የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
الذهاب إلى القناة على Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
إظهار المزيد4 374
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
4 374
#ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር
•••• #ክፍል_4 ••••
#የሰንበትን_ቀን_ትቀድሰው_ዘንድ_አስብ ፦ የቃሉ ትርጉም አቆመ አረፈ ማለት ነው። ይህ ማለት የሰው ልጅ ከጌታ ጋር የሚቀራረብበት መገናኛ መንገድ ነው። ከማንኛውም ስጋዊ ተግባር የምናርፍበት ፣ ትርጓሜው የእግዚአብሔርን ሥራ እንድናስታውስ የሚያደርግበት ቀን ነው። #ሰንበት የመንግስተ ሰማይ ምሳሌ ነች። የሰው ልጅ በዓለም ሠርቶ ወርዶ በመልካም ሥራው የሚያርፍበት ቦታ ናት። ሰው ዕረፍት ያስፈልገዋል የሰንበት ቀን የተፈጠረውም ለዚህ ነው። የሰንበት ቀን የዕረፍት ቀን ስለሆነ የሚከተሉትን ሁለት ነገሮች ያሳስበናል።
#1ኛ ሰው በኀጢአት ከመውደቁ በፊት ከአምላኩ ጋር ያለውን ግንኙነት የነበረውን ዕረፍት
#2ኛ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን ዘላለማዊ የነፍስ እረፍት። በሐዲስ ኪዳን ሰንበት ሁለት ናቸው #ቅዳሜና_እሁድ። #ቅዳሜ ማለት የበፊቷ የቀደመችው ማለት ነው። #እሑድ ማለት ደግሞ መጀመሪያ ስለሆነ ከዚህ ጀምረን ስንቆጥር ቅዳሜ ሰባተኛ ቀን ይሆናል። በ3ኛው ትዕዛዝ እንዲከበር የታዘዘው ይህ ቀን ነው። ፈሪሳውያን በሰንበት ቀን እግር ከዘረጉ አያጥፋም ፣ ከአጠፋም አይዘረጉም መልካምም ሥራ ቢሆን አይሰሩም። #እሑድ ሥነፍጥረት የጀመረበት ፣ ኀላም ጌታ የተነሳበት፣ መንፈስቅዱስ የወረደበት እንዲሁም ጌታ የሚመጣበት ዕለት ነው። ስለዚህ እናከብረዋለን። በቤተክርስቲያን ታሪክ ደግሞ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ቀን ስለሆነች ሥራ እንዳይሰራ በሕገመንግስቱ አፅድቆ እንዳወጀና እንደወሰነ ይነገራል። ስለዚህ ሰንበት የእረፍት ቀን ነው ስለተባለ ሥራ ፈተን መዋል የለብንም። በእግዚአብሔር ቤት በመገኘት ማስቀደስ ፣ ቃሉን መማር ፣ መዘመርና ማመስገን አለብን። ከዚህም ሌላ ጌታ በሰንበት መልካም ሥራ ማድረግ ተፈቅዷል ስላለ የታመመና የታሰረ መጠየቅ ፣ የተጣላ ማስታረቅ ፣ ያዘነ ማፅናናት ፣ ለተቸገረ ደግሞ ምፅዋት መመፅወት አለብን። እንግዲህ በክርስትና ሰንበት የሚከበረው እንዲህ ነው።
••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••
4 374
#ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር
••• #ክፍል_3 •••
#የእግዚአብሔር_የአምላክህን_ስም_በከንቱ_አትጥራ
ስም ሲባል አንድ ነገር ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት መጠሪያ ነው። ስም ጠባይን ግብርንና ሁኔታን እንደሚገልጥ ሆኖ ሊሰየም ይችላል። እግዚአብሔርም ባሕርዩን ሕልውናውን ግብሩን የገለፁ ብዙ ስም አለው። በሐዲስ ኪዳንም እግዚአብሔር ወልድ በስጋ ሲገለጥ #አማኑኤል #ኢየሱስ #ክርስቶስ በሚባሉ ስሞች ተጠርቷል። የእግዚአብሔር ስም ባዶ ቃል አይደለም። ኃይሉን ግርማውን ይዞ ይገኛል። የማይታየው እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው በስሙ አማካኝነት ነው። በተለይም ክርስቶስ በስጋ በተገለጠ ጊዜ ስሙን ለዓለም አስታውቋል። /ዮሐ 17:26/ ስሙም ከሁሉ በላይ ነው። /ፊል 2:9/ ስሙ #ቅዱስ ነውና አክብረን ልንይዘውና ልንቀድሰው ይገባል እንጂ በከንቱ ልንጠራው አይገባም። መላዕክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሚያመሰግኑት አምላክ መሆኑን አውቀን ስሙን በከንቱ መጥራት ግብሩን ማርከስ ነው። በማህበር ስንኖር ከሳሽ ተከሳሽ ስለሚኖር የክርክሩ መፈፀሚያ የእውነት ማረጋገጫ መሐላ ስለሆነ ዳኛው እንዲምል ካስገደደው መማል ይፈቀዳል። /ዘፀ 22:11 ዕብ 6:13/ ከዚህ ሌላ ቃል ለመግባት አንድ ነገርን ለመስራት መሐላ መማል ቃል መስጠት የእግዚአብሔር ስም መጥራት የሚያስፈልግባቸው ጊዜ አለ። እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማገልገል ሲሉ ብፅዓት የሚያደርግ አለ ይኸውም በቤተክርስቲያን ስርዓት የተፈቀደ ነው። ለምሳሌ በድንግልና ለመኖር ።
