ar
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

الذهاب إلى القناة على Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

إظهار المزيد
4 374
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
#ቅዱስ_ኡራኤል ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞ #_ቅዱስ_ኡራኤል_መልአክ_ብርሃን✞ ☞✞ኡራኤል የሚለው ስም 'ዑር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሰረተ ስም ነው ። ☞✞ኡራኤል ማለት ትርጉሙ "የብርሃን ጌታ" የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው ። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ አለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልዓክ ነው ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መፅ ሄኖክ {6፤2} ☞✞ሚስጢር ሰማይና እዉቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለፀለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል ። መፅ ሄኖክ {28 ፤13} ☞✞ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ መንገድ የመራ ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎ ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ ፤ እዉቀት ለተሰወረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ፅዋ ጥበብን ያጠጣ መለአክ ነው ። 🙏በረከቱ በሁላችንም ላይ ባለንበት ቦታ ይደርብን፡፡🙏

🌿🌾 #ደብረ_ምጥማቅ 🌾🌿 ግንቦት ፳፩ ✅እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ በወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ነው። ✅ጌታችን ፈጣሪና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ወደ ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ፣ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር። ቦታውንም ባርኮና ቀድሶ ይህ ቦታ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎ ለእናቱ ለእመብርሃን ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር። ቦታው ደብረ ምጥማቅ ከመቀደሱ የተነሳ አካባቢውን በርካታ መነኮሳት ይኖሩበት ነበር። ✅እመቤታችንም በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን በልጇ ፈቃድ ግንቦት ፳፩ ቀን አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት ትገለጽላቸው ነበር። ✅በዚህም መገለጥ እመብርሃን ድንግል ማርያም ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ሌላ እምነት የነበራቸውም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየሀገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ ፤ድንግልም ከግንቦት ፳፩ ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር። ✅ህዝቡም የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል?! ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን?! ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን?! አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል፤ እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር። ✅አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር፤ ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር፤ ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው። ወይ ግሩም ታዲያ ይህ በዚያ ደጉ ዘመን ነበር፤ አሁን ግን ኃጢያታችን ስለበዛም በገሃድስ ተገልጻ አትታይም። በረድኤቷ ብዛት እና ለበቁ ጻድቅ አባቶቻችን ካልሆነ በስተቀር። ✅የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባት ነበረች። ፈልገው የሚያጡት፣ ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም። እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች ምንኛ የታደሉ ናቸው፤ እነዚያ በፊቷ የቆሙ እግሮች ምንኛ የተመረጡ ናቸው...። አምስቱን ዕለታትም ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል ነበር። እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በብርሃን መስቀል ባርካቸው አጅበዋት ከመጡት ከቅዱሳኑ መላዕክት ጋር ታርጋለች። "የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው። ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው። በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ።... በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ። በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ። ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ። (መዝ. 44፥12-17) 🌿🌾 #አባ_መርትያኖስ🌾🌿 ✅ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን አባ መርትያኖስ አረፈ፤ ይህም በህጻንነቱ መንኩሶ ለ፷፯ ዓመት በፍጹም ተጋድሎ የኖረ ነው። ይህ ገድል ትሩፋቱ በሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ እነሆ አንዲት በዝሙት ስራዋ እጅግ የምትታወቅ ሴት ዘንድ ወሬው ደረሰ፤ እርሱ እኮ የሴት ፊት ስላላየ ነው እንጂ በፍትዎት ይወድቃል፤ ከክብሩም ይዋረዳል አለቻቸው ባልንጀሮቿም የለም በፍጹም አያደርገውም አሏት፤ እኔ በዝሙት ከጣልኩት ምን ትሰጡኛላችሁ አለቻቸው ብር እንሰጥሻለን አሏት፤ በዚህ ተወራርደው ሄደች፤ ሽቶ ተቀባብታ አምራ ተውባ ሄደች። ✅ስንክሳሩ እጅግ ውብና መልከ መልካም ነበረች ይላታል፤ እስኪመሽ ከገዳሙ አቅራቢያ ቆይታ በሩን አንኳኳች የመሸቢኝ እንግዳ ነኝ አሳድረኝ ትለዋለች፤ ነፍሱ ተጨነቀች ባስገባት የዝሙት ጦር ይነሳብኛል ብተዋት እንግዳ ሆኜ መጥቼ መቼ ተቀበላችሁኝ ብሎ ይፈርድብኛል ደግሞም አውሬ ይበላታል ብሎ አሰበ፤ ባስገባት ይሻለኛል ብሎ አስገባት የተቀበችው ሽቶ ዝሙት የሚቀሰቅስ ነው። ቀረበችው፤ አባቴ በዚህ ማንም አያየንም አብረን እንተኛ አለችው፤ እሳት እያነደደ ነበርና እሺ ምን ችግር አለው እዚህ አሳት ላይ ምንጣፍሽን አንጥፊና እንተኛለን አላት። ✅አንድም እግሩን ወደ እሳቱ ማገደው ይላል፤ አይንህ ብታሰናክልህ ካንተ አውጥተህ ጣላት አይደል የሚለው መጽሐፉ፤ ደነገጠች ምንድን ነው አባቴ አለችው፤ ይህ ያስደንቅሻልን የገሃነም እሳትን ታዲያ እንዴት ልትችይው ነው አላት። እግሩ ስር ወድቃ ይቅር በለኝ አለችው እርሱም ሌሊቱን ሙሉ ሲያስተምራት አደረ። ሲነጋ አልተመለሰችም አመንኩሰኝ ከዚህ በኃላ ወደ ዓለም አልመለስም አለችው። አመነኮሳት ከደናግል ገዳም ወስዶ ለእመምኔቷ አደራ ሰጣት። የሚገርመው ይህች እናት ከብቃቷ የተነሳ የመፈወስ ሀብት ተሰጣት ብዙ በሽተኞች ወደርሷ እየመጡ ይፈወሱም ነበር። ✅አባ መርትያኖስ ግን ድጋሚ ሌላ ሴት መጥታ እንዳትፈትነው ሰው የማይደርስበት ከባህር መካከል ባለች ደሴት ብቻውን መኖር ጀመረ። ከብዙ ዘመን በኃላ መርከብ ተሰብሮ ብዙዎች ሲሞቱ አንዲት ሴት በመርከቡ ስባሪ ተጣብቃ እርሱ ካለበት ደሴት ደረሰች ባያት ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ከእርሷ ጋር በአንድነት ስለመኖሩም አዘነ። የምትበላውን ሰጥቷት የምትለብሰውን አዘጋጅቶላት ሲያበቃ ተወርውሮ ወደ ባህሩ ገባ ዓሳ አንበሪም ተሸክሞ ወደ የብስ አደረሰው ከዚህ በኃላ በአንድ ቦታ ላለመቀመጥ ወስኖ በመቶ ስምንት አገሮች የሚገኙ ታላላቅ ገዳሞችን ዞረ። በመጨረሻም በዛሬዋ ቀን ግንቦት ፳፩ በክብር አረፈ። 