9፤ እርሱም። እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ በሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን እመልካለሁ አላቸው። 10፤ እነዚያም ሰዎች ከእግዚአብሔር ፊት እንደ ኰበለለ እርሱ ስለ ነገራቸው አውቀዋልና እጅግ ፈርተው። ይህ ያደረግኸው ምንድር ነው? አሉት። 11፤ ባሕሩንም ሞገዱ አጥብቆ ያናውጠው ነበርና። ባሕሩ ከእኛ ዘንድ ጸጥ እንዲል ምን እናድርግብህ? አሉት። (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1) ---------- 12፤ እርሱም። ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው። 13፤ ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመለሱ አጥብቀው ቀዘፉ፤ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብዝቶ ይናወጥባቸው ነበርና አልቻሉም። 14፤ ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው። አቤቱ፥ እንደ ወደድህ አድርገሃልና እንለምንሃለን፤ አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳታደርግ እንለምንሃለን አሉ። 15፤ ዮናስንም ወስደው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ። 16፤ ሰዎችም እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ፥ ለእግዚአብሔርም መሥዋዕትን አቀረቡ፥ ስእለትንም ተሳሉ። ይቀጥላል....

✞✞✞ #አሥሩ_የቅድስና_ማዕርጋት ✞✞✞ 1 ጽማዌ 2 ልባዌ 3 ጣዕመ ዝማሬ፣ ንጽሐ ሥጋ ይባላሉ። 4 ኩነኔ 5 ፍቅር 6 አንብዓ ንስሐ 7 ተሰጥሞ፣ ንጽሐ ነፍስ ይባላሉ። 8 ሑሰት 9 ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ 10 ከዊነ እሳት፣ ንጽሐ ልቡና ይባላሉ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የሰው ልጅ በዚህ ምድር ሲኖር በቅድስናና በንጽሕና እያደገ ሲመጣ የሚደርስባቸው አሥር መንፈሳዊ ማዕረጋት አሉ፡፡ እነዚህ አሥር መንፈሳዊ ማዕረጋት በሦስት የሚከፈሉ ሲሆን፡- ንጽሐ ሥጋ ፤ ንጽሐ ነፍስና ፤ ንጽሐ ልቡና ይባላሉ፡፡ አሥሩንም ማዕረጋት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡ 1⃣. ጽማዌ፡- ይህ ማዕረግ የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን ትህትናን፤ ራስን ዝቅ ማድረግን፤ መታገሥንና ነገሮችን በውስጥ ይዞ ማሰላሰልን ወዘተ…ይይዛል፡፡ እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው የዚህን ዓለም ውጣ ውረድ ከማውራት ይከለከላል በብዙ ነገሮች ላይ ዝምታን ይመርጣል፡፡ 2⃣. ልባዌ፡- ይህ ማስተዋልና ልብ ማለትን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች የሚገኙበት ደረጃ ነው፡፡ እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች ልናገር ሳይሆን ልስማ ፤ ላስተምር ሳይሆን ልማር ይላሉ፡፡ የመጽሐፉ ቃል የሚለውን ማስተዋልና አብዝተው ኃጢአታቸውን ያሰላስላሉ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ፡፡ 3⃣. ጣዕመ ዝማሬ፡- እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው አንደበቱን ከንባብ ልቡናውን ከምሥጢር ያቆራኛል፡፡ እዚህ ደረጃ የደረሱ ቅዱሳን አንደበታቸው ዝም ቢል በልባቸው ግን ዝም ብለው አያውቁም ከሰውነታቸውም ንጽሕና አይለይም፡፡ የሚያነቡትን መጽሐፍና የሚጸልዩትን ጸሎት ምሥጢሩን በደንብ እየተረዱት ስለሚያደርጉት አይሰለቻቸውም፡፡ እነዚህ ከ1-3 ያሉት የንጽሐ ሥጋ ማዕረጋት ናቸው፡፡ 4⃣. አንብዕ፡- እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች የጌታቸውን ፍቅር እያሰቡ እስከ ሞትና መከራ የተጓዘውን ጉዞ እያሰቡ ዘወትር ያለቅሳሉ፡፡ ያለምንም ተጽዕኖ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይወርዳል፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት ለዚህ ዓለም ፍላጎታቸው መሟላት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ምሕረትና ቸርነት በመናፈቅ ነው:: 5⃣. ኩነኔ፡- ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ሥጋዊ ፈቃድ ሁሉ ለነፍስ ፈቃድ ይገዛል ፤ ነፍስ በሥጋ ፍላጎት ላይ ትሰለጥናለች፡፡ ምድራዊ (ሥጋዊ) ፍላጎቶች ይጠፉና ሰማያዊ (የነፍስ) ፍላጎቶች ቦታውን ይወርሳል፡፡ 6⃣. ፍቅር፡- ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ማንንም ሳይመርጡ ወዳጅንም ጠላትንም መውደድ ይጀምራሉ፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ያደረገውን ታላቁን የፍቅር ሥራ እርሱን በመምሰል ሕይወት በመኖር በተግባር ይገልጻሉ፡፡ 7⃣. ሁሰት፡- ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ቅዱሳን ባሉበት ቦታ ሆነው ሁሉን ነገር ማየት ይችላሉ፡፡ የቦታ ርቀትና የገዘፉ ቁሶች ሳያግዳቸው ፤ ሁሉን ያያሉ፡፡ እነዚህ ከ4-7 ያሉት የንጽሐ ነፍስ ማዕረጋት ናቸው፡፡ 8⃣. ንጻሬ መላእክት፡- ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ መላእክትን ሲወጡና ሲወርዱ ማየት ይቻላል፡፡ 9⃣. ተሰጥሞ፡- ከዚህ ማዕረግ የደረሰ ሰው በብርሃን ባሕር እየተመላለሰ በምድሪቱ ላይ ያለውን ሁሉ ማወቅ መረዳትና መመልከት ከመቻላቸውም አልፈው ሥሉስ ቅዱስ ከመመልከት በስተቀር በሰማያት ያለውንም ምሥጢር ወደ መረዳት ይደርሳሉ፡፡ 🔟. ማዕረገ ከዊነ እሳት/ ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/፡- ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ሰዎች ሥላሴን በዙፋኑ ላይ ሆኖ እንደ እስጢፋኖስ መመልከት ይጀምራሉ፡፡ እንዲሁም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በአካለ ነፍስ ተነጥቀው ወደ ሰማያት በመውጣት ሰማያትን መጎብኘት ወደ መቻል ይደርሳሉ፡፡ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✝✝✝ ✞✞✞ ✝✝✝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን ✝✝✝ ✞✞✞ ✝✝✝ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ወንድሞቼ፡ሆይ፥የእምነታችኹ፡መፈተን፡ትዕግሥትን፡እንዲያደርግላችኹ፡ዐውቃችኹ፥ልዩ፡ልዩ፡ ፈተና፡ሲደርስባችኹ፡እንደ፡ሙሉ፡ደስታ፡ቍጠሩት፡ ያዕ ፡1፥2-3

✞✞✞ #ዘምር_ዘምር_አለኝ ✞✞✞ ዘምር ዘምር አለኝ ልቤ ተነሳሳ /2/ የአምላኬን ቸርነት እንዴት ብዬ ልርሳ ያደረገልኝን እንዴት ብዬ ልርሳ የሚቃጠለው ስም በፊትህ ምንድን ነው ሰማይ እና ምድር ሁሉም ገንዘብህ ነው ያለኝን ሰብስቤ ባሆረው በፊትህ ዋጋ አይሆንም ጌታ ስለቸርነትህ #አዝ ፨፨፨፨፨፨፨ ይበዛል ይሰፋል የእግዚአብሄር ምስጋና አይቆምም በዘመን ማዕበል ነው እና እንኳን ድንጋይ ቀርቶ ጣርያው ቢናድብኝ ይበዛል ፍሬየ ማንም አይወስድብኝ #አዝ ፨፨፨፨፨፨፨ የጶውሎስ የሲናስ መከራው ቢፀና አልተውም ቅኔውን የአምላኬን ምስጋና ሊያስጥለኝ አይችልም እስር ሰንሰለቴ አለብኝ ውለታ የሰማይ አባቴ #አዝ ፨፨፨፨፨፨፨ የተደረገለት ብዙ የተቀበለ ይኖራል በፍቅሩ እየተቃጠለ ክብሬን ሁሉ ትቼ ልዘምርልህ ይህ ነው ችሎታዬ ላንተ የምሰጥህ

ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት1.96 MB

21-25) ፨፨፨፨ ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውክፈ እምእለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሂቅ እምንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ፨፨፨፨ ( ጌታ ሆይ ከብልፅግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።) ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

ውስጥ ቁሞ በነበ ረ ጊዜ ከእግሮቹ ብዙ ደም ፈሰሰ ከሕዝብ ጋር የቆመ አንድ ሰው ነበረ እርሱም ለምጻምና ዕውር ነበር ከደሙም ወስዶ ዓይኖቹን ቀባ ያን ጊዜ አየ ከለምጹም ነጻ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የምታመን ክርስቲያን ነኝ ብሎ ጮኸ ራሱንም እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘና ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። የከበረ አባ ቢፋሞንንም ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አርያኖስ አዘዘ ቢፋሞንም አገልጋዩን ዲዮጋኖስን እንዲህ ሲል ሥጋውን በሥውር እንዲጠብቅ ደሙንም በበፍታ ልብስ እንዲቀበል ገድሉንም በአውሲም አገር ላሉ ምእመናን እንዲነግር አዘዘው የመከራው ወራት ያልፍ ዘንድ አለውና ከዚህም በኋላ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ብሎ በመስቀል ምልክት አማተበ ወደ ጭፍሮችም ቀርቦ የታዘዛችሁትን ፈጽሙ አላቸው እነርሱም ወደ ሌላ ቦታ ብቻውን ወስደው ራሱን በሰይፍ ቆረጡት ። ከአንገቱም ብዙ ደም ፈሰሰ አገልጋዩ ዲዮጋኖስም ከእርሱ ዘንድ ያለውን በፍታ ዘርግቶ የቅዱስ ቢፋሞንን ደም ተቀበለበት። በዚያም ቦታ እጅግ ጣፋጭ የሆነ መዓዛ መላ ጭፍሮች እስኪያደንቁና እስኪደነግጡ ድረስ ታላቅ ፍርሀት ወረደባቸው ከዚያም ቦታ ሸሹ። ከዚህም በኋላ ምእመናን መጥተው ሥጋውን ወሰዱ ብዙ ሽቱ አምጥተውም በመዘመር በክብር ገነዙት ከከተማም ውጭ ተሸክመው ወስደው ቀበሩት ከመቃብሩም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ አገልጋዩም ያቺን በፍታ ወስዶ ጠበቃት ወደ ሀገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜ የሚፈራ ሆነ ምን እንደሚያደርግም አሰበ የከበረ ቢፋሞንም ተገለጠለትና ለወዳጁ ለቴዎድሮስና ለሀገሩ ሰዎች ዜናውን እንዲነግር አዘዘው እግዚአብሔርም ምእመናን ሰዎችን ላከለት እነርሱም ከእርሳቸው ጋር በመርከብ አሳፍረው ወሰዱት በመርከብም ውስጥ ሳለ የክብር ባለቤት ጌታችን ከዚያች በፍታ በከበረ ቢፋሞን ደም