ar
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

الذهاب إلى القناة على Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

إظهار المزيد
4 374
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
photo content

✔❖ ታቦተ ጽዮን በሄደችበት ሁሉ በረከትን ትሰጥ እንደነበር የአቢዳራን ቤት በበረከት እንደሞላች፤ የዮርዳኖስን ባህር እንደከፈለች፣ የኢያሪኮን ቅጽር እንዳፈረሰች፣ የፍልስጤማውያን ጣዖት ዳጎንን ቀጥቅጣ እንዳጠፋች ሀገሪቱ ትባረክ ዘንድ ርኲሳን መናፍስት ይርቁ ዘንድ ምድሪቱ በቃል ኪዳኑ ታቦታት ትቀደስ ዘንድ ታቦታቱ በመጡበት መንገድ እንዳይመለሱ ታላቅ ዐዋጅ አሳውጀው በዐዋጁ መሠረት ዛሬ ድረስ በደመቀ መልኩ በዓሉ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ✔❖ ከባሕር ማዶ ሰዎች ውስጥ ቼሩሊ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ቁመቱ 14 ወርዱ 8 ክንድ የኾነ ባሕረ ጥምቀት እንደተዘጋጀ ሲጽፍ፤ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐጼ ልብነ ድንግል በተገኙበት እጅግ ታላቅ ድንኳን በባሕረ ጥምቀቱ ዙሪያ እንዴት ተተክሎ እንደተከበረ ፍራንቺስኮ አልቫሬዝ ገልጿል፤ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረውን የበዓለ ጥምቀት አከባበር ደግሞ ፔድሮ ፔየዝ ዘግቦት ነበር። ✔❖ አሁን ባለንበት ጊዜም ዳዊት በመዝ 44፡16 ላይ “በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ” በማለት እንደተናገረ ከመቼውም በበለጠ እግዚአብሔር የወጣቱን ልብ በረድኤት ጎብኝቶት ለቃል ኪዳኑ ታቦታት ክብር አካባቢውን እያስዋበ፣ ታቦታቱ የሚሄዱበትን መንገድ እየጠረገ፤ ታላላቅ ምንጣፎችን ታቦታቱ በሚሄዱበት መንገድ እያነጠፈ ለቃል ኪዳኑ ታቦት እንደ ነቢዩ ዳዊት ከፍተኛ ክብር በመስጠት እግዚአብሔርን እያገለገለ ይገኛል (1ኛ ነገሥት 6፡1-23)፡፡ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት”(ኢያ 3፡3) 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏 ✍ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾✞ #ጥምቀት ✞🌾 ✔❖ ጥምቀት ማለት ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውሃ ውስጥ ገብቶ መውጣት” ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ማለት አንድ ሰው አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በተጸለየበትና በተባረከ ውሃ ሦስት ጊዜ ጠልቆ ዳግመኛ ከሥላሴ ተወልዶ የቤተ ክርስቲያን አባል የእግዚአብሔር ሕዝብ ወገን የሚሆንበት ቅዱስ ምስጢር ነው (ማቴ 28፡19-20)፡፡ ✔❖ ምስጢረ ጥምቀት ምስጢር መባሉ ካህኑ ለጥምቀት የተመደበውን ጸሎት አድርሰው ለማጥመቅ የተዘጋጀውን ውሃ ሲባርኩት ውሃው ተለውጦ በዕለተ ዐርብ በመስቀል ላይ ከጌታ ጎን የፈሰሰውን ውሃ ስለሚሆንና ለተጠማቂው ሰው በሚፈጸምለት የሚታይ ሥርዐት የማይታይ የልጅነት ጸጋ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሚሰጥ ነው (ዮሐ 3፡5)፡፡ ✔❖ ምስጢረ ጥምቀትን የመሰረተልን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ሲመሰርትም በማዘዝ ብቻ ሳይሆን በሥራ በማሳየት ጭምር ነው (ማቴ 3፡17፤ ማር 1፡9፤ ሉቃ 3፡21፤ ዮሐ 1፡31)፡፡ ✔❖ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እከብር አይል ክቡር የባሕርይ አምላክ ሆኖ ሳለ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ (በፍጡሩ) በዮሐንስ የተጠመቀበት ምክንያት፦ 1) አንድነቱን ሦስትነቱን ለመግለጽ 2) የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ 3) በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመቀደስ 4)ለጥምቀታችን ኀይልን ለመስጠት 5) ለአብነት ርሱ ተጠምቆ እናንተም ተጠመቁ ብሎ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በ30 ዘመኑ ጥር 11 ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት፤ ማግሰኞ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ✔❖ ጌታችን በዮርዳኖስ እንደሚጠመቅና የዮርዳኖስ ወንዝ ጌታን ስታይ እንደምትሸሽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 113፡3-5 “ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ፤ ተራሮች እንደ ኮርማዎች፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ፤ አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ ምን ሆናችኋል?” በማለት ከ1000 ዓመት አስቀድሞ ትንቢት የተናገረ ሲሆን፤ ብዙ ምሳሌም አለው፨ ✔❖ ምስጢሩ ግን ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ መከራ አጸናባቸው፤ ከዚያም ለኔ የባርነት ስም ብትሰጡኝ መከራውን አቀልላችሁ ነበር አላቸው፤ እነሱም “አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ” (አዳም የዲያብሎስ ወንድ አገልጋይ ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው አሉ፤ ርሱም ይህንን በዕብነ ሩካም አድርጎ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል ጥሎት ነበርና፤ ጌታም በዮርኖስ ጥልቅ ወንዝ የተጣለውን የሰው ልጆች ሁሉ የዕዳ ደብዳቤ በጥምቀቱ ለማጥፋት ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ✔❖ ዮሐንስ ወደ ጌታችን መምጣት ሲገባው ጌታችን ወደ ዮሐንስ የሄደበት ምክንያት ትሕትናን ለማስተማር ሲሆን ሁለተኛው ለአብነት ለምሳሌ ነው፤ ይኸውም ዮሐንስ ሄዶ አጥምቆት ቢሆን ዛሬ ባለሥልጣናቱ ካህናትን ቤታችን ድረስ መጥታችሁ አጥምቁን ይሏቸው ነበርና ሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያን ተጠመቁ ለማለት ሄዷል። ✔❖ ዮሐንስ ግን ወደርሱ በትሕትና የመጣው አምላኩ ክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ሲል ጌታችንም “ጽድቅን ልንፈጽም” ይገባናል ብሎ ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽም እንደመጣ ሲነግረው ዮሐንስ እሺ አለ። ✔❖ ከዚያም ተያይዘው ወደ ዮርዳኖስ ሲወርዱ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት የዮርዳኖስ ወንዝ 40 ክንድ ወደ ኋላዋ ሸሽታለች በዚህም ዳዊት በመዝ 77፡16 ላይ “አቤቱ፥ ውኆች አዩህ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውኆችም ጮኹ” ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ። ✔❖ ጌታችንም ተጠምቆ ከውሃው ከወጣ በኋላ አብ በሰማይ ኹኖ “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ” (በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው) ብሎ ሲመሰክር፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስም በጽንፈ ዮርዳኖስ ቁሞ ታየ፡፡ ✔❖ ይኸውም በምስጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደምንረዳው ከሰማይ ኾኖ የመሰከረው ክርስቶስ በቃልነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ያሉበት (ሕልው የኾኑበት) አብ ነው፤ ወርዶ በወልድ ራስ የተቀመጠው አብ በልቡናነት ክርስቶስ በቃልነት ሕልው የኾኑበት መንፈስ ቅዱስ ነው፤ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ የታየው አብ በልቡናነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ሕልው የኾኑበት አካላዊ ቃል ክርስቶስ ነው፤ እንዲኽ አድርገው የአካል ሦስትነታቸውን የፈቃድ አንድነታቸውን ለማስረዳት አብ በደመና ኾኖ መሰከረ፤ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ታየ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ ታየ። ✔❖ በዚኽም የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሚገባ ሲታወቅ በተጨማሪም “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ እግዚአብሔር አብ በመመስከሩ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው በኋለኛው ዘመን ከእመቤታችን ያለ አባት በኅቱም ድንግልና የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ብቻ መኾኑ በሚገባ ተረጋግጧል፤ ዕለቱም በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋንያ ሲባል በግእዝ አስተርእዮ በዐማርኛም የመታየት የመገለጥ ጊዜ ተብሏል፡፡ ✔❖ ኢትዮጵያ ሀገራችን ስለ ነገረ ጥምቀት የሰማችው ከሌላው ዓለም አስቀድማ ጌታችን ባረገ በጥቂት ወራት (በ34 ዓ.