🙏የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ ጣዕም፣ ፍቅር፣ ረድኤትና በረከት አይለየን፤ የጻድቁ አባታችን የአባ መርትያኖስ ጽናት፣ ተጋድሎና ዕምነት ሁላችንንም ይጠብቀን አሜን። ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾🍇✝✟✞ #እርገት ✞✟✝🍇🌾 #እያዩት_ወደ_ሰማይ_ዐረገ (ሉቃ ፳፬÷፶ የሐዋ ፩÷፱) 🌺በስመአብ🌺 🌺 ወወልድ 🌺 🌺ወመንፈስ ቅዱስ🌺 🌺 🌺አሃዱ🌺 🌺አምላክ🌺 🌺አሜን🌺 ✞“#ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን” (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) ✞“#በዐቢይ_ኀይል_ወሥልጣን” (በገናና ኀይልና ሥልጣን) ✞“#ዐሠሮ_ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው) ✞“#አግአዞ_ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው) ✞“#ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ) ✞“#እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ) ✞“#ኮነ” (ሆነ) ✞“#ፍሥሐ_ወሰላም” (ደስታ ሰላም) ✅ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ለሰላሳ ዘጠኝ ቀናት ያህል ለሐዋርያቱ በተለያየ ጊዜ እየተገለጠ ለአገልግሎት ሲያዘጋጃቸው እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምስጢር እያስተማራቸው ከቆየ በኋላ በ፵ኛው ቀን በሐዋርያቱ ፊት አርጓል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው የጌታችን አበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው። ✅ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣ በ፵ኛው ቀን ወደ ሰማይ አረገ ያረገበትም ቦታ ቢታንያ አጠገብ የሚገኘው ደብረ ዘይት የሚባለው ተራራ ነው። አሥራ አንዱ ሐዋርያትን እዚያ ድረስ ከወሰዳቸው በኋላ ባርኳቸው እያዩት ዐረገ። ደመና ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሩ፤ በመለኮታዊ ክብሩ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ ተቀመጧል። ጌታችን ያረገውም በለበሰው ሥጋ በመሆኑ እና ለሁለተኛ ጊዜ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ ይህን ክብር እኛም እንድናገኝ ምሳሌ ሲሆነን ነው። በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ኤፌ. ፪፥፮ ✅ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕርገቱ አስመልክቶ ከተናገራቸው ሦስት ነገሮች ውስጥ፦ ✔የመጀመሪያው፤ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። ዮሐ. ፲፪፥፴፪ ✔ሁለተኛው ደግሞ፤ ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሐ. ፲፬፥፲፰ ✔ሶስተኛው፤ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። ዮሐ. ፲፮፥፯ ✅የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ለእኛ ትልቅ ተስፋ ነው። ስለዚህም ሐዋርያት ጌታችን ሲያርግ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ይመለከቱት እንደነበር እኛም በታላቅ ተስፋ የጌታን ነገር ልናስብ ይገባል። ነቢዩ ዳንኤል ስለ ጌታችን ዕርገት እና በአብ ቀኝ ስለመቀመጡ እንዲህ ሲል በትንቢት ተናግሮ ነበር፤ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ። ✅በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው። ዳን. ፯፥፲፫ -፲፬ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ስንል ጌታ ከአብ ጋር እኩል ነው ማለታችን ነው። ከ፬ቱ ወንጌላት ውስጥ ይህን የዕርገቱን ታሪክ የመዘገቡት የማርቆስ ወንጌልና የሉቃስ ወንጌል ናቸው። ✅ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ። እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤ እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደታያት ሲሰሙ አላመኑም። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤ እነርሱም ሄደውለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም። ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ። እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። ማር. ፲፮፡፱-፲፱ እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ። እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። ሉቃ. ፳፬፡፵፰-፶፩ ✅ቅዱስ ሉቃስ የሐዋርያት ሥራን ሲጽፍ ስለ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት አብራርቶ ጽፎታል። እንዲህ ሲል፦ ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው። ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤ ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ። እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለው ጠየቁት። እርሱም አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው። ሐዋ. ፩፡፫-፲፩ ✅ክርስቲያኖች በሰማያት ስፍራ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው እንደሚቀመጡ የእርሱ ዕርገት ያረጋግጥልናል። ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ጌታችን እርገት እንዲህ ሲል ይመክረናል፤ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና። ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበትጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ። ቆላ. ፫፥፩-፬ 🙏 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ ሕይወትን እንድንወርስ ይርዳን። ልዑል እግዚአብሔር በኑሮአችን ሁሉ ባርኮን፤ ቀድሶን፤ በእርሱ ፈቃድ እንድንኖር ይርዳን። የምንሻትን መንግስተ ሰማያትን ያወርሰን ዘንድ የእናቱ የድንግል ማርያም አማላጅነት፤ ስለ እርሱ ክብር ሲሉ ሕይወታቸውን ሰውተው ያለፉት ቅዱሳን ሰማዕታት ምልጃ እና ጸሎት አይለየን አሜን።