ከታለለችው ተአምራትን ገለጠ አገልጋዩ ዲዮጋኖስም ገድሉን ነገራቸው አደነቁ ጌታችንንም አመሰገኑት እርሱንም ወደ አገሩ ወደ አውሲም አደረሱት ዲዮጋኖስም ለወዳጁ ለቴዎድሮስና ለሀገሩ ሰዎች ሁሉ የገድሉን ዜና ነገራቸው ያቺንም በደም የታለለች በፍታ ሰጣቸው ይህችም የመከራው ወራት አልፎ ደጉ ቈስጠንጢኖስ ነግሦ በሀገሮች ሁሉ በክርስቲያን ወገኖችም ላይ ሰላምና ጸጥታ እስከሆኑ ድረስ በእነርሱ ዘንድ ተጠብቃ ኖረች። እግዚአብሔርም የከበረ የቢፋሞንን ሥጋ ለምእመናን አለኝታና መጽናኛ ለበሽተኞችም የሚፈውስ ኃይል እንዲሆን ሊገልጠው ወደደና በእርሱም በላይኛው ግብጽ በጥማ አውራጃ በቃው ከተማ በጥር ሃያ ሰባት በዚች ቀን በሰማዕትነት የሞተ ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ተጋዳይ ቢፋሞን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ለቢፋሞን ዘነድየ ወተጸነሰ። እንዘ ይዘሩ ንዋዮ እምኀበ አቡሁ ዘወረሰ። ከመ ቤተ ከብካብ የሐውር ኀበ ዓውደ ስምዕ ጌሠ። እንዘ ይለብስ በፍሥሓ ሠናያነ አልባሰ። ወእንዘ ይጼዓን ፀዓዳ ፈረሰ። ሰላም እብል ዘቢፋሞን መድበለ። ኃምስተ ምእተ ወምስለ እሙ ሕውለ እንዘ ይጸመዱ ወእንዘ ይትጋደሉ ገድለ። ትግርምተ መኰንን ረሰዩ ቀሊለ። ወእሳተኒ ነፋሰ ወጠለ። ፨፨፨ =>በዚችም ዕለት የሰማዕታት ትውፍሎን ዮስና የሰርኒስ መታሰቢያቸው ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን። ✞ #ቅዱስ_ኄኖክ_ነቢይ ✞ =>በዚችም ዕለት የያሬድ ልጅ ኄኖክን የመላልኤል ልጅ የቃይናን ልጅ የኄኖስ ልጅ የሴት ልጅ የአዳም ልጅ ኄኖክን መላእክት ይዘው አሳረጉት ይኸውም በመባርቅትና በነፋሳት ላይ ተጭኖ በመብረር ወደ ሰማይ ወስደው ከረቂቃን መላእክት ጋር አኖሩት የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ጸሐፊ ተባለ። እንዲህም አለ ከማደሪያው ከሚወጣው ከቅዱሱና ከገናናው በጸናች ኃይሉ ከሠራዊቱ ጋር በሲና ተራራ ከሚገለጠው ጋር በመነጋገር ተመላለስኩ። ሁሉም ይፈሩ ነበር በውኃ ዳርም ሳለሁ የልመናቸውን መታሰቢያ ጻፍኩ እስከ አንጎላቸሁና ሕልም እንደሚያይ እስከምሆን ይችም በአርሞን ግራና ቀኝ ያለች አገር ናት። በደብር ቅዱስ ለነበሩ ለኃጢአት ለሚተጉ ለሴት ልጆች ይዘልፋቸው ዘንድ ቃል እንደጠራውና እንዳሳየው ተናገረ። እንዲህ አለ በበረድ ደንጊያ ወደ ተሠራ ታላቅ ቤት ቀረብኩ በበረድ ደንጊያ የተሠራ የዚያ ቤት ግድግዳ እንደ ሳንቃ ልዝብ ነው ከዚህ ቤት የሚበልጥም ሌላ ቤት አየሁ ደጃፉም የተከፈተ ነው በእሳት ቅጽርም የተሠራ በክብር ከሁሉ የሚበልጥ ነው። በውስጡም ከፍ ያለ የእግዚአብሔርን ዙፋን አየሁ መልኩም እንደ ውርጭ ነው አጎበሩም እንደሚያበራ ፀሐይ ነው ከዙፋኑም በታች የኪሩቤል ድምፅ ይሰማል። ዳግመኛም ወደ ሰባት ተራራዎች ደረስኩ ሦስቱ በምሥራቅ በኵል ሦስቱ በአዜብ በኵል ናቸው የመካከለኛው ግን ሰማይ ጠቀስ ነው የመላእክትም ጌታ በላዩ አለ። ሌሎች አራት ገጾች ኪሩቤልን አየ ስለ ክርስቶስም እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ የዘመናት አለቃ ወደ ሆነው የሰው ልጅ ተጠራ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የነበረ ሆነ ሁለተኛም ለጻድቃን የጽድቅ በትር ለአሕዛብም ብርሃን ተስፋ ለሌላቸውም አለኝታ ይሆናል አለ። በሰማይ ገጽ ስለሚመላለሱ ብርሃናት እንዲህ አለ አንዱም አንዱ በየወገናቸው በሠለጠኑበትና በተሠየሙበት ጸንተው ይኖራሉ ስለ ነፋሳትም መውጫዎች እንዲህ ብሎ ተናገረ ሦስቱ በሰማይ ገጽ ሦስቱ በምድር ገጽ ሦስቱ በቀኝ ሦስቱ በግራ ናቸው። ስለ አዳምም እንዲህ አለ እነሆ በሬ ከምድር ወጣ ፀዓዳም ሆነ ስለ ሔዋንም ደግሞ ሴት እምቦሳ ከርሱ ወጣች አለ። ስለ ምኵራብም ያንን አሮጌ ቤት እስከሚአሳንሰው ድረስ አየሁ አለ ምሰሶዎቹንም ከውስጡ አወጣ። ሰለ ቤተክርስቲያንም ጌታ አዲስ የበጎች ቤት አምጥቶ እስቲሠራ ድረስ አየሁ ከቀድሞውም ቤት የበለጠ ነው በጎችም ሁሉ በውስጧ ይሠማራሉ አለ። ስለ ምእመናንም የእሊህም በጎች ፀጕራቸው ንጹሕ ነጭ ነው የተበተኑትም ከአራዊት ጋራ ይሠማራሉ ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ገራሞች ሆነዋልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ለኄኖክ እንተ ተመሥጠ በዓውሎ። በአጽናፈ ሰማይ ይርአይ ሙላደ ብርሃናት ኵሎ። እሰከ ዕለተ ሣህል ይከውን ወእስከ መዋዕል ዘተበቅሎ። ኀበ ሞት ኢይበጽሖ ወኀበ ኀዘን ኢይክሎ። በጥበበ አምላክ ክቡተ ወሥውረ ሀሎ። ፨፨፨ ጥር 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረገበት) 2.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ) 3.ቅዱስ አባ ቢፋሞን ሰማዕት 4.ቅዱስ ሰራብዮን ሰማዕት 5.ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት (ከ7ቱ ሊቃናት አንዱ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ 2.አቡነ መባዐ ፅዮን 3.አባ መቃርስ ርዕሰ መነኮሳት 4.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 5.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት 6.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ =>+"+ የተጠራችሁለት ለዚህ ነው፣ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም ፣ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ:: +"+ (1ኛዼጥ. 2፥