ም) ነው (የሐዋ 8፥26-39)፤ ይህም በዐል ከዘጠኙ ዐበይት በዐላት አንደኛው ሲሆን ጌታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ስላመራ ይህንን ለማሰብ ታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ያመራሉ። ✔❖ ሊቀ ትጉኃን ኃይለ ጊዮርጊስ በጻፉት የነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ ላይ በስፋት እንደጻፉት በኢትዮጵያ በዚህ መልኩ መከበር የተጀመረው ከ515-529 ዓ.ም ለ14 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በአጼ ገብረ መስቀል ዘመን ሲሆን በጊዜው ቅዱስ ያሬድ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ ከዝማሬው በመነሣት ታቦታቱ ጥር 11 ጠዋት ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አምርተው አመሻሹ ላይ ይመለሱ ነበር፡፡ ✔❖ ከዚያም ከ1157-1197 ዓ.ም ድረስ ለ40 ዓመት ኢትዮጵያን በመራው በታላቱ ጻድቅ ንጉሥ በላሊበላ ዘመን በአንድ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስትያናት ታቦታቱ ባንድ ላይ እንዲያከብሩ ንጉሥ ላሊበላ ታላቅ መንፈሳዊ ዐዋጅን አሳውጆ በአንድ አካባቢ፣ ወረዳ፣ ያሉ በአንድ ላይ ማክበር ጀመሩ፤ በርሱ ዘመን የነበሩት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በጎንደር፣ በሸዋ፣ በአንኮበር፣ በመርጡለ ማርያም እየሄዱ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡ ✔❖ በመቀጠልም ከ1245-1268 ዓ.ም ለ23 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በዐጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሳሳቢነት ታቦታቱ በባሕረ ጥምቀት ሲውሉ ምእመናን በታላቅ ድምቀት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንዲውሉ መንፈሳዊ ዐዋጅ አሳወጁ፡፡ ✔❖ በመቀጠል ከ1426-1460 ዓ.ም ለ34 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በታላቁ ንጉሥ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥትም ንጉሡ ከሊቃውንት ጋር በመወያየት የበዐሉን ታሪክ ተከትሎ ታቦታቱ ጥር 10 ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት እንዲወርዱና ጥር 11 እንዲመለሱ ተወሰነ።

🌾✞ #ጾመ_ገሃድ ✞🌾 #ለህዝበ_ክርስቲያን_በሙሉ ✔በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ ብርሃነ ልደቱን በሰላም አድርሶ እንዳሳለፈን አሁንም ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላምና በጤና ያድርሰን አሜን፡፡ ስለ ጾመ ገሃድ ብዙ ክርክሮችን እንሰማለን፡፡ እናም መቼ እንደሚውልና ስለ ጾሙ ምንነት ልናካፍላችሁ ወደድን እነሆ ሁሉም ላልሰማ ያሰማ፡፡ #ገሃድ ማለት ለውጥ ወይም ልዋጭ ማለት ሲሆን። የቃሉ ፍቺ ግን ከዘይቤው ጋር አይገናኝም። ይህ ማለት “ገሃድ” ቀጥተኛ ትርጉሙ “ግልፅ” ማለት ነውና። ✔ቤተ ክርስቲያናችን ከሏት አጽዋማት አንዱ “ጾመ ገሃድ” ነው፡፡ የገሃድ ጾም የሚጾመው በጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው። በዓለ ጥምቀት ረቡዕ ወይም ዓርብ ባይውልም ዋዜማው (ጾመ ገሃድ) በመባል ይጾማል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ባለማወቅ የልደትን ዋዜማም "ገሃድ" ብለው ይጾማሉ። ነገር ግን የልደት (ገና) ዋዜማ መጀመሪያውኑ በጾመ ነቢያት ውስጥ ያለ በመሆኑ ድርብ ጾም የለምና ለብቻው አይጾምም። ✔ጾመ ገሃድ ጥምቀት ረቡዕና ዐርብ በሚውሉበት ጊዜ ቀድመው ያሉት ማክሰኞና ሐሙስ የፍስክ ቀንነታቸው ወደ ጾምነት ተለውጦ ይጾማሉ። በነሱ ለውጥ ጥምቀት የሚውልባቸው የጾም ቀናት (ረቡዕና ዐርብ) የፍስክ ቀን ሆነው ይከበራሉና። ✔ገሃድ የረቡዕና ዐርብ ለውጥ ነው ብለናል። ነገር ግን ጥምቀት በሌላም ቀን ቢውል የጥምቀት ዋዜማ ይጾማል። በዓለ ጥምቀት እሑድ ቢውል ቅዳሜ የግድፍት/የፍስክ ምግብ አይበላም። ጥምቀት ሰኞ ቢውል እሑድም አይበላም። እንደሌሎች የአጽማዋት ቀናት ግን የፆም ምግቦች እህልና ውሃ ግን አይከለከሉም። ወይም ዋዜማው ከሰኞ እስከ አርብ ከሆነ እነደ ማንኛውም ጾም ይጾማል ማለት ነው፡፡ ✔አንዳንድ ሰዎች ግን ጥምቀት ሰኞ ሲውል ከቅዳሜና እሑድ አዋጥተው በመጾም ቅዳሜና እሑድ ጥሉላት አይበላባቸውም ወይም ይጾምባቸዋል ይላሉ። ነገር ግን “ገሃድ” አንድ ስለሆነ (ስንክሳር ጥር 10 “ሰላም ለዕለት ዋሕድ ዘስሙ ገሃድ” እንዲል) ጥምቀት ሰኞ ሲውል ቅዳሜን መጾም አጉል የገባ ልማድ ወይም ከስርዓት ውጭ የሆነ አስተምሮ ነው። ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🤔ለመሆኑ እስካሁን ትልቁን 📚የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የመጻሕፍት ቻናል በቴሌግራም ተቀላቅለዋል❓ ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ። ➨@Orthodox_Books 📚 የተለያዩ የብራና ፣ የ Gunda Gunde
🤔ለመሆኑ እስካሁን ትልቁን 📚የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የመጻሕፍት ቻናል በቴሌግራም ተቀላቅለዋል❓ ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ። ➨@Orthodox_Books 📚 የተለያዩ የብራና ፣ የ Gunda Gunde Manuscripts ቅዱሳት መጻሕፍቶች ይለቀቃሉ። ይቀላቀሉ👉https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw ➖➖➖➖➖➖ ▶️ዩቲዩብ || YOUTUBE ↪️ https://youtu.be/SY-D-qGgT0U

የስላሴን መንበር.m4a9.67 KB

ምስጋና ለስላሴ.wma8.00 KB

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡ ✔የጥር ሥላሴ በዓል አስደናቂ ታሪክ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ(ዶ/ር) ✔✞ በጥር 7 ሥሉስ ቅዱስ የሰናዖርን ሕንፃ ማፍረሳቸውና የከለዳውያንን ቋንቋቸውን እንደበተኑ የሚነገር ሲኾን፤ በተጨማሪም በዐጼ ኢያሱ አድያም ሰገድ የተሠራው የሥላሴ መቅደስ ቅዳሴ ቤቱ ነው። ✔✞ይኽስ እንደምን ነው ቢሉ? ከ፲፮፻፸፬-፲፮፻፺፰ (1674-1698) ዓ.ም. ኢትዮጵያን የመሩት ታላቁ ንጉሥ ዐጼ ኢያሱ ቀዳማዊ (አድያም ሰገድ) ሥላሴን በእጅጉ ከመውደዳቸው የተነሣ የአድባራት ኹሉ ንግሥት ብለው የሠየሙትን የሥላሴን ቤተ ክርስቲያን ለየት ባለ መልኩ ማሳነጽ ጀመሩ። ✔✞እጅግ ድንቅ ኾኖ እንዲታነጽ ካላቸው ታላቅ ፍላጎት በመነሣት የሕንጻ አዋቂዎች የኾኑ በጊዜያቸው አሉ የተባሉ ታላላቅ ባለሙያዎችን መረጡ፤ ለረዥም ዘመናት ሊቆዩ የሚችሉ ዕንጨቶችን ከያሉበት በማስመጣት እጅግ ድንቅ የኾኑ በድንቅ መልክ የተጠረቡ ደንጊያዎችን አስመጥተው በዘመናቸው በጎንደር ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተወዳዳሪ የሌለው ኾኖ እንዲታነጽ አደረጉ፡፡ ✔✞ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ካለው ታላቅ ፍቅር በመነሣት ቤተ መቅደሱን በወርቅ እንዳሣነጸው፤ ንጉሥ ዐጤ ኢያሱም ለቤተ ክርስቲያኑ የወርቅ ጉልላት በላዩ ላይ አሠርተው ከወርቅ የተሠራ መስቀል በላዩ ላይ እንዲደረግ አደረጉ፤ ከወርቁ ጽርየት የተነሣ በቀን እንደ ፀሓይ በሌሊት እንደ ጨረቃ ያንጸባርቅ ነበር ይላሉ፤ ከማይነቅዝም ዕንጨት በአዋቂዎች እጅ አስደናቂ መንበር አሠርተው በዝኆን ጥርስ አስጊጠው እንዲያምር ተደረገ፡፡ ✔✞በዕውቅ ሠዓሊ አማካይነት እጅግ አስደናቂዎች ቅዱሳት ሥዕላት ተሣሉ፤ ጣራውም በመላእክት ሥዕል ተመላ፤ ቅጽረ ኢያሪኮ ሰፊ እንደነበረ የቤተ ክርስቲያኑ ግቢው እንዲሰፋ ተደርጎ ዙሪያው ረዥምና ሰፊ ኾኖ ታጠረ፤ በፊት ለፊትም መውጪያና መግቢያ ሊኾኑ ኹለት በሮች እንዲሠሩ አደረጉ፤ በበሮቹም ላይ የርእሰ አንበሳ ቅርጽ ያለው ባለ ግርማ ግንብ ተሠርቶ በዙሪያው ዐሥራ ኹለት እንቁላል ግንቦች ታነጹ፡፡ ✔✞ለሥላሴ መቅደስ የሚኾኑ ግዙፋን የኾኑ ኹለት ታላላቅ ደውሎች በጠንካራ ገመድ ታስረው እንዲንጠለጠሉ ኾኑ፤ ከጽርየቱ የተነሣ በጊዜው ከእነዚኽ ደውሎች የሚወጣው ድምፅ ከጎንደር ዐልፎ ወጣ ወደሚሉ ግዛቶች ጭምር ይሰማ ነበር ይላሉ፡፡ ከዚያም ለቅዳሴ ቤቱ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳት እንዲዘጋጁ ተደርገው ካህናቱ ዲያቆናቱ ልብሰ ተክህኖ ለብሰው፤ ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው ዐጤ ኢያሱም ከመሳፍንቱ ከመኳንንቱ ጋር በታላቅ ደስታ ከቤተ መንግሥት ወደ ቤተ መቅደሱ ጉዞ ተደረገ፡፡ ✔✞ታቦተ ጽዮን በታላቅ ግርማ ትታጀብ እንደነበር፤ በተመሳሳይ መልኩ የመሰንቆ፣ የእንቢልታ፣ የነጋሪት፣ የእንዚራ ድምፅ እየተሰማ፤ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን ከፍተኛ የምስጋና ድምፅን እያሰሙ፤ ንጉሥ ዐጤ ኢያሱም በሰራዊታቸው ታጅበው “ጒቤን” በሚባለው ፈረሳቸው ተቀምጠው፤ እጨጌ አባ ጸጋ ክርስቶስ ታቦተ ሥላሴን ተሸክመው ጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ በር ላይ ሲደርሱ፤ ንጉሥ ኢያሱ ለሥላሴ ካላቸው እጅግ ጥልቅ ፍቅር ተነሥተው ታቦቱ ገና አልተባረከም ነበርና ጳጳሱን አስፈቅደው ታቦቱን ከእጨጌው ተቀብለው እስከ ቅድስት አደረሱ፤ ካህኑም ከቅድስት ተቀብሎ ወደ መቅደስ ካገባው በኋላ የሥላሴ ታቦትን ግብጻዊዉ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ በቅብዐ ሜሮን ባርከው ቅዳሴ ቤቱ ተቀደሰና የታቦቱ አገባብ በታላቅ በዓል ጥር 7 ታስቧል፡፡ ✔✞እንደ አዛዥ ሐዋርያ ክርስቶስ ያሉ ሊቃውንት ዐጼ ኢያሱን በቅኔ ያወደሷቸው ሲኾን፤ ሥላሴ በተባለው የቅኔ ዐይነት፡- “አምላክ ዘኢፈቀድከ ደቂቀ ቆሬ ወዖዝያን ሶበ ማዕጠንተ ወርቅ ነሥኡ ከመ ይኩኑ ካህናተ ነሥኡ ተቀሥፎ ወለብሱ እሳተ እለ ይፈርሁከ ሰብአ ባሕቱ እምኀበ ረከብከ አንተ በዘወሀብኮሙ ትእምርተ አመ ርኅበ በልዐ ዳዊት መሥዋዕተ ወኢያሱ አንሥአ ጽላተ” (የዖዝያንና የቆሬ ልጆች ካህናት ለመኾን ዐስበው አምላክ ያልፈቀድኸውን የወርቅ ማዕጠንት በወሰዱ ጊዜ ተቀሥፈው እሳት በላቸው፤ አንተን የሚፈሩኽ ሰዎች ግን በሰጠኻቸው ምልክት ተመርተው፤ ዳዊት ቢራብ መሥዋዕትን በላ፤ ኢያሱም ጽላትን አነሣ) እያሉ ተቀኙላቸው፡፡ ✔✞የዐማርኛ ገጣሚውም በጊዜያቸው በአንክሮ ኾኖ፡- “ ወዴት ኼዶ ኖሯል ሰሞነኛ ቄሱ ታቦት ተሸከመ ዘውዱን ጥሎ ኢያሱ የተሸሸገውን ያባቱን ቅስና ገለጠው ኢያሱ ታቦት አነሣና አየነው ኢያሱ ደብረ ብርሃን ቆሞ ልክ እንደ ኪሩቤል ሦስቱን ተሸክሞ ሥላሴን ቢሸከም ኢያሱ ገነነ ለአራቱ ኪሩቤል ዐምስተኛ ኾነ” በማለት ገጠመላቸው፡፡ ✔✞ካህናቱም ሕዝቡም፡- “የልዑል እግዚአብሔር ወዳጆች ደጋግ ነገሥታት የነበሩ የእነ ቆስጠንጢኖስን፣ የእነ አኖሬዎስን፣ የእነ አርቃዴዎስን … የክቡራን ነገሥታትን ኹሉ በረከት ያሳድርብዎ” እያሉ ንጉሡ ዐጼ ኢያሱን አመሰገኗቸው፡፡ ቅዳሴ ቤቱ ጥር 7 ተደርጎ ከዚያም ዐጤ ኢያሱ ለሦስት ቀናት በቤተ መንግሥታቸው እጅግ ታላቅ ግብዣ አደረጉ፤ የጥር ወር በገባ በ፯ኛው ቀን ኹሌም በዓሉ እንዲከበር አዘዙ፤ ለሥላሴ መቅደስም 170 ካህናት እንዲያገለግሉ አድርገው እጅግ ብዙ ርስት ሰጥተዋልና የመልክአ ሥላሴ ደራሲ አባ ስብሐት ለአብም ይኽነን የዐጤ ኢያሱ አድያም ሰገድን ውለታ ባለመዘንጋት በዚኽ መጽሐፉ ላይ ይኽነን ታሪክ እንደ ወርቅ አንከብልሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ ታሪኩን፦ “ ሰላም ለርእስክሙ ዘአስተዋደደ ርእሰ አጋዕዝተ ሥጋ ሥላሴ እንዘ ኢትሌልዩ ነፍሰ በርእሰ ኢያሱ አንብሩ አክሊለክሙ ሞገሰ በስምኩሙ አሐዱ እስመ ያመልክ ሥሉሰ ወበስምክሙ ሐነጸ መቅደሰ” (ራስን ያስማማ ለኾነ ራሳችኊ ሰላምታ ይገባል፤ ነፍስን ሳትለዩ ሥጋን የፈጠራችኊ ሥላሴ ሆይ ባለሟልነት ዘውዳችኹን በኢያሱ ራስ ላይ አኑሩ፤ እግዚአብሔር በሚባል አንድ ስማችኊ፤ ሦስት አካላትን ያመልካልና፤ በስማችኹም ቤተ መቅደስን ሠርቷልና) በማለት ይገልጣል፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#6_ቅትለተ_ዘካርያስ፦ ~~~~~~~~~~~~~ ይህ ማለት የካህኑ ዘካርያስ መሞት ፣ መገደል ማለት ነው። የእግዚአብሔር ካህን የነበረው ዘካርያስ የተገደለው በተልዕኮ ላይ እያለ በቤተመቅደስ ውስጥ በመሠዊያው አጠገብ ነበር። እርሱም የሞተው ጥፋት ኖሮበት ሳይሆን በግፍ ነው። እንደዚሁም ሁሉ የእግዚአብሔር ዓይኖች (አዕይንተ እግዚአብሔር) የተባሉ እውነተኞች ካህናት በሐሳዊ መሲሕ ጊዜ አገልግሎታቸው ለእውነተኛው አምላክ ለኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ መከራ ይደርስባቸዋል ፣ በአገልግሎትም ላይ እያሉ ይገደላሉ። ስለዚህ ይህ የሚያመለክተው የቅዱሳን ካህናትን መከራ መቀበልና በሰማዕትነት ማለፍ ሲሆን እነ ሄኖክና ኤልያስ ሌሎችም የተሰወሩ ቅዱሳን አባቶቻችን ሞት በሰው ልጆች ትክሻ ላይ የተሰየመ ነውና ወደዚህ ዓለም መጥተው