#ምስባክ፦ ዐረገ እግዚአብሔር በይባቤ፤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤ ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።

ዐረገ_በእልልታ_የዕርገት_መዝሙር_Arege_Besibat.mp35.64 MB

photo content

🌿🌾✞✞✞ #እርገት ✞✞✞🌾🌿 የዛሬው እርገት በሥጋ የተደረገ እርገት እንጅ እግዚአብሔር በባሕርዩ ከዚህ ያለ ከዚያ የሌለ ሆኖ ከዚህ ወደዚያ ሄደ ማለታችን አይደለም፤ ሰው በሆነ ጊዜ ከሰማየ ሰማያት ወረደ ማለታችን ከዚህ የሌለ በዚያ ብቻ ያለ ነው ማለታችን ሳይሆን ምድራዊነትን ገንዘብ አደረገ ማለታችን እንደሆነ ሁሉ አሁንም ወደ ሰማይ ወጣ ስንል በሥጋ ግብር መናገራችን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ ልንረሳው እማይገባ ዋናው ነገር የሥጋ እርገት የቃል ርደት የተፈጸመው በማኅፀነ ማርያም መሆኑን ነው ለዚህ ነው ሊቁ አባ ሕርያቆስ እመቤታችንን ባመሰገነበት ድርሳኑ ‹‹ኦ ምዕራግ እምድር እስከ ሰማይ፤ ከምድር ወደ ሰማይ መውጫ መሰላል ሆይ..›› ብሎ ማመስገኑ፡፡ ጌታችንም ከእርገት አስቀድሞ በመዋዕለ ስብከቱ ‹‹አልቦ ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ፤ ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም›› ዮሐ 3÷ 13 ብሎ ያስተማረው እርገት በማኅፀነ ማርያም ስለተፈፀመ ነው፡፡ ታዲያ እንዲህ ከሆነ የዛሬው እርገት ምንድነው? ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር፥ #ዛሬ_ስለ_ሁለት_ነገር_ቤተ_ክርስቲያናችን_የእርገትን_በዓል_ታከብራለች፦ #፩~ በሥውር የተፈፀመውን እርገት በግልጥ ለማሳየት ነው ✅በማኅፀነ ማርያም የተፈጸመውን ምሥጢር ከእናቱ በስተቀር ሌላ ማን ሊያውቀው ይችላል፤ ይሄ ከሁሉም ፍጡራን የራቀ የረቀቀ ምሥጢር ነበር እንዲያውም ቅዱስ አትናቴዎስ ‹‹ወአልቦ ዘአእመረ ምጽዓቶ ለቃል እምእለ ሀለው ይቀውሙ በአርያም፤ በሰማዩ ቤተ መቅደስ ከሚያገለግሉ ባለሟሎቹ የጌታን ወደ ዓለም መምጣት ያወቀ ማንም አልነበረም›› ብሎ ነው የሚገልጠው። ✅ነገር ግን ዛሬ ወደ ሰማይ ያረገውን ጌታ ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤ እግዚአብሔር በእልልታና በመለከት ድምጽ ዐረገ ›› መዝ 46÷ 5 ተብሎ በይባቤ መላእክት ማረጉ እንደተነገረለት ሁሉ በማኅፀነ ማርያም ባደረም ጊዜ ሰው ለሆነው አምላክ ምስጋና ከሰማያውያንና ከመሬታውያን ቀርቦለታል፡፡ #፪~ ዳግም ተዋርዶ በሌለበት ዘለዓለማዊ ክብር የሚኖርበት ጊዜ እንደደረሰ ለማስረዳት ነው። ✅በዚህ ዓለም ሳለ ጲላጦስ ፈረደበት፣ ሊቃነ ካህና ዘበቱበት፣ የአይሁድ ጭፍሮች ምራቃቸውን ተፉበት፣ በጠቅላላው እስከ መስቀል ሞት ድረስ የታዘዘ ሆነ ከእንግዲህ ግን እንዲህ አይደለም፤ ቤተ ክርስቲያናችን ‹‹ገብአ ኀበ ስብሐቲሁ ወክብሩ፤ ወደ ቀደመ አነዋወሩ ተመለሰ›› ትለዋለች መሞት መታመም መራብ መጠማት መድከም እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሉበትም ማለቷ ነው፡፡ እኛ በዚህ ምድር ሳለን ያለንበት ዓለም ዓለመ ሥጋ ስለሆነ ነፍሳችን ሥጋን መስላ ትኖራለች በወዲያው ግን ዓለመ ነፍስ ስለሆነ ሥጋችን ነፍሳችንን መስላ እንድትኖር የጌታችንም በዚህ ዓለም ሳለ መለኮቱ ሥጋውን መስሎ የባሪያውን መልክ ይዞ አየነው በወዲያው ግን ሥጋ የጌታውን መልክ ይዞ በፍጹም ባሕርያዊ ጌትነት እናየዋለን እንጅ ከእንግዲህ በትህትና ወደ እኛ አይመለስም ስትል ነው፡፡ ✅በእውነት ይህ ቀን የቤተ ክርስቲያናችን ታላቁ የተስፋ ቀን ነው፡፡ ምክንያቱም እኛም እሱ ወዳለበት እንደምንሄድ እናምናለንና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እምነታችንን አጽንተን ብንጠብቅ የክርስቶስ ተካፋዮች ነን›› እብ 3÷ 14 እንዳለ የእርሱን መንግሥት ለመውረስ ወደዚያ እሱ ወዳለበት እንሄዳለን፡፡ በዚያውስ ላይ ‹‹መዝገብህ ባለበት ልብህ በዚያ ይኖራል›› ማቴ 6÷ 21 አይደል የተባለው የቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ በስተቀር ሌላ ምን መዝገብ አላት፤ አባ ጊዮርጊስ ስለዚህ የተናገረው በእውነት ድንቅ ነው ‹‹መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሰራቂ፤ ሌባ የማያገኘው መዝገባችን›› ብሎ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን መዝገብ እንደሆነ ይናገራል። ✅እናም ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ልቧን መዝገቧ ክርስቶስ ባለበት ታኖረው ዘንድ ‹‹በሰማይ የሀሉ ልብክሙ ልባችሁ በሰማይ ይሁን›› የሚለውን ቃል እየነገራችው እጁንም አንሥቶ እየባረካቸው ወደ ሰማይ ሲወጣ ተመለከትነው አባቶቻችንም ሐዋርያት ‹‹እወ የሀሉ በሰማይ ልብነ አወን እውነት ነው ልባችን ባንተ ዘንድ በሰማይ ይሁን›› እያሉ አሻቅበው በትኩረት ተመለከቱት። ሥራ 1÷ 11 ✅ከዚህ ቀን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን ዓለምን ድል ነሥታ መኖሪያዋ በሰማይ እንደሆነ ተረጋገጠ ያውም ደሞ በአርባኛው ቀን ማድረጉ በአርባ ቀን በሚገኝ ጥምቀት ሰማያዊነትን ገንዘብ ታደርጋላችሁ ማለቱ ነበር፡፡ የቀድሞው ጸጋ በድካም የሚወረስ ስለነበረ አባቶቻን የተስፋይቱን ምድር የወረሱት በአርባ ዓመት ነበር እኛ ግን በአርባ ቀን ሆኖልናል፡፡ ጌታ ዛሬ አሳልፎ የሰጠው ሰው ይሁዳ በሀፍረት እየተመለከተው በክብር በሐዋርያት ጉባኤ መካከል ብርህት ደመና ተቀብላው ወደ ሰማይ ዐረገ ቤተ ክርስቲያንም ራሷ ክርስቶስ ባለበት በዚያ ልትኖር ጠላቶቿ አጋንንት በሀፍረት እየተመለከቷት በክብር ታርጋለች፤ ከዚያ በፊት ግን ቤተ ክርስቲያን በሁለት መንገድ ክርስቶስን መምሰል ይገባታል። *በስቅለተ ልቡና እና *በትንሣኤ ልቡና ነው፡፡ ስቅለተ ኅሊናና ትንሣኤ ኅሊና የሌለው ክርስቲያን ዕርገተ ኅሊና ላይ መድረስ አይችልም፡፡ ✅ከከተማ ውጭ ማድረጉስ ስለምን ነው ካላችሁኝ ከዓለም ተለይታችሁ ብትፈልጉኝ እባርካችኋለሁ ማለቱ ነበር ይህን ምሥጢር ያየንባት የእጁን በረከት የተቀበልንባት ቢታንያ የተባረከች ትሁን፡፡ መጀመሪያም የትንሣኤን ምሥጢር ያንባት የአልዓዛር መንደር ናት አሁንም እርገቱን ያየንባት፡፡ እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁ! ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ገብርኤል ከሰማይ.m4a1.03 MB

ገብርኤል ስለው.m4a8.76 KB

ገብርኤል መጣ.aac9.77 KB

ገብርኤል ሃያል.m4a1.04 MB

#እንደ_አናንያ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#ገብርኤል_ማን_ነው? 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 #ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡ #ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ 👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡* ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ 👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡* ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ 👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡* የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ 👉*ገብርኤል ነው፡፡* የአሸናፊና የኃይል መልአክ *ገብርኤል ነው፡፡* ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ *ገብርኤል ነው፡፡ 🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏 ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

➲➲➲✞ #ክፍል_፫ ✞➲➲➲ ✅ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን በሥዕላት አማካይነት ፈጣሪዋን ታመልካለች፣ ቅዱሳንን ደግሞ ታከብራለች እንጂ ሥዕላቱን አታመልክም፡፡ በመዝሙር ፈጣሪን ማምለክ ማለት መዝሙርን ማምለክ እንዳልሆነ ሁሉ በሥዕል ፈጣሪን ማምለክም ሥዕሉን ማምለክ አይደለም፡፡ በሥዕላቱ ፊት የምናደርገው ስግደትና አክብሮትም ለሥዕሉ ሳይሆን ለሥዕሉ ባለቤት ነው፡፡ በድርሳነ ሚካኤል ‹አኮ ዘንሰግድ ለረቅ ወለቀለም ወለ ግብረ ዕድ› ‹የምንሰግደው ለወረቀቱ ለቀለሙ ወይም ለሰው የእጅ ሥራ አይደለም› ተብሎ እንደተጻፈው በሥዕሉ ፊት የምናደርገው ነገር ሁሉ የሚመለከተው በሥዕሉ የተወከለውን አካል እንጂ ሥዕሉን አይደለም፡፡ ✅በዓለም ታሪክ እንደሚታወቀው በስምንተኛው ክፍለ ዘመን በክርስትናው ዓለም የሥዕላት ውዝግብ (Icon controvercy) ተነሥቶ ብዙ ደም አፋስሶ ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ሥዕላትን የሚያመልኩ (iconolatrilism) እና ሥዕላትን የሚጠሉ (iconoclasm) ሆነው በሁለት ጎራ ተከፍለው ነበር፡፡ በወቅቱ ሥዕል ጠሎቹ ከቄሣሩ ጋር ተመሣጥረው መተኪያ የማይገኝላቸውን ጥንታውያን ሥዕሎች ሲያቃጥሉና በመዶሻ ሲያፈርሱ ነበር፡፡ ቄሣሩም የክርስቶስን ሥዕል በመሬት ላይ አስነጥፎ እየረገጠ ‹እኔ ክርስቲያን ነኝ ይኼን ሥዕል ግን ጌታ ስላልሆነ እረግጠዋለሁ›› እስከማለት ደርሶ ነበር፡፡ ✅የኒቆማድያው እስጢፋኖስ የተባለ አባት በቄሣሩ ፊት ታስሮ በቀረበ ጊዜ በወቅቱ የቄሣር ምስል ይታተምበት የነበረውን መገበያያ ገንዘብ ከመሬት ላይ ጥሎ ረገጠው፡፡ ወታደሮቹ ነገሩን ሳያስተውሉ ‹እንዴት የቄሣርን ምስል ትረግጣለህ› ብለው ሊመቱት ሲቃጡ ‹‹ይህ ቄሣርን የሚወክል ምስል እንጂ ቄሣር አይደለም ስረግጠው ግን ተቆጣችሁኝ፤ የሰማይና ምድር ንጉሥ የክርስቶስ ምስልን ግን ቄሣራችሁ ሲረግጠው እያያችሁ ክርስቶስ አልተነካም ብላችሁ ዝም ትላላችሁ›› ብሎ ገሥፆአቸዋል፡፡ ✅በዚህ በምዕራቡ ክርስትና የሁለት ጎራ ውዝግብ ያልተሳተፈችው ምሥራቃዊቷ ቤተ ክርስቲያናችን በዚያ ብትኖርም ኖሮ ሁለቱንም ጎራ አትደግፍም ነበር፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያናችን ሥዕላትን አትጠላምም፤ አታመልክምም፡፡ በሥዕላት የሚከበረው የሥዕሉ ባለቤት ነውና የሚሠጠውም ቦታ እንደተወከለው ባለቤት ማንነት ይወሰናል፡፡ ይህ ውዝግብ ያበቃው በታሪክ ሰባተኛው የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ (The seventh ecumenical council) ተብሎ በሚታወቀው ጉባኤ ላይ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆን የመሳሰሉ አባቶች ባቀረቡት ሚዛናዊው ኦርቶዶክሳዊ አቋም ነው፡፡ ስለ ሥዕል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትና አስፈላጊነት ይህችን ታህል ካየን፤ ❔ #በሥዕላት_ተአምር_ይፈጸማል_ወይ❔ ✅ለዚህ ጥያቄ መልሱ ‹‹ጳጳሱ ቅስና አላቸው ወይ›› ብሎ ለጠየቀው ‹‹ተርፏቸው ይናኙታል›› የተባለው መልስ ትዝ አለኝ፡፡ ሥዕላት ተአምር እንደሚሠሩ ከማስረዳት መልሱ ኪሩቤል የተሣሉባት ታቦተ ጽዮን ተአምር ሠርታለች ወይ ብሎ መጠየቅ ይቀልላል፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላው ያረፈባቸውን ሕሙማንን ይፈውስ ነበር፡፡ (ሐዋ. 5፡15) የጴጥሮስ ጥላው ያለ ብሩሽ በብርሃን ረዳትነት የተሣለ ሥዕሉ አይደለምን❔ የጳውሎስስ ልብስ አልፈወሰምን❔ (ሐዋ. 19፡11) ልብሱስ የጳውሎስ በረከት ያደረበት ጨርቅ አይደለምን❔ በፈጣሪና በቅዱሳኑ ስም የተሣሉ ሥዕላትም በራሳቸው ኃይል የላቸውም፡፡ በሥዕላት የተወከሉት ቅዱሳን ግን ከፈጣሪ በተሠጣቸው ሥልጣን በሥዕሉ ላይ ተአምር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ከጥቅስ ይልቅ ወዝ የሚፈስሳቸውን የእመቤታችንን ሥዕላት፣ በሀገራችን ዓመት ጠብቆ በማሕሌት መካከል በከበሮው ምት ትክክል በሥዕሉ ላይ ያለው ፈረስ የሚዘልለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕልን እንድትጎበኙ እንጋብዛለን፡፡ ✍ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

❔ #ሥዕላት_ለምን_ይጠቅማሉ❔ ➲➲➲✞ #ክፍል_፪ ✞➲➲➲ ✅ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ሥዕላትን የሰማይ መስኮቶች ይላቸዋል፡፡ በቤተ መቅደስ ቆሞ የመላእክቱን ሥዕል፣ የሥላሴን ዙፋን፣ የቅዱሳኑን ኅብረት የሚመለከት ሰው ለአፍታ በሕሊናው ወደ ሰማያት መመሰጥና የላይኛውን ነገር ማሰብ ይችላልና ሥዕላት የሰማይ መስኮቶች ናቸው፡፡ የሚያስደንቀው ሥዕላት ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚበልጡ የእግዚአብሔር ቃል መማሪያዎች ናቸው፡፡ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሊገነዘብ የሚችለው ወይ ሊያነበው በሚችለው ቋንቋው ተተርጉሞ ሲቀርብለት ነው፤ አለዚያም ደግሞ ማንበብ የሚችል ፊደል የተማረ ሰው ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ✅ሥዕላት ግን ከዚህ መድልዎ የጸዱ አስተማሪዎች ናቸው፡፡ የየትኛው ቋንቋ ተናጋሪ ያለ አስተርጓሚ ሥዕላትን አይቶ ሃሳባቸውን ለመረዳት ይችላል፡፡ ምንም ፊደል ያልቆጠረ ሰው ቢሆንም ሥዕላትን አይቶ መማርና መጠቀም ይችላል፡፡ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ከጌታችን የዕለተ ዓርብ መከራ ሥዕላት ፊት ብናቆማቸው ሁለቱም የጌታችንን ሥቃይ፣ መውደቁን መነሣቱን፣ መገረፉንና መሰቀሉን አይተው ያለቅሳሉ፡፡ ያለ ቋንቋ እንቅፋትነት አብረው ሊማሩ የሚችሉት ስብከት የሚገኘው ሥዕላት ላይ ብቻ ነው፡፡ ያልተማረ ሰውም ከሌሎች የማነስ የበታችነት ሳይሰማው እኩል መረዳት የሚችልበት አስተማሪው ቅዱሳት ሥዕላት ናቸው፡፡ ✅የቤተ ክርስቲያን ሐኪሞች (Doctors of the Church) ከሚባሉት አባቶች አንዱ የሆነው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የጌታችንን ስቅለት የሚያሳይ ሥዕልን ባየ ጊዜ የተሰማውን ሲገልጥ ‹‹ይህንን ሥዕል በተመለከትሁ ጊዜ ያለ ዕንባ ልመለከተው አልችልም፤ ምክንያቱም ሰዓሊው በጥበባዊ መንገድ ታሪኩን ፊቴ ላይ ስላመጣብኝ ነው›› ብሏል፡፡ ይህንን የጎርጎርዮስን ምስክርነት ያየው ዮሐንስ ዘደማስቆ ደግሞ በእንተ ሥዕላት አምላካዊያት (On the Divine Images) በተባለው ጥንታዊ መጽሐፉ ‹‹ሥዕላት እንዲህ ዓይነቱን የቤተ ክርስቲያን ሐኪም እንዲያለቅስ ከረዱት ለአላዋቂ የዋሐንማ ምን ያህል ይረዳቸው ይሆን?›› ብሎ አድንቋል፡፡ ✅ውድ አንባቢያን፤ ሁሉም ሰው እግዚአብሔርን የሚያገለግለው በጸጋው እንደሆነ መቼም ታምናላችሁ፡፡ የመዘመር ጸጋ ያለው ሰው የክርስቶስን መከራውን የሚገልጽ ዝማሬን ሲዘምር ሰዎች ዝማሬውን ተጠቅመው ከፈጣሪ ጋር በተመስጦ ይገናኛሉ፡፡ ጥሩ የመስበክ ጸጋ የተሠጠው ሰው ደግሞ የጌታን መከራ በርቱዕ አንደበቱ በመግለጽ ሰዎች በሕሊናቸው ወደ ቀራንዮ እንዲገሰግሱ ያደርጋል፤ ጸሐፊው ደግሞ በብዕሩ መሣሪያነት ሰዎች የጌታን መከራ እንዲያስቡ ያደርጋል፡፡ ✅ሠዓሊስ❔ ጥሩ የመሣል ጸጋ ያለው ሰው እንደ ዘማሪው መዘመር፣ እንደ ጸሐፊው መጻፍ፣ እንደ ሰባኪው መስበክ ባይችል በተሠጠው ጸጋ የጌታችንን በደም የተለወሰ ፊት፣ በመስቀል እንደ ቆዳ የተወጠረ ሰውነት በቀለምና በብሩሹ ተጠቅሞ በመሣልና በማሳየት ምስል መከሰትና ሰዎች የተዋለላቸውን ውለታ እንዲረዱ ማድረግ ይችላል፡፡ እንግዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሥዕል አያስፈልግም የሚሉ ሰዎች በተዘዋዋሪ እያሉ ያሉት ‹‹ሠዓሊያን በተሠጣቸው ጸጋ አያገልግሉ›› ነው፡፡ (ይኼን ጉዳይ የሠዓሊያን ማኅበር ቢያስብበት ሳይሻል አይቀርም) የሰባኪ ዓላማው ክርስቶስን በሰዎች ልቦና እንዲሣል ማድረግ ነው። ✅ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ‹‹ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል›› ብሎ ነበር፡፡ አክሎም ‹‹የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ ማን አዚም አደረገባችሁ›› ብሎም ገሥፆአቸው ነበር፡፡ (ገላ. 4:19 ፣ 3፡1) ይህ ሁሉ ጥረቱ ሰዎች ክርስቶስንና የመሰቀሉን ነገር በልባቸው እንዲሥሉ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ የሐዋርያው ንግግር ሁለት ነገሮችን መረዳት እንችላለን፡፡ ✔አንደኛው ምጥ እስኪይዘው በሰዎች ልብ በስብከቱ ለመሣል የሞከረውን የክርስቶስ መከራ ሠዓሊ ቢሆን ኖሮ ሥሎ ከማሳየት እንደማይመለስ፡፡ ✔ሁለተኛው ደግሞ በጳውሎስ ትምህርት ሰዎች ጌታን እንደተሰቀለ ሆኖ በልባቸው መሣል (imagination) ከተፈቀደላቸው በልባቸው የሣሉትን የመስቀሉን መከራ የሥዕል ችሎታ ኖሯቸው በወረቀት ላይ ሲያሠፍሩት ኃጢአት ሊሆን አይችልም የሚለውን ነው፡፡ ✅ሥዕልን መከልከል የሠዓሊነትን ጸጋ ለጣዖት አምልኮ እንጂ ለክርስትና የማይሆን ጸጋ ነው እንደማለት ነው፡፡ ‹ሥዕላት ከማስተማሪያነት ያለፈ እግዚአብሔርን ለማምለክ ይውላሉ ወይ❔› ከተባለ መልሱ ስብከትና መዝሙር ለአምልኮ አይውልም ወይ ነው፡፡ ሥዕላት ማለት የተሣሉ ስብከቶች፣ የተሣሉ መዝሙራት ናቸው፡፡ ሠዓሊያንም በቡሩሽ የሚሰብኩና የሚዘምሩ ድምፅ አልባ ሰባኪያንና ዘማርያን ናቸው። ➲➲➲✞ #ይቀጥላል ✞➲➲➲