ራትንም ጨመሩ። ከዚህም ነገር በኋላ በሰባተኛው ወር አባቱ አረፈ የከበረ ቢፋሞንም ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ምጻዋትን አብዝቶ ሰጠ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም የተጠመደ ሆኖ የከበረ የወንጌልን ትእዛዞች ለመፈጸም ይጋደል ነበር። በዚያንም ወራት የፋርስ ሰዎች በሮም ሰዎች ላይ ጦርነት አስነሥተው ነበር የሮም ንጉሥም በጦርነት ሙቶ መንግሥት ያለ ንጉሥ ተቀመጠች መኳንንቱ እና የመንግሥት ታላላቆች ተሰብስበው ተማከሩ ከሁሉ አገሮችም ተዋጊዎች የሆኑ አርበኞችን ይሰበስቧቸው ዘንድ አዘዙ። ከላይኛውም ግብጽ ልበ ደንዳና የሆነ አንድ ሰው ተገኘ እርሱም ስሙ አግሪጳዳ የሚባል የሰይጣን ማደሪያ የሆነ ፍየሎችን የሚያረባ ነው ወደ አንጾኪያ ከተማም ወስደው ለመንግሥት ፈረሶች ባልደራስ አድርገው ሾሙት። በአንዲትም ዕለት ሁለት ሸምበቆ አንሥቶ በአንድነት አሥሮ ዋሽንት ነፋባቸው በፈረሶች ሰይጣን አደረባቸውና ፈረሶችም እየጨፈሩ ያሽካኩ ጀመር የሞተውም ንጉሥ ሴት ልጅ በቤተ መንግሥት አዳራሽ ሁና በመስኮት ሲዘፍንና ዋሽንት ሲነፋ አግሪጳዳን አይታው እጅግ አማራት ሰይጣንም በልቧ የዝሙትን ፍላጎት ጨመረ ወደርሷም አስጠራችውና አገባችው ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ አሰኝታ አነገሠችው። ታናሽ እኅቷም ታላቂቱ እኅቷ ያደረገችውን በአየች ጊዜ ቀናች እርሷም መክስምያኖስ የሚባል አንድ መኰንን መልምላ አገባች ልብሰ መንግሥትም አልብሳ ንጉሥ አደረገችው መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስም በአንጾኪያና በሮም ተስተካክለው ነገሡ። ከዚህም በኋላ ሰይጣን ተገለጠላቸውና እንዲህ አላቸው ነገሥታት እስከአደረግኋችሁ ድረስ በንጉሡ ሴቶች ልጆች የዝሙትን ፍቅር በልባቸው የጨመርኩ እኔ ነኝ። አሁንም ትእዛዜን ከሰማችሁ በምድር የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉንም በእጆቻችሁ ውስጥ አደርጋቸዋለሁ እናንተም ስገዱልኝ የወርቅና የብር ምስሎችንም ሠርታችሁ አማልክት በሏቸው ስማቸውንም አጵሎን፡ አርዳሚስ ብላችሁ ጥሩአቸው ሰዎችንም ሁሉ ዕጣን እንዲአሳርጉላቸው እንዲሰግዱላቸውም እዘዟቸው አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ ዝጉ የአማልክትንም ቤቶች ክፈቱ ትእዛዛችሁን ሰምተው ለአማልክት የማይሰግዱትን ግን በየአይነቱ በሆነ በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃዩአቸው ራሶቻቸውንም በሰይፍ ቊረጡ። እሊህም ሰነፎች ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ በሰሙ ጊዜ ሰገዱለትና እኛ የአዘዝከንን ሁሉ እናደርጋለን አሉት። በዚያንም ጊዜ በግብጽ አገር ሄሬኔዎስንና አርያኖስን ሁለቱን መኳንንቶች ሾሙ ለጣዖት የማይሰግዱትን ሁሉ እንዲአሠቃዩ አዘዙአቸው። የከበረ አባ ቢፋሞንም ይህን ዜና በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ የሆነውንም እስቲረዳ ድረስ ተሠወረ ወዳጁን ቴዎድሮስንም ጠራውና በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ደማቸውን ያፈሱ ዘንድ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ ከክፉ ነገርም ሁሉ ያድናቸው ዘንድ በአንድነት ጸለዩ። የከበረ ቢፋሞንም በጎ ሥራን አብዝቶ ይሠራ ነበር ወሬውም በንጉሥ መክስሚያኖስ ዘንድ ተሰማ እንዲህ ብለው ከሀዲዎች ነግረውታልና በምስር አውራጃ በአውሲም ከተማ ስሙ ቢፋሞን የሚባል አንድ ሰው አለ እርሱም የነገሥታትን ትእዛዝ የሚተላለፍ አማላክትን የሚረግምና የሚያቃልል ነው። በዚያንም ጊዜ የከበረ ቢፋሞንን ለአማልክት እስከሚዐጥን ድረስ እንዲአሠቃየው ያለዚያም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጥ ንጉሥ ወደ አርያኖስ ደብዳቤ ጽፎ ላከ የእግዚአብሔርም መልአክ የሆነውን ይነግረው ዘንድ ለአባ ቢፋሞን ተገለጠለት በሰማዕትነትም እንደሚሞት እናቱም እንደምትሞት አስረዳው እግዚአብሔርም ያዘጋጀላቸውን አክሊላት አሳየው አገልጋዩን ዲዮጋኖስን ከእርሱ ጋር እንዲወስደው አዘዘው። ያን ጊዜ ተነሣ ወደ እናቱም ገብቶ ያየውን ሁሉ ነገራት እርሷም ይህንኑ ራእይ እንዳየች ነገረችው በአንድነትም ደስ አላቸው ወደ ማደሪያውም ሒዶ እስቲነጋ ድረስ ሊጸልይ ቆመ በነጋ ጊዜ ወደ ወዳጁ ቲዎድሮስ ልኮ አስመጣው ራእይንም እንዳየ ነገረው ከዚህም በኋላ እንዲህ ብሎ አዘዘው የመከራው ወራት ካለፈ በኋላ በዚች አገር አንተ ኤጲስቆጶስነት ትሾማለህና ቤተ ክርስቲያን ሥራልኝ ይህንንም ነግሮት ሰላምታ ተለዋውጠው ተሳስመው ተለያዩ። ከጥቂት ቀኖች በኋላ ወደ አውሲም ከተማ መኰንኑ አርያኖስ ደረሰ የሀገር ታላላቆችንም አቅርቦ ስለ ከበረ ቢፋሞን ጠየቃቸው እርሱ አማልክትን እንደሚረግም