በዚህ አውሬ (ሐሳዊ መሲሕ) ዘመን በሰማዕትነት ያርፋሉ የሞትንም ጽዋ ይቀምሳሉ። ሚል 4፥5 ፣ ማቴ 23፥25-36 ፣ ራዕይ 11፥3-13 --------------------//---------------- #7_ሞተ_ወልደ_እግዚአብሔር፦ ~~~~~~~~~~~~~~~~ ይህ ማለት ንፁህና ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ስለሰው ልጆች ፍቅር እና ሕይወት እንጂ አንዳች በደል ኖሮበት ወይም ተገኝቶበት አይደለም። ንፁሐ ባህርይ አምላክ ሆኖ ሳለ እውነተኛ ፍርድ ስለጠፋ ነው በቅንዓተ አይሁድ የሞተው ፤ እንደዚሁም በዚህ ሐሳዊ መሲሕ ዘመን እውነተኛ ፍርድ ትጠፋለች ፣ ፍትህ ትጓደላለች ፣ ክርስቲያኖች ያለ አግባብ ይታሰራሉ ፣ ይሰቃያሉ ፣ ይገደሉማል። ዮሐ 15፥18-20 ፣ ማቴ 10፥16-20 ---------------------//---------------- ከዚህ በኋላ ደግሞ ፦ "ዘንዶው ኃይሉንና ዙፋኑንም ትልቅም ሥልጣን ሰጠው" ይላል ራዕ 13፥2 #ዘንዶ_የተባለው_ማነው? ~~~~~~~~~~~~~~ የዘንዶውን ማንነት ለማወቅና ለመረዳት ደግሞ ወደ ራዕይ 12፥3 ፣7፣ 9 እንመለሳለን። በዚህ በራዕይ 12፥3 "ታላቅ ቀይ ዘንዶ" ማለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ስለዘንዶው ማንነት ይናገራል። ይህም ዘንዶ የተባለው አባታችንን አዳምና እናታችን ሔዋንን ያሳተው ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ ነው። ዘፍ 3፥1 ^ታላቅ^ መባሉ የቀድሞውን ተፈጥሮውንና ክብሩን ለመግለፅ ነው፣ የመላዕክት አለቃ ነበርና! "ቀይ" መባሉ ደግሞ ተፈጥሮው እንደ ሌሎቹ ብርሃናዊያን እሳታዊያን ቅዱሳን መላዕክት ከእሳትና ከነፋስ ስለሆነ ነው። መዝ 103፥4 ፣ ዕብ 1፥7 ፣ ሕዝ 28፥14 ፣ ኢሳ 14፥12 ። #ምድር_ሁሉ_አውሬውን_ይከተላል ራዕ 13፥4 መላው ዓለም በአውሬው የተመሰለው ይህ ሐሳዊ መሲሕ በሚያደርገው ምትሐታዊ ተአምር ይሳባል ፣ ይደነቃል "እውነተኛ አምላክ ነው" እያለም ይከተለዋል ማለት ነው። በምትሀታዊ ተአምራቱም ሕዝቡን ሁሉ ያስገርም ዘንድ ሥልጣን ለሰጠው ለዘንዶውም ይሰግዱለታል ፣ ይገዙለታል። አውሬውን "ማን ይመስለዋል? ማንስ ይስተካከለዋል? ብቸኛ ገናና አምላክ ነው" ብለው ያመልኩታል ማለት ነው። ዘዳ 13፥1-8 ፣ ማቴ 12፥38-39 #አውሬው_ተሳዳቢ_ነው (ራዕ 13:5-7) አውሬውም ታላቅንም ነገርንና ስድብ የሚናገርበት አፍ ተሰጠው ፣ አርባ ሁለት ወርም እንዲሰራ ሥልጣን ተሰጠው" ይላል ራዕይ 13:5 ይህ አውሬ (ሐሳዊ መሲሕ) በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ይሰድባል። "እግዚአብሔር ማን ነው? የትስ አለ? እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አምላክ እኔ ነኝ።" ይላል። እውነተኛውን አምላክ ሰዎች እንዳይረዱና እንዳያመልኩት ርኩስ መንፈስ በልባቸው ያሳድርባቸዋል ፤ ደግሞም ያስታቸዋል። ዛሬም ቢሆን ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ "ፍጡር ፣ አማላጅ" የሚሉ አሉ። እነዚህ ለአውሬው ጥርጊያ መንገድ የሚያዘጋጁ ናቸው። ምክንያቱም በዮሐ 1፥1 ላይ መጀመሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ቃልም ሥጋ ሆነ" ተብሎ የተነገረለትን እግዚአብሔር ወልድን ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አሳንሶ "ፍጡር አማላጅ" ነው ማለት እግዚአብሔር መሳደብ ነው። እግዚአብሔርም ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለምና ፣ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለምና። አውሬው (ሐሳዊ መሲሕ) ስድቡን በዚህ አያበቃም አርባ ሁለት ወር (ሶስት አመት ከስድስት ወር) ሙሉ የወደደውን ምትሐታዊ ተአምር እየሰራ ራሱን ብቻ ከፍ በማድረግ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ይሳደባል። ይላል ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕይ 13፥6! #የእግዚአብሔር_ማደሪያ_ማን_ናት?! የእግዚአብሔር ማደርያ የተባለችው ጌታን ያየንባት በሁለት ወገን ድንግል የምትሆን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። እንግዲህ ድንግልን ነው ዘንዶውና ተከታዮቹ ማርያም አታማልድም፣ ሞታለች፣ ሌላም ሌላም እያሉ የሚሰናከሉባት። እንግዲህ ትንቢት ነውና ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ! ይማረክም ዘንድ እጁን አይስጥ!! 🙏አቤቱ ወደውና ፈቅደው ከሚጠፋት ጋር አታጥፋን!!🙏 ✞ #አሜን_አሜን_አሜን ✞ ------------------//----------------