❔ #መጽሐፍ_ቅዱስ_ሥዕላትን_ይፈቅዳልን❔ ➲➲➲✞ #ክፍል_፩ ✞➲➲➲ ✅በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ የሚመለከት ሰው እጅግ የተዋቡ የጌታችን፣ የድንግል ማርያም፣ የመላእክትና የቅዱሳን ሰዎች ሥዕላት ቤተ መቅደሱን ሞልተውት ያገኛል፡፡ ኦርቶዶክሳዊያን በሥዕላቱ ፊት ዕጣን ሲያጥኑ፣ መብራት ሲያበሩ፣ ሲሳለሙና ሲሰግዱ ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ደግሞ "ይኼ እኮ ጣዖት አምልኮ ነው!" ‹‹በላይ በሰማይ ካለው፤ በታች በምድርም ካለው ከምድርም በታች በውኃ ካለው የማናቸውንም ነገር ምሳሌ ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው አታምልካቸውም›› ተብሎ በዐሠርቱ ትእዛዛት ላይ ተጽፎ የለምን? ብለው ይከራከራሉ፡፡ (ዘጸ. 20፡4) ✅በእርግጥም እግዚአብሔር በሰማይም፣ በምድርም፣ ከምድርም በታች ባሉ በማናቸውም ነገር የተቀረጸ ምስል አታድርግ ብሎ በግልጥ ማዘዙ ማስተባበያ የሌለው እውነት ነው፡፡ ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይህ ትእዛዝ በግልጥ ተጽፎ ካለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ካሉ የመላእክትን፣ በምድር ካሉ የቅዱሳን ሰዎችን ሥዕላት ለመቅረጽም ሆነ ለመሳል እንዴት ደፈረች❔ እውነት ይኼንን በግልጥ የተቀመጠ ሕግ እያየች ሥዕላትን ለማዘጋጀት ምን አነሣሣት❔ የሚለው ጥያቄ የግድ መመለስ ያለበት ነው፡፡ ✅በቀጥታ ወደ ምላሹ ከመግባታችን በፊት ከዚያው ከኦሪት ዘጸአት ሳንወጣ ጥቂት ምዕራፎችን እንሻገርና እናንብብ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለው፦ ‹‹ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ… አንደኛውን ኪሩብ በአንድ ወገን ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላ ወገን አድርገህ ሥራ… ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘርጉ፤ የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፤ ፊታቸውም እርስ በእርሱ ይተያያል… እኔም በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ አነጋግርሃለሁ›› (ዘጸ. 25፡18-22) ✅ልብ አድርጉ፤ ከአምስት ምዕራፎች በፊት ‹ከሰማይ፣ ከምድርና ከባሕር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› ብሎ ለሙሴ ያዘዘው እግዚአብሔር አሁን ደግሞ በሰማይ ካሉ መላእክት መካከል የሆኑትን የኪሩቤልን ሁለት ምስል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፣ ክንፎቻቸውን እንዲዘረጉና እንደሚናተፍ ዶሮ እንዲተያዩ አድርጋቸው፣ እኔም በእነርሱ መካከል አነጋግርሃለሁ አለው፡፡ ከዘጸአት ሳንወጣ እግዚአብሔር አሁንም ለሙሴ እንዲህ አለው፦ ‹‹መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ አድርግ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁኑ›› በማለት ከወርቅ ከተቀረጹት ሁለት ኪሩቤል በተጨማሪ በመጋረጃ ላይ በጥልፍ መልክ ኪሩቤል እንዲሣሉ አዘዘው፡፡ (ዘጸ. 26፡30-31) ✅እግዚአብሔር በሰማይ ካሉት የማንንም ምሳሌ አታድርግ ብሎ ያዘዘውን ትእዛዝ ራሱ የሚጥስ አምላክ ነው ሊባል ይችላልን❔ ኪሩቤል ‹በሰማይ ካለው ማናቸውም ነገር› ውስጥ አይደሉምን❔ የተቀጠቀጠ ወርቅስ የተቀረጸ ምስል አይደለምን❔ ይህን ጥያቄ እንደ ዋዛ መተው እንዴት ይቻላል❔ መጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘጸአት ብቻ ቢሆን ሁለት ማስረጃ ጠቅሰን እንተወው ነበር፡፡ ሆኖም መጽሐፉ በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር ‹‹እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሠጠው›› ተብሎ የተነገረለት ጠቢቡ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ሲፈጽም ይህንን አደረገ፦ ✅‹‹በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ፤ የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሌላኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ… ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው›› ይላል፡፡ (1ነገሥ. 6፡23-28) ጠቢቡ በዚህ አልበቃውም፤ የቤተ መቅደሱን ግንብ ዙሪያውን ባዶ እንዲሆን አልተወውም ‹‹በቤቱም ግንብ ዙሪያ በውስጥና በውጪ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ›› ይላል፡፡ (1ነገሥ. 6፡29) በአጭሩ ጠቢቡ ሰሎሞን እንደ ሙሴ በመጠን ያነሡ ሳይሆኑ ዐሥር ክንድ የሚረዝሙ ኪሩቤልን ከወይራ ሠርቶ በወርቅ ሲለብጥ ከምድርም አበባና ዘንባባን በቤተ መቅደሱ ምስል አድርጎ ቀረጸ፡፡ ✅‹የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› የሚለው ቃል የመላእክትን ሥዕልና ቅርጽ የሚከለክል ከሆነ ይህ ሕግ ክብር ይግባውና ሕጉን ባወጣው በእግዚአብሔርና በባሪያዎቹ በሙሴና በሰሎሞን ተጣሰ ማለት ነው፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር ሕግ ስለእነዚህ ዓይነቶቹ የቅዱሳን ሥዕላት የወጣ ሕግ አልነበረም፡፡ ሕጉ የሚጠናቀቅበት ‹አትስገድላቸው አታምልካቸውም› የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር የከለከላቸው የተቀረጹ ምስሎች አምላኬ ነህ ተብለው ለፈጣሪ የሚገባ የአምልኮ ስግደት የሚሰገድላቸው ጣዖታትን እንደሆነ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ✅ለማንኛውም በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ከሰማይ ከምድር ከባሕር ያሉ ፍጥረታትን በምስል ቀርጾ አምላኬ አንተ ነህ ብሎ እንዳይሰግድ የተከለከለው ክልከላ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳን መላእክት መቅረጽ አይገባም ለማለት ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የተሳሳተ መሆኑን ራሱ ባለቤቱ ሕጉን ከሠራ በኋላ በዚያው ዘመን የመላእክቱን ሥዕልና ቅርጽ በማሠራት አሳይቶናል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር እናስተውል፤ ከላይ ባየናቸው የቤተ መቅደሱ ውስጥ ሥዕላት በተደጋጋሚ የተሣሉት መላእክት ብቻ ከመላእክትም ኪሩቤል ብቻ ናቸው፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን እንደምናየው ከሙሴ በፊት የነበሩ እንደ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉ ቅዱሳን ሥዕላቸው በቤተ መቅደሱ ለምን አልተሣለም❔ ምናልባት ለቅዱሳን ሰዎች ሥዕል አይገባ ይሆን❔ ያሰኛል፡፡ ✅አይደለም፤ እንደሚታወቀው ቤተ መቅደሱ የሰማያት ምሳሌ ሲሆን በሰማያት በልዕልና የሚኖር አምላክ ከሕዝቡ መካከል በረድኤት የሚገለጥበት ሥፍራ ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ያሉት ነገሮች ሁሉም በሰማያት በእግዚአብሔር መንግሥትና ከእግዚአብሔር ጋር ያሉትን ነገሮች የሚወክሉ ናቸው፡፡ ቅዱሳን ሰዎች ሁሉ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ሆኖ ወደ ሲኦል በወረዱበት በዚያ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከእግዚአብሔር ረድኤት ርቀው በሞት ጥላ መካከል ናቸውና የእግዚአብሔር መንግሥት ምሳሌ በሆነው መቅደስ ውስጥ አልተሣሉም፡፡ በዚያ ቤተ መቅደስ የተሣሉት መላእክት ከመላእክትም ለታቦቱ ዙፋንነት ምሥጢር የሚቀርቡት በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋኑን የሚሸከሙት ኪሩቤል ናቸው፡፡ ➲➲➲✞ #ይቀጥላል። ✞➲➲➲