#በከንቱ_አትጥራ
ከንቱ ማለት በእግዚአብሔር የተናቀ የማይገባ ነገር ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ስም በእንዲህ አይነት ሁኔታ መጥራት እንደማይገባ ይህ ትዕዛዝ ያስተምረናል። እነሱም፦
1.ስጋዊ ፍቃድ
2.ጣኦትን ማምለክ
3.ሐሰተኛ ትንቢት
4.በእግዚአብሔር ስም መማል
5.በእግዚአብሔር ስም መራገም
6.በእግዚአብሔር ስም መጠንቆል ... በነዚህ ሁሉ ስሙን መጥራት በከንቱ መጥራት ነውና በማስተዋል ልንጠብቀው ይገባል።
#የእግዚአብሔርን_ስም_የምንጠቀመው_ምን_ጊዜ_ነው ?
1.በፀሎት ጊዜ 2.በሰላምታ ጊዜ 3.በአምልኮ ጊዜ 4.በቡራኬ ጊዜ
••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••
4 374
#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር
••• #ክፍል_2 •••
#አታምልክ
ማምለክ ሲባል እምነትን ተስፋን ፍቅርን በአምላክ ላይ መጣል ነው። አንድ ሰው እምነቱን ተስፋውን ፍቅሩን ከእግዚአብሔር ላይ አንስቶ በሌሎች አማልክት ላይ ሲጥል ነው ሌላ አምላክ አመለከ የሚባለው። #አምልኮት በተግባር የሚውለው በሚከተሉት ነገሮች ነው። #1በስግደት #2ጸሎት #3መስዋዕት #4ውዳሴ #5መገዛት #6ፍርሃት ወዘተ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከእግዚአብሔር ውጪ ለሌላ ነገር ብንሰጣቸው ሌላ አመለክን ማለት ነው። ይህን ህግ የሚያፈርሱ ሰዎች ብዙ ዓይነት በደል ይበድላሉ። ይኸውም #1የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የተባለውን ትዕዛዝ ይለውጣሉ። #2ከቤተክርስቲያን አንድነት ውጭ ይሆናሉ #3ተስፋ ቢስ ሁሉ የጨለመባቸው ሆነው ይገኛሉ። #ሌሎች_አማልክት_የተባሉት፦ ሰው እንደ እግዚአብሔር የሚያያቸውና ብቸኛውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ የሚሰጣቸው ነገሮች ሁሉ አምላክ ሊሆኑበት ይችላሉ። እነሱም፦ #1 ገንዘብ ማቴ 6:24 #2የሰው ሃይል ኤር 17:5 #3የሰው ጥበብ እውቀት ኤር 9:23 #4ሆድ ራስ ወዳድነት #5 የምንታመንባቸው ሰዎች (ባለ ሃብት ባለ ስልጣን ) #6አባትና እናት #7ተድላ ደስታ #8የተቀረፀ ምስል ዘፀ 20:4 አምልኮ ከእግዚአብሔር ውጪ ለማንም አይሰጥም። አክብሮትና የጸጋ ስግደት ግን ለቅዱሳን መላዕክት እና ለቅዱሳን ሁሉ ልናደርግ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳንን #አማልክት ይላቸዋል። ለምሳሌ ሙሴን ለፈርኦን አምላክ አድርጌሃለው በማለት እግዚአብሔር ነግሮታል። በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳንን እናከብራለን ይህ ከትዕዛዙ ወይም ከህጉ ጋር አይጋጭም የእግዚአብሔርን አምልኮትና አክብሮት ለቅዱሳን አንሰጥምና። እንዲያውም ለእነርሱ የምንሰጠው ክብር እግዚአብሔርን ማክበር ስለሆነ በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር እናቀርባለን።
••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••
4 374
#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር
••• #ክፍል_1 •••
#10ቱ_ትዕዛዛት (ኦሪ ዘፀ 20)