#7ቱ_ሀገሮች_እና_7ቱ_የኃጢአት_ራሶች ~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ➊ ፋርስ ➋ ባቢሎን ➌ ግሪክ ➍ ሜዶን ➎ ግብፅ ➏ ሮም ➐ ኢየሩሳሌም በመጨረሻው ዘመን እነዚህ ሰባቱ ሀገሮች በሐሳዊው መሲሕ ወይም በውሸተኛው ክርስቶስ ቁጥጥር ሥር የሚውሉ መላውን ዓለም በክህደት ትምህርትና በታላላቅ ምትሐታዊ ተአምራት የሚያስቱና የሚያናውጡ ናቸው። _____________\\____________ #ሰባት_ራሶች፦ የተባሉት በመጨረሻው በሐሳዊ መሲህ ዘመን የሚፈጸሙ ሰባቱ ዋና ዋና ኃጢያቶች ናቸው። እነዚህም 7ቱ አርዕስተ ኃጣውዕ ወይም 7ቱ የኃጢአት ራሶች ይባላሉ! እነርሱም፦ ➊ ኃጢያተ አዳም (ወይም የአዳም ኃጢያት ➋ ቅትለተ አቤል (የአቤል መገደል) ➌ ጥቅመ ሰናዖር (የሰናዖር ህንፃ) ➍ ኃጢያተ ሰዶም (የሰዶምና ጎሞራ ሰዎች ኃጢያት) ➎ ኃጢያተ እስራኤል (የእስራኤላዊያን ኃጢያት) ➏ ቅትለተ ዘካርያስ ካህን (የዘካርያስ ካህን መገደል) ➐ ሞተ ወልደ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ወልድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት) ናቸው። -------------------//-------------- #1_ኃጢያተ_አዳም፦ ~~~~~~~~~~~~ ይህ ማለት የአዳም ኃጢያት ማለት ነው። የመጀመሪያው ሰው አዳም አምላክነትንና ፈጣሪነትን ስለሻተና ስለተመኘ አትብላ የተባለውን "ዕጸ በለስን" በላ። በዚህም ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ ከክብር ቦታ ከገነት ተባርሮ ወጣ። አሁንም በዚህ በመጨረሻ ዘመን የሚነሳው ይህ ሐሳዊ መሲሕ "እኔ አምላክ ነኝ፤ እኔ ፈጣሪ ነኝ፤ ለእኔ ስገዱ" እያለ የሚመጣ ሰው ነው። በሞተ-ወልደ እግዚአብሔር ተደምስሳ የነበረችውም የአዳም ኃጢያት (አምላክነትን መሻት) በዚህ በሐሳዊው መሲሕ ዘመን ለመጨረሻ ጊዜ አይላ ትፈፀማለች ማለት ነው። ዘፍ 3:1 በምንም የሚያስታችሁ አይኑር ፤ ክህደት ሳይመጣና የአመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያቺ ቀን አትመጣምና። ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ለሁሉም እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ የሚል በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የሚቀመጥ ራሱንም እንደ እግዚአብሔር የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው።" 2ኛ ተሰ 2፥3-5 -------------------//---------------- #2_ቅትለተ_አቤል፦ ~~~~~~~~~~~ ይህ ማለት የአቤል መገደል፤ መሞት ማለት ነው። አቤልና ቃየል የአዳምና የሔዋን ልጆች ናቸው። ዘፍ 4:1-12 ቃየን የገዛ ወንድሙን በግፍና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ገድሎታል። አሁንም በዚህ የአውሬው (የሐሳዊው መሲሕ) ዘመን መገዳደል እጅግ ይበዛል ፤ ርህራሄ ከሰው ልጆች ዘንድ ትርቃለች። ወንድም ወንድሙን ይገድላል። እህት እህቷን ትገድላለች ማለት ነው። ማቴ 10:21-36 "ወንድምም ወንድሙን ፣ አባት ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል። ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሳሉ ፤ ይገድሉዋቸዋልም።" -------------------//---------------- #3_ጥቅመ_ሰናዖር፦ ~~~~~~~~~~~ ይህ ማለት የሰናዖር ሕንፃ (ግንብ) ማለት ነው። ባቢሎናዊያን በቀድሞ ወቅት ሰይጣን በልባቸው አድሮ፣ ልባቸው በትዕቢት ተወጥሮ፣ የማይታየውን ረቂቅ አምላክ እናየዋለን ፣ የማይዳሰሰውን አምላክ እንዳስሰዋለን ፣ በጦርም ወግተን ከዙፋኑ እናወርደዋለን፣ በማለት በእግዚአብሔር ላይ በትዕቢት ተነሳስተው ግንብ መገንባት ጀመሩ። የግንቡም ርዝመት 5532 ክንድ ነበር። በዚህን ጊዜ ጌታ እግዚአብሔር ሦስትነቱን ገልጦ እንዲህ አለ፦ ንዑ ንረድ ወንከአው ነገሮሙ ለከለዳውያን። ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው" ዘፍ 11:7 ወዲያውኑ ቋንቋቸው ተደበላለቀባቸው። ድንጋይ አቀብለኝ ሲለው ውኃ ፣ ውኃ አቅብለኝ ሲለው ደግሞ እንጨት ያቀብለው ጀመር ፤ በዚህም ዓይነት ቋንቋቸው ተደበላለቀ። እግዚአብሔርም በትዕቢታቸው ምክንያት በተናቸው። (መዝ 2:5) ዛሬም በእኛ ዘመን የሚያጣላን የዘረኝነት ጉዳይ ነው። አስተውለን ካየነው የቋንቋችን ብዛትና ልዩነት በኃጢአታችን ብዛት እንዳንደማመጥና እንዳንስማማ የተደበላለቀብን እንጂ የጽድቃችን ምልክት አይደለም። አሁንም በዚህ ሐሳዊ መሲሑ ዘመን ከዚህ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ቴክኖሎጂው ይራቀቃል፣ ይሰለጥናል። ሰዎችም እጅግ ኮምፒዩተራይዝድ በሆኑ መሳሪያዎች እግዚአብሔር ያለበትን ቦታ ለማግኘት ከጨረቃ አልፈው ይመጥቃሉ ፣ እግዚአብሔርን ግን አያገኙትም ፤ አያዩትም። መዝ 2፥4-5 እንዲህ ይላል፦ "በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቅባቸዋል። እግዚአብሔርም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቁጣው ይናገራቸዋል ፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።" ትንቢተ አብድዩ 1፥1-4 "ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰማሁ ፤ ከባቢን ወደ አሕዛብ ልኮ ፥'ተነሱ ፤ በላይዋም እንነሳና እንውጋት። እነሆ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ። አንተ እጅግ ተንቀሃል። በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ እንደሚኖር ማደሪያውንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ ፤ በልቡም ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? እንደሚል ፥ በልብህ ትዕቢት እጅግ አኩርቶሃል። እንደንስር መጥቀህ ብትወጣ ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያም አወርድሃለሁ' ይላል ጌታ እግዚአብሔር። በዚህም ጊዜ ሐሳዊው መሲሕ እግዚአብሔር የት አለ? አምላክ ፣ ፈጣሪ እኔ ነኝ" ይላል። ለዚህም ሙት ያስነሳል። እሳት ከሰማይ ያወርዳል ፣ ታላላቅ ተዓምራትን ያሳያል። በዚህም እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እያስነገረ በቤተ መቅደስ ይቀመጣል። በዚህን ጊዜ መላው ዓለም አውሬውን ማን ያህለዋል? ማንስ ይመስለዋል? እያለ ይከተዋል፤ ይሰግዱለታልም። ማቴ 24፥23-27 ፣ 2ኛ ተሰ 2፥4 ፣ ራዕ 13፥4 -------------------//---------------- #4_ኃጢአተ_ሰዶም፦ ~~~~~~~~~~~~ ይህ ማለት ኃጢያተ ሰዶም ተብሎ የሚጠራው በሎጥ ዘመን በሰዶምና በገሞራ የተፈፀመው የኃጢያት ስራ ነው። ሰዶምና ጎሞራ በአንድ ወቅት ትዕዛዘ-እግዚአብሔርን አፍርሰው ሕጉንም ተላልፈው ለባሕርያቸው የማይስማማውን የማይገባውን እንስሳዊ ግብር በመፈፀማቸው እግዚአብሔር ተቆጥቶ ከሰማይ እሳት (ዲን) አዝንቦባቸዋል። ዘፍ 19፥24 ፣ መዝ 48፥12 ፣ ሉቃ 17፥18-30 ፣ 2ኛ ጴጥ 2፥6-8 ፣ ሮሜ 1፥22-32 ይህ ግብረ ሰዶም በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም ላይ እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው። በተለይም በሰለጠነው ዓለም ይህ ግብረ ሰዶም ሕጋዊ እንዲሆን ተደርገዋል። በብዙዎችም ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷል። ይህ የሚያስረዳን የጊዜው መቃረብና ከዛሬ ሦስት ሺህ ዓመተ በፊት የነበረው ኃጢአት በዚህ ሐሳዊ መሲህ ዘመን እንደ አዲስ መምጣቱንና የግብረሰዶም ኃጢያት በገሀድ እንዲፈጸም መደረጉን ያሳያል። ማቴ 24፥15 ------------------//---------------- #5_ኃጢያተ_እስራኤል፦ ~~~~~~~~~~~~~~ ይህ ማለት ሀገረ እግዚአብሔር ፣ ህዝቡም "ሕዝበ እግዚአብሔር" ይባሉ እንደነበር በመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ ሁላችንም የምናውቀው ነው። እስራኤላዊያን ግን በዚያን ጊዜ የአባቶቻቸውን አምላክ የእስራኤልን ቅዱስ እግዚአብሔርን ትተውና ረስተው ሕጉንም ተላልፈው በአሕዛብ ጣዖታት ያመልኩና ለጣኦታቱም ይሰግዱ ነበር። እንደዚሁም ሁሉ በዚህ በሐሳዊ መሲሕ ዘመን ብዙ ሰዎች ከአምልኮተ እግዚአብሔር ወጥተውና ተለይተው ወደ ተለያየ አምልኮተ ጣዖት ይገባሉ። የአውሬው (የሐሳዊው መሲሑ) ስምና መንፈስ ፣ መለያ ቁጥሩ ለሆነው 666 ላለበት ጣዖት ይገዛሉ። ራዕይ 13፥15 ------------------//----------------------