ሰምቷልና የሀገር ሽማግሌዎችም ስለ ቅዱስ ቢፋሞን አዘኑ እርሱ በእነርሱ ዘንድ ተወዳጅ ነውና። በዚያንም ጊዜ አባ ቢፋሞን ተነሥቶ ረጂም ጸሎትን ጸለየ ቤተ ሰቦቹንም ሁሉ ተሰናበታቸው ያማሩ ልብሶችንም ለብሶ በነጭ ፈረስ ተቀምጦ የአገር ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወዳሉበትም ሔደ እነርሱም በአዩት ጊዜ አክብረው ሰላምታ ሰጡት ተከትለውትም ወደ መኰንኑ ወደ አርያኖስ ሔደ አርያኖስም አባ ቢፋሞንን በአየው ጊዜ ደስ አለው ከወንበሩም ተነሥቶ ሰላም ላንተ ይሁን ብሎ ሰላምታ ሰጠው ። አባ ቢፋሞንም እንዲህ ብሎ መለሰለት ለምን ሰላም ትለኛለህ የሰላም ትርጓሜው ደስታ ነውና ለእኔ ግን በጌታዬ በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ደስታ አለኝ ለአንተና ለባልንጀሮችህ በሰማያት ደስታ የላችሁም ብሏል መጽሐፍ። አርያኖስም እኔ ክፉ ነገርን እንድትነግረኝ አልመጣሁም ለአማልክት እንድትሠዋ በንጉሡ ደብዳቤ ታዝዤ መጣሁ እንጂ አለው ቅዱሱም መልሶ ይህ አይገባም ትክክለኛውስ ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ለእርሱም እንድንሰግድ ይገባል እሊህ አማልክቶቻችሁ አፍ አላቸው አይናገሩም ዓይን አላቸው አያዩም ጆሮ አላቸው አይሰሙም አፍንጫ አላቸው አያሸቱም እጅ አላቸው አይዳስሱም እግር አላቸው አይሔዱም በአንደበታቸውም አይናገሩም በአፋቸው ውስጥ ትንፋሽ የለምና የሠሩአቸውም እንደነርሱ ይሁኑ እኔ ግን ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያለውን ሁሉ ከፈጠረ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለሌላ አልሰግድም አለው። አርያኖስም ከቅዱስ ቢፋሞን አፍ ይህን ነገር ሰምቶ እጅግ ተቆጣ በየዓይነቱም ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ዳግመኛም በፈረስ ጅራት አሥሮ መላ ከተማውን አስጎተተው እናቱና አገልጋዮቹም ሁሉ ወደርሱ መጡ እነርሱንም ከከበረ የወንጌል ቃል አስተማራቸው ገሠጻቸውም በዚያንም ጊዜ በግልጽ እኛ ክርስቲያን ነን ብለው ጮኹ የመኰንኑን ወንበር ገለበጡ መኰንኑም ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸውና እሳትንም አንድደው በውስጡ በሕይወት ሳሉ እንዲወረውሩአቸው አዘዘ እንዳዘዘውም አደረጉባቸው ቊጥራቸውም አምስት መቶ ነው። ምስክርነታቸውንም እስኪፈጽሙ የከበረ ቢፋሞን ያጽናናቸውና ያስታግሣቸው ነበር እናቱም ልጅዋ ቢፋሞንን በላይዋ እንዲጸልይ ለመነችው እርሱም በመስቀል ምልክት በላይዋ አማተበና በሰላም ሒጂ አላት በዚያንም ጊዜ ሰውነቷን በእሳት ውስጥ ጣለች። ከእነሱ ጋርም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች። የከበረ ቢፋሞንን ግን አርያኖስ ወደ ንጉሥ መክስምያኖስ ሰደደው ንጉሡም የነገሥታትን ትእዛዝ የምትተላለፍ ለአማልክት የማትሰግድ ሥራየኛው ቢፋሞን አንተ ነህን አለው። ቅዱሱም ሥራይን ግን አላውቅም ለረከሱ አማልክትም አልሰግድም አንተና አማልክቶችህ በአንድነት ወደ ገሀነም እሳት ትወርዳላችሁና አለው ንጉሡም ተቆጥቶ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ከማሠቃየትም በሰለቸ ጊዜ ወደ ኄሬኔዎስ ሰደደው እርሱም ወደ አርያኖስ ሰደደው በእነዚያ ቀኖችም ምንም አልበላም። አርያኖስም ወስዶ በብረት ችንካሮች ቸነከረውና ለአማልክት ካልሰገድክ አጠፋሃለሁ አለው ቅዱሱም እርሱንና አማልክቶቹን ዘለፈ ረገማቸውም ከዚህም በኋላ በከተማዪቱ ሁሉ መንገድ እንዲጎትቱትና ከእንዴናው ከተማ ውጭ በእሳት እንዲአቃጥሉት መኰንኑ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት ጌታችንም ያለ ጥፋት በጤና ከእሳት ውስጥ አወጣው የከበረ ቢፋሞንም ከእሳት

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞✞✞ ✞✞✞ #ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር_፳፯ ✞✞✞ ✞ #ቅዱስ_ሰራብዮን_ሰማዕት ✞ => አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ሃያ ሰባት በዚች ዕለት ከግብጽ ደቡብ ከታችኛዪቱ ምስር አውራጃ በብኑዲ ከምትባል መንደር የከበረ ሰራብዮን በሰማዕትነት ሞተ። ለዚህም ቅዱስ ብዙ የገንዘብ ጥሪት እንስሳትም አሉት አብዝቶ መመጽወትንም የሚወድ ነው ስደትም በሆነ ጊዜ የክርስቲያን ወገኖችን ፈልጎ ያሠቃይ ዘንድ መኰንኑ ኄሬኔዎስ በየሀገሩ እንደሚዞር ሰማ ለርሱም ስማቸው ቴዎድሮስና ሁለተኛውም በግ አርቢ ሰርማ የሚባሉ ወዳጆች ነበሩት እነርሱም ተከተሉት ይህም ቅዱስ መኰንኑን ሊገናኘው ከሀገሩ ወጣ መኰንኑንም በአገኘው ጊዜ በፊቱ ቁሞ ከወገኖቹ ጋር በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ሁሉንም አሠራቸው። የሀገር ሰዎችም በሰሙ ጊዜ ሁሉም ተሰብሰቡ መኰንኑን ገድለው ቅዱስ ሰራብዮንን ከእጁ ሊወስዱ ሽተው የጦር መሣሪያ በመያዝ ለጦርነት የተሰለፉ ሠራዊት ሁነው ደረሱ ቅዱሱ ግን ከለከላቸው እንዲህም አላቸው እኔ በጌታዬ ክርስቶስ ስም ደሜን አፈስ ዘንድ በፈቃዴ የመጣሁ አይደለምን መኰንኑም በመርከብ ተሳፍሮ ከዚያ ሔደ ቅዱሳኑም አብረውት ሔዱ። ወደ እስክንድርያ አገርም በደረሰ ጊዜ የከበረ ሰራብዮንን በመንኰራኵር ውስጥ ጽኑዕ ሥቃይን እንዲአሠቃዩት ወደ እሳት ማንደጃም ይጨምሩት ዘንድ አዘዘ። ከዚህም በኋላ ከነዳጅ ድፍድፍና ቅመማቅመም ጋር በወጭት ውስጥ ቀቀሉት የሥጋውንም ሥሮች ቆረጡ በብረት ዐልጋ ላይም አስተኝተው በችንካር ቸነከሩት ይህን ሁሉ ሥቃይም የሚታገሥ ሆነ የእግዚአብሔርም መልአክ ሥቃዩን ከላዩ ይቀበልለት ነበር። ከዚህም በኋላ ከእንጨት ላይ ሰቅለው በፍላፃዎች ነደፉት የእግዚአብሔርም መልአክ እርሱን ከተሰቀለበት አውርዶ በእርሱ ፈንታ መኰንኑን አሥሮ ሰቀለው። የከበረ ሰራብዮንም እንዲህ አለው ሕያው እግዚአብሔርን በክርስቶስ ስም የታሠሩትን ሁሉንም እስከምታወጣቸውና የሞታቸውን ፍጻሜ እስከምታዝዝ አንተ ከእዚህ ከተሰቀልክበት ዕንጨት እንደማትወርድ ዕወቅ። በዚያንም ጊዜ ሁሉንም አውጥተው ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧቸው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ የእነዚህም ሰዎች ቊጥራቸው አምስት መቶ አርባ ነፍስ ሆነ። ከዚህም በኋላ የከበረ ሰራብዮንን ወደ ሀገሩ ከእርሱ ጋር ወስዶ ያሠቃየው ዘንድ ከኀሳቡም ካልተመለሰ እራሱን በሰይፍ ይቆርጥ ዘንድ ኄሬኔዎስ አንዱን መኰንን አዘዘው። መኰንኑም ከርሱ ጋር በመርከብ ወሰደው ሌሊትም በሆነ ጊዜ ወደ አንድ ወደብ ደርሰው በዚያ ተኙ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ያቺ መርከብ ወደ ቅዱስ ሰራብዮን አገር ደረሰች በጥዋትም በነቁ ጊዜ የመሔጃቸው አቅጣጫ ተለውጦ አገኙ እጅግም አደነቁ ወደ ሰራብዮንም እነሆ ይቺ ሀገርህ ናት የሚል ቃል ከሰማይ መጣ ከመርከብም አውርደው ታላቅ ሥቃይን አሠቃይተው ራሱን በሰይፍ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። መኰንኑም ልብሶቹን አውጥቶ ገንዞ ለዘመዶቹ ሰጠው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም እብል ለሰራብዮን ሰማዕት። ዘኵኑን አባሉ በፍልሐተ ቅጥራን ወዘይት። ወሰላም ካዕበ ለማኀበራኒሁ ዐበይት። ምሰለ ቴዎድሮስ ወሰርማ ሱቱፋነ ሕማም ወሞት። ወዕደው አርብዓ ወኃምሳ ምእት። ፨፨፨ †ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ)† =>በዚችም ቀን የከበረ ሐዋርያ ጢሞቴዎስ ከኤፌሶን አገር ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ የሥጋው ፍልሰት ሆነ። ጻድቁ ቈስጠንጢኖስም መንግሥትን በያዘ ጊዜ የከበሩ የሐዋርያትን ሥጋቸውን ከሰማዕታትም ብዙዎችን ከቦታው ሁሉ ወደ ቊስጥንጥንያ አፈለሳቸው ስለ ሐዋርያ ጢሞቴዎስም ሥጋ በኤፌሶን አገር እንዳለ ሰምቶ ካህናትንና ምእመናንን ላከ እነርሱም አፍልሰው ወደ ቊስጥንጥንያ አድርሰው በከበሩ ሐዋርያት ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖሩት። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ለፍልሰተ ሥጋከ በዕለት ዝንቱ። ቈስጠንጢኖስ ታዕካ ኀበ ሐነፀ ሎቱ። ጢሞቴዎስ ረድእ ለቃለ ትምህርትከ ከመ ትምህርቱ። ኢያሕምም ክበድየ ስቴ ማይ ባሕቲቱ። ወይነ ኂሩትከ ውዲ ወቶስሕ ውስቴቱ። ፨፨፨ =>በዚችም ቀን ሳፍራ የሚባል የመልአክ ሱርያል በዓል ነው እርሱም ከነቢይ እዝራ ጋር የኖረ የተሠወረ ምሥጢርንም የገለጠለት ነው እርሱም ስለ ሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር የሚለምን ነው። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ለከ እንተ ረከብከ ሞገሰ። ኀቡአተ ትፍትን ወዘማዕምቅት ከርሠ። ሱርያል መልአክ እንዘ ትስእል መንፈስ። ፍጥረታተ ኵሎ አመ በማየ አይኀ ደምሰሰ። እግዚአብሔር አትረፈ ስማኒተ ነፍሰ ። ፨፨፨ ✞ #ቅዱስ_አባ_ቢፋሞን_ሰማዕት ✞ =>በዚችም ቀን የከበረ ቢፋሞን በሰማዕትነት ሞተ ይህም ከታናሽነቱ ድንግል የሆነ እግዚአብሔርን የሚወድ ለድኆችና ለችግረኞች የሚመጸውት ይህንንም ዓለም ንቆ የተወ ነው። አባቱም ከከበሩ ወገኖች የሆነ ስሙ አንስጣስዮስ የእናቱም ስም ሶስና ነው። እነርሱም መመጽወትን የሚወዱ ክርስቲያኖች ናቸው የጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችንን ድንግል ማርያምን የከበሩ ሰማዕታትንም ሁሉ በዓላት ለድኆችና ለምስኪኖች ምጽዋትን በመስጠት ያከብራሉ የሚኖሩትም በምስር አውራጃ አውሲም በሚባል አገር ውስጥ ነው። እግዚአብሔርም መልኩ እጅግ ያማረ ይህን የተባረከ ልጅ ቢፋሞንን ሰጣቸው በእርሱም ደስ ብሏቸው በጎ መሥራትንና ትሩፋትን አበዙ አድጎ ወደ ዘጠኝ ዓመትም ሲደርስ ያሰተምረው ዘንድ እግዚአብሔርን ለሚፈራ አንድ ቄስ ሰጡት እርሱም ተቀብሎ ወስዶ ጥበብን ጽሕፈትን ተግሣጽን አስተማረው የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም መጻሕፍት አጠና በቤተ ክርስቲያንም ሁል ጊዜ ያገለግላል እጅግ በመትጋትም በጾም በጸሎት በመስገድ ይጋደል ነበር። እግዚአብሔርም በእጆቹ ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ ከእሊህ በቊስል ደዌ እጆቹንና እግሮቹን የታመመ አንድ ድኃ ነበረ የከበረ ቢፋሞንን ምጽዋትን ለመነው ሊሰጠውም እጁን ሲዘረጋ በዚያን ጊዜ ከደዌው ድኖ ጤነኛ ሆነ ሕዋሳቱም ሁሉ ጠነከሩ። ሁለተኛም በሌላ ጊዜ በዳዊት መዝሙር ሲያመሰግን ከዚያ አንድ ጋኔን የሚጥለው ሰው ነበረ የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ተወኝ ከዚህ ቦታ ልጥፋ በሎ ጮኸ የከበረ ቢፋሞንም ወደ ጌታችን ጸልዮ ያንን ጋኔን ያደረበትን ሰው አዳነው መምህሩም አይቶ አክብሮትን ለቢፋሞን ጨመረ። እርሱ ያለ ማቋረጥ በመንፈሳዊ ትሩፋት ሥራ የሚያድግ ሁኗልና የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማደሪያው ውስጥ የሚገለጥለት ሆነ ቅዱሳን መላእክቶቹም ከርሱ ጋር አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያምም በአንድነት ያጽናኑት ነበር በመምህሩም ዘንድ ስምንት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ እየተጋደለ ኖረ በየሰባት ቀንም በመጾም ከሰንበት ቀን በቀር አይበላም ወላጆቹ ሚስት እንዲአገባ ጠየቁት እርሱም በዚህ በሚአልፍ ዓለም ከሴት ጋር መኖር ለእኔ ምኔ ነው ፍላጎቱ ሁሉ ያልፋልና አላቸው። ወላጆቹም በርሱ ደስ አላቸው በጎ መሥ

ሰማዕት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት 2.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ 3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት 4.አቡነ አቢብ 5.አባ አቡፋና ††† "የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና . . . " ††† (ዕብ. 11:35) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

✞✞✞ #እንኳን_ለታላቁ_ሰማዕት_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ዓመታዊ_የተአምር_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን።✞✞✞ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ መርቆሬዎስ ኃያል ††† ††† ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው:: ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር:: አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር:: እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል:: እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው:: ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው:: "ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት:: ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ:: አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው:: ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ:: ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ:: በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው:: እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ:: በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት:: በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ:: ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቋቋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት:: እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም:: ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ:: በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው:: "ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው:: ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:- "አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም:: እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም:: አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት:: ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል:: እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል:: ሰማዕቱ በዚህች ዕለት : በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖችን ያሰቃይና ይገድል የነበረውን ዑልያኖስን ያጠፋበት መታሠቢያ ይከበራል:: የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው! ††† አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን:: ቸሩ እግዚአብሔር እድሜ ለንስሃ ዘመን ለፍሥሃ አይንሳን:: ††† ጥር 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ 2.ቅዱሳን ባስልዮስና ጎርጎርዮስ 3.ብፁዕ አባ ዼጥሮስ ጽሙድ (ለምጽዋት ራሱን የሸጠ አባት) 4.ቅዱስ ሰብስትያኖስ ሰማዕት 5.ቅዱስ አስኪላ

††† #እንኳን_ለአባታችን_ለቅዱስ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ዓመታዊ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ ††† ††† ልደት ††† ††† መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል:: በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል:: ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል:: ††† ዕድገት ††† የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል:: ††† መጠራት ††† አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ:: የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ:: ††† አገልግሎት ††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ 2 መልክ ነበራት:: 1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል:: 2ኛው ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር:: ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል:: ††† ገዳማዊ ሕይወት ††† ††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል:: እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል:: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል:: ††† ስድስት ክንፍ ††† ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር:: ከወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:- *በቤተ መቅደስ ብስራቱን *በቤተ ልሔም ልደቱን *በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን *በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን *በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር:: የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ:: በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው:: ††† በዚያም:- *የብርሃን ዐይን ተቀብለው *6 ክንፍ አብቅለው *የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው *ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው *ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው *ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው *"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል:: ††† ተአምራት ††† የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው:: *ሙት አንስተዋል *ድውያንን ፈውሰዋል *አጋንንትን አሳደዋል *እሳትን ጨብጠዋል *በክንፍ በረዋል *ደመናን ዙፋን አድርገዋል:: ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና:: ††† ዕረፍት ††† ††† ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው: መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል:: ††† በዚህ ዕለት አባታችን ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት የቆሙበት ቀኝ እግራቸው መሠበሩንና በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመታት ቆመው መጸለያቸውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስባለች:: ††† ጥር 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅድስት ማርያ ግብጻዊት 3.ታላቁ አባ ቢፋ 4.አባ አብሳዲ ቀሲስ 5.ቅዱሳን ጻድቃነ ሐውዚን ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አቡነ ዘዮሐንስ (ዘክብራን ገብርኤል-ጣና) 2.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ 3.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ 4.ቅዱስ ሙሴ ጸሊም 5.ቅዱስ አጋቢጦስ 6.ሃያ አራቱ ካህናተ ሠማይ ††† "በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" ††† (፪ቆሮ ፲፩፥፳፫) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††