#1.እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ ነኝ ከኔ በቀር ሌሎቹ አማልክት አይሁኑልህ፡፡
#2.የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አታንሳ፡፡
#3.የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡
#4.እናትና አባትህን አክብር
#5.አትግደል
#6.አታመንዝር
#7.አትስረቅ
#8.በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር
#9.የባልንጀራህን ቤት አትመኝ
#10.ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ።
የክርስትና ህግ የፍቅር ህግ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈፅሞታል ካለ ቡሃላ ከ10ቱ ትዕዛዛት የተወሰኑትን በመጥቀስ #ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍፃሜ መሆኑን በግልፅ ይናገራል። /ሮሜ 13:8/ ጌታችን እንዳስተማረን ፍቅር #በ2 ይከፈላል። #1ኛ_ፍቅረ_እግዚአብሔር #2ኛ_ፍቅረ_ቢፅ። በሌላ በኩል ደግሞ ከአዎንታዊና አሉታ ከመነገራቸው አንፃር #በ2 ይከፈላሉ።
#1ኛ_ሕግ_በአሉታ_የተነገሩ /አታድርግ/
#2ኛ_ትዕዛዝ_በአዎንታ_የተነገሩ /አድርግ/ ይባላሉ። ከዚህም ሌላ ከአፈፃፀማቸው አንፃር ሲታዩ #በ3 ይከፈላሉ።
#1ኛ_በሐልዩ /በማሰብ/ የሚፈፀሙ ህግ1,3,4 እና 9
#2ኛ_በነቢብ /በመናገር/ የሚፈፀሙ ህግ 2,8
#3ኛ_በገቢር /በማድረግ/ ህግ 5,6,7,10 ናቸው።
#10ቱ ትዕዛዛት ለሙሴ በተሰጡ ጊዜ በሁለት የድንጋይ ፅላቶች ላይ ተፅፈው ነበር። እንዲሁም ሁሉ በተለይም እስራኤል ዘነፍስ የምንባለው ለእኛ ለክርስቲያኖች ከልባችን ፅላት ላይ በመንፈስ ልንፅፈው ይገባል። በቤተክርስቲያናችን በፅላቶቻችን ላይ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይገኛል። ጌታችን ደግሞ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለው ካለ ቡሃላ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ ብሎ አስተምሯል። እንዲህ ከሆነ የሚያስፈልገንን ነገር ለመለመን የጌታችን ስሙ ስለተፃፈበት በዙሪያው ተሰብስበን መለመን ያስፈልጋል። ህጉ ከልባችን ስለማይጠፋ ሕጉን መጠበቅና መፈፀም ይገባናል።
••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••
4 374
#ክርስቲያናዊ_የሥነ_ምግባር_ትምህርት
#መግቢያ
"መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያመሰግኑት ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ " ማቴ 5:16 ክርስቲያን የክርስቶስ ወገን ማለት ነው ። ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ማለት የክርስቶስ ወገን የሆነ ሁሉ ሊሰራው የሚገባ ያማረ ትክክለኛነትና አርአያነት ያለው ስራ ማለት ነው ። ክርስቲያናዊ ስነምግባር መገለጫው የተለያየ መልክ ሲኖረው ከስፋቱና ከአይነቱ አንፃር በ2 ከፍለን እንመልከተው ። እነሱም ግላዊ ስነምግባር እና ማህበራዊ ስነምግባር ናቸው ።
#1ኛ_ግላዊ_ሥነ_ምግባር ፦ መንፈሳዊ ሰው በመጽሐፍትና በመምህራን የተላለፋለትን አምላካዊ ቃል በህሊናው ጽፎ በልቦናው ቀርፆ ከሰውነቱ ጋር አዋህዶ ሁልጊዜም ደግና መልካም የሆነውን ነገር እየፈፀመ ክፉ ከሆነው ነገር ደግሞ ተቆጥቦ እና ሸሽቶ በእለት ተእለት ህይወቱ የሚከተለው ( የሚተገብረው ) የሥነ ምግባር አይነት ነው። ግላዊ ሥነምግባር ገላጭ ባህርያት ከሆኑት በጥቂቱ፦
➊ በትህትና እና እራስን ዝቅ በማድረግ መኖር
➋ ቃሉን በመጠበቅ በትክክለኛው መንገድ በመራመድ
➌ እግዚአብሔርን ከመበደል በመጠበቅ
➍ ራስን መግዛት
➎ ፈቃደ ሥጋን ለፍቃደ ነፍስ ማስገዛት እና ወዘተ...
#2ኛ_ማህበራዊ_ሥነ_ምግባር፦ አንድ ክርስቲያን በዕለት ተዕለት ሥራውና በማህበራዊ ኑሮ ግንኙነቱ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ሲኖር መተሳሰብን ፍቅርን አንድነትን የሚገልጥበት ፣ ሰዎችን አለአግባብ መቃወምን ግለሰቦችን መናቅን ቁጣን እና ራስ ወዳድነትን የሚያስወግድበት በአጠቃላይ ከሰዎች ጋር ተስማምቶ እና ተፋቅሮ የሚኖርበት የሥነ ምግባር አይነት ነው ። ከመገለጫዎቹ በጥቂቱ፦
➊ተግሳፅን መቀበል
➋ሌሎች ሰዎች ከእኔ የተሻሉ ናቸው ብሎ ማሰብ
➌ሰብአዊ ርህራሄ
➍ከግል ጥቅም ይልቅ ማህበራዊ ጥቅምን ማስቀደም
➎ይቅር ማለት እና ወዘተ...
በአጠቃላይ ለክርስቲያናዊ ስነምግባር መሠረቱ ሕገ-እግዚአብሔር ቃለ-እግዚአብሔር ሲሆን ህጉን ለመጠበቅ እና እንደ ቃሉ ለመኖር ትልቁ ኃይል ፈሪሃ-እግዚአብሔር ነው ።
••••••• ✞ #ይቀጥላል ✞ •••••••
4 374
💠ቅዱሳን ሥዕላት💠
ክፍል 2
⛪️መምህር ጸጋ ወ/ትንሳኤ
https://telegram.me/EOTC2921
https://telegram.me/Ethio_Orthodox1
4 374
💠ቅዱሳን ሥዕላት💠
ክፍል 1
⛪️መምህር ጸጋ ወልደ ትንሳኤ
https://telegram.me/EOTC2921
https://telegram.me/Ethio_Orthodox1
4 374
"ከዕቅበተ እምነት"
💠ለተሐድሶድሶ የተሰጠ መልስ💠
ክፍል 5
አዘጋጅ - ማኅበረ ቅዱሳን
ቪዲዮ
https://telegram.me/EOTC2921
https://telegram.me/Ethio_Orthodox1
4 374
⛪️ቅዱሳን ስዕላትን ለምን እንጠቀማለን?
https://telegram.me/EOTC2921
https://telegram.me/Ethio_Orthodox1
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
4 374
ማርያም የውርስ ኃጢአት አለባት?
🌺መጋቤ ሐዲሳት ሮዳስ ታደሰ🌺
መንፈስ ቅዱስ #ይፀልልሻል ለምን ተባለ?
#ሁሉ #ኃጢአትን #ሰርቷል ተብሎ የለ?
እርሷ ራሷ ስትፀልይ "...በጌታዬና #በመድኃኒቴ.." ብላ የለ?
ሰው እስከሆነች ድረስ እንዴት ኃጢአት አይኖርባትም?
መምህራችን ድንቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ አላቸው
https://telegram.me/EOTC2921
https://telegram.me/Ethio_Orthodox1
4 374
✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሃዱ አምላክ አሜን✞
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
🌿🌿✞ #ምስጢረ_ስላሴን ✞🌿🌿
✞ #ለህፃናት_እንዲህ_እናስተምር ✞
#ማን_ፈጠረን?
☞✞ ስላሴ
#ስላሴ_ስንት_ናቸው?
☞✞ አንድም ሶስትም
#ሶስትነታቸው_በምን_በምን_ነው?
☞✞ በስም፣ በአካል፣ በግብር
#አንድነታቸውስ_በምን_ነው?
☞✞ በባህሪ፣በህልውና፣ በመለኮት፣ በፍቃድ፣ በስም፣ በአካል፣ በግብር ይህችን፣ አለም በመፍጠርና በማሳለፍ
#የስም_ሦስትነታቸው_እንዴት_ነው?
☞✞ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ
#የአካል_ሶስትነታቸው_እንዴት_ነው?
☞✞ #አብ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ
ፍፁም ገፅ አለው።
☞✞ #ወልድ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገፅ አለው።
☞✞ #መንፈስቅዱስ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገፅ አለው።
#የግብር_ሶስትነታቸው_እንዴት_ነው?
☞✞ አብ=ወላዲ፤ ወልድ=ተወላዲ፤
መንፈስ ቅዱስ=ሰራፂ
#አብ_ምን_ማለት_ነው?
☞✞ አባት፦ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ፤ ያለእናት ወልድን የወለደ
#ወልድ_ምን_ማለት_ነው?
☞✞ ልጅ፦ የሚወለድ፤ ያለእናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ
#መንፈስ_ቅዱስ_ምን_ማለት_ነው?
☞✞ ሰራፂ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ ሁኖ ከአብ የሰረፀ
✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞
የእግዚአብሔር አብ በረከት፣
የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣
የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡
✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞
4 374
#አይነ_ጥላ ክፍል ሁለት
✍መምህር ቀሲስ ሔኖክ ወለደ ማርያም
https://telegram.me/EOTC2921
https://telegram.me/Ethio_Orthodox1
4 374
#አይነ_ጥላ ክፍል አንድ
✍መምህር ቀሲስ ሔኖክ ወለደ ማርያም
https://telegram.me/EOTC2921
https://telegram.me/Ethio_Orthodox1
4 374
#በከንቱ_እንዳንደክም_መጾም_እንደሚገባን_እንጹም
https://telegram.me/EOTC2921
✔በመጾም እየደከምን ሳለ የጾም አክሊልን ካላገኘን፥ እንዴትና በምን ዓይነት አኳኋን ይህን ልንፈጽመው እንደሚገባው ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ፈሪሳዊዉም ጾሞ ነበርና፤ ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤቱ የኼደው ባዶ እጁንና የጾሙን ፍሬ ሳያገኝ ነውና (ሉቃ.18፡12)፡፡ ቀራጩ ደግሞ በአንጻሩ አልጾመም ነበር፤ ነገር ግን ከጾመው ፈሪሳዊ ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው እርሱ ነው፡፡ ይህም የኾነበት ምክንያት [ቀራጩ ባይጾምም ተጠቀመ፤ በመፃዒ ሕይወቱም ጾም አላሻውም ለማለት ሳይኾን ከተአምኖ ኃጣውእ ጋር] ሌሎች ግብራት ካልተከተሏት በቀር ጾም ረብ ጥቅም እንደሌላት [እና ትሕትና የጾም አጣማጅ መኾኑን/ የምትሠምረው ከትሕትና ጋር መኾኑን] እንድታውቅ ነው፡፡
✔የነነዌ ሰዎች ጾመዋል፤ የእግዚአብሔር ምሕረትንም አግኝተዋል (ዮና.3፡10)፡፡ እስራኤላውያንም ጾመው ነበር፤ ነገር ግን እያጉረመረሙ ተመለሱ እንጂ በመጾማቸው አንዳች ጠቀሜታን አላገኙም (ኢሳ.58፡3-7፣ 1ኛ ቆሮ.9፡26)፡፡ ስለዚህ እንዴት መጾም እንዳለባቸው ለማያውቁ ሰዎች የጾም ጉዳቱ ትልቅ ነውና በጥርጣሬ እንዳንኼድ፣ እንዲሁ አየርን እንዳንደልቅ፣ እንዲሁ ከጨለማ ጋር እንዳንጋደል፥ ይህን የምናከናውንባቸውን ሕጎች ልንማር ያስፈልገናል፡፡
✔ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ
4 374
✞✞✞ #የአምላክ_አቃቤ_ሕግ ✞✞✞
https://telegram.me/EOTC2921
ገባሬ መንክራት በግብሩ ያወቅነው፣
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው፣
ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ አቃቤ ህግ፣
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ፡፡
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
ፀሐይ /2/ የምድራችን ፀሐይ፣
በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ፣
የመላዕክት ወዳጅ /2/ ገብረ ህይወት ሰማይ፡፡
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
መብረቅ/2/ ሰረገላው መብረቅ፣
የቃል ኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ፣
የፍጥረቱ ደስታ/2/ ገብረ ህይወት ጻድቅ።
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
ኮከብ/2/ ክብረ ገዳም ኮከብ፣
አለምን የሚያስንቅ መዓዛው የሚስብ፣
አልክ ስሉስ ቅዱስ/2/ ገብረ ህይወት ኪሩ።
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
ስሒን/2/ ፄና ልብሱ ስሒን፣
የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን፣
የሚነበብ መጽሐፍ/2/ ገብረ ህይወት ድርሳን።
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
መቅረዝ/2/ የማህቶት መቅረዝ፣
ምድረ ከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ፣
የዝግቲው ፈዋሽ/2/ ገብረ ህይወት ምርኩዝ፡፡{➋}
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
https://telegram.me/EOTC2921