የአብነት ትምህር ቤት ✞❀ ወራዙት አፍቀሩ ልሳነ ግእዝ ይትማህሩ ❀✞ ✞✿ ወጣቶች የግእዝን ቋንቈ ይማሩ ዘንድ ወደዱ ✿✞ ☞✞ ለቅድስት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ብሎም ለአለም መንፈሳዊም አለማዊም ሁሉ የአብነት ትምህርት መጀመሪያ የሆነው የግዕዝ ቋንቋ መሠረት ነው፡፡ ☞✞ በአለማችን የመጀመሪያውና የመጨረሻው ቋንቋ ግዕዝ መሆኑን ያውቃሉን? ☞✞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የአብነት መሠረት የሆኑትን ሁሉ እንማራለን፡፡ https://t.me/Geez_Abinet

photo content

✅ከዚህ በኋላ ወደ ፈጣሪዋ ሄዳ አቤቱ ፍርድህ የቀና ምህረትህ የበዛ ነው እያለች ለጌትነቱ ክብር ሰገደች፡፡ ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በቁመቷ ልክ ጉድጓድ አስቆፈረችና ሦስት የተሳሉ ጦሮች በፊቷ ሦስት ጦር፣ በኋላዋ ሦስት ጦር፣ በቀኝ ጎኗ ሦስት ጦርና በግራ ጎኗ ሦስት ጦር ተከለች፡፡ አንዲት መበለትም ጠርታ የፊጥኝ ወይም የኋሊት በገመድ እንድታስራት አደረገች፡፡ ✅ከዚህ በኋላ ስለ ዓለም ሁሉ ትጸልይ ጀመር፡፡ በምትሰግድበትም ጊዜ ጦሩ እየወጋት ከቁስሉ የተነሳ ጦሩ የወጋት ገመዱ የከረከራት መላ ሰውነቷ ሸቶ ተልቶ ለዓሥራ ሁለት ዓመት ተጋድሎ አደረገች፡፡ #ዜና_ዕረፍቷ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ሌሎች ቅዱሳንን ሁሉ አስከትሎ ወደ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘንድ መጣ፡፡ ✅አንዲህም አላት "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዛሬ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም አሳርፍሽ ዘንድ መጥቻለው አላት፡፡ ድካምሽ ወደ ዕረፍት፣ ኀዘንሽም ወደ ደስታ ችግርሽም ወደ ብልጽግና ተለውጦልሻል አላት።" ✅በዚህ ጊዜ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኔ ባሪያህ በፊትህ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆን አንድ ነገር እንድናገር ፍቀድልኝ አለችው፡፡ እሱም ትናገሪ ዘንድ ፈቅጄልሻለው አላት፡፡ "አቤቱ ሥጋዬ የሚቀበርበት ቦታ ወዴት እንዲሆን ታዛለህ አለችው፡፡" መቃብርሽ በዚህች #ንጉል በምትባል ደሴት ይሆናል አላት፡፡ከዚህም አምላካዊ ቃል በኋላ በነሐሴ 24 ቀን የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት መታሰቢያ በዓል በሚከበርበት ዕለት ነፍስዋ ከሥጋዋ በክብር ተለየች፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት በዝማሬና በእልልታ ቅድስት ነፍሷን አሳረጓት፡፡ ✅እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ከዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ የኖረችው ሦስት መቶ ሰባ አምስት(375) ዓመት ነው፡፡ የተሰጣት ቃልኪዳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናታችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የገባላት ቃልኪዳን የሚከተሉት ናቸው፡፡ ✔✞እውነት እውነት እልሻለው በፍጹም ደስታ መታሰቢያሽን ያደረገ በመንግሥተ ሰማያት አስደስተዋለው፡፡ ✔✞በችግሩ ወይም በጭንቁ ጊዜ በመታመን ስምሽን ቢጠራ እኔ ከመከራ ነፍስ አድነዋለሁ። ✔✞የገድልሽን ዜና የሚናገረውን መጽሐፍ የጻፈ ወይም ያጻፈ እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፡፡ ✔✞ቤተክርስቲያንሽን የሠራ ወይም ያሠራ ያሳነጸ እኔ በመንግሥተ ሰማያት ንጹሕ አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ፡፡ ✔✞በስምሽ ለተራበ ያበላ፤ ለተጠማ ያጠጣ እኔ በዕለተ አርብ ከተቆረሰው ሥጋዬና ከፈሰሰው ደሜ አበላዋለው አጠጣዋለሁ፡፡ ✔✞በዓልሽ በሚከበርበት ዕለት ጧፍ፣ ዕጣን፣ ወይም ዘይትና ንጹሕ ስንዴ የመሰለውን ሁሉ መባ ያገባ መሥዋዕቱን እንደ አብርሃምና እንደ መልከጼዴቅ መሥዋዕት አድርጌ እቀበልለታለሁ አላት፡፡ ✔✞እንዲሁም መታሰቢያሽን እያደረገ በስምሽ በታነጸው ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ የሚቀበረውን እስከ ዓሥር(፲) ትውልድ እምርልሻለው፡፡ ✔✞እውነት እውነት እልሻለው ሥጋሽ ከተቀበረበት ሄዶ መካነ መቃብርሽን የተሳለመ የእናቴን የማርያምን መካነ መቃብር እንደተሣለመ ይቆጠርለታል፡፡ ✔✞እውነት እልሻለው አንቺን ያከበረውን እኔ በሰማያዊ መንግስቴ አከብረዋለሁ፡፡ይህን ሁሉ የምህረት ቃልኪዳን ከሰጣት በኋላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ መታሰቢያዋ የሚደረጉበት ዕለት በግንቦት 12 ቀን የልደቷ መታሰቢያ በዓል ነው፡፡ በነሐሴ 24 ቀን የዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል ነው፡፡ ወር በገባ በ24 ወርኃዊ መታሰቢያ በዓሏ ነው፡፡ #ሰላምታ_ይድረሳት ሰላምታ ይድረሳት ለክርስቶስ ሠምራ ሰውን የምታስምር ራሷ ተምራ ቤት ንብረት ልጆቿ ትታ ዘመዶቿን በትርህምት ኖረች ለአያሌ ዘመን በነፍሳት መዋረድ መረገጥ በደይን ነፍሷ ተጨንቃባት ተሰምቷት ኀዘን ይተወዋል ብላ ስቶ ማሳቱን ያንን ከንቱ ፍጡር ዓመጸኛውን ትተከው ውጣና የእሳት ግዛቱን ላስታርቅህ አለችው ከአምላክህ አሁን እርሱ ግን ውርደቱን ቆጥሮት እንደ ክብር አልወደደም ከአምላክ ታርቆ ለመኖር ድሮም አይጥማትም ለአህያ ማር ከፈጣሪ ጋር ተጣልቶ መኖር እያዩ መግባት ነው ወደ እሳት ባህር ይልቅስ ይሻላል መታረቅ በቶሎ ዋይ ዋይ ላለማለት በሲኦል ተጥሎ ✅ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያደረገችው አስተዋጽኦ ፩. በስሟ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት እንዲታነጹ አድርጋለች፡፡ ፪. ለክርስቲያኖች በተለይም ለሴቶች የቅድስና ተግባር እንዴት ማከናወን እንዳለባቸውና ማድረግ እንደሚችሉ አሳይታለች፡፡ ፫.የምንኩስና ተግባር ምን እና እንዴት እንደሆነ አሳይታለች፡፡ ፬.የጸሎት ሕይወትን ለምዕመናንና በዘመናችን ለሚገኙ መነኮሳት አሳይታለች፡፡ ፭.ለእናቶች ማለትም ልጆች የወለዱና ትዳር ያላቸው ሰዎችም ለቅድስና መብቃት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየች ታላቅ ቅድስት እናት ናት፡፡ ፮.ምዕመናን በቃልኪዳኗ አምነው እየተማጸኑ ድኅነት እንዲያገኙ አድርጋለች፡፡ ፯.ለእግዚአብሔር አምላካችን የገባነውን ቃልኪዳን /ስዕለት/ መፈጸም እንዳለብን በተግባር አሳይታለች፡፡ ፰.ሀገራችንን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን በጸሎቷ ከተለያዩ መቅሰፍቶች ጠብቃለች ወደፊትም ትጠብቃለች፡፡ ✅በስሟ የታነጹ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ፩.በተወለደችበት በቅዱስ ጌየ የሚገኝ ታላቅ ገዳም፡፡/በሰሜን ሸዋ ቡልጋ/ ፪.በጣና ቂርቆስ የሚገኝ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ገዳም/ባህር ዳር/ ፫.ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተክርስቲያን፡፡ /አዲስ አበባ፡ጉርድ ሾላ/ የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልመናዋና በረከትዋና ፍቅሯ ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ዋቢ መጻሕፍት፦[ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